Saturday, June 21, 2025

የአዲስ ዓለም ሥርዓት መሪዋ አሜሪካ ያስቀመጠቺው የአፍሪኮም አዛዥ ጄነራል ማይክል ላንግሌይ እና ባገኘው የወንድ ደረት ላይ የሚለጠፍ “መናምንቴው” አሸከራቸው አብይ አሕመድ ጋር ሰሞኑን ተገናኝቷል! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/21/2025

 

አዲስ ዓለም ሥርዓት መሪዋ አሜሪካ ያስቀመጠቺው የአፍሪኮም አዛዥ ጄነራል ማይክል ላንግሌይ እና ባገኘው የወንድ ደረት ላይ የሚለጠፍ “ናምንቴው” አሸከራቸው አብይ አሕመድ ጋር ሰሞኑን ተገናኝቷል!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/21/2025

ሐፍረት የማያውቅ አብይ አሕመድ በህ ወር ውስጥ ሁለት የኮሎኒያሊስትዋ አሜሪካ አለቆቹ አዲስ አበባ ድረስ መጥተው አነጋግረውታል

እነዚህም  ሕዝባችንን በገዳይ ክትባት ለመቀነስ የጣረ ቢል ትስ የተባለው ዓለም የተጠየፈው ሐሰተኛ ሰው እና ጂቡቲ ውስጥ ሆኖ አፍሪካን እንዲቆጣጠር  የተሾመው “የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ “AFRICOM” አዛዥ የሆነው “ጸረ አፍሪካ” ነው ተብሎ በታዋቂ የአፍሪካ  ምሑራኖች የተወገዘው ጄነራል ማይክል ላንግሌይ  በመለስ ዝናዊ እና  በሃይለማረያም ደሳለኝ ቦታ የሾሙት አዲሱ አሽከራቸው አብይ አሕመድ እንዴት እንደሚያገለግላቸው ሁለቱ ጸረ አፍሪካ ገለሰቦች በየተራ  መመሪያ ስጥተውት ሂደዋል።

“AFRICOM ማዘዣው መሰረቱ ያደረገው ጀቡቲ ውስጥ ነው። የአፍሪካ ማፈርያ እያልኩ የምጠራት ማፈርያ የሆንችብን “ጀቡቲ” የተባለች መንደር ፤ ባሕርዋ በሙሉ  አፈሪካን ለመቆጣጠር የሚፈልጉ የዓለም ቅኝ ገዢዎች የተባሉት ሁሉ ፤ ከነጭ እሰክ ዓረብ ፤ ከኤሺያ እሰክ አጥናፍ ያሉት ሁሉ የባሕር ማዘዣና መገልገያ  ሰጥታ የአፍሪካን ሕልውና እንዲደፈር በባንዳነት ሥራ  ከተሰማራች ዘመናት ሆኗታል። ስለዚች ማፈርያ መንደር ካሁን በፊት አንድ አርቲክል ጽፌአለሁ። በዚሀ ሁሉ የተላላኪነት ሥራ ስተሰማራ “ተይ የሚለዋት” የተማሩ ሰዎች ያሉባት አትመስልም።

ያም ሆኖ ይህ ጥቁር አሜሪካዊ ጀነራል ባለፈው ወራት በሃገረ ቡርኪና ፋሶ የታየው ሕዝባዊ/አፍሪካዊነት መነሳሳትና መሪያቸው ኢብራሂም ትራኦረ የቀየሰው አስገራሚ ራስን የመቻል ጸረ ኮሎኒያሊስቶች ፖሊሲ የሃገሩና የመላ አፈሪካ  ሉዓላዊ ነጻነት እንዲከበር አበራታች በሆነ ለአዲስ መንገድ በመነሳቱ ምከንያት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ  የቡርኪና ፋሶ መሪው ኢበራሂምን ለመፈንቀል በሐሰት ስሙን በማጠለሸቱ  በብዙ አፈሪካ መሑራን እና ወጣቶች መወገዙን ታሰታወሳላችሁ።

ይህ ጸረ አፈሪካ የሆነ ጥቁር አሜሪካዊ ሰው ፤ የተላከበት አጀንዳ የምትፈጽም ሃገር ኢትዮጵያ  ምቹ ሆና ስላገኛት ቅጥረኛቸው ሥልጣን ላይ አውጥተው ኖቭል ሸልማት ያስሸለሙትን አሽከራቸው አብይ አሕመድና እንዲሁም ሌላው የኬኒያው አሽከራቸው William Ruto በኩል የምስራቅ አፈሪካና የመሳስሉ ሃገሮችን ለመቆጣጠር እንዲያስችላቸው ወደ ናይሮቢና አዲስ አበባ በመሄድ አንድ በአንድ በየተራ ለአሜሪካ ምን መስራት እንዳለባቸውና በምትኩ አሜሪካ ለሥልጣናቸው መደላድል እንደምታመቻቸላቸው ትእዛዝ ሰጥቷቸው ሄዷል።

አስቡት! በአፍሪካ ምሑራን ዘንድ የተጠሉ ሁለት ጸረ አፍሪካ የሆኑ ሁለት አሜሪካኖች ቢል ጌትሰ እና ጄነራል ማይክል ላንግሌይ  አበይን ባንድ ሳምንት ሲያገኙት፤ ምን እንደሆነ ይገባችኋል የሚል እምነት አለኝ።

“AFRICOM የአፍሪካን ሀገራት ሉዓላዊነት እንዲያዳክም እና ለአዲሱ ዓለም ሥራዓት (New World Order) ግብ መሳካት የተመሰረተ ጣለቃ ገብ “ኮሎኒያል ሠራዊት” ነው።

ታዲያ አለመታደል ሆኖ እንደ የቡርኪና ፋሶ መሪ ኢበራሂም ትራኦረ እና የመሳሰሉ ሃገራዊያን  ሀገራችን ባለመታደልዋ የድህነት ተመሳሌት ፤ የጠባብ ብሔርተኞች መጫወቻ ፤ የኮሎኒያሊስቶች ፤ የግብረሰዶሞች፤ አዲስ አበባ ወሰጥ የፋ የ666 ኢሉምናቲ ደላሎች ፈቃድ ሰጪ ፤ የገራፊዎች፤ የዘራፊዎች ፤ የደፋሪዎች ፤ የካኒባሊስቶች ሰው ሰውን በሊታዎች መናሃሪያ ሆናለች።

አምላክ ሆይ እጆችዋ ዘርግታለች እጅህን ዘርጋላት!

ሰላም ሰንብቱ

ጌታቸው ረዳ

 

No comments: