Adwans are the Chiefs of the Chiefs among the TPLF
ክፍል -2- የዓድዋዉ ቡድን ህወሐትን እየመራ ነዉ
ጌታቸዉ ረዳ
ወደ ዋናዉ አርዕሰት ይዤአችሁ ከመሄዴ በፊት፤ በክፍል-1- (የመጨረሻዉ ሐተታየ- የግልፍተኝነት የእንካ ቴስታ…በሚለዉ) ገብሩ አስራት በተገኘበት መድረክ ተደርጎ በነበረዉ የጥያቄ እና መልስ ላይ ባለፈዉ አንስቼዉ ከነበረዉ አንድ ዋናዉ ለሐተታየ መነሻ በአንድ የትግራይ ሰዉ እና አቶ ጌታቸዉ… በተባሉ ሰዉ በአስተያየት መረዳት ላይ ያለ መግባባት እንደበረ ገልጨ ነበር። ፡አንባቢዎች በኢ-ጦማር ጽፈዉ “ዋን ሞር ታይም-“ በሚለዉ የፈረንጅ አባባል “አንዴ ደግመህ ግልጽ ብታደረገዉ?” ብለዉ ስለጠየቁኝ ያኔ ተዘንግቶ ያልጠቀስኩት የመጀመሪያ የአቶ ጌታቸዉ…. ንግግር (ጥያቄ) ዛሬ የአቶ ጌታቸዉን አባባል ቃል በቃል ምን ብለዉ ገብሩን እንደጠየቁት ልግለጽ ።
ባጭሩ ሰዉየዉ የጠየቁት <ከገዢዉ የህወሓት አመራር መሃል ዉስጥ አንቀጽ 39 ኝን እንዲቆይ የሚፈልጉት የመገንጠል ፍላጎት ያላቸዉ ስላለቸዉ ነዉ ወይ..? ብለዉ የጠየቁትን ጥያቄ፡ አስተያየቱ ለትግራይ ሕዝብ ነዉ ብሎ የተቆጣዉ አድማጭ ስሕተቱን ለማሳየት የአቶ ጌታቸዉ ሙሉዉን ጥያቄ ይሄዉ። የአቶ ጌታቸዉ… ጥያቄ ቃል በቃሉ እነሆ፦ <<…ካማራዉ እየለመነ የሚኖርበት ሁኔታ እንቀበልም፡ ስለዚህ በመገንጠልም አማራጭ የሆነዉን ኢንፍራስትራክቸር እና ሌሎች መደላድሎች አዘጋጅተን መቆየት አለብን፤ ከሕገ መንግሥቱም ዉስጥ እንቀጽ 39ኝን መቆት አለበት የሚለዉ አመለካከታቸዉ ከዚህ ነዉ ወይ የሚመነጨዉ? የዚህ ዓይነት የመገንጠል ስሜት አመለካከት ከሚመሩት ሰዎች መሃል አለ ወይ?>> የጥያቄዉ መጨረሻ።
እንግዲህ ይህ ነበር የተጠየቀዉ። ይህ እንደ ጥያቄ ነዉ የቀረበዉ (ያዉም ሁሉንም አመራር አላሉም -ህወሐትን ከሚመሩ ሰዎች መሃል አለ ወይ? ነበር ጥያቄዉ። የተቆጣዉ ትግራዩ ሰዉ ምን አለ?
ልጥቀስ <<“….. ያለዉ ነገር ሰምታችሁታል? አንድ የተናገረዉ መርዝ አለ።ምንድ ነዉ ያለዉ!? አማራዉን አስከ መቸ ጊዜ ድረስ ልንለምን ነዉ ብላችሁ ልትገነጠሉ ነዉ ወይ? አለን!.. Right at our face!!! How dare!? አንዴት?... እንደዚህ እየተናገርን ነዉ መለስን ምናወረደዉ?.......... አሜሪካ ዉስጥ ያለዉ ከ-----አስ.. ከ አፍራሽ ነዉ። ሕዝብ እና መንግሥት መለየት አልቻልንም!”
በወገንተንነት ስሜት ተደግፈዉ ደማቅ “ጭብጨባ”ተለገሰለት። መንግሥት እና ሕዝብ ለይቶ የቀረበ ጥያቄ መረዳት ያቃተዉ ማን ነበር?፡ መለየት ያቃተዉ ሰዉ እና ዕዉራን አጨብጫቢዎቹ ወይስ የአቶ ጌታቸዉ ጥያቄ? አስቲ ይህነን የመገንጠሉ እና የልማቱ ወገናዊነት የግንባታ ጥድፍያዉ እዉን መሆኑን አኔን ካላመናችሁ በሌሎች መረጃዎች መልክ ላቅርበላችሁ።
ልጥቀስ TPLF's secret document
According to information obtained in Addis Ababa by The Indian Ocean Newsletter, the Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi has written a 22 page document entitled Tigray in the new Millenium calling for a strengthening of the construction of a Tigray Regional State which is in a position to “survive on its own means if necessary”. This text was approved by Seyoum Mesfin, Abay Tsehaye and Sebhat Nega and is now circulating in the executive circles of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF, hard core of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front in power in Addis Ababa) as a confidential document. According to our sources, it lists the various infrastructure projects already completed in Tigray, laying special emphasis on the Tekezie hydro-electric dam for its role in the electrification of the country, calls for the expansion of other sectors of activity in this region in the North of Ethiopia and praises the close relations between the Tigray Regional State and China. This text also considers that the Tigrayan Diaspora abroad should be “educated and mobilized to invest” in this regional state. Finally, it stresses the need to establish close relations with certain Eritrean opponents. This theoretical assemblage is similar to the thesis in favor of creating an independent state, coupling Ethiopian Tigrayans and Christian Eritreans from the high plateaux. The idea of such a Tigray-Tigrigni State was favored two decades ago by certain Ethiopian Tigrayan and Eritrean nationalists. .ምንጭ Ethiomedia.comይችንም ጣል ላድርግላችሁ፡Addis Engineering Consulting 10,000,000; Mesfin Industral comp 500,000,000; SUR Construction 150,000,000; Star Pharmacculicals 53,000,000 Almaden Garment Factory 660,000,000 እያለ በጠቅላላ 50 እንዱስትሪዎች/ፋበሪካዎች/ኢነሹራንስ ኩባኒአዎች/የጭነት ታንክ መጠገጫ እና መለዋወቻ ዕቃዎች የሚገልጽ list of TPLF Companies established between the year 1992-1997 EC“ የሚለዉ ዘገባ አንብቡት እና በሌሎቹ ግፍለሀገራት ኢትዮጵያ ጋር የእሴቱ ክምችት ኣና የኩባንያዎቹ ብዛት እና ፍጥነት አወዳድሩት።
ወደ ሁለተኛዉ ጥያቄ ልዉስዳችሁ።
ገብሩ አስራት፡ አሜሪካ አገር ነዉ ያለዉ ብያለሁ። እየተዘዋወረም ስለ ጎሳ ድርጅቱ ገለጻ እያደረገ ነዉ። በእገረ-መንገዱ በዝርፍያም በሕግም ያከማቹትን ሃብት ለሌላዉ ሳትቆጩ ልትግራይ ብቻ እያዳላችሁ ትግራይን አበልጽጋችሗል፡ የሚሉትን ክሶች ገበሩም ሆነ ባጠቃላይ የወያኔ መሪዎች እና ፡ይግረም ብሎም፤ የመለስ አብዛኛዉ ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያምኑት ለትግራይ አልተደረገልትም አድልዎ አልተፈጸመም እያሉ ይከላከሉላቸዋል።ኩባኒያ ካለ ተጠቃሚዉ ከፍጆታ እና ከቀረቤታዉ ሕግ (ኢኮኖሚሰት ባልሆንም -ተራ ዕዉቀት የሚያዉቀዉ ነዉ እና…) ህዝቡ የሚሸምተዉ ጎንደር ይም ወሎ በኮሎኛ ወይም በወረፋ እየጠበቀ ሳይሆን በቀጥታ እቤቱ ደጃፍ የተተከለለትን ኢንዱስትሪዉ የሚያፈራዉን ሸቀጥ /ዉጤት ነዉ እሩቅ ሳይጓዝ ለወራት ሳይጠብቅ ሚያገኘዉ(ሓዋርያ ላይ ያቀረብኩትን ጽሁፍ አንብቡት)። ምንም ብትሉ ምንም በፍጆታ እና በቀረቤታ ሕግ የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ነዉ! መቀሌ ከተማ እያንዳንዱ የቤተሰብ መኖርያ ብታዩት (መረጃዉ እንደደረሰኝ ሳሎን ያልነበረዉ ዘመናዊ ሳሎን፤የቤት ዕቃዉ ዓይነት በጣም ንጹህ እና ዘመናዊ አንደሆነ ነዉ። የመቀሌ ሱቆቹ በሙሉ የኤሌከትሮኒክ ዕቃዎች ተገጥግጠዉበታል…የታክሲዉ ብዛት “በጃጅ” እየተባሉ የሚጠሩት (የአስመራ ልጆች-ላመብሬታ ብለዉ ሚጠሯቸዉ) የሞተር ሳይክል ታክሲዎች ከተማዉ ኣእላፍ ታክሲ መኪኖች እሽቅድድም አጣብበዉታል። ፈራ ተባ ለምንድ ነዉ ሃቅ መናገር ያስፈራል? አንወያይ!
አለማፈራቸዉ 10 ሺህ አና 20 ሺህ ዶላር ከስንት ዓመት አንዴ ከትግራይ ተወላጆች ከዚህም ከዛም የምትጠረቃቀመችዋን ገንዘብ (ኮንትርቢዩሽን- እርጥባን ) በቢልዮኖች ዶላሮች የሚንቀሳቀስ አሁን ላለዉ ሰፊ የትግራይ ልማት ዕድገት ምንጩ ከኪሳችን የተወጣጣ ነዉ፡ በማለት ወያኔዎች የደለሉዋቸዉን መሸፈኛ ቅጥፈት ተመልሰዉ ያንኑ ሞኝነታቸዉ በማስረዳት የወያኔ አድልዎ እና ዘረፋ ለመከላከል ይጥራሉ።
ይህንን በሚመለከት በክፍል -3- ከጥቂት ቀናት በሗላ ስለሚቀርብ አዚሁ አንተዉና ወደ ሁለተኛዉ የአቶ ጌታቸዉ ሌላኛዉ ስለ ዓድዋ ቡድን ስልጣን የመምራቱ ጥያቄ እነሆ፦
<<በመንግሥቱ መዋቅር ላይ በተለያዩ ሥራዎች ከአማራዉ፤ከ ኦሮሞዉ..ወዘተ ግለሰዎች በአምባሳደር ደረጃ አና ሌላ ሌላ ስልጣን ቢኖሩም ዉሳኔ የሚሰጡ እና የሚቆጣጠሩት ሰዎች የትግራይ ከትግራይም ደግሞ ከዓድዋ ምናልባትም ደግሞ የኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ዲቃላዎች መሆናቸዉ አጠራጣሪ ነዉ ወይ?>>
የሚለዉ ጥያቄ አቶ ገብሩ አስራት አጣምሞ ያልተባለዉን ነገር የዓድዋ ሕዝብ ተጠቅሟል የተባለ አስመስሎ ያልሆነ መልስ ሰጥቷል። አዎን ስርዓቱን በበላይነት የሚመሩት በዋናነት የዓድዋ ልጆች ናቸዉ ላለማለት ፈርቶ “አልለማንም፤አላደግንም፤ተቸግረናል ብሎ የሚጨሆዉ ያዉም የዓድዋ ሕዝብ ነዉ። እንትጮ፤የዓዲ ዓፍሮም፤የነበለት. የገጠር ሕዘብ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል..ወዘተ…> በማለት ዝባዝንኬ አነብንቧል። የተጠየቀዉ ቀጥተኛ ጥያቄ ገብፋ በአዉራጃዊነት፤ የመቧደንና ትሸሽት የመኖሩ ለመካዱ ለመሸፈኛ ወደ ሕዝቡ አቤቱታ እያንተራሰ ላለመመለስ ሲሸሽ ተደምጧል።
በበላይ የሚመሩት በዋናነት ዓድዋ ናቸዉ ። ይሄ ደግሞ አጠራጣሪ አይደለም። አቶ ገብሩ እንዴት ትመለከተዋለህ? ነዉ የተባለዉ። ይሄ ለኛ በጣም ግልጽ ነዉ።ጎጠኞች ናቸዉ። ብሎም መንደርተኞች ናቸዉ፡ ነበር የጠያቂዉ መልእክት። ገብሩ ይህ ሁኔታ ከካደዉ፤ የበረሃዉ የድሮዉ የ “አሽዓ” “ሕንፍሽፍሽ (ዓድዋ አኽሱም ሽሬ” ) አንደለመደዉ ሊክደዉ መመኮሩ ነዉ። ዶ/ር ሃይሉ መንገሻ (ሎስ አንጀለስ) እና ግርማይ ለማ (ግርማይ በህሊ)- (ችካጎ) እና ሌሎች ሺህ ታጋዮች ለሕንፍሽፍሽ መነሻዉ አዉራጃዊነት እና ጎጠኝት እንደነበረ በደምብ ያስረዱት ጉዳይ ነዉ። አሁን በገብሩ መደምደሚያ እነ ስብሐት ነጋ ከዓድዋዊ ስሜት ነጻ ናቸዉ እያለ እየሞገተን ከሆነ፤- አቶ ገብሩ ማን ነበሩ? የሚለዉ ብስራት አማረ “ከዚያ አስከ እዘህ ድረስ ያደረሰዉ መንገድ” በሐዋሪያ ጋዜጣ መመለክት ነዉ። ካስፈለገም፤ አንባቢዎች እንዳቀርብላቸዉ ከጠየቁኝ ላቀርበዉ እሞክራለሁ።
ስለዚህ ገብሩ የተጠየቀዉን ትቶ “ዓድዋዉ ቡድን ስርዓቱን እየመራ ይሆን? ለሚለዉ ጥያቄ “ ቡዱኑ ለዓድዋ ሕዝብ እየጠቀመ ነዉ እንደተባለ አስመስሎ ዉዥምብር ዉስጥ መግባቱ - ግራ አጋቢ ነዉ።መንግሥቱ ሃይለማርያም የራሱን ኮርሶች (አብረዉ ከእርሱ ጋር የተመረቁ ዋና ዋና ቁልፍ ቦታዎችንና የምስጢር ስራዎችን እንዲሁም የሚዋሹለትንም ሲመለምል እንደነበረዉ እና የሗላሗላም ሲመናመን ወይም ሲክዱት ፤ሌሎች ለሱ ተገዢ መሆኑን ሲያረጋግጥ፤ ቦታ ሰጥቷቸዉ ነበር። ልክ መንግሥቱን ከከዱት የኮርሱ ልጆች መለስም ከዓድዋዉ የከዱት እነ ዓለምሰገድ ገብረ አምላክ (የወያነ የርእዮተ-ዓለም ሃለፊ የነበረዉ) እና እነ አዉዓሎም ወልዱ/ትኩእ ወልዱ (የኤርትራ አምባሳደር የነበረዉ-በአባቱ ኤርትራዊ- አሁን ገብሩ አስራት ምክትል የዓረና ሃላፊዉ ያሉበት) ታናሽ ወንድሙ ለመለስ ዜናዊ ያደረዉ አባይ ዴራ/አባይ ወልዱ (ትግራይ ዉስጥ ከፍተኛ የህወሐት ባለ ስልጣንና የመአከላዊ ኮሚቴ አባል)። ልክ ገብሩ ዳር ዳሩን ነካ ነካ እንዳደረገዉ ከዚያም ከዚህም ስልጣን ላይ ያሉ አሉበት። ያዉም የአሉላንና የዮሐንስን ቃል የከዱ ከያካባቢዉ የተጠረቃቀሙ ሆዳሞችና ሚጢጢዎች ባለስልጣኖች የእንደርታ፤ራያ ዓዘቦ፤ተምቤን፤የዓጋመ አዉራጃ ችዋዋዎች (ቡችሎች) እና በጣም ጥቂት ከ አክሱም፤ከሽሬ ተሰግስገዉበታል፡ ነገር ግን ዋናዎቹ ፊታዉራሪዎቹ የኤርትራዉና የዓድዋዉ ጋንግስተሮቹ ነዉ ብለን በ እርግጠኝነት አሰምርበታለሁ። ለዚህም ነዉ በጣም አስገራሚ የሆነ መረጃ (ለጊዜዉ የት እንደሰወርኩት አጥቸዋለሁ ሆኖም ፈልጌ መዋቅሮቹን ላቀርብላቸሁ ነዉ። “ፈራ ተባዉ!” አልገባኝም።
ይህንን በአንድ አክሱማዊ የተጻፈ እሮሮ “ጊዜ ስታገኙ ያሁ.ካም ገብታችሁ አንብቡ Another Axumite Victim - Kinfe G/Medhin! By: Gobezay Wedi-Tigray, M.A
እነ ገብሩ የተጠየቁትን ጠለቅ ብለዉ ሚስጥር ለመግለጽ የማይፈልጉበት ምክንያት ለምን እነደ ሆነ ልንገራቸሁ? ልጥቀስ፦
“They were mute, and their muteness was rather hailed as "iron-discipline. People would openly say "there is no slip of the tongue with TPLF leaders. If they want, they can listen to you all day long - if necessary for days and weeks - and in the end, you haven't heard a word from them while they have gone away with tons of information about you."…….” "TPLF leaders never leak secrets. They never knew that transparency –“------“Both the Ethiopian and masked Eritreans lived as members of the TPLF family for nearly 30 years. When the Ethiopians woke up from their long slumber, and asked Meles, "Who are you?"…” ምንጭ ኢትዮ-ሚድያ “TPLF’s Secret Document.”
ሌላዉ ስለ ትግራይ እድገት እና አድልዎ የተናገረዉ ሁኔታ ምን ለማለት እንደፈለገ ግራ ገብቶኛል። የሚቀጥለዉ አባባሉን ልጥቀስ << አዲስ አበባ ወደ እሩብ ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ አለ። 90-95% በድህነት አረንቋ ዉስጥ የሚገኝ እንጂ እንደሌላዉ ሕዝብ ሃብትም ያፈራ አይመስለኝም። ስለዚህ በተለየ አጠቃቀም ተጠቃሚ ነዉ የሚለዉ እኔ አይገባኝም>>። ይላል ገብሩ አስራት።
በዚህ አነጋገሩ ከሄድን “እንደ ሌላዉ” ህዝብ “ሃብትም ያፈራ” አይመስለኝም ሲል- ሌላዉ ሃበት አፍርቶ እነኚህ ሰዎች ሃበት ያላፈሩበት ምክንያት መለስ/ህወሓት ሌላዉን ሕዝብ እየጠቀመ /ሀብት እንዲያፈራ ሲያደርግ/ሲረዳ ትግሬዎቹ ሃብት እንዳያፈሩ እያዳላ ነዉ ለማለት ይሆን? የትግራይ ሕዝብ በልማት የተራመደዉ ታታሪ በመሆኑ እና አስተዳዳሪዎቹም ከሌሎቹ አስተዳዳሪዎች ብልህ እና ታታሪዎች በመሆናቸዉ ነዉ! ተብሎ ነበር “በዘመነ ገብሩ” ትዝ ይ ላችሗል? መለስ እና አርከበ እንዲሁም ቱባ ወያኔዎች ፤ታታሪ የወርቅ ልጆች በሚያስተዳድሩት ከተማ አዲስ አበባ እንዴት 95% ትገሬዉ ድሃ ሆነ? በዚህ ስሌት 95% በድህነት አረንቋ ወለል እየኖረ ከሆነ ትግራይ ዉስጥ ያለዉ ኗሪም 95 በመቶ በድህነት አረንቋ ነዉ ማለት ነዉ ወይስ ስሌቱ ይለያያል? ክፍል 3 ከጥቂት ቀናት በሗላ ወደ ዋናዉ ክርክር እንገባለን።-….. ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment