የናዚዎች ሥርዓተ ትምህርት በኢትዮጵያ የሥርዓት ትምህርት መማርያ መጽሐፍት የመካተቱ አስደንጋጩ ክስተት!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
3/23/24
በአገር ውስጥ ተባባሪዎች ምክንያት በቅኝ ግዛት አስተዳዳሪዎች ስር ነን እያልኩ መጻፍ የጀመርኩት ኢትዮጵያ በዘመዶቼ ትግሬዎች በ1983 በቁጥጥራቸው ሥር ከወደቀቺበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ያኔ አድማጭ አልነበረም (ድድብና ይዞት ነበር) ፡ ዛሬም አድማጫችን ከያኔ ቢሻልም አገራችን በቅኝ ባዕዳዊ አስተሳሰብና ጸረ ኢትዮጵያ በሆኑ ቅጥረኞች እየተገዛች መሆንዋን ለማመን የተቸገሩ ብዙ ሚሊዮኖች አሉ (ያውም ምሁራን ናቸው)፡፡ በዛው ቀምበር ጫማ ሥር ከወደቅን አሁን ወደ 35 አመት ሆኖናል፡፡ ምሕረቱን ያውርድ!!
ችግራችን የማያነብ ትውልድ ላይ ሆነን ሁኔታዎችን ለማስረዳት በጽሑፍ ስናስረዳ ስንት አንባቢ እንዳለን ስንመለከት ውጤቱ አሳዛኝ ቢሆንም ከማስተማር አልቦዘንም፡፡
ዛሬ የማቀርብላችሁ በኡሉመናቲና በአለም አቀፍ የናዚ ቅጥረኞች ኢትዮጵያዊያን መገዛታችንን
በሥርዓተ ትምህርት መጽሐፍት ውስጥ ምን እንደተጻፉና ተማሪዎቹ
የወላጆቻቸው ልጆች ሳይሆኑ የመንግሥት ልጆች መሆናቸውን ፤ ሰው ናችሁ እንሰሳ
ናችሁ ብየ የምወስን እኔ መንግስታችሁ እንጂ ሌላ ፈጣሪ የላችሁም፡*ሥልጣኑ ያለው በመንግሥት እጅ ነው፡፡ ዜጎች መሆናችሁንም የውልደታችሁ ፈቃጅና ከልካይ
ብቸኛ ፈጣሪያቸሁ ''አሃዱም ክል ኤቱም ሰለስቱም'' እኔና እኔ
ብቻ ነኝ!” እያለ መንግሥት የኢትዮጵያ ህዝብ ፈጣሪ መሆኑን ህጻናት እንዲቀበሉ ያስተምራል (ናዚዎች ጀርመንን ሲገዙ እንደዚሁ
ነበር)፤ዛሬ ይህንን ጉድ እንመለከታለን፡፡
የትምህርት ገበታው ተማሪዎቹ ገንዘብ እንጂ ማሕበራዊ ትስስርና የመረዳዳት ባሕል መከተል
እንደሌለባቸውና ማንም ቢቸገር ለመርዳት አትድከሙ እያለ ያስተምራል፡፡ አገራችሁ መናጢ ናት ድሕነቱ የሚጠገን ስላልሆነ አካባቢያቸሁ ለማሻሻል
ከመጣርና ወደ ውስጥ ከማትኮር ይልቅ ወደ ሩቅ በመመልከት ለደህንነታችሁና ህይወታችሁ ዋስትና እንድታገኙ ዙርያችሁ ተስፋ ስለሌለው
ወደ ስደት ሂዱ፡፡ ...
እንዲያውም ወደ እዚህ የመንግሥት
ንብረት የሆነቺው ኢትዮጵያ ወደ ምትባለዋ ምድር የመጣችሁ ከሌሎቸ አገር ሕዝቦች ተሰድዳችሁ የመጣችሁ ስደተኞች ስለሆናችሁ ወላጆቻችሁ
ከወደመጡባቸው አገሮች ሂዱ ፤ እዚህ የሚሻሻልና የሚድን አገር አይደለም፡፡ በማለት በተዘዋዋሪ “እናታችሁ” እያለ በወላጅ እናት
አስመስሎ የሚጠቅሳት ኢትዮጵያ ቀጥሎ ባለው ውስጠ ወይራ ይገልጻታል
<<*እናታችሁ ከመንግሥት ይሁን ከሌላ እጅ ልታድናችሁ አትችልም፡፡ ምክንያቱም አቅም
የላትም፡፡ ለራስዋ ለመኖር የምትንገዳገድ ደካማ ናት፡፡ በማንኛውም ጊዜ ልትሞት
ትችላለች፡፡ከሞተች ቆይታልች አጥንትዋም የተገኘው በቅርብ ነው”>> እያለ ተማሪዎች አገራቸው እንዲጠሉና በሰው አገር መኖር
እንዲመኙ አገርና ትውልድ እንዲፈርስ ያተምራል፡፡
በመቀጠልም “የውጭ አገር ሰዎች ስታዩ ሂዳችሁ አዋርዋቸው፤ ሃብታሞች ናቸው ገንዘብ
አላቸው” እያለ ታዳጊ ወጣትና ህጻናት ምን እንደሆኑ ሳይታውቁ 'እየተደፍሩ በግብረሰዶምና በእጽ ሱስ እንዲጠቁና በበሽታ እንዲበከሉ፤
ታፍነው በማይታወቁ የውጭ ሰዎች እንዲሸጡ” ይቀሰቅሳል፡፡
መጪወ አዲስ ዓለም ብለው የሚጠሩት One World Order የተባለው በኡሉምናቲዎች
እየተቀረጸ የሚገኘው ሴራ እንዲሳተፉ መጪዋን ዓለም እውን ለማድረግ ዓለም በሞላ ተግቶ እየሰራ ነውና እናንተም በዚያች ዓለም ድርሻ
እንዲኖራችሁ ተግታችሁ አስተዋጽኦ ማድረግ አለባችሁ፡፡' ይላል፡፡ ኢትዮጵያ መቸውም አትድንም እንደማትድንም አድርገን እየሰራን ንውና
በሞተች አገር አትኑሩ ፤ተንቀሳቀሱ ኢትዮጵያን ለማንሳት ሳይሆን ከዚያች ምድር በመልቀቅ ሃብታም ሆናችሁ ስለ መጪው ኢሉሚናቲያዊው
አለም አቀፍ ግምባታ እየተዘዋወራችሁ ተሳተፉ፡፡ ለራሳችሁ እንጂ የተቸገረ ወገናችሁን በመርዳት አትድከሙ ይላል፡፡ ተወረናል የምላችሁም
ለዚህ ነው፡፡
ይህንን ጉድ ያጋለጠቺው የአዲስ አበባ ኗሪ የሆነቺው ወጣት ምሁርዋ ዶ/ር መስከረም ለቺሣ “UTOPIA ዩቶፕያ “ በሚባለው
የዩቱብ መድረክዋ “ከፍል 24 ክተመሰቃቀለው የትምህርት ሥርዓታችን ጀርባ ያለው ጥልቅ መንፈሳዊ ችግር ፟ በሚል ርዕስ ትናንት ያዘጋጀቺው ትንተና ቀልቤን ስቦታል፡፡
ማብራሪያው የኔ ስለሆነ በማብራሪያው ላይ የተገኙ ስሕተቶች ሓላፊነቱ የኔ መሆኑን
ለማሳውቅ እፍለጋልሁ፡፡
በኢትዮጵያ የሥርዓት ትምህርት መማርያ መጽሐፍት ውስጥ ባደረገቺው ጥናት የመማርያ መጽሐፍቶቹን የጻፉዋቸው ኢትዮጵያዊያን/ ኢትዮጵያዊያት (ስማቸው የተጻፈና ማን እንደሆኑ
ቢታወቁም በሚዲያ ለመግለጽ ባትፈልግም) የጻፉት ጉድ ስትመረምር “ኢሉሙናቲያዊ” ብሆነ ሴራ የተዘጋጀ የታዳጊ ወጣት አስተሳሰብ
የሚበርዝ አደገኛ የሆነ ሰበካ በማዘጋጀት ፤ ተማሪዎች የመንግሥት እንጂ የወላጆቻቸው ልጆች አለመሆናቸውን የሚያውጅ አሳሳቢ ትምሕርት
ሆኖ ያገኘቺውን ጥናት ይፋ አድርጋለች፡፡
መጽሐፍቶቹ ዛሬም በከፋ መልኩ ተግባራዊ ሆኖው በዚህ “በግራኝ አብይ አህመድ” ዘመንም ትውልዱ ብሶበት እንዳለና
ይህ ትውልድ እባብ ጠብሶ መብላትን፤አህያን፤ውሻን ፤ሰው መብላት፤ 'የወንደ - ሰዶም' እና 'የሴተ - ሰዶምን' መስፋፋት 'ዝርፍያ' ፤
ሽማግሌ እናትን አባትን መድፈር፤ መስደብና መግደል፤ አገር ማፍረስ፤ማንኴሰስ ወዘተ... ፣ የተበራከቱበት ምክንያት ክታች የቀረበው የመንግስት ይሁነኝ ተብሎ የተቀረጸ
ስብከት ነው ፡፡
በተመራማሪዋ የቃል ትንተና ውሰጥ አንዳንድ ነጥቦች 'በሊንክ' የለጠፍኩት ይምህርትዋ
'ቪዲዮ' ላይ የማትስማሙባቸው የማብራሪያ ነጥቦች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል፤ ሆኖም ጉልህ የሆኑ የህጻናትን ሕሊናን በናዚያዊና ኡሉሚናቲያዊ
ስነ ልቦና እንዲቀረጽ የተደረገው የማያከራክር ዓይን ያወጣው ደባቸውን ያጋለጠችበትን ነጥብ ግን አያከራከርም፡፡ ከጥናትዋ
ያገኘቺው አዘጋጆቹ በጻፏቸው የመማርያ መጽሐፍቶች ውስጥ ክተጻፉት አንዱን ክፍል እንዲህ ይነበባል ትላለች ይህች ምህርት፤ ለሶሰተኛ
ዲግሪዋ (ዶከተሬት ከ University of Cincinnaty) ለማግኘት
ባደረገቻችው የተለያዩ የጥናት ዘርፎችዋ ከፍል ካንደኛው ጥናትዋ ውስጥ የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምሀርትን በሚመለከት (በፈረንጅ አቆጣጠር
ብ2014 ባቅረበቺው ምርምር)፡ (Social Study Students Text Book ከሚለው የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምሀርት መንግሥት
ተብየው ያዘጋጀውና በከልል ደረጃም እንዲሁ የተዘጋጁ ‘የማሕብረ ሰብ ጥናት/አካባቢ ሳይንስ) መጽሐፍቶች የታዘበቺውን ጥቂቱን
ካቀረበቺው አሳጥሬ አቀርብላችሁ አለሁ፡፡ የኮከብ ምልክቶች ፤ ጨረትና መስመሮች እንዲሁም በቀይ ቀለም የተጻፉ አረፍተ ነገሮች ቱክረት
ለማጉላት ከኔው የተጨመሩ ናቸው፡፡ ቀለሞችና መስመሮች በድረገጼ ላይ
እንጂ በዚህ ፌስ ቡክ ላይ አይታዩም፡፡
መጽሐፉ በሰው ንግግር የተቀረጸ ያህል ተማሪዎቹን እንዲህ ይላቸዋል ትላለች ዶ/ር መስከረም ለቺሣ እንደሚከተለው፦
<< ያላችሁት
ኢትዮጵያ በምትባል የመንግሥት መሬት ላይ ነው፡፡ እዚህ ስለተወለዳችሁ የዜነት ተሰጥቷችኋል፡፡በሃገሪቱ ላይ መንግሥት እውቅና *ይሁንታ
ካልሰጣችሁ በቀር ምንም ዓይነት ማንነት ሊገልጻችሁ አይችልም *፡፡እናንተ ማን እንደሆናችሁ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው *መንግሥት ነው *፡፡ ሰው መሆን አለመሆናችሁ እንኴ መወሰን የሚችለው *ሥልጣኑ ያለው በመንግሥት
እጅ ነው *፡፡
ኢትዮጵያዊ መሆን አለመሆናችሁንም የሚወስንላችሁ *መንግሥት ነው *፡፡ የመንግሥትን በጎ ትኩረት *ለመሳብና ለመታየት * መጣር አለባችሁ፡፡ምክንያቱም መንግሥት አያውቃችሁም፡፡
በዚች አገር ሲኖር የምታዩት ይህ ሁሉ ሰው ከሌላ ቦታ ፈልሰው ከመጡ ሕዝቦች የተዋለደ
ነው (*እርስበርሱ አይተዋወቅም፤ ኣንዱ ላንዱ ባዕድ ነው *)፡፡
በህይወታችሁ ልትከተሉት የሚገባው ዋነኛ ግብ ገንዘብ ነው፡፡ያለ ገንዘብ መኖር አትችሉም፡፡
ማን እንደመሆናችሁና በዙርያችሁ ያሉ ሰዎች 'ምናችሁ እንደሆኑ የሚነግራችሁ
መንግሥት ነው'፡፡ 'በራሳችሁ ግንዛቤ መመራት' አትችሉም፡፡
... ሁሉም ሰው የሚሰራው ለራሱ ጥቅም ሲል ነው፡፡ ስለዚህ *የማንንም ችግር ለመፍታት መድከም የለባችሁም *
ሌሎች ባህላዊና ጠቃቅን ትንንሽ የሥራ ዘርፎች ምንም ገንዘብ አያስገኙም፡፡
*እናታችሁ ከመንግሥት ይሁን ከሌላ እጅ ልታድናችሁ አትችልም፡፡ ምክንያቱም አቅም
የላትም፡፡ ለራስዋ ለመኖር የምትንገዳገድ ደካማ ናት፡፡ በማንኛውም ጊዜ ልትሞት
ትችላለች፡፡እንዳውም የሰው ዘር እናት እራስዋ ክሞተች ቆይታለች *
አጽሟንም በቅርብ ጊዜ ነው ያገኘነው፡፡
የህይወት ትርጉሟ ምንድ ነው? ከኛ በፊት የነበሩ ሰዎች ምን ዓይነት ነበሩ፤ለወደፊትስ
በምድራችን ምን ይፈጠራል? የመሳሰሉት ጥያቄዎች ላይ አዕምሮአችሁና ግዜአይችሁን
አታባክኑ፡፡ ምክንያቱም ለነዚህ ጥያቄዎች አጭር መልስ አለ፡፡ ባለፉት ዘመናት በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳ ከኛ በፊት የነበሩ
የሰው ዘሮች ሞተው አልቀዋል፤ሙታን ናቸው፡፡እንዴት እንደኖሩ ምን እንዳጋጠማቸው መገመት እንችላለን እንጂ እርግጠኛ የሆነ መረጃ
የለንም፡፡ ጥሩ የሆነችና የተሻለች ዓለም ገና ልትመጣ ነው፡፡ ዓለም በሙሉ እስዋን እውን ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ነው፡፡እናንተም
በዚያች ዓለም ድርሻ እንዲኖራችሁ ተግታችሁ አስተዋጽኦ ማድረግ አለባችሁ፡፡ትምሕርት የሚያስፈልጋችሁ ለዚያ ነው፡፡
ትምሕርት ቤት ውስጥ የሚነገራችሁ ሁሉ ማመን እና ያንኑ መልሳችሁ ማስተጋባት አለባችሁ፡፡በናንተ
ሕይወት ውስጥ ትልቅ ተአማኒነት ሊኖራችሁ የምትችሉባቸው ሰዎች ቢኖሩ መምህሮቻችሁ ናቸው፡፡
የውጭ አገር ሰዎች ስታዩ አዋሯቸው፡ሃብታሞች ናቸው፡ ገንዘብ አላቸው፡፡ በብዙ ጥረት የመጨረሻ ግብ መሆን ያለበት በሰዎች ላይ የምትሾሙበትና በሁሉም
ረገድ ከሌላው ሰው የተሻለ አቅም ያላችሁ መሆኑን ለማሳየት ሁሉም ሊስማቸሁ በሚችልበት ደረጃ ላይ መድረስ ነው፡፡ .... እዚያ
ላይ እስክትደርሱ ተንቀሳቀሱ፤ ባንድ ቦታ ላይ ረግታችሁ አትቀመጡ፡፡ አጠገባችሁን አትዩ፤ አጠገባችሁ ምንም የለም፡፡ ባካባቢያችሁ
ምንም የሚታይ ነገር የለም፡፡ ወደ ሩቅ ተመልከቱ፤በምትኖሩበት ቦታና ባጠገባችሁ ምንም የሚስብና የሚረባ ነገር የለም፡፡
ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ተመልሶ ይስተካከላል የሚባል አይነት አይደለም፡፡ ደህንነቱ
ለተረጋገጠና ዋስትና ላለው ሕይወት ሳታቋርጡ መዞርና ሃብት ማካበት
ልምዳችሁ ማድረግ ይገባል፡፡\>>
በማለት የኢሉሚናቶቹና የናዚ ፋሺስት ቅጥረኛው ቡድን የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ
ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ይህ ጽሑፍ ከተለጠፈበት እስካሁንዋ ዛሬ 2016 ዓ.ም ድረስ ታዳጊ ወጣቶች እንዴት እየበከላቸው እንደሚገኝ
ይህ ማስረጃ ስንመለከት በቅኝ ግዛት ጫማ ሥር መሆናችን አመላካች ነው፡፡
የላቀ ምስጋና ለዶ/ር መስከረም ለቺሣ አቀርባለሁ!
ጌታቸው ረዳ
24 - ከተመሰቃቀለው የትምህርት ሥርዓታችን ጀርባ
ያለው ጥልቅ መንፈሳዊ ችግር (በዶ/ር
መስከረም ለቺሣ)
https://youtu.be/sB8o7Jr1QXc?si=FLQFLWj5H83vfs5Z
No comments:
Post a Comment