Monday, June 7, 2021

ትግሬዎች እነማን ናቸው? የትግሬዎች “አክሱም ኬኛ” የታሪክ ስግብግብ ዘረፋና ትምክህት ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay) 6/7/2021

 

ትግሬዎች እነማን ናቸው?

የትግሬዎች “አክሱም ኬኛ” የታሪክ ስግብግብ ዘረፋና ትምክህት

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay)

6/7/2021


በፎቶግራፉ የሚታዩት ምስሎች “ት ”ግሬ”” እና “የ ት ”ግረ” ” ቤጃ ምስሎች ናቸው። ልጃገረዶቹ አንዷ ቤጃ ነች ሌላኛዋ ትግሬ ነች። የተቀሩት ወንዶች ቤጃዎች እና ትግሬዎች ናቸው። የመልካቸውን ቅርጽና ቀለም መመሳሰል፤ ተመልከቱልኝ። በተለይ በሁለቱ ወንድ ትግሬዎች የሚታይ የመልክ አቀራረጽ የጥንቶቹ ቤጃዎች መልክ የያዙ መሆኑን ካገነዛብኳቸው ጥንታዊ የመጽሐፍት ፎቶዎች ለማወቅ ችያለሁ። 

“አክሱም የጥንታዊት ኢትዮጵያ ስልጣኔ እምብርት፣ የጠንካራ መንግሥታዊ አስተዳደር ማዕከል እና የድንቅ ባህል መድረክ እንደነበረች ይታወቃል። የታቦተ ጽዮን መገኛ፣ የቅዱስ ያሬድ መፍለቂያ፣ የመጀመሪያው ጳጳስ አባ ሰላማ (ፍሬምናጦስ) መንበር፣ የዘጠኙ ቅዱሳን በዓት የነበረችው አክሱም በኢትዮጵያ የክርስትና ሐይማኖት ታሪክ ልዩ ክብርና ስፍራ አላት። አክሱም የመጀመሪያዎቹ የሙሃመድ ተከታዮች ከሃገራቸው በተሰደዱ ጊዜ በእንግድነት ተቀብላ መጠጊያ ስለሆነች በሙስሊሙ ዓለምም ውለታዋ የሚዘነጋ አይደለም።

የአክሱም መንግሥት በትንሹ ከመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ መኖሩ ሲታወቅ፤ ጠንካራ መሪዎችና የራሱ የሆነ የመገባበያ ገንዘብ እንደነበረውም ይታወሳል። በዚሁ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ዞስካለስ በመባል የሚታወቀው ንጉሥ የግሪክኛ ቋንቋን በደንብ የሚያውቅና የአዶሊስ ወደብን በዋና የንግድ ማዕከልነት ይጠቀም እንደነበር ተመዝግቧል። የአክሱም መንግሥት ኃያልነት ከ2ኛው እስከ 3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበረው የአዶሊስ ሐውልት ጽሑፍ (Adulis Inscription) ላይ ተጠቅሷል። በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ማኒ የተባለ ፐርሺያዊ ጸሐፊ አክሱምን ከሮም፣ ከፐርሺያና ከቻይና ጋር በመደመር በዘመኑ ከነበሩት የዓለም ሃያላን መንግሥታት ተርታ አስቀምጧታል። ከ4ኛው እስከ 6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ለነበረው ከፍተኛ የሆነ የአክሱም መንግሥት እድገትና ብልጽግና ከበቂ በላይ የታሪክ ምስክሮች ይገኛሉ። የ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመኑ ንጉሥ ኢዛና እና የ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመኑ ንጉሥ ካሌብ በቤተመንግሥትም ሆነ በቤተክህነቱ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያላቸው ናቸው። (የዘመነ አክሱም ስልጣኔ ቅርሶች የማን ናቸው ቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨስቲ ፣ ስዊድን)

ጸሓፊው በዚህ ጽሑፋቸው “አክሱም” ውስጥ ከማንኛቸውም የዘመኑ ነገዶች ከፈተኛ ድርሻ የነበረው “የአገው” ነገድ እንደሆነ ይከራከራሉ።

ስለሆነም የዚህ ታሪክና ሥልጣኔ ባለቤት “እኔ ብቻ ነኝ” የሚለው በፋሺሰት ልቦና የደነደነ የ ህ.ወ.ሓ.ህ.ት ምሁርና ጀሌ ለ17+27 = ለ44 አመት በግሃድ ሲደሰኩር ሰምተናል። ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት “አክሱማዊ” በሚባል የወያኔዎች ‘የዩቱብ ሚዲያ’ ላይ ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ የተባለው አሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያስተማረ ፤ የታሪክ መምህር ነኝ የሚል ድሮ ‘ኢሕአፓ’ ተዋጊ የነበረ ፤ ዛሬ ዋና የወያኔ የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ አቀንቃኝ በመሆን በቃለ መጠይቁ የሰማሁትን አስቂኝ ነገር ልንገራችሁ።

“አክሱም ከተማ ውስጥ በጥንት ጊዜ “ቤተ ዘውገ” ሲባል የነበረው የሗላ ትግሬዎች “ዑና እንዳ አቦይ ዘውገ”  “የኣቦይ ዘውገ የፈራረሰ ወና ቤት” በማለት ልክ የዛሬ ወያኔዎች የጥንት ስሞች፤ ከተሞች፤ተራሮች፤ገጠሮች፤ ወንዞችና የታሪክ ቦታዎች በወያኔ ታጋዮች ስም እንደሰየሙዋቸው ሁሉ ፤ ከአክሱም መውደቅ በሗላ የተከሰቱ ትግሬዎችም “ስሙን” ወደ ትግርኛ የሰየሙት መንደር አለ ። ይህ ስፍራ /ቤት ገርግስ/ በሚባል ልጆች ሆነን ስንጫወትበት የነበረ ከሃውልቶቹ ትንሽ ራቅ ብሎ ዳገት ተራራ ስር ላይ የሚገኝ መንደር ነው። ዛሬ ከተሜዎች የሚኖሩበት መንደር ነው። ታዲያ ገላወዴዎስ “ያቺ”  ዘውገ የምትል አርኪዮሎጂስቶች የጻፉዋትን ተመልክቶ “ወደ ወሎ ሄደው ህንጻውን የሰሩት እነዚህ ዘወገ የተባሉ ትግሬዎች ናቸው”” ሲል “ዘውገ” የሚለው ግዕዝ (ነገድ/ዜጋ ማለት ነው ትርጉሙ ፡ለምሳሌ ዘውገሚካል) ግዕዝ መሆኑን ሳያውቅ ትግርኛ ወይንም አገውኛ መስሎት ከአገው “ዛጉዌዎች” ስም አገናኝቶ ትግሬዎች “ዘውገ” የሚባል የትግርኛ ቃል ጥንት አክሱም ይታወቁ ነበር፤ ለማለት ሲጠቀምነት አድምጬው “እጅግ ነበር የሳቅኩት”።

“የኔ ብቻ” የሚል ባለቤትነት ዛሬም ወያኔ የተባለው የሌቦችና የነብሰገዳይ ፋሺሰቶች ጥርቃሞ ቡድን “ትግራይን ነፃ በማውጣት የትግራይ ሃገርነት” እምሰርታለሁ ብሎ ወደ ጫካ ከፈረጠጠ በሗላም ይህንኑ “ብቸኛ ባለቤትነት” ቅስቀሳ ታጋይ ህጻናቶችን ሰብስቦ መቀስቀሱን ቀጥሎበታል።

ትግሬዎች “የኬኛ” በሽታ እንደተጠናወታቸው እንደ ኦሮሞ ምሁራን ሁሉ ትግራዎች እንጂ ትገሬዎች/ትግሬዎች/ አይደለንም የሚል ከጥንት ስማቸው ለመሸሽ በመሞከር፤ያ አልሆን ሲል ደግሞ “አጋአዚያን” በሚል መጠሪያ ለመጠራት ሲዳዳቸው እያነበብናቸው ነው።

 ትግራይ ውስጥ ያሉት የታሪክ ቅርሶች እና በአካባቢው በድል የተጠናቀቁት ጦርነቶች የትግሬ ባለቤትነትነት “ብቻ” በማድረግ ኦሮሞቹ “አክሱም ኬኛ” እያሉት አንዳሉት ሽሚያ “ትግሬዎቹም” በታሪክ የሽሚያ እሽቅድድም ገብተው በሽታቸው እየባሰ መጥቶ ዛሬ ደግሞ “ሃገረ ትግራይ” ምስረታ እውን እናደርጋለን በማለት የትግራይ ወጣቶችና ገበሬዎች ለርሃብ እና ለጦርነት ማግደውታል ።

 በዚህ አስከፊ ህይወት የመጓዝ ወይንም የማስወገድ ብቸኛ መርጫ የያንዳንዱ የትግራይ ሰው ሲሆን፤ “ትግራይ ለትግሬዎች ብቻ” የሚለው የፋሺስቶች ስግብግብ ትረካ ግን እንደ ትግሬነቴ እውነታውን ለመጋፈጥ በታሪክ ፊት ቀርቤኣለሁ እነሆ።

ትግሬዎች ትግራይን መገንጠልም ሆነ የባለቤትነት ብቸኛ ይዞታ የሕግም የታሪክም ማስረጃ የላቸውም።

ትግሬዎች እነማን ናቸው? የዘር ሐረጋቸው ከየት ይመዘዛል?

የሚለው ጥያቄ በኔ መልስ ልጀምር።

የኔ መልስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ እንደ ትግሬዎች ከአይሁዶቹ ከእስራል ነገዶች፤ዓረቦች፤ ጠያይሞችና ጥቋቁር ቤጃዎች፤ ግሪኮች፤ ቱርኮች፤ ሕንዶች፤ ጣሊያኖች ወዘተ……ወዘተ…..  የተደበላለቀ ቅይጥ  የደም ሐረግ ያለበት ነገድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ትግሬ ነገድ ያለ አይመስለኝም። እንኳን እና እኛ የሺ አመታት የዘመን ቅይጥ ውጤቶች እነ “ንጉሠ ነገሥት ኢዛና” እራሱ የብዙ ነገዶች ሐረግ እንዶሆነ “እኔ ኢዛና የኤላ አሚዳ ልጅ…ብሎ” በመጀመር የጻፈውበትን የነገድ ሐረጉ በቂ ማስረጃ ነው። ይህ አጭር የኔ መልስ ነው። ወደ ምሁራኖቹ እና እራሳቸው ትግሬዎች ማንነታቸው የሚገልጹበትንም  ምስክርነት ያዤአችሁ ልግባ።

የትግሬዎች የዘር ሥር (ሐረግ) ከየት ይመዘዛል? ይህንን በሚመለከት መልስ የሰጡን የተለያዩ የታሪክ ምርምር በማስመዝገብ የተለያዩ የክብር ሽልማት የተሰጣቸው የኢትዮጵያዊው ምሁር የዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ምሁራዊ ትንታኔ “ፓራፍሬዝ” ልጥቀስ።

“አክሱም የትግሬዎች ብቻ ነው እየተባለ የሚነገረው ሙግት “መሰረት የማይገኝለት ከእውነታው ጋር የሚጋጭ፤ የተረት ትረካ ነው”። በማለት ይቀጥሉና

“የአክሱም ሥልጣኔ ተብሎ የሚታወቀው ከመጀመሪያው ክ/ዘመን እስከ 9ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ አስገራሚ ሕዝባዊ አስተዳዳርና የስነ ህንጻ ግንባታዎች ያከናወነ ሕዝብ ነው። ሥልጣኔውና አስተዳደሩ አክሱም ከተማ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ሰፊ ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር። እንዲህ እያለ፤ የአክሱም ንገሥነትና ነገሥታት የትግሬዎች ብቻ ነው እየተባለ የሚነገረው ፍጹም እውነታ የራቀው ነው። ምክንያቱም እራሳቸው ትግርኛ ተናጋሪዎቹ ትግሬዎች ከአክሱም ሥልጣኔ በሗላ የተከሰተ ማሕበረሰብ ነው። አክሱም ውድቀት በሗላ ከነበሩ የዚያ ማሕበረሰቦች እየተዳቀሉና ጉልህ እየሆኑ የመጡ ናቸው። በተለይ በዘመነ አክሱም ነበር እየተባለ የሚነገረው ዛሬ አክሱም ውስጥ የሚገኘው ትግርኛ ተናጋሪው ክፍል ሳይሆን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘው “ትግረ” ነገድ የተባለው ነው።” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አከሱም ባለቤት አለው የሚባል ስህተት አባባል ቢሆንም “የሚባል ከሆነ ግን” አገዎች እንጂ ትግሬዎች አይደሉም። ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ ለንደን እንግሊዝ አገር ካለው “ኢሳት ቲቪ” ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ አገው ህዝብ ሲናገሩ 

"ዛሬ በኢትዮጵያ ባህልነት የሚታወቁ የምግብ እና የመጠጥ አይነቶች ‘ጤፍና ጥራጥሬ” ጨምሮ ብዙዎቹ በዋናነት ያስተዋወቁትና ያመነጫቸዉ አገዎች ናቸው ይላሉ። ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ አገዎች ከአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ ካሉ የፈጠራ ችሎታ ካላቸዉ ህዝቦች የሚመደብ ጠንካራ ህዝብ መሆኑን ይመሰክራሉ፡፡ ትግሬዎች ግን በዚህ ነጠቃ ሲያደርጉ አይተናል።

በቅርበ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሚገርም “ትግራይ/ትግርኛ/ የሚባል ነገር አክሱም ውስጥ ስላልተመዘገበ እኛ “አጋአዚያን” ነን ወደማለት ክርክር ሲገቡ እያደመጥንም ነው።

                                     አጋአዚያን እነማን ናቸው?

መልሱ የምናገኘው ትግሬዎች ድርጅታችን ነው ብለው ከሚከተሉት የራሳቸው የወያኔ ድርጅት ስለ አጋዚያን ማንነት በማኒፌስቶ 1968 ያሳተመውን ላስነብባችሁ፡

እንዲህ ይላል፡

  “The people of Tigray have a rich history of thousands of years. In the past, they were Known by various names such as Axumites, Habeshas, etc. Before 1000 BC, present day Tigray was inhabited by Nilotic and Hamitic peoples of African origin, who led a primitive communal life.....the tribes of South Arabian origin known as the Sabean, Agazeans, Habeshats, and Himyarites began to cross the Red Sea and settle in the areas which are today Tigray and Eritrea. These tribes were at a more advanced stage of development than the indigenous people. / People's Democratic program of TPLF, May 1983) >>

የህወሃት ማኒፌስቶ የግንቦት 1983 ዓ.ም.

“የትግራይ ህዝብ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታት የበለፀገ ታሪክ አለው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ስም ባለፉት የታሪክ ዘመናት ውስጥ ፣ እንደ አክሱማውያን፤ ሀበሾች ወዘተ…. ባሉ የተለያዩ ስሞች ይጠራ ነበር። የዛሬዋ ትግራይ ከ 1000 በፊት ከክርስቶስ ልደት በፊት “ሗላ ቀር” በሆነ ጥንታዊ የአናኗር ዘዴ ሲኖሩ በነበሩ ኒሎቲክ እና ሀሜቲክ አፍሪካዊያን ሕዝቦች መኖሪያ ነበረች። ፣ ሳባዊያን የተባሉ የደቡብ አረቢያ ነገዶች የነበሩ “አጋዚያን ፣ ሀበሻት እና ሂምያራውያን” የተባሉ ነገዶች ቀይ ባህርን አቋርጠው የዛሬ ትግራይ እና ኤርትራ በተባሉት አካባቢዎች መኖር ጀመሩ። እነዚህ ነገዶች የላቀ የእድገት ደራጃና ስልጣኔ ከአገሬው ተወላጆች የላቁ ነበሩ፡፡

 (የህወሓት መርሃግብር/ማኒፌስቶ/ ግንቦት 1983)

Beja Kingdoms 750 AD

The Bejas are still remembered in the orla traditions of people residing in the highlands of Eritrea as the “Belew” peoeple. The Belew were Chritian Bejas-zed Arabs who ruled in the highlands and lowlands of Eritrea. By the 13th century AD, much of the Bejas would gradually stat converting to Islam."

(Conti Rossini 1928; The Archiology of Ancient Eritrea (by Peter Ridgway Schmidst, Mathew C. Curtis, Zelalem Teka, pg.284; Muinzinger 1864)

እነዚህ በለው ከለው የተባሉት ቤጃዎችም በደብተራ ፍስሐ ጊዮርጊስ በዘመነ ምኒሊክ የተጻፈ የትግርኛ የእጅ ጽሑፍ መጽሐፋቸውም “ከለው” እንጂ ትግሬ/ትግራይ/ተጋሩ/ የሚባሉ ነገድ አክሱም ውስጥ አይጠቅሱም።

ከዚህ ሌላ በቅርብ አመታት የተመሰረተው “ደቂባት አጋኣዝያን” (አጋኣዚያን ተወላጆች) በሚል ስም ከሦስቱ አጋኣዚያን ድርጅቶች አንዱ የሆነው ይህ ድርጅት በትግርኛ እንዲህ ይላል፡

                                    “ደቂባት ኣግኣዝያን፦

                                          ትግርኛ

 “ኣግኣዝያን ማለት ብግምት ኣስታት ካብ ሓደ ሽሕ ዓመታት ንላዕሊ ቅ.ል.ክ. ኣቢሉ ይኸውን፣ ኣግኣዝያን ዝተባህሉ ስማውያን ህዝብታት፣ካብ ከባቢ የመንን ጆርዳንን ኢራቕን ተበጊሶም፣ብቀዪሕ ባሕሪ ኣቋሪጾምን ፈለግ ኒል ተኸቲሎምን፣ንወገን ከበሳ ክሳብ ፈለግ ተክዘ፣ኣብዚ ሎሚ ኤርትራን ትግራይን ዝብሃል ዘሎ ቦታ ተሃዘቡ። ካብኡ ከኣ ንወሎን በጌምድርን ጎጃምን ሰሜናዊ ሸዋን ተስፋሕፍሑ።.” ይብሎም። “ኣጋኣዝያን-ደቀባት ምልክቶም ኣንበሳ እዩ” ድማ ይብል።”

                                  ወደ አማርኛ ልተርጉመው፡

“አጋኣዚያን ማለት በግምት ከ1000 አመታት በላይ ማለትም ከክርስቶስ ልደት በፊት ኣጋኣዝያን የተባሉ ሰማዊያን ህዝቦች፤ከየመን ፤ጆርዳን፤ ኢራቅ ተነስተው በቀይ ባሕር አቋርጠው የኒል ፈለግ ተከትለው ደጋማው አካባቢ እስከ ተከዜ ድረስ ዛሬ ኤርትራ እና ትግራይ በሚላዩት ቦታዎች ሰፈሩ። ከዚያም ወደ ወሎ፤በጌምድር፤ጎጃም እና እስከ ሰሜናዊ ሸዋ ተስፋፉ።” ይላል።

 የዚህ ድርጅት ምልክት መለያው ደግሞ “አንበሳ” እንደሆነ ይገልጻል።

የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍ አግኝቼ ባላነበውም ዶ/ር ፍቅሬም የትግሬዎች ስርወ አመጣጥ ከቲግሪስ ባቢሎን (ዒራቅ) አንደተነሳ ገልጿል ይባላል። እንግዲህ የሌሎቹን ትተን የወያኔ ማኒፌስቶም ሆነ አሁን የበቀለው የትግርይ “አጋዚያን ተወላጆች ፓርቲ” እራሳቸው ከየት አንደመጡ እየመሰከሩ ከሆነ ሌላ ማስረጃ መጠራጠር አይቻልም።

በ9ኘው ክ/ዘመን አካባቢ ልክ እንደ ወልቃይቶች የአክሱም መንግሥት ሲተናኮሉ የነበሩ የቤጃ ነገዶች ለዛሬዎቹ ትግሬዎችም በደምና በአጥንት በመወሃድ ክልሰውናል። ቤጃዎች እጅግ በጣም ሰፊ ቦታ የሸፈኑ የታወቁ ሃይለኛ ጥንታዊ ተዋጊዎች፤ ጥበበኞች እና ከብትና ግመል አርቢዎች ነበሩ።  ከምስር/ግብፅ/ በረሃ ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ የሱዳን ምስራቅ እስከ ኤርትራ ድረስ  የተዘረጉ ናቸው። በወረሩት አካባቢ እየተዳቀሉ ስለቀሩ ዛሬ ቁጥራቸው እንደ ትግሬዎቹ ትንሽ ነው።፡በአንደኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የቤጃ ሥርወ መንግሥት ሜሮዌን በመያዝ የኩሽን መንግሥት ይገዙ እንደነበር የተቀረጹ ምስሎች ያሳያሉ። በ 6 ኛው ክፍለዘመን ውስጥ በከፊል ክርስትና የገቡ ሲሆን ደቡባዊ ቤጃ በመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ላይ የአክሱም መንግሥት አካል የነበሩ ናቸው፡፡ ቤጃዎች በ 15 ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ እስልምናን የተቀበሉ ነገዶች ናቸው ፡፡

ወደ አክሱም የመጡት ወደ 9ኘው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል። የአሁኗ እስላማዊ ቤጃ በተጠቀሱት አካባቢዎች አሉ። የትግሬ የሚል ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሑፍ ተጠቅሶ የሚገኘው በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው ቢባልም እኔ አላየሁትም ሆኖም ያየሁት ግን በ13ኛው ክ/ዘመን ከአክሱም መንግሥት ማክተም በኋላ ነው። ትግረኛ/ትግራይ/ተጋሩ/ ትግርኚ/ትግርኛ/ የሚለው የተጠቀሰው ግን በ19ኛው ክ/ዘመን አካባቢ ነው።

አክሱምን የወረሩ ነገዶች ባርካን የወረረው ከአምስቱ የቢጃ ነገዶች አንዱ የሆነው “ሳናፊጅ” የተባለው እና ሃደንዳዋ የተባለው የቤጃ አንደኛው ነገድ ነው። እነሱን ተከትሎ እንደተከሰተው የዛሬው የትግሬ ነገድ “ክራር እየተጫወተ” “በሰይፍና በጦር “ጋሻ” እየዘለለ የሚዋጉ “ሃይለኛ” ጦረኞች ስለሆኑ፤ ለምሳሌ በ 18 ኛው ክፍለዘመን እንግሊዚ ሱዳን ሲቆጣጠር ሃንደንዳዋ ቤጃ ብዙዉን ምስራቃዊ ሱዳንን መክቶ በመቆጣጠር ፡፡ በ 1880 ዎቹ እስከ 1890 ዎቹ ባለው የማህዲስት ጦርነት ውስጥ ቤጃ በሁለቱም በኩል ተዋግቷል ፣ ሀደንዳዋ ከአማፅያኑ ጋር ሲተባበር ቢሻሪን እና አማረር የተባሉ የቤጃ ጎሳዎች ከእንግሊዝ ጎን እንደተሰለፉ ዘገባዎች ይገልጻሉ።

መልካቸው በፎቶግራፉ እንዳቀረብኩት ከኛ መልክ በምንም የማይለዩ በአካል ቀጫጭኖች የጥቁርና የቀይ ዳማ እንዲሁም ባለ ቡናማ ቀለም መልክ ያላቸው ናቸው። አንድ ሱዳን ውስጥ የተቀረጸ የቤጃ በዓል በቪዲዮ ስመለከት እስክስታቸው በትክሻ የሚመታ ከኛ ከትግሬዎች ጋር እጅግ የሚመሳሰል እስክስታ አይቻለሁ። ለሰዎችም ልኬ አሳይቼኣቸው ገርሞቸዋል። እሱን ፈልጌ እለጥፋለሁ።

ትግሬዎች አመጣጣቸውም ሆነ የስም አጠራራቸው ምንጩ ከላይ የጠቀስኩት የጥንት ታሪክ ሊቅ ‘ኮንቲ ሮዚኒ’ እንደተገለጸው ከሆነ እና በራሳቸው በትግሬዎቹም በታመነበት የየመናዊነትና የ ኢራቅ ትግሪስ አመጣጣቸው እንዲሁም አክሱማዊያን ነገሥታትም (ግሪኮችና እስራኤሎች) (ባጭሩ ሰማዊ ነገድ ያላቸው ነገሥታት) በተለይ መጽሐፈ አክሱምም ይሁን የተዋህዶ ክርስትና መጻሕፍት የሚነግሩን ከሆነ የአክሱሞች ስራ/ሥልጣኔ/ “የእስራል ምኒሊካዊ አይሁዳዊ ነገዶችና ነገሥታት ዘር ስራ” እንደሆነ ነው።

 ይህንን እራሳቸው ትግሬዎችም በጽሑፍና በሃይማኖታቸው መጻህፍት ካመኑበት እራሳቸው ትግሬዎች “አክሱም” በሁለተኛ ዜጋኔት የመጡባትና የተዳቀሉባት ግዛት ነበረች ብለን ለመከራከር በቂ ምክንያት አለ። ስለዚህ የመጨረሻ አስታራቂ ድምዳሜ የሚሆነን የአክሱም ስልጣኔም ሆነ ትግራይና አካባቢዋ የተደረጉ የድል አድራጊ ጦርነቶች የሁሉም ሱታፌ የነበረበት የጋራ “ኢትዮጵያዊያን” ብለን በጋራ ካልተጓዝን “ይህንን የበላይነትም ሆነ ሁሉም አክሱማዊ ሥልጣኔም ሆነ የተደረጉ ድል አድራጊ የጦርነት ድሎች “የትግሬዎች የኛ በቻ” (ኬኛ) በሽታ፤ ትግሬ ብቻውን “ልዩ ፍጡር፤ አድራጊ ፈጣሪ፤ ነጋሽና አንጋሽ” የሚል የናዚ መፈክር አባዜ ቆም ብለውማስብ ጊዜው አሁን ነው።

እንዲህ ያለው ትምከህትም ትግሬዎች ሳያስቡት “‘ወልቃይት የትግሬዎች ነው” ብለው የሚመክተን ታረክ የለም ብለው ጉራ ነዝተው ወልቃይትና አካባቢው በጉልበት አጠቃልለው ‘ወስደው’ ከንቱ ጉራ ሲነዙ ከርመው በድንገት ዛሬ ማንም ሊመክተው የመይችል “የወልቃይት ጉዳይ” የሚለው የወጣት ታሪክ ተመራማሪው አቻምየለህ ታምሩ አዲስ መጽሐፍ “የወልቃይት፤ጠገዴ፡ጠለምት እና ሁመራ የወሰንና የመለክዓ-ምድር ታሪክ ምርምር ውጤት (ከ323 ዓ.ም. እስከ 1983 ዓ.ም) የሚለው በ2012 ዓ.ም አምና የታተመው መጽሐፍ ብቅ እንዳለ ሁሉ፤ ስለ ትግሬዎቸ ነገድም ያልተሰሙ ምርምሮች እንዲወጡ ስለሚያስገድድ፤ ሁላችንም በወንድማዊ እና እህታዊ አንድነት ብንኖር የተሻለ ነው እላለሁ።

ማጠቃለያ፡

በ16ኘው ክ/ዘመን የተከሰቱ ኦሮሞዎች በመላዋ ኢትዮጵያ ተንሰራፍተው ወልደው ተጋብተው ነባሩን ሕዝብና የቦታዎቹን ስም ኦሮሙኛ አድርገው እንዳናገሩትና እንደሰየሙት ሁሉ ማንም የትግራይ ሰው ለዘመናት እዛው በመኖሩ ፤ ትግርኛ በመናገሩ ብቻ ቅድመ አያቶቼ አክሱማዊያን የነበሩ ትግሬዎች ናቸውና፤ አክሱም አገው (አማራ) ፤ ኩናማ፤ ሳሆ፤ ዓፋር ወዘተ… ባዕድ ነው ፤ ትግራይ/አክሱም/ ለእርሱ ምንሙ አይደለም ፤ “አያገባውም” የሚልበት ምንም የሕግም የታሪክም “የደም ንፀህነቱንም” መከራከሪያ ሊያቀርብ አይችልም።

አመሰግናለሁ: ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethiopian Semay


No comments: