Thursday, May 22, 2025

አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነትና ፋሽዝም በኢትዮጵያ - በዶክተር አሰፋ ነጋሽ በድጋሚ የተለጠፈ Ethiopian Semay 5/22/25

 

አክራሪ  የትግራይ ብሄረተኛነትና ፋሽዝም በኢትዮጵያ -

በዶክተር አሰፋ ነጋሽ

በድጋሚ የተለጠፈ 

Ethiopian Semay 5/22/25

ከድረገጹ ዘግጅት

ለአንባቢዎች ማሰታወሻ

ዋና ዋና ቁም ነገሮችን በቀላሉ የአንባቢን ግንዛቤ እንዲረዳ አቅልሞት የተጨመሩት በደራሲው ሳይሆን በድረገጹ አዘጋጅ ነው። የትም የማታገኙት ትምሕርት እንደምታገኙበት ተስፋ አለኝ። ጽሑፉ በዶ/ር አሰፋ መልካም ፈቃድ በመጽሐፌ ውስጥም የተካተተ ነው።

ተቃዋሚዎች ወያኔን ፋሽስታዊ ተፈጥሮውን ሳናውቀው አርባ ሁለት ዓመታት ቆጠርን!!!!!!”

ለአስራሰባት ዓመታት በርካታው የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢትዮጵያ ምሁራን እስከ ተራው ሰው፤ ከኢትዮጵያ ፓለቲካ መሪዎችና የጦር ጄኔራሎች ጀምሮ በየፈፋውና በየሜዳው ወያኔን ሲፋለም እስከነበረው ተራ ወታደር ድረስ በዚህ በትግራይ ማህበረሰብ ማህጸን ውስጥ ስለተፈጠረው የፋሽስት ጽንስ፤ የአማራን ህዝብና በዚህ ህዝብ የተመሰለችውን ኢትዮጵያን የጥላቻው ዋነኛ ዒላማ ስላደረገው የትግራይ የፋሽስት እንቅስቃሴ ምንነት ሳያውቅ፤ ሳይረዳ ቀረ። ደርግን የተቀላቀሉት ምሁራንም ሆነ የኢሰፓ ካድሬዎች  መሪያቸውን ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያምን ተከትለውአብዮታዊት እናት ሀገር ወይም ሞት፤ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር፤ወደፊት በሉለት ይለይለትእያሉ መፈክር ከማሰማትና የኢትዮጵያን ወጣት ለጦርነት እሳት ከመማገድ፤በውስኪ ከመራጨትና ጮማ ከመቁረጥ በስተቀር በትግራይ ምድር ውስጥ እንደ እሳት ይንቀለቀል የነበረውንና በትግራይ ህዝብ የጎሳ ማንነት ላይ ተመስርቶ ስር እየሰደደ የመጣውን አዲሱን የፋሽስት የፓለቲካ እንቅስቃሴ ተፈጥሮና ባህርይ ሊረዱ አልቻሉም። በሀገሪቱ ሆነ በውጭ ሀገራት ተሰደን ያለነውና ቀለም ቆጠርን ብለን የምንል ኢትዮጵያውያን ምሁራን ነን ባዮች ይህንን በትግራይ ውስጥ እያበበና ስር እየሰደደ የመጣውን የፋሽዝም ችግኝ ተፈጥሮና ባህርይ አልተረዳንም ነበር።

በዚህ ዓይነት ለአስራ ሰባት ዓመታት በደርግ ወታደራዊ አምባገነን ስርዓት ምክንያት ክፉኛ የተቀጠቀጠውና ቀለም የቆጠሩ ልጆቹትን በቀይ ሽብር የተነጠቀው የመሃል ሀገሩ ህዝብ (በተለይ ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ) ራሱንም ሆነ ሀገሩን ከዚህ አስከፊ በትግራይ ህዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ የቆመ የፋሽስት ድርጅት ጥቃት ለመከላከል ሳይችል ቀርቶ በደርግ መውደቅ ማግስት የትግራይ ፋሽስቶችና የኤረትራ ግብረአበሮቻቸው መዳፍ ስር ወደቀ 

የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት አዋላጅነት የተጸነሰ የፋሽስት እንቅስቃሴ ተፈጥሮና መዳረሻ ባለማወቁ ባለፉት ሃያ ሰባ ዓመታት ለተጫነበት ታይቶና ተሰምቶ ለማይታወቅ እጅግ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ ፋሽስታዊ (የወያኔ የአፓርታይድ ስርዓት) አገዛዝ ተጋላጭ ሊሆን ችሏል።  በደርግ ዘመንም ሆነ አሁን ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ በነበሩት ሃያ ስድስት ዓመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል እንመራለን ብለው የተነሱ የተቃዋሚ ድርጅቶች ፓሊሲዎችም ሆነ የፓለቲካ አመራር በእውቀት ሳይሆን በደመነፍስ በስሜት የሚመሩ ስለሆነ ህወሃት ከትጥቅ ትግሉ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ የሚከተላቸው ፓሊሲዎች ከፋሽስታዊ ተፈጥሮ የሚመነጩ መሆናቸውን ለመገንዘብ አልቻሉም። በጥናትና በእውቀት የሚመራ የፓለቲካ አሰራር በማይታወቅባት ኢትዮጵያ ውስጥ የህወሃትን ፓሊሲዎችና ድርጊቶች ተቃዋሚዎች አንዴ ከህወሃት ኮሚኒስትነት፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከህወሃት ስታሊስትነት፤ ጠባብነት ወዘተ ሲፈርጁ ታይተዋል። 

ለነገሩ ህወሃት እስታሊናዊ ዘዴዎችን ለህዝብ ማፈኛነት መጠቀሙ ኮሚኒስት ወይም ሶሻሊስት አያሰኘውም። ፋሽስቶች የግራም ሆነ የቀኝ ክንፍ የፓለቲካ ኃይሎችን ዘዴዎች እንደሚጠቀሙ የታወቀ ነው። ግን ይህ ፋሽስቶችን ሶሻሊስት ወይም ካፒታሊስት አያሰኛቸውም። ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት እንኳን የዚህን ስርዓት ፋሽስትነት አበክረው በድፍረትና በግልጽ ሲናገሩ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦችንም በጸረ-ትግሬነት ከመፈረጅ ባለፈ የሚሉት ነገር ምንድነው ብለን ለመመርመር ሙከራም አላደረግንም።

እዚህ ላይ አጽንኦት ልሰጥ የምፈልገው ኢህአፓ ወያኔና ሻቢያ የመሳሰሉት ቡድኖች የደርግ መንግስት ፋሽስት ነበር የሚለውን ግልብ፤ እውቀት-አልቦ የሆነ የድንቁርና ትንተና እንደማልቀበልና ደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት እንጂ ፋሽስት የሚያሰኘው ባህርይ እንዳልነበረው በግልጽ ላሰምርበት እፈልጋለሁኝ። 

ምክንያቱም አንድን መንግስታዊ ስርዓት ከምንም በላይ ፋሽስት የሚያሰኘው መስፈርት መንግስት በአንድ ጎሳ ወይም ህዝብ ማንነት ላይ በተመሰረተ አክራሪ የሆነ ብሄረተኛነት ላይ የቆመ መሆኑና መንግስታዊ ፓሊሲዎችም የሚቀረጹት የአንድን ምርጥ ህዝብ የፓለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ ወታደራዊና የባህል የበላይነት ለማረጋገጥ መሆኑና ያንን ቆምኩለት የሚለውን ህዝብ እንደ አዲስ ህዝብ በዳግም ልደት ለመፍጠር መመኮሩ ነው። 

ደርግ በማናቸውም መለኪያ እነዚህን ሁለት ዋና ዋና የፋሽስት ስርዓት መስፈርቶች የሚያሟላ አልነበረም። ደርግ እንደ ወያኔ ትግሬዎች መንግስት ያንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ጎሳ የበላይነት አልሰበከም፤ ያንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ጎሳ የፓለቲካ፤ የኢኮኖሚ የበላይነት አልተከለም፤ አልተገበረም ደርግ አንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ጎሳ ለይቶ አንተ ወርቅ ነህ ሌሎቹ ግን ጨርቅ ናቸው ብሎ ያንድን ጎሳ ተወላጆች በአዲስ ዓይነት አስተሳሰብ አልቀረጸም በማንአህሎኝነት የአንድን ጎሳ ተወላጆች አነሳስቶ ሌሎችን ጎሳዎች እንዲንቁና እንዲጠየፉ አላደረገም 

ደርግ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳደረጉት አንድን ጎሳ ለይቶ የአዲስ ማንነት ባለቤት በማድረግ በአመለካከታቸውም ሆነ በድርጊታቸው ኢትዮጵያ ህብረተሰብ ባህልና እምነት ያፈነገጡ በእብሪት ተወጥረው ታሪካችን፤ ባህላችን፤ ዘራችን ከሌላው የበለጠ ነው በሚል ትዕቢት ከበሮ ይዘው አምስተርዳምና ዋሽንግተን፤ ትግራይና አዲስ አበባ ላይ አደባባይ ላይ እንዲጨፍሩ አላደረገም ለዚህ ነው ደርግ አምባገነናዊ የወታደራዊ መኮንኖች መንግስት እንጂ እነ ኢህአፓና ሌሎች የግራ ድርጅቶች፤ ኦነግ፤ ወያኔ ሻቢያን የመሳሰሉ ቡድኖች ድንቁርናና በጭፍን ጥላቻ ላይ ተመስርተው እንዲሚሉት የፋሽስት መንግስት ነበር ብዬ የማላስበው።

የፋሽስት ጥንስስ እርሾ የሆነው የጎሳ ብሄረተኛነት መሰረቶች በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ  

- በዘመናዊ የኢትጵያ ታሪክ ውስጥ የጉሳ ብሄረተኛነት ሰንኮፍ ኢትዮጵያ ውስጥ የተተከለው በጣሊያን ወራሪዎችና በሚሲዮን ሰባኪዎች ነው። ጣሊያን ኤርትራ ውስጥ እግሩን ከተከለ በኋላ በኤርትራና በትግራይ ኃላም በሙሶልኒ ወረራ ጊዜ በመላዋ ኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት የጎሳን ፓለቲካ ተክል ተክሎ ነበር። የእንግሊዝም ቅኝ ገዢዎች ጣሊያን ከኢትዮጵያ ወጥቶ ኤርትራን ለአስር ዓመታት ያህል በሞግዚትነት በሚያስተዳድሩበት ወቅት ትግራይ ትግርኝ የሚለውን የብሄረተኝነት መርዝ በመትከል በፋሽስት ጣሊያ ወረራ ጊዜ ተጀምሮ የነበረውን የጎሳ ብሄረተኛነትን ችግር ይብልጥ በማቀጣጠሉ ሂደት ተሳትፈዋል።

- ሚሲዮኖችም በተለይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (ወለጋ ወዘተ ያደረጉት መስፋፋት) ኋላ ላይ ጎሳ-ዘለል- ጎጥ-ዘለል፤ ኃይማኖት-ዘለል ከሆነ ኢትዮጵያዊ በተጻራሪነት የቆመውን ተገንጣይነትን የሚሰብክ የኦሮሞ ብሄረተኛነት መሰረት በመጣል በኩል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል። ጊልሂርስት የሚባል አሜሪካዊ ይህንን ሚሲዮኖች የኦሮሞን ብሄረተኛነት እንዴት እንደኮተኮቱና እንዳሳደጉ ሲገልጽ “One such consequence was the evolution & entrenchment of the Oromo sense of identity”ብሎ ነበር።

- ሶስተኛው የጎሳ ብሄረተኛነት መርዝ የተሰራጨበት መንገድ ደግሞ ዘመናዊ ትምህርት ያስተዋወቀው ጥራዝ ነጠቅ የግራ ፓለቲካ ነው። በተለይ ይህ ሶስተኛው ዘዴ የኢትዮጵያን ወጣት ዓይን በመጋረድና የዛሬውን አደጋ ቀደም ብሎ እንዳያይ በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጾዖ አድርጎአል። እነዚህን ከዘመናዊነት ጋር የመጡትን አደጋዎች ቀደም ብሎ ያዩት ከዘመናዊ ትምህርት ቤት የወጡት የኢትዮጵያ ምሁራን ሳይሆን ከባህላዊ የኢትዮጵያ የትምህርት ተቋም የወጡ መምህር አስረስ የኔሰው የሚባሉ ታላቅ ምሁር ሲሆኑ የእኚህ ሰው ስራዎች ቀርቶ ስማቸው በበርካታ ኢትዮጵያዊ ዘንድ አይታወቅም።    

የኢትዮጵያ ዐብዮት፤ 1967 .   የመሬት ይዞታ አዋጅና በትግራይ  ህዝብ  ህይወት ላይ ያስከተለው አሉታዊ  ውጤቶችና የትግራይን ብሄረተኛነት በማቀጣጠል ያደረጉት አስተዋጽዖች የሲአይኤ አባል ፓል ሄንዘ ለመለስ ዜናዊ ያቀረበለት ጥያቄ፡

 ክዚያ በፊት ግን ይህንን መንደርደርያ ማጤን አሰፈላጊ ነው።

አብዮታዊ ትርምስና የአክራሪ ብሄረተኛነት አነሳስ በትግራይ በኢትዮጵያ ፋሽዝም መቼና በምን ሁኔታ ተጸነሰ?

አብዮትን የመሰለ ስር-ነቀል የሆነ ሁኔታ ተከስቶ ይኖሩበት ነባር የሆነውን ማህበረሰብ ህይወት እንዳልነበር አድርጎ ሲለውጥና አብዮቱ በተራው ፓለቲካዊ ምስቅልቅል፤ ማህበራዊ ጉስቁልንናና የኢኮኖሚ ችግሮች ወዘተ እንዲከሰቱ ሲያደርግ የ-አንድ ማህበረሰብ አባሎች እለታዊ ህይወት ትርጉም የለሽ ይሆናል። አንድ የፓለቲካ ስርዓት ስር-ነቀል በሆነ ሁኔታ (በአብዮት) ተገርስሶ ሲወገድ ባንድ ሀገር ውስጥ የነበሩ ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ይባባሳሉ። ለወትሮው ላንድ ማህበረሰብ የስነልቡናዊ እርጋታና ሰላም የሚሰጡ እሴቶች (Platt) እምነቶች ወዘተ ስር-ነቀል አብዮትና እሱን ተከትሎ በሚመጣ ያንድ ማህበረሰብ መታመስና መመሰቃቀል ምክንያት  ይዳከማሉ ወይም ይወድማሉ። ዚህ ሁኔታ ውስጥ ነባር አስተሳሰቦች፤ እምነቶችም ሆነ ርዕዮተአለሞች የሰው ልጆች በእለታዊ ህይወታቸው ለሚገጥሟቸው ችግሮች መፍትሄ መስጠት ይሳናቸዋል በእነዚህ ምክንያቶች ባንድ ህብረተሰብ የጋራ ወይም የወል ህይወት ውስጥ የስነልቡና ቀውስና ክፍተት ይፈጠራል በዚህ ዓይነት የስነልቦና ቀውስ ውስጥ የገባና ሰማይ የተደፋበትና መሄጃ ያጣ ህዝብ አዲስ ተስፋና አማራጭ ይዘን መጥተናልና ከዚህ ትርጉም-የለሽ ህይወት አወጣሃለሁ ብሎ የአክራሪ ብሄረተኛነትን እርካብ ረግጦ የሚነሳን የፋሽስት ድርጅት መከተል የሚጀምረውና ወያኔን ለመሰለ የአክራሪ ብሄረተኛነት አራማጅ ኃይል ድጋፉን የሚሰጠው። በዚህን ጊዜ ነው የቸገረው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ ይህን መሰል በችግር የተናጠና መድረሻ ያጣ ማህበረሰብ አባሎች ለችግራቸው መፍትሄ እሰጣለሁኝ ብሎ ብቅ ለሚል ፋሽዝምን ለመሰለ የአክራሪ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነ ፍልስፍና ልባቸውን የሚሰጡት::

 የወያኔ ትግሬዎች ድርጅት የኢትዮጵያን አብዮት ያስከተለውን የገጠር መሬቶችን መወረስ ተከትሎ በተፈጠረው ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መስራት ያለመቻል ምክንያት በተለይም ለወትሮው ብዙ ተዘዋዋሪ ሰራተኞች (migratory workers) መፍለቂያ የሆነውና የተፈጥሮ ሃብቱ የተመናመነው (Tigrai is an ecologically degraded area which could not support its population – see my article entitled “Ecological Degradation, Ethno-nationalism and Political Conflict in Ethiopia” which can be accessed from Welkait.com website - Ethiopiansemay.blogspot.com) የትግራይ ክፍለ-ሀገር ህዝብ የገጠመውን ከላይ የጠቀስነውን ዓይነት ህይወትን ትርጉም-የለሽ የሚያደርግ ቀውስና ይህ ቀውስ የፈጠረውን ምሬት በመጠቀም የትግራይን ህዝብ በቀላሉ መቀስቀስ ጀመረ።

እዚህ ላይ ፈረንጆቹ እንደሚሉት ከፈረሱ-አፍ መስማት ስለሚሻል መለስ ዜናዊ የተባለው የህወሃት-መሪ (ነፍሱን ይማረውና) የትግራይ ህዝብ ለወያኔ ድርጅት ከፍተኛ ድጋፉን እንዲሰጠው ያስገደደውን ምክንያት ፓል ሄንዘ ለተባለው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት አባል የሰጠውን ቃለ መጠይቅ እዚህ ለአንባቢ ግንዛቤ እንዲረዳ እጠቅሳለሁኝ።

የፓል ሄንዘ ጥያቄ ለመለስ ዜናዊ፤

ምን ያህል ትግሬዎች ከትግራይ ውጭ ባሉ የኢትዮጵያ ክፍሎች ይኖራሉ ብለህ ትገምታለህ?”

መለስ ዜናዊ ለፓል ሄንዘ የሰጠው ምላሽ፤

ምናልባት አንድ ሶስተኛው የትግራይ ህዝብ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ይኖራል። ትግሬዎች ሁልጊዜ ወደ ሌሎች  ቦታዎች እየጓደኑ በጊዜያዊ ሰራተኛነት ሲሰሩ ጥቂቶች ደግሞ እዚያው እሄዱበት ይቆዩ ነበር። ከመጀመሪያው ጀምሮ ትግሬዎችን ከደርግ ካለያየው ምክንያቶች አንዱ ይህ ነበር። የትግራይን ህዝብ ያስቆጣው 1967 . የመሬት ይዞታ አዋጅ ሳይሆን ህዝብ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መስራት እንዳይችል በደርግ የተጣለው እገዳ ነው። ትግሬዎች ወደ ብዙ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ለስራ በመሄድ አንዳንድ ጊዜ ከግማሽ ዓመት በላይ ይቆዩ ነበር። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሰርተው ያገኙትን ጥሪት ይዘው በመምጣት ቤተሰባቸውን ይደግፉበት ወይም ማሳቸው ላይ በማዋል ምርታቸውን ለማሻሻል ይጠቀሙበት ነበር። በዚህ ዓይነት ወደሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመሄድ በሚገኝ ጥሪት ከትግራይ ህዝብ  ይበልጥ ተጠቃሚ የነበረ ህዝብ በኢትዮጵያ  አልነበረም። ደርግ ደደብ ስለነበር ህዝቡን ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ እንዳይሰራ አደረገ ደርግ ይህንን በማድረጉ የትግራይን ህዝብ ድህነትና ተስፋቢስነት ውስጥ ከተተው በዚህ ምክንያት ደርግ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ለእንቅስቃሴያችን ጠቃሚ ድጋፍ ሊያሰጠን ቻለ (ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ ትርጉም የአሰፋ ነጋሽ ነው) ለዝርዝሩ “Paul Henze’s Conversation With Meles Zenawi, Washington DC, April 1990 ይመልከቱ)

- ይህ የመሬት ይዞታን አዋጅ መታወጅ ተከትሎ ከቦታ ቦታ ለመዘዋወርና ለመስራት ያለመቻል ችግር ለትግራይ አክራሪ ብሄረተኛነት አንዱ መለኮሻ ምክንያት እንጂ ብቸኛው ምክንያት እንዳልሆነ እዚህ ላይ ላሰምርበት እፈልጋለሁኝ። ሌሎች

- ታሪካዊ (በአማራ ስልጣን ተነጠቅን የሚል ከመቶ ዓመታት በላይ ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የነበረ ቁጭትና ብሶት)

 ባህላዊ ማለትም የትግራይ ማህበረሰብ ባህል መገለጫ የሆነ እጅግ ወደ ውስጥ ተመልካች (inward looking, ከራስ ጎሳ ወይም ነገድ ውጭ ላለ ህዝብ ጥቅምና ደህንነት አለመጨነቅ፤ ራስ-ወዳድነት ያጠቃው፤ ጎሰኛነትና መንደረኛነት የተጠናወተው ይሉኝታን የማያውቅ ባህል)

አካባቢያዊ (በአካባቢያችን ያሉ ኢትዮጵያን በበጎ የማይመለከቱ ሱዳንን፤ ግብጽን፤ ሶማሊያንና የነዳጅ ባለቤቶች የነበሩ የአረብ ሀገራት ድጋፍ)

- አለምአቀፋዊ (በተለይ ከኢትዮጵያ አብዮት በኋላ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ ተደርጎ ኢትዮጵያ የቀዝቃዛው ጦርነት መፏከቻ ሀገር በመሆን ወያኔና ሻቢያ በረሃብ እርዳታ ስም ከምእራብ መንግስታት ሰፊ የገንዘብና የዲፕሎማቲክ ድጋፍ ማግኘት)

የኢትዮጵያን አብዮት ተከትሎ የተፈጠረውና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከዚህ ቀደም ባልታወቀ መልክ ሰፊውን ህዝብ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሰገባ ሁኔታ) በትግራይ  ውስጥ ለአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ስሜት ለሚመራና ኋላ ላይ በሂደት ወደ ፋሽስታዊነት ላመራ ድርጅት መጠናከርና ለፋሽስት ስርዓት መፈጠር ምክንያት ሆነ ብዬ እሞግታለሁኝ 

የትግራይ ማህበረሰብ ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት አክራሪ ብሄረተኛነት በፈጠረው አዲስ አስተሳሰብ ምክንያት አመለካከቱ በአዲሱ የትግራይን አክራሪ ብሄረተኛነት መገለጫ በሆነው የፋሽስት ፍልስፍና በመቀረጹ ኢትዮጵያዊነት የምንለውን የጋራ ማንነት ተጻራሪ የሆነና የአንድን አናሳ (minority) የትግራይ ህዝብ ማንነት በአምልኮ ደረጃ እንደጣዖት የሚያመልክ በአንድ ወጥ አስተሳሰብና ሃሳብ የሚመራ የፋሽስት ስርዓት ተሸካሚና አራማጅ ሆኖአል ብዬ እሞግታለሁኝ።

ሶስቱ የአክራሪ ብሄረተኛነት ማጠንጠኛዎች

አክራሪ ብሄረተኞች አንድን የቸገረው ህዝብ የሚከተሉትን ሶስት ነገሮች በመንተራስ የብሄረተኛ ዓላማቸው ተከታይ  በማድረግ አንድን ህዝብ እንደ መንጋ ባንድ ሃሳብና ባንድ መሪ ድርጅት ስር በማሰለፍ ይጋልባል

- በአፈ-ታሪክና በአብዛኛው በውሸት ላይ የተመሰረተ አዲስ ታሪክ በመፍጠር አንድ ህዝብ እጅግ ደማቅ የሆነ በእጅጉ ገናና የሆነ ታሪክ ባለቤት እንደነበረ ይተርኩለታል።

- ይህ ትላንት በታሪክ የደማቅና ገናና ታሪክ ባለቤት የነበረ ህዝብ በዛሬው ዘመን እየተፈጸመበት ያለውን በደል፤ ወርድትና ብሶት ያስተጋቡለታል።  

- ይህ ትላንት ደማቅና ገናና ታሪክ የነበረው ዛሬ ደግሞ የውርደት፤ የበደል ሰለባ የሆነ ህዝብ ራሱን እነዚህን አዲስ የነጻነትና የአክራሪ ብሄረተኛነት ዜማ የሚያዜሙ መሪዎችን ቢከተል ሊያገኝ የሚችለውን ሲሳይ ይተርኩለታል። ከዚህም በላይ ብሄረተኞች ወገናችን ነው የሚሉትን አንድ ምርጥ ህዝብ አንተ የእኛን መሪነት ተቀብለህ በስራችን ታቅፈህ ከታገልክ ምድራዊ ገነት እናወርስሃለን፤ ከችግርና ከጉስቁልና እናወጣሃለን ብለው የተስፋ መና በማስጨበጥ አንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ነገድ በአዲስ ተስፋ ለትግል ያነሳሱታል።  እነዚህ ሶስት ነገሮች የብሄረተኝነት ማጠንጠኛ ድርና ማጎች ናቸው።

እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ሶስት ነገሮች የፋሽዝም መሰረት የሆነው የአክራሪ ብሄረተኛነት ማጠንጠኛ ድርና ማጎች ሆነው የሚያገለግሉ ዋና ዋና መሳሪያዎች ናቸው የትግራይ ብሄረተኞችም እንደ ማናቸውም አክራሪ ብሄረተኞች ለትግራይ ህዝብ ትላንት እጅግ ደማቅ የነበረ የአክሱማዊ ስልጣኔ ፈጣሪና ባለቤት ነበርክ፤ አንተ ጀግናው የትግራይ ህዝብ ከምንሊክ ጀምሮ ስልጣን ላይ በወጡ የአማራ ተወላጆች ተዋረድክ፤ ተበደልክ፤ መሳለቂያና መዘባበቻ ሆንክ አሁን እኛን ብትከተለን ከዚህ ውርደት፤ መከራና ጉስቁልና እናወጣሃለን፤ አዲሲቷን ትግራይን ገንብተን የትግራይን ህዝብ የበላይነት በማምጣት የትግራይን ህዝብ የቀድሞ ክብሩና ግርማ ሞገሱን እናስመልስለታለን ትግራይን የልማት፤ የእድገት፤ የእውቀት፤ የጥበብ፤ የደስታ፤የሀሴት ምድር፤ ዜጎቿንም እጅግ ኩሩና በሌሎች ህዝቦች የሚፈሩ፤ የሚከበሩና የሚደገደግላቸው እናደርጋለን ብለው ተነሱ። እንደዚህም ብለው የትግራይ ህዝብ በጨቋኙ የአማራ ህዝብ ላይ እንዲነሳ ቀሰቀሱ። ተከስተ የሚባል የወያኔ ካድሬ አይሬ በሚባለው ቦታ (በአጋሜ አውራጃ ውስጥ) በአንድ ቤተከርስቲያን ውስጥ ለተሰበሰቡ የትግራይ ተወላጆች  1968 . ያደረገው ንግግር ይህንን የብሄረተኞችን የቅሰቅሳ ዘዴ ግልጥ አድርጎ ያሳየናል።

ትግራውታይ ገናና ታሪክህን ተቀማህ የአክሱምን ሥልጣኔ የኛ ነው ብለው የሸዋ መኳንንት አረከሱብህ። በማንነትህ እንድታፍር አደረጉህ፤ አንተ ከመሪዎችህ ጋር ሆነህ የውጭ ወራሪዎችን  ስትመክት ውድ ልጆችህ በየጦር ሜዳው ሲሞቱ ምንሊክ ከባዕድ ኃይሎች ጋር በማበር በጦርነት በዛለው ገላህ ላይ የሸዋን የበላይነት መሰረተብህ  (የዚህ ጥቅስ ምንጭ ያሬድ ጥበቡ የሚባለው የወያኔ አገልጋይ የነበረ የቀድሞው EPDM ካድሬ ቃለ መጠይቅ ያደረገበት የአድማስ መጽሄት ነው)። 

 ሌላው ቀርቶ የጣሊያንን ቅኝ ገዢዎች አሳፍሮ ለመመለስ ከመላው ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሶ ኢትዮጵያን በታሪክ መዝገብ ላይ ከፍ ብላ እንደ ፈርጥ እንድትታይ ያደረጋትን የአድዋን ጦርነት ዘመቻ ምንሊክ የአማራ ወታደሮችን አምጥቶ ትግራይን ለሁለት እንድትከፈል ያደረገበትና ትግራይን ያዳከመበትና ያደኸየበት የተንኮል ስራ ነው ብለው ተከታታይ የትግራይ ብሄረተኞች የትግራይን ህዝብ ቀሰቀሱ

ዐጼ ምንሊክ ትግሬ ከጠገበና አንድ ከሆነ አይገዛም የሚል ፍልስፍና እንደነበራቸው አያቶቻችን ይናገራሉ። ለዚህም ነው የትግራይን ህዝብ ዳግም በማያንሰራራበት ደረጃ ለመምታት እልፍ አእላፋት ሰራዊት አስከትለው የዘመቱት መምህር ገብረኪዳን ደስታ (የትግራይ ህዝብና የትምክህተኞች ሴራገጽ 93 ላይ ይመልከቱ)

የወያኔ ድርጅት እ አ አ በ1983  ዓ.ም  ባወጣው የፓለቲካ ፕሮግራም  ውስጥ፤  

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሆን ተብሎ ካለ ስንቅ የተላኩ የምንሊክ ጦር ወታደሮች የትግራይን መንደሮች ዘረፉት። ባጭር ጊዜ ውስጥ የትግራይ ህዝብ የኢኮኖሚና የማሀበራዊ ሁኔታ በፍጥነት አሽቆለቆለ። ከዚህ በተጨማሪ ሆን ብሎ የትግራይን ህዝብ ቋንቋ ባህልና ታሪክ ለመጫን እርምጃዎች ተወሰዱ። እነዚህ  የጭቆና እርምጃዎች የትግሬዎችን ብሄረተኛ ስሜት በመቀስቀስ ኃይለኛ የሆነ ብሄራዊ  ቅራኔን ፈጠሩ። ይህም ሁሉ እንኩዋን ሆኖ ግን የትግራይ ህዝብ በራሱ ብቻቸውን ሆኖ  ድንበር ጥሶ የመጣውን ጣሊያንን መልሷል። ኋላም ስመ-ጥር በሆነው የአድዋ ጦርነትም  ላይ ጣሊያንን በማሸነፍ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል (ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም፤ አሰፋ ነጋሽ)

ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ተቃዋሚ ነኝ ብሎ እንደ እስስት ቀለሙን እየለዋወጠ አንዴ Multi-Ethnic Coalition ባለፉት ዓመታት ደግሞ Tigrean Alliance for National Democracy (TAND) የሚል የውሸትና ተከታዮች የሌለው ተቃዋሚ ድርጅት ነኝ የሚል ማታለያ ይዞ ቀደም ሲል ኢተፓድህ በሚባል ከንቱ የሆነ የስደት ድርጅት፤ ቀጥሎ ደግሞ ህብረት በሚባል በአብዛኛው የጎሳ ፌዴራሊዝም  ፓለቲካ አራማጆች የተቋቋመ ድርጅት፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞሸንጎየሚባል በዚህ በስደት ሆኖ የኢትዮጵያን ትግል አስተባብራለሁ የሚል ከንቱ የስደት ድርጅት አባል በመሆን የሚያጭበረብረውና በሆላንድ ውስጥ አንዳች ስራ ላይ ሳይሰማራ ባለፉት ሃያ ዘጠኝ አመታት በሆላንድ ታክስ ከፋዮች (welfare) ድጎማ (ሳይሰራ በመንግስት ቀለብ እየተሰፈረለት) ህይወቱን የሚመራው የቀድሞው የወያኔ መሪና የጦር አዛዥ አረጋዊ በርሄ ደግሞ የዐጼ ምንሊክ ጦር በአድዋ ጦርነት አሳቦ በትግራይ ህዝብ ላይ አደረሰ የሚለውን ጥፋት በሚከተለው መንገድ ይገልጽልናል። 

የምንሊክ ጦር የጣሊያን የቅኝ ገዢዎች ጦር ያደረሰውን ያህል ጥፋት እንዲያደርስ በትግራይ ላይ መረን ተለቀቀ። የትግራይ ህዝብ ይህንን ጊዜ ዘመነ ሸዋ ብሎ ያስታውሰዋል፤ ይህም ማለት ትግራይ በሸዋ አገዛዝ ሥር  የወደቀብት ዘመን ማለት ነው በርካታ የትግራይ ምሁራን ምንሊክ ትግራውያንን እንደራሱ ህዝብ የማያይ መሪ አድርገው ይቆጥሩታል። የምንሊክ ሰሜኑን የመከፋፈልና የማዳከም ሃሳብ የትግራይን ግማሽ ጣሊያን በቅኝ ግዛትነት ይገዛው ዘንድ በመስጠት ሂደት የታጀበ ነበር። ምንሊክ ትግራይ አንዴ ለሁለት ከተከፈለች እሷን እንደፈለጉ መግዛት ይቻላል ብሎ ያምን ነበር (ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም፤ አሰፋ ነጋሽ)

የትግራውያን  ቁጭት የተሞላበት ትውስታ  የትግራይ አክራሪ ብሄረተኛነት እርሾዎች ስለመሆናቸው

ትውስታ ዛሬ ላይ ሆነን ስላለፈው የህይወት ዘመናችን የምንቀርጸው ስዕል ወይም ምስል ሲሆን ስሜታዊነት የሚያጠቃው፤ ተጨባጭነት የሌለውና -አመክንዮታዊ (irrational) ሊሆን የሚችል ነው አንድ ሰው ያልተደረገውን ተደረገ ብሎ ማስታወስ ይችላል፤ በተቃራኒው የተደረገውን አልተደረገም ብሎ ሆን ብሎ ከትውስታው መዝገቡ ሊያወጣው ይችላል። ከትውስታ በተቃራኒ የቆመው ታሪክ (history) ደግሞ ባብዛኛው ስላለፈው ጊዜ ወይም ያለፈ ዘመን ሲዘግብ በተጨባጭና የዓይን ምስክርነትን ጭምር ባካተቱ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ፤ ከተለያዩ ወገኖች የተሰበሰቡ መረጃዎችን አገናዝቦ ያለፈውን ዘመን ድርጊቶች ይዘግባል:: Megill  የተባለ የታሪክ ጸሃፊ ብሄረተኞች እንደሚያደርጉት "የግለሰብም ሆነ የወል ትውስታ የአዲስ ማንነት መቅረጫ ሆኖ ሲውል ለታሪክ ፈተና ይሆናል ይለናል። በመቀጠልም ታሪክ ለሚዘግባቸው ነገሮች አብዛኛውን ጊዜ ማስረጃን ያስቀምጣል፤ በተቃራኒው ትውስታ ከስሜታዊ ትርጉም በዘለለ እንደ ታሪክ ማመሳከሪያ የሚሆኑ ማስረጃዎችን አያቀርብም" ብሎ ይሞግታል።

ትግሬ በዳግማዊ ምንሊክ ጊዜ ፈጽሞ ጠፍቶአል። የትም የትም ብትሄድ በዚያች ሀገር የለማ መንደር አታገኝም። ሰው ከሚኖርባችው ጎጆዎችዋ ይልቅ የድሮ ልማትዋን የሚመሰክሩ ፍርስራሽዎቿ ይበዛሉ። የትግሬም ጎበዝ በዛሬ ዘመን ባባቱ ሀገር አይገኝም፤ አውራ እንደሌለው ንብ አድራሻው ሳይታወቅ ወደ አራቱ የዓለም ማእዘኖች ተዘርቷል እንጂ። ባገሩም ላይ ድህነት ሰፍታለች የሌሎች ወገኞች መተረቢያ እስቲሆን ድረስ። ሁሉም መሬ በሰላም ሲኖር ምስኪኒቱ ትግሬ ገን ሽፍታና ወንበዴ አልተለያትም። ባላባቶቹም ዘወትር እርስ በርሳቸው ሲዋጉ ይኖራሉ  የአድዋው ተወላጅ ነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ ዐጼ ምንሊክና ኢትዮጵያ  በሚል ርዕስ የጻፏትን ጽሁፋችውን ተመልከት

እስቲ አሁን ደግሞ በህይወት የሌለውና (ነፍሱን ይማረው) ትግራይ ተወልዶ ጎንደር ውስጥ ያደገውና የተማረው ክንፈ አብርሃም የሚባል የትግራይ ብሄረተኛንምሁርንቁጭት ላስነብባችሁ።

እንደ እውነቱ ከሆነ የትግራይ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወይም ትግል ቀስ በቀስ የሰውና የቁስ-አካላዊ ክህሎቷ ወይም ሃብቷ ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት መጠበቅ ሲባል እየጠፋ የሄደችው ትግራይ ውጤት ነው። ትግራይ ለአካባቢዋ ብርሃን እየሰጠች ራሷ የምትከስመውን ሻማ ትመስላለች። በተለይም ትግሬዎች -ፍትሃዊ የሆነውን ታሪካዊ ሂደት ማለትም የኢትዮጵያ የበላይ ገዢነት ከዐጼ ዩሃንስ ወደ ዳግማዊ ምንሊክ የተላለፈበትንና በዚሁም ምክንያት ትግራይ ከኢትዮጵያ ማእከልነት ወደ አንድ ተራ ክፍለ ሀገር መሸጋገሯ ትግሬዎችን በጣም አስቆጭቶአቸዋል  (ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም፤ አሰፋ ነጋሽ) የዚህ ከላይ የጠቀስኩት ጽሁፍ ጸሃፊ ሟቹ (ነፍሱን ይማረውና) / ክንፈ አብርሃም ሲሆን የጽሁፉ ምንጭ “Ethiopia from Bullets to the Ballot Box, the Bumpy Road to Democracy & the Political Economy of Transition” published by the Red Sea Press in 1993,

ምንሊክ ስልጣን ቀምቶና ትግርኛ ተናጋሪውን ለሁለት ከፍሎ እኛን አደኸየን፤አዋረደን፤ ትግራይን በደለ የሚል ከመቶ ዓመታት በላይ የቆየ ሮሮና በምድጃ ዳር ወላጆች ለልጆቻቸው ሲግቱዋቸው የነበሩት ተረቶች ኤርትራውያንም በተወሰነ ደረጃ የሚጋሩት ነው ምንሊክና ተከታዮቹ የሆኑት የኃይለስላሴና የደርግ መንግስታት ትግሬዎችን ካላስራብን ልንገዛቸው አንችልም ብለው ትግሬን አስርበውታል፤ እስቲ የወያኔ ድርጅት የቀድሞ መሪና የጦር አዛዥ አረጋዊ በርሄ (ዛሬ በተቃዋሚነት ስም የሚያጭበረብር  አክራሪ የትግሬ ብሄረተኛ) ደግሞ ስለትግሬዎች ብሶትና ጭቆና ምን እንደሚለን ከዚህ ቀጥሎ ከጻፈው ጽሁፉ እንመልከት፤

የኑሮ ሁኔታዎች እዚያ የተሻሉ ስለነበረ ትግሬዎች ስራ ለመፈለግ ብለው የቀድሞዋ የጣሊያን ቅኝ ግዛት ወደነበረችው ኤርትራ፤ ወደ አዲስ አበባና ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች ይጓድኑ ነበር። ነገር ግን ትግሬዎች ወደ  እነዚህ አካቢቢዎች ያደረጉት መጓደን ክብራቸውን የሚነካ አዋራጅ ስም አሰጣቸው። ትግሬዎች በስፋት ተንቀሳቅሰው በመላ ሀገሪቱ ውስጥ በመገኘታቸው በሽሙጥ መልክ ትግሬና የላንድ ሮቨር ጂፕ የማይገባበት ቦታ የለም እየተባለ ተቀለደባቸው። ትግራይ ከእህል ይልቅ ድንጋይ እንዲያበቅል ተረግሟል ተብሎም ተነገረ። ተከታታይ የትግራይ ትውልዶች በጣም ከሚያሳዝን ተስፋ አስቆራጭ ስሜት ጋር ይኖሩ ነበር  (ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም፤ አሰፋ ነጋሽ) የዚህ ጥቅስ ምንጭ፡ (For details see “The Origins of the Tigray People’s Liberation Front”, African Affairs journal (2004), Volume 103, No. 413, page 573) 

ወለጋ ውስጥ የቀን ሰራተኛ ወይም ኩሊ ለመጥራት የወለጋው ኦሮሞ የሚጠቀምበት ቃልጎጄ ጎጄ እያለ ነው ኩሊ የሚጠራው። በዚህ ጎጃሜዎች ተዋረድን ብለው እንደ ትግራውያን ኢትዮጵያን ለመበተንና ለማጥፋት ብረት አላነሱም

ከገብረህይወት ባይከዳኝ ጀምሮ የተነሱ የትግራይ ልሂቃን ትግራይ ፈራርሳ ወደቀች፤ አክሱም የራሷን ተወላጅ (ትግሬን) ሳታነግስ ቀረች የሚል ቁጭት ከዐጼ ዮሃንስ ሞት ጀምሮ ያነቀንቁ ነበር። ይህ ውስጥ ለውስጥ ሲንተከተክ የነበረው የትግሬ ልሂቃን ቁጭትና በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የተደበቀ ጥላቻ በተለያዩ የታሪክ ወቅቶች ውስጥ በተለያዩ ሽፋኖች ስር ሲገፋ ቆይቷል። ባለፉት ስድሳ ዓመታት የትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች ይህንን በውስጣቸው ሲንቀለቀል የነበረውን የአማራ ጥላቻ በተራማጅና ግራ-ቀመስ የፓለቲካ ካባ ስር በተማሪውና በግራው ትውልድ እንቅስቃሴ ውስጥ በስፋት ይገፉ ነበር ያኔ ግን ይህንን የተደበቀ ዓላማቸው ዛሬ ግልጽ እንደሆነልን በዚያን ጊዜ አልተገለጸልንም ነበር። ወያኔና ሻቢያ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ተራማጅ ነበርን ብለው የዓለማቀፋዊነትን መፈክር አብረውን ሲያሰሙ የነበሩት ትግሬዎችም ሆኑ ኤርትራውያን በንጉሱም ሆነ በደርግ ጊዜ የታገሉት እጅግ አምርረው የሚጠሉትን አማራንና በአማራ የመሰሏቸውን ሁሉቱን የቀደሙትን መንግስታዊ ስርዓቶች እንደነበረ ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ያሳዩን ድርጊቶቻቸው በግልጽ አሳውቀውናል።   

ይህ ከመቶ ዓመታት በላይ ውስጥ ውስጡን ሲግም የነበረ የጥላቻ ማንነት እስከ የዙፋናዊ ስርዓት መውደቅ ድረስ ውስጥ ውስጡን ከዙፋናዊው ስርዓት ጋር በአምቻና በጋብቻ ቁርኝት ባለው የትግሬ የገዢ ቡድን ጭምር በምድጃ ዳር ለትግራይ ልጆች በሚነገርአማራ የዮሃንስን ዘውድ ነጥቆ ትግራውያንን ለድህነትና ለውርደት ዳረገበሚል ትረካ መልክ ሲገፋ ቆየ ከኢትዮጵያ አብዮት በፊት እነ አበበ ተሰማ የተደራጀ የባህል ቡድን የትግራይን ባህል መጠበቅ በሚል ሽፋን በትግራይ አስተዳዳሪ በራስ መንገሻ ስዩም እውቅናና ድጋፍ በገጠረይቷ ትግራይ በየ አወራጃውና እሰከ ኤርትራና አዲሰ አበባ ድረስ  ሰፊ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር 

በከኢትዮጵያ አብዮት ጀምሮ ደግሞ የትግራይ ብሄረተኛነት ከዘመናዊ የትምህርት ማእከላት በወጡ የትግራይ ልሂቃን  ቡድን አማካይነት ቅርጽና ህይወት አግኝቶ የየካቲት 1966 . ዓብዮት በፈጠረው ምቹ ሁኔታና ግርግር ውስጥ 1967 . የፓለቲካ ኃይል ሆኖ ብቅ አለ በንጉሱና በደርግ ዘመን በተማሪውና በግራው እንቅስቃሴ ውስጥ የተራማጅነት ካባ ደርበው የአማራውን ህዝብ አንዴ ገዢ መደብ፤ አንዴ ትምክህተኛ፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ጨቋኝ ብሄር እያሉ ሲወነጅሉ የነበሩት የትግራይ ተራማጆች (ተማርኩ የሚለውም የአማራው ተወላጅ ባብዛኛው ይህንን አመለካከት ያስተጋባ ነበር) የተራማጅነት ጭምብላቸውን ጥለው የትግራይ ብሄረተኛነት ዋና አራጋቢዎች ሆነው ካለአንዳች እፍረት ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ወደፊት ብቅ አሉ 

ስንቶች የዛሬው የወያኔ አንዱ መሪ አባይ ጸሃዬ (አመሃ) 1966.. የኃይለስላሴ ዩኑቨርሲቲ የተማሪዎች ማህበር መጽሄት የእንግሊዘኛው ክፍል አዘጋጅ እንደነበረ ያውቁ ይሆን? አባይ ጸሃዬ በዚያን ጊዜ በማርክሲዝም-ሌኒንዝም ሲምልና ሲገዘት በርካታው የአማራ ልጅ አብሮት ይል ነበር የአማራው ህዝብ በጅምላ የንጉሱና የደርግ መንግስታት ደጋፊና በእነዚህም መንግስታት ዋና ተጠቃሚ ተብሎ የጥቃት ፕሮፓጋንዳ ሲሆን፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎች ሲሰደዱ፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሲገደሉና ሲጠፉ የቀድሞው ዘመን የትግራይ ተራማጆች ከወያኔ ጋር ሆነው የአማራውን ህዝብ ፍጅት ፕሮግራም ነድፈው ሲተገብሩ አይተናል የአማራውን ህዝብ ማንነት ጥላሸት ለመቀባትና ይህንን  አማራውን  የጅምላ መሳደድና ፍጅት ሲደግፉ አይተናል እነዚህ የቀድሞ የትግራይ ተራማጆች ስለ አማራው ህዝብ የጅምላ ፍጅት ድምጻቸውን የሚያሰሙትን ጥቂት ግለሰቦች አክራሪነትና በጸረ-ትግሬነት ይወነጅሉ ነበር እነሆ ዛሬ ትግራይ ፋሽዝም እውነተኛ ገጽታው ወጥቶ አማራው በስፋት በሚኖርባቸው በጎንደርና በጎጃም በወገኖቻችን ላይ በአስቸኳይ አዋጅ ስም የጅምላ ፍጅት እያደረገ  ነው ህጻናት፤ አሮጊቶች፤ ሽማግሌዎች በቤታቸው በገፍ እየተገደሉ ነው። ወጣቶች እንደ አውሬ እየታደኑ ነው። በብር ሸለቆ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ፤ የአገው ተወላጆች ፍዳቸውን እያዩ ነው። የኦሮሚያ ክልል በሚባለውም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ፍዳቸውን እያዩ ነው።

ብሄረተኞች በተፈበረከ ትውስታ ላይ ተመስርተው የተጨቋኝነትና የሰለባነት ማንነት ይፈጠጥራሉ

የጎሳ ብሄረተኞች ያለፉትን ዘመናት ድርጊቶች ሲጽፉና ሲያስታወሱ  ተፈጽመዋል የሚሏቸውን ነገሮች ሆን ብለው በማዛባት ለዛሬው ዘመን ፓለቲካቸው በሚስማማና በሚጣጣም መልክ በመተርጎም ወይም በማጣጣም ነው። የጎሳ ብሄረተኞች ያልተደረገውን ተደረገ ብለው አዲስ የተጨቋኝነት ማንነት ለህዝባቸው ይፈጥራሉ። የወያኔ ትግሬዎችምንሊከ አድዋ ረሃብ ያጠቃቸውን የአማራ ወታደሮች አምጥቶ ትግራይን ዘረፈ፤ አደኸየእያሉ  ያልተደረገውን እንደ ተደረገ አድርጎ የሚያቀርብ ትውስታ (socially constructed memory) በመፍጠር ለትላንትናውና ለዛሬው የትግራይ ትውልድ በአማራ የተጨቆንክ ነህ በማለት የጭቆና ሰለባነት ማንነት (identity of victimhood) አወረሱት።

በዚያ ቀን የሸዋ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ ዘረፈው፤ በአካባቢው የነበሩ መንደሮችም በሙሉ ተዘረፉ። እንደርታም እንዳልነበረች ሆነች። በየመንገዱ ትልቅ ትንሽ ህፃን ሳይሉ ሰለቡት። ቀጥሎም የምንሊክ ሰራዊት እንደርታን አወደማት። እንዳልነበረች ሆነች። ብቻ የወንድ ልጅ ይሁን እንጂ የተገኘ ሰው ሁሉ ይገደላል። የእንደርታ ሰዎችም ቢሆኑ ዝም ብለው አልታረዱም። በየቋጥኙና በየጫካው እየተደበቁ የምንሊክን ሰራዊት ሲፋለሙት ነበር። የምንሊክ ሰራዊት የመግደልና የመስለብ ሱስ ያለበት ነው። ሰዎችን በገደለና በሰለበ ቁጥር ይፎክራል። ሌላው ይቅርና በመላ ኢትዮጵያ የተከበረውን የአብርሃ ወአጽብሃ ገዳምም እንዳለ ዘርፈውታል (ጥቅሱን ያገኘሁት ገብረኪዳን ደስታ የተባለው አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛ በቅንጅት ምርጫ ማግስት 1998 .. ከጻፈውየትግራይ ህዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትላንት እሰከ ዛሬከሚለው መጽሃፉ ነው።የደብተራ ፍስሃ ጊዮርጊስታሪክ ኢትዮጵያበሚል ርዕስ በትግርኛ ቋንቋ ከታተመው መጽሃፍ ከተወሰደው ጥቅስ ያስረዳናል። ደብተራ ፍስሃ በጣሊያን አገልጋይነቱ ጣሊያን ሀገር ድረስ ተወስዶ የነበረ የትግራይ ተወላጅ ነበር።

1881 .. ትግራይ እንደገና በሸዋ አማራ ገዢዎች አፈናና ጭቆና ስር ወደቀች። ከባድ ታክስ በትግራይ ህዝብ ላይ ተጣለ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሆን ተብሎ ካለ ስንቅ የተላኩ የምንሊክ ጦር ወታደሮች የትግራይን መንደሮች ዘረፉት። ባጭር ጊዜ ውስጥ  የትግራይ ህዝብ የኢኮኖሚና የማሀበራዊ ሁኔታ በፍጥነት አሽቆለቆለ። ከዚህ በተጨማሪ ሆን ብሎ የትግራይን ህዝብ ቋንቋ ባህልና ታሪክ ለመጫን እርምጃዎች ተወሰዱ። እነዚህ  የጭቆና እርምጃዎች የትግሬዎችን ብሄረተኛ ስሜት በመቀስቀስ ኃይለኛ የሆነ ብሄራዊ  ቅራኔን ፈጠሩ። ይህም ሁሉ እንኩዋን ሆኖ ግን የትግራይ ህዝብ በራሱ ብቻቸውን ሆኖ  ድንበር ጥሶ የመጣውን ጣሊያንን መልሷል። ኋላም ስመ-ጥር በሆነው የአድዋ ጦርነትም  ላይ ጣሊያንን በማሸነፍ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ---›ምንጭ፤ የወያኔ ሃርነት ፕሮግራም (TPLF program adopted at the 2nd Congress of TPLF in May 1983) (ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም፤ አሰፋ ነጋሽ)

አረጋዊ በርሄ የወያኔ ተቃዋሚ ነኝ ካለ በኋላ እንኳን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 1993 .. ከጻፈው የማስተርስ ጽሁፉ ላይ የሚከተለውን ጽፎ ትቷል፤

የምንሊክ ጦር የጣሊያን የቅኝ ገዢዎች ጦር ያደረሰውን ያህል ጥፋት እንዲያደርስ በትግራይ ላይ መረን ተለቀቀ። የትግራይ ህዝብ ይህንን ጊዜ ዘመነ ሸዋ ብሎ ያስታወሰዋል፤ ይህም ማለት ትግራይ በሸዋ አገዛዝ ሥር  የወደቀብት ዘመን ማለት ነው በርካታ የትግራይ ምሁራን ምንሊክ ትግራውያንን እንደራሱ ህዝብ የማያይ መሪ አድርገው ይቆጥሩታል። የምንሊክ ሰሜኑን የመከፋፈልና የማዳከም ሃሳብ የትግራይን ግማሽ ጣሊያን በቅኝ ግዛትነት ይገዛው ዘንድ በመስጠት ሂደት የታጀበ ነበር። ምንሊክ ትግራይ አንዴ ለሁለት ከተከፈለች እሷን እንደፈለጉ መግዛት ይቻላል ብሎ ያምን ነበር። የማይካደው ሃቅ ግን ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ለሁለት ጌቶች ማለትም ከመረብ በላይ ያለው ህዝብ ለጣሊያን፤ ከመረብ በታች ያለው ህዝብ ደግሞ ለምንሊክ ተከፍሎ ተሰጠ። ይህ ለወትሮው አንድ ወጥ በነበሩትና አንድ ላይ ቢሆኑ (የምንሊክን) ሥልጣን ለመቀናቀን በሚችሉት ትግሬዎች መካከል የተፈጠረው ከፋፋይ መስመር (fault line) መነሻ ወይም ምንጭ ነው። በዚህም ምክንያት ነው የሸዋ አማራ የገዢ መደብ ትግሬዎችን የማዳከም ዘመቻ በዚህ ታሪካዊ ወቅት የተጀመረው  ። አረጋዊ በርሄ እ አ አ በ1993 ዓ.ም ለማስተርስ ዲግሪ ከጻፈው ጽሁፍ የተወሰደ  (ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም፤ አሰፋ ነጋሽ )።

የቀድሞው የወያኔ መሪ ድርጅት አርጋዊ በርሄ 1984 .. በጻፈው የወያኔን የፕሮፓጋንዳ ዘዴዎች የተመለከተ ጽሁፉ ውስጥ እሱም ሆነ እሱ የፈጠረውና የመራው የወያኔ ድርጅትና ተከታዮቹ እንዴት ብለው በጠላትነት በሚያዩት የአማራ ህዝብ ላይ ቅስቀሳ በማድረግ የትግራይን ህዝብ ያነሳሱ እንደነበር እንደሚከተለው ያስረዳል።

 የወያኔ ሬዲዮ ጣቢያም ሆነ የወያኔ የፕሮፓጋንዳ ጽሁፎች የትግራይን ህዝብ ብሄረተኝነት ስሜት ለመቀስቀስና ለማነሳሳት ማናቸውንም የትግራይን ህዝብ ስሜትና ምኞች የሚኮረኩሩና የሚነኩ ነገሮችን በስሜታዊነት ይቀሰቅሱ ነበር።፡ይህንንም የሚያደርጉት ታሪክና ቀኖናን በመንተራስ ነበር። ትግላችን የፖለቲካ ስልጣንን ጉዳይ፤ የኢኮኖሚ ዋስትናንና ደህነነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ነበር። ይህ ነበር የትግራይ ብሄረተኛ ትግል ዓላማ። ይህም የወያኔ ሀርነት ትግራይ ዓላማ ባለፉት የአማራ መንግስታት ዘመናት እኛ ትግሬዎች ያጣናቸውን መብቶች ማስመለስ ነበር፡፤ የወያኔ ድርጅት ግጥሞች፤ ዘፈኖች ሁሉ በቅርጽና በይዘታቸው የትግራይ ህዝብ በተከታታይ የአማራ መንግስታት ዘመናት የተነጠቀውንና ያጣውን መብት እንዴት ማስመለስ እንደሚችልና እነዚህንም የተነጠቃቸውን መብቶች ለማስመለስ ምን ዓይነት መስዋእትና ዋጋ መክፈል እንዳለበት የሚያመለክቱ ነበሩ። በሌላ አነጋገር ጨቋኙን የአማራ ብሄር ለመዋጋት ህዝቡን የሚያነሳሳና የሚያንቀሳቅስ ቅስቀሳ ይደረግ ነበር። ከዚህም በቀር  ለትግራይ ህዝብ ጨቋኙ አማራ  ጠላቱ ስለሆነ የወያኔ መገናኛ ብዙሃን (ሬዲዮ፤ የጽሁፍና የቃል ፕሮፓጋንዳ ወዘተ) የትግራይን ህዝብ ታጋዮች አንድ አድርጎ በማንቀሳቀስ ጨቁኙን አማራ የማያዳግም ምት እንዲመታ አደረጉት (ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም፤ አሰፋ ነጋሽ። አረጋዊ በርሄ ( See Aregawi Berhe’s paper entitled “How the Media of the TPLF Emerged and Countered the Dominant Media of the Ethiopian State: Could It Be Viable Alternative for Societal Transformation? Paper presented as a term paper presented to the Institute of Social Studies, the Hague, the Netherlands 1992) 

አረጋዊ በርሄ ዘመነ ሸዋ የሚለው ዳግማዊ ምንሊክ ወደ አድዋ ጦር ይዘው የዘመቱት የጣሊያን ቅኝ ገዢዎችን  ለመፋለም ብቻ ሳይሆን የሸዋን አማሮች ስልጣን ሊቀናቀኑ ይችላሉ ብለው የገመቱትን ትግራይን ሁለት ቦታ በመክፈል (ትግራይና ኤርትራ) ለማዳከም ነው የሚለው አስተሳሰብ ጥቂት ትግራውያን ብቻ ሳይሆን ብቻ ሳይሆኑ በርካታ ትግራውያን ተከታዮቻቸው ከመቶ ዓመታት በላይ ውስጥ ውስጡን ሲያመነዥጉት የቆዩት ጉዳይ ነው 

የቀዝቃዛው ጦርነት ያመቻቸው ሁኔታዎች

የምዕራቡ ዓለም በሰብዓዊ እርዳታ ስም ለወያኔና ለሻቢያ የሰጠው በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ዶላር የሚገመጥ እርዳታ እንዴት የደርግን መንግስት በመጣል ለዛሬዋ በወያኔ የጎሳ ፓለቲካ ለተከፋፈለችውና ለተዳከመችው ኢትዮጵያ መሰረት እንደጣለ ለመረዳት ለሚፈልጉ አዳማጮች በራሳቸው በምዕራቡ ሀገር ተወላጆች የተጻፈውንWithout Troops and Tanks – Humanitarian Intervention in Ethiopia & Eritrea” የሚለውን Mark Duffield & Johan Prendergast መጽሃፍ እንዲያነቡ እመክራለሁኝ። 

Max van de Berg የተባለ የደች ፓለቲከኛና ሁላ ደግሞ NOVIB የተባለው ትልቅ የእርዳታ ድርጅት ኃላፊ . . . 1993 በአንድ SALTO ለተባለ በአምስተርዳም ከተማና አካባቢዋ የሚተላለፍ ቴቪእኛ እኮ የምንሰጠው እርዳታ ከሰሃራ በታች ትልቅ ጦር ነበረው የተባለለትን የኢትዮጵያዊ ወታደራዊ መንግስት ለመጣል አስችሏልበሚል ኩራት ተናግሯል።

ፋሺዝም  የአክራሪ ብሄረተኛነት የተጋነነ መገለጫ ነው።

ፋሽዝምን የሚገልጹ በርካታ መገለጫዎች ወይም ባህርይዎች ቢኖሩም ዛሬ ስል ፋሽዝም እድሜያቸውን በሙሉ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንቶች (ስኮላርስ) በዋናነት የፋሽዝም ስርዓት መገለጫ የሆኑት ሁለት መለያዎችና የፋሽዝም ገላጭ ባህርያት ብለው የተስማሙባቸው  መስፈርቶች፤

ስለ ፋሽዝም ሰፊ ጥናት ባደረገው እንግሊዛዊው የፋሽስት ጥናት ሊቅ ግሪፊን አመለካከት ባጭሩ (1) ፋሽዝም በአንድ ምርጥ ህዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ የቆመና የአንድን ምርጥ ህዝብ የበላይነት የሚሰብክ የአክራሪ ብሄረተኛነት(ultranationalism) ፍልስፍና ሲሆን (2) ዓላማውም የአንድን ምርጥ ህዝብ ዳግም ልደት (palingenesis) በማብስር አዲስ በሆኑ የሞራል እሴቶች የታነጸ አዲስ ሰው መፍጠር ነው ፋሽስቶች በእሳት ነዳ አመድ ከሆነች በኋላ  እንደገና ህይወት ዘርታ እንደተነሳችው የፊኒክስ Phoenix ወፍ እንደገና ተወልደህ ታላቅ የክብርና የዝና ባለቤት ትሆናለህ በሚል ተረትና አፈታሪክ ላይ ተመስርተው አንድን ህዝብ በስሜት ለትግል አነሳስተው አዲስ ታሪክ እንዲሰራ ይጠራሉ አስገራሚው ነገር የቀድሞው የወያኔ ታጋይ ወይዘሮ የውብማር አስፋው (ማለትም የታጋይ ገብሩ አስራት ባለቤት) “ፊኒክስዋ ሞታም  ትነሳለች” (2001 .. የታተመ) በሚል ርዕስ የጻፈችውን መጽሃፍ ይህን ስያሜ የሰጠችበትን ምክንያት በሚከተለው መንገድ ትገልጸዋለች።ፊኒክስ በተለያዩ ክፍለ ዓለማት በተለይም በግሪክና በግብጽ የሚተረትባት በድንቅ ውበቷና በመረዋ ድምጽዋ የምትታወቅ ተአምረኛ ወፍ ናት። ተረቱ እንደሚለው ፊኒክስ ከአምስት መቶ እስከ አንድ ሺህ (ከዚያም በላይ) ዓመታት ከኖረች በኋላ ድካምና እርጅና ሲጫጫናት የተለያዩ የማጥንት እንጨቶች አሰባስባ ራሷን አቃጥላ ትሞታለች ሆኖም ከተቃጠለችበት እሳት ፍምና ረመጥ ዳግም ታድሳ ተጠናክራና ወጣት ሆና ትነሳለች በመሆኑም ፊኒክስ በብዙ እምነቶች ትንሳዔ ሙታንን ህያውነትን አይበገሬነትን ጽናትን ወድቆ መነሳትንና ተስፋን የምታስረዳ ምስል ነች 

አንባቢን ለማስገንዘብ የምፈልገው የፊኒክስ ወፍ አፈታሪክ በዛሬው ዘመን ፋሽዝም የሚያቀነቀንውን አንድ ህዝብ አርጅቶ ከሞተ በኋላ በአልበገሬነቱ እንደገና እንደ አዲስ በትንሳዔ መነሳቱን የሚያበስር ስለሆነ የፋሽስት ስርዓትን የዳግም ትንሳዔ ወይም ልደት ምልክት ነው።

(3) ፋሽዝም አክራሪ-ብሄረኛነትን በሚያቀነቅንና የአንድን ምርጥ ህዝብ ማንነት የማእዘን ራስ ላይ ቆሞ በማያቋርጥ አብዮታዊና ስር-ነቀል በሆነ መንገድ አንድን ህብረተሰብ በመለወጥ አንድ-ወጥ አስተሳሰብ ያለው ህብረተሰብ ለመፍጠር የሚሞክር የፓለቲካ ርዕዮተ ዓለም ነው። ከዚህ ነባሩን አፍርሶ በአዲስ የመተካት እምነታቸው የትግራይ ፋሽስቶች የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ነባር እሴቶች፤ ነባር የሆኑ ብሄራዊ ተቋሞች፤ ባህል፤ እምነት፤ ወዘተ ስር-ነቀል በሆነ መልክ በማጥፋት ራሳቸው በፈጤሯቸው አዲስ ተቋማትና እሴቶች ተክተዋቸዋል። (እንደ አሜሪካዊው የፋሽስት ታሪክ ጸሃፊና ሊቅ ፕሮፌሰር ስታንሌ . ፓይን አመለካከት) ፋሽዝም የአክራሪ ብሄረተኛነት አንድ ገጽታ ሲሆን የአንድን ምርጥ ህዝብ ዳግም ልደት ወይም እንደገና እንደ አዲስ መወለድ የሚሰብክ፤ ስልጣን የአንድ ምርጥ ነገድ ተወላጆች የሆኑ ጥቂት መሪዎች እጅ መያዝ አለበት ብሎ የሚያምን ነው ወያኔ ነባር ሰፈሮችን በልማት ስም ሲያፈርስና ከእነዚህ ሰፈሮች መፍረስ ጋር አንድ ህዝብ ተወልዶና አድጎ ከብዶ ልጆች ያፈራበትን በጎ ትዝታ ጭምር ማጥፋቱ ህብረተሰብን በራሱ አስተሳሰብ ለመቅረጽ ያለውን ጭፍን አምባገነናዊ ፍላጎቱን ያሳያል። ዛሬ የጀግኖችን መቃብር (የታላቁን አርበኛ፤ ደራሲ፤ ታሪካዊ ተውኔት ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴን ሃውልት ሲያፈራርስ የመልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀንበሬን መቃብር አፍርሶ "አጽም አስነስቶ" ከአዲስ አበባ እንዲሰደድ ሲያደርግ የእነ ደጃዝማች አፈወርቅ ወልደ ሰማያትን (ቆራሄ ላይ የፋሽስት ጣሊያንን ጦር ሲፋለሙ ህይወታቸውን ለሀገር ነጻነት የሰጡ ታላቅ ኢትዮጵያዊ አርበኛ) ሃውልት ኦጋዴን ላይ ሲያፈርስ የታላቁን አርበኛ የልጅ ኃይለማርያም ማሞን መታሰቢያ ሆስፒታል ስም ናዝሬት ላይ ሲፍቅ ወዘተ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት እየፈጸመ ያለው ህብረተሰብን በራሱ አምሳልና አስተሳሰብ እንደገና የመቅረጽን የማህበራዊ ምንድስና (ሶሻል ኤንጄነሪንግ) ፋሽስታዊ  ድርጊት ነው

(4) - ፋሽዝም የሰዎች ህይወት የማያቋርጥ ትግል የሚካሄድበትና ኃይለኛው ወገን ደካማውን ወገን አሸንፎና አጥፍቶ የራሱን ዝርያ (የተመቻቸ ህይወት) በደካማው ኪሳራ ማስቀጠል አለበት ብሎ የሚያምን በሶሻል ዳርዊንዝም ፍልስፍና የተቃኘ አስተሳሰብን አስፋፋ ባጭሩ ፋሽስቶች በማያቋርጥ የአሸናፊና የተሸናፊ ትግል የሚያምኑና ሁሉጊዜም ዓለም የአሸናፊዎች መድረክ ነች ብለው የሚያምኑ ናቸው

የፋሽስት ፍልስፍና ብሄር ነገድ ጎሳ ወይም ህዝብ  የሚለውን ስብስብ ዋነኛ የታሪክ ኃይል አድርጎ ይወሰዳል።ፋሽዝም በሰው ልጆች መካከል ነገድን ወይም ወያኔዎች/እነ ኦነግ ብሄር/ብሄረሰብ ብለው የሚሉትን ስብስብ መሰረት ያደረገ ተፈጥሮዋዊ ልዩነት አለ ብሎ የሚያምን ፍልስፍና ነው ፋሽዝም በጎሳ ወይም ቡድን መብት ሳይሆን በአንድ ነጻ ግለሰብ ምርጫ ብቻ ላይ መሰረቱን የጣለውን የዲሞክራሲ ስርዓት በጽኑ ይቃወማል ፋሽዝም ማናቸውንም ከተለዩ ጎሳዎች የወጡ ያንድ ሀገር ዜጎች የሚጋሯቸውን ጎሳ-ዘለል (supra-ethnic) ኃይማኖት-ዘለል (supra-religious) የወል እሴቶችን (collective values) ያፈርሳል ፋሽዝም ከሰብዓዊነት በፊት ያንድ ህዝብ ወይም የጎሳ ማንነት መቅደም አለበት የሚለውን ፍልስፍና ያስፋፋል። የፋሽስት የፓለቲካ ስርዓት አንድን የራሴ ጎሳ የሚለውን ህዝብ በሌሎች ጎሳዎች ኪሳራ ልዩ ጥቅም በመስጠት ከጎኑ ያሰልፋል ከዚህም በቀር ፋሽስቶች የራሳችን የሚሉትን ያንድ ጎሳ ህዝብ አምባገነናዊ የፕሮፓጋንዳና የቁጥጥር ዘዴዎችን በመጠቀም ከሌሎች ጎሳዎች ተለይቶና ሌሎችን ጎሳዎች እየፈራና እየሸሸ እንዲኖር ያደርጉታል ወገናችን ነው የሚሉትን አንድ ጎሳ ያንድ ጠባብ የጎሳ ማንነት እስረኛ በማድረግ ከእሱ ጀርባ ይሸሸጋሉ።ፋሽስቶች የራሳችን የሚሉትን ወገን ወይም ጎሳ ህዝብ ላይ አንድ-ወጥ (homogeneous) የሆነ አስተሳሰብ ሲጭኑበት፤ በሌላ በኩል ከእነሱ ውጭ ባሉት ህዝቦች ወይም ጎሳዎችን በኃይል ከማስገደድ ጀምሮ እስከ ጅምላ ፍጅት በሚደርስ እርምጃ አማካይነትና አምባገነናዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ፍላጎታቸውን በግድ ይጭኑባቸዋል ዛሬ የትግራይ ፋሽስቶች በጎንደር፤ በጎጃም፤ በወሎ፤ በሸዋ፤ በኦጋዴን፤ በአርሲ፤ በባሌ፤ በወለጋ፤ በጎሙ ጎፋ በጋምቤላ ወዘተ እያደረጉ ያሉት ይህንን ነው።

(5) - ፋሽስቶች ፍጹማዊ (ቶታሊቴሪያን) በሆነ መንገድ የአንድን መንግስታዊ ስርዓትና የአንድን ማህበረሰብ  ሁሉንተናዊ ገጽታዎች ማለትም ፓለቲካውን፤ ኢኮኖሚውን፤ ባህሉን፤ ስነ-ጽሁፉን፤ ስነ-ጥበቡን፤ ሀይማኖታዊ ተቋማትን፤ ስነ-ምግባሩን ወይም ሞራላዊ ጉዳዮችን ወዘተ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር  አዲስ ዓይነት ማህበረሰብ አዲስ ዓይነት ዜጎች በመፍጠር ማህበረሰባዊ፤ ፓለቲካዊና፤ ባህላዊ አብዮት በማስነሳት አንድ-ወጥ የሆነ ማህበረሰብ እንደገና በዳግም ልደት ለመፍጠር ይነሳሉ 

ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት በትግራይ ስር የሰደደው አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ይህን መሰል በፋሽስት አስተሳሰብ የሰከረ አንድ-ወጥ ማህበረሰብ በትግራይ ውስጥ ፈጥሮአል ብዬ እሞግታለሁኝ ለዚሁም ቆየት ብዬ ይህንን አባባሌን የሚያረጋግጡ አስረጂና ነቃሽ ማስረጃዎችን አቀርባለሁኝ (ዛሬ የትግራይ ተወላጆች የሚያሰሟቸው ዘፈኖች፤ ፉከራዎች፤ የሚሰሯቸውና የሚያሳዩአቸው ድራማዎች፤ ፊልሞች ወዘተ ይህንን ይመሰክራሉ)

ፋሽዝምን ልዩ የሚያደርገው አክራሪ ብሄረተኛነት በሚፈጥረው ስሜት አንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ጎሳ ተቀብሬ በውርደት ኖርኩበት ከሚለው የጭለማ ህይወት በትንሳኤ ሙታንነት አስነስቶ የክብር ማማ ላይ መልሼ አስቀምጥሃለሁ የሚል ተስፋ በመስጠት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሰፊ የሆነ ብሄረተኛ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ በማስገባት የተከታዮቹን ልብ ለመማረክ መቻሉ ነው በዚህ ዓይነት በመጀመሪያ ላይ የጥቂት መሪዎች አስተሳሰብ የነበረ የፋሽስት አመለካከት አንድን ምጥር ነህ ተብሎ የሚሰበክ ህዝብ ራሱን በትንሳዔ ሙታን መንፈስ አስነስቶና ትላንት ከነበረበት አስከፊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ውስጥ አውጥቶ ከማንም ህዝብ በላይ ነኝ በሚል እብሪት የሌሎችን ድንበር እንዲገፋ፤ መብት እንዲገፍና የሌሎችን ማንነት በኃይል እንዲደፈጥጥ ያነሳሳል ከሰባት መቶ ሺህ ያላነሰ ቁጥር ያላቸውን የወያኔ ትግሬዎች የአማራውን ህዝብ ይዞታ በኃይል በመውረር አማሮች ነን ብለው የሚያምኑትን የወልቃይት የጸገዴ የጸለምት ተወላጆችን ይዞታ በመቀማት አማሮቹን በመግደል፤ በማሰር፤ በማሰደድ ለራሳቸው ጥቅም አውለውታል የወያኔ ትግሬዎች መንግስት የእነዚህን ወገኖቼ ብሎ የሚጠራችውን የትግራይ ተወላጆች ህይወት አዎንታዊ በሆነ መንገድ በመቀየር በወልቃይት አማሮች መቃብር ላይ አዲስ ህይወት እንዲመሰርቱ አድርገዋል እነዚህ በትግራይ ማንነታቸው የበላይነት የተነሳ የአማራዎች ይዞታ የነበሩ ቦታዎች የወሰዱ የትግራይ ተወላጆች ልክ ዳግም የተወለዱ ያህል የአዲስና ከዚህ ቀደም የማያውቁትን የምቾና የድሎት ህይወት ባለቤት ሆነዋል 

ፋሽዝም ብዙሃን ለጥቂት ምርጦች ታዛዥና ካለአንዳች ጥያቄ አድርጉ የሚባሉትን ትዕዛዝ ካለማወላወል ተቀብለው እንዲፈጽሙ የሚያደርግ፤ ወታደራዊ አደረጃጀት ያለው የፓለቲካ ስርዓት የሚያደራጅ፤ ኃይለኝነትን፤ ጠበኛነትና ጦረኛነትን እንደ በጎ ነገር የሚያይ ጭፍን የአምባገነን ስርዓት ነው ፋሽዝም ዲሞክራሲን፤ ሊበራሊዝምን፤ ሶሻሊዝም/ኮሚኒዝም ይጠላል። እጅግ የተማከለና በጥቂት ልሂቃን የሚመራ ሁሉን የሰው ልጆች ህይወት ዘርፎች ልቆጣጠር የሚል ጭፍን አምባገነናዊ (ቶታሊቴሪያን) የፓለቲካ ስርዓትን ይመሰርታል ፋሽዝም እጅግ ጠበኛነትንና በኃይል ማናቸውንም ነገር በግዴታ ማስፈጸምን መመሪያው ያደረገ የፓለቲካ ስርዓት ይፈጥራል

የፋሽስት ርዕዮተዓለም የሰውን ልጅ አስተሳሰብና ምኞት በጎሳ ክልል ውስጥ ያጥራል ፋሽዝም ሰዎች የጎሳ ድንበራቸውን በመዝለል ከእነሱ ጎሳ ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር ሁሉን-አቃፊ ወይም ሌሎችን የሚያካትት (inclusive values) እሴቶችን እንዳይጋሩ እንቅፋት ይሆናል። ስለ ፋሽዝም ሰፊ እውቀት በለገሰን Nolte አመለካከት ፋሽዝም የጎሳን፤ የሃይማኖትን ድንበሮች በመሻገር ሰዎች የሚፈጥሯቸውን ጥልቀት ያላቸውን ሰብዓዊ መስተጋብሮችና ሰብዓዊ እሴቶች ይቃወማል(Fascism opposes transcendence) ፋሺዝም የሰው ልጅ አይምሮና አስተሳሰብ ሰዎች የፈጠሩዋቸውን የጎሳ፤ የሃይማኖት ወዘተ ድንበሮችና አጥሮች ተሻግሮ ከእነዚህ ሰው-ሰራሽ ልዩነቶች ባሻገር ዓለምን በምሉእ ይዘቷ ከሌሎች ጋር የሚጋራባትን ሂደት ይቃወማል (Nolte). ፋሽዝም በላይ እኔ የፍጹማዊ እውነት ባለቤት ነኝ (I am the source of absolute truth) በማለት በባህል፤ በማህበራዊ ስብጥርም ሆነ ርዕዮተዓለማዊ ብዝሃነት (a society with cultural, social and ideological diversity) ባለው ማህበረሰብ ላይ ራሱን በኃይል የሚጭን እብሪተኛና ፍጹም አምባገነናዊ የፓለቲካ ስርዓት ነው።

ፋሽስቶች የአንድን ህብረተስብ ነባር እሴቶች ቀይረው አንድ-ወጥ በሆነ አስተሳሰብ የታነጸ ማህበረሰብ ለመፍጠር ይፈልጋሉ ስለዚህ አይነት የፋሽስቶች ወይም ናዚዎች ፍልስፍና “The Nazi Conscience”, በሚል ርዕስ ጥናት አድርጋ በእንግሊዘኛ መጽሃፍ የጻፈችው Claudia Conz የሚከተለውን ትለናለች።

አስፈላጊውን የእሺታ ወይም የስምምነት ደረጃ ለማምጣት መሰረታዊ የሆኑ እሴቶች መለወጥ ወይም መቀየር ነበረባቸው 

ፋሽዝም ማህበረሰባዊና የሞራል አብዮት በማስነሳት፤ አንድን እወክለዋለሁ የሚለውን ጎሳ ወይም ህዝብ አስተሳሰብና አመለካከት ስርነቀል በሆነ መንገድ ይቀይራል።ይህ  ስር ነቀል የፋሽስት አብዮት የሚያስከትለው የባህልና የእሴቶች ለውጥ ፋሽዝም ንደ አዲስ በሚፈጥረው ስርዓት ውስጥ የሚኖሩትን ያንድ ጎሳ ተወላጆች አስተሳሰብ፤ ግብረገብ፤ ስነምግባርና የሞራል እሴቶቹን ሙሉ በሙሉ በመለወጥ አዲስ ሰዎችን (homo fascisticus ) ለመፍጠር ያለመ ነው እነዚህ የፋሽስት ስርዓት የሚፈጥራችው አዲስ ሰዎች ከነባር ታሪካቸው የወጡ፤ ነባር የሀገራቸውን ታሪክ፤ ባህል፤ ልማድ የሚጠየፉ ሰዎች ይሆናሉ።

እኔ ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት የወያኔ ድርጅት በትግራይ ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ባህላዊ እሴቶች፤ ስነምግባርና አመለካከት የወጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ፈጥሮአል ብዬ እሞግታለሁኝ 

የአደባባይ ምሁራኖቻችን ባለፉት ዘመናት ላይ ተመስርተውና የእነ አሉላ አባነጋን ታሪክ እየጠቀሱ የሚነግሩን የትግራይ ህዝብ አርበኛነትና ለኢትዮጵያዊነት ያለው ቀናኢነት ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት ውስጥ የወያኔ ድርጅት በፈጠረው አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነትና ከእሱም በፈለቀው የፋሽስት ፍልስፍና ምክንያት ከትግራይ ጠፍቷል ብዬ እሞግታለሁኝ ይህን ስል ደግሞ እንደነዚህ የአደባባይ ምሁራን በስሜት ሳይሆነ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች ከሚያሳዩት ጉልህ የሆኑና በጸረ-ኢትዮጵያዊነት ከተቃኙ ምግባሮቻቸውና የግልም ሆነ የወል ድርጊቶቻቸው በመነሳት ነው። 

በምሳሌነትም ከዚህ በታች አንዳንድ አስረጂና ነቃሽ የምላቸውን ከኢትዮጵያ ባህል፤ ትውፊትና እምነትና ጸንቶ የቆየ የይሉኝታ ባህል የወጡ የትግራይ ተወላጆች ድርጊቶች አቀርባለሁኝ።  

በብሄረተኛነት ዘመን ማህበረሰቦች ጭምብላቸውን ጥለው በግልጽና ካለእፍረት ራሳቸውን ያመልካሉ  የልዩ ነን ባይነታቸውን ምሳሌ እዚህ  (ቪዲዮም) - አምስተርዳም ትግራይ ፌስቲቫል ያለፈው ዓመት የተደረገው ፋሽዝም በሚፈጥረው እብሪትና የማንአህሎኝነት ስሜት የሚሰክሩት ያንድ ምርጥ ጎሳ ተወላጆች  የሆኑ አዲሶቹ የፋሽስት ስርዓት ፍጡሮች  ካለ እኛ በስተቀር ሰው የለም ብለው መዘባነን ይጀምራሉ፤ ከእነሱ ውጭ ያሉ ጎሳዎችን ተወላጆች መናቅ፤ መጠየፍ ይጀምራሉ። ራሳቸውን ከሌሎች ጎሳዎች የተለየ  ሰብዓዊነት ያላቸው አድር ገው መቁጠር ይጀምራሉ። በማናቸውም መልክ የራሳቸውን ምርጥ ዘርነት፤ የልዩ ታሪክ፤ ባህልና እሴቶች ባለቤትነት በአደባባይ ካለአንዳች ይሉኝታም መለፈፍ ይጀምራሉ። እኛ ቆንጆ ነን፤ ታሪካችን ከሌላው የበለጠ ነው፤ ማንነታችን ከሌሎች የተሻለ ነው በማለት የራሳቸውን ማንነት ታላቅነት ማምለክ ይጀምራሉ 

Gellner የተባለው ታዋቂ እንግሊዛዊ ምሁርና የብሄረተኛነት ንድፈ-ሃሳብ ሊቅ እንደጻፈው በብሄረተኛነት ዘመን ማህበረሰቦች ጭምብላቸውን ጥለው በግልጽና ካለእፍረት ራሳቸውን ያመልካሉ ሃያ ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ የታዘብነው ጣሪያ የነካ የትግራውያን እብሪትና ማንአህሎኝነት ከዚህ አዲሱ የፋሽስት ስነምግባርና እሴቶች ይመነጫል

የትግራይ የጎሳ ብሄረተኝነት ምን አይነት በእብሪት የተወጠረ ህሊና-ቢስ ትውልድን እንዳፈራ የሚከተለው አንድ በኦንታሪዮ (ካናዳ) ነዋሪ የሆነና የራስ ሚካኤል ስሁል ዝርያ ነኝ የሚል TIGRAI-ONLINE የሚባል ድህረ-ገጽ ባለቤት የሆነ የወያኔ ጀሌ ጽሁፍ ያስረዳል።

ትግራይ በአፍሪቃ ቀንድ ያሉ ስልጣኔዎች ሁሉ እናት ነች። የግእዝ ፊደል፤ የክርስትናና የእስልምና ምንጭ ነች። ትግራይ የቅዱስ ያሬድ፤ የአክሱም፤ የሃና ውቅሮ ነጋሽ ሃገር ነች። ትግራይ የአይበገሬዎቹ ንጉሰ ነገስታት የእነ ኤዛና፤ ካሌብ፤ አርማሃ፤ አብርሃ፤ ፍላምዳ፤ ዘርዓያቆብ፤ ዮሃንስ፤ ራስ አሉላ፤ ጄኔራል ሃያሎምና ሌሎች ብዙዎች ሃገር ነች። ትግራይ የሙሴ ታቦት መቀመጫ፤ የፍትሃዊ ሰዎች፤ የደፋሮች፡ የነጻና ዳኝነት አዋቂ ሰዎች ሃገር ነች። በታሪካችን ይቅርታ የምንጠይቅበት፤ አጠፋሁ ማሩኝ የምንልበት፤ የምንፈራበት ምክንያት የለም (2006 Tigrai Online website ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛው ትርጉም በአሰፋ ነጋሽ)

የፋሽዝም ማጠንጠኛ የሆነው የትግራይ  ብሄረተኛነት በትግራይ ተወላጆች መሃል ጉልህ የሆነ የስነልቦና  ለውጥ አስከትሏል ፋሽዝም የተጋነነ የጀግንነትን ስሜት ያጠናክራል፤ የወያኔ ትግሬዎች ዘፈኖች የትግራውያንን ታላቅነት፤ ጀግንነት፤ የልዩ ታሪክ ባለቤትነት፤የሴቶቻቸውን ማህጸን ቅድስናና የጀግና ልጆች ፈጣሪነት እንደዚሁም ከላይ የታጋይ ገብሩ አስራት ሚስት የውብማር አስፋው እንዳለችው የትግራዉያንን የጽናት ተምሳሌትነት በኩራት ያዜማሉ።

ፋሽዝም በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ባስከተለው የስነምግባር፤ የአመለካከት ለውጥ ምክንያት ለምሳሌ ያህል ከሰባት መቶ ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች በኃይል ተከዜን ተሻግረው የወልቃይትን፤ የጸገዴን፤ የጠለምትን ወዘተ መሬት ሲነጥቁ አመለካከቱ በፋሽስት አመለካካት የተቀረጸው የዛሬው የትግራይ ትውልድ ይህንን የሌላውን መሬት ነጥቆ በስግብግብነት የመውሰዱን ድርጊት እንደ ህገ ወጥና -ሞራላዊ ድርጊት አልቆጠረውም። እንዲያውም ይህንን ህገወጥና ነውረኛ ድርጊት እንደ ጀግንነት ስራ ቆጥሮ ይፎክርበታል https://www.youtube.com/watch?v=hScfnfaqLOY

 (ይህንን ከላይጠላቶቻችን በቅናት ምራቃቸውን እንደ ራበው ውሻ ያንጠባጥቡ። እኛ አልፎልናል፤ ድል አድርገናል፤ ተደስተናል፤ እኛ  ያሰብነውን  ፈጽመናል፤ ጠላቶቻችን ግን ፈዝዘው  ቀርተዋል/ይፍዘዙ እያለ ይዘፍናል፤ ይፎክራል። ወልቃይት አገሬ እሷን ነበር የምመኛት፤ ዛሬ በትግል (በጉልበት) አግኝቻታለሁ። ትግራይ አገሬ፤ ቆንጂት አገሬ፤ ጠላቶችሽ ፈዝዘው ይቅሩ፤ አንቺ ነሽ ሞራሌ፤ አንቺ ነሽ ወኔዬ። የትግራይ ልጅ፤ የወያኔ ልጅ በማንነቱ የማይደራደር፤ በምንነቱ የማይሳሳት….በጥፍሩ ጥሮ ግሮ ሃብት የሚያፈራ/የሚያለማ። በጥፍሩ ጥረቱን አሳይቶ ባሸናፊነት የወጣ የትግሬ ልጅ። ዘራፍ አለ በወልቃይት፤ በደጀና በቃብቲያእሰይ ይበል የትግሬ ልጅ ባለ ድርብ ዋልታ። እሷ(ወልቃይት)ነበረች በትግል  ወቅት  ስመኛት  የነበረች፤ አሁን አግኝቻታለሁ። የምንመኛትን ወልቃይትን አንለቃትም፤ በል የወያኔ ጎበዝ፤ እና የወያኔ ተረከዝ ተከታይ፤ ቦታ የለንም ለትምክሕተኞች። እሷን ለትምክሕተኞች አንለቅም። ጣፋጭ ፍሬ የተሸከመውን ወይም ያረገዘውን ዛፍ አንሰጥም። የወልቃይትን ለም መሬት ለትምክሕተኞች (ለአማራ) አንለቅም። አራስ ላማችንን፤ ፍሬ ያላት ዛፋችን ለአማራዎች አንሰጥም፤ (ለአማራ) ትምክህተኛ ኃይል አንሰጥም  የጠየቀስኩትን በጸያፍ ቃላቶች የታጀበ የትግራውያን ፉከራ ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎመልኝ ወዳጄ አቶ ጌታቸው ረዳ ነው)

የአንድ ህዝብ ወይም ጎሳ ተወላጆች የአክራሪ ብሄረተኛነት መገለጫ በሆነው የፋሽስት ስርዓት እብደት ውስጥ ጭልጥ ብለው ሲገቡ እንደዚህ ከላይ በጠቀስኩት መልክ ይሉኝታንና ነውርን በማያውቅ መልክ በእብሪት ይደነፋሉ፤ ይፎክራሉ።

በጦርነትና በአብዮቱ ምክንያት ትግራይ ውስጥ የተጸነሰው ፋሽዝም

የጣሊያን ፋሽዝም አውሮፓን አውዳሚ የነበረውን የአንደኛው የዓለም ጦርነት ታኮ ስልጣን ላይ እንደ ተቆናጠጠ ሁሉ የትግራይ ፋሽዝም ኢትዮጵያን አውዳሚ ከነበረው የአስራ  ሰባት ዓመታት ጸረ-ደርግ ትግልና ኢትዮጵያን የቀዝቃዛው ጦርነት ዋና መራኮቻ ካደረገው የካፒታሊስቱ (የምዕራቡ) ጎራና የሶሻሊስቱ (የምስራቅ አውሮፓ) ጎራ ፉክክር ዋነኛ አትራፊ ሆኖ በግንቦት ሃያ ቀን 1983 . ስልጣን ተቆናጧል። በዚህም ምክንያት ይህ የወያኔ ብቸኛ የስልጣን ባለቤት መሆን የትግራይን ህዝብ በኢትዮጵያ መቃብር ላይ የምትገነባው የአዲሲቷ የበለጸገች ትግራይ ባለቤት ከማድረጉም በላይ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ በታች ያለውን የኢትዮጵያን ሃብት በብቸኝነት እንዲዘርፉና ታይቶ የማይታወቅ የሃብት ባለቤት እንዲሆኑ አስችሎአቸዋል። የትግራይ ተወላጆች የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ተቀላቅሎ በታሪካቸው አይተውት የማያውቁት ፍስሃና ልማት ያመጣላቸውን መንግስት የሚጥሉበት ምክንያት የለም ብዬ ከሃያ ስድስት ዓመታት በላይ ስንሟገት የነበርነውን ጥቂት ኢትዮጵያውያን እንደ ጥላቻ ሰባኪ ሲያየን ቆይቶአል። እላችሁላሁኝ የትግራይ ህዝብ የወያኔን የፋሽስት ስርዓት እስከ ወደቀበት የመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ አብሮት ይዋጋል፤ ይዋደቃልም። ከወያኔ መውደቅም በኋላ የትግራይ ህዝብ ካለ አግባብ ወያኔ እየዘረፈ ትግራይን የገነባበት ሂደት እንዲመለስ ጠመንጃውን ይዞ ተተኪውን የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት ይገጥማል። ይህንን ዛሬም በድጋሚ ከዛሬ ሃያ ስድስት ዓመታት ጀምሮ እናገር እንደነበረው ካለጥርጥር በጥላቻ ሳይሆን በእውቀት ላይ የተመሰረተን ጥናት ተንተርሼ በእርግጠኛነት እናገራለሁኝ።

ጭፍን አምባገነንነትን የሚያራምድ ወይኔን የመሰለ ፋሽስታዊ የፓለቲካ ስርዓት ተከታዮቹን በማያቋርጥ አብዮታዊ እንቅስቃሴና በማያቋርጥ ፋሽስታዊ ፕሮፓጋንዳና ትምህርት ጠምዶ በማደንዘዝ ይገዛል። ጭፍን አምባገነንነትን የሚያራምድ ወይኔን የመሰለ ፋሽስታዊ የፓለቲካ ስርዓት ተከታዮቹን በማያቋርጥ አብዮታዊ እንቅስቃሴና በማያቋርጥ ፋሽስታዊ ፕሮፓጋንዳና ትምህርት ጠምዶ በማደንዘዝ ይገዛል 

N. Padellaro የተባለ የኢጣሊያ ምሁር የፋሽዝም አስተምሮት ዋና እምነትካለ ፓለቲካ እንቅስቃሴ የሰው ልጅ መልካም ምግባሮች ይበላሻሉ። ስለሆነም የፋሽስት ስርዓት የማያቋርጥ የፓለቲካ እንቅስቃሴዎች ያስፈልጉታልይለናል። የፓለቲካ እምነትም ሆነ ኃይማኖታዊ እምነት ካለ አጃቢ ስነ ስርዓቶችና (rituals) ምልክቶች (symbols) ዘላቂነትና ረጅም እድሜ እንደማይኖራቸው ከማንም በላይ ፋሽስቶች ይረዳሉ። ፋሽስቶች አፈታሪካዊ ትረካ(myth) በስነ ስርዓትና ምልክቶች የታጀበ አስተምህሮትና ፕሮፓጋንዳ በተከታዮቻቸው ዘንድ የፋሽዝምን የፓለቲካ እምነት ለማስረጽና ለማጠናከር ከማንም በላይ ይገነዘባሉ 

በእነዚህ ዘዴዎች ነው የፋሽዝም እምነቶች የተከታዮቻቸው የወል እምነት የሚሆነው። ፋሽስቶች ሰፊው ህዝብ አመክንዮ (reason) ሳይሆን ስሜት (feeling) እንደሚጫናውና-እንደሚገዛው ጠንቅቀው ያውቃሉ። በዚህም ምክንያት ፋሽስቶች የአፈታሪክ ትረካን፤ ባህላዊ ምልክቶችና (cultural symbols) አጃቢ ስነ ስርዓቶች (rituals) በመጠቀም የሰፊውን ህዝብ ስሜት በቀላሉ ለመቀስቀስና ህዝብን ለአንድ የድርጊት ዓላማ ያነሳሳሉ የወያኔ ትግሬዎች ዛሬ ከትግላቸው ዘመን ጀምሮና በተለይም ስልጣን ላይ ወጥተው በርካታ የባህል ዘፈን ቡድኖችን ካደራጁ በኋላ የትግራይን ህዝብ ታላቅ ነህ፤ ወርቅ የሆንክ ልዩ ህዝብ ነህ፤ ከሌሎች ተራ ህዝቦች ሳይሆን ካንተ ከወርቁና ከጀግናው ህዝብ በመፈጠራችን ወዘተ እንኮራለን እያሉ በስሜት ሊያሳብዱት የቻሉት ስሜትን በሚቀሰቅሱ ዘፈኖች፤ አፈታሪካዊ ትረካዎች፤ ድራማዎች፤ ኃይማኖታዊ-መሰል ስነ ስርዓቶች ወዘተ በታጀቡ ህሊና አሳዋሪና አደንዛዥ ዝግጅቶች ነው። ከወያኔዎች በፊት በተለይ የጣሊያን ፋሽስቶች በዚህ ረገድ በነሙሶልኒ የዓለም መሪዎች እንሆናለን ብለው የጣሊያንን ህዝብ በስራቸው በማሰለፍ በመጨረሻ አይወድቁ ውድቀት ወድቀው መጥፎ ታሪክና ትዝታ ጥለው አልፈዋል።የአፈታሪኮች ትረካ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ዋና አንቀሳቃሽ ሞተር ይሆናል። ፋሽስቶች በፕሮፓጋንዳ ወገኖቻችን ለሚሉዋቸው ያንድ ነገድ አባሎች የሆኑ ተከታዮቻቸው የሚመግቡዋቸው አፈ-ታሪኮች ተከታዮቻቸውን በስሜት ከማነሳሳታቸውም በላይ እነዚህ ያንድ ነገድ ተወላጆች በቆራጥነት ተነሳስተው አሁን እንደ ኃይማኖት የወል እምነታችው ያደረጉትን በብሄርተኛ ስሜት የተቃኘ የፓለቲካ ግብ ለማሳካት ይታገላሉ።

ባህል የሰዎችን አመለካከት በመቅረጽ ለድርጊት የሚያነሳሳቸውን ሃሳብና ዓላማ እንድንረዳ ያደርገናል።

በታሪክ ውስጥ አንድ ህዝብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚወስኑት የኢኮኖሚና የፓለቲካ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆኑ ባህላዊ እሴቶችም ጭምር ናቸው።፡ባህል የሰዎችን አመለካከት በመቅረጽ ሰዎች በስሜትና በገፍ አንድ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገቡ የሚያነሳሳቸውን ሃሳብና ዓላማ እንድንረዳ ይረዳናል ይለናል ሞሴ የተባለ ስለፋሽዝም ብዙ ጥናት ያደረገ ሊቅ። ባህል በፋሽዝም ርዕዮተዓለም ውስጥ ህዝብን በስሜት አነሳስቶ በማንቀሳቀስና ያንድ ፋሽስታዊ የፓለቲካ እንቅስቃሴ ደጋፊ በማድረግ በኩል የሚጫወተው ሚና ክፍ ያለ ነው።ባህልና ከባህል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አፈታሪኮች፤ ባህላዊ ስነስርዓቶች፤ ዘፈኖች፤ ባህላዊ ፉከራዎች/ሽለላዎችን ወዘተ በመጠቀም አንድ የፋሽስት ቡድን ህዝብን በስሜታዊነት በማነሳሳት የባህልን ውጤቶች የፋሽስት የፓለቲካ ዓላማ ማሳኪያና ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ያደርጋል ባህላዊ ምስሎችና ምልክቶች (cultural images and symbols) ሰዎችን በስሜት አነሳስተው የማሳወር አቅምና ችሎታ አላቸው። እኔም ከላይ የጠቀስኩትን የትግራውያን ፉከራ ይዘት ያካፈልኩዋችሁ የዚህ ፉከራ ይዘት የአንድን በፋሽስት አስተሳሰብ ያበደ ህዝብ አመለካከት ፍንትው አድርጎ ስለሚያሳይ ነው

ኪነጥበብ፤ ክብረ-በዓላትና ባህላዊ ምልክቶች የፋሽስት እምነት ማስፋፊያ መሳሪያዎች ይሆናሉ። 

Smith የሚባል እንግሊዛዊ የብሄረተኛነት ጥናት ሊቅ በብዙ ረገድ ብሄራዊ ምልክቶች ልማዶች ክብረ በዓሎች ኃይለኛና ዘላቂ የብሄረተኛነት መገለጫዎች ናቸው”. ፋሽስቶች እነዚህን በአንድ ህዝብ ውስጥ ጥልቅ መሰረት ያላቸውን ምልክቶች፤ ልማዶችና ክብረ በአሎች ህዝብን በስሜታዊነት ለማነሳሳት ለሚያደርጉት ያላቋረጠ ትግል በመሳሪያነት ይጠቁሙበታል

Payne የተባለ አሜሪካዊ የታሪክ ጸሃፊ ጀርመናዊ ታሪክ ጸሃፊ የሆነውን P. Reichel ጠቅሶ እንደጻፈው ምናልባትም ከማናቸውም በዚህ ዘመን ከተነሱ ጨቛኝ መንግስታዊ ስርዓቶች በስነጥበብና በህዝባዊ በዓላት አማካይነት ለራሱ ስልጣን ህጋዊነትን የሰጠና ራሱን በእነዚህ የህዝባዊ ባህል መገለጫዎች የሆኑ በዓላትና ስነጥበባዊ ውጤቶች የገለጸ ስርዓት የለም በማለት የናዚና የፋሽዝም ስርዓቶች ባህልን ዋነኛ ህዝብን በስሜት የሚያንቀሳቅሱበት መሳሪያ ማድረጋቸውን ያስረዳል በናዚ ጀርመን ውስጥ የመገናኛ ብዙሃንን (ሚዲያን) በመጠቀም ህዝብን በፕሮፓጋንዳ ማነሳሳትና ማንቀሳቀስ ዋነኛ የናዚ የባህላዊ ቅስቀሳ ዘዴ ነበር ጄንቲሌ የሚባል የታሪክ ጸሃፊ ደግሞ በፋሽስት አገዛዝ ስር የወደቀቸ ጣሊያን ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ከተሞቿም ሆኑ ገጠሮቿ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿ በከበሮ ድለቃ የታጀቡ የብሄራዊ በዓላት ማክበሪያ መድረክ፤ የፋሽስታዊ አብዮት ድሎች የሚከበሩበትና የወደቁት የፋሽስት ጀግኖች የሚያሞግሱበት መድረክነት መቀይሯን ይነግረናል።

ሌላው ቀትሮ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የትግራይን ልዩ ማንነት በሚገልጹ አሸንዳን የመሰሉ ከባህላዊና ኃይማኖታዊ ይዘታቸው ይልቅ ፓለቲካዊ ድምጸታቸው ጎልቶ የሚከበሩ ክብረ በዓላት ዛሬ የፋሽስቱ የወያኔ መንግስትና ይህንን መንግስት አቅፎና ደግፎ የቆመው ሰፊው የትግራይ ህዝብ በእውነትም ምን ያህል ማናቸውንም ሃይማኖታዊና ባህላዊ ምልክቶችን እንኳን ድንበር መፍጠሪያ ግርግዳዎች እንዳደረጉዋቸው የሚያሳይ ነው

የትግራይ ህዝብ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት አማካይነት የራሱን ነገድ ማንነትና ታላቅነት እንዲያመልክ ተደርጎ ለብዙ ሺህ ዘመናት አብሮ ከኖረው የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በስነልቦናም ሆነ በእለታዊ ህይወቱና ማህበረሰባዊ ተራክቦው (social interaction) እየተለየ መጥቶአል ዛሬ የትግራይ ህዝብ ራሱን ኢትዮጵያውያኖች በጋራ ከሚጋሩዋቸው ብሄራዊ እሴቶች በተቃራኒ የቆሙና ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ፤ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የተቃኙ ፋሽስታዊ እሴቶች ባለቤት በማድረግ ጨርሶ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ወጥቷል ማለት ይቻላል የኪነጥበብ ስራዎች፤ ዘፈኖች፤ ትያትሮች፤ ፊልሞች ወዘተ የህዝብ መዝናኛዎች መሆናቸው ቀርቶ ጦረኝነትን፤ የትግራይን ህዝብ የበላይነት፤ ምርጥነት፤ የንጹህ ዘር፤ የንጹህ ደም ባለቤትነት፤ ልዩና ወደር የሌለው የታሪክ ባለቤትነት፤ የሥልጣኔ ባለቤትነት፤ ጀግንነት፤ አዋቂነት፤ ወዘተ አጉልተው የሚያሳዩ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች ሲደረጉ በሌላው በኩል ዘፈኖችን፤ ፉከራዎችን፤ ትያትሮችን፤ ፊልሞችን የመሳሰሉ የኪነት ስራዎች ከምርጡ የትግራይ ህዝብ ወይም ጎሳዎች ወይም ህዝቦች ውጭ ያሉትን የሌሎችን ፈዛዛነት ትንሽነት፤ ፈሪነት፤ ድንቁርና፤ ኋላቀርነት፤ የአይምሮ ዘገምተኝነት (Retards የሚለውን የአንዲት እብሪተኛ የትግራይ ብሄረተኛ ሴት ስድብ ዩቲዩቭ ውስጥ (ገዛ ተጋሩ GEZA TEGARU የተባለ "የፓል-ቶክ ውይይት መድረክ" አዘጋጅ የሆነች ለአንጂኦ (ዩ ናይትድ ነሺን) የምትሰራ የራያ ተወላጅ ወ/ት አባዲት- በፓልቶከ የቅጽል ስም መጠርያዋ “ሕድያት ትግራይ” ከላይ የተጠቀሰው ሰለተናገረቺው አቶ ታቸው ረዳ የትግራይ በሕረተኞቸ በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? የሚለውን መጽሐፉን ማንበብ ይቻላል።እንዲሁም የተላላፉ የድምፅ ቅጆችንና የተለያዩ ዮ- ቱብ ቪዲዮዎችን ማየት ) ወዘተ... አጉልተው የሚያሳዩ መሳሪያዎች ይሆናሉ። 

ዛሬ በርካታ የትግርኛ ዘፈኖችን ይዘት ብታዳምጡ የሚያሰሙት ፉከራ ስለ ትግራይ ህዝብ ልዩ ጀግንነት፤ አልበገሬነት፤ ታላቅነት ስለሌላው ደካማነትና ፈሪነት ነው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ ህዝብ እንደዚህ ይሉኝታን ባጣ መንገድ ታላቅነቱን፤ ብቸኛ ጀግንነቱን፤ አልበገሬነቱንና በሌሎች ላይ ያለውን የበላይነት የሰበከበት ወቅት ተፈልጎ ሊገኝ አይችልም

በአንድ ህዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ በመሆን ወደፊት ብቅ ያለው ፋሺዝም የተባለውና የአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነው አዲሱ የፓለቲካ ኃይማኖት ከእሱ እንደሚቀድመው የኢጣሊያን የፋሽስት ስርዓት አዲስ ምድራዊ የፓለቲካ ሃይማኖት እምነትን (አክራሪ ብሄረተኛነትን) እያስፋፋ ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በመንግስትነት ሰይሞ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ላይ ራሱን በኃይል በመጫን ለትግራይ ህዝብ የደስታን ዘመን ከትግራይ በታች ላለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የጭለማና የመከራ ዘመንን አብስሯል ።ይህ የትግራይን ህዝብ የወል ማንነት (በወያኔ ቋንቋ የትግራይ ብሄር) እንደ ሃይማኖቱ አድርጎ የሚያየው፤ የትግሬነትን የወል ማንነትንና የትግራይ ብሄረተኛነትን መመሪያው ያደረገ ፋሽስታዊ ፍልስፍና የትግራይን ህዝብ የወል ማንነት የተቀደሰ አድርጎ ከማየቱም በላይ የትግራይ ተወላጆች ይህንን በወያኔ መንግስት ቅድስና የተሰጠውንና ከሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ሁሉ በላይ ወርቅ አድርገው ራሳቸውን እንዲያዩ ያደረጋቸውን አዲሱን ማንነታቸውን ህይወታቸውን ጭምር መስዋእት አድርገው እንዲጠብቁትና እንዲከላከሉት ያስተምራል ጊዜውን አግኝቶ የትግራይን ቴሌቪዥን በየጊዜው ለሚከታተል ሰው የትግራይ ህዝብ በልማት ስራ ላይ ብቻ አለመጠመዱን ይመለከታል። የትግራይ ህዝብ ልጆቹ ምስጋን ይግባቸውና ታጋዳላይ ጀግኖች ልጆቹ ያጎናጸፉትን አዲሱንና አኩሪ የወርቅ ማንነቱን በየጊዜው በሚያከብራቸው አዲስ በዓላቱ (የየካቲት 11 የግንቦት 20 የአሸንዳ፤ የሰማእታት ቀን፤ የሰራዊት ቀን፤ የሴቶች፤ የወጣቶች ቀን፤ በጦርነት የተጎዱ አካል ጉዳተኞች በዓላት ቀናት ወዘተ በስሜት ሰክሮ ከበሮ እየደለቀ፤ በኦርቶዶክስ ቀሳውስትና ታቦት ታጅቦ ታላቅነቱን፤ ልዩ ጀግንነቱን ጠመንጃ ይዞ በቀረርቶ፤ በፉከራ ጭምር ያስተጋባል። በቴሌቪዥን መስኮቶች የትግራይ ህዝብ ልዩ ጀግንነት በእነ አሉላ አባነጋ፤ ዐጼ ዮሃንስ፤ ኃያሎም ዓርዓያ፤ አሞራው ወዘተ ምስሎች ታጅበው ይቀርባሉ። እነዚህ ዓይነት ያንድን ህዝብ ታላቅነት የሚዘክሩ ትዕይንቶች ወያኔዎች ከደርግ ጦር ጋር በተደረጉ የእርስ በርስ ውጊያዎች በጦር ሜዳ የበላይነት ባገኙባቸው ምስሎች ታጅቦ ይቀርባል። በእነዚህ የጦር ምስሎች ታጅበው የሚቀርቡት የቴሌቪዥን ዝግጅቶች የትግራይን ህዝብ የህዳሴ ጉዞ (renaissance) የዳግም ልደት (rebirth) የሚያሳዩ፤ የትግራይ ህዝብ ከመቶ ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ ነበሩ በሚባሉ የአማራ ህዝብ መሪዎች ተቀብሬ ነበር ብሎ ከሚያምንበት መቃብር በጀግና ልጆቹ መስዋእትነንትና ሰማእትነት በትንሳዔ ተነስቶ አዲስ ታሪክ እየጻፈ መሆኑን ያስገነዝቡናል።

ጭፍን የአምባገነን አገዛዝ (ቶታሊቴሪያን) የፋሽዝም ኃይማኖታዊ አምልኮ

ፋሽዝምን ጭፍንና አምባገነን የሚያደርገው እንደ አንድ አክራሪ ሃይማኖት የተከታዮቹን ሁለንተናዊ ህይወት ማለትም አስተሳሰባቸውን፤ ምኞችታቸውን፤ ድርጊታቸውን፤ ምግባራቸውን፤ ህልማቸውን፤ የሚጠሉትን፤ የሚወዱትን ወዘተ ሁሉ ለመቆጣጠርና ለመወሰን ስለሚነሳ ነው ባጭሩ ፋሽዝም የግለሰቦችን ነጻነት የሚቀናቀንና የማይፈቅድ ፍልስፍና ነው።

ቤኒቶ ሙሶልኒ እንደተናገረው ለፋሽስቶች መንግስት ሁሉንም ነገር ነው፤ ካለ መንግስት በቀር አንድም ሰው ወይም መንፈሳዊ ነገር አይኖርም ወይም አንዳችም ዋጋ አይኖረውም”. 

ሃይማኖት ለሰው ልጆች አጠቃላይ የህይወት መመሪያ እንድሚሆን ሁሉፋሽዝም የኃይማኖትን ዋነኛ ተግባር ለራሱ በመውሰድ ሁሉን ነገር እኔ ልቆጣጠር፤ እኔ ልወስን የሚል ነው። ከዚህ ሁሉን ነገር እኔ ልቆጣጠርና  እኔ ልወስን ከሚለው ፍልስፍናው በመነሳት አንድ የፋሽስት መንግስት ራሱን በእጅጉ የታላቅነትና የፍጹማዊ እሴት ምንጭ አድርጎ በመቁጠር ለብዙ ሚሊዮን ህዝቦች (ወንዶችና ሴቶች) ህይወትና ኑሮ መሰረታዊ  ትርጉም ለመስጠትና  የህይወታቸውን ግብ ለመወሰን ይነሳል (ጄንቲሌ)

ፋሽዝም ፍጹማዊ አምባገነነት የሰፈነበት ስርዓት ነው። ፍጹማዊ አምባገነንነት የፋሽዝም መሰረትና እጅግ የነጠረ የፋሽዝም ርዕዮተዓለም መገለጫ ነው።) Benitto Mussolini, B. Fascism: Doctrine and Institutions, 1968በሚለው መጽሃፉ በሚከተለው አኳኋን የገለጸውን አሰራር የሚከተል ነው። 

በሌላ አነጋገር እኛ በዓለም ውስጥ ያሉትን ኃይሎች ሁሉ የምንቆጣጠር መንግስት ነን። እኛ ፋሽስቶች የፓለቲካ ኃይሎችን፤ የሞራል ኃይሎችን፣ የኢኮኖሚ ኃይሎችን፣ ማናቸውንም በመንግስታችን ስር ያለውን ሁሉ እንቆጣጠራለን። ሁሉም ነገር በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆን አለበት፤ ምንም ነገር ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ መሆን የለበትም።  ማናቸውም ዓይነቶች ሰብዓዊና መንፈሳዊ እሴቶች እንኳን ዋጋ ሊኖራቸው ይቅርና  ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ መሆን አይችሉም። ማናቸውም ግለሰቦች ሆኑ ወይም ቡድኖች (የፓለቲካ ፓርቲዎች፤ የባህል ማህበሮች፤ የኢኮኖሚ ህብረቶች፣ የማህበረሰብ መደቦች) ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሊኖሩ አይችሉም  

ፋሽዝም ከግለሰብ አንስቶ ቤተሰብ፤ እድር፤ ማህበር፤ ሰንበቴ፤ የእምነት ተቋሞች፤ የባህላዊ ተቋሞች፤ ወዘተ ሁሉ ውስጥ በመግባት የአንድን ህብረተሰብ ወይም ሀገር ነዋሪዎች ህይወት ለመቆጣጠር የሚተጋና የሚጥር ጭፍን አምባገነናዊ ስርዓት

ጉሪያን የተባለ የጀርመን ምሁር ፋሽዝምን የመሰለ የጭፍን አምባገነን መንግስት (totalitarian state) የሚያስፋፋው የፓለቲካ ሃይማኖት አምልኮን ብቻ ሳይሆን ያንድን ነገድ ወይም ህዝብ ማንነት አምልኮን ጭምር ነው ይለናል። በዚህም ምክንያት ያንድን ፈላጭ ቆራጭ ያንድ ሰው ወይም ስርወ መንግስት አምልኮ ከሚያስፋፋው (absolutist regime) ይለያል።

ፋሽዝም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድ ህዝብ፤ ነገድ ወይም ጎሳ አባሎች የራሳቸውን ማንነት እንደ አምልኮ ምስል፤ የእምነት ምልክት አድርገው እንዲያዩና እንዲያመልኩ  የሚያደርግ አክራሪ ፍልስፍና ወይም ርዕዮተዓለም ነው። 

ባለፉት 43 አመታት የወያኔ ፋሽስቶች የትግራይን ህዝብ ማንነት እንደ አምልኮ ምስል፤ የእምነት ምልክት አድርገው የሚያዩና የሚያመልኩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የጎሳ ተከታዮችን ፈጥረዋል። ይህ አዲሱ የትግራይ ፋሽስቶች የፈጠሩት አምልኮ የትግራይን ህዝብ ታላቅነት፤ ልዩ ሰብዕና፤ ጀግንነት፤ የልዩ ታሪክ ባለቤትነት፤ ወርቅነት ወዘተ የሚያስርጽ እምነት በመሆን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች አክራሪ ብሄረተኛነትና እሱን ተከትሎ በሚመጣው ስሜታዊነት እንዲሰክሩና ህሊናቸውን እንዲስቱ በማድረግ ኢትዮጵያውን ከሚጋሯቸው እሴቶች በተጻራሪ እንዲቆሙ አድርጎአችዋል  

እንግዲህ አንባቢዎቼ በውል ልታዩ እንደሚችሉት ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ውስጥ በወያኔ አገዛዝ ስር ያስተናገድነ ይህንን ሙሶልኒ ያለመውን የአንድ ፋሽስት ስርዓት መገለጫዎችን የተገበረ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ነው 

ጭፍን አምባገነንነት ስርዓት ስል ያንድ ብቸኛ ፓርቲ አገዛዝ፤ የሽብርን ዘዴዎች በመጠቀም፤ ህዝብን በፈለገው መንገድ የሚያንቀሳቅስበት ስርዓት ማለት ብቻ አይደለም። ጭፍን አምባገነንነት አንድ መንግስት በሁሉም የአንድ ህብረተሰብ መዋቅሮችና ተቋሞች ውስጥ እየገባ  ኢኮኖሚውን፤ ባህሉን፤ የእምነት ተቋማትን፤ የጦር ኃይሉን፤ የፍትህ ስርዓቱን ወዘተ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ሁሉ ያካትታል ወያኔ በስራ ቦታዎች፤ በሰራተኛ ማህበራት፤ በቀበሌ ማህበራት፤ በሴቶች፤ በወጣቶች ማህበራት፤ በእድሮች፤ በሃይማኖታዊ ተቋማት (ክርስትና፤ እስልምና ወዘተ) በትምህርት ቤቶች፤ በመስሪያ ቤቶች፤ በሰዎች የግል ህይወትና ትዳር ውስጥ ጭምር እየገባ የኢትዮጵያን ህብረተሰብ አፍኖ ለመግዛት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከዚህ ፋሽስታዊ ባህሪው ይመነጫል

ሌላው ቀርቶ ቀልደኛውና ቁምነገረኛው አርቲስት አቶ ክበበው ገዳፓሊሱ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ትዕይንት ውስጥ የምታዩት የአንድ ጥልቅ-ብዬ የወያኔ ትግሬ ፓሊስ ድርጊት የዚህ ሁሉን ነገር ልቆጣጠር የሚል የፋሽስት ስርዓት ነጸብራቅ ነው

Guido Gamberini የተባለ የጣሊያን ምሁርለፋሽስቶች ዋነኛና ተመራጭነትና ዋጋ ያለው ችሎታ እውቀት ሳይሆን ጭፍን እምነት ነው። ፋሽስቶችን ለቆሙሉት ዓላማ በቆራጥነት እስተመጨረሻው እንዲዋጉ የሚያደርጋቸው ጭፍን እምነታቸው ነው

በደንብ ያላጤናቸውና ያላስተዋልናቸው የትግራይ አክራሪ ብሄረተኞች  ሲያስተጋቡዋቸው የነበሩት የእነ ሙሶልኒ ፋሽስታዊ አስተሳሰቦች ምን ይመስላሉ?

ብስራት አማረ የሚባል የወያኔ ካድሬና የወያኔ ዋና የመግደያና የማሰቃያ እስር ቤት ኃላፊ በመሆን ለብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን፤ በተለይም ለአማራ ተወላጆች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆነ ግለሰብፍኖተ ገድልበሚል ርዕስ ስለ ወያኔ ሃርነት ትግል በጻፈው መጽሃፉ ውስጥ የትግራይ ሽማግሎች ለወያኔ ተዋጊዎች የሰጡትን ምክር እንደሚከተለው አስፍሮአል። 

ዮሃንስ አራተኛ ከሞቱ ልክ ከአንድ መቶ አምስት አመታት በኋላ መጋቢት 1981 .. ህውሃት መላውን ትግራይ ነጻ አውጥቶ መቀሌን ተቆጣጥሮ ወደ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ሲገሰግስ በእድሜ አንጋፋ የሆኑት ትግራውያን እነሱና አያቶቻቸው የከፈሉትን ታሪካዊ ሰቆቃ አስታውሰው በታላቅ ክብር ለታጋዮቻቸው ሲመክሩኢትዮጵያ የናነት ናት። አሁን የሚያቆማችሁ ኃይል የለም። ልጆቻችን ከእነሱ ይበልጥ ጠቢብና አሳቢ እንደሆናችሁ የንጉስ ምንሊክ ሰዎች አሁን ይማራሉ። እናንተን ለማሸነፍም ሆነ ለማስቆም የሞራል ብቃት የላቸውም። ትግራይ አንዴም ተሸንፎ አያውቅም። ምንሊክ የትግራይን ህዝብ እንደ ጠላት ቅልስልስ አደረጋቸው። እግዚአብሄር ይባርካችሁና በአባቶቻችን እና በራሳችን ስም እናመሰግናችኋለን ብለው ምንሊክ ባንድ ወቅት ታላቅ ለነበረችው ሀገር የተወላት ብልሹና ከፋፋይ አስተሳሰብ እንደ ነበር አስገንዝበዋል (ለዝርዝር መረጃ የብስራት አማረን - “ፍኖተ ገድልየተሰኘ መጽሃፍ ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ)

መለስ ዜናዊ በየካቲት 1984 . መቀሌ ላይ ለአስራ ሰባተኛው የወያኔ ምስረታ በዓል ላይ አንድ ሚሊዮን ለሚሆኑ በቦታው ለተሰበሰቡ የትግራይ ተወላጆች ያደረገው ንግግር

ይህ ሕዝብ አንኳን የሌሎች/የባእዶች አልሆነ። እንኳን ከእናንተ ተፈጠርን። ይህ የእያንዳንዱ ታጋይ አምነት ነው። እንኳን ከናንተው ማህፀን ተፈጠርን። አንኳን የኛ ሆናችሁ። አንኳን የባዕዳ የሌላ አልሆናችሁ። አንኳን በማዶ እያየናችሁ የምንቀናባችሁ የሌሎች አልሆናችሁ። አናንተ ወጣቶች!እዚህ ያላችሁበት መድረክ እንደትደርሱ ሲባል ታላላቆቻችሁ ላባቸውና ደማቸው አፍስሰዋል፤ታላላቆቻችሁ በየጉራንጉሩና፤ በየሸለቆው እና ተራራው ቀርተዋል። ታላላቆቻችሁ አጥንቶቻቸው በየተራራው ተበትኗል። አጥንቶቸው  በየተራራው የተበተነበት ምክንያትም ትግራይ አንድትለማ በሚል ነው። እነኚህን አጥንቶች እንዳትረግጧቸው፤ አንዳታራኩሷቸው!ሁኔታውን ካመቻቹላችሁ በኋላ አንዳትከዷቸው ሌት ተቀን መጣር ይኖርባችኋል(ምስጋና ይድረሰውና ወዳጄ የሆነው፤ወያኔን በግምባር ቀደምትነት በመታገል የሚታወቀው የአክሱም ተወላጅ አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን እዚህ የጠቀስኩትን በመተርጉም የሁል ጊዜ ትብብሩን አድርጎልኛል)

ከላይ የጠቀስኳቸው የትግራይ ተወላጆች ለወያኔ ታጋዮች ትግራይን ከደርግ ነጻ ባወጡበት 1980 . የሰጡት ምክርና መለስ ዜናዊ በየካቲት 1984 . መቀሌ ላይ ያደረገው ንግግር ይዘቶች ወያኔ ስልጣን ላይ ሳይወጣ በፊት ከተራው የትግራይ ሽማግሌዎች እስከ መሪዎቹ ድረስ በአክራሪ ብሄረተኛነትና የእሱ መገለጫ በሆነው የፋሽስት አስተሳሰብ የተመረዙ እንደነበረ ያሳያል። ይህንን በትግራይ ውስጥ በግልጽ ሲንጸባረቅ የነበረ ፋሽስታዊ ክህስተት ደርግ፤ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች፤ ምሁራንም ሆነ በመሃል ሀገር የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ አልተረዱም ነበር።   

ባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር . 2016  ከመላው አውሮፓ አምስተርዳም ላይ ተሰብስበው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች የአማራና የኦሮሞተወላጆች በአጋዚ አልሞ-ተኳሾች በግፍ በተጨፈጨፉበት ማግስት (20-08-2016 Tigray Festival of the union of Tigrians in Europe Amsterdam Eden singer 2016 ) እዚህ አምስተርዳም ውስጥ ለሶስት ቀናት ባደረጉት የጭፈራና የዳንስ ፌስቲቫል ላይ የሚከተለውን እያሉ ነበር የጨፈሩት። ምንጭ-

ትግሬዎች ፈጣሪ ሲፈጥራቸው ጥቂቶች ቢሆኑም ልዩ ፍጡር አድርጎ ነው የፈጠራቸው፤ እኛ ሁሉም ነን ማለትም የታሪክ፤ የቅርስ፤ የጀግንነት መፍለቂያዎች ነን። እኛ ትግራውያን  ጀግኖች ባለ ሱሪዎች ነን። እኛ ወያኔዎች የእነዚያ ከጠራ ዘር የወጣን እንክርዳድ ወይም ቆሻሻ የማይደባለቅባቸው ትግራውያን ልጆች ነን! አምሳ ቢወለድ አምሳ ነው ጉዱ። ትግራዋይ ግን አንድ ይበቃል ሃምሳዎቹን ይመክታል በአንድ ክንዱ!

የነዚያ የጀግኖች ልጆች፤ የነዚያ ደምና አጥንታቸው ለነጻነት ሲሉ ግብር የከፈሉ፤ የእነዚያ  በጥቂትነታቸው የተሰባሰቡ፤ ወኔ የታጠቁ፤ የነዚያ ማንም የማይናገራቸው ልጆች፤የነዚያ  ባንዲራ አቅኚ ልጆች፤ የእነዚያ ኢትዮጵያን ያኮሩ ኩሩ ልጆች፤ የእነዚያ ለመስዋዕትነት  የሚሽቀዳደሙ ወያኔዎችና የወያኔ ልጆች።

የት ነው አገርሽ ብለው ቢጠይቁሽ ትግራይ ነው በያቸው። የት ነው አገርሽ ብለው ቢሉሽ  ትግራይ የጀግኖች አገር ብለሽ ንገርያቸው። የነዚያ ስለ ሕዝባቸው ሲሉ የታጠቁ  ከደደቢት  የፈለቁ ትግሬዎች ናቸው፤ የሕዝባቸውን ወኔ የታጠቁ፤ ከደደቢት የፈለቁ ትግሬዎች ናቸው፤ ባለ ሱሪዎች፤ ጀግኖች ናቸው፤ የጠሩ፤ (ምንምጉርዲዘይለግቦም ጉርዲ ይለዋል በትግርኛ ዘፋኙ) "ጉረዲ" (እንክርዳድ) (እህል ውስጥ የሚደባለቅ ቆሻሻከሌላ ጎሳ ያልተደባለቁ (ዘፋኙ የፈለገው የጠራ ዘር ለማለት ነው) (ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም አቶ ጌታቸው ረዳ)

ይህ ከላይ የጠቀስኩት ዘፈንና ዘፈኑ ውስጥ የተነገሩት ሃሳቦች ፋሽዝም በትግራይ ውስጥ ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት የፈጠረውን አዲስ የትግራይ ማህበረሰብና አዲሶቹ የትግራይ ማህበረሰብ አባሎች አመለካከታቸውም ሆነ ስነ ምግባራቸው ጨርሶ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ መሆኑን ያሳያል። ይህ በአዲስ የፋሽስት አስተሳሰብ የተቀረጸው የትግራይ ማህበረሰብ በርካታ አባሎች እንደ ሰው የሚገልጻቸውን በጥልቅ የማሰብና የማመዛዘን ክህሎት እንዳጡ ያሳየናል 

በዚህ ዘፈን ውስጥ በአክራሪ ብሄረተኛነት የተለከፉ ያንድ ጎሳ አባሎች ህሊናቸውን ስተው አዙሮ ማየትና ራሳቸውን መመልከት እንደተሳናቸው እናያለን። ይህ የህሊና መታወር በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩትን የትግራይ ማህበረሰብ አባሎች ባንድ መሪ ድርጅት፤ ባንድ ባለራእይ መሪእየተመሩ በጭፍን ወደ ገደል እንዲገቡ ያደርጋል።

የጣሊያን ፋሽስቶች ጣሊያናዊ መሆን ማለት ፋሽስት መሆን ነው፤ ፋሽስት መሆን ደግሞ ሙሉ ሰው መሆን ነውየሚል መፈክር ነበራቸው። ይህ ዛሬ ወያኔዎችወያኔ ማለት ትግራይ ማለት ነው፤ ትግራይ ማለት ደግሞ የክብር፤ የሞገስ፤ የጀግንነት፤ የአዋቂነት ወዘተ ምልክት ነው እያሉ ከሚኩራሩበት መፈክራቸው ጋር ይመሰላል።

ፋሽዝም ጠላቶቹን አሸንፎ በኃይል በማጥፋት እንጂ ከቶ በድርድር አያምንም

ፋሽዝም በድርድር፤ በሰጥቶ-መቀበል የሚያምን የፓለቲካ ኃይል አይደለም። የፋሽስት ድርጅትም ሆነ መንግስት ዓለምን የሚያየው በአሸናፊና ተሸናፊ መድረክነት ነው። ፋሽስቶች ከተፎካካሪያቸው ጋር በመደራደር ሳይሆን ተፎካካሪያቸውን አታለውም ሆነ አስፈራርተው በኃይል በማስገበርና በማጥፋት ያምናሉ።፡ የፋሽስቶች ቋንቋ ኃይል ነው እንጂ ድርድር ወይም ሰጥቶ መቀበል አይደለም። የወያኔ ፋሽስቶች እንደ ፓለቲካዊ ጦር ምንጊዜም ወታደራዊ ዝግጅት አድርገው በተጠንቀቅ በመቆም የአብዮታችን ጠላቶች ናቸው የሚሏቸውን ወገኖች ለማጥፋት ይተጋሉ። በዚህም ምክንያት ምንጊዜም እነሱ በአይምሮአቸው በጠላት ተከበናል የሚል አስተሳሰብ ስለሚመላለስ ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ይጠባበቃሉ 

ዛሬ የትግራይ ተወላጆች ከማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የበለጠ ከባድ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ከመሆናቸውም በላይ በትግራይ ውስጥ ከህጻናት እድሜ ክልል ጀምሮ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ጠላቶቻቸውን እንዴት አድርገው እንዲሚያጠፉ በፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን በወታደራዊ ስልጠና ጭምር እየተደራጁ ይገኛሉ። ዛሬ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የትግራይ ማህበረሰብ በወታደራዊ አደረጃጀት የተዋቀረና ከትግራይ ክልል በታች ያሉትን የሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ተወላጆች በተለይም አጎራባች የሆነውን የአማራ ክልል ህዝብ ለማጥፋት ሙሉ ዝግጅት አድርጎ የሚጠባበቅ ነው። ተባባሪዬ የሆነው የአክሱም ተወላጅ አቶ ጌታቸው ረዳ የላከልኝን የትግራይ ህጻናት እንዴት አድርገው በልጅነት እድሜያቸው ለጦርነት እንደሚዘጋጁ የሚያሳይ ምስል ከዚህ ጽሁፍ ጋር አባሪ አድርጌ አውጥቻለሁኝ። ፎቶግራፉ ግልጽ ባለ መልክ ስለማይታይ ለጥራቱ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ (ፎቶ)

የትግራይ ህዝብ ወያኔ ተነስቶ ይጥላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ወይስ ሞኝነት?

እስቲ ዛሬ ያለውን የኢትዮጵያን የህዝብ ስብጥር እንመልከት። ዛሬ በኢትዮያ ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ 93.3% የሚሆነው እድሜው 54 ዓመት በታች ነው (ይህ ባለፈው ዓመት በነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ላይ ባደረግሁት ስሌት ላይ የተመሰረተ ነው፤ ዘንድሮ ይህ ፐርሰንቴጅ ከፍ ይላል) እስቲ የወያኔ ትግሬዎች የጎሳ ፓለቲካና የትግራይ ብሄረተኛነት በትግራይ ህዝብ ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ የሚከተለውን መላምት እንውሰድ። ወያኔዎች የጠመንጃ ትግላቸውን በየካቲት 1967 . ከነበሩት የትግራይ ተወላጆች በዚህ አክራሪ የብሄረተኛነት አስተሳሰብ አይምሮአቸው የተበከለው በእድሜ ልጅ የሆኑት ልጆች ማለትም 0-13 እድሜ ክልል ያሉት የትግራይ ተወላጆች ብቻ ናቸው በወያኔ ጸረ-ኢትዮጵያ አመለካከት የተበከሉት ብለን በጣም ለጋስ (generous assumption) ሆነን እንገምት ማለትም ወያኔ ትግሉን ከጀመረ በኋላ ባካሄደው ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛንት ቅስቀሳ በጊዜው 13 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸው የትግራይ ተወላጆች በዚህ የጸረ-ኢትዮጵያ ቅስቀሳ በምንም ዓይነት አይምሮአቸው አልተመረዘም ማለት ነው ይሄ እንግዲህ በጣም ለጋስ ተሆኖ በሚሰጥ የመላ ምት ነው እንጂ የወያኔ ድርጅት እድሜያቸው ከአስራ ሶስት በታች የሆኑ ልጆችን ጠመንጃ አሲይዞ እንዳልተዋጋ እናውቃለን። እንግዲህ እንዲህ ለጋስ ሆነን እንኳን ብናስብ ዛሬ ካለው የትግራይ ህዝብ 93% የሚሆነው በአብዛኛው በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ወያኔያዊ በሆነ አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት አመለካከት ተቀርጾ ያደገ ነው

ዛሬ የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ጸንቶ ኢትዮጵያን ሊከላከል ይችላል ብለው የሚሉን ሰዎች ይህንን በመሬት ላይ የሌለ፤ በመረጃ ሊደገፍ የማይችል ምኞታቸውን ለተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ መመገባቸው ከትግራይ በታች ያለውን የኢትዮጵያ ህዝብ በተስፋ እጁን አጣጥፎ የትግራይ ህዝብ እስከሚነሳ ድረስ እንዲጠብቅ የሚያደርግ ነው እውነቱን እንነጋገር ላለፉት አርባ ሁለት ዓመታት በዚህ ዓይነት ጸረ-ኢትዮያ ቅስቀሳ የታነጸን አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ወደ ኢትዮጵያዊነት መጥቶ ከሌላው በወያኔ ከሚሰቃየው ኢትዮጵያዊ ጋር ይቆማል ማለት ከቅዠት የተለየ ጉዳይ አይደለም

እነሆ ከላይ በጠቅስናቸው ምክንያቶች ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የወያኔ ትግሬዎች ደጋፊዎችና አባሎች በአዲሱ ቅድስናን ባገኘው የፓለቲካ ሃይማኖታቸው ምክንያት በጭፍን አዲሱን አምላካቸውን ማለትም የትግራይን አክራሪ ብሄረተኛነት የህይወታቸው መመሪያ አድርገው፤ የህልውናቸው መሰረት አድርገው ይከተላሉ መሪውን የህወሃት ድርጅት በሙሉ ልብና እምነት ካለአንዳች ጥያቄ ይከተላሉ አዲሱን የዚህ የትግራይ ብሄረተኞች ሃይማኖት ግብ ማለትም የትግራይን ህዝብ ማንነት የበላይነት የማስረገጡንና የትግራይን ህዝብ የጥቅም የበላይነት መመሪያቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ። 

በሚሊዮን የሚቆጠሩ የወያኔ ድርጅት ተከታዮች የሆኑ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዲስፕሊንና በፍጹም ታማኝነት ድርጅታቸው የሚላቸውንና የሚያዛቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። ድርጅታቸው ጥሉ ያላቸውን ይጠላሉ፤ ውደዱ ያላቸውን ይወዳሉ። ድርጅታቸው በጠላትነት ለይቶ የነገራቸውን ጠላታቸውን (የአማራን ህዝብና በዚህ ህዝብ የተመሰለውን ኢትዮጵያዊነት) አጥብቀው ይጠላሉ። ማናቸውም እምነት ተከታዮቹን በእምነቱ ካሳመነና ጭፍን ተከታይ ካደረጋቸው በኋላ ትልቅ ኃይል የመፍጠር አቅም አለው። 

የጭፍን እምነት ተከታዮች የተጠየቁትን መስዋእትነት ካለአንዳች ማንገራገር ለመፈጸም የሚያስችል ዝግጁነት አላቸው ለጭፍን እምነታቸው ሲሉ ካለአንዳች ማንገራገር ደማቸውን ለማፍሰስ በቀላሉ ይነሳሉ። ይህ ጭፍን ኃይል ነው ህወሃትን በመሰለ የአክራሪ ብሄረተኛ ፍልስፍና መገለጫ በሆነ የፋሽስት ፍልስፍና በሚመራ ድርጅት ሲታዘዝ ተራሮችን የሚያንቀሳቅሰው፤ በፊቱ እንቅፋት ይሆንብኛል የሚለውን ሁሉ ከፊቱ በኃይል እየጠራረገ ዓላማውን የሚያሳካው። በአስራ ሰባት ዓመቱ የጸረ-ደርግ ትግል ህወሃት የትግራይን ህዝብ በስሩ ለማሰለፍ ብዙ ችግር ገጥሞት ሊሆን ይችላል። ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ግን በብዙ ረገድ እሰጥሃለሁኝ ብሎ ቃል የገባለትን ጥቅም የሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ይዞታ በመንጠቅና ከትግራይ በታች ያሉትን የኢትዮጵያ ተወላጆች በጎሳና በኃይማኖት እየለያየ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ሞትና ጥፋት ትግራይን ገንብቷል። ከሰባት መቶ ሺህ በላይ የሆኑ የትግራይ አርሶ አደሮችን በጉልበት ከጎንደር ላይ በተነጠቁ ለም መሬት ላይ አስፍሮ ጉልህ ተጠቃሚ አድርጎአል እነዚህ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ለዚህ አስበውት ለማያውቁት ሲሳይ ያበቃቸውን ህወሃት እሰከ መጨረሻዋ እስትንፋሳቸው ድረስ እንደሚዋጉለት ጥርጥር ሊገባን አያስፈልግም 

ስለዚህ የትግራይ ተወላጆች የወያኔን ፋሽስታዊ መንግስት ለመንቀል በሚደረገው ሀገራዊ ትግል ትርጉም ያለው አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብሎ መጠበቅ፤ የትግራይ ተቃዋሚ ነን እያሉ ተቃዋሚው ውስጥ እየገቡ ተቃዋሚውን የሚከፋፍሉትንና የሚያዳክሙትን አረናን ታንድን ወዘተ የመሰሉ የትግራይ ብሄረተኛነት አራማጆች ወያኔን ይቃወማሉ ብሎ ማመን ከንቱ ነው 

ትግራይ ህዝብ ዛሬ ከሚገኝበት የትግራይ ብሄረተኛነት ጭፍን አምልኮ ተላቆ ዓይኑን የሚከፍተው የህወሃት ወታደራዊ ኃይል ከትግራይ በታች በሚገኘውና የወያኔ ፋሽስታዊ ዋነኛ ሰለባ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አከርካሪውን እንደ ናዚ ወይም የጣሊያን ፋሽስት ጦር ሲመታ ብቻ ነው።እስከዚያ ድረስ እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ከወያኔ መንግስትና ድርጅት ጎን ቆሞ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደሚፋለም ጥርጣሬ የለኝም የዓለም ታሪክና የናዚና የፋሽስት ስርዓቶችታሪክ የሚያስተምረንም ይህንን ነው።  

Ethiopian Semay

 

No comments: