27 በትግሬዎች 6 ዓመት በኦሮሙማ ኦሮሞዎች የሚያዙት አየርመንገድ መንገደኛን በማስለቀስ ዕርግማን እየደረሰበት ያለው
የአየርመንገዱ የፓስፖርትና ደህንነት ክፍል
ክፍል 1
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
3/13/25
ቪዲዮውን ብቻ እንኳን ስትመለከቱ ያች አገር ባለጊዜዎቹ እንዴት እየተጫወቱባት እንደሆነማ እዩልኝ! እግዚሔርም ኢትዮጵያም “ተጠልፈው” ተይዘዋል የምንለው እኮ ለዚህ ነው! ኦሮሙማ እና ትግራዋይነት ማለት ከዚህ ትርጉም ሌላ እስኪ አምጡልኝ? አገሪቱ እኮ እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ተጫውተውባታል። በዚህ ክፍል 1 የምንመለከተው ኢትዮጵያን ላጭር ጊዜም ቢሆን መንታ መንግሥት በመሆን የትግሬዎች የነበረው አየርመንገድ ለመጎብኘት ጠ/ሚኒስትር ጃዋር መሐመድ ቦሌ አየር መንገድ ሲጎበኝ አየር መንገዱ ለኦሮሞዎች እንደሚተላለፍ ስላወቁ የወቅቱ ሓላፊዎቹ እንዴት ተሽቆጥቁጠው ጠ/ሚኒሰትር ጃዋር መሐመድን ይሰግዱለት እንደነበር በዚህ የቪዲዮ ማስረጃ እንመለከታለን።
በክፍል 2 ደግሞ ቦሌ የአብይ አሕመድ አየርመንገድ የፓስፖርትና የደህንነት ፍተሻ ሠራተኞች በተጓዥ መንገደኛ ላይ እያደረሱት
ያለው ግፍ የሕዝብ ዕርግማን እንመለከታለን።
ከ8 አመት በፊት ወዳጄ ይሄይስ አእምሮ “የኢትዮጵያ ወይንስ የትግራይ አየር መንገድ?” በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ አስተናግዶን
እንደነበር ይታወሳል። በዚያ ጽሑፉ ውስጥ አየርመንገዱ ውስጥ የሚሰራ አንድ ውስጥ አዋቂ ያጫወተውን ምስጢር በመገረም ነበር የጀመረው
እንዲህ ሲል፤
የ2008ን
የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ
አንድ <<የኢትዮጵያ ይሁን የትግራይ
ውሉ ባልታወቀ አየር መንገድ>>
ውስጥ የሚሠራ ሰው በቤቱ
ምሣ ጋበዘኝ፡፡ …በሀገር ተቆርቋሪነት
ስሜት በቀድሞው አጠራር ስለኢትዮጵያ
አየር መንገድ በአሁኑ ደግሞ
ስለ”ትግራይ አየር መንገድ”
እየተንገፈገፈ ሲናገር አደመጥኩ፡፡
ኢትዮጵያዊ
የሆንክና አሁን የምነግርህን ከአሁን
በፊት ያልሰማህ ሁሉ ይህን
የወያኔዎች ቅሌት ልብ ብለህ
ስማ! ኢትዮጵያ ዳግመኛ እንዳታንሠራራ
ሆና በወያኔ መዶሻ እየተቀጠቀጠች
ነው።
ካለ በሗላ የተነገረው ታሪክ እንዲህ ይገልጻል፤
<<ባለፈው ሰሞን
አየር መንገዱ 27 ሆስተሶችን (የሴት
አስተናጋጆችን) አስመርቋል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ
ሃያ ሰባቱም ትግሬዎች ናቸው፡፡
አዲስ አበባን የማያውቁና ብዙዎቹ
አዲስ አበባ ውስጥ ቤተሰብ
የሌላቸው ፍጹም ባላገር ሴቶች
ናቸው፡፡ የተቀጠሩት ሁሉም ከትግራይ
ምድር ነው፡፡ ለመሃላ እንኳን
አንድም የሌላ ዘውግ አልተቀላቀለባቸውም
– ቴክኒሻንና አብራሪም ሲመለመል እንዲሁ
ነው፡፡ ከነዚህ ሆስተሶች ብዙዎቹ
ዐማርኛ ቋንቋ አይችሉም፤ እርግጥ
ነው – ከልጅነት እስከ ዕውቀት
ዘመናቸው ዐማርኛ ከሚወገዝበት ክልል
ተወልደውና አድገው የመጡ ወጣቶች
በመሆናቸው በነሱ አይፈረድም፡፡ ነገር
ግን የአየር መንገዱ አንደኛው
የሥራ ቋንቋ የሆነውን ዐማርኛን
ባለመቻላቸው ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ
– ማኅበራዊነት (ሶሻላይዜሽን) ስለሚጎድላቸው ደግሞ
ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በቀላሉ
መግባባት ካለመቻላቸውም በተጓዳኝ ቋንቋ
አለመቻላቸው ሥራቸው ላይ ትልቅ
አሉታዊ ጫና እየፈጠረባቸው ነው፡፡
አንድ
ተጨባጭ ምሣሌ እንይ፡፡ በውነቱ
ሕወሓት የትግራይ ሕዝብ በቀጣይ
ታሪኩ እጅጉን የሚያፍርባቸው ብዙ
ሰቅጣጭ ተግባራትን እየፈጸመ ነው፡፡
ስለወያኔ ትግሬዎች ሁላችንም ማፈር
አለብን፡፡ ሃያ ሰባቱም ትግሬ?
ውይ …ው ይ….ውይ…!>>
ኢልና በመቀጠል ኤርምንገዱ አየር ላይ እየበረረ ሳለ የሆነውን እንዲህ ሲል ያጨውተናል፤
<<ባለፈው አንድ ጊዜ
ወደ አፋር
ዋና ከተማ ወደ ሠመራ አንድ የሀገር ውስጥ
በረራ ነበር፡፡ አንዷ ዐማርኛ
እንደቁመት ያጠራት አስተናጋጅ ትግሬ
“ሕዚ ናብ አሥመራ ስለዝተቃረብና ለቀቦቷቹ አጣብቁት>> በማለት ለተሣፋሪዎች ማስታወቂያ
በመናገሯ ተሣፋሪዎችም አውሮፕላኑ ተጠልፎ “አሥመራ” ገብቶ ነው በሚል ተደናግጠው ክው ይላሉ፡፡ በኋላ
ግን የቋንቋ ችግር መሆኑ ተነግሯቸው “አሥመራ” ሣይሆን “ሠመራ” እንደደረሱ
ተገልጾ ይቅርታ ተጠይቀዋል – ተሣፋሪዎች፡፡>>
እያለ አየርምንገዱ ከአብራሪዎች እስከ ተራ ሰራተኛና ሆስቴስ በትግርኛ ተናጋሪዎች እንደተሞላ ያወጋው የአየር መንገዱ
ውስጥ አዋቂ ያወጋውን አካፍሎናል።
ከዚህ ተነስቼ እንደምታዘበው
ይህን ጉዳይ በሚመለከት ችግር
የለም ብሎ ማለት ፈጣጣው አውነት መካድና ራስን ማታለል የዋህነት ነው።
ለዚህ ነው “ከ27 አስተናጋጅ
አንድ ሰባት ያህል እንኳን
ለማስመሰል ከሌላው ብሔር ቢቀላቀል
ምን ነበረበት?” እያለ አግራሞቱ ያጫወተን።
ትግሬዎች በወቅቱ (የዛሬ አያድርገውና) በዕብሪት ተነፍተው ሃይ የሚላቸው አንድም
ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ አካል
አልነበረም። ለዚህም ነው “የኢትዮጵያ
አምላክ” እየተባለ የሚንቆለጳጰሰው አምላከ
ሰማይ ወምድር ምን ሆኖ
ነው እንዲህ በኛ ላይ
የጨከነው? ምን ኃጢኣተኞች ብንሆን
አለርህራሄ እንደክርስቶስ ይህን ያህል
እንድንወገር መፍቀዱ ለምን ይሆን?
ሲል ወዳጄ የሚብከነከነው።
ያውም እኮ “ሀገረ ማርያም ኢትዮጵያ
በነዚህ ጥፍራም ወያኔዎች ስትጠፋ፣
ባልተገራ ብልግናቸው እንዲህ ሲጨመላለቁብን
በውነቱ ፈጣሪ በመንበሩ ካለ
እንዴት አስቻለው? በትምህርትም ሆነ
በልምድ እዚህ ግቡ የማይባሉ
27 ባላገር ትግሬዎች በዘረኝነት
ከአንድ ክፍለ
ሀገር ተለቅመው ይህን በዓለም
አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የነበረ
አየር መንገድ እንዲቀላቀሉና በዘረኝነት
ግማት እንዲያከረፉት ከተደረገ በሌላው
ማኅበራዊና መንግሥታዊ ተቋምማ ከዚህ
የበለጠ ወንጀል እንዴት አይሠራ?”
ሲል ነበር የጠየቀው።
የዘረኛነት አድሎአዊ አሰራራቸውም ስለገረመው ፈጣሪ እንዳገቱትም መጠራጠሩ እንዲህ
ገልጾት ነበር
<<ወያኔዎች ፈጣሪንም አግተው
እንደያዙ አሁን አሁን መጠራጠር
ጀምሬያለሁ፤ እንዲያ ባይሆን ይህን
ሁሉ ግፍ እየሠሩ ሃይ
የሚላቸው ባልጠፋ ነበር እላለሁ፡፡
…. በርግጥም ለኢትዮጵያ አሁን ያልታዘነ
መቼም አይታዘንላትም፡፡ 27 ሰው ከአንድ ቀየ?
የመንግሥት ተቋማትን ሁሉ በአንድ
ክልል ሰዎች ማስያዝ?
27… ወይ
መድሓኔ ዓለም… ምኑን አመጣህብን፤
ምን ጉድ ነው እያሳየኸን
ያለኸው… ለማንኛውም እግዜሩን እግዜር
ይይለት>> ፤በማለት ምሬቱን መቋጨቱን አስታውሳለሁ።
ያ እሮሮ ገና ሳይደርቅ ኦሮሞዎቹ እነ ጠ/ሚኒሰትር ጃዋር እና እነ ጠ/ሚኒሰትር አብይ አሕመድ ያንን ዙፋን ተረክበው
በትግሬ ተይዞ የነበረው አየርምንገድ ለኦሮሞዎች ተላልፎ ትግሬዎቹም በተራቸው በሰፈሩት ቁና ለመሠፈር በላያቸው ላይ
<<የቀን ካብ ፎርሶባቸው” ለኦሮሞዎቹ ለባለጊዜዎቹ ለቀው
መስገድና መሽቆጥቆጥ ጀመሩ። ቀን አይፍረስብህ የሚባለው ለካ እንዲህ ነው።
በክፍል ሁለት ደግሞ ዛሬ ቦሌ ላይ ኦሮሞዎች የሚያዙት
አየርመንገድ መንገደኛን በማስለቀስ ዕርግማን እየደረሰባቸው ያለው የአየርመንገዱ ጉቦኞቹና ዕብሪተኞቹ የፓስፖርትና የደህንነት ክፍል ሠራተኞች ሰሞኑን በክፍል 2 እንመለከታለን።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment