Thursday, October 9, 2008

በገብሩ አስራት ላይ እመሰክራለሁ ያለን በቀለም ያበደ በጥንቃቄ የተደጎሰዉ ታሪክ ለምስክርነት ቀጠሮ ያስያዘዉ ባለ 160ዉ ገጽ መጽሐፍ

በገብሩ አስራት ላይ እመሰክራለሁ ያለን
በቀለም ያበደ በጥንቃቄ የተደጎሰዉ
ታሪክ ለምስክርነት ቀጠሮ ያስያዘዉ
ባለ 160ዉ ገጽ መጽሐፍ
ጌታቸዉ ረዳ ወያነ ትግራይ ለጎሳዉ እያዳላ ሌሎቹን በእኩል ዓይን እና በልበ ርሕሩህ አልተመለከታቸዉም። በዚህ ምክንያት ከሌሎቹ ይልቅ በተለያዩ-ጠቀሜታዎች/የማሕደረ ትምሕርት (ስኮላርሺፕ) ዕድሎችና እንደዚሁም ልማትም ጨምሮ የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ ሆኗል። የሚለዉን አቋማችን ገብሩ አስራት (ወያኔዎች እና ተከታዮቻቸዉ) እና በጠቅላላዉም የወያኔ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጭምር “ከ.. እስ..ከ በሙሉ” ክርክራችንን ተቃዉመዉታል።
የመንግሥት ሥልጣን ተጠቅሞ ለቤተስብ እና ለብሔሩ ሲያዳላ የተገኘ ባለ ስልጣን ወንጀል በመሆኑ ለወደፊቱ በሕግ ፊት እንደሚያስቀጣ ያዉቃል እና አልተደረገለትም ብለዉ ወያኔዎች ቢከራከሩ የሚአስገርም አይደለም። የሚያስገርመዉ ግን “ተቃዋሚዎች” የተባሉት በዚህ ረገድ ከወያኔዎች ጋር መስማማታቸዉ እና ሲከላከሉላቸዉ ማድመጥ ለምን ተብሎ አንደሆነ ትንሽ ይገርመኛል።ገብሩ ‘’ከአማራ፤ ከኦሮሞ፤ከአፋር ከአደሬ…..ወዘተ የወያኔ ባለሞያዎችና አሽቃባጮቻቸዉ ሃበታም ሆነዋል..ወዘተ፡ ነገር ግን እነዚህ ወገኖች ትግራይን ለመጥቀም ተነስተዋል ወይም እየጠቀሙ ነዉ ብሎ በአድልዎ መክሰስ ልክ አይደለም። በማለት የተደረጉት ልማቶች ከሌሎቹ አካባቢዎች ምሳሌ እያመጣ ሊከላከል ተደምጧል።
ካፍንጫ የማይርቅ የገብሩ አስራት እነ መለስ ዜናዊ፤ጸጋይ-በርሄ፤ቴድሮስ ሐጎስ፤ስብሐት ነጋ ወዘተ በልማት በኩል ለትግራይ የጠቀሙት ነገር የለም፡ አድለዎ አላደረጉም ይለናል። የነሱ ተከላካይ መሆኑን ወደ ጎን እንተወዉና፤ ወደ ራሱ ወደ 10 ዓመቱ ዘመን እሱ የሚያዉቀዉ የአድልዎ ዘመን ላንዳፍታ እንጓዝ እና ራሱን አንዲከላከል እንጠይቀዉ።
ከዚያ በፊት ግን አንድ ልበላችሁ።“ትግራይ ኢንዱሰትሪ ቢተከል እኔ ችግር የለብኝም፤ ሌለዉም -“ክልል”-አብሮ ይጠቀማል ማለት ነዉ”- የሚለዉ የገብሩ እና መላዉ የወያኔ ተከታዮች አነጋገር ሳትረሱ ወደ ሰፊዉ ክርክር በሗላ ስለምመለስበት በልቦናችሁ ያዙት። የትግራይ ተወላጆች በለስ ቀንቷቸዉ በብረት መንግሥታዊ ሥልጣን ከመቆጣጠራቸዉ በላይ ያገኙትን ሥልጣን መከታ አድረገዉ ለጎሳቸዉ ለትግራይ ክፍለሀገር ኗሪ በተለያዪ መንገዶች ጠቀመዉታል እና አድገናል ካሉ አብረን አላደግንም። በሚሉ እና “የለም አልጠቀሙትም” ከሌሎቹ ጋር በዕኩል ይመለከቱታል፤ልየ ትኩረት አልሰጡትም”። በሚሉ አቋሞች የጠራ ክርክር አስካሁን ድረስ አልተደረገ የሚል።ያልተደረገበት ምክንያትም “ፈራ -ተባ” የሚለዉ ተቃዋሚዉም “ተጠቅሟል ብንል የትግራይ ሕዝብ ሊቀየምን፤ሊነጥለን ነዉ፤ ደጋፊ አናገኝም” እያለ አንደሚዋቃዥቅ ጥርጥር የለኝም።
ወይንም በትግራይ ክፍለሃገር ተወላጆች የመካራከሪያ “ሦስት” መካራከሪያ ነጥቦቻቸዉ። (1)“ይህንን ካልን ለወደፊቱ ህዝባችንን ለጥቃት እናጋልጠዋለን” (2)ይህችን ካልን ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ድጋፍ ሊያሳጣን ነዉ።ለነፍጠኞቹ ቂም አጋልጠዉ ሰጥተዉ ለወደፊት ጥቃት እያጋለጡሁ ነዉ ወዘተ.. እያለ የትግረይን ሕዝብ ድጋፍ ሊያሳጣን ነዉ” (3) የፈለገዉ ቢጠቅመዉም፡ልጆቹን ገብሮ በደሙ ደርግን ገርስሶ ለሌሎቹ “ነፃነት ስላመጣለት” ቢደረግለትም ይገባዋል! ማን በሞተልት ሊጠቀም ነዉ? የሚሉ አሉ። የታቃዋሚዎቹም ሆነ የወያኔ ወይም ወያኔ ያልሆኑ የትግራይ ሰዎች አልተጠቀመም የሚለዉ አቋምና፤ “የራሰው ምታት ይዞህ አስፕሪን እንኳ እንደልብ የማይገኝበት የነበረዉ አካባቢ ትልቁ የአፍሪቃ የመድሃኒት -ፋርማሲ የሚቀመምበት ቦታ ሲያቋቁሙለት አንዴት ሲሆን አልተጠቀመም ይባላል? የሚሉ በተቃራኒ የቆሙ የዜጎች እሮሮ ”ከተደመጠ ወደ16 ዓመታት ሆኖታል። ይህ እሮሮ በከንቱ ለይስሙላ የመጣ እሮሮ አይደለም። ዕሮሮዉ እዉነታን ይዞ ቆሟል።
ክርክሩ ይፋ እንዳይሆን መከላከያዉ አጥር ብዙ ነዉ። በ10 ዓመቱ የገብሩ ዘመን ኢትዮጵያ የምትባል ምድር ከትግራይ ክፍለሃገር አካባቢ በዕኩል እያደገ ነበር? ለሚል ጠያቂ- በእኛ በኩል አላደገም፡ አድሎዎ ተደርጓል ብለናል። አድልዎ የሚፈጽመዉ የትግራይ ህዝብ ሳይሆን ያ በወያኔ ትግራይ ስም ስልጣን የያዘ የዓድዋዉ ቡድን እና የዮሐንስን እና የአሉላን ኢትዮጵአዊ መንፈስና ያስረከቡንን ድመበር ንቀዉ እና አጥላልተዉ ለግማሽ ዓድዋ እና ለግማሽ ኤርትራዊ ትዉልድ ላላቸዉ ጥቂት ድርጅቱን በበላይንት ለሚመሩ አፈጮሌዎችና አታላዮች ጭራቸዉ በመቁላት በተለይም ለከርሳቸዉ ያደሩ፤ ከእንደርታ እና ከራያ-ዓዘቦ፤ከዓጋሜ፤ከተምቤን ከሽሬ’ ከአክሱም ሁለት አዉላዕሎ…ወዘተ…. የተዉጣጡ ጥቂት “ጭራቸዉን የሚቆሉላቸዉ ዉሾቻቸዉ” ወገንተኞች እንጂ ሕዘቡ ዘርፈህ አብላኝ ብሎ ትዕዛዝ አላስተላለፈም እና በሃላፊነት የሚጠየቅበት መንገድ የለም።
ይህነን ስንል የትግራይ ሕዝብ እንዳለ በሞላ ተጠቅሟል ወይም የፍሬዉ ተቋዳሽ ሆኗል ማለት አይደለም። በሌላ አነጋገር ትግራይ ዉስጥ የተቸገሩ የሉም ማለት አይደለም። በሺዎቹ አሉ። ነገር ግን፤ከሌላዉ ሲነጻጸር በፍጹም የማይታለም ነዉ (ሪፖርቱን ማንበብ ነዉ)። አዲስ አበባ ዉስጥ ከትግራይ የመጣ ሰዉ በልመና ተሰማርቶ እየለመነ አገኘሁት ብሎ በጥቆማ ለትግራይ የመልሶ ማቋቋም ድርጅት ባለስልጣኖች ወይም ለሚመለከተዉ ማንም የትግራይ ነክ ቅርንቻፍ ለጠቆመ ጠቋሚ ለእያንዳነዱ ጥቆማ $1000 ብር ፤ ከትግራይ የመጡ 20 ለማኞች ከጠቆመ 1000x20= $20.000 ሃያ ሺህ ብር ሽልማት/ጉርሻ ይሰጠዋል። እንክብካቤዉ እና ለጎሳዉ መስገብገቡ አስከዚህ መጥቋል መለቴ ነዉ(ምንጭ “ገዛ ተጋሩ ፓል ቶክ” እያሉ የሚጠሩት “ ወገባቸዉን አለጥልጠዉ አመቻችተዉ በወያኔ ለመገዛት የተዘጋጁ አዳዲስ ምስኪኖች እና በማህደረ- ትምህርት ለትምህርት ወደ ዉጭ የላካቸዉ የድሮ ታጋዮቹንም ጭምር ያካተተ የጎሰኝነት ትኩሳታቸዉ የሚለቅቁበት የፓል ቶክ መድረክ በእንግዳነት የመልሶ ማቋቋም ባለስልጣኖች ለቃለ መጠይቅ አቅርበዋቸዉ ከተናገሩት “አይጋፎረም” ላይ የተለጠፈ የድምጽ ማሕደር (አዉዲዮ)።
ይህ ለአንድ ጥቆማ 1000 ሺህ ብር የሚከፈለዉ ከትግራይ ለመጣ ለማኝ የሚጠቁም እንጂ ከወለጋ ወይም ከጎጃም፤ወሎ፤ጎንደር ወይም ከሐረር ወዘተ… ለመጣ ለማኝን የሚጠቁም ጠቋሚ ሰዉ አይመለከትም። (እያዳመጣችሁን ነዉ?!)
ልቀጥል። እንግዲህ ከላይ የተባበልነዉን ለማስታወስ ያህል፤ በአድልዎ የመጠየቀዉ ድርጅቱን እና ስርዓቱን የሚመሩ አድልዎ ፈጻሚዎቹ ብቻ ናቸዉ እያልን ስንጠቁም፡ ቡድኑ ራሱን ላለማጋለጥ እና የትግራይን ሕዝብ ድጋፍ ለማግኘት ሲል እንዲሁም አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆችም “ሕዝባችን ሳይበላ በልቷል-ተጠቃሚ ነዉ እያሉ፡ ለጥቃት እያጋለጡት ነዉ።” እያሉ የተገላቢጦሽ እኛኑን ተመልሰዉ ይከሱናል።አድልዎ አልተፈጸመም ዕኩል እያደጉ ናቸዉ ብለዉ ከሌሎቹ ክፍላተ ሀገሮች የሚከራከሩበት የልማት ማወዳደርያ ሰነድ ግን አስከዚችዉ ደቀቃ ድረስ አላቀረቡልንም! እናቅርብ እንኳ ቢሉም ከየት ይመጣል! አያቀርቡም።እነ ጌታቸዉ ረዳ እና ጥቂት ኢትዮጵያዉያን “ተከሳሹ” “የትግራይ ህዝብ ነዉ” ብለዋል፤ህዝበችን ሊያጋልቱት እየሞከሩ ነዉ ወዘተ… በማለት የማምለጫ እና አምታች ዘዴያቸዉን በመጠቀም ነገሩን ሲያጠ’ሙ እና ወንጀላቸዉን ወደ ህዝቡ በመጣል ራሳቸዉን ለመከላከል ይጥራሉ። ጮክ ብለዉ ያለ ሐፍረት ስለሚናገሩ እና ስለሚጽፉ አንዳንድ ኢትዮጵአዊያን እንዲያፈገፍጉ ሆኖ፤ ደፍረዉ ላለመናገር ምራቃቸዉ ዋጥ ስለሚያደርጉ፡ዘዴአቸዉ ለጊዜዉም ቢሆን አድማጭ ሳያገኙ አልቀሩም። አንድ እንኳ ሳይቀር ተቃዋሚ የሚባል በሞላ -“ኢሕአፓ”ም ጨምሮ የትግራይ ሕዝብ አልተጠቀመም ፤ህወሓት በዚህ በኩል ወገንተኝነት አላሳየም ቢሉንም፡ ሀቁ የኮሶን ያህል ምርሬት ቢመርም፤ ዕዉነታዉ መድፈን አይቻልም እና “የትግራይ ህዝብ ጠላቶች” ተብለን በወያኔ እና በጭራ ቆሊዎቻቸዉ ዉንጀላ አንደበት ከተፈረጅነዉ ከእኛዉ በኩል የምናቀርበዉ መራራዉ ሀቅ አብረን ይሄዉ እናንብበዉ። ለዛሬ መረጃየ በወቅቱ ከሌሎች አካባቢዎች ለማነጻጸር በእስታትስቲክ የተደገፈዉን ኣእላፍ መረጃ ወደ ሌላ ቀን አቆይቼ- ላጠቃላይ ለክርክር አጋዥ አንዲሆን ጦቢያ መጽሄት ላይ በ1992 (መጋቢት) ላይ የታተመዉ “አብረን እያደግን አይደለም-የብሔራዊ ራእይ ተሸካሚ አልሆኑም” የሚለዉን የጦቢያዉ አምደኛዉ አቶ ጸጋዮ ገብረመድህን አርአያን ይህ ክርክር አስመልክቶ ያተቱትን መለስ ብለን እንቃኝ እና ግምገማዉ ለናንተዉ ሳስተላልፍ ሃቁ ይሄ አይደለም የሚል ሰዉ ካለም የክርክሩ መድረክ ክፍት ነዉ። “ግብዣየ እነሆ”። ከናንተ ለመስማት እጠባበቃለሁ። ጹሁፉ ላይ ብዙ ቁም ነገሮች ታትተዋል-፡ ቢሆንም ረዢም በመሆኑ አንዳንዱን ዘልያቸዋለሁ። እንደሚረዳችሁም ተስፋ አለኝ። ተተከሉ የተባሉት የምርት ዕድገቶች (የአገሪቱ ታለላቅ/ከፍታኛ/ተወዳዳሪ የሌላቸዉ/ዋናዉ አከፋፋይ ቀማሚ/ሰሪ/ መጋቢ…..የሚባሉትን ቃላቶችን ነዉ እንድታተኩሩባቸዉ የማሳስበዉ።) እላይ የተመለከቱት ቃላቶች የፋብሪካዉ/የምርቱ ጉልበት እና ጥራትን ስለሚጠቁሙ፡ እነኚህ ዋሳኝንነታቸዉ በሌሎቹ ክፍለ ሃገሮች ተተከሉ ከሚባሉት ጋር ትይዩ ለማወዳደርም ሆነ ለማነጻጸር ስለሚረዳ ነዉ። ከባዶ/ከምርት አልባነት ተነስቶ በ5 ዓመት ዉስጥ “ትልቁ/ዋናዉ” አካፋፋይ ወደ መባል ተቀይሮ -ሌላዉ ክፍል ግን “ተቀባይ” “ቸርቻሪ” “ገዢ”… ወደ መሆን የታለመዉ ዕድገት ከአድልዎ ሌላ ቃላት መጠቀም ያስቸግራልና ክርክራችን በዚሁ እንየዉ።
ልጥቀስ፦“ ….አንድ የደቡብ አሜሪካ ጸሃፊ “የምናልም መሆናችንን ስናልም የንቃቱ ዘመን ደረሰ ማለት ነዉ።” ይላል። ለቋንቋዉ ዉበትና ለአነጋገሩ ዘይቤ ሲባል በእንግሊዝኛዉ ባቀርበዉ ምናልባት ይትበሐሉን ከነለዛዉ (nuance) ለመጨበጥ ትችሉ ይሆናል። “when we dream we are dreaming, the moment of awakkenin is at hand…” ይላል Novails.
በእጄ አንድ መጽሃፍ አለ። በቀለም ያበደ፤በጥንቃቄ የተደጎሰ፤አገር ለመገንባት የወጡ ብዙ የተማሩ ሰዎች በየገጹ ተደርድረዉ በፈገግታ የሚታዩበት የክልሉ መልክአ-ምድር አረንጓዴ ምንጣፍ የለበሰ የሚመስልበት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ያ ክልል ስዊት ዘርላንድን ዴንማርክን፤ኔዘርላንድን ወዘተ፤ወዘተ የሚያስተካክል የሆነበት ነዉ። በሕትመቱ ዓለም ዉስጥ መጠነኛ ሚና ስለነበረን ያነን መጽሀፍ (160 ገጽ) በአሥር ሺህ ቅጂ ለማሳተም እንኳ (በዉጭ አገር ነዉ የታተመዉ) ከመቶ ሺህ ብር በላይ በላይ ይጠይቃል። ስለቅርጹ ትተን መጽሄቱ ስላካተተዉ ይዘት በጨረፍታ እንመልከት። · 1176 ፕሮጆክቶች ተግባራዊ ሆነዋል፤ · በ806 መንደሮች የሚገኝ 1.7 ሚሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ ሆናል። ይኸ በመጽሄቱ ሽፋን ላይ ወልል ብሎ የሚታይ ነዉ።በእንግሊዝኛዉም Implimented 1176 projects in 806 vilages benefiting over 1.7 milion people ይላል። · በኢትዮጵያ ትልቁ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ · በኢትዮጵያ ትልቁ የሲሜንቶ ፋብሪካ · በኢትዮጵያ ትልቁ የትምህርት እንቅስቃሴ ማዕከል ·በኢትዮ ከፍተኛዉ የጤና አጠባበቅ ዘመቻ የሚካሄድበትና ታላላቅ
መሰረቶች የተጣሉበት፤ ·በኢትዮጵያ ስፍር ቁጥር የሌላቸዉ የንግድ የኮንስትራክሽን የማስታወቂያ የባህል የአመራር ማሰልጠኛ ወዘተ ተቋሞች ባለቤት የሆኑ መሪዎችና ደርጅቶቻቸዉ የዳበሩት፡ · ምረምር እና ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ የሚያካሄድበት · ኤች አይ ቪ( ኤይድስ-ን የሚያስከትል ቫይረስ)መከላከያ (ፕሮፊላክቲክስና) ጥናት በሰፊዉ የሚጠናበት · ዬዩኒቨርሲቲዎች እና የሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች መሰረት የተጣለበት (በነገራችን ያ መሰረት ዛሬ(2001ዓ.ም) ትግራይ ዉስጥ የሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ ተጠናቆ በሰዉ እና በአጋዥ ቁሳቁሶች ተሟልተዉ በሥራ ላይ ያሉ እና ሦስተኛዉ አዲግራት ላይ በመከናወን ላይ የሚገኝ ያገሪቱን የትምሕርት ተቋማት የሚያስንቁ ተሰርተዋል። - ኤርትራ እንደ አገር የምትጠራዋ ባለ ሁለት ወደቧ ምጥጢዋ ኤርትራም እንኳ 1ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነዉ ያላት። (በሃጽሮት የተመለከቱት -የኔ-‘ጌታቸዉ’)። · እንደ ወባ መከላከያ ያሉት ከነድርጅታቸዉ ከመሃል ተወስደዉና ጠንክረዉ የሚሰራባቸዉ፤ · ከረሃብ ጋር የተለያየ ክልል እንደ እግዚአብሐር ሳይሆን እንደ እቅዱ!! ስለሆነም አያሌ ታለላቅ ሪቆች (የእህል ዘመናዊ ማከማቻዎች) የተሰሩበት · ለወደፊቱ አገዛዝ መቀጠል ዋስትና ያገኝ ዘንድ የክልሉ ወጣቶች በአገር ዉስጥና በዉጭ ጭምር የአመራር ኮርስ (leadership course) የሚያገኙበት ለሚቀጥሉት አንድ ሺህ ኣመታት (ሚሌኒየም) የአገዛዙ ስርአት የሚሞከርበት ወዘተ፤ ወዘተ ትርዒት በትግራይ ይታያል።
“እንግዲህ…” ይላሉ አምደኛዉ፦ “እነዚህ ከላይ በጥቅልና በናሙና መልክ ያቀረብኳቸዉን ወቅታዊ ጉዳዮች በሌላዉ ኢትዮጵያ ካለዉ ነባራዊ ሁታ ጋር ካስተያየን፤ ስዕሉ ይህን አገር አይወክልም። ማወዳደር ማነጻጸር የተለያየ ትርጉም አላቸዉ። የትግራይን የግንባታ ልማትና የእድገት እንቅስቃሴ በሌላዉ ኢትዮጵየያ ካለዉ ጋር ማወዳደር ማለት በመሰረቱ በሌላ ኢትዮጵያ የልማት እመርታ የእድገት ሰፊ መድረክ አለ ወይም ተጀምሯል ብሎ ማመን ይመስላል።
ማነጻጸር ከሆነ ግን ያለዉ እና የሌለዉን የተተኮረበትን እና የተረሳዉን የተወደደደዉንና ተናቀዉን ጎን ለጎን ማቅረብ ማለት ነዉ። እንግዲህ እንደሚከተለዉ ላስረዳ። እነዚህ የትግራይ ጥጋብ ዘመናት ፤ በሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል ስምንት ሚሊዮን ሕዝብ በድርቅና በረሃብ ይጠበሳል። የስምንትኛዉ ሺህ ተአምር ሆነና አድአ ሲዳሞ፤ጎጃም እየተራቡ በትግራይ ገበያዉ ጠግቦ እህል ጥንቡን ጥሎ ቢያድር አይገርመኝም። በትግራይ አንደ ኤች አይ ቪ ያሉ በሽታዎች በጥራት ለማጥናትና ለመከላከል ከፍተኛ ሙከራ እየተደረገ ሲሆን በሌላዉ ኢትዮጵያ ግን አስታትስቲኮች እንደሚነግሩን በቀን በመቶዎች ሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ መቅሰፍታዊ በሽታ ያልቀሉ። በዚያን ሰሞን በአንድ ጋዜጣ ላይ እንደቀረበዉ በወባ ተዉሳክ የተነደፈዉ ሕዝብ በሚሊዮኖች ይቆጠራል። ይኸም ቢሆን ከሕዝብ ተደብቆ መቆየቱ ለ አንዱ ክፍል የሚታሰበዉን ያህል ሌላዉ ደንታ ቢስነትን የሚያሳይ መሆኑን አያጠራጠርም። ለመሆኑስ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልክ ተቋቁሞ ከመከላከል ወደ ማጥፋት ደረጃ ተሸጋግሮ የነበረዉ የወባ ማጥፊያ ድርጅት የፈረሰዉ ለምንድ ነዉ? የትግራይ ሕዝብ የኢትዮያ ሕዝብ እንደመሆኑ ሁሉ ጎንደሬዉ፤ከምባታዉ ወሎየዉ ሸዌዉ…ከፍቾዉ፤ ወለጌዉ፤ወዘተም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ። ከቶ ለአንዱ ክፍል እልቂት ለሌላዉ ድሎትና ሕይወት የታቀደለት ለምንድነዉ? የዚህ ሥርዓት መሓንዲሶች ወደፊት የታሪክ ፍርድ ይጠብቃቸዋል ተብለዉ በቀጠሮ የሚታለፍና ለእግዚአብሔርም ፍርድ የሚቆዩ አይደሉም። እንዲህ ያለዉ ተግባር በራሳቸዉ ቋንቋ ሲገለጥ በሰዉ ዘር ላይ የሚፈጸም ከባድ ወንጀል ነዉ። ከዚያ በታች ሊወርድ አይችልም። ….በዚህ አንጻር ሀብታሙን እያደኸየ ራሱን የሚያበለጽግ የፖለቲካ ድርጅት፤አሸንፌአለሁና ሁሉም የኔ ነዉ የሚል የፖለቲካ ተቋም ተቀዳጅተናል። ወያኔ ኢሕአዴግ! ይህ ተቋም ገና በትግራይ፤በወሎ በጎንደርና በጎጃም በአማጺነት ሲንቀሳቀስ በእጁ የገባዉን የመንግሥት ንብረት፤ድርጀት ፤ወዘተ፤በመዉረስ ሥልጣን ከያዘ በሗላ ደግሞ ያንኑ መልሶ ለቀድሞ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ሊያከራይና ሲሸጥ መቆየቱን እናስታዉሳለን። የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴና የክለል ኮሚቴዎች ድርጅቶች እንዳሉ ወደ ኢሕአዴግ ንብረትነት የሚዛወሩበት፤የተወረሱ የማምረቻና የማከፋፈያ ድርጅቶች ዕለቱን ወደ ተቋሙ ንብረትነት የሚሸጋገሩበት ሁኔታ ኢሕአዴግ መጥቶ ሒያጅ ወይም ለኢትዮጵያዉያንና ለኢትዮጵያ ባይተዋር መሆኑን ይፈነጥቃል። ከዚህ በላይ በሌሎች ክፍላተ ሀገር ሰዎች ጥሪታቸዉን አጋብተዉ ተስፋ ያላቸዉ የልማት ፕሮጀክቶች ለማቋቋም የነበራቸዉ ሕልም መና ሆኖ የቀረቡትን ሁኔታ አንድ ሁለት ብሎ በማስረጃነት ማንሳት ይችላል። በ1985 በአፋር ክልል (ክልል ሁለት) ብቻ አልመሽን ጨምሮ አሥራ አንድ ታለላቅ ሐዲዶች (በእርሻ ኮንሴሽኖች) በልዩ ልዩ ሥልት ተዳክመዉ መዘጋታቸዉን በትካዜ እናስታዉሳለን። በደርግ ጊዜ ከአዲስ አበባ አስከ ባሕር ዳር ድረስ መሬቱን ደን ለማልበስ “አዲስ ባህ” የሚባል ታላቅ ፕሮጀክት እንደነበርም አይዘነጋም። የዓለም ባንክ በ400.000.000 ዶላር (አራት መቶ ሚሊዮን ዶላር) ሊደግፈዉ የተስማማበት ይህ የልማት እቅድ ለመን ተሰረዘ? …..ነገሩን የአዲስ ዘመን ጋዜጠኛ ጨርሶት ነበር። በ1983 መጨረሻ (1984) መግቢያ አካባቢ) የወጣች አንዲት ግጥም የወያኔን ተልእኮ (ብሉ ፕሪንት) አሸጋግራ በማየት “ትግራይ አስክትለማ፤ሌላዉ አገር ይድማ!) ብላ ነበር።አስቆጣች! አስቆጣች! ሓቁና ጉዱ እያደር እንደ ጅራት የማይደበቅ ሆነና እነሆ ትግራይ፤ እነሆ ሌላዉ አገር!
ትግራይ ለምን ለማች ብሎ የሚያኮርፍና በንዴትም የሚንጨረጨር ሰዉ የለም። የሌሎች የኢትጵያ ክፍሎች (ክልሎች ነዉ የሚሉት?) ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ነዉ አጠያያቂዉ ጉዳይ! ዓይን ያለዉ እንደሚያየዉ፤ጀሮ ያለዉ እንደሚሰማዉ እና ሕሊና ያለዉም እንደሚገነዘበዉ “ፍትሃዊ ልማት የለንም”። ከአሜሪካ የተገኘ የቆየ ቃለ መጠይቅ ያለበት ቴፕ በእጄ ይገኛል።የወያኔ ኢሕአዴግ ሉስሎቭ (የርእዮተ ዓለም ሓላፊ) ጓድ ዓለምሰገድ ገብረ አምላክ “ሰላም” በተባለዉ ራዲዮናቸዉ ቃለመጠይቅ ቀርቦላቸዉ ነበር። “ኢሕአደግ ብዙ የንግድና የኢኮኖሚ ተቋሞች ማቋቋሙ ትከክክል ነዉን?” ጓድ ዓለም ሰገድ ሲመልስ “በትግል ላይ በነበርንበት ጊዜ ብዙ ንብረት አፍርተናል። ዛሬ ስልጣን ይዘናል ብለን ልንከፋፈለዉ አይገባምንም። ስለዚህ ኢንቬስት አደረግነዉ”። አሉ። ይህንን መልስ ነዉ ብሎ ያለ አይጠፋም; ይህ ገንዘብ ራሱ ከየት መጣ? እንዴት ተገኘ? በ1984 መጨረሻ ግድም ጦቢያ መጽሔት የጤና ጥበቃ ሚኒስትርዋን ዶክተር አዳነች ኪዳነ ማርያምን አነጋግሮ ነበር። “ክብርት ሚኒስትር የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ከወያኔ መድሃኒት ገዝታልና 4=7= 11 ሚሊዮን ብር ይከፈላቸዉ” የሚል ዉሳኔ ሰጥተዋል። “”ወያኔ ኢሕዴግ <ታጋይ.> ነበር እንጂ ዓለም አቀፍ የመድሃኒት ነጋዴ አይደለም። አርስዎም የገንዘብ ሚኒስቴርን ደንብ አልተከተሉም። ይህን አህል ገንዘብ ለወያኔ ለማሸከም ሥልጣን የለዎትም>> ደፋር ጥያቄ ነበር። ድፍረት ምን ማለት እንደሆነ ስላለወቅን እንጂ ተራ ጥያቄ ነበር። ዶክተር አዳነች << አሱን አንተ ነህ የምትለዉ። ልትከስሰኝ ትችላለህ!>> አሉ። ለማንኛዉም የኢሕዴግ የሃብት ምስጢር ሲነሳ ኢትዮጵያን በጠቅላላዉ መዉረሳቸዉን መግለጡ ይበቃል።
ለዚህ ሕዝብስ? ለዚህ ሕዝብማ፦ ለምሳሌ በአራዳዉ አካባቢ የሚታወቅ አንድ አፍቃሬ ወያኔ በ1983 ግንቦት ሰዎቹ ሥልጣን እንዲያዙና ያገኙትን “ሹምና ግልገል ሹም” ሁሉ ሽብ ሲያደርጉ አንድ አሳብ አቅርቦ ነበር /በቴሌቪዥን/።
“ይመስገን” ወረዳ 22 ፓሊስ ጣቢያን በማሰራት የቀረበዉ አሳብ፤- ለመሓል አገሩ ሕዝብ በርከት ያሉ እሥር ቤቶችን ማሰራትን ነበር። በእርግጥም-በመሃል፤በደቡብ፤በምዕራብ በምስራቅ ኢትዮጵያ የእስረኛዉ መበርከት ብዙ እስር ቤቶች እንዲቋቋሙ የሚገፈፋ ሆኗል። ትምርት፤ዩኒቨርሲቲዉ ፤የምርምር ጣቢያዎቹ፤ፋብሪካዎቹ፤ከማሳቹስትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲስተካክል የተፈለገዉ የመቀሌ ኢኒስቲትዩት ኦፍ ቴክኔሎጂ (MIT).. ሆስፒታሎች፤መንገዶች፤ብዙ መግለጫ ተሰጥቶላቸዋል። በግፍ የተሰሩ፤ ከኢትዮያ ሕዝብ በተቀማ ሀብት የተቋቃሙና በፍርደ ገምድልነት የተቆረቆሩ ስለሆኑ የታሪክን ፍርድ አያመልጡም ብለን ልናልፍ አይገባም። የግፍ ብድራት(poetic of justice) አጋጥሞ በመቀሌ፤በአዲግራት፤በአድዋ፤በ አክሱም፤በሽሬ፤ የተቃቋሙት የልማትና የባሕል ማዕከሎች ሻዕቢያዎች በጥቃታቸዉ ዒላማ ሊያደርጉላቸዉ ይችላሉ። በጠባብነት እና በስግብግብነት ካልሆነ በቀር፤ በስትራቴጂዉ ረገድ እንኳ በትግራይ ላይ ይህን ያህል የአገሪቱ ሀብት በዚህ ሰዓት ሊፈስስ አይገባምዉም ነበር። ከኢኮኖሚዉ ኢፍትሀሓዊነት በተጨማሪ የሰላም ኪሳራነትና ከላይና ከታች ተቃዉሞ ያለበት ነዉና። በጠቅላላዉም ተግባሩ ራሱ ይሉኝታ ያልታየበት፤የሕዝብን አስተያየት ከመጠፍ ለመቁጠር ያልተፈለገበት ነዉ።
ለፈረንጆችም ቢሆን ንጽጽሩ አሳፋሪ እዉነታ በመሆኑ ከእኛ ይልቅ የበለጠ እነሱ ይበልጥ ይነጋገሩበት ጀምረዋል። ለትግራይ የትግል ፍጻሜ ሆነና ለትግራይ ዲሞክራሲ የታገሉ ወያኔዎች ናቸዉ ተባለና በ አያሌ ሚሊዮን ብር በሃወልት ስም የድንጋይ ካብ ይታነጻል። በሚሊዮን በሚቆጠር ብር የተጠናም ሆነ ያልተጠና (ወይም ለማዕከል ተብሎ የተጠና ፕሮጀክት) የልማት ዕቅድ ይዘረጋል። በፍጥነት ወደ ፈረንጅ ኣዕምሮ የሚመጣዉ ንጽጽር <<በፍጥነት ለ8 ሚሊዮን የኢትየጵያ ረሃብተኛ በ860,000 ቶን እህል ያስፈልጋል>> የሚለዉ ነዉ። << በፍጥነት መቶ ሺህ ቶን መድሃኒት መድረስ አለበት>> የሚለዉ እርዳታ ሰጭ በተባሉት በ አሜሪካኖች፤በካናዳዊያን ባዉሮፓዉያን መንግሥታት ተወካዮች ጀሮ ዉስጥ ይይጮሃል። የኢትዮጵያ ገዢዎች መሰሎቻቸዉን ሰብስበዉ በመቀሌ ግብር ሲያስገቡ ፤መጠጡ ሲረጭ፤ዲስኩሩ ሲገጠገጥ ኢትዮጵያ እሳት እየበላት ነበር። ባሌ፤ኤሊባቡር፤ኦጋዴን፤ሲዳሞ፤ ባለቅኔ ሲራቀቅበት፤ፋኖ ወገቡን አጥብቆ በጓደኝነት “ጥራኝ-ጥራኝ ጥራኝ….ደኑ > ሲልለት የኖረዉ ደን እየነደደለት ነበር። አገር ነድዶ ነድዶ ሌላ የሚነድድ ወደ መጥፋቱ ገደማ የመጣፊያ ባለስልጣኖች ሰምተናል። <<አዲስ አበባም እኮ ወያኔ በገባ በሳምንቱ-ግንቦት 27-1983 ነድዳ ነበር። አሁን ተረኛዉ ደኑ ሆነ እንጂ!>> ታዲያ ይህ የአስረሽ ሚቺዉ ከረሃባችን ከሕመማችን አብሮ ይሄዳልን?
ከእነዚህ የኢትዮጵያ ገዢዎችና አጋፋሪዎቻቸዉ ጋር አብረን የ ኢትዮጵያን መካራ እየቀመስን አይደለም። አብረንም እያደግን አይደለም። የነደደዉ የደቡብና የምዕራቡ ደን ከፍተኛ ቃጠሎ፤ ንብረትና የሕይወት አደጋ የደረሰበት የዚያች አገር ክፍል በትግራይ ዉስጥ ቢሆን ኖሮ ምን እናደርግ ነበር ምን እንሆን፤ምን እንታዘዝ እንደነበር አገምታለሁ። ኒሮ እና ኮላዉዲዮስ ተባሉ የሮማ ቄሳሮችን የሚያስታዉስ ድርጊት በአሳፋሪ ተዉኔት መልክ እየተከሰተ ነዉ። ልሰማዉ የማልወድደዉና ለግንዛቤዮ እንደ ስድብ ይቆጠራል ብየ የምጠላዉ የሰዎቹ ክርክር <<ትግራይ ልማት በራስ አገዝ መልክ የተቀየሰ ነዉ>> የሚለዉ ነዉ። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፤ከኢትዮጵያ ኪሶች የተገኙ የወያኔ የንግድና የኢኮኖሚ ተቋሞች፤ ወፋፍራም ደመወዝ የተቆጠረላቸዉ የወያኔ-ባለሥልታኖች ለመንዝ ነዉ ወይስ ለወለጋ? ለከንባታ ነዉ ወይስ ለጋሞጎፋ? ሌላም እኮ አሳዛኝ ድርጊት አለ። አሜሪካኖች ራሳቸዉ ያወጡት ሪፖርት እንደሚያስረዳዉ USAAID በየዓመቱ ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የእህል እርዳታ ወደዚህች አገር ይልካል። USAID እና Michigan State University በጋራ ባወጡት የአቋም ሰነድ መሠረት ከሚላከዉ መካከል ስድሳ-ከመቶዉ ወደ ትግራይ ይሄዳል። እሱም ቢሆን በቁሙ ሦስት ጊዜ ይሸጣል (ለ አዉሮፓ ሕብረት፤ምናልባት ለካናዳ ምናልባትም ለጃፓን፤ወዘተ)። ይኸም ማለት <<እህሉ ስላለን ገንዘቡን ብቻ ላኩ>> በሚል ነዉ። ይኸ የሚያኮራ አይደለም። ሌብነት ነዉ ለማለት ደግሞ ድፍረትን ይጠይቃል። ባጠቃላይ ለመናገር ከመነሻዉ ጀምሮ በሕዝቡና በዚህ ሥርዓት መካካል መተማመመንና ልብ ለልብ መፈቃቀድ ባይኖርም በሂደት ደግሞ ርቀቱ እየሰፋ ይሄዳል። አረጋዊ በርሄ ጥሩ ይከራከራል፤ ወ ያኔን ከራሷ የበለጠ ያዉቃታል። ይሁንና ከአረጋዊ ጋር የማልጋባበዉ "ለትግራይ አንድም ነገር አልተደረገላትም" በሚለዉ ሀሳብ ነዉ። ቁሳዊ መሰረቱ በመጣልና በመሳሰለዉ ረገድ ግን ከማንም ኢትዮጵያዊ ይልቅ የፈረንጅ ነቃሽ ለማምጣት ይቻላል። ከአረጋዊ ይልቁንስ “ስብሐት ነጋ” የተባሉት ከወያኔ ግንባር ቀደምቶች አንደኛዉ ለሪፖረተር መጽሔት የሰጡት መግለጫ አይናችንን ትክ ብለዉ እየተመለከቱ የሚያፌዙብን ይመስላቸዋል።
ከተባለዉ መጽሔት ቅጽ 3 ቁጥረ 24 የሚከተለዉን ልጠቅስላችሁ እፈልጋለሁ። “ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይቶት በሕይወቱ ፤ በታሪኩ የማያዉቅ የልማት ጎዳና ተዘርግቷል። የልማት እንቅስቃሴም ጀምሮአል።ምንም እንኳ በሚገባዉ መጠን ባይሆንም ተጀምሯል። ትግራይ ደግሞ እንደማንኛዉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ፓርላማ፤መንግሥት የመደበለትን በጀት መሰረተ ልማት እያፋጠነበት-ነዉ።…ትግራይ የተሰጣቸዉ በጀት በብቃት ስራ ላይ ከሚያዉሉት ክፍሎች አንዱ ነዉ።… የሲሚንቶ ፋብሪካም ቢሆን የሀገር ሲሚንቶ ነዉ። ጨርቃ ጨርቁም የሀገር ጨርቃጨርቅ ነዉ። ምርቱ ሁሉ የሀገር ምርት ነዉ። ባሕር ዳር ይሰራ ትግራይ የሀገር ምርት ነዉ":: ይላሉ።
ለትግራይ የተደረገዉ ሁሉ ለመላዉ ኢትዮጵያ እንደተደረገ ቁጠሩት እያሉን ነዉ። በዚያዉ ልክ በትግራይ ላይ የፈሰሰዉን ሁሉ እየካዱ ናቸዉ፡ ዓይን አዉጣ አትበሉት። ሰዉየዉን የልብ ዉፋሬ ከይሉኝታ መሰናበት የሃላፊነትን የሐፍረትን የመጨረሻ ድንበር መጣስን ያመለክታል። ንግገራቸዉ አለላለቀም << ስለሌላዉ አያገባኝም። የተነሳነዉም ለትግራይ እንጂ ለሌላዉ አለመሆኑ ይታወቅ>> የሚለዉ ዓረፍተ ነገር ቢጨመርበት ከአስመሰላቸዉ ሎጂክ ርቆ አይሄድም ባይ ነኝ። (እኔም -“ጌታቸዉ ረዳ”- አዚህ አንድ ነገር ልጨምር።ሗላ እንመለስበታለን ብየ ከመግቢያዉ ጽሁፌ ላይ የተዉኩትን -ይህነን የገብሩ አስራት ንግግርም ባለፈዉ አድምጣችሁታል። እሱ ያለንም ልክ የስብሐት ነጋ ንግግር ነዉ። ተቋቁመዋል የተባሉት የልማት ድርጅቶች የትግራይ ሕዝብ ቢጠቀምበት ችግር የለኝም! (ለንግግሩ ጭብጨባ ተለግሶለታል) ትግራይ ዉስጥ የተቋቋሙት ልማቶች ለሌሎቹም ስለሚጠቅም ትግራይ ዉስጥ ቢቋቋም ልዩነት ተደረገ አያሰኝም”።ብሎ ነበር።ለትግራይ የተደረገዉ ሁሉ ለመላዉ አገሪቱ እንደተደረገ ቁጠሩት ሲሉን ፦ገብሩም ሆነ ስብሐት፦ነፍጥ አንግበዉ ወደ ጫካ ሄደዉ “ተሓህት”ን ለመመስረት ያበቃቸዉ የክሳቸዉ መነሻ ምክንት ያደረጉት- በሌሎቹ ክፍለሀገሮች ትምህርትና ፋበሪካ ሲቃቋም/ ሲስፋፋ ለትግራይ አልተደረገለተም ነበር የክሱ ምክንያታቸዉ። ያኔ የነበሩ ተቋማት ሸዋም ሆነ ባሕር ዳር ቢመሰረት ትግራይም ስለሚጠቅም ያገሪቱ ሀብት ነዉና ለትግራይ እንደተቋቋመለት አስቡት ተብሎ መልስ ሲነገራቸዉ አልተቀበሉትም። ይልቅኑስ “ብረት አንገቦ መዋጋት እና አሁን ካለበት ሂደት መድረስ ”ነበር መልሳቸዉ!! አሳዛኙ ነገር _እነሱ ጋ ሲደረስ ትግራይ ተመሰረተዉ ልማት ለማላዉ አገሪቱ እንደተሰራ አስቡት ሊሉን ሌሎቹ ስርዓቶች በሌሎች ክፍል በገነቡበት ወቅት ግን አካባቢዉ አንጂ ለትግራይ ምኑም እይደለም ሲሉዋችሁ- የማጭበርበር እና የዉሸት የመጨረሻ ድንበር መጣስ ከዚህ ወዲያ ምን ሊኖር ይችላል?)
..ልጨምርላችሁ -
ዶ/ር ሰለሞን ዕንቋይም ቅድም በተጠቀሰዉ በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቀዉ ባለ 160 ገጽ (TDA) ባሳተመዉ የትግራይ ልማት ሪፓርት ላይ በመጀመሪያዉ አንቀጽ ላይ እንዲህ ይላል። "ትግራይ ለብዙ ዓመታት ከተገፉት የኢትዮጵያ ክልሎች አንደኛዉ ነዉ;። ከሚኒሊክ አስከ መንግስቱ ድረስ የነበሩት ተከታታይ መሪዎች ክልሉ እንዳይሻሻል ዓላመቸዉ አድረገዉት ቆይተዋል”። እንዲያዉም ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት ሕዝቡን በሌሎች አካባቢዎች ለማስፈር በመመሞከር ልማት እንዳይኖር አሉታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ትግራይ በየጊዜዉ በድርቅ ቢጎበኝም የሚያስከትለዉን ሁሉ ለመቋቋም ምንም እርምጃ አልተወሰደም"
ያለፉት መንግስታት በዚህ ረገድ ትግራይን ነጥለዉ አይተዉ በሕዝቡ ላይ የሕሊና ጭንቀት አድረሰዉ ከትግራይ ዘርፈዉ ሌላዉን ክልል አልምተዉ ከሆነ ኮናኒም፤ነፃ አዉጭም ሊሆኑ ታሪክ ዕድል እንስጠዉ። ታሪክ ደግሞ እንደ ጅረት ፈሳሽ ነዉና ሌላ ምዕራፍ ላይ አድርሶናል። የዛሬዉን በዓይኑ እያየ እና በእጁ እየዳሰሰ የሕሊና ዳኝነቱ የሚኮንነነዉ ሰዉ ስለ ትናንቱ ማንሳት አይገባዉም። ማመዛዘን፤ማመሰካርና ማስተዋል (reason) ጋር መጣጣም ይኖርበታል። ስለዚህ ልናቀርበዉ የምንገደደዉ መከራከሪያ ትግራይን ከሌላዉ የትዮጵያ አካላት(ክልል)ጋር ማወዳደር ይሆናል። የትግራይ መጨቆን፤ ከዕድገት ይሁነኝ ተብላ ወደ ሗላ እንድተቀር መደረግ፤ የተሰሩትን እንዲፈርሱ ወይም ያሉት እንዲዘጉ መንግታቱ (መስተዳድሮቹ) ባወጡዋቸዉ ፖሊሲዎች መወሰናቸዉ አስከተገለጠ ድረስ ሌሎቹ ክፈላተሀገር ከትግራይ ቀድመዉ ሄደዋል ማለት ይሆናል። ሸዋ ለምቷል፤ጎንደር ለምቷል፡ ወለጋ በልጽጓል፤ወሎ መንገሰተ-ሰማት መስሏል ማለት ይሆናል።ዶከተር ሰለሞን ዕንቋይ ትናንት በትግራይ ላይ በደል ተፈጽሟልና የዛሬዉ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ኢፍትሓዊነት ትክክለኛ አፀፋ ነዉ ባይ ናቸዉ። ማንኛዉ ክልል ነበር ተጠቃሚ የነበረዉ? ማንኛዉ ሕዝብ ነዉ የትግራይን ህዝብና ትግራይን የበደለ? ከሆነስ የበደልን ብድራት መበቀል ያለበት በቀል እናስተካክለዋለን የሚል አቋም መያዝ ነዉ?
ያኔ ትግራይ ከባሌ፤ከኤሊባቡር፤ከወለጋ ከጎጃም፤ ከአርሲ ከሲዳሞ ከወሎ ትሻል ነበር።;… በጠቅላላዉ ግን በአመለካከትም በዕድገትም ከመንግሥት ጋር ብቻ ሳይሆን ከደጋፊዎቹም ጋር እየተራራቅን ሄደናል"።
በገብሩ አስራት ላይ እመሰክራለሁ ያለን በቀለም ያበደ በጥንቃቄ የተደጎሰዉ ታሪክ ለምስክርነት ቀጠሮ ያስያዘዉ ባለ160ዉ ገጽ የልማት መጽሐፍ አፈላልጉ እና አንብቡት። በዛ ጊዜ ሌሎቹ ክፋለተ ሀገር በምን ሁኔታ እንደ ነበሩ ሌሎች ዘገባዎችም ጨምሩበት እና አገናዘቡት። ብዙ ትገነዘባለችሁ። ከመዝጋቴ በፊት ወደ አቶ ጸጋየ ገብረመድህን አርአያ መደምደሚያ አስተላልፌ ልሰናበታችሁ። በዚች አጋጣሚ እንለያይ።
"… በአንድ ትምህርተ ቤት ጥቂት የሕዝብ ልጆች በርከት ያሉ አዳዲስ የመኳንንንት ልጆች ይማራሉ አሉ። አንድ ቀን የክፍሉ መምህር <<ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት የምትፈልጉ ሁሉ አስኪ ቁሙ እና ልያችሁ?>> ሲል አነዚያ የሕዝብ ልጆች ተቀምጠዉ ቀሩ። መምህሩ አንዲቱን ተቀምጣ የቀረች ልጅ ስም ጠርቶ "አንቺ ለምንድነዉ ያልተነሳሺዉ መንግስተ-ሰማያት ለመግባት አትፈልጊም ማለት ነዉ?" ይላታል። ልጅቹ ያለምንም ድንጋጤ "እፈልጋለሁ። ግን ከእነዚህ ልጆች ጋር ለመሄድ አልፈልግም" አለችዉ አሉ። አብረን አላደግንምሕልም አልተካፈልንምአብረን የምንሄድበት ቦታ የለም።//-// ---// http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

No comments: