Saturday, May 31, 2025

ተፈጥሯዊ ድፍረስና ጌታቸው ረዳ 5/41/25

 

ተፈጥሯዊ ድፍረስና

 

ጌታቸው ረዳ

 

5/31/25

በዚሀ ቪዲዮ የምትመለከቱት ድምፀት ምክንያቱ በማይታወቅ በሰው ልጆች ላይ የሚከሰት “የተፈጥሯዊ ድፍረሰና” ክስተት ነው። በአምሐራ ሕዝብ ላይ ጥላቻውን ያለምንም ይሉኝታ በተከታታይ በዩቱብ ሚዲያና በቲክ-ቶክ ሚዲያዎች እያሰራጨ ያለ ይህ “ማደግ ያቃተው ህጻን” “ናትናል አስመላሽ” ይባላል።

እንደምታስታውሱት በቅርቡ ህዳር 2012 ላይ የትግራይ ፋሺስቱ ድርጅት ህዝባዊ ወያነ ርነት ትግራይ (ህወሓት) በኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ዋና መምሪያ በሚገኘው በመቀሌ እና ሌሎች ካምፖች ላይ ድንገተኛ የጭፍጨፋ ጥቃት በመሰንዘር የትግራይ ጦርነት መቀሰቀሱ የታወሳል።

በጦርነቱ ወቅት የአብይ አሕመድ አጨብጫቢ ሆኖ በመገኘት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጰያ በመሄድ በአብይ አሕመድ  ሚዲያዎች ላይ እየተገኘ ስለ ወያኔ  እርኩስነት  ቃለ መጠይቅ በማድረግ አሁን እያሞካሸው ያለውን ወያና ተዋጊዎቹን “ተደምስሰው መጥፋት አለባቸው” እያለ አብይን “መሪያችን“ በማለት የሚያወድስበት ቃል እስኪያጥረው  ድረስ ሲያሞካሸው እንደነበር በዙዎቻችሁ ታስታወሳላችሁ።

አሁን ደግሞ “የኢሳያስ ነፃነት” ለማክበር ወደ አስመራ በተደጋጋሚ በመሄድ  ሰለሞን ተካለኝ የመለስ ዜናዊን ቅንድብ በማድነቅ “ቅንድቡ” እያለ እንደዘፈነለት ሁሉ አሁን ደግሞ ይህ ልጅ “የኢሳያስ ርዝማኔና ቁመና” እንደ ሴት በማድነቅ “እያፏሸገ” አብይ አሕመድን ሲያጠላላ ይደመጣል።

 እርግጥ ልጁ የፖለቲካ ድንቁርና ያጠቃው “እዚሀ ግባ የማይባል ያልበሰለ” በመሆኑ በልጁ ላይ ዝርዝር መጻፍ አንባቢን ማሰልቸት ስለሚሆን ቪዲዮውን በቻ ማድመጥ ይበቃል።

 “ፋሺቶች” ከሚጠቀሙባቸው “የውስጥ ሙታንታ አጣቢዎቻቸው” (የሃብታሙ አያሌው አገላለጽ ልዋና) እንዲሀ ያሉ “አገልጋዮች” በማሰማራት መልእከታቸውን ያሰራጫሉ (አምና አበይን ሲያገለግል ነበር ፤ ዛሬ ደግሞ ወያኔና ሻዓብያን እያገለገለ ነው)።

እንዲህ ያሉ “ተፈጥሯዊ ድፍርስና” ያጠቃቸው ሰዎና ርጀቶች ወዳጄ ይነጋል፤እንዲህ ይገልጻቸዋል፦

 «በኢትዮጵያ የዘመናችን ድፍርስና amorphous ፖለቲካ እንደወያኔና እንደ ኦህዲድ ሥነ ተፈጥሯዊ ብልሽት የሚገርመኝም ሆነ የሚያሣዝነኝ የለም፡፡» ይላል።

እንዲሀ ያለ “ተፈጥሯዊ ድፍርሰና” በዚህ ልጅ ስታደመጡ ይህ ልጅ አያሳዝናችሁም?

Ethiopian Semay

No comments: