Wednesday, June 30, 2021

አመድ ልሳ እንደተነሳችው እንደ “ፎኒክስዋ ወፍችሁ ‘ዳግም ልደታችሁ” ለማየት በማዕቀብ ፈተና እንዲፈትናችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ እጠይቃለሁ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 6/30/2021

 

አመድ ልሳ እንደተነሳችው እንደ “ፎኒክስዋ ወፍችሁ ‘ዳግም ልደታችሁ” ለማየት በማዕቀብ ፈተና እንዲፈትናችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ እጠይቃለሁ!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

6/30/2021

አርዕስቱን እንደምታነብቡት ጥሪው ማዕቀብ የማድረግ ጥሪ ነው። ብዙ ተመጻዳቂዎች እንዴት በኢትዮጵያ ግዛት ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ ታደርጋለህ የሚሉ ተመጻዳቂዎች በበጎ መልክ እንደማይመለከቱት አውቃለሁ። እነሱ “ኢትዮጵያ ግዛት ነው” ከሚሉት እውነታ የተለየ ሁኔታ ስለተከሰተ እውነታውን ለመጋፈጥ ያለው አማራጭ የትግራይ ሕዝብ ወያኔን አምኖ አገር የመመስረት ፍሎጎቱ ስላሳየ ኢትዮጵያ ከምንላት አገር የሚፈልቅ “ሶርስ” ሁሉ ማቋረጥ የግድ ነው። ሃገረ ትግራይ የመሰረተ "ኢትዮጵያን የጠላት አገር ብሎ የፈረጀ ተዋጊ ማሕበረሰብን የመመገብ ግዴታ ካለ አስረዱኝ።

ፈረንጆቹ “ቴስት ዘዋተር” የሚሉት የመዋኛ ፈተና አለ። ፍላጎታቸውን እንዲያጣጥሙ የመፈተኛ ወቅት እንስጣቸው ማለቴ ነው። አሜሪካኖች ማዕቀብ እንዲጣል አድርገው አልነበረም? ያ እኮ ውጤት እንደሚያመጣ ስላወቁ ነው። ታዲያ እዚህ ጋር ቆም ብለን “በፋሺሰቶች ጉያ ታቅፎ ያደገ አዲሱ የትግራይ ማሕበረስብ “ሃገረ ትግራይ” የሚል “አዲስ አገር” መስርቷል እና የማዕቀብ ጥሪ ማድረግ መብታችንም ሕጋዊም ነው እና ጥፋቱ የት ላይ ነው?

ድሮ ወጣቶች ሆነን አክሱም ውስጥ ስናድግ “አንዱ ቁረጥ አንዱ ምረጥ” የሚባል አባባል ነበር። እነሱ ሃገረ ትግራይ መርጠዋል፤ እኛም በውሳኔአቸው መቁረጥ የወቅቱ ጥያቄ ነው። ስንቆርጥ ደግሞ ፡ሃብታችን፤ ምሁራኖቻችንም” ወደ እዚያ ፍጆታ እንዳይውል ማድረግ ሕጋዊም መብትም ነው። አይደለም እንዴ?

 ችግሩ አብይ አሕመድ እውን ያደርገዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ ከባዱ ጥያቄ ነው። ከእንደዚህ ያለ መሪ የስልት ሥራ ይሰራል ብሎ የሚጠበቅ አይደለምና አይሞክረወም። ይበልጥኑ ኢትዮጵያ እንድትቆረቁዝ እነሱን በመቀለብ ሃብት ማባከኑ አይቀሬ ነው። በመጨረሻ እነሱ “ሥርተ-አልባ ማሕበረስብ” Anarchical Society “ይመሰርታሉ፤ኢትዮጵያም እነሱን ለማስታመም ባባከነቺው ሃብት ቆርቁዛ ትቀጥላለች::

 ይህ ሁሉ እንዴት ተከሰተ? ወደ እዚህ ውስብስብ ያስገቡን በታሪካችን ለሁተኛ ጊዜ ማተባቸውን የበጠሱ ከሃዲ የውጭ አገር ቅጥረኞች መለስ ዜናዊ እና አብይ አሕመድ የኢትዮጵያን አንድነት እንዲናጋ በማድረግ የታሪክ ተጠያቂዎች ናቸው። እነዚህን ያበረከቱልን ደግሞ ኦሮሞዎች እና ትግሬዎች ናቸው። መለስ ዜናዊ በፈጣሪ ቁጣ ወደ መቀመቅ መሬት መውረዱ ስንደሰት፤ በምትኩ አብይ አሕመድ የተባለ “አጭበርባሪ” ከዚህ መጣ በማይባል በውጭ አገሮች ምስጢራዊ አሰራር ሥልጣን ያዘ። በምላሱ ‘ኢትዮጵያ እና እግዚአብሔር’ የሚሉ ቃላቶች እያስቀደመ ሕዝባችንን አማለለው። ትንሽ ቆይቶ የተደበቀው ማንነቱ ተገልጦ ወያኔ የመሰረተው “አፓርታይድ ሕገመንግሠትን” በጀግኖች ደም የተመሰረተ  ነው እያለ በመንከባከብ ይኼው አገሪቱ ለዘር ፍጅት እና ለውርደት ጋረጣት።

ወያኔ የሚባል ፋሺሰት ለ27 አመት ኢትዮጵያዊያንን በተለይ አማራውን ከምድረገጽ ለማጥፋት በሚዘገንን ፍጅት ፈጀው። ሴቶችም በወንዶችም እስርቤት እያስገባ በዜጎች ላይ ግብረሰዶም ፈጸመ። የ27 አመት ሥልጣኑ በሕዝብ አመጽ ተንኮታኮተ። ያንን ተከትሎ በሕገመንግሥቱ ያሰፈረውን ለዚህ ዘመን የሚጠቅመውን አንቀጽ 39 የተባለው የፋሺሰቶች አንቀጽ እውን አደርጋለሁ ብሎ ወደ መቀሌ ተሰብስቦ ጦርነት ከፍቶ ኼው “አገረ ትግራይ” መስርቷል። ወደ አዲስ አባባ ሲመጣም መሰሪ ተንኮሉ እንዳልጣለ ብዙዎቻችን አስጠንቅቀን ነበር። ሆኖም ብዙ ምሁራን እና ዜጎቻችንን ከጨፈጨፈ በሗላ ስናስጠነቅቀው የነበረውን ማስጠንቀቂያ ዛሬ በስንት መከራ ሕዝቡ “አመነን”;;

ለአንባቢዎቼ የማስገነዝበው አለኝ። ይኼውም በፋሺስቱ ወያኔ “ጥቃት ተፈጽሞበት” ወደ ትግራይ እንዲዘምት ግድ ሆኖበት የዘመተው ሰራዊታችን አብይ አህመድ የሚመራው ጦር ቢሆንም “እየመረረንም ቢሆን” የኢትዮጵያ ጦር መሆኑን መካድ አይገባም። መሪዉ አብይ አሀምድ ግን ከሓዲ ጸረ ኢትዮጵያ መሆኑን ማመን አለባችሁ። ስለሆነም ወያኔን እንደ ዓይጥ በየጥሻው ሲያራውጠው የነበረው ጦር በትግራይ ሕዝብ “አልተባበርም” ባይነት ጦርነቱ በከፊል “ተኮላሽቶ” ወደ ሗሊት አፈግፍጎ የተያዙት ቦታዎች አስረክቦ ወደ አዲስ አባባ ድንገት ተመልሷል። መራራውን ከኒና መዋጥ የግድ ነው። እንደ ጉሬዛ ከየገደሉ በመጫኛ እየተጎተተ እጁ ሲሰጥ የነበረው በደም የተጨማለቀው ወያኔ ኢትዮጵያን ጦር በጦርነት ማሸነፉን የምታምኑ ሰዎች ካላችሁ ሞኞች ናችሁ ማለት ነው። ሴራው ሌላ ነው።

የሕዝቡ አለመተባባር እንዳለ ሆኖ ከሰራዊቱም ውስጥ የታየው የመጨረሻው ኩልሽት ግን ፤ድንገተኛ  እና ያልተጠበቀ ሴራ ተፈጽሟል። ይህ አሳፋሪ ነው። አሳፋሪ የሚያደርገው በሦስት መልክ ነው። (1ኛ) አብይ አሕመድ ጦር መምራት እና ማስተዳዳር ስለማይችል ጦሩ በዚህ ሰውየ ሥር መውደቁ ለውርደት ዳርጎታል። ኢትዮጵያ መሪ ማጣትዋ ሐፍረት ተከናንበናል። (2ኛ) ሓፍረታችን ደግሞ ‘እኔ’ የተወለድኩበት አካሌ የሆነው የትግራይ ሕዝብ ከሐዲነቱን አሳይቷል። (3ተኛ) ጦሩ በተለያዩ ምክንያቶች እንደማንኛውም የዓለም ወታደር ያፈርንበት አሰራር በትግራይ ሕዝብ ላይ መፈጸሙ ይነገራል፤ አውነት ከሆነ እና ተጣርቶ ከተረጋገጠ በሥን ሥርዓት ጉድለትና ወንጀል "እናፍራለን"። እዚህ ላይ በፍርድ የተረጋገጠ ወንጀል ሰርተው ከሆኑ  በዚህ ወንጀል የተሳተፉ ጥቂት አባላቱን እንጂ የጠቅላላ ጦሩን አይመለከትም። አሁንም አርበኝነቱና አገር ወዳድነቱን አደንቃለሁ!

ሕዝቡ ለምን ከወያኔ ጋር ወገነ? ወንጀል ስለተፈጸመበት ዋተ ዋተ……….የሚለው አውነተኛውን ስዕል መሸፈኛ ከመሆን አያልፍም። ወንጀል ተፈጽሞበታል ወይ? አዎ! ግን በግፍ ወደ በረሃ ከወያኔ ጋር ሊከትት ለምን ደፈረ የሚለው ግን ምክንያቱ ሌላ ነው። ወደ ሗላ ልመልሳችሁ በ7/27/2018 ደብረጽዮን በመቀሌ ስታድየም፤ ሕዝቡን ሰብስቦ 13 ነጥብ የያዘ  የሕዝቡ ውሳኔ እንደሆነ እና ተግባራዊ እንዲሆኑ በንባብ ያስደመጠንን በወቅቱ አስነብቤአችሁ ነበር። ያንን ከፈለጋችሁ እዚሁ ፌስቡኬ ታገኙታላችሁ።

 7/27/2018 (ፈረንጅ አቆጣጠር) በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተጀመረውን የሰላም ጥረት በመደገፍ የመቐለና አካባቢው ነዋሪዎች ህዝባዊ ሰልፍ ማድረጉን ካሁን በፊት በጽሑፍ ያስቀመጥኩትን ሐተታ አሁን ለታየው ጦርነት እና የሕዝቡ ልብ መሸፈት በጣም ጠቃሚ ማሳያ ነበር። በወቅቱ የታየው ሕዝባዊ ሰልፍ እና ትዕይንቱን በቪዲዮ አሳይቼአችሁ ነበር።ያቺ ወቅት ከመቸውም ጊዜ በላይ ትግሬዎች ከኢትዮጵያዊነት ዜጋ ወጥተው በወያኔ ፋሺስታዊ ርዕዮት ስሜት በረዢም ሂደት ቀስ በቀስ ወደ ትግራዋይነት አጥር የመሽጉበት የህሊና ማፈግፍግ ያየንበት ወቅት ነበር።

ሃገረ ትግራይ የመመስረትና “ኢትዮጵያን የመበታተን” መርሃ ግብር የተቀመጠላቸው አንቀጽ 39 ምርጫቸው መሆኑን በይፋ በዕልልታ ያሰመሩበት የተቀበለበት ትዕይንት ነበር። ብዙ ሰዎች አሁን ለታየው ጦርነት ወያኔ የቀሰቀሰው ከ7 ወር በፊት እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል። መንግሥት ተብየውም እንዲሁ በዚህ ያምናል። ሆኖም አይደለም።

በመቀሌ እስታዲየም 7/27/2018 (ፈረንጅ አቆጣጠር) የተደረገው ሰልፍ ያየነው ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገው የወያኔው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶግራፍ ይዘው ነበር የተሰለፉት። ይህ ተደራርቦ የሚያሳየን ክስተት እና ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ አንባቢ ሊፈርደው ይችላል።ባጭሩ ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ስሜት በተጻራሪ እንደሆነ የሚያመላክት መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

ብዙ ጊዜ በመጽሐፍቶቼም በቃለ መጠይቆቼም ለበርካታ አመታት እንደነገርኳችሁ። እኔ ትግሬ ስለሆንኩኝ ትግራይ ውስጥ የበቀለው የፋሽስት ችግኝ እንዲነቀል ብዙ ታግያለሁ።እንደ እኔ የመሰሉ በርካታ የታሪክ አዋቂ ሽማግሌ እና ወጣቶች በወያኔዎች ጥይት ተበልተዋል። ግማሹም ጠፍተዋል፤ ተሰድደዋል፤ንብረታቸው፤ከብቶቻቸው ያለ ምንም ፍትሓዊ የሕግ ተቀውዋም ተዘርፏል (በሃሳብ ልዩነታቸው ብቻ!!)። ሰሞኑንም መቀሌ ውስጥ ያንን መሳይ ግድያ ተደግሟል። እንዲያም ትግል አድርገንም ቢሆን መጨረሻ ተከታዮቹ የተከተሉት ርዕዮት “አሁን ወደ አሉበት የጭንቅ የመከራ የመገለል፤የመዋረድ፤የመጠማት ዕድል እንደደረሳቸው” እያየን ነው።

አሁን ግን በባሰ መልኩ በሙዚቃ እና በጀብደኝነት እንደተለመደው ጦዘው ወራሪን አባርረን “ሃገር ትግራይ” መስርተናል፤  ብለውናል። እኛም እንኳን ደስ አላችሁ ብለናል። እንኳን ደስ አላችሁ ስንላቸው ከጦዘው ደስታቸው ጋር “ማዕቀቡንም” በደስታ መቀበል እንጂ “ለጌቶቻቸው ኢሜሪያሊስቶች” መብራት፤ነዳጅ፤ስልክ ኢንተርኔት፤አየር መንገድ፤ የመኪና መንገድ፤ ባንክ እህል ወዘተ…… ተዘግቶ ማዕቀብ ተደርጎብናል እና ማዕቀቡ ይቁም ፤ ድምበሩን ክፈቱልን የሚል አቤቱታ እንዳያስሙ እንማጸናቸዋለን። ባለሱሬ ሱሬውን አጥbeቆ መቆም አለበት እንጂ ከማያውቃት የጠላት አገር “ማዕቀቡ እንዲከፈትለት” መጠየቅና ማለቃቀስ የለበትም።

ዛሬ የታየው የጦሩ ወደ ሗላ ማፈግፈግ ተሸንፎ ነው የሚለው ዝባዝንኬ አልቀበለውም። አሁን የሆነው ለ17 አመት የተካሄደው ጸረ አማራ የተከተሉት የፋሺዝም መስመር በደርግ የሚታዘዘው ሠራዊት በውስጥ አስተዳደር ጉድለት በደረሰበት የሞራል መላሸቅ ሆን ብሎ መዋጋቱን በማቆም ‘መሳርያውን እየጣለ “ፋሺስዝም በኢትዮጵያ ለማስፈን” ሲታገሉ ለነበሩት የትግራይ ታጋዮች እጁን በመስጠት፤ ወያኔዎች ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ መደረጉን አስታውሱ።

በወቅቱ ተጫዋች የነበረው ድግሞ ልክ እንደ ዛሬው “የትግራይ ሕዝብ” ነው። የትግራይ ሕዝብ ያበረከተልን የፋሺዝም መሪ “መለስ ዜናዊ” ወደ ሥልጣን አስገብቶ ጣሊያኖች ያሰመሩቱትን የፋሺስቶች አስተዳዳር በማስቀጠል “ወደብ ዘግቶ” ‘ኢትዮጵያ በቋንቋ እና በነገድ” ሸንሽኖ ያፈረሰ ወያኔ የተባለ እና መለስ የተባለው መሪ አበረከተውልናል። የትግራይ ሕዝብ የሰራው ወንጀል ቁጥር አንድ መዝግቡልኝ። ዛሬም በቁጥር ሁለት እሱንን ደግፎ ፏሲዝም በመምረጥ ተነጥሏል። የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን ይወዳል የሚል ዝባዝንኬ ካሁን ወዲህ መስማት በበኩሌ አልፈልግም፤ አምኜውም አላውቅም። እንዲህ የምለውም ለ47 አመት የታዘብኩት ስለሆነ!!! በምክንያት ነው።

 “መጀመሪያ እኔ ሰው ነኝ” የሚለውን ከማስቀደም ይልቅ “መጀመሪያ እኔ ትግራዋይነቴን ቀዳሚው እንጂ ሰው በመሆኔ ሰብኣዊነቴን ወይንም አገራዊነቴን አላስቀድምም” እንዲል የተበከለው የትግራይ ወጣትም “ኢትዮጵያን እየረገመ” ኢትዮጵያን የጠላት አገር ብሎ በመሰየም ‘ሃገረ ትግራይ” እና “ትግራይ ትግርኚን” የመመስረት ቅዠት እውን ለማድረግ በሙሉ ሃይሉ “ከህጻን እስከ አዋቂ” ወደ በረሃ ሄዶ የፋሺሰት የሽምቅ ተዋጊ ወታደር እንደሆነ በተግባር አረጋግጦልናል። ይኼ በተንኮል ሴራ የተመታ ሠራዊት ያሸነፈ መስሎት ሲፎክር ማድመጥም አንጅትን ያስቆጣል። ግን መራራ ሐቅ ነውና መቀበል ነው።

ማወቅ ያለባችሁ “ለ47” አመት ወጣቱም ሕዝቡም የተሰለፈው በኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅአላማ ስር ሳይሆን “የሼል ነዳጅ እና የሜክዳኖልድ ምልክት የሆነው “ቀይ እና ቢጫ” ምልክት ያለው የወያኔ ባንዴራ ሥር ነው። እዚህ ላይ በግልጽ የትግራይ ሕዝብ ምርጫው ምን እንደሆነ አሳይቶናል። ስለዚህም “ኣንታ ወያናይ ትግራዋይ” (የትግሬ ወያናይ ፤ አንተ እምቢተኛው፤ ሃሞተ ኮስታራው!) በማለት በጣም የተጋነነ ነገዳዊ ፋሽስታዊ የማበረታቻ ፕሮፓጋንዳ የተሞላ በረሃ ውስጥ እየጨፈረ ለ7 ወር ቆይቶ አብይ አሕመድ ባደረገው የፈረንጅ የሴራ ክንዋኔ እና ጠንከር ያለ የጦር ዲሲፕሊናዊ አመራር አለመውሰድ ምክንያት አንዳንድ የጦሩ አባላት ባሳዩት ወራዳ ተግባር ምክንያት ወያኔ መቀሌን ለመቆጣጠር በቅቷል።  አሁን እኔ የምጠይቀው “እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትነህ ወርቅነትህን ዓለም ሙሉ አስመሰከረሃል” እያሉ የሚዘምሩ “የትግራይ ትዕወት/አሸንፋለች” ዘማሪዎች፤ የምጠይቀው አብይ አያደርገውም እንጂ ወርቅ ናችሁ እና “የማዕቀቡንም እሳት ውስጥ ገብታችሁ ወርቅነታችሁ እንድታረጋግጡ እጠይቃለሁ” ።

                 አመድ ልሳ እንደተነሳችው እንደ “ፎኒክስዋ ወፍችሁ ‘ዳግም ልደታችሁ” ለማየት በዚህ በማዕቀብ ፈተና እንዲፈትናችሁ ኢትዮጵያን ሕዝብ እጠይቃለሁ። (ሼር በማድረግ ሕዝቡን አንቁ፤ መረጃ ሃይል ነው!!!!)

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

No comments: