ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶምን
ገልጠን ብናያቸው
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
10/20/25
ዛሬ በሕይወት የሌሉ በኤርትራ ክ/ሃገር የተወለዱ ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶም የሶማሌ ወራሪዎችን ያርበደበዱ ዕውቅ ወታደራዊ ጀነራል ፤ በንጉሡ ዘመን የመከላከያ ሚኒስቴር የነበሩ ፤ የንጉሡ ሥርዓት ተሽሮ ደርግ በሚል መጠሪያ የተከሰተው ወታደሮች በተኩት የወታደሮች ሥርዓት ውስጥ የመጀመሪያው የጊዝያዊው ወታደራዊ መንግሥት ሊቀመንበር ሆነው በወታደሮቹ የተሾሙት ጀነራል አማን ዓንዶም ትውልዳቸው የባሕረ-ምድር የመረብ ምላሽ ቀጠና (ኤርትራ) የሐማሴን ተወላጅ ናቸው።
ትምሕርታቸው የተከታተሉት አዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤በሃገረ አሜሪም በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ እና ሱዳን ውስጥ ወታደራዊ ሥልጠና አድርገዋል።
በቅርቡ ባንድ የድረገጽ “ስዕለ ደምፅ” ሕትመት የቆየ ጀነራሉ ካንድ የውጭ ጋዜጠኛ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ በወቅቱ ንጉሡን አስመለክተው የሰጡት አሉታዊ (ነጋቲቭ) ቃለምልልሳቸው አድምጨ ነበር።
ታዲያ ጀነራሉ
ወደው አምነውበት ሲያገለግሉት የነበርውን ሥርዓት እርግፍ አድርገው በመክዳት ንጉሡ ለሃገራቸው ኢትዮጵያ ፤ ለመላው አፈሪካና ለዓለም
ያበረከቱትን ታሪክ የማይሽረውን አስትዋጽኦ ለቤተሰቦቻቸው ብቻ የጠቀሙ ለሃገሪቱ ምንም እንዳልሰሩ ጥላሸት በመቀባት ሲናገሩ ሰምቻቸው፤
ይህ ገደብ የጣሰ ፍጹም አሉታዊ ልሳናቸው ሰዎች ለጀነራሉ የነበራቸው በጎ ገጽታ እንደገና እንዲፈትሽ ይህንን አቀርባለሁ።ጀነራሉን
እስኪ እንደገና ገልጠን እንያቸውና ታሪክ በራሱ ሚዛን እንዲመዝናቸው ይህንን ላስተናግዳችሁ።
ታሪኩን ያቀናጀሁት
ከተለያዩ የጀነራሉ ማንነት የቀረቡ ዘግባዎች ሲሆኑ ለዚህ ዋናው ድጋፍ የሆነኝ ደግሞ “ትዕድልቲ ቆራጽነት” (ደራሲ ሰናይ ከሰተ)
(ቆራጥነትን መታደል) የሚል የትግርኛ መጽሐፍ ነው። ሰናይ ከሰተ ማለት እዚህ ውጭ ሃገር ሆኖ ከምስት አመት በፊት ወያነ ወሎ ውስጥ
ገብቶ የቤት ለቤት ዘረፋ ፤ ንግድ ቤቶችን ፤ሆስፒታሎች፤ ከሊንኮች የግል ፋርማሲ ቤት መድሃኒቶችን ሲዘርፍ ፤ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ህጻናት ሴት ልጆችን ፤ መነኮሲቶችና ባለተዳሮችን ሲያምጽና እና የዘር ማጥፋት
ወንጀል ሲፈጽም በነበረበት ወቅት “የውግያው ስልት/ንድፍ/” የሰጠኋቸውና የውግያ አማካሪ የነበረኩት እኔ ነኝ እያለ
በፌስቡክ ሚዲያ በቃለ ምልልስ ሲናገር የነበረ፤ ከጦርነቱ በፊት ፍጹም ሃገረ ወዳድ ኢትዮጰያዊ የነበረ የትግራይ ተወላጅ ነው።
ሰናይ እንዲህ
ይላል፤ (ለንባብ እንዲመች አጠር እያደረግኩ ነው የምጠቅስው፡
« ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶም የመከለከያ ሚኒስትር ሆነው
በተሾሙበት ወቅት በመላው ሃገሪቱ ሕዝባዊ ዓመጽ ተፋፍሞ በሰራዊቱ
ውስጥም አለመግባባት እና ሥራአተ አልቦነት ሰፍኖ የመስመር መኮንኖችም አለቆቻቸውን በቁጥጥር ሥር እያደረጉበት ባሉበት ሰዓት ስለነበር
፤ ዕዝ እና ቁጥጥር የላላበት ፈታኝ ወቅት በመኖሩ፡ ኤርትራ ክ/ሃገር ለነበሩ ወንበዴዎች ግን ወቅቱ የጫጉላቸው አየር የተነፈሱበት
ነበር። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወታደራዊ ኃይላቸውና አሰላለፋቸው ሲያስተካክሉ ቆይተው የማጥቃት እርምጃቸውን በማስፋት “ጀብሃ”
የትግራይና የኤርትራ ድምበር በሚያዋስነው “ኦምሓጀር” ወረዳ ውስጥ ሐምሌ 9/1974
ዓ.ም የማጥቃት እርምጃ በመውሰድ አንድ የብርጌድ አዛዥ የነበረ ኮሎኔል ገድሎ ከሥፍራው ተሰወረ።
በእርምጃው
የተቆጡ ወታደሮች 200 የኦምሐጀር ሯሪዎችን በገፍ ጨፈጨፉ። በዚህ እርምጃ የተቆጡ በኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት የነበሩ 23 የኤርትራ ክ/ሃገር ተወላጆች የሥራ
መልቀቂያ ማመልከቻ ለፓርላማው አቀረቡ።
በወቅቱ የሚኒስትሮች
ዋና ሰብሳቢ የነበሩት “ራስ ሚካል ዕምሩ” ለመለቀቂያ ማመልከቻቸው ምክንያት ሲጠዩቁዋቸው ኤርትራኖቹ የሰጡት መልስ ኦምሐጀር የተፈጸመው
ጭፍጨፋ እንደሆነ ሲገለጹላቸው፤በወቅቱ የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር
የነበሩት ጀ/አማን ዓንዶምን ከነበራቸው የመከላከያ ሚኒስቴርነት ሥልጣናቸው በተጨማሪ የኤርትራ ክ/ሃገር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።
በዚህ መሰረት
ወደ ኤርትራ ሄደው ከሕዝብ ጋር እንዲነጋገሩ ጉብኝት እንዲያደርጉ በተወሰነው መሰረት ወደ አሥመራ ሄዱ።
እዛው እንደደረሱም
“ኤርትራ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት በንጉሡ ዘመን የነበሩ አድሐሪ ባለሥልጣናት እንደመፍትሔ የወሰዱት “ወታደራዊ ፍልሚያ”
ነበር ፡ ዛሬ ግን ‹ኢትዮጵያ ትቅደም» በሚል መርሕ ተዘጋጅተን በዚህ ምድር ውስጥ የጥይት ጩኸት እንደማይሰማ ላሳውቃችሁ እሻለሁ።» የሚል ንግግር ለሕዝብ አደረጉ።
ባጠቃላይ
አሥመራ “ሳባ እስታዲዮም” ውስጥ ወደ 80 ሺሕ የሚገመት ሕዝብ በተሰበሰበበት እንዲህ የሚል ንግግር አደረጉ።
«እንደምታውቁት
በኃይለሥላሴ ዘመን የኤርትራን
ጉዳይ አንስተህ መወያየት ከባድ ወንጀል ተደረጎ ይታይ የነበረ ጉዳይ ነው። ይህ እርምጃ ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን
ድምጻቸው እንዳይሰማ ያደረገ የመብት ረገጣ ነበር። ሆኖም በዓለም ታሪክ ኤርትራ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ግዛት የነበረች ነች። የኤርትራ
ታሪክና ጀግንነት ኢትዮጵያው ሁሉ የሚያውቀው እውነታ ነው።» የሚል ንግግር ካደረጉ በኋላ፤
በተጨማሪ
ኡምሐጀር ውሰጥ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የታመነባቸው ከላይ እሰከታች የነበሩት ወታደሮችና አዛዦች ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በማድርግ ክሱም በወታደራዊ ፍ/ቤት እንዲታይ ትዕዛዝ
አስተላለፉ።
በወቅቱ በኡምሐጀር ሕዝብ ተወዳጅነት የነበራቸው “ሻለቃ” ረጋሳ ጂማ (በኋላ ጀነራል) የነበሩት
የኮለኔልነት ማዕርግ ተሰጥቷቸው በብርጌድ አዛዥነት ተመድበው ወደ
ኦምሐጀር ተመድበው እንዲያረጋጉ ተመደቡ።
ይህ እንዲህ
እንዳለ፤ አሥመራ ውስጥ የሚኖሩ በሕዝቡ ተሰሚነት ይኖራቸዋል የተባሉ ከሽማግሌዎች፤ ከካሕናትና የመሳሰሉ የተውጣጡ ሰዎች ለማነጋገር ፤ ዓረቦች ያደራጁት “ጀብሃ” የተባለው ተገንጣይ ለመምታት
አመቺ የሆነው ተቀናቃኙ የክርስትያን ስብስብ ነው ተብሎ ሲነገርለት
ወደ ነበረው ወደ “ሻዕቢያ” በመላክ በኛ በኩል ተኩስ የማቆም ፈላጎት ያለን መሆኑን “ፍላጎት” ብቻ ሳይሆን «የኢትዮጵያ መከላከያ
ሰራዊት ከካምፑ እንዳይወጣ ጭምር እናደርጋለን» በላችሁ ንገሯቸው በማለት ሽማግሌዎቹን ወደ ሻዕቢያ ላኩ።
የጀነራሉ
ከፈተኛው የመጀመሪያው ስሕተት ይህንን ውሳኔ ሲወሰኑ ከማንንም የመንግሥት አካልም ሆነ ባለሥልጣኖች ሳያማከሩ ለብቻቸው የወሰኑት
ነበር።
ደራሲው እንዲህ
ይላል፡
«የቶክስ
ማቆም ስምምነት ግጭትን ከማቆም እና ደም ከመፍሰስ የሚገታ አንዱ አማራጭ መፈትሄ ቢሆንም፤ አንደኛው ወገን ብቻ ከካምፑ እንዳይወጣና
እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ስምምነት መወሰን ግጭቱን የሚያስቆም ሳይሆን ግጭትን የሚያባብስ ነው። ያም ስለሆነ ሻዕቢያ ይህንን ዕድል
በመጠቀም “ሰረጀቓ” በሚባል ንኡስ ወረዳ ከጀብሃ ጋር የተጧጧፈ ውግያ ሲያካሂድ የነበረበት ውቀት በመኖሩ ፤ ሽማግሌዎቹ ያንን መልዕክት
የዘው መምጣታቸው ተፋላሚዎቹ ትንፋሽ የሚያገኙበት ዕድል አገኙ።
ሽማግሌዎቹ
ሰረጀቓ እንደደረሱ በሻዕቢያ እና ጀብሃ መካከል የለየለት ውግያ መካሄዱን ሲያዩ “ጀነራል አማን አደራ ብለው አምነው የላኩዋቸው
መልዕክት በልተው ፤ ሽማግልዎቹ የሚከተለው ንግግር ለሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መከሩዋቸው፦
«ምን እየሆናችሁ
ነው? ከዛሬ ነገ ከአማራ መንግሥት ቅኝ “ነፃ ታወጡናላችሁ ብለን ስንጠብቃችሁ እርስበርሳችሁ ትጋደላላችሁ?!!” በማለት ሊያስታርቁዋቸው
ገቡ።
ጀነራሉ የወሰኑት
በክ/ሃገሩ ውስጥ በየጦር ሜዳ ካምፖች ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ሠራዊት ከካምፑ እንዳይወጣ ያደረጉት ስሑት ውሳነ ለተገነጣዮቹ
የማጥቃትና የዝግጅት ዕድል የሰጠና የተግንጣዮቹ ሞራል ከፍ ያደረገ የልብ ልብ የሰጣቸው ያልታሰበ ዕድል ሰላገኙ ፤ ክጥቂት ወራት በኋላ ሁለቱ ተፋላሚ ኤርትራ ተገንጣይ ቡድኖች አንድነት ፈጥረው “መንግሥት ለመመሥረት” አስመራ ከተማን ለመያዝ ከተማይቱ ውስጥ
ቶክስ በመክፈት ወደ ፍጹም ዕብደትነት አጎለበታቸው።
ደራሲው ይህንን
በተመለከተ እንዲህ ይላል፤
“ጀነራሉ ወደ ተገንጣዮቹ የላኩዋቸው ሰላም ለማምጣት የተላኩ ሽማግሌዎች አደራ
በልተው ደም ወደ እሚፈስበት ወደ ተባባሰ ደረጃ ሰለተጠመዱ ፤ ተገንጣዮቹ
የልብ ልብ አግኝተው አሥመራ ከተማን ለመያዝ ያደረጉት ፍልሚያ በጥር
1975 ዓ.ም በከተማዋ ያለቁ ሰላማዊ ሰዎች ተጠያቂዎች ናቸው።” ይላል።
ጀነራሉ ቀጥለው የፈጸሙት ከፈተኛ ጥፋት
የእንግሊዝ
ኢምፐሪያሊዝም ፋሺስት ጣሊያንን ተክቶ ኤርትራ ክ/ሐገር ውስጥ አዲሱ
ቅኝ ገዢና ከፋፋይ አካል ለመሆን በወሰነበት ወቅት ከዚህ አዲሱ ቅኝ ገዢ ጋር ፊትለፊት ገጥመው ሕዝቡን በማንቃት «ፈደረሺን የሚባል
የባዕድ ሃይሎች የጫኑብንን ዲቃላ አስተሳስብ አንፈለግም» በማለት
ኤርትራ ወደ እናት ሃገርዋ ወደ ኢትዮጵያ እንድትዋሃድ ያደረጉ “የሃገር ፈቅር ማሕበር” መስራች አባላት እንደ እነ ታዋቂዎቹ “መልአከ ሰላም ንብረኡድ ዲሜጥሮስ ገ/ማርያም
እና ቢትወደድ አስፍሃ ወልደሚካኤል ላይ “የወንበዴዎች ደጋፊ አባላት ክስ በማሰማት”
የንጉሡ ደጋፊዎች ናቸው ተብለው ከታሰሩት እስር ቤት ውስጥ አብረው እንዲታሰሩ አደረጉ።
ጀነራል አማን የፈጸሙት ሦስተኛው ጥፋት
ሻዕቢያና
ጀብሃ ሰረጀቓ ላይ እርስበርሳቸው ሲተራረዱ ሃይላቸው በተዳከመበት ወቅት
በውቅቱ የዋልያ ክ/ጦር ዋና አዛዥ (በኋላ የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ሊቀመንበር) ወንበዴዎቹ መዳከማቸው ባደረጉት ጥናት
ሰለተገነዘቡ ፤ አዳክሞ ለማጥፋት ምቹ ወቅት ነው ብለው ሰላመኑበት ተጨማሪ ሠራዊት በመጠየቅ ወሳኝ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ ሲያናግሩዋቸው
፤ ጀነራል አማን ‘አይሆንም’ በማለት የተፈሪ በንቲን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ አሰናከሉት።
በወቅቱ ለሃገሩ
ሉዓላዊነት ሲዋደቅ የነበረው ሠራዊት ሁኔታው ሲሰማ ከፈተኛ ቅሬታና ሐዘን ተሰማው። ጀነራሉ ለእገዳው የሰጡት ምክንያት ይላል ደራሲው
«የተጀመረው
የሰላም ሽምግልና እንዳይሰናከል የሚል ምክንያት ቢሰጡም፤ ሃቁ ግን «የስጋ ጉዳይ ሰልሆነባቸው ነው» ይላል ደራሲው። በሌላ አነጋገር
«ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ» ማለቱ ነው።
ጀነራሉ ይህንን
ተግባር ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ፤ የሰላም ምፍትሔ ሰነድ ብለው ባለ 19 ነጥቦችን ለሚንስትሮች ጉባይ አቅርበው
ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠየቁ። የሰነዱ ዋናው ይዘት «ኤርትራ ውስጥ ዳግም ፍደረሽን እንዲጸድቅ የሚል ነው»
ደራሲው ይህንን
አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦
«ጀነራል
አማን ያቀረቡት የፈደረሺን ዳግም መመለስ ሰነድ የሰላም አምጪ መፍትሔ መሰሎ ቢታይም ባንድ እጅ ማንጨበጨብ እንደማይቻል ሁሉ ሃገር
ገንጣይ እሳት ጫሪዎቹ በሽማግሌዎቹ በኩል ስለ ተላከላቸው ጥያቄ መልስ ሳይገኝና አቁዋማቸው ሳያውቁ ጀነራሉ ተቻኩለው ሰነዱ እንዲጸድቅ
መጠየቅ ባንድ እጅ እንደማጨብጨብ መሞከር ነው» ይላል።
ሰነዱ ወደ
መኒስትሮች ጉባኤ እንደቀረበ በወቅቱ የደርግ ም/ሊቀመንበር ሻለቃ በኋላ የደርግ ሊቀመንበርና የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ፕረዚዳንት
የነበሩት ኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም እንዲሁም፤ የደርጉ ባለሥለጣኖች ሻለቃ ብርሃኑ
ባይህ፤ ሻለቃ አጥናፉ አባተ፤ ሻምበል መጎስ ወልደሚካኤል እና ሌሎች ደጋፊያቸውን በማስከተል ደርግ ዳግም ፈደረሺን የማጽደቅ አጀንዳ
ሰላልነበረውና ሰላለተወያየበት ስብሰባው በዚህ ሁኔታ ሊነጋገር አይችልም በማለት ስብሰባው ተበተነ።
ፕረዚዳንት
መንግሥቱ ጀነራሉ ይህንን ሰነድ ይዘው ለማጽደቅ የመጡበት ምክንያት «በፈደረሺን ሰበብ ኤርትራን የሚያስገነጥል ሰነድ ሳናሰላስለው
እንድናጸድቅላቸው ድንገት ይዘውልን መጡ»
ሻለቃ ሑሴን አሕመድ (በኋላ ም/ጅነራል -የ2ኛ አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ) ጀነራሉ ከጦር መከላከያነት
ወደ ደረጉ ሊቀመንበርነት ሆነው ከተሾሙ የአስተዳደረና የሕግ አማካሪያቸው ሆነው ከተመደቡት 7 በሕግና አስተዳደር ትምህርት የተመረቁ
ባለሞያ ወታደሮች፤አንዱ የነበሩት ሑሴን አሕመድ ስለ ጀነራሉ አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡
« ጀነራል
አማን ኤርትራ ደርሰው ወደ አዲሰ አበባ እደተመለሱ ባሕሪያቸውና የሥራ ፍላጎታቸው እየተቀየረ መጣ። የአመራር መንፈሳቸው እየተለወጠ
መጣ። እኔ የአስተዳደር ጉዳይ አጋዥያቸው ሆኜ እሰራ ሰለነበር ከዕለት ዕለት ሥራዎችና ሁኔታዎች በተገቢው ከመከታተል ይልቅ ጊዜያቸው
ከተለያዩ ታዋቂ ሰዎች ጋር መገናኘት ጀመሩ። የግል አማካሪያቸው ሆኖ የቀረበው የሕግ ባለሞያው ዶ/ር በረከተአብ ሃብተሰላሰ ነበር»።
ጀነራሉ ስለወሰዱት
እርምጃ በወንበዴዎቹ ካምፕ ሽብራና ፍራቻ ፈጥሮባቸው ሰለነበር፤ የኤርትራ ሕዝብም ጀነራሉ ደግፎ በመታየቱ ተገንጣዮቹ ከሕዝብ ይነጥለናል
የሚል ፍራቻ ሰላደረባቸው፤ ፈጣን ማጥቃት እንሚያደርጉ ዛቱ።
በዛቱት መሠረት ጥቅምት 25, 1974 ዓ.ም አሥመራን በዙርያ በመክበብ ማጥቃት
ጀመሩ። አብዮታዊ ሠራዊት በወሰደው የአጸፋ ማጥቃት እርምጃ ተገነንጣዮቹ ክፉኛ ተጨፍልቀው ሙትና ሙርከኛ ሆነው የተቀሩት ቁስለኞቻቸውም
ይዘው ፈረጠጡ። ሆኖም ተገነጣዮቹ አስመራን መቆጣጠር ባይችሉም ከከተማዋ
የሚያሰወጡና የሚያስገቡ መውጫና መግቢያ 4 መንገዶች በ10 ኪ.ሚ. ራዲያስ ከብበው የክፍለሃገሩ ጸጥታ ከማንኛውም ወቅት በከፋ የስጋት
ድባብ ውስጥ አስገቡት።
ለፀጥታው ስጋት ምክንያት የሆነው ይህ ጥቃት ከመፈጸማቸው
ካንድ ወር በፊት ሁለቱ ተገንጣይ ቡድኖች እርስበርሳቸው ሲተራረዱ በነበሩበት ወቅት እነ ተፈሪ ባንቲ ወቅቱ አመች ነውና እናጥቃቸው
ሲሉ ጀነራል አማን አይሆንም ብለው ሠራዊቱ እንዳይንቀሳቀስ በማገዳቸው ተገንጣዮቹ እንደልብ ሲንቀሳቀሱባቸው ከነበሩት ተራሮችና ምሽጎቻቸው
በሰፋት እንዲንቀሳቀሱ ዕድል የሰጣቸው የጀነራሉ ስሑት ወሳኔ ተገንጣዮቹ ሠራዊቱና አካባቢውን ሊያወኩ የበቁበት ምክንያት አንድ ወገን
ብቻ (ሠራዊቱ) ከካምፑ እንዳይወጣ በማድረጋቸው ነው።
በዚህ ምክንያት
ይሁን በሌላ ምክንያት ሻለቃ መንግሥቱ ሃይለማርያም የደህንነት ሚኒስትሩን
ተሰፋየ ወ/ልደሰልሴ መጀመሪያ ሕዳር 1975 ዓ.ም. ወደ አሥመራ ላኩት።
ተሰፋየ ወ/ልደስላሴ አሥመራ ደርሶ
እንደመጣ ሻለቃ መንግሥቱ አጠቃላይ የደረግ አባላት ጉባኤ በመጥራት
«ጓድ ተሰፋየ ኤርትራ ደርሶ ሰለመጣ በክፍለሃገሩ ያለው ሁኔታ እንዲነግረን ጉባኤው እንዲከፍትልን እጠይቃለሁ» በማለት ሰባሰባው ተጀመረ።
የደህንነት
ሚኒስትሩ ተሰፋየ ወ/ልደስላሴ በክፍለሃገሩ ሰላለው ሁኔታ አሲያስረዳ
« ወንበዴዎቹ
ካሁን በፊት አይተነው በማናውቅ ጉልበት አግኝተው አሥመራ ዙረያ ከበብው በማንኛውም ወቅት ከተማዋ እንደሚቆጣጠሩና በማንኛውም ወቅት
መንግሥት ሊያውጁ የሚችሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ጀነራል አማን ወደ ወንበዴዎቹ የላኩዋቸው የሽማግሌዎች « ልጆቻቸን ነፃ ሊያውጡን ተቃርበዋል»
በማለት የሕዝቡን ልብ አሸነፍዋል። ከዚህ ወደ ክ/ሃገሩ የተሟላ ረዳት ጦር ካልላክን ወንበዴዎቹ ክ/ሃገሩን ይገነጥሉታል።» በማለት
ንግግር አደረገ።
ይህ ንግግር
በጥሞና ካደመጡ በኋላ ጀነራል አማን እንዲህ ሲሉ መልስ ሰጡ፦
«ለመሆኑ
ከየት ያገኘኸው ዘገባና ጥናት ነው ይህንን ለማለት ያበቃህ? የኤርትራ ጉዳይ የሚፈታው በሠራዊት ሳይሆን በሠላም ነው። ይህ ደግሞ እኔ
ራሴ የያዝኩት ጉዳይ ሰለሆነ ለኔ ተወው» ሲሉ መልስ ሰጡ።
ይህንን አስመልክቶ
ደራሲው እንዲህ ይላል፡
«ባጠቃላይ
የጀነራሉ መልስ ምክያታዊ ቢሆንም፤ 3 ሚሊዮን ሕዝብ ለ10 ሺሕ የኢትዮጰያ ሠራዊት የሚደረግ ቁማር ነው። መዲናዋን ከብበው ወንበዴዎቹ
ኤርትራ ነፃ ወጥታለች ብለው ለዓልም ሊያውጁ በተቃረቡበት ወቅት ባለፉት ሦስት ወራት ሙሉ ሠራዊቱ ከካምፑ እነንዳይወጣና ቶክስ እንዳይከፍት
ሆኖ ወንበዴዎቹ እንዳሻቸው ቶክሰ ከፈተው መዲናዋን በከበቡበት አንድ ወገነ ብቻውን በአንድ እጅ እንዲያንጨበጭብ በተደረገበት ሁኔታ “ሰላም፤ፈደረሺን ወዘተ..” በሚል መመጻደቅ “ጉዳትን በገዛ
እጅ በራስ ማወጅ ነው”። ሰለዚህም የጀነራሉ ሐሳብ ቁማር መጫወት ሆኖ ሰለታየ በተሰብሳቢዎቹ ጀሮ አላገኘም»።
ተሰብሳቢው
በድምፅ ብልጫ ድምፅ ተሰጥቶ ውሳኔ የሰጠበት ተብሎ አብዛኛው ሠራዊት ተጨማሪ ልዩ ተዋጊ ጦር ይላክ በሚል አጸደቀው። ጀነራሉ ደጋፊ
ሲያጡ “የ3ኛ/አምበሳ ክ/ጦር ይላክ በማለታቸው፤ ውደቅ ሆኖ ኮንቨንሺናል አርሚ ሳይሆን በከባድ ተራራና ጸለቆች ወጥቶ
ወርዶ መዋጋት የሚችል እግረኛ ብቻ ይላክ በሚል ውድቅ ሆኖ በምትኩ
ሌሎች ክፍሎች ሰለተላኩ (ከነሱ ውሰጥ ናቅፋ ውሰጥ ተአምር ሰርቶ የተዋጋ 15ኛ ሻለቃ) እና የመሳሉ ተዋግዎች ይላክ ሰለተባለ፡
ጀነራሉ አኩርፈው «እኔ አሻንጉሊት አይደለሁም» በማለት
ከመደበኛ ሥራቸው በመቅረት እቤታቸው ተቀመጡ። ሃገሪቱ ተጋፍጦባት ባለው ሁኔታ የሃገር መሪ እቤቱ መቀመጥ ማለት በሃገሪቱ ላይ የሚወርድ መከራ
መገመት አያስቸግርም።
ሁኔታው አሳሳቢ
ሰለነበር፤ ደርግ 4 ባለሥልጣኖች ጀነራሉን ለማነጋገር እና ችግሩን ለማወቅ ወደ ቤታቸው ላከ። ባለሥለጣኖቹ ጀነራሉ ይቅርታ ጠይቀው
ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ቢጠይቁዋቸውም አሻፈረኝ በማለት ተስፋ አስቆርጠውና ቅድመ ሁኔታ አስይዘው ሸኙዋቸው።
ወደ ጀነራሉ
መኖርያ ቤት ሊያነጋግሩዋቸው ከተላኩት የደርግ ሸምጋዮች አንዱ ከዛ በፊት በነበረው ያለመጣጣም ያስከተለው ሰብሰባ ላይ ጀነራሉ በመጥፎ
ዓይን ያዩት ይደህነነቱ ሹም ኮለኔል ተሰፋየ ወ/ለደሰልሴ ሰለነበር ከሽምግልና መልስ ወዲያውኑ የመኖሪያ ቤታቸውና የመሥስርያ ቤታቸው
ስልኮች እንዲጠለፍ አደረገ።
ከተጠለፈው
ስልክ አንዱ የምድር ጦር እስታፍ ዋና አዛዥ የነበሩት ጀነራል ግዛው በላይነህ «ደርግ ሊያሰራኝ አልቻለም» የሚል የስልክ ልውውጥ
ቀድቶ ተሰብሳቢው እንዲያደመጠው ኮለኔል ወልደሰላሴ አቀረበው።
ጀነራል አማንን
ወክለው ወደ ደርግ የላኩዋቸው የ3ኛ ክ/ጦር (አንበሳ ክ/ጦር) አባሎች ከሐረር ወደ አዲሰ አበባ በመምጣት ስለ ደህንነታቸውና ሁኔታቸው እንዲያረጋግጡ ወደ ቤታቸው ሄደው ምን እንደገጠማቸው ሲጠይቁዋቸው፡ ሕዳር 22/1974 ዓ.ም አጠቃላይ የደረግ ሰብሰባ ሰላሚካሄድ እዛ ሂዳችሁ
ስለተከሰተው ሁኔታ አስረዱን በሉዋቸው በማለት አስናበትዋቸው።
የጀነራሉ
ደህንነት ያሳሰባቸው አባሎች ወደ ስብስባው በመሄድ ሁኔታው ለማዳመጥ ተገኙ። ስብሰባውን የመሩት የደርጉ ም/ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያም ስለ ጀነራሉ
እንዲህ ሲል ዘገባ አቀረቡ።
« ኤርትራ ከእናት ሃገርዋ ከኢትዮጵያ ጋር እንደትዋሃድ ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉት መልአከሰላም ዲሞጥሮሰ ገ/ማርያም እና ቢትወደድ አስፋሃ ወ/ሚካኤል
እንዲታሰሩ አድርገዋል።
አበዮታዊ
ሠራዊት ከካምፑ እንዳይወጣ አግደው ቶክስ እንዳይከፍት በማድረግ ወምበዴዎቹ ግን እንዳሻቸው እንዲንቀሳቀሱና በሠራዊታችን ላይ ቶክስ
እንዲከፍቱ ምቹ ሁኔታ ፈጥሩላቸው።
በመጨረሻም
ርዕሰ መዲናዋ አሥመራ ከተማን ለመያዝ ከብበው ሲያሰጨንቁ ባለበት ወቅት
ከዚህ ረዳት ሠራዊት ይሂድ ሲባል አሻፈረኝ አይሆንም ብለው ሲያስቸግሩ በመጨረሻም ይላክ የምትሉ ከሆነም “መካናይዝድ
ብርጌድ” ይሂድ በማለት ተቀባይ ሲያጡ በዚህ አኩርፈው እቤታቸው ተቀመጡ።»
በማለት ሻለቃ
መንግሥቱ ለተሰበሳቢው ሲያስረዱ
ተሰብሳቢውም
«እውነት
ጀነራሉ ይህንን ፈጽመው ከሆኑ ተጠርተው እዚህ መጥተው እንሲያሰረዱን
ይደረግ»
ሲሉ፤ ሻለቃ መንግሥቱም፤ መምጣት አያሰፈለጋቸውም፤ ይህንን የስልክ ቅጅ አድመጡ
ብለው ከጀነራል ግዛው በላይነህ ጋር አማን ያደረጉት የሥልክ ልውውጥ እንዲሰሙት ተደረገ።
ተሰብሳቢውም
«መንግሥቱ ያንድ የመሳርያ ግምጃ-ቤት ሐላፊ የነበረ መኮንን ነው፤ አብረውት ያሉትም እንደዚሁ ናቸው፡ እያሉ ጀነራል አማን ለሻለቃ
መንግሥቱ ያላቸው ንቀት የሚናገር ንግግራቸው ካደመጡ በኋላ ተሰበሳቢዎቹ በቁጣ ነደዱ።
ስብሰባው
ዕልባት ለመሰጠት በማግሥቱ ቀጠሮ ተደርጎ ተበተነ።እዚህ ላይ ማወቅ የሚገባን፤ የጀነራሉ መኖርያ በመድፍና በታንክ ተከብቦ ስለነበር
ጀነራሉ “የእቤት ቁም እስረኛ” እንደነበሩ ነው።
በይደር የተላለፈው
ስብሰባ በማግስቱ ቀጠለ። ም/ሊቀመንበር መንግሥቱ ስብሰባውን በመክፈት “ይህች አገር አደጋ ላይ ነች። በተለይ በላቀ ሐላፊነትና
እምነት የመሩናል ብለን የጣልንባቸው ሰዎች በተራቸው እኛው ጋ ብትራቸውን ለመሰነዘር እየቃጡብን ነው። ሰለዚህም አገሪቱን ለማዳን
እርምጃ መውሰድ አለብን ካሉ በኋላ፡ ይህ እርምጃ የተባለው ከባድ እረምጃ በጀነራሉ ላይ ለመውሰድ በወቅቱ የደህንነት ኦፐረሺን ሐላፊ
የነበርው ሻለቃ ዳንኤል አስፋው ወደ ጀነራሉ መኖርያ ዘንድ በመሄድ ተሎ በቁጥጥር ውስጥ እንዲያውላቸው ትዕዛዝ ተሰጠው።
ከጥቂት ቆይታ
በኋላ ሻለቃ ዳኒኤል አስፋው ወደ ጉባኤው አዳራሽ በመሄድ “ ጀነራሉ እጃቸው እንዲሰጡ ቢጠየቁ ፈቃደኛ አለሆኑም» በማለት አስረዳ።
ልክ በ05.00
ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቤተመንግሥት አርሞር ታንኮች ወደ ቦሌ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ጀመሩ።አቅጣጫቸው ያመሩት ወደ ጀነራሉ መኖርያ ነበር።
ሻለቃ ዳኒኤል የሚመራው ይህ በመድፈኛ ታንክ የታጠቀ ልዩ ተልዕኮ የተሰጠው ሠራዊት የሚመራው “የአየር ሃየሉ ሻለቃ ዳኒኤል አስፋው”
ነብር።
ሠራዊቱ ከጀነራሉ
መኖርያ እንደደረሰ እጅ እንዲሰጡ ቢጠየቁ አሻፈረኝ በማለት መትረየስ በመጥመድ ካንድ ሰዓት በላይ የሚሆን የተኩስ ለውውጥ አደረጉ።
ከዚያ በኋላ እጃቸው ለመያዝ ሰላለተቻለ፤ አንድ ታንክ የግቢውን መኖርያ በሩን በርግዶ ወደ ውስጥ ገባ። ሆኖም ባሳዛኝ ሁኔታ ጀነራሉ
እራሳቸውን ገደለው ተገኙ።
ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶም ‘ሶባ’ በሚባል ሱዳን ካርቱም ከተማ አቅራቢያ ወታደራዊ ካምፕ ውሰጥ የመኮንኖች ሥልጠና በመውሰድ በከፈተኛ ማዕረግ የተመረቁ ቆፍጣና ወታደር ነበሩ። ጀነራሉ
በ1924 ዓ.ም.በአሥመራ ከተማ ተውልደው መጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው አሥመራ ካምቦኒ ት/ቤት ተምረው ፤ ከዚያም አዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአሜሪካ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ዕውቅ መኮንን ነበሩ። ሆኖም ያ
ሁሉ ወታደራዊ ዕውቀትና ትምህርት አካብተው እሰከ ጀነራለነትና የሃገር መከላከያ ሚኒስትርነትና የሃገሪቱ ጊዝያዊ ወታደራዊ መንግሥት ሊቀመንበር ሆኖው ያገለገሉ የታወቁ ወታደር ቢሆኑም፤ የወቀቱ የፖለቲካ ስንክሳር በቅጡ የተረዱት ሰላለነበረ
ለሞት ተዳረጉ።
ለዚህ ሁሉ
የዳረጋቸው ጥፋቶች፤ ለማጠቃለል እንደገና ባጨሩ ላስታውሳችሁ፦
ከጣሊያን
እና እንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ኤርትራን ነፃ አውጥቶ ኤርትራ ወደ እናት ሃገርዋ ለማዋሃድ “የሃገር ፍቅር ማሕበር” (ማሕበር ፍቕሪ ሃገር) መስረተው ከራቢጣ
እሳላሞችና የመሳሰሉ አክራሪ ተገንጣይ ክርሰትያን አባሎች ማሕበሩን በግምባር መሪነት ታግለው አኩሪ ሥራ የሰሩ መልአከ ሰላም ንብረእድ ዲሞጥሮስ ገ.ማርያም እና ቢትወደድ አሰፍሃ ወ/ሚካአል እንዲታሰሩ ጀነራሉ በመወሰናቸው፤
ከዚያም ለተገነጣዮቹ ምቹ ዕድል የከፈተ ያንድ ወገን የቶክስ አቁም ውሳኔ አሳለፈው
ሰራዊቱ እንዲጠቃ በማድረጋቸው።
ተገንጣዮቹ
ለማነጋገር ጀነራሉ የላኩዋቸው ሽማግሌዎች አደራ በመብላት ሳይመለሱ መሰወራቸው ሲረዱ፤ ቀደም ብለው ያስተላለፉት ያንድ ወገን ቶክስ አቁም ውሳኔ ዳግም መፈተሽ ሲኖርባቸው ውሳኔውን
ሳይሸሩ በዛው እንዲቀጥል በማድረጋቸው እና ተገንጣዮቹ አሥመራን እስከመክበብ ያድረሰ ውሳኔ መኖሩን ።
ከዚያም ረዳት
ሠራዊት እንዲጨመር ሃሳብ ሲቀረብላቸው አለመቀበላቸው እና እንዲሁም ተገንጣዮቹ እርስበርሳቸው እየተታኮሱ እየደከሙ ስለነበር፤ ኮለኔል
(በኋላ ጀነራል) ተፈሪ በንቲ ያቀረቡትን የመልሶ ማጥቃት ሃሳብ አልቀበልም ማለታቻው፡
ጦሩ ሳይንቀሳቀስ
ካምፑ ውስጥ እንዲቀመጥ በመደረጉ በጥር 10/1975 ዓ.ም ተገነጣዮች አሥመራን ለመያዝ ቶክስ እስከመክፈት ጉልበት ማግኘታቸው፡
እንዲሁም
ቅደም ጥናት ሳይደረግበት ኤርትራ በፈደረሽን እንድትተዳደር ካቀረቡዋቸው ነጥቦች መካከል እና ከላይ የቀረቡ ነጥቦች ተደማምረው በጥረጣሬ ዓይን እንዲገቡ ሆነ።
በመጨረሻም ባሳዛኝ ሁኔታ ራሳቸው ገድለው ተገኙ።
ለዘገባው
ደራሲ ሰናይ ከሰተ እና የምሳሰሉ መረጃዎች እያመሳከርኩ ያጠናከረኩትን
አንባቢ የራሱ ገንዛቤ እንዲወሰድ አድርጌአለሁ።
አምሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay

No comments:
Post a Comment