አፓርታይዳዊው የኦሮሙማው ሥርዓተ ዘመን የፓስፖርትና የደሕንነት ክፍሎች በተጓዦች ላይ እያደረሳችሁት ያለው ሰቆቃ እግዚአብሔር አምላክ ድፍት ያርጋችሁ!!!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian
Semay
3/15/25
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian
Semay
3/15/25
ስለ ቦሌ አየርፖርት እና ስለ ዋናው “የፓስፖርት እና ኢሚግረሺን” መ/ቤት ጉቦኛነት በሕዝብ ሕይወት ላይ እያደረሱት ያለውን ስቃይ ከመግባቴ በፊት ለዚህ ሁሉ ብልሹ አሰራር ተጠያቂው የዛሬው <<ሥርዓተ ኦሮሙማ>> እና የተወገደው <<ሥርዓተ ትግራዋይነት>> የአመራር ብልሹነት እንደሆነ አንድ ነገር ብየ ወደ ዋነው ርዕስ እገባለሁ።
ባለፈው በአፓርታይዳዊው የትግሬዎች ሥርዓተ ዘመን እና አሁን ደግሞ 6 አመት
ያለንበት ኦሮሙማዊው የኦሮሞዎች ሥርዓተ ዘመን ሥራየ ብለው ኢላማ ያደረጉት በተለያዩ ‘የመንግሥት’ ዘርፎሮች ሕዝብን በማስለቀስ የተጠመዱ ናቸው።
ሁለቱ አፓርታይድ ሥርዓቶች አፓርታይድነታቸውን የተገበሩት በተለይም በአምሐራ ሕዝብ ላይ (የጋሞዎችን እንዲሁም የጉራጌዎችን ስቃይ ሳንረሳ ማለት ነው) ሲሆን ሁለቱ አፓርታይዶች እየተፈራረቁ ያደረሱትን በደል አሁን ግልጽ እንደሆነላችሁ እገምታለሁ።
የኦሮሙማ እና ትግራዋይነት
ትርጉም ደጋግሜ እንድንነጋገርበት ሁሌም የምጽፈው ከምንም ተነስቼ አይደለም። ምክንያት አለኝ። ሁለቱም ቃላቶች በጥሬ አተሮጓጎም
እየተተረጎሙ የሚነገሩ ትርጉሞች ብዙ የዋሆችን ለማታለል ተሞክሯል። ሃቁ ግን ሁለቱ ማሕበረሰቦች እንደ “መከታችን” ናቸው ብለው
የሚከተልዋቸው ድርጅቶች አሉዋቸው። ሁለቱ ድርጅቶች ደግሞ ትግሬው (በትግራዋይነት) ኦሮሞዎቹ ደግሞ (በኦሮሙማ) ርዕዮት የሚመሩ
ናቸው።
ሁለቱም የሚመሩበት
ማኒፌስቶ “ፋሺዝም” ነው።
ሌላ ቀርቶ ሁለቱ
ማሕበረሰቦች የሚከትለዋቸው የተለያዩ ሃይማኖቶቻቸው ሳይቀሩ ጭምር ከማንኛቸውም ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ይልቅ ግንጠላንና ጥላቻን ለሚሰብኩ
<<ለኦነጎች/ ኦፒዲኦዎች እና ለወያኔዎች>> ከፍተኛ ድጋፍና ፍቅር እንዳላቸው የሚያከራክር አይደለም።
ኦነግ ማለት ለዘመናት በብዙሓኑ የኦሮሞ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ድርጀት ነው። <<ኦነግ ማለት ኦሮሞ>> <<ወያነ ማለት ትግራይ ሕዝብ ነው>> ስል የከረምኩነት ክርክር ሁለቱ ማሕበረሰቦች ከሚከተሉትና ከሚሰጡት ድጋፍ በመነሳት ነው። በቁጥር ብዘሓን የሚባሉት ትግሬዎችም ሆኑ ኦሮሞዎች “ወጣት የዕድሜ ጣራ” ያለ ክፍል ነው። ወጣቱ ደግሞ የነዚህ ድርጅቶች አማኝ ነው።
ስለሆነም ርዕሱ ለይ የጠቀስኩት ቃል <<ኦሮሙማ>> በየዋህ
ተርጉሙ ሳይሆን በሚወስዱት “መንግሥታዊ” እርምጃ እና ፖለቲካዊ ትርጉሙ ዘመናዊ ትምሕርት በቀሰሙ የኦሮሞ ተገንጣይ “ምሁራን” እምነት
(ኦነገ መሪዎች ዳውድ ኢብሳ ዲማ ነገዎ፤ ሌንጮ …ጫልቱ….ብዙዎቹ አብይ በሚመራው ኦሮሙማዊው መንግሥስት ሥር ዛሬም እፓርላመውም
ሆነ በሚኒሰትሮች ደረጃ ሥልጣን ላይ ሆነው ፖለቲካዊው የኦሮሙማው አጀንዳ በመተግበር ላይ ናቸው) “ኦሮሙማ” የሚል ቃል ሲተረጉሙት <<ኦሮሚያን በቅኝ ግዛት የያዘው የአቢሲኒያ (ኢትዮጵያ)
ተስፋፊነት ማለትም የቢሲያኒ ሃበሻዎች ሥልጣኔ ባሕል ፤ቋንቋ፤ እና ሃይማኖት የሚጻረር ነጻ አሮሚያ ለመመስረት የምንጠቀምበት አታጋይ
መርህ ነው>> በማለት << (ኦሮሙማ) ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ
በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን የዐምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ
ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ ይታይ ነው።>> ሲሉ በግልጽ ነግረውናል።
አንዳንዶቹ ደግሞ <<ኦሮሞነት>> ማለት እንጂ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጻረር ባሕሪ ነገር የለውም ሲሉ ሰምተናቸዋል። ከላይ ያለው የመጨረሻው አባባል የዋሃን ሊያታልል ይችል እንደሆን እንጂ ከሥር መሠረቱ የቃሉ አመጣጥና የቃሉ ለውጥ ከጥንት የተጻፉ መጻሕፍት ስንመረምር እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን ትርጉም ያለው የዜግነትና ሌላ ሃገርነትን የሚመኝ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የሚያልም አጠራር ነው።
የትርጉም ጉዳይ በዚህ
ከሄድንበት አሁን “ፍንፍኔ እና ሥልጣን ኬኛ” ብሎ በኢ-ሕጋዊ አያያዝ ሥልጣን የያዘው የኦሮሙማው ቡድን <<የፓስፖርትና
የደህንንት ክፍል>> (ኢሚግረሺን እና ፓስፖርት) ብሎ ራሱን የሚጠራው ኦሮሞዎችና ኦሮሙማው ሥርዓት የሚያገነብሱ የተሰገሰጉበትና
የሚቆጣጠሩት ድርጅት ከዋናው ጽ/ቤቱ
ጀምሮ ቦሌ ላይ ያቋቋመው ቅርንጫፉ ዘርን (ነገድ ማለት ነው) በተለይም ትግሬዎችን እና አምሐራዎችን እየለየ ጉቦ ለመቀበል እንዲያስችለው
ተጓዡ ለበረራው አንድ ወይንም ሁለት ሰዓት ሲቀረው “ፓስፖርታቸውን እየነጠቀ>> ጉቦ እንዲሰጡ ልዩ ቦታ በማሰር ያሰቃይዋቸዋል። አንዳንዱም
እንደሚገርፏቸው ይነገራል።
ባለፈው ጥቂት ወራት
የአንድ ወዳጄ ባለቤት ከዚህ ወደ አገርቤት ሄዳ ስትመላስ የገጠማትን ልንገራችሁ። ከወራት በፊት አገር ቤት ሄዳ ተመልሳ ወደ አሜሪካ
መምጣትዋን ታስታወስና እንደገና ተመልሳ ለሁለተኛ ጊዜ እንደ እናትዋ የምታያቸው የባለቤትዋ እናት “በማረፋቸው” ለቀብር መሄድ ስለነበራት አንደገና
ተመልሳ በመሄድዋ የቦሌ አያርፖርት የፓስፖርት ሰውየ በነገዱ <<ኦሮሞ>> የሆነ መጀመሪያ ያነጋገራት በኦሮምኛ
ሲሆን <<አዝናለሁ እኔ ኦሮምኛ አላውቅም ትግርኛ ወይንም አምሐርኛ ነው የማውቀው፤ ምን እንዳልክ አልገባኝም>>
ብላ ስትለው፤ <<ጊዜሽ አልፏል
በግድ ኦሮምኛ አማወቅ አለብሽ፤ ለመሆኑ ምን ምስጢር ስላለሽ ነው የምትመላለሺው? >> ሲል
ይጠይቃታል።
ልጅትዋም << ተደናግጣ ፤ ምንም ምስጢር የለኝም አገሬ ነው ፤ መመላለስ አልችልም እንዴ? አሁን የናቴ ቀብር ፈጽሜ ወደ አሜሪካ እየተመለስኩ ነው>> ብላ ስታስረዳወ <<አገርሽ አሜሪካ ነው በማለት “ፓስፖርትዋን” ነጥቆ “ስልክዋን እና ዕቃዋን ነጥቆ” ብዙ “የሶርያ ተወላጆች” በታጎሩበት ማጎርያ እስርቤት ወስዶ በረራዋን አስሰርዞ ሙሉ ቀን አስሮ ሲመሻሽ መጨረሻ አንድ ደግ ሰው ሰልክ አሾልኮ እንድትደውል ስላደረገ፤ ቤተሰቦችዋም መብረርዋን እንጂ “መታገድዋን” ሳውቁ ደንግጠው ሁኔታው ከነገረቻቸው በሗላ፤ ጉዳዩ የዘር ጉዳይና “ጉቦ” መሆኑን ስለተረዱት ልጅቷ ወደ አሜሪካ ወደ ሥራዋ በአስቸኳይ መመለስ ስለነበራት ፤የመክስስና ከባለጊዜዎች ጋር መነካካት እዛ ለሚኖሩ ቤተሰብ አደጋ ስሰለሚኖሮው ሰግተው አማራጭ የወሰዱት መነገድ “ኦሮሞ” የሆኑ የሚያውቋቸው አንድ ጎረቤት ሰው ወደ ቦታው ይዘው በመሄድ “ፓሰፖርቱን” የያዘው የፓስፖርትና የደሕንንቱ ሰውየ ዘንድ በመሄድ “ስለ ጉዳዩ በመነጋገር፤ በማግስቱ እንደ ሚጋብዙትና በአንድ የግብዣ ቦታ እንደሚገናኙ ተቀጣጥረው፤ ልጅቷን አስፈትተው በማግስቱ ተገናኝተው ለሰውየው “ጉቦ” ሰጥተው “ፓስፖርትዋን” በኪሱ ይዞ እንደሚመጣ ስለነገራቸው ፓስፖርቱን መልሶላቸው ካሰበቺው የመብረር ቀን ተሰናክላ እንደገና ጊዜ ጠብቃ ልጅቷ ሌላ በረራ ፈልጋ ወደ አሜሪካ መመለስዋን ነገረችን።
በየአመቱ 25 ሚሊዮን መንገደኛ የሚጓዝበት የቦሌ አየርፖርት “ሕገ ወጥ ዕጽ” አመላላሾች ምቹ የማሸጋገሪያ መስመር መሆኑን በብዙ ዜናዎች መዘገቡን እንዳለ ሆኖ፤ ቦሌ ላይ የሙስና አሰራር በማንኘውም ኢትዮጵያዊ እና የውጭ አገር ተጓዥ የገንዘብና የወርቅ ዝርፍያ ቦሌ ላይ እየደረሰባቸው እንደሆነ በየጊዜው ሪፖርት እየተደረገ ቢሆንም በተለይ ግን መንገላታቱ የሚበረታው “አምሐራዎችና ትግሬዎች” ላይ ከፍኛ በደል በኦሮሞ ተናጋሪ “የፓስፖርትና ኢምግረሺን” ሠራተኞች አማካይነት መሆኑን በተደጋጋሚ የደረሰ ያለ በደል ነው።
አየርፖርቱ ይህንን
አስመልክቶ ከጥቂት ወራት በፊት <<“መስፍን ጣሰው” ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ>> ወደ
ሚዲያ ቀርቦ የተነጋረውን እዚህ ላስታውሳችሁ እንዲህ ይላል፡
<<አንዲት
መንገደኛ ወደ አሜሪካ ስትሄድ ‘ፐርሰናል ቫሊዩ’ ይዤ ነበር “ወርቅና ዶላር” ይዘሽ መውጣት አትችይም ተባልኩ፤ ከብዙ ውጣ ውረድ
እንግልት በሗላ “ዶላሩን ወስዳ ሌላውን ለቀቀቺሊኝ” የሚል ክስ ነው የቀረበው። በጊዜው ይሄ መረጃ እንደ ደረሰ “በ ሲ ሲ ቲቪ”
ታይቶ ሠራተኞቹ ተለይተው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ሕጋዊ ክስ ይመሰረትባቸዋል፤
አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃም ይወሰድባቸዋል።በነዚህ “ጉምሩክ ካስተም” ሕጋዊ እርምጃ ይወስድባቸዋል ብለን እናስባለን።>>
ማለቱ ይታወሳል።
አቶ መስፍን መግለጫውን ሲያጠቃልል በደምበኞች ላይ ለሚደርስ በደል የቅሬታ
ማቅረቢያ “ዴስኮች” ፈጥረናል ፤ በጥቂት ቃናት ውስጥ ሥራው ይጀምራል።>> ሲል ጉዳዩ ለማስቆም የተደረገ ጥረት መኖሩን
ከሥራ አስኬያጁ ቢነገርም፤ ዛሬም ጉበኞች ተጓዡን እያሰቃዩት ነው።
የቅሬታ “ዴስክ”
ቢዘጋጅም ደምበኞች ለወፊቱ ሲመለሱ በነሱና በቤተሰቦቻቸው “ሪቨንጅ”
(የብቀላ ጥቃት) እንዳይደርስባቸው የሚሰጉ ስለሚኖሩ እውነት ኦሮሙማው ሥርዓተ መንግሥት ይህንን በደል ለማስቆም ፍላጎት ካለው የደምበኛ
ቅሬታ ማቅረቢያ ክፍል (ዋናው ኢሚግረሺን ውስጥ የለም) ኤርፖርቱም ውስጥ ካለም << ከደምበኛች ቅሬታ መቀበሉ በጎ እርንጃ
እንዳለ ሆኖ፤ ሌላ ተጨማሪ ሃሳብ ላቅርብ፡
ይሄውም ”የሚመለከታቸው
ድርጅቶች” <<አንደር-ካቨር>> (የምስጢር ሰራተኛ) ተራ መንገደኛ አስመስሎ ወርቅና ዶላር አስይዞ አንዲያልፍና
“ጉበኛ ሠራተኞችን” እንደ ዓሳ ለማጥመድ እንዲመቸው ምስጢራዊ (አንደር ካቨር ፖሊስ) ማዘጋጀት ይኖርበታል። ካልሆነ “ቅሬታ ማቅረቢያ”
ሳጥን እና ክፍል ብቻ ሙሰኛን ለማስቆም በቂ አይደለም። በተለይ በዋናው መስርያቤት የሚታየው አስለቃሽ የፓስፖርት ዘረኛ አሰራር
የምንሰማው ዕሮሮ አሳሳቢ ነው።
በተረፈ ወደ አረመኔዎቹ የዓረብ አገሮች በባርነት እየሸቀሉ ያጠራቀሙትን ጥቂት
ገንዘብና ወርቅ እንዲሁም ሻንጣ እየዘረፉ እህቶቻችንን ደም የሚያስለቅሱ ጨካኞች ‘ልጅቷ እንዳለቺው’ <<እግዚአብሔር አምላክ
ድፍት ያርጋችሁ!!!!>>
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment