ወያነ እና የትግራይ ሴት አዳሪዎች ያየሁት አሳዛኝ ታሪክ በሱዳን
ከጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
11/26/26
በዚህ የቃላት ትርጉም ልጀምር
«ሥጋ ውድበይ» (በድርጅቴ ሥጋና (አጥንት) ሥም እምላለሁ) የወያኔ ጽንፈኛ ሴት አባላት የሚምሉበት “የማይናወጥ የመሃላ ቃል ነው” ።
ጎቶግራፉ እንግሊዛዊው “ሳይመን” በሱዳን/ገዳሪፍ የ UN የስደተኞች አጣሪ ሓላፊ ሲሆን በቀኝ በኩል ያለው ደግሞ የስደተኞች ታሪክ አጣሪ (እስክሪነር) ሆኘ ስሰራ በነበርኩበት አንዲት አምሪካዊት ሥራ ላይ እያለን የሁለታችንን ፎቶግራፍ ያነሳችን ፎቶ ነው።
ይህ ታሪክ ለትግርኛ አንባቢዎች “ሥጋ ውድበይ” በሚል ርዕስ ሱዳን ውስጥ በሴትኛ አዳሪነት ኑሮ ሲገፉበት የነበረው አስቸጋሪ ሕይወት እና ወያኔ እነዚህን ምስኪኖች እንዴት ይጠቀምባቸው እንደነበር የሚገልጽ በመጽሐፍ መልክ ለማሳተም አዘጋጅቸው ከነበረው የተቀነጨበ ታሪክ ነው።
የታሪኩ አመዛኝ ታሪክ በርዕሱ የተመረኮዘ ቢሆም እነዚህ መስኪኖች በመጠቀም ወያኔ በተቃዋሚዎቹ ላይ ሱዳን ውስጥ ሲያደርጋቸው የነበረው አጠቃላይ የሽብር እንቅስቃሴ በተለይም በሱዳን የጃዕፋር አል ኑመሪ መንግሥት እና የወያኔ ግንኙነትን የሚዳሥስ ይጨምራል።
ከዚህ በተጨማሪ እኔ እና 3 ጓደኞቼ የኒመሪን እስላማዊ መንግሥት ለመገልበጥ የተላኩ ኮሚኒስቶች ናቸው በሚል “መኮንን በሚባል ሱዳን ያደገ፤ የትግራይ ተወላጅ፤ ሱዳኖችን በስለላው እና መረጃ የሚያገለግል፤ የወያኔ ታማኝና የድርጅቱ አባል የነበረ፡ መልኩም ንግግሩም አለባበሱም ሱዳናዊ የሚመስል የትግራይ ተወላጅ ፤ በመኪና አፍኖ ወደ ኩማንዳኒያ (ፖሊስ ጣቢያ- ከዚያም ወደ ዶሽ/ጦር ሰራዊት ካምፕ) በመውሰድ የወያኔ አባል አንሆንም በማለታችን እና ተቃዋሚዎች ናቸው በሚል የውሸት ክስ ለሱዳን የደህንነት አባላት በማስረከብ እንዳሳሰረን የመሳሰሉ ታሪኮችን ለማካተት ያቀድኩት ታሪክ የተቀነጨበ ነው።
በሻዕቢያ አስተዋዋቂነትና ድጋፍ ወያኔ በዓረብ አገሮችና በሱዳን ውስጥ ለበዙ አመታት ጽ/ቤት ከፍቶ የንግድ እና የዕርሻ ተቋማት መስርቶ “ሃብት አከማችቶ” የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን ንብረት እያገበሰበሰ የማፊያ ዓይነት ስራ በመስራት ሲንቀሳቀስ የብዙ ንጹሃን ሰዎችን ሕይወት ሲያበላሽ ነበር።
የ “ኢ ዲ ዩ/EDU” እና “ህ ወ ሓ ት/TPLF” ተከታዮች የነበሩ የትግራይ ተወላጆች እርስበርስ እንዲገዳደሉ እና የተጠለሉባቸው የስደተኞች መጠለያ “እምጉልጃ” ፤ “ጉልጅ”፤ “ቱባባ” ወዘተ.. በሚባሉ የስደተኞች መጠለያ ቦታዎች “ሰዎች በተኙበት ቤቶቻቸውን በእሳት እንዲነዱ በማድረግ የስደተኞች ህየውት አስቸጋሪ እንዲሆን ማድረጉን አስታውሳለሁ።
ህ ወ ሓ ት (TPLF) በገዳሪፍ፤ በከሰላ እና ሌሎችም ቦታዎች፤ ሲያደርስ የነበረው ወንጀል በዙ ነው። ለምሳሌ ድሃ የትግራይ ሴቶችን በዝሙት አዳሪነት እንዲሰማሩ በማድረግና ሱዳን ውስጥ ለብዙ አመታት በሴትኛ አዳሪነት ህይወት ሲገፉ የነበሩ የትግራይ ሴቶች ወደ ድርጅቱ በመመልመል አባሎች አድርጎ ሲበዘብዛቸው የነበረ ታሪክ ልብ ሰባሪ ነበር።
አንዲት የትግራይ ሴት ይህን ታሪክ ስትነግረኝ፣ ያ ቦታ ለመጽሐፉ ጠቃሚ ግብዓት ሆነኝ።
በሱዳን፣ በኡምራኩባ እና በካርቱም ንውድበይ (ለድርጅታችን) በሚል ፣ ወያኔ ያሰማራቸው የሴቶቹን ደህንነት የሚቆጣጠሩ “ማዓረስ” (አቃጣሪ” Pimp men) ለሚባሉት” ከዝሙት ያሰባሰቡትን ገንዘብና ወርቅ በሙሉ ያስረከባሉ። እነሱም ሴቶቹ ጋር አበረው ወደ ወያኔ ጽ/ቤት ስብሰባ በሚኖርበት ሳምንት በመገኘት ገንዘቡን ለህወሓት ተወካዮች ያስረከባሉ። ሴቶቹ እንደነገሩኝ “የተሰበሰበው ገንዝብና ወርቅ” እቶት (ገቢ) እያሉ ይጠሩታል።
የሚገርመው ነገር፣ እነዚህ አባሎች ከሰዎች ጋር ባንድ ነገር ሳይስማሙ ቀርተው “ለመማል” ሲፈልጉ በወላጆቻቸው ስም እንኳን አይምሉም፤ ይልቁንም መሃላቸው “ሥጋ ውድበይ (በድርጅቴ ሥጋ ስም እምላለሁ) ይላሉ።
የነዚህ መስኪኖች የስራ ቦታ እና ህይወት እንመልከት፤
የሥራ ቦታቸው በመንግስት የተፈቀደው የሴተኛ አዳሪነት የተገለለ ስፍራ ነው። ይህ ስፍራ (የቦታው ስማ ካልረሳሁት “ሱፋ?” የሚባል ይመስለኛል) ፤ ሆኖም ከከተማው ምስራቃዊ ክፍል ወጣ ብሎ፣ እጅግ ረጅም አጥር በታጠረ በርካታ ጎጆዎች በተሰባሰቡበት ስፍራ ይካሄዳል።
እነዚህን ሴተኛ አዳሪዎችን ለማግኘት ወደዚያ ሥፍራ የሚሄዱ ሱዳናውያን ሁለመናቸው ያስፈራሉ፡ ረዣዥሞች እና ቀጭን ናቸው፤ ይቆዳ ጥቁረታቸው ከሰል የሚመስል አይኖቻቸው እንደ ጥንዚዛ በጣም የቀላ ባጭሩ በተለምዶ “ጥብሊያቆስ” ተብሎ የሚጥራ ዓይነቶች ናቸው።
እነዚህ በሁለት ይከፈላሉ አንዳንዶቹ ሰፋፊ የሱዳን እርሻ ቦታዎች ዘንጋዳ (ማሽላ) በማጨድ የሚተዳደሩ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በቆርቆሮ በርሚል ተጠራቅሞ የተሞላ የሰው ዓይነምድር ራሳቸው ላይ ተሸክመው ወደ “ቦጥ” መኪና በመድፋት የሚተዳደሩ ናቸው።
በዙዎቹ ፤ ከማሽላ እና ከጎመን የሚዘጋጅ፣ አእምሮን የሚያስትና እጅግ አስካሪ የሆነ የአተላ መጠጥ ይጠጣሉ። ስትጠጋቸው እንግዳ የሆነ ቀፋፊ የጠረን ሽታ ያመነጫሉ!
አንዳንዶቹ፤ ቆዳቸው ነጭ የእሳት አመድ የተነሰነሰበት የሚመስል ፤ ከእርሻ በማሽላ ቆረጣ ሥራ ሰለሚሰሩ ምክንያት ከንዶቻቸው በምላጭ የተተለተለ የሚመስል ቆዳቸው ላይ የተሰነጣጣቀ የደረቀ እና እርጥብ ደም ይታያል።
አንዳንዶቹም ሽንት ቤት ለማጽዳት የሚጠቀሙባቸው አንዳንድ ልብሶቻቸው እንደለበሱ ወደ ተጠቀሰው ሥፍራ ይሄዳሉ። ለብሶቻቸው በቆሻሻና በደም እድፍ የተበከሉ ናቸው። ሥፍራው ረዢም የሰዎቹ ረድፍ ተሰለፈው ሲታዩ ቦታውም ይሁን ሰዎቹ ከዚህ ዓለም ያልሆኑ የሚያስፈሩ ናቸው።
ከተማ ውስጥም እዚህ ሰዎች ወደ ማታ አካባቢ ይታያሉ። በገዳሪፍ ከተማ ወደሚገኙ ሱቆች ሲገቡ፣ ከልብሳቸውና ከጠጡት መጠጥ መጥፎ የጠረን ሽታ የተነሳ ሁሉም ሰው ወደ ኋላ ይሸሻል። አብዛኛዎቹ ወደ ሱቅቤት ሲገቡ ሰክረው ስለሚገቡ፣ ያገኙት ሰው ጋር ጠብና ግጭት ያሰኛቸዋል።
ከተማ ውስጥ ቀን ላይ በየቤቱ እየዞሩ በርሚል ሙሉ ሰገራ (ዓይነ ምድር) ሲሸከሙ ውለው ለብሳቸውና ገላቸው ሰለሚበላሽ ስራ ጨርሰው ማታ ላይ መታጠብ ፤ ሳሙና እና ሽቶ መቀባት ሰላለባቸው።ሳሙና ለመግዛት ወደ ሱቅ ከሄድክ ሳሙና አታገኝም። ምክንያቱም ሳሙናውን ጨምሮ በሱቁ ውስጥ ያሉትን ጥሩ ሽቶ ያላቸው “የፍሊት” (ስፕረይ) ሁሉ ገዝተው ይጨርሱታል (እንዲያውም የሽቶ ጠርሙሶች ገዝተውት ሰለሚያልቅ አንድም ሽቶ አታገኝም) ።
ስፍራው ላይ ሲመጡ የሚታዩ አስገራሚን አስፈሪ ክንውኖች
ወያኔዎች የገንዘብ ምንጭ በማድረግ የሚበዘብዙዋቸው ሴት አዳሪዎች ለማግኘት ወደ ስፍራው የሚሄዱት እነዚህ ሱዳናውያን፣ በየተራ (በእኛ አቆጣጠር ከጠዋቱ 1 ሰዓት ላይ) ፣ በረጅም ሰልፍ ደጃፍ ላይ በቆሙ አጋፋሪዎች (ፒምፖቹ) (Pimp Men) በተራ እንዲሰለፉ ይደረጋል። አንድ ገብቶ አንዱ ጨርሶ ሲውጣ አንድ በአንድ እየገቡ 24 ሰዓት ሰልፉ ይቀጥላል።
በቦታው የሚገኘውና በሩን የሚከፍተውና በሚዘጋው አጋፋሪ ሰው (ፒምፕ)፣ ሰልፈኛውና ባለተራው ሲገባ ፤ ሴቶቹ ከየጎጆቸው እየወጡ በግቢው ውስጥ ባለው ሰፊ ቦታ ተቀምጠው ይታያሉ። ግቢው ውስጥ የሚገኙት ትግራይ ሴቶች እንዲሁም ጥቂት ሱዳናውያን እና ናይጄሪያውያን ሴቶች ሲሆኑ፣ ለዝሙት ስራ ተመርጠው የቀረቡ ናቸው።
ከሚያገኙት ገንዘብ ውስጥ ለቦታው የኪራይ ክፍያ ከፍለው (ቦታው ጊዜያዊ ጎጆ እንጂ መኖሪያቸው አይደለም)፤ ቀሪውን ወርቅና ገንዘብ ደግሞ ህወሓት ለሚያካሂደው ጦረነት ድጋፍ በዕርዳት ስም ይወስደዋል።
በመግቢያው ላይ እንደጠቀስኩት አንዲት የትግራይ ሴት ይህን ታሪክ ስትነግረኝ፣ እኔን እና ጓደኞቼ እሷ ራሷ ወደ ቦታው እንድናየው ወስዳን፣ ከጓደኞቼ ጋር ወደ ውስጥ ስንገባ የተመለከትነው ታሪክ ልብ ሰባሪ ነበር።
እዚያ ስንደርስ አንዳንዶቹ ሴቶች ወደ እዛ ሥፍራ መምጣታችንን አይተው ደነገጡ፤ «ክፉ ነገርን ለማየት ለምን እዚህ ድረስ መጣችሁ? ይህ እኮ እናንተን የመሰለ ያገራችን ሰዎች እንድታይ የሚገባ ቦታ አይደለም፤ ባጠቃላይ ሕሊና ያለው ሰው ሊጎበኘው የማይገባ ሥፍራ ነው አሉን»።
እውነትም እነዚያ ሰማይ የሚያክል ርዝማኔ ያላቸው በተሰነጣጠቀ ቆዳቸው ላይ በደረቀ እና በትኩስ ደም የተገጣጠብ ቆዳቸው በዛ ላይ ፤ ሰክረው እይተወላገዱ ሴቶቹን እየጎተቱ ወደየ መጋረጃ ክፍሎች ሲገቡ ስናይ እጅግ ቀፈፈን ፤ፈራን፤ እውነትም እውነታቸው ነበር ፤ ‘ሁለመናው ልክ እንደ ሲኦል አስፈሪ እና ለማየት የማይገባ ቦታ ነበር!’።
ሌላው አስደንጋጭ ነገር፣ ህወሓት/TPLF/ ሰው ለመግደል ወይም ለመጥለፍ ከፈለገ፣ በእነዚህ ምስኪን ሴተኛ አዳሪዎች አማካኝነት ወጥመድ ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል። ወይንም ሴተኛ አዳሪዎቹ ጉበኞች የሆኑትን የደህንነት ሓላፊዎችን በመፈለግ ሴትነታቸውን በመስጠት ተፈላጊው ወጥመድ ውስጥ ያስገቡታል።
ለምሳሌ የደህንነት ኃላፊ የሆነው የገዳሪፍ (Gedarif) ዲስትሪክት ኃላፊ “ዛብጥ ዓሲር (መቶ አለቃ ዓሲር) -የወያኔዎች ዋና ወዳጅ ነበር።በዛው ላይ የሱዳን ደህንነት ዋና ሓላፊ የነበረው ሱዳናዊው “ጀነራል አልፋታሕ ማርዋን” የወያኔ አባል ስለነበር በስሩ ያሉትን አውራጃ ፖሊሶቸ እና ደህንነቶች እንደ ዛብጥ ዓሲር የመሳሰሉት ግፈኞችን በማዘዝ ወያኔዎች የሚፈልጉትን ሰው ያስጠለፉ፤ ያስገድሉ እና ያሳሰሩ ነበር።
አንድ ሰው የወያነ አባል ሆኖ ወንጀል ከሰራ እና ከታሰረ እነዚህን ያልተማሩ ምስኪን “ሴተኛ አዳሪዎች” ወደ “ኮማንዴኒያ” (ፖሊስ ጣቢያ) አስልከው ባለሥልጣኖችን በማነጋገር “ዛሬ ማታ ወደ ቤት ና እና የፈለግከው ነገር (ግብረ ስጋ) እንፈጽምልሃለን እያሉ ሹማምንቶቹን እያሳሳቁ በማማለል ወንጀለኛውን ያስፈቱታል።
በነገራችን ላይ ‘ሱዳናውያን ሚስቶቻቸው ከእኛው ከኢትዮጵያ ቆንጆጅቶች የማይተናነሱ ቆንጆዎች ያሉዋቸው ቢሆኑም ለኢትዮጵያ ሴቶች እንጂ ለሱዳን ሚስቶቻቸው ምንም ዓይነት ስሜት የላቸውም’። በከታምውም ውስጥ የታዘብኩት በሚገርም እይታ ሱዳኖቹ ለኢትዮጵያ ሴቶች ያለቸው የመማረክ ስሜት፤ እኛም ለሱዳን ሴቶች ያለን ስሜት እኩል ነው።
በኒመሪ ዘመነ መንግሥት “አልኮሆል” ክልክል ሰለነበር ይህንን በማውቅ የ “ቲ. ፒ. ኤል” ኤፍ ተወካዮች ሱዳን ውስጥ “በአረቂ ጠርሙስ” እንኳን ሳይቀር ለወታደር አዛዦችና “የደህንነት ባለስልጣናት” ጉቦ በመስጠት የፈለጉትን ሰው በማስፈታት ወይም፣ የፓርቲያቸው ተቃዋሚ የሆነ ሰውን ከሱዳን እንዲባረር እንዲፈናቀል ወይም እንዲታሰር ያደርጉ ነበር።
አስገራሚው ክስተት ደግሞ፤ህወሓት ከሱዳን እና ከመሳሰሉ የዓረብ አገሮች ወያነን ሲደገፉ የነበሩት እነዚህ ሴቶች ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ እና ወደ መሳስሉት አገሮች በሕጋዊ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ - UNHCR - እና ወያኔም መንግሥት ከሆነ በኋላም ሥልጣኑን ተጠቅሞ ኢማባሲዎችንና የደህንነት ሰራተኞቹን የውሸት ፓስፖርት እና የውሸት ታሪክ እንዲሰሩላቸው እያዘዘ በየሃገሩ ጥገኝነት እንዲያገኙ በማድረግ (አብዛኛዎቹን ያልተማሩ ሴቶች ሰለነብሩ) እነሆ እሰካሁን ድረስ ውጭ አገር ሆነው ለወያኔ ያላቸው ድጋፋና ፍቅር አልተውትም።
እነዚህ ሴቶች አሁን የህወሓት ደጋፍዎች በመሆን፤ በህወሓት የድግስ (ፈስቲቫል) ዝግጅቶች በብዛት እየተገኙ “ስጋ ውድበይ” /የፓርቲዬ ሥጋ ይውጋኝ!” እያሉ ሲጨፍሩ “በየ ዩትዩብ ስዕለ ድመፅ” በብዛት የሚታዩት እነሱ ናቸው።
አብረው የሚጨፈሩትና የሚጮሁት በዙዎቹ ወጣቶችም ሰለ ሃገራቸው ኢትዮጵያ የሚያስተምራቸው በጎ ታሪክ ስለሌላቸው፤ በዙዎቹ በሱዳን የተወለዱ ልጆቻቸውም እንዲሁ ህወሓትን የሚደግፉና የህወሓትን ፖለቲካ የሚቀበሉ መሆናቸውን አሳዛዛኝ ያደርገዋል።
ህወሓት ወጣት ሴቶችንና እናቶችን፣ እንዲሁም በስደት ላይ የሚገኙ ሰዎችን የመበዝበዝ ወንጀሉን አንሶት አሁን ደግሞ የትግራይ ወጣቶች በገንዘብ ለሱዳን ወታደራዊ መንግሥት እየሸጣቸው መሆኑን በዳርፉር ተዋጊዎች እየተማረኩና ባሳዛኝ ትዕይንት እየተደበደቡ እደሆኑ ማስረጃዎችን እያየን ነው።
ህወሓት እነ ጀነራል አልፋታሕ እንዲሁም እነ «ዛብጥ ዓሲር» (መቶ አለቃ ዓሲር) ተጠቅሞ ያሰቃያቸው ስደተኞች፤ እንዲሁም በስደት ወደ ሱዳን የሚጓዙ የኦሮሞ ተወላጅ የተማረኩ ወታደሮች እና የመሳሰሉ ሱዳን ውስጥ በነበራቸው ሰፊ የእርሻ ማሳዎች ላይ ያለፈቃዳቸው በማሰማራት ማሽላ እና የመሳሰሉ አዝርዕቶችን እንዲያጭዱ አስገደደው በማስቀረት በዙ ግፍ ሰርተዋል።
እዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው ሰለ ኦነግ/ OLF/ ነው።
ካነጋገረኩዋቸው አንዳንዶቹ ከነዚህ ሰዎች ዕርሻው ውስጥ ተገድደው ሲሰሩ
በነበሩበት ወቅት፤ ከዕርሻ ዕርሻ ያለጠባቂ እያጨዱና እየተሸከሙ ሲንቀሳቀሱና ሰብሉን ሲሰበስቡ ያገኙዋቸው «ዘላን የሱዳን ቤጃ ነገዶች»
በግመል እያሳደዱ ከበሬ ብልት የተሰራ አሳማሚ ጅራፍ እየተገርፉ ሕየወታቸው ያጡ ሰዎች እንደነበሩ ሲያጫውቱኝ፤ የተቀሩት ደግሞ ወደ
አገራቸው ወደ ትውልድ ሥፍራ ኢትዮጵያ ለመሄድ ፍላጎት ስለነበራቸው፤ ከወያኔ የዕርሻ ብዝበዛ ወጥተው ወደ ገዳሪፍ ከተማ በመምጣት
በወያኔዎች ምክር ወደ ካርቱም ተጉዘው ወደ ወለጋ/ሸዋ እና አርሲ፤ ጂማ ወደ መሳሰሉት ቤተሰቦች እና ለጆቻችን ጋር ለመኖር እንጂ
ወደ ተጨማሪ ስደት አንፈልግም፡ ወደ አገራችን አሸጋገሩን ብላችሁ ወደ ካርቱም “ኦነግ/ OLF/” ተወካይ አነጋገሩት ብለውን ወደ
ካርቱም ተጉዘን፤ “ኦነግ/ OLF/” ስናነጋግራቸው «አይሆንም የኛ ተዋጊ ለመሆን ካልፈቀዳችሁ አናሻግርም!» ብለውን እነሆ ሕይወታችን
እንዲህ ሆነናል»። ብለው ወደ እመሰራበት የስደተኞች ጽ/ቤት ቅርንጫፍ መጥተው አሳዛኝ ታሪካቸውን አጫውተውኛል።
“ኦነግ/ OLF/” ለሕዝብ አስባለሁ የሚለው የውሽት ታሪኩ በነዚህ መስኪኖች
ሕይወት ሲቀልድ ነበር።
ሻዕቢያም ፤ ኦነግም ይሁን ወያኔ የሱዳን ደህንነቶችን በማባባል ተቃዋሚዎቻቸውን
ጠልፎ በመውሰድ ፤
በማሳሰር እና እንደ ግድያ ያሉ አሰቃቂ የሰሯቸው ወንጀሎች እስካሁን በምንም መልኩ አልተጣሩም፤ ይህንንም ለማጣራት የተደረገ ምንም ዓይነት ጥረት የለም! ታሩኩን ግን አቅም በፈቀደ ያለመሰልቸት ለታሪክ
እያስመዘገብን ነው። ያ ሁሉ ወንጀል ሳይበቃቸው ፤ እነሆ አሁንም ወያኔ ተዋጊዎቹን በ1000 ብር ለሱዳኖች በመሸጥ ወንጀሉ እንደቀጠለ ይገኛል።
ፍትሕ መች ትመጣ ይሆን?
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

No comments:
Post a Comment