የበሰበሰ አማራ
እና
የበሰበሰ
አማራ፣
ሲያሻም በላዩ ላይ ሌላ ተጨማሪ የበሰበሱ አእላፍ አማራዎች ጨምሩበት--- ብዙ
የበሰበሱ
አማራዎችን
ማከማቸትና ማስታጠቅ ይቻላል
- ጥሩ
ጤናማ
አማራ
ግን በጭራሽ
አያስገኝም!
ጌታቸው ረዳ
5/18/25
አንብበው ሲጨርሱ ከሥር
የተለጠፈው ቪዲዮ ያድምጡ።
በርዕሱ የጠቀስኩት ወደ ራሴ አባባል የለወጥኩት Rotten Apple, plus a rotten apple, plus a rotten
apple---you may continue adding up more rotten apples—will Never Produce a Good
Healthy Apple! የሚል ነብሳቸው በገነት ይኑር የሟቹ ፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴ አባባል ነው።
ይህም ግትልትሉ
ጥርሰ ቢስ ተቃዋሚውና
ብሔረተኛውን ለመተቸት የተጠቀሙበት አባባል ነበር። ያንን ጥቅስ በራሴ መንገድ “አፕሉን ወደ ሰው” የተጠቀሙኩበት አባባል ነው።
ላጭር ወቅት
ቢሆንም ሰለ በሰበሰው የትግሬ ፖለቲካ መተቸት ካቆምኩ ቆይቻለሁ (በስብሷልና በስብሶ የከረፋን አካል ጥምቡ እስኪለቀው ድረስ
ትኩረቴ ያደረግኩት “13” የመንደር አጉራዘለሎችን በመደገፍ በመበስበስ ሂደት ላይ የሚገኙ “አንዳንድ የአመሐራ ማሃይም መሑራኖችና ጋዜጠኞች
ተበየ” ከወያኔ የቀሰሙት “በሔረተኞች የተቃኘ ፒዛንት ሪቮሊሽን”
(የፋሺዝም አብዮት) በሚያቀነቅኑ
ደጋፊዎቻቸው ላይ ነው የዛሬ ተኩረቴ)።
በዚህ የተለጠፈ
አጭር ቪዲዮ የምትመለከትዋቸው ሦስት ሰዎች አንዱ እመየ ኢትዮጵያን የመታገያ ምርኩዙ ያደረገ
ልበ ደንዳናው የታላቁ የእስክንድር ነጋ የትግል ጔድ የሆነው አርበኛ ደረጀ በላይ ሲሆን ፤ ሁለቱ ደግሞ ከደረጀ በላይ ፊደል የቆጠርን ነን የሚሉ የፋሽስት
ዓብዮት የሚያቀነቅኑ የዘመነ ካሴ ደጋፊዎች “አሳየ ደርቤ” የተባለ
(ቴዲ አፍሮን ከዘረኛው ብርሃኑ ነጋ ጋር በማገናኘት በባንዳነት
(በጸረ አምሓራነት/በጠላትነት/ በመፈረጁ ምክንያት ‘አንድ ተቺ ምን ማለቱ እንደሆነ ባይገባኝም “አማርኛ የሚናገር ዓረብ ይለዋል “አሳየ
ደርቤን” ሲተች)፤
ነገሩን ለማታወቁ አንባቢዎች አሳየ ደርቤ ማለት የዘመነ ደጋፊ ነው፡ አሳየ የተባለው“የዝነኛ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ስም አጥፊ ሲሆን” በቴዲ አፍሮ ላይ የጻፈው ስም የማጠፋት ዘመቻ እንዲሀ የላል፦
«አማራ የመከራ ዶፍ ሲወርድበት በገንዘቡም ሆነ በሀሳቡ ለማገዝ ሞከሮ የማያውቅ አርቲስት ቴዲ አፍሮ በብልጽግና ስፖንሰር አድራጊነት በመላው ዓለም ሊያካሂድ ያሰበውን ኮንሰርት እቃወማለሁ።ከዚህ ባለፈም የቴዲ አፈሮ ኢትዮጵያ ከብርሃኑ ነጋ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን መናገር እፈልጋለሁ» ይላል ስም አጥፊው (አሳየ ደርቤ)::
ሌላው አንሙት አብረሃም የተባለ የዘመነ ABS ዮቱብ ቲቪ ዘጋቢ ነው የሚባለው ሲሆን ፡ እነዚሀ ሁለት የዘመነ ደጋፊ አምሐራዎች “አምሐራውን ከፋሺዝም ወደ ፋሺዝም” ለማሸጋገር እንዴት እንደሚደክሙ ታደምጣላችሁ።
የነዚህ ልጆች
ከተቀሩት ፋሺስቶች ለየት የሚያደርገው ፋሺስታዊ ባሕሪያቸው ፤ ብዙዎቹ ታዋቂ ፋሺስቶች አገራቸውን ይወዳሉ፤ የነዚህ ሁለት ሰዎችና
የመሰሎቻቸው ባሕሪ ግን ሃገር ውዳዶች ኢትዮጰያዊያንን አጠራር በሃገራዊ የስም አጠራራቸው “የአንድነት ሃይሎች” ላለማለት “ኢትዮጵያኒስት” በማለት ከፈረንጅ የተዋሱት ቃላት በመጠቀም “ጸረ አምሐራዊ ሃገርነት”
(“ጸረ የአምሐራ ብሔረተኛነት) የሚንቀሳቀሱ ናቸው በማለት ፤ የአምሐራ
ብሔረተኛነት “የጤነኞች ፖለቲካ” አድርገው በመስበክ የከስዋቸዋል።
በየሚዲያውና ፓልቶክ አምሐራ ወጣቶችና አንዳንድ አረጋዊያን የአምሐራ ምሑራን “በአምሐራ ብሔረተኛዊነት አድፈው በስብሰው ገምተዋል”፡ ለማድመጥ የሚቀፍ የወያኔን ባሕሪ የሚያስንቅ ዘረኛ በደም ጥራትና በክልልነት ዕብሪት የተሞላ ፋሺስታዊ ንትርክ ስታደምጡ “ከፋሺዝም፣ ወደ ፋሺዝም” እየተንጠራሩ እንደሆነ ትታዘባላችሁ።
የገበሬ ዓብዮት (ፒዛንት ሪቮልሽን) ጀማሪና አሰትዋዋቂው ወያኔ የገዛ ራሱን አቁስሎ እንደ ወሻ “የገዛ አከላቱን” በልቶ በስብሶ እንዲገማ ያደረገው ፖለቲካ “ኤትኒክ ናሺናሊዝም” እንደሆነ ለባሞች አትዘነጉትም።
የፋሺስቶች
መለያ ባሕሪ ብዙ ቢሆኑም አራቱ ባሕሪዎቻቸው ማለትም አገር ወዳድነት፤
ዕብሪት ፤ ውሸትና አከራሪነት
የሚታወቁባቸው ጠባያቸው ሲሆኑ ፡
ፋሺስቶች
ሃገሬ ለሚሏት ሃገራቸው ሃገር ውዳዶች ቢሆኑም በዋናነት ውሸትና ጠባብነት
ግን መለያ ባሕሪቸው ነው (ትሬድ ማርካቸው ነው)።
እነ አሳየ ደርቤ ግን ሃገራቸው ኢትዮጵያ እንደገደለቻቸው አድርገው በመመደብ ኢትዮጵያዊነትን በሁለተኛ ደረጃ መድበው “አምሐራዊነትን ይወዳሉ / ያሰቀድማሉ።ቅኝ ገዢውን ለመዋጋት ከወያነ የተላበሱት የአካባቢያዊ አክራሪነት ካባ ለብስዋል።
ኢትዮጰያን ይጠላሉ ፤ ለመጥላታቸው መለያ ደግሞ “እስክንድርን ኢትዮፒያኒስት” (ኢቲዮጵያዊ) (የኢቲዮጵያዊነት-አቀንቃኝ) እንጂ አምሐራ አይደለም/ “የአምሐራ ብሔረተኛ አይደለም” ይላሉ። (የነዚህ ለጆች ንግግር ብቻ ሳይሆን የነዘመነና የተፈራ ማሞ ንግግሮችን አሰታወሱ) “በሔረተኛነት በመስበክ ፤ አሳየ የአንድነት ሃይሎችን ሲጠላና ሲያጠላላ በገሃድ ይደመጣል፡(በቪዲዮው ላይ ሁለቱ ሰዎች ታድመጥዋቸዋላችሁ)።
የልጁ አክራሪነት
ሌላው ጭፍን የፋሺስት ባሕሪው ‘ፈጣጣ ውሸት ሲዋሽ ታደምጣላችሁ። ፋሺስቶች ሰለ መጪው ማሕደራቸው አያስቡም፤ “ትዝብት ላይ እንወድቃለን
አይሉም። እንዲህ ይላል፡ አሳየ ደርቤ የታላቁ አርበኛ እስክንድር ስም ሲያጠለሽ፡
“የእስክንድር ቡድን ተተኳሽ የሚያገኙት አብይ አሕመድ ከሚልክላቸው
ትጥቅ ነው” የድምጽ ቅጂም አግኝተናል ሲል ዓይኑ ሳያሽ አፈጥጦ ይዋሻል።
ይህ ባሕሪ
ካስተዳደጉም ሊሆን ይችላል ፤ከሚከተለው ፖለቲካም ሊሆን ይችላል፡መዋሸት እንደ ነውር ሳይቆጠር “ስለተለመደም” ሊሆን ይችላል፡ ብቻ
አደገኛ የፋሺስት የውሸት ባሕሪ ሳይሳቀቅ ሲዋሽ ታድምጡታላችሁ)።
ሦስተኛው
የፋሺስቶች ባሕሪ “ የሚከተሉት ፖለቲካ ውስጥ የሰብአዊነትና ሃገራዊነት *ዲሰንሲ* ሳይሆን ፖለቲካቸው “የደም ጥራትን ቀጥተኛ የማንነት
የማጣሪያ ወንፊት” አደርገው መታገያቸው አድርገዋል። ሁሉም ነገድ እንዲቀላቀላቸውና “የአምሐራ ትግል ሁሉም ያቀፈ ፤ ጸረ ኮሎኒያሊያዊ ትግል ከማድረግ
ይልቅ “ትግሉ ለአምሐራ በአመሐራ ብቻ” በማለት በደም ጥራት ምርመራ ውስጥ ገብተው ራሳቸውን ለማጽዳት ሲሞክሩ ይደመጣሉ።
ይህ የፋሺስቶች ቀዳሚ መለኪያ እንደ መመዘኛ አድርገው እየተንፏቀቁበት ነው።
ከነዚህ በጠነቡና በበሰበሱ አምሐራዎች የምናደምጠው ይህንኑ “መለኪያ’’ “የፒዛንት አብዮት” ብለው የሚጠሩት ከተሜው በሁለተኛ ደረጃ ተሳታፊ ያደረገ “አብዛኛው ከተሜው እና ገበሬው ታዛቢ በሆነበት የጸጥታ ዓበዮት ወስጥ የትግሉ መለኪያ የደም ጥራት መለኪያ በማድረጋቸው ፤ ወደ “ፋሺስት ዓበዮት” ተሻግሮ የተቀለበሰው ይህ “የሕልውና አበዮት” “ለዓይን በማይታይ ሕሊና ውስጥ የሚፈነዳ ፋሺሰታዊ ቦምብ ልክ እንደ ትግሬና ኦሮሞ ብሔረተኝነት በአመሐራ ወጣት ሕሊና ውስጥ በመቀጣጠል ላይ ይገኛል።
ከሚናገሩት ንግግር የምናደምጠው የወያኔን ሕገ መንግስት በጉልበትም ሆነ በሕጋዊ መንገድ ለማስቀጠል እንደሆነ ብሔር ለመሆን እየጠየቁ እንዳሉና ክልል እንደሆኑት “አፓርታይድ ብሎኮች” እኛም እንደ እናንተው ብሔረተኞች ነንና “እቀፉን” ብለን ተመበረክከን መቅረብ አለብን ፡ ሲል በዚሀ ቪዲዮ ውስጥ ከአሳየ ደርቤ ጋር የሚለፈልፈው አንደኛው የዘመነ ካሴ ደጋፊ (የABS ጋዜጠኛ የሆነው አንሙት አብረሃም) ሲለፈልፍ ታደምጡታላችሁ።
ለምን ብሔረተኛነት ለአመሐራ ሕልውና አዋጪ እንደሆነና እንደመረጠ ሲናገር ወያነና አብይ አሕመድ ያደራጁዋቸው የ36 አመት “አፓርታይድ ተቀባይ” ፋሺስቶች እንደእነሱ (ፋሺት) ሆነን ካልተገኘን የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎች ፤ ነፈጠኞች ፤ የነዚያ ልጆች፤ የምንሊክ ነፍጠኛ ለጆች “ኢትዮጵያኒስቶች” መጡ ብለው "ሲዳሞዎች፤ የበቀለ ገርባ ኦነጋዊ ኦሮሞውዎች፤ ሶማሊዎች፤ ሃዲያዎች ትግሬዎች....አይቀበሉንም የላል።
ንግግሩ ይሚገርም የሕጻን ሕሊና ቢሆንም ይህ የተመብርካኪነትን ባሕሪ ለ37 አመት አምሐራን አስጠቅቷል። ይህ አባባል አዲስ ባይሆንም ' እነ በርሃኑ ነጋ ሲሰብኩበት የነበረው "ሐሞት አስፈቺ (ፍርሐት ቀፍቃፊ) “scaremongering እና principle አስፈቺ ባሕሪ" አሁን በዚህ ልጅ ፕሮፓጋንዳም ተደገሞ ተመበርካኪዎች ሲሉት የነበረው «የአንድነት ሃይሉ ምን አቅም ኑሮት ነው ይሚንጠራራው “ኦነጎችን አናሰቀይም"»፤ ሲሉን የነበሩት እንደ እነ ዶ/ር ጌታቸው መካሻ የመሳስሉ፤ "አምሐራ የኦሮሞን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለበት" ሲሉ የነበሩት እነ “ዘላለም” እና የመሳሰሉ የተመበረካኪ አምሐራዎች ባሕሪ በመድገም ነው አንሙት አብረሃምም እዚህ ቪዲዮ ወሰጥ ሲናገር የምታደምጡት።
የአምሐራ
የ45 አመት ትውልድ እርግጥ መበስበሱን ይህ ዋና ማሳያ ነው። 36 አመት የአመሐራን ሕዝብ ያስቀጠቀጠውና ሐሞቱን ያስፈታው እንዲሀ
ያሉ ተምበርካኪዎች በመበራከታቸው ምክንያት ነበር። እንዲህ ያሉት ወጣቶች በዛ መራራ ትግል ልሳናቸው አሁንም እንደ ገደል ማሚቶ
ሲጮሕ በዚኀ ጋዜጠኛ ምላስ መራራው ትውስታችን ይመጣል።
ፋሺስቶች እንዲያደመጡህና እንዲቀበሉህ ፋሺስትነት መከተልን ለምን ውጤት? እውነት ፋኖ ከተመሠረተ ወዲህ ይህ እሰማለሁ በየ ገምቸው አላውቅም።
እኛ የህንን ብሔረተኛነት የሚንድ ትግል እንዲጠናከር አምሐራውን ስናነቃ የዘመነ ደጋፊ ቡደኖች ደግሞ
የህወሓት/ኦነግ ሕገ
መንግስት እንዲቀጥልና ሕልውናውን ለማስቀጠል “የአምሐራ ሕዝብ” ታማኝነቱንና
ድጋፉን ለተቀሩት “ብሔር ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች” ተብለው ወያነና ኦነግ የፈጠሯቸው የአፓርታይድ ፋሺስት ክልሎች እውቅናውን መሰጠትና መለማመጥ አለብን የላል።ካልሆነ
የነዚያ የምኒልክ ልጆች የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎችና የነፈጠኞች ልጆች
ሊሉን ነው የላል።
እንዲሀ ያለ ነውር “ተምበረካኪነት” አምሐራውን ክ50 አመት በላይ ሲያሠጭፈጭፈው ከርሞ ዛሬ ጠመንጃ ታጠቆም እነሆ “ለብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” “እንምበርከክ” ይላችኋል የእነ ዘመነ ካሴ ቡደን ጋዜጠኛ አንሙት አብረሃም።
ለዚህ ነው የበሰበሰ አፕል በስብሷል ተብሎ ካልተጣለ፡ በስመ “አፕል”፡አግበስብሶ በበሰበሰ አፕል ላይ ክምር የበሰበሰ አፕል በትከምር ጤናማ አፕል አያመጣም የሚባለው!
ሰለዚህም
ነው በነዚህ ዓይነቶቹ የበሰበሱ አምሐራዎች “በበሰበሰ አማራ ላይ፣ የበሰበሰ አማራ ፣ ሲያሻም እልፍ አእላፍ የበሰበሰ ሌላ አማራ ጨምሩበት--- ብዙ የበሰበሱ አማራዎችን ማከማቸትና ማስታጥቅ
ይችላል እንደሆን እንጂ- ጥሩ ጤናማ አማራ ግን በጭራሽ አያመጣም!
ለዚህ ነው ውድ መምሕሬና ወዳጄ በሞት የተለዩን ሊቀ ሊቃውንቱ የፖለቲካ ሳይንስ ፤ የታሪክና የጥንት
ጥናት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዓለሜ እሽቴ እንዳሉት፦
“A
Rotten Apple, plus a rotten apple, plus a rotten apple---you may continue
adding up more rotten apples—will Never Produce a Good Healthy Apple!” በማለት “ቅድሚያ
የሀገሪቱን አደጋ ፋሺዝም መሆኑን ተገንዝቦ የራሱና የሀገሩን ሕልውና ሳይነጣጥል እንደ ዱባ ተንሰራፈቶ ካለው የፋሺስቶች አደጋ ለመዳን
“ኢትዮጰያዊነትን” የትግሉ ዋና መርሕ የማያደርጉ ጥርስ አልባ ተቃዋሚዎችና ‘ክልል አፈቃሪ’ ቡደኖች በቁጥር ቢበራከቱም ለሃገራችንና
ለሕዝቡ ሕልውና “ፋይዳ” እንደሌለው የገለጹት አገላለጽ ነበር።
ሰላም ሰንብቱ
ኢትዮጵያ የመታገያችን ዘንግ ነች!
ቪዲዮውንም ይኸው አድምጡ
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment