Tuesday, June 17, 2025

የመአዛ መሐመድ ቅሌትና የሄልኮፕተርዋ መመታት ጉዳይ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/17/25


የመአዛ መሐመድ ቅሌትና የሄልኮፕተርዋ መመታት ጉዳይ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/17/25

ይህ በቅንፍና በቢጫ ቀለም የቀለመ የምትመለከቱት ጽሑፍ ከለጠፈኩ ከጥቂት ሰዓት በኋላ የተጨመረ ነው።

<<<<ይህ ጽሑፍ ከለጠፈኩ ከጥቂት ሰዓት በኋላ ድንገት “ዩ ቱብ” ሰገባ አሰገራሚው የመአዛ “የጀብዱ ሽሚያዳግም አየሁ። የኸውም፤ ሄልኮፕተሩ “እንደተከሰከሰ እንጂ እንዳልተመታ” የሰራበትና የካደቺበት የነ ፋኖ ደረጀ ጀብዱ፤ ወዲያውኑ በመትኩ “በአማራ ፋኖ በሔራ ሃይል” (የራሰዋ ቡድን) እደተመታ እንጂ በአፍሃድ (የደረጀ ጎንደር ፋኖ ቡን) እንዳልተመታ የጅበዱ ሽሚያ ሰበር ዜና ብላ ሰርታለች።>>>>>»

እንዲህ ስትል

ሰበር ዜና | የፋኖ ምላሽ ባለስልጣናቱን ጭና ስትጓዝ ስለተመታችው ሄሊኮፕተር!”

https://youtu.be/3a5ipF_pDnM?si=ruuXWox6AJn4X6xH


 በሚል ካንድ ቀን በፊት 6/16/23 በሮሃ ሚዲያ ያሰተላለፈቺውን  “በሄልኮፕተሩ በአደጋየሞቱ ሰዎች” ብላ ነው ያስተላለፈቺው።ማስረጃውን አድምጡ። ይህ ጉድና የጀብዱ ሽሚያ ምን ትሉታላችሁ?

ትንሽ ሳታፍር ደግሞ

የነ ደረጀ  ጀብዱ ለማሳነስ ስትል ያስተላለፈቺው ደግሞ የሚከተለው አድምጡ


የፋኖ ሃይሎች ተጣምረው ታሪክ ሰሩ! ድንገት በአዲስ አበባ የተካሄደው ውጊያ! የደህንነት ተቋሙ ተመታ! አዛዡ ተገደሉ!

https://youtu.be/YPTvjfYZO3Q?si=KJgJTeZB1NFB7Wz6


    እስኪ የመአዛ ምንነት እንመልከት

አሜሪካ ውስጥ የምትኖር የሮሃ ሚዲያ አዘጋጅ የሆነቺው “ጋዜጠኛ መአዛ መሐመድ “ በፋኖ ወገንተኝነትዋ የእነ ተፈራ ማሞ የዘመነ ካሴና የመሃይሙ የፋኖ ምሬ ወዳጆ ጋዜጠኛ ነች።

መአዛ ከነበረባት የክብር ማማ በመፈጥፈጥ ባንድ “ወሎ ውስጥ” አንድ ፋኖ ብቻ መኖር እንዳለበት እርሱም  ከእነ ምሬ ወዳጆ ፋኖ ውጪ እንደ የእነ “ኮሎኔል ፋንታሁን ሞሐቤ” ያሉ በሃሳብና በአደረጃጀት የተለዩ ፋኖዎች ወሎ ውስጥ መንቀሳቀስ እንደሌለባቸውና መወገድ እንዳለባቸው (መደምሰስ እንዳለባቸው) “ወንድም ከወንድም ጋር” እንዲጋደል የሰበከች “ዮዲት ጉዲት መሳይ” ባንድ ቀን ወደ  አረመኔነት የተለወጠች “ደም የጠማት” አስደንጋጭ ሴት ነች።

ሰሞኑን  በጀግኖቹ በጎንደሬዎቹ የፋኖ አርበኞቹ በእነ ደረጀ በላይ አልሞ ተኳሽ ተዋጊዎች ተቶኩሶባት ተመትታ ከሰማይ የተጣለችው የአገዛዙ ፋሺስት ባለ ሥልጣናት የያዘች ሄልኮፕተር አስመልክታ መአዛ መሐመድ ዜና ስትሰራ ፤የአገዛዙን ሚዲያ በመወገን “በአደጋ መከስከስዋን" እንጂ ሄልኮፕተርዋ በፋኖዎቹ "ተተኩሶባት" እንዳልወደቀች በሮሃ ሚዲያ  ዜና አሰራጭታልች።

አንባቢዎች ልጠይቅ የምፈልገው ፤ ሄልኮፕተርዋ በራሰዋ ፋኖ ቡድኖች ብትመታ ኖሮ ፤ ሄልኮፕተርዋ መከሰከሰዋን/ መሰባበርዋን/ እንጂ ‘ተመትታ እንዳልወደቀች” ትዘግብ ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ ላቀርብ እፈልጋለሁ። በእርግጠኛነት “በጀገኖቹ በእነ ምሬ ወዳጆ ተመትታ ወደቀች” ትል ነበር።

ሆኖም ያንን የነ ደረጀ በላይ ፋኖ ቡድን መኖር የለበትም ከምትል ሰው ፤ ከነ ጭራሹ ሕልውናቸው መደምሰስ አለበት ከምትላቸው ፋኖዎች አስገራሚ ጀብድ በመሰራቱ ያንን ማድነቅ ውርደት መስሎ ሰለታያት ፤ የአገዛዙን ፕሮፓጋንዳ ደግፋ ““በአደጋ መከስከስዋን” ዜና መስራዋ ክፉ ሰው (ኢቭል) መሆነዋን አሳይታናለች። በሚገረም ዜናዋ ደግሞ የኦንግ ታጣቂዎች አዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ያገዛዙን ሰራዊት ማጠቃታቸው ዘግባለች። የ አ ፍ ሕ ድ -የነ መከታው/እስክንድር ፋኖ የሚያደረገው የጦር ማጥቃት ግን ዘግባ አታውቅም። ለምን?

የማትደግፈው ቡድን ቢሆንም አንድ ያልተጠበቀ አስገራሚ (ሰርፕራይዝ) የጋራ ጠላት በምትለው መንግሥት ላይ ጉዳት ሲፈጽም (ላንድ አምሐራ ነፃነት ነውና የተፈጸመው ጀብዱ እንደ መአዛ የመሳሰሉ ጋዜጠኞች due diligence” "ተገቢውን ትጋት" ለመፈጸም ቢያንስ መጠነኛ የሞራል ግዴታ ማሳየት ነበረባቸው። ጨዋ ጋዜጠኞች ወገንተኛነትን፤ ጎጠኛነትን ንቀው ከሥነ ምግባር አኳያ ትክክለኛውን ማሰራጨት ይጠበቅባቸዋል

ዜና ሲሰራጭ በህይወት እና ነፃነት ላይ የሚያሳርፈው ጉዳት ተስፋና ጥቅም መመዘን ፤ በንጹሐን ሰዎች ላይ የመብት ረገጣ ፤ ያልተገባ ቅጣትና ሞት ሲደረስ ሞያው “የሞራል ድንጋጤ እንድትተገብር ይጠይቃል።

በዚህ በኩል መአዛ ወድቃለች። የአብይ አሕመድ ፕሮፓጋንዲሰቶችን በመወገን መአዛ  መሐመድ ያስደመጠችን “የደስ አይበለው” ከፉ ባሕል ለወደፊቱ ይታሰብበት።

 ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

No comments: