Saturday, May 2, 2026

የዶ/ር ተኸስተ ነጋሽ ቃለ መጠይቅ ሃገር ፍቅር ማሕበር አጠንክረው የሚጠልዋት የነበረች ነገር “”የኤርትራ ነፃነት” የምትለዋ ጭራሽ የሚሸሹዋት ነገር ነበረች»”ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 5/2/26

 

 

የዶ/ር ተኸስተ ነጋሽ ቃለ መጠይቅ

ሃገር ፍቅር ማሕበር አጠንክረው የሚጠልዋት የነበረች ነገር “የኤርትራ ነፃነት” የምትለዋ ጭራሽ የሚሸሹዋት ነገር ነበረች»

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

5/2/26

የሚከተለው የዶ/ር ተኸስተ ነጋሽ ቃለ መጠይቅ  Eritrean Studies Journal (ESJ) ከሚባሉት የኤርትራ መሑራን ባዘጋጁት መድረክ ቀርቦ ያደረገው የቃለ ምልልስ ውይይት ከትግርኛ ወደ አማርኛ እንድተረጉምለት አንድ ወዳጄ ጠይቆኝ ትርጉሙ ጠቃሚ ቁም ነገሮች ስለያዘ እነሆ። በጣም የሚገርም ቃለ ምልልስ ነው። የታሪክ መሑር ዶ/ር ተኸስተ ነጋሽን እያመሰገንኩ ለማንኛውም ስሕተትና ተጨማሪ አስተያየቶች ካለ የራሴ እንጂ የምሑሩ አይደለም። እጅግ ገራሚ ክርክር ያለበት ነው፡ አንብቡት 5/2/26

ወደ ጉዳያችን ከመግባታችን በፊት Ethiopian Semay በአፕሪል ወር 30 ቀናት ውስጥ 474,663 አንባቢ እንደተጎበኘ ያሳያ

የዶ/ር ተኸስተ ነጋሽ ቃለ መጠይቅ  እነሆ!

Prof. Tekeste Negash: Italian colonialism and the shaping of Eritrea’s history 12/6/2025

Eritrean Studies Journal (ESJ)

ሰላም ለሁላችሁም፤ እንደምን አላችሁ? ስለ ጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ።እዚህ ደረጃ ላይ እደርሳለሁ በየ ገምቸ አላውቅም፤ ማለትም ትጋብዙኛላችሁ በየ ገምቸ አላውቅም። ስለዚህም ደስታ ተሰምቶኛል። ዓይን ለዓን ተያይተን  ትንሽም ይሁን ትልቅ ጥያቄ ለመግለጽ ዕድል ማግኘት ለኔ ትልቅ ትርጉም ያለው ቀን ነው። መጀመርያ ስለ ራሴ ማን እና ምን እንደሆንኩኝ ከዚያም ምን አደረግሁ የሚሉት እነግራችኋለሁ።

ተከስተ ነጋሽ እባላለሁ፤ የ “ዓዲ ማዕረባ” (አከለጉዛይ አውራጃ) ተወላጅ ነኝ። እናቴም አባቴም የ“ዓዲ ማዕረባ” ተለወጆች ናቸው። እኔ ሳድግ ማዕረባ ወደ 450 አራሽ ገበርዎች የነበሩት አካባቢ ነው። ማዕረባ የራስ ተሰማ ትውልድ ቦታ ነው። አባቴ እና ይደጃዝማች ተሰማ በአባታቸው የ«ደቂ ልዕመት» ዘሮች ነን። ሆኖም አባቴ እና ራስ ተሰማ አይዋደዱም። ምክንያቱም ወላጆቼ የደጃዝማች ተሰማ ፖለቲካ አይደግፍም ነበርና  ፤ በዚህ ምክንያት አይዋደዱም ነበር።

ማዕረባ የራሰ ተሰማ አገር ነው ሰለተባለ በመላው  ማዕረባ  የራሰ ተሰማ ደጋፊ ነው የሚል እመነት የተሳሳተ ነው።ወይንም አከለጉዛይ እንዳለ በሙሉ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ነበረው ማለት ሰሕተት ነው።  450 ግብር የያዘ አካባቢ የፖለቲካ አስተሳሰቡ አንድ አልነበረም ለማለት እወዳለሁ።

እዚህ ላይ ለገልጽላችሁ የምፈልገው አባቴ እና የራስ ተሰማ አባት ትውልድ ባንድ የሐረግ ዘረ የተገኙ የማዕረባ ተወላጆች ይሁኑ እንጂ  ባንድ ዘመን ከሌላ አካባቢ ወደ ማዕረባ ፈልሰው የመጡ ገዢዎች ናቸው።

በእናቴ ግን « ደቂ ጋዕቡር» እንባላለን (የጋዕቡር ልጆች እነባላለን) ። ጋዕቡር አፋሮች ናቸው።  እናቴ የማዕረባ ቀንደኛ የጋዕቡር ርስተኞች ተወላጆች ነን። (እንድጂነስ)። ጋዕቡር በዓፋር ሲገዛ የነበረ አካባቢ ነው።

አከለጉዛይ ማለት  «ማዕረባ፥  ሐደግት፥ ሰለስተ ሐደግቲ እና ሓሙሽተ ጉዛይ» ያቀፈ ነው። አከለጉዛይ የሚል ስም ከ300 አመት በላይ እድሜ የለውም። አከለጉዛይ  የሚል ስም በሁለቱ ነገዶች የተጠሩ ናቸው። አከለ እና ሓሙሽተ ጉዛይ ናቸው «አከለጉዛይ» የሚል ስም የሰየሙዋት እነዚህ ሁለቱ ናቸው።

 ሰለዚህ አከለጉዛይ የሚል ስም የተሰጣት ከ300 አመት በፊት አይበልጥም።፡በ1630 አንደ የፖርቱጋል ተወላጅ አዘጋገብ አክሱም ከተማ ውስጥ ሆኖ ስለ አካባቢው ሲጽፍ አሁን አከለጉዛይ እየተባለ ያለ አካባቢ ሰሙ «ቡር» የባል ነበር «ታች ቡር እና ላይ ቡር»። በኋላ ነው፤ ሦስት ወንደማማቾች «ማሉቕ፤ ጫሉቕ ሻሉቕ» የተባሉት ወንድማማቾች «ለአከለጉዛይ ሕዝብ፥ ለሓምሴን እና ለሰራየ ሕዝብ የወለዱ፡ በደምቢያ (ጎንደር) አድርገው በትግራይ አደርገው አከለጉዛይ ሰራየ እና ሓምሴን ወርረው አክለጉዛይ ብለው የሰየሙዋት ብለው በ1630 (ፈረንጅ አቆጣጠር)። ሰለዚህ ሰሞች ይለዋወጣሉ፤ በዚህም ምከንት አከለጉዛይ ጥንታዊ ስም አልነበረም። ስሙ «ቡር» ነው።

ደጋማው ኤርትራ ስንመለከት፤ ደጋ ተብሎ የሚጠራው በተለምዶ አከለጉዛይ ሰራየ እና ሓማሴን ሲባል ተሰማላችሁ።  ያ ስሕተተ ነው። ደጋማ ኤርትራ የሚባሉ 5 ናቸው። ደቂ ተስፋ ፤ (ቋሓይን - ደቂ መለጋ) የሚባሉትንም የሚጨምር ነው። ደጋማዉ አርትራ 5 ምድሮች ናቸው። ጣሊያን ከመጣ ወዲህ ግን ወደ 3 ለወጦ አከለጉዛይ ፥  ሰራየ እና ሓማሴን ብቻ አደረገው። እነዚህ የግዛት ስሞች ናቸው።

እንግዲህ ማንነቴ እንደገለጹኩት ሲሆን ከማዕረባ ወደ አሥመራ 6 አምት ሲሆነኝ ነው አሥመራ የሄድኩት። ለወላጆቼ አንድ በቸኛ ለጅ ነኝ። አሥመራ |ካምፖ ሲንታ” በሚባል ስፍራ ነው ያደግኩት። ሁሉም የሚሰብሰብበት ቦታ ነው። አንድ ነገር ቢደርስብህ ተሎ የሚደርሰብህ ዘመድ ሳይሆን ወዳጅህ አብሮ አድገህ በሚል ግንዛቤ ነው ያደግኩት። ከተለያዩ ቦታ የመጡ ሰዎች አካባቢ ያደግኩ ስለሆነ ; በመጥፎ ቀን ደራሾቹ ዝምዶች ሳይሆን ወዳጆቼ እና ጎረቤቶቼ ነበሩ።

 አካለጉዛይ ሓማሴን ሰራየታይ የሚባል አካባቢ አላድግኩም ሁላችንም እንደ ሰው ነው ያደግነው። ካምቦኒ ተማርኩ ፤ከዚያም ጂማ ሄድኩ ከዚያም ወደ አሥመራ ዩኒቨርሲቲ ተመልሼ ትምሕርቴን ጨረስኩ። ይህንን ይመስላል።እንዲህ ነው ያደግኩት።

ብ1980 ጋሽ በረከት ሃብተስላሰ Conflict in the horn of Africa  የሚል መጽሐፍ ሲጽፍ በወቅቱ የ PhD ተማሪ ነብርኩ። የበረከት መጽሐፍ ሳነብ «ደስ አላለቺኚም»፡ ምክንያቱም  የ             ኤርትራው እደጋማ ታሪክ እና የትግራይ ታሪክ ጨማድዶ አጨማድዶ በሁለቱም በኩል ምንም የታሪክና የባሕል ገንኙነት እንዳልነበራቸው በማስመሰል ፤ የገዢና የተገዢ ግንኙነት  እንዳላቸው አድርጎ በማቀረቡ ‹እሱ የጻፈውን እኔ ሰወቀስና ስቃወም፤ እሱ 90 አምት ሲሞላው እኔ 80 አመት ሞላኝ»። እና በረከት ጽሑፎቹ በሙሉ ተቃራኒዎች ናቸው። የኔ ሕይወት ከጋሽ በረከት ህይወት ጋር እሱ የጻፍውን እኔ ሰቃወመው ነው አሁንም እንዲህ ያለነው።

 ስለዚህ በጻፋቸው ሰነዶች እየተከታተልኩ የተሳሳተባቸውን ሁሉ ሕዝብ እንዲያውቃቸው አድርጌአለሁ።

ጋሽ በረከት የሕግ መሑር እንጂ የታሪክ ምሑር ሰላልሆነ ብዙ የተሳሳታቸው የታሪክ ግንዛቤዎች አሉ። ብዙ የታሪክ ዕውቀት የለውም። ለዚህ ነው ብዙ ስሕተቶች ውስጥ የወደቀው። ከበረከት ጋር ዓይን ለዓይን ተገናኝተን ተከራክረናል።

ከበረከት ይልቅ በጣም ያናደደኝ ያበሳጨኝ የዓለምሰገድ ተሰፋይ መጽሐፍ ነው። አሁን ስለ በረከትም ይሁን ዓለምሰገድ ተሰፋይ ለመናገር ብየ ሳይሆን የመጣሁት፤ ሆኖም በሰነድዋቸው ታሪካዊ ጽሁፎች  ያለሞያቸው እያጨማለቁት ስላየሁ ነው አንድ ነገር ለማለት የፈለግኩት። ዓለምሰገድ ተሰፋይ በቅርቡ የጻፈው አዲስ መጽሐፉ (ተከሰተ መጽሐፉ ስሙን ባይጠቅስም እንደሚመስለኝ እኔ የተቸሁት የዓለምሰገድ ተሰፋይ አዲሱ መጽሐፍ An African People's Quest for Freedom and Justice: A Political History of Eritrea, 1941-1962 – April 15, 2025 የሚለው ሳይሆን አይቀርም)፡ ተከሰተ በመቀጠል- ሰለዚህ አዲሱ መጽሐፉ እና ሌሎች ሁለት መጽሐፍቶቹ እንብቤ አቸዋለሁ በተለይ በአዲሱ መጽሐፉ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት አድርጌ በመጽሐፍ  መልክ ለማሳተም ምናልባት በመጪው ፈብሪዋሪ መጨረሻ አገባድደዋለሁ እላለሁ።

 በመጽሐፉ ላይ ያለኝ ግምገማ ለማውቅ ጣሊያን አገር የሚታተም አንድ መጽሔት አስተያየት መሰጠት ከቻልክ እባክህን አስተያይትህን አካፍለን ብሎ ጠይቆኝ፤ እሺ በየ ልኬላቸው እናሳትመው ብለውኝ..... ካለ በኋላ (ድምጹ እጅግ እየራቀ መጥቶ ምን እንዳለ መስማት አልቻልኩም)

.... በመቀጠል እንዲህ ይላል፤

፤ እንግዲህ ይህን ሳደርግ 50 አመት ሆኖኛል። ጋሽ በረከት ጋር ከ1982 ጀምሮ ነው ከበረከት ጋር ስከራከር የቆየሁት እሰካሁን ድረሰ ወደ 45 አመት ሆኖናል ስንከራከር።

ኤፍሬም ናይዝጊ የሚባል፤ እናንተው አገር አካባቢ የሚኖር ኤርትራዊ ለናንተም ለኔም ጥያቄዎቹ ልኮዋል። እሱም እዚህ ፎረም ውስጥ ካለ› እስኪ አረጋግጡልኝ። «አዎ አለሁኝ! አለሁኝ» ግሩም፤ እንግዲህ 4 ጥያቄዎች ናቸው የቀረቡልኝ።

ባጭሩ አፍሪካ ውሰጥ  ‘በኮሎኒያል ባውንድሪ’ በጣሊያን በፈረንሳይ፤ እንግሊዝ የተፈጠሩ ወሰኖች (ባውንድሪዎች) መክንያቱ ምንድነው? የሚል ነው ጥያቄው።

መልስ ፤ - ምክንያት የላቸውም። የነበረው በመሳሪያ «ሃይል» ነው። እነሱ ሃያል ሰለነበሩ እኛ ደካሞች ስለነበርን የፈለጉትን ነገር ወስደዋል። ኮሎኒያሊስቶቹን የሚያቆም ኃይል ስለላነበረ ብዙ  ብልሽት ፈጽመዋል። እነሱን የሚያቆም ኃይል መኖር አለበት። ለምሳሌ በወቅቱ ጣሊያንን ያሰቆመ ኃይል ኢትዮጰያ ነች። ጣሊያን ኢትዮጰያን ሊወር ሲሞክር ኢትዮያ ኃያል ሰለነበረች መክታ አሸንፋዋለች። ኮሎኒያሊስቶችን ማስወገድ የሚቻለው ኃይል ሲኖርህ ብቻ ነው።

ሌላው ለምንድነው ወሰኖች መከለል ያስፈለገው ለሚለው ምክንያት፤ መልሱ ለአስተዳደር እንዲመቸው ነው። አንድ ነገር ማወቅ ያለብን ቀድሞ ፈደረሽን ኤርትራ ውስጥ «አውራጃ የሚባል»፡አልነበረም። በጣሊያን ጊዜ «ኮሚሳሪያት» እንግሊዝ ጊዜ ደግሞ የነበረው «ዲስትሪክት» ነበር ሲባል የነበረው። በኢትዮጵያ አስተዳደር ደግሞ «አውራጃ» ብለው ሰየሙት። ከዚያ በፊት ግን አካባቢው «መረብ ምላሽ› የሚል አጠቃላይ ከመረብ ወዲያ ያለ ቦታ ማለት ነው። ጣሊያን ከመምጣቱ በፊት ግን መረብ ምላሽ የሚል አጠቃላይ የአጠቃላይ መጥሪያ ሆኖ 5 የመሬት መጠሪያዎች ነበሩት። እነሱም ሐማሴንአከለጉዛይሰራየደቂ-ተስፋአከለ መለጋ (ቋሓይን) ናቸው። በነዚህ 5 መሬቶች የየራሱ ጉልት አሉዋቸው። የሚተዳደሩትም በነዚህ የጉልት አስተዳደር ነው። ስለዚህ አወራጃ የሚለው ኋላ የመጣ ነው።

3ኛው ጠያቄ- ሰለ የቀኝ ግዛቱን ጉዳይ ስናነሳ ፤ የኤርትራ አይደንቲቲ ፈጥሯል ወይስ አልፈጠረም? የሚል ነው፡ ይህ ትልቅ ጥያቄ ነው።

 ኤርትራኖች ሲታገሉ « ማንንት አልነበረንም ብለው ነው የታገሉት (ከጣሊያን ወዲያ ስለሚቆጥሩት)፡ ስለዚህ በዚያ ማንነት

ካመኑ ማንነታቸውን ለማስከበር ታግለዋል፤ ይህም  ባንድ ወገን አበርትቶታል፤ ሆኖም ማነንታቸው በትግል የተፈጥረ ነው። ሆኖም ወደ 200 አመት ስንመልከት «መረብ ምላሽ» ባራሱ ይተዳደር ነበር። ሆኖም ወደ ጎንደር በመሄድ «ሹመት፤ማዕረግ» ለማግኝት ይሄዱ ነበር እንጂ “አስተዳዳሪ ከሌላ ቦታ ለማስመጣት አልነበረም። «ጎንደር ሄደህ ምን አመጣህ?» የሚለው አባባል የመጣው ከዚህ ነው። «ጎንደር ሄደህ ምን አመጣህ? ተብለው ሲጠየቁ ጎንደር ህይጅ የአከለጉዛይ ወይንም የለጎሳርዳ፤ ወይንም የሓሙሽተ ደጉዛይ....... አስትዳዳሪ ሆኘ ተሾምኩኝ» ይላሉ።ለዚህ ምክንያት ነበር ጎንደር የሚሀዱት እንጂ አስተዳዳሪን ለማምጣት አልነበረም።

አሐማሴንም ይሁን የአክለጉዛይ ሰው ጎንደር ሄዶ ነው ተሹሞ የሚመጣው። ሲሾም፤ ለንጉሡ ግብር የከፋላል። ስለዚህ ማነነቱን ስንፈትሽ ሰራየም ይሁን አከለጉዛይና ሐምሴን ሹመት የሚያገኙት በንጉሡ ይሁን እንጂ አስተዳዳሪዎቹ እራሳቸው ናቸው።

ጣሊያን ከመምጣቱ በፊት 1600 እሰከ አፄ ዮሐንስ ድረስ የተጠቀሱት የኤርትራ መንደሮች ከጎንደር ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበር። ሹመት የሚሰጣቸው ከንጉሡ ከጎንደር ሰለነበር ያቺን ሹመት አግኝተው ራሳቸው ያስተዳደሩ ስለነበር «ማነንት» የሚባለው ምንጩ ያ ነው። ያ የማንነት ነገር «ጃንሆይ»  በመጠኑ አልተረዳቸውም ነበር ፣ መንግሥቱ ግን ጭራሽ አበላሸው፤ አልተረዳውም ነበር።

አሁን ወደ ጣሊያን ቅኝ ግዛት እንገባለን ማለት ነው።

ይህ በኤርትራ ቅኝ ግዛት መጽሐፍ ጽፌአለሁ። ይህች መጽሐፍ ስጽፍ አንድ ነገር አሳሰበኝ። ጣሊያን እሰከ 1941 ገዝዋት። አሁን የመጣብኝ ጥያቄ ጣሊያን ሲወጣ በጣሊያን ቅኝ ገዢነት ታሪክ ከመፈታት ይልቅ ለእንግሊዝ ተላለፈ፡ ማለትም ከ1941- 1952 እንግሊዞች አስተዳደሩዋት። የኔ ጥናት ግን ጣሊያን ሲገዛ ኤርትራ ውስጥ ምን ሰሩ? ምንስ ችግር ትተው ሄዱ በሚል ነው። ይህችን ጥናት ለማድረግ ሳስብ ማለት በ1980ዎቹ ትንሽ አስቸገረኝ፡ ማለትም ጣሊያኖች 50 አመት ሲገዙ ይገዙበት የነበሩት “ጥናት” አላቀረቡም። ማለትም 50 አመት ስንገዛችሁ ይህ ፤ይህ አድረገናል ፤ አሁን ግን በዚህ ፤ በዚህ ምክንያት  ለቅቀናል ፡ ብለው ራፖርት ለሕዝቡ አላቀረቡም።

የሆነው ምንድነው “ተሸነፉ” ፤ ሲሸነፉ በቦታቸው እንግሊዝ ተተካ፡  እንግሊዝ ደግሞ እንደምናውቀው ብጥብጥ አመጣብን። ስለዚህ በዚህ ሁኔታ የጣሊያን አገዛዝ በሚያጠግብ ጥናት አጥንተህ ማቅረብ ይቻላል ወይ? የሚል ትልቅ ፈተና ገጠመኝ።

ምክንያቱም እንግሊዞች ኤርትራን ባያስተዳድሩ ኖሮ ጣሊያኖች ብቻ ቢሆን ኖሮ ብ1941 ሲሸነፉ፤ ተሸንፈው ኤርትራን ለማንም ሳያስረክቡ ለቀው  ቢሄዱ ኖሮ አርትራ ምን ትሆን ነበር? የሚለው ሃሳብ ሲደቀንብኝ ፈተና ሆነብኝ። ይህ ለመጥየቅ ቀላለ ነው፤ መልስ ለማግኘት ግን አስቸጋሪ ነው!!

 ቢሆንም ይህ ችግር ሰለገጠመኝ በተቻለ መጠን ኣጠናዋለሁ ብየ ጥናት ጀመርኩኝ።ጣሊያን ክ1905 እስከ 1941 ሲገዛ ኤርትራ በሞላ ወታደራዊ ሰፈር ነው ያደረጉት። ኤርትራ የጣሊያን ወታደሮች ማከማቻ እና ኤርትራዊያን አስካሪስ የምታፈራ አገር ነበረች። ኤርትራዊያን የጣሊያን ወታደር ከምሆን ወጭ ሌላ ስራ አልነብራቸውም። ሶማሊያን ሲይዙ ዋናው እና ቀዳሚ ኃይላቸው የኤርትራ አስካሪሶችን ይዞ ነው ሶማሊያን በቅኝ ግዛት ስር እንድትሆን ያደረጋት። ምክንያቱም  የኤርትራ ተዋጊ ወታደሮች ከጣሊያኖች በ10 እጅ የበለጡ ጠንካራ ተዋጊዎች ነበሩ። መክንያቱም ረሃብ ይችላሉ፤ ሩጫ ይችላሉ፤ ስለዚህ አማራጭ እነሱ ነበሩ። በዚህ ምክንያት ጣሊያኖች ሶማሊያን እንድይዙ ከፍተኛውን ሚና ተጫወቱና ሶማሊያ በቁጥጥር ሆነች።

በ1911 ጣሊያን ሊቢያን ሲይዝ 20 አመት ሙሉ ሊቢያ በጣሊያን ስትገዛ 5 እና 6 ሺሀ ኤርትራ አስካሪዎች በየወቀቱ በባሕር እይተጫኑ ሊቢያ  በጣሊያን እንድትገዛ ያደረጉ ኤርትራዊያን አስካሪስ ናቸው። የጣሊያን ኤርትራዊያን ወታደሮች በሁለት አፍሪካዊ ሀገሮች በጣሊያን ቅጥጥር ሥር እንዲወደቁ ትልቁ ሚና ስለተጫወቱ፤በዚህም ጣሊያኖቹ በውጤቱ ስለተደሰቱ ኤርትራ ውስጥ “የቆየ ሕግና ባህል” እንዳይነካ አደረጉ። በራሳቸው ሕግና ባሕል እንደ ጥንቱ በራሳቸው  ምስለኔ እና ጭቃ እንዲተዳደሩ አደረገ። የሚገርመው ነገር ‘መሬትም’ በጣሊያኖች እንዳይያዝ ተድርጎ እያለ አንዳንዱ የኤርትራ ምሁራኖች ግን ጣሊያን የኤርትራኖችን መሬት ወርሶ ባዶ እጃቸው አስቀራቸው እያሉ ሲጽፉ ነበር። ይህ ግን ውሸት ነው። ጣሊያን  ደጋማው አካባቢ 6 ሺ ሄክታር ምርት ብቻ ነው የተጠቀሙት። ቆላማኤርትራም ቢሆን 3 ሽህ ሄክታር ብቻ ነበር የያዙት፡ እሱም የማያመች እና ሃሩርማ የሆነ ፤ ብዙ ሰው ስለማይኖርበት ሊጥቀሙበት አልቻሉም።

ኤርትራኖች ከበሳውም ቆላውም በወታደርነት ስራ ሲያገለግሉ ‘እስላሞቹ ለብቻ ክርስትያኖቹ ለብቻ’ ነበር የተደራጁት። ስለዚህ ግንኙንታቸው የላላ ነበር። ከጣሊያን አገዛዝ በፊት ሰራተኛ የሞያተኛ ማሕበር የምናምን ማሕበር የሚባል ነገር አልነበረም። ምክንያቱም ማሕብራት እንዲመሰረቱ ፈላጎት ሰላልነበራቸው ነው።

ጣሊያን ኤርትራን ሲገዛ ኢትዮጵያ ኤርትራ ወስጥ ነበረች። ይህ ምን ማለት ነው? በ1896 በጣሊያን እና በኢትዮጵያ የተደረገው ውል «ደብረ-ቢዘን» ከነ ርስትዋ ከነ መንኮሳትዋ እና ቀሳውስትዋ ጭምር ኢትዮጵያዊት ነች  የሚል ውል አምኖ ተቀበሎ ተዋውሎ ነበር። ይህ የጣሊያን መግሥት አምኖ የተቀበለው ነው እስከ’ነ ርስቶችዋ እና ገዳምዋ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ቀሳውሰቶቹ በየቦታው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ (ኤርትራ ውስጥ የኢትዮጵያ ባንዴራ ይዘው እያውለበለቡ ነበር ሲሰብኩ የነበረው። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊያን ናቸው ። ሰንደቃላማቸውን ይዘው መስበክ መብታቸው ነበር።ዚህ ከ1896 ጀምሮ  የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በጣሊያን ወቅት ደበረቢዘን ቤተክርስትያን ውስጥ ይውለበለብ ነበር።

ቢዘን ኤርትራ ውስጥ ከነበሩት 20 ገዳም አንዷ ነበረች። ስለዚህ 20ዎቹ ደጋማ ኤርትራ ውስጥ የሚገኙ ገዳማት/ቤተክርስትያናት ግንኙነታቸው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስለነበሩ፤ በዚያው ልክ ሓማሴን ፤አከለጉዛይ እና ሰራየ (ደጋማ ኤርትራ) እኛ 50 አመት ሙሉ ጣሊያን ጋር ስንኖር ያኔም ዛሬም ኢትዮጵያዊያን ነን፤ «ካቶሊክ አንሆንም፤ ከንሻም አንሆንም» እያለ ለ50 አመት የታገለ ሕዝብ ነው።

ጣሊያኖች ኤርትራን ካቶሊክ ለማድርግ ያልሰሩት ነገር አልነበረም። ከ1932 ጀምሮ ስዊዲን ሚሺነሪዎች እንደልባቸው እንዲሰብኩ ፈቀዱላቸው። በካቶሊክ ደግሞ ጣሊያን ሆን ብሎ ሕዝቡ ካቶሊክ እንዲሆን ኤርትራ ውስጥ የነበሩ ት/ቤቶች በካቶሊክ ሥር እንዲተዳደሩ አደረገ።ካቶሊክ ለሚከተሉ ሁሉ ዕርዳታ እየሰጠ ሕዝቡ ወደ ካቶሊክ እንዲገባ ሞከረ። በሚገርም ሁኔታ በ50 አመት ውሰጥ 8 ሺ ካቶሊክ ተከታዮችን ብቻ አፈራ። ስለዚህ ሓማሴን ፤ሰራየ አከለጉዛይ ፤  ደቂ ተስፋ ፤ ደቂ  መለጋ (ጠቅላላ 5 ቱ ኤርትራ ደጋማው ክፍል) በሃይማኖቱና በእምነቱ፣ እንዲሁም በሃገሩ አይደራደርም ነበር።

በዙዎቹ የሻዕቢያ ደጋፊዎች “የኤርትራ ታሪክና ማንነት ከጣሊያን ነው የሚጀምረው›፡ይላሉ። የኢትዮጵያን ኤርትራ ታሪክ በጣሊያን ጊዜ የጀመረ ነው እንጂ ከዚያ በፊት ይህ ነው የማይባል ታሪክ አልነበራቸውም ይላሉይህ የተሳሳተ ሃሳብ በሁለቱም በኩል የነበረ ሕዝብ ማነንትና ታሪክ እንዳልነበረውና ያ ማንነት ደጎሞ ትርጉም የለሽ እንደሆነ አድርገው የሞግታሉ። ይህ ፍጹም የታሪክ ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎች የሚሞግቱት አሳብ ነው

እኔ ያጣናሁት ታሪክ የጣሊያን ትልቁ ራስ ምታት ሆኖበት የነበረው ኦርቶዶክስ ክርስትያን የሚባል የደጋማው ሕዝብ የጣሊያን ትልቁ ራስ መታት ሆኖበት ነበር። ጣልያኖች ሲሉ የነበረው «ይህ ሕዝብ ክርስትያን ነው፤ ኢትዮጵያዊ ነው»። ነበር ሲሉት የነበረው።

ወደ እስላሙ ማሕብረሰብ ሲመጣ ግንጣሊያኖቹ እስላሙ ክፍል “ኤርትራዊ ነው” እኛንም ያምነናል እኛም እናመነዋለን፤ ከእስላሙ ጋር ምንም ችግር የለንም እያሉ በመጀምሪያ አካባቢ በወታደራዊ ማዕረግ ውስጥ ቀዳሚ ማዕረግ ሲስጡት የነበረው ለእስላሙ ነበር። ስለዚህ ጥሊያኖች ክርስትያኑ ደጋማ ኢትዮጵያ ክርስትያን ነን ስለሚል እምነት አልነበረውም። በዚህ የመጀመሪያው ዕርከን አለፈ።

አሁን ጥያቄው የነበረው ጣሊያን  ኤርትራን ሲገዛ እና ከሄደ በኋላ እንግሊዝ ባይረከበው ኖሮ የኤርትራ ማንነት ምን ይሆን ነበር የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው የጫረብኝ። እኔ የደመደምኩት እምነት፤ ጣሊያን ለእንግሊዝ ሳያስረክብ እና እንግሊዝ ባይኖር ደጋማው ክፍል በተለይ ወደ ኢትዮጵያ እንግባ ብሎ እራሱ ጠይቆ ይጠቃለል ነበር የሚል እመንት አለብኝ። ይህ በሙሉ ልብ መናገር አይቻልም ይሆናል፤ ምክንይቱም ሁኔታው ሰላልተከሰተ፡ቢሆንም ቢክሰት ኖሮ ነው ይህን እምንት የምለው። ሆኖም ከስተቱ ባይከስትም፤ እንግሊዝ ሲረከበው የደጋማው ሕዝብ ስሜት የሚንግረን ይህ ዓይነት እምነት ነው። ከዚያ ምልክት ማየት ይቻላል። ምክንያቱም ሕዝቡ (ደጋማው) በ1947 በ1948 ያየነው ክስተት ነው።

አሁን ሌላ ጉዳይ እንመልከት ጣሊያን በነበረበት ወቅት ደጋማው ሕዝብ ከነበረው ጥንታዊ የሕዝብ ቁጥር 3 ዕጥፍ ጨምሮ ነበር። ከ100 ሺ ወደ 300 ሺ ሕዝብ አደገ፡ ያ እሰላማዊ ቆላማ ሕዝብ 2 እጥፍ ብቻ ነው ያደገው። በ1905 መጀምሪያ ላይ ከክርስትያኑ ሕዝብ በላይ ቁጥሩ ከፍተኛ ነበር። በ1939 ስንመጣ ግን በ20 እና 30 ሺ ሕዝብ ቁጥር ደጋማው ክርስትያን ሕዝብ አደገ። ይህ ትልቅ ትርጉም አለው። ምክንያቱም 65% ኤርትራ ውስጥ ደጋማው ሕዝብ ነው። ኤርትራ ውስጥ የእስልምና ሃያምኖት የሚ ከተሉ 8 ብሔሮች (ነገዶች) ተደማመረው 35% ናቸው። ይህ ትክክለኛ ዲሞግራፊ ነው።

ይህ የሰው ብዛት ፖለቲካዊ ትርጉም አለው። በ1940ዎቹ ሆን ብለው ጣሊያኖች እና እንግዝሊዞች ኤርትራ 75% እስላም ሕዝብ ነው፤ 25% ብቻ ክርስትያኖቹ ናቸው ብለው ፖለቲካዊ ጨዋታ በመጫወታቸው  ለእስላምዊ ሊግ ፖለቲከኞች አምቺ ፕሮፓጋንዳ አገኙና ተጠቀሙበት። ይህ ግን ጣሊያኖቹና እንግሊዞቹ  ደጋማውን የክርስትያኑ ሕዝብ ፖለቲካ ለመምታት ሲሉ ያድርጉት እንጂ ሃቁ 65% ክርትያን እንደነበር ያውቃሉ። ይህ ሃቅ ማየት የማትችሉት በ40ዎቹም ሆኑ ከዚያም በኋላ በየትምሕርት ቤቶች 85% የምታዩዋቸው ክርስትያኖች ናቸው።ምክንይቱም ብዛት ሰላላቸው። ይሁን እንጂ ጣሊያኖች ውለው አድረው 20% ደጋማው ክፍል ዕድገቱ ዝቅ ያለ ቢሆንም ጣሊያን 3 እጅ እንዲያድግ ሰላደረገ መላው ኤርትራ የበላይነት እንዲይዙ አመች ሜዳ ፈጥሮላቸዋል። ሁለተኛ ኑሮአቸው አደገ። ከ1905 1940 ኑሮው እያደገ መጣ። ኑሮው እያደገ መጣ ስንል ትይዩ የምናደርገው ኢትዮጵያን ነው

ከመጀመሪያ የጣሊያን መግባት ጀምሮ በጣሊያን ዓይን ኤርትራ እና ከኢትዮጵያ እንዲሁም አጎራባች የተለያዩ ሃገሮች ዕኩል አድርጎ እያያቸውም ነበር። ምክንያቱም፤ ወደ ኤርትራ ሲገባ ለመቆየት ሳይሆን ዓላማው ኢትዮጵያን ለመያዝ ነው። ኤርትራን የያዘባት ምክንያት አመቺ መስፈንጠሪያ  እንዲሆነው እንጂ እዛ እንዲቀር አልነበረም። ሰለዚህ መሰፍንጠሪያው እንዲሆንለት አደረገ። ኤርትራ ደጋማዎቹን በትምሕርት እና በኑሮ እያመቻቸ እናንተ ኤርታርኖች ናችሁ እያለ፤ ከትግራይም ከአኢትዮጰያዊያንም የተሻለ ዘምናዊ ኑሮ ነበራቸው። ምክንያቱም ቢያንስ 5 ሺ ኤርትራዊ የጣሊያን አስካሪስ ወታደር ሆኖ ሊቢያ ውሰጥ ለብዙ አመታት እዛ ሆኖ ደሞዝ እያገኘ ወታድሮቹ የሚያገኙ ደሞዝ ለቤተሰብ እንዲሰጣቸው ያደርጉ ስለነበር ኑሮአቸው «ኢኮኖሚ» ተሻሻለ።

በ937 60ሺ ኤርትራ አስካሪዎች ከጣሊያን ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ሲወሩ፡ ጣሊያን ያወጀው «ከዚህ ወዲህ ኤርትራኖች Native አይደሉም  “አማራዎች፤ትግሬዎች ወዘተ (ኢትዮጵያ ሐብሻዎች) Native ናቸው፤  ኤርትራዊያን ግን ከነሱ ጋር አንድ አይደሉም ኤርትራዊያን ግን «ኤርትራዊያን» መባል አለባቸው» በማለት ኤርትራኖቹ ከኛ ጋር ሆነው አፍሪካ ውስጥ ለፈጠርነው አዲስ ኢምፓየር አብረውን ሰልገነቡ «እናሳድጋቸው» ብለው አዲስ ማንነት ሰጥተው ‹ኤርትራ እና ኤርትራኖች» ብለው ሰየሙዋቸው።

ይህ ሁሉ ሲድረግ ደጋግመው ሕዝብ ሃይማኖቱ እና ማንነቱን ሳይለቅ 50 አምት ሙሉ የታገለ ሕዝብ ነው።

April 1941 እንግሊዞች ጣሊያኖችን ሽረው አስመራ ገቡ። ጃንሆይም በሱዳን በኩል ጎጃም አድርገው አዲሰ አበባ ገቡ። በማግስቱ አስመራ ውስጥ  ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ። «እኛ ኢትዮጵያዊን ነን ፤ ከሃገራችን ጋር ለመዋሃድ እንፈልጋለን» በማለት አስመራ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ሃገር ፍቅር ማሕበር የሚባለው ሰላምዊ ሰልፉን መራው። አሳዛኙ ነገር “ተማርን ይሚሉ እንደ የሻዕቢያው ዓለምሰገድ ተሰፋይ እና ሻዕቢያ ያልሆኑ መሑራን ነን የሚሉ ኤርትራኖች ይህንን ታሪክ እየካዱ”ያልሆነ ስም ሲስጡት አይቻለሁ።  50 አመት ሙሉ በጣሊያን ስር የነበረው ደጋማው ክፍል ሕዝብ ላንዲት ቀንም እንኳ ብትሆን «ኢትዮጰያን ረስተዋት አያውቁም»።  እንካድ ብለው ለመካድ ይፈልጉ እንጂ ዓይኑን ከፍቶ ታሪክ ያየ ደጋማው ከፍል ሌላ ልብ ይዞ አያውቅም ነበር። 1941 እንግሊዞችን በሰላማዊ ሰልፍ ያስፈራሩትና ሁለተኛ እንዲያስብ ያድረጉት «ማሕብር ፍቕሪ ሃገር» (የሃገር ፍቅር ማሕበር) አባላት ናቸው። ብዙዎቹ ተዋህዶ ቢሆኑም ካቶሊኮችም ተጨምረውበታል።

ልታስምሩባት የምፈልገው ነገር «ሃገር ፍቅር ማሕበር አጠንክረው የሚጠልዋት የነበረች ነገር “”የኤርትራ ነፃነት”የምትለዋ ጭራሽ የሚሸሹዋት ነገር ነበረች»”።ምክንያታቸው ሲያቀርቡ «የኤርትራ ነፃነት የእሳላሙ እና የጣሊያን መንግሥት እንጂ የኛ ነፃነት ልትሆን አትችልም» «እስላሞቹ  እንጂ ደጋማዎቹ ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን ወደ ሃገራችን ኢትዮጰያ ነን መዋህድ የምንፈልገው» ብለው ተከራከሩ። ስለዚህ ኤርትራ ሕላዊ (ነፃነት) ተቀብሎ አያውቅምጭራሽ ነፃ ኤርትራ የምትባል ሕሊናው ውስጥ መዝግቧት አያውቅም። በ1948 (1949) የታየው የጣሊያን አስተዳደር ወቅት የታየው ክስተት ይህ ነበር።

ብዙ ጥያቄዎች ተቃውሞዎች ሊኖራችሁ ይችላል። እኔ በዛ አልጨነቅም፤ ይህ  የኔ እምነትና ያደረግኩት ጥናት ነው።100% ልክ ነኝ ብየ ባልሞግትም፤ የተለየ አስተያየት ወይንም ተቃውሞ ካላችሁ አካፍሉኝ ላድምጣችሁ። በማለት ተከስተ ነጋሽ የተጋበዘበትን ሐሳብ   ካካፈለ በኋላ። አድማጮቹ ጥያቄ አቀረቡለት።

ጥያቄ---------፡

አይርትራ ውስጥ በጣሊያን ጊዜ ምን ትመስል እንደነበር ነው የነገርከን። ኢትዮጵያስ እንዳሁንዋ አንድ ነን እንደሚሉን አንድ ሃገር ነበረች? በተለይ በዘመነ መሳፍንት ወይንም ዮሃንስ ከሞተ በኋላ የነበረች ኢትዮጵያ በትገልጽልን ደስ የለኛል።

መልስ-ተከስተ

 አሁን እንደምናየው የተሳሰረች አገር አልነበረችም። ግን የሚያስተሳስራት (ያጋመዳት ገመድ) ግን ነበራት። እውነት ነው አውራጃዎቹ ለምሳሌ ጎንደር በለው፤ ጎጃም በለው  ትግራይ ውስጥም እንዲሁ እርስበርሱ ገዢዎቹ ከውጊያ አርፈው አያውቁም።ግን ማወቅ ያለብን ያ ውግያ እርስበርሰ ቢሆንም ለመለያየት ወይንም፣ አገር ለመመስረት አገር ለመገንጠል ሳይሆን  እኔ ልግዛ እኔ ልግዛ ነው  የነበረው ውግያ። በዘመነ መሳፍንቱም ወደ ኋላ ብትሄድ ከዚያ አልተለየም። የአንድ አወራጃ ወይንም የአንድ ከፈለሃገር ገዢ ሌላውን ጠቅልሎ ለመግዛት እንጂ ውግያው አገር ለመመስረት አልነበረም።

አይርትራም ብትህይድ ጎንደረ እና ኤርትራ ገዢዎች « በ16ኛ ክ/ዘመን በትግርኛ የተጻፈው “የኮልመዲን” (ስዊዲናዊ ነው) መጽሐፍ  ብታነቡት» ጥሩ ምንጭ ይሆናችኋል። እዛ ላይ ስትመለከቱ ኤርትራ ውስጥ የኢትዮጵያ አስተዳደር በግልጽ ታያላችሁ። ንጉሱ ከኤርትራ የሚፈልገው «ግብር» ነው። ኤርትራኖቹ የሚፈልጉት የተሰጣቸው መብት ራሳቸው እንዲያስተዳደሩ ነው፡ ሆኖም ግን ንጉሥ የበላያቸው እንዳለ ደግሞ ያምናሉ።  ወደ ጎንደር ሄደው ሹመት ያገኛሉ በምትኩ ግብር ለንጉሡ ይከፍላሉ፡ «ጎንደር ከይድካ እንታይ አምጻእካ» (ጎንደር ሄደህ ምን አመጣህ?) የሚለው ከዚያ ከሹመት ጋር የተያያዘ ንግግር የመጣ ነው።

ጥያቄ---------------- አህን አንተ ያልከው ሰምቸዋለሁ ደጋማው ክርስትያን ለ50 አመት ሙሉ ኢትዮጵያ ይል ነበር ብለሃል፤ እውነት ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ለምሳሌ የአከለጉዛዩ እነ ራስ ተሰማ የመሳሰሉ የነጻነት «ኢንፍሊወንሻል አይካኖች »ኢትዮጵያ ነን ከሚሉ ማሕበሮች ይልቅ እሰላማዊ ራቢጣዎቹ ጋር የጠነከረ ግንኙነት ነበራቸው። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ወደ ሌላ አካባቢም ብትሄድ እነ ደጃች ኪዳነ ፤ ዓዲ ቐይሕ (አከለጉዛይ ውስጥ) ልክ እንደ ራሰ ተስማ የኤርትራ ነፃነት የሚጠይቁ ነበሩ። አሁን አንተ እንደምትለው ደጋማው ከፍል ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያ የሚል ነበር የምትለው 50 አምት ሙሉ ከሃይማኖቱ እና ከኢትዮጵያዊነቱ ፍንክች አላለም ከምትል  እንደሰጠሁህ ምሳሌ ደጋማው ሕዝብ የተከፋፈለ ሃሳብ ነበረው ብትል ብታሻሽለው  አይሻልም ነበር? የሚል ነው ጥያቅየ?

ሌላው ደግሞ ኢትዮጵያ ሲሉ የነበሩት በራስ ሥዩም አማካይነት ገንዘብ እየተከፈላቸው ብዙ ሽፍቶች ነበሩ እነሱ ናቸው ገፊቱን ሲያጋግሉት የነበረው፡ ምን ትላለህ?

መልስ---------------- የነ ራስ ተሰማ ጉዳይ ብዙ የጨቀየ  ፖለቲካ የገባበት ጉዳይ ነው። እሳቸውም ቢሆን መጪዋ ኤርትራ/ነፃነት ኤርትራ › እንታገል ብለው አላሉም። የሳቸው መስመር እንግሊዝ የመሰረተላቸው Liberal Progressive Party (LPP) ነው።  ከትግራይ  ጋር እንዋሃድ ነው እንጂ ነፃ ኤርትራ የሚል አልነበረም።  ወይንም ፖለቲካ ትግራይ የሚል ነው ይህ መሰመር ኢትዮጵያዊያን ነን ከሚሉት የተለየ ቢምስልም ጠለቅ ብለህ ስታይ  ብዙም  የተለየ  አልነበረም።

ስለ ራሥ ሥዩም እና ሽፍቶች ገንዘብ እየከፈሉ ኢትዮጵያ ንነ ለሚሉ ይገፋፉዋቸው ነበር ሰላልከው ራሥ ሥዩም ራሳቸው አቅም አልነበራቸውም፡ አንተ ስለእምትለው ስለ ሽፍቶቹ ጉዳይ እንግሊዞቹ ያጠኑት ተሞርኩዠ መጽሐፍ ላይ አሳትሜዋለሁ (Eritrea and Ethiopia: The Federal Experience)። እንግሊዞች በሚጋባ ስለ ኤርትራ ሽፍቶች አጥንተዋል፤ የሰው` ሃይል እና ጊዜም ስለነበራቸው በሚገባ የሽፍቶቹ እንቅስቃሴ ተከታትለው ጥናት አድርገዋል።  እንግሊዞች እራሳቸው ፈተና የሆነባቸው ብዙውን ጊዜ ሽፍታው ሳይሆን ደጋማው ማሕብረሰብ ነው። ምክንያቱም እንግሊዞች ሕንዶችን ሲገዙ ተቃውሞ የደረሳቸው ቢሆንም አፍሪካ ውስጥ ግን እንደ ኤርትራኖች ፈተና የሆነባቸው አገር የለም፡  እና ኢትዮጵያ ነን ብለው ከ1941 ጀምሮ  እንግሊዝን ፈተና ሆኑበት። ስለዚህም የተጠቀሙበት ስልት ፥እንግሊዝ ‘’የሃገር ፍቅር ማሕበር አባላት ኢትዮጵያ ነን የሚሉት የኢትዮጵያ ተቀጣሪ ተላላኪዎች ናቸው ፤ እያለ እንቅስቃሴው ለማሳነስ ሞከረእነዚህ ኢትዮጵያዊያን ናቸው ኤርትራኖች አይደሉም ወዘተ የሚለው የጀመረው ብ1941 የጀመረ ነው። እነሆ እሰካሁን ድረስ እኛንም በዛው ነው የሚጠሩን። ማወቅ ያለባችሁ እንግሊዞች ሴረኞች ናቸው መላዕክት አይደሉም፡ ሕዝቡ ለጣሊያን እሺ ብሎ 50 አመት ሲግዛላቸው ለኛ እሺ ብለው ለምን አልተገዙልንም በሚል “አንድነት” የሚሉትን ማበጣበጥ ጀመረ። ስለዚህም ጉልህ እንቅስቃሴ ሲያድርጉ የነበሩት የአንድነት ሰዎች እየፈለገ ያጠቃቸው ነበር።

ጥያቄ---------------------- እንዴት ነው እነ ራስ ተሰማ የሚያክል ብዙ ተከታይ አልነበራቸውም ስለዚህ ስለ ኤርትራ ነፃነት አያስቡም ነበር የምትለው?

መልስ-------- ቀደም ብየ ወደ እዚህ ውይይት ከመምጣቴ በፊት ግንዛቤ እንዲሰጣችሁ በሚል አንድ ጽሑፍ በኢመይል ለያንዳንዳችሁ እንዲደርስ ለአዘጋጂውን ልኬለት ነበር፡ ይድረሳችሁ አይድረሳችሁ አላወቅኩም;። ጽሁፉ ስለ ራስ ተሰማ እና ጣሊያኖች ብ48 ፤49 እና 50 ብዎቹ  ከጣሊያን  ‘ኢንተረስት’ ጋር እንዴት የተያያዘ እንደነበር ነው የሚያሳየው። እንኳን ሕዝቡ ሊከተላቸው ቀርቶ የገዛ ልጃቸው  ደጃዝማች አብርሃ ተሰማ  በ1950 ከሳቸው ተለይቶ ወደ አንድነት ኢትዮጵያ ወደ ሚሉት ማሕበር ነው የገባው። እርግጥ ነው ራስ ተሰማ ከኢትዮጵያ ጋር አንዋሃድም ይሉ ነበር ሆኖም የራሰ ተሰማ  አባባል በብዙ ትርጉም ሊተረጎም ይችላል። እርግጥ ነው ከራስ ተሰማ ጋር ሆነው የነበሩ ታዋቂ ሰዎች ከሸዋ ጋር አንፈልግም ሲሉ ነበር፤ ይህ ዝንባሌ ራስ ተሰማ እንደ ማስረጃ ልታቀርቡት ይቻላል፡ ሆኖም ብዛት እና ሃይል (ተከታይ) አልነበራቸውም፡ አብዛኛው ሕዝብ ኢትዮጵያ ነን ባይ ነበር

ጥያቄ

-------ልክ ነው ትግራይ ትግርኚ የሚሉት እንደ ራስ ድጃዝማች አብርሃ ተሰማ እንደ ወልደ አብ ወልደማርያም የመሳሰሉት እውነት ነው እንዲያ ይሉ ነበር ፤ሆኖም እንዳነበብኩት ይህ ሐሳብ ማለትም የነ ደጃች ተሰማ አስመሮም የትግራይ ትግርኚ ፖለቲካ በብዙውን የትግራይ ሕዝብ ተቀባይ አላገኙም ነበር። ኤርትራ ውስጥም እንዳልከው ተቀባይ አላገኙም ነበር።ሰለዚህም It died (ከሰመ)።

መልስ -ተከስተ፦

እውነትህ ነው፡ ሆኖም የኔ ጥናት እሰከ1941 ነው የሚያቆመው።ከዚያ በኋላ ያለው ክስተት ልነካካው ያልቻልኩበት ምክንያት የበፊተኛው ውጤት ያስከተለው ስለሆነ ነው።ከዚያ በኋላ ኤርትራ በተለያየ መንገድ የተከሰተ “ደቨሎፕመንት” አለ። አንዱ የማነነት ክስተት ነው። ማንነት በየጊዜው እንደየሁኔታው ይፈጠራል።ከ1950 ዎቹ እሰከ 90ዎቹ የነበሩት ወቅቶች የተከሰቱ ክስተቶች ነበሩ። ክሰተቶቹም የተለያዩ ማንነቶች አዝለው ተከስተዋል።እዛ ላይ ብዙም ላተኩርበት አልፈለግም። ትኩረት የሰጠሁት ክስተት ግን እናንተም የምትጠይቁኝና የምትከራከሩኝ ነጥብ በ1941 ጀምሮ ደጋማው ሕዝብ የኢትዮጵያዊነት ስሜት እና ማነንት  ያንጸባርቅ ነበር ወይ ለሚለው ክርክር የኔ አቋምና ድምዳሜ “ጠንካራ የሆነ ስሜት ነበረው አዎ!” የሚል ነው። ለምሳሌ ጠያቂየ እየሞገተኝ ያለው መከራከሪያው “ከሸዋ ጋር ልንቀላቀል አንፈልግም ሲሉ የነበሩት እነ ራስ ተሰማ አስመሮም እና የመሳሰሉት የከበሳ አክባቢ ሰዎች አልነበሩም ወይ ለምንድ ነው እነሱንም ጨምረህ “የከበሳው ሕዝብ (ደጋማው ሕዝብ) እንዳለ በሞላ ኢትዮጵያዊ ስሜት እንደነበረው አድርገህ የምትደመድመው? ሰላልከኝ ፤ ይህ ለእውነታው አይቋጥርም። አዎ ከሸዋ ጋር አንድነት ልንፈጥር አንፈልግም ትግራይ ትግርኚ የሚሉ ነበሩ፤ እነዚህ ግን እዚህ ግቡ የማይባሉ እሚንቶች ነበሩ። በዛው ወቅት አብዛኛው የደጋው ማሕበረሰብ ማንነት ኢትዮጰያዊያን ነን የሚል ሕዝብ ነው የነበረው የሚል ድምዳሜ ነው ያለኝ።

 

ጥያቄ፦ ተወልደ ስዕሉ እባላለሁ። የኔ ጥያቄ በወቅቱ የነበረው የብ ሔሮቹ የሕዝብ ብዛት ቁጥር ያደረግከው ጥናት ምን ይመስላል? እንዳውም እነዚያ 9 ብሔሮች እንደ ብሔር ተብለው ለመጠራት ክራይተርያው ያሟላሉ ወይ? ሁለተኛው ጥያቄ እሰላሙ ቆላማው እና ደጋማው ክርስትያን 65

ለ35 (ረሺዮ) ነበር ብለህ ነበር የሚል ጥናትህ አሳይተሃል። ይህ “ሴንሳስ” ጥናቱ የመቸ ነው? ሱዳን ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ እሰላምዊ ማሕብረሰብ ኤርትራ ዜጎች እኛን ያልጨመረ “የሕዝብ ቆጠራ” ስለሆነ እሰላሙን ያሳነሰ የሕዝብ ቆጠራ ነው አንቀበለውም የሚሉ ነበሩና አንተ የምትለው ካለ? ከዚህ ጋራ የምጨምረው ጥያቄ፤ ከዛው ከጣሊያን ወቅት በኋላ አውራጃ በሚል ሲጠሩ የነበሩት የድምበር “ደሊሚነሺን /የድምበር ምልክቶች ነበራቸው ወይ?

ተከስተ መልስ

ብዙ ጥያቄ ነው። የመጨረሻው ጥያቄህ የመመለስ አቅም የለኝም።  ሁለተኛው ጥያቄህ ግን ልመልስልህ ፤መጽሐፌ ላይ እንዳሰፈርኩት ጥናቱ የ1935 ጥናት ነው።

ጥያቄ - ዶ/ር ገብረ -

የኔ ጥያቄ፤ በዶ/ር በረከት ሃብተስላሴ እና በዶ/ር ዓለምሰገድ ላይ ያለህ አስተያየት ከነሱ ጋር በስነ ሐሳብ ትንታኔ እንደማትስማማ ገልጸሃል። በዚህ ጉዳይ ያለህ ሪዝርቨሺን ‘እነሱ የታሪክ ምሑራን አይደሉም’ የሚል ነው። እንደዚህ ስትል ‘አንድ የታርክ ሞያተኛ መከተል ያለበት የሞያተኛ አግባብ ስላልተከተሉ ነው፡ ወይንስ ትንታኔአቸው ጎደሎ የሆነ መረጃ ስለሚያቀርቡ ነው? የሚል ጥያቄ ነው ያለኝ።

መልስ ተከስት ነጋሽ፤-  አዎ፡ ያቀረቡዋቸው የምርምር ጥናቶች  የሚያሳዩት ተገቢው የታሪክ ምርምርና አቀራረብ አላሟሉም፡ ከኔው የጥናትና የምርምር ዘገባ አብሮ አይሄድም። ማየት የሚገባቸው ጥናትና ምርምሮች ሳያዩት ሆን ብለው አልፈውታል።በወቅቱ የተደረጉትና የነበሩት የታርክ ድርጊቶችና የነበሩት  ክንውኖች እያዩትም ፤ እንዳላዩት አድርገው አለፈውታል። ስለዚህ በነዚህ ሁለት ሰዎች ላይ ያለኝ ግላዊ ሳይሆን ታሪካዊና ምሁራዊ የጥናት አለመግባባት ብዙ ስህተቶችና ጎርባጣ አቀራረብ ሰላላቸው ነው

ጥያቄ-ዶ/ር ገብረ- ጎርባጣ እና ቅንነት የጎደለው ያልከው ጉድለታቸው ምን ላይ ነው?

 

መልስ-ተከስተ-

በጣም በርካታ! አሁን እዛ ልገባ አልፈልግም፤ ምክንያቱም በጣም ሰፊ ርዕስና ትንታኔ የሚጥይቅ ስለሆነ ሌላ ቀን ፕሮግራም ብታዘግጁልኝ ከጋሸ በረከትና ከዓለምሰገድ ተስፋይ ጋር ያለኝ ተቃራኒነት የግል ሳይሆን የታሪክ አቀራረብ ትንታኔ ልዩነታችን ላብራራላችሁ ፈቃደኛ ነኝ።

ማየት የሚገባቸው ሆን ብለው ኣያወቁትና እያዩት ያለፈዋቸው የታሪክ አቀራረቦችና ግድፈቶች ልዩነት ነው ያለን

 

ጥያቄ ያንተ ጥናት የራስህ ፋክቶች እንዳሉህ ነው ካነጋገርህ የተረዳሁት

መልስ፤ - ልዩነታችን እንደዚያ አይደለም። ልዩነታችን ማየት የሚገባቸው ምንጮች አላዩዋቸውም፤ እያዩዋቸውም እንዳላዩዋቸው ዘልለውታል ነው እያልኩ ያለሁት

በሌላ መልክ ላስረዳህ። ጥናታህን አይቸ- እንዲህ እንዲህ ያሉ ነገሮች አልፈሃቸዋል፤ ምክንያቾቹና መረጃዎች ይህ ፥ይህ፥ ይህ እና በዚህ ቦታ ማግኘት ትችላለህ ብየ በተቁምህ እና እየተነገረህም ዕርምት ሳታርም እና እነዚያን መረጃዎች ባለመጠቀም ከቀጠልክ ሆን ብለህ እያውቅክ ለማይታወቅ ውሎ ለማዋል አስበሃል ማለት ነው።

አስተያየት (የመድረኩ መሪ)= ለምሳሌ ባንተ ጥናቶች ላይ አንዳንድ ክርቲክ ያቀረቡ አንዳንድ የታሪክ ተማራማሪዎች ሪቻርድ ሪድ ()  ቶም ክልዮን () እና የማነ ምስግና፡ ባንተ ጥናት ልዩነታቸው ትንሽ አይቸ ነበር (Very critical of your work)። ለምሳሌ የሪቻርድ ሪድ አንተን የሚተችህ ስለ ኤርትራ ያለህ አቀራረብ እና ከሻዕቢያ ጋር ያለህ ልዩነት ያንተ የታሪክ አቀራረብ የኢትዮጵያን ቨርዢን አቀራረብ ነው ይልሃል። ለምሳሌ ኤርትራ ውስጥ የነበረው የሰራተኛ ማሕበራት ተቃውሞ እንቅስቃሴ ቸል (ኢግኖር)  አድርገኸዋል ይለሃል፡ ሰለ ናሺናል አይደንቲቲ ደግሞ “ኢቮልቪንግ ፕሮሰስ እንጂ......... ለምሳሌ አይደንቲቲ ላይ ከራስህ ካነበብኩት ክራይተሪያ ውስጥ አንዱን ልጥቀስ “ኤርትራ ውስጥ የተማረ ክፍል አልነበረም፤ በቂ የምጣኔ ሃብት ዕድገት አልነበራትም” ብለሃል፤ እነዚህ ብቻ ናቸው እንድ የኤርትራ አይደንቲቲ መለኪያዎች?

ሌላው ደግሞ ኤርትራዊ እኔ ኤርትራዊ ነኝ ብሎ እሰከ ነጻነቱ ማወጅ እና ማምጣት የደረሰው ተከስተ ከሻዕቢያ ጋር ልዩነት ሰላለው ነው....’ የሚል ነው  የነሱ ክርቲክ። በነዚህ አንድ ነገር ብትለን።

ተከስተ መልስ፦ ውይ! አስተያየትህ ሰፊ ርዕስ የያዘ ሰፊ ጊዜ የሚጠይቅ ነው፤

የምድረኩ አዘጋጅ- ንግግሩን በማቋረጥ- «ይገባኛል እንዳው ስለ ከርቲክ ሰጪዎቹ “ባጭሩ /ሳመሪ” አድርገህ ብትሰጠን በየ ነው።

ተከሰተ በመቀጠል እንዲህ ይላል፦ አዎ ጆን ሪድ  (ጠያቂው “ሪቻርድ ሪድ” ይለዋል፤ ተከስተ ግን ጆን ሪድ” ነው የሚለው)- ትልቅ የታሪክ ተመራማሪ ነው፤ የኔ ጥናት እጅግ ተንሽየ ጥናት ነች፡ ሆኖም ከጆን ሪድ ጋር ልዩነታችን «ሰውየው ስለ ኤርትራ ታሪክ ከሚያውቀው በላይ ነው የሚጽፈው”። ስለ ቶም ክልዮን፤ እወነቱ ነው ስለ ሌበር ሙቭመንት አንስቶታል፤ እውነት የሌበር ዩንዮን እንቅስቃሴ በዛ የፈደራል አክስፐርይንስ መጽሐፌ ውስጥ አላየሁትም፣ ያ እውነት ነው። ሆኖም ይህችኛዋ ነጥብ የመጽሓፌ “ኮንክልዥን” (እውነታ) ሊያፈርሰው አይችልም። እኔ እና ቶም ክልዮን ለዩነት አለን።

ጥያቄ - እኔ የቤተክሕነት ምሁር አይደለሁም- ግን ሰለ ደብረቢዘን (ጠያቂው ደብረቢዘንን \ደብረዘይት እና ደብረሲና/ እያለ እያመታታ ነው የሚጠቅሰው ሰለዚህ ራሴ አስተካክየዋለሁ ደብረቢዘን እያልኩ። ተከስተም ሰውየውን የደብሩ ስም እንዲያስተካክል አላደረገም ) ቤተክርስትያን ሰላነሳኸው ጉዳይ ነው የምጠይቀው፤። ይኸውም ሰለ ደብረቢዘን አንድ ኤርትራዊ የኪነት ምሁር  የሰጡኝ ትንሽ ጽሑፍ እፊቴ ላይ ነች ያለቺው እንዲህ ይላሉ “ክስርስትና ኤርትራ ውስጥ እንደተጀመረ ነው የነገሩኝ። ያውም ክርስትና ከደብረ ቢዘን ወደ ኢትዮጵያ ክርስትና እንደሄደ ነው” የነገሩኝ፤ ማስረጃቸውም 9ኙ (ተስአቱ) ቅዱሳን የሚባሉት መጀመሪያ እዛ ነበር ያረፉት ደብረቢዘን ውስጥ ነው፤ ወደ ኢትዮጰያ ክርስትና የገባው ኤርትራ ውስጥ ኖሮ ክ40 አመት በኋላ ነው ወደ አትዮጵያ እነዚህ ቀዱሳን የዘውት የሄዱት  ያውም “ኢትዮጰያዊያን አዲስ ኣበባ ወስጥ መለስ ዜናዊ በተገኘበት ያከበሩት የሚሊየነም ዘመን “የኤርትራ አቆጣጠር ነው” ኢትዮጰያዊያን ሚሊይነም ብለው ማክበር የነበረባቸው። ገና 40 አመት ይቀራቸው ነበር በለው ነው እኚሕ የሃይማኖት መሪ የነገሩኝ።

 ደብረቢዝን የነበሩትም መነኮሳትና መዕመኖች የኢትዮጵያ ባንዴራ ያውለበልቡ ነበር ብለሃል ግን ታሪኩ ተቃራኒ ነው። አንተ ከምትለው እና በዚህ በኩል ያለው ታሪክ። ስለዚህ  የምታውቀው ነገር ብትነግረን። (ጠያቂው በመሁራንነት ስም የተቀመጡ ተወያዮች ውስጥ አንዱ ነው ከዚህ የምንረዳው «ሁሉም ኬኛ» የኦነጎቹ ባሕሪ ነው።)

ተከስተ ነጋሽ መልስ፦ ሃያምኖትን በሚመለከት «ታሪክ ኤርትራ» የሚል በመሪጌታ በርሃነ የተጻፈ መጽሐፍ አለኝ፤ የኔ መንጭም ያ መጽሐፍ ነው። እሳቸው ያሉት፤ «ክርስትና የተጀመረው “አክሱም” ውስጥ ነው»። ብለዋል። እኔ የሃይማኖት ምሑር ሰላልሆንኩ ክርስተያን የት ተጀመረ የሚል አልጠቀስኩም። ርዕሴም አይደለም፡ እኔ ያልኩት ደብረቢዘን ውስጥ የነበሩት ምዕመናን የተዋህዶ አማኞች ስለነበሩ ሲያውለበልቡዋት የነበርዋት ስንደቅ ዓላማ ‘ልክ እንደ የኢትዮጵያ ስንደቅ ዓላማ የነሱም ያቺኑ አርማ ነበር ሲያውለበልቡ የኖሩት” ይህም ለጣሊያኖች ትልቅ ትርጉምና ራስምታት ነበረውመንኮሳቱና ታቦት ሲያወጡ ሰው ሲሞት ቀብር ላይ የሚያውለበልቡዋት ሰንደቅ ዓላማ ‘የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ’ ነበር። ነው ያልኩት እንጂ ክርስተና የት ተጀመረ የሚል አልተወያየሁም፤ አልጻፍኩም። እንደ መሪጌታ ብርሃነመስቀል መጽሐፍ ግን ክርስትና የተጀመረው “ትግራይ ውስጥ ነው።”

ጥያቄ- ከዶ/ር በረከት እና ዶ/ር ዓለምሰገድ ተስፋይ ጋር ያለህ ‘ልዩነት ሰፊ ስለሆነ ሌላ ቀን ፕሮግራም ብታዘጋጁ መወያየት ይቻላል ብለሃል፤  ያ ጥሩ ነው፡ ያ እንዳለ ሆኖ  ጥቂት ነጥቦች እንዲህ ፥ እንዲህ ያሉ ልዩነቶች አሉን ብለን እና ብትገልጽልን? በንግግርህ ግን እንዲህ ብለሃል፤ “ጣሊያን ኤርትራ ለብዙ አመት ቢገዛም ፤ “የተወው የጥናት ስነድ” የለም ብለሃል፡ ለዚህ ላለመተው ምክንያት ምንድነው? ኤርትራ እንደ ሃገር ሰላለቆጠራት ወይስ እንደ የኮልኒ ማፈናጠሪያ ፥ እንደ ሚሊታሪ ማዘዣ (ቤዝ) ሰላያት ነው? What was the intent?

በመጽሐፍህ ውስጥም የኤርትራ ፈደረሺን ያልሰራበት ምክንያት ፈደረሺን inherently weak ስለሆነ ሳይሆን  ወረቀት ላይ ስለሰፈረ፤ ነው ብለሃል፤ ማለትም ፍደረሺኑ በትክክል ቢሰራ ኖሮ በ40ዎቹ የነበረው የነፃነት እንቅስቃሴ በፈደረሺኑ ታስሮ ይቆይ ነበር (የነፃነት ጥያቄው ይቆም ንበር) ወደ እሚል አባባል ያዘነበልክ ይመስላል፤ ምክንያትህ ምንድነው?

3ኛው ጥያቄ፤ ጣሊያን ኤርትራን ሲገዛ በኢንዳስትሪ አበልጽጓታል፤ አትዮጵያን ግን የነሱ (የጣሊያን) አዲዮሎጂ ፕሮፓጋንዳ መሺን አድርጓት ነበር፤ ምንድነው የጣሊያን እስትራተጂ “ኤርትራን በኢንዳስትሪ ሲያሳድጋት ኢትዮጵያን በአዲዮሎጂ ሊአሳድጋት የፈለገው?

ተከስተ መልስ፡ በመጨረሻዋ ጥያቄ ልጀምር። በመሰረቱ ጣሊያን ኤርትርራን በእንዳስትሪ አበልጽጓት ነበር የሚለው እኔ በብዙም ትርጉም አልሰጠውምየነበሩት ኢንዳስትሪዎች በጣያልያኖች የሚካሄዱ የጣሊያን ነብርቶች ናቸው። የኤርትራኖች አስተዋጽኦ የጣሊያን ኢንድስትሪ “ሸቃዮች፥ሰራተኖች” እንጂ ባለ ንበርቶች አልነበሩም

ሌላው ጣሊያን በ1935 ኢትዮጵያን ሲወር የኖረበት አመት 5 አመት ብቻ ነው፡ ስለዚህ ሊያደርጋቸው የሚችለው በጣም ውስን ነው። ኤርትራ ግን «ለናፖሊ» (ጣሊያን) የባህር ቅርበት ሰላለው የሚሊታሪ ማስፈንጠሪያ (ቤዝ) «ፋይናንሺያል ቤዝ ሚሊታሪ Militari base, Financial base, Economic base, Industrial base to occupy Ethiopia’ የምታገለገል አቀማመጥ ሰላላት ነበር

በ1939 ኤርትራ ውስጥ አስመራ ውስጥ ብቻ 58 ሺሕ ጣሊያኖች ነበሩ። የኤርትራኖች ብዛት ቁጥር 45 ሺ ነበሩ። ይህ ስትመለከቱ ላንዲት አገር “ኢንዳስትራላይዝ ማድርግ ነው ተብሎ ሊወሰድ ነው? ማለት አይቻልም።” ኢትዮጵያ እያደገች ስትሄድ ኢንዳስትሪ ባለሃብቶች የነበሩት ጣሊያኖች እየደከሙ ሲሄዱ የነበርዋቸው ኢንዳስትሪዎ ይዘው ወደ ሃገራቸው ሄዱ ወይንም ዘግተዋቸው ሄዱታሪኩ ይህ ነው

 

ስለ ፈደረሺኑ ጉዳይ ስላነሳኸው፡ ፈደረሺን የሚባለው መከሰት ያለነበረበት ክስተት ነውተድላ ባይሩም ይሁን አስፍሃ ወ/ሚካል እነዚህ የአንድነት አባላት እና የፍደረሺኑ መሪዎች የነበሩ ናቸው፤ እነሱ ሲሉ የነበሩት “ፍደረሺን” የሚባል ቃል ለትግርኛም ይሁን ለአማርኛ የማይታወቅ ቃል ሰለሆነ «አንድነት በውል ማለት ምን ማለት ነው?» ይህ ውል አያስፈልገንም «ለአንድነት ውል አያስፈለገውም» ብለው ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጣን የተረከቡት እነዚህ ነበሩ። ስለዚህ ፈደረሺን የሚባል ቃል ብቋንቋችን ሰለሌለ አፍርሰነዋል/ ለአንድነት ውል አያስፈልግም ብለው አፍርሰውታል።

ከመጀመሪያውኑ ሊከሰት አይገባውም ነበር፤ ሆኖም ተከሰተ፤ በዚያም ተበላሸ

ወደ ኤርትራ መምጣትና መኖር የጣሊያን /intent ምን ነበር? ብለህ ሰለጠየቅከኝ ጉዳይ- መልሴ “ጣሊያን ኢትዮጵያን ሺ አመት ለመግዛት ነበር”። ሃገሪትዋን በቋንቋ በሃይማኖት ከፋፍሎ 1000 አመት ለመግዛት ነበር የመጣው (5 አመት ሲኖር አይዲዮሎጂ ያልኩት ያንን ለማመቻቸት ነው) ። ይሁን እንጂ 1000 አመት ሊኖር የወጠነው 5 አምስት አመት ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ ኤርትራ ውስት ግን 50 አመት ኖሮ ተሸንፎ ተባርረ

ጥያቄ- ፈደረሺኑ ወረቀት ላይ በመሰፈሩ እንጂ በአግባብ ቢሰራ ኖሮ የኤርትራ ነፃነት ስሜትና እንቅስቃሴ ይቆም ነበር ብለህ መጽሐፍህ ላይ የጠቀስካትን መልስ አልመለስክልንም፤

ተከስተ መልስ ፦ ፈደርሺኑ እንዳይሰራ የሚፈልጉ ወገኖች በጣም ብዙ ነበሩ። በሌላ በኩል ደግሞ በ40ዎቹ የነበሩ «የሊግ» አባሎች ፈደረሺኑ እንዲሰራ ከልባቸው ይፈልጉ ነበር። እነሱ ነበሩ ሲያንቀሳቅሱት የነበሩት። ፈደረሽንዋ እንዳትፈርስ ጠንክረው ሲሰሩ የነበሩ የሙስሊም ሊግ አባሎች ናቸውምንያቱም ፈደረሺኑ ተግባራዊ ከሆነ በኢትዮጵያዊያን ክርስትያን ሃይሎች እግር ውስጥ አንወድቅም የሚል ስሜት ስለነበራቸው ነው። አዎ ፍደረሺኑ በትክክል ቢሰራ ኖሮ የኤርትራ ነፃነት ባልተነሳ ነበር። ይህ ግን እኛ እንደ ታሪክ ተማሪዎች “ሆኖ ቢሆን ወይንም ኖራ ብትኖር ኖሮ...” የሚል ክርክር ረዢም አይሄድም፤ እኛ እንደ ታሪክ  ተማሪዎችና ተመራማሪዎች አንቀምበለውም፡ አልሰራም።

ጥያቄ- - ግራ የሚገባ ነው። ጣሊያን ኢትዮጵያን 1000 አመት ለመግዛት ነበር ፍላጎቱ ግን አልተሳካለትም፤ በለሃል ኤርትራ የወታደራዊ ሰፈር አድረጎ ኢትዮጵያን ለመውረር ነው የተጠቀመባት በለሃል፤ በሌላ በክል ድግሞ ኤርትራን በኢንዳስትሪ አሳድጓት ነበር ብለሃል እየተጋጨብህ ነው፤ ኢንዳስትሪን ማሳድግ እና ወታደራዊ ‘ቤዝ’ እንዴት የጣጣማል?

መልስ ተክስ ፤- በኢንዳስትሪ በልጽጋ ነበር ያልከው አንተ እንጂ እኔ አይደልሁም። እኔ የገለጽኩት ስለ ኡንዳስትሪ ባለቤቶች ማን እንደነበር ገልጫለሁ፡ ሸቃዮቹ የፋብሪካዎቹ ሰራተኞች ማን እንደነበር አብራርቻለሁ። ያ ብልጽግና አይደለም በማለት ግልጽ አድርጌልሃለሁ።

ትንሽ ላብራራልህ፤ ጥሊያን 50 አመት ኤርትራ ውስጥ ሲኖር ኢትዮጵያን ለምወረር የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ፥ የወታደራዊ ፥ የሰው ሃይል ተዋጊ ሁሉ አሰልጥኖ አደራጅቶ ወደ ኢትዮጵያ ተሸጋገረ፡ በሁለቱም ወረራዎች ወቅት አልቀናውም። ኤርትራ እኮ የኢንድስትሪ ቦታ ሊያድረጋት ፈላጎትና ዕቅድ ቢኖሮው ኖሮ የወታደራዊ ሰፈር ማድረግ አይጥበቅበትም ነበር። ወታደራዊ ሰፈር ሰለነበረች ነው ኤርትራኖችን ወደ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ወደ ሊቢያና ሶማሊያ ድረስ ሄደው ቀኝ ግዛቱን እንዲያግዙት አድር ጓል። ግማሽ ሚሊዮን የሚያክል ጣሊያን ነው ከጣሊያን አገር ተሰድዶ ወደ ኢትዮጰያ የገባው። ለነሱ ሲሉ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንዳስትሪዎች መስርቶ ነበር።

ጥያቄ ላቃርብልህ  ኤርትራ ውስጥ የአግሪካልቸራል ኢንዳስትሪ ነበር እኮ!

የተከስተ መልስ... ኤርትራ ውስጥ የአግሪካልቸር ደቨሎፕመንት ይህ ነው የሚባል አልነበረም። “ተሰነይ” ውስጥ “የኮክ” (ፒች ማለቱ ነው ኮክ ሲል) ፈራፍሬ እርሻ ነበረች ያቺም እንደ ኢንዳስትሪ መቁጥር አትችልም።

ጥያቄ እዚህ ላይ እኔም ጣልቃ ልግባ በማለት አንድ ጠያቂ  እንዲህ ይላለ፦  ኢትዮጵያን ለመያዝ ሳይሆን ኤርትራን ኮሎኒ ለማድረግ ነው ዋናው ትኩርቱ፡ ለምሳሌ “ጉራዕ“ኩዶ ፈላሲ” ወታደራዊ ሰፈር ሲያድረግ እነ ደጃች ባሕታ ሃጎስ (አከልጉዛይ) ነበሩ ጣሊያን መሬት መያዝ ሲጀምር ነበር መስሎኝ በጣሊያን ተቃወሞ የተነሱት። ጣሊያን ዋናው ወደ ኤርትራ የመጣው ከአሜሪካ እና ጣሊያኖችን እያመጣ ሊያስፍራቸውና ጥሩ ምቾት እንዲኖሩ አርትራ ኮሎኒ ለማድረግ ነበር ዋናው ዓላማው። ኤርትራኖች ተቃውሞ ሲያድረጉ ነው እንደማይሰራ ሲያውቅ ዓይኑ ወደ ኢትዮጵያ አዘንበሎ ኤርትራ ወደ ወታድራዊ ሰፈር የቀየራትና ወደ ኢትዮጵያ የሄደው። ልክ ነኝ?

ተከስተ መልስ- አዎ ልክ ነህ! ይላል ተከስተ ደካማ እና ይታሪክ መሁርነቱ ያኮላሸበት መልስ ሲምለስ። (መጀምሪያ ነገር ከምጽዋ ወደ መሃል እና ወደ አስመራ ኤርትራ ጠርተው ጋብዘው ያመጡት እራሳቸው ኤርትራኖች ናቸው፡ ሌላውን ማስረጃ ለተውና እራሱ የሻዕቢያው ካድረ ዶ/ር ዓለምሰገድ ተስፋይም ያመነበት ነገር ነው። ለምን ግባ ብለው እንዳሰግቡትም ግራ የሚገባ ነገር ነው ሲል ዓለምሰገድ እራሱ ተናግሯል- ጽፏልም ፡ 2- ባህታ እራሱ የጣሊያን ባንዳ ነበር ፤ በኋላ ነው ጣሊያኖችን የተቃወመው፡)

ጥያቄ  ታሪክ የሚጠናው መቸ ነው?

ተከስተ - መልስ ፤ ታሪክ የሚጠናው 50 አመት ካደረገ በኋላ ክንዋኔዎች በደምብ አድርጎ ለጥናት ስለሚታዩና ቀላል ስለሚሆኑና የቆመ ስለሆነ፤ ያን ጥናት ማድረግ ይቻላል። አሁን ሰላሉት ነግሮች የቅርብ ስለሆኑ ሙሉ ታሪክ መጻፍ አይቻልም፤ ቀጣይ ስለሆነ ማለት ነው።

ቀደም ሲል ሰዎችና ሰለ ታሪክ መቀያየር ስትናገር ስለ ጌታቸው ረዳ (ወያኔው) አንስተህ ትናንት የተናገረው እና ዛሬ የተናገረው ተጻራሪ ንግግሮች ናቸው ብለሃል። አዎ ለምሳሌ ስለ ጌታቸው ላጥና ብትል የተሟላ ታሪክ አይሆንም፤ ምክንያቱም ወጣት ነው፤ ነገም ሌላ ንግግር እና የሚምታቱ ወይንም ወደ ነበረበት ሐሳብ የሚመለስ ንግግር ሊናገር ይችላል፤ ወጣት ነውና ቀጣይ ክስተት እናያለን፤ የማንም መሪዎች ወይንም ገለሰብ ታሪክ እንደዚያ ነው። ስለ ጌታቸው እንጻፍ ቢባል አሁን አያቻልም፡ ሙሉ ታሪክ የሚሆነው ከሞተ 50 አመት ሙሉ ታሪክ ይሆናል። ምክንያቱም የተደበቁ መረጃዎች ሁሉ ቁልጭ ብለው ይወጣሉ።

በነግራችን ላይ እሱ ስለ ኤርትራ ሰላለው መስመር በሃሳብ መመጎት ነው እንጂ መጥላት የለብንም፡ ለምሳሌ እኔ ተውልዴ አከለጉዛይ ‘’ማዕረባ” ከሚባል ገጠር ሲሆን ዜግነቴ ደግሞ “ኢትዮጵያዊ ነኝ”። አከለጉዛይ አውራጃ ተወላጅ ሆኜ ኢትዮጵያዊ መሆን እናንተ እንድትጠሉኝ አይገባምመከራከር ግን ይቻላል

ያቄ አንድ ተመልካች ጣልቃ ገብቶ እንዲህ ይላል -

ዶ/ር ተከስተ እወነቱ ነው ለዚህ ነው ኢትዮጵያኒስቶች ያላቸውን ሃሳብ እዚህ መድረክ እየመጡ ቢወያዩ ከጦርነትና ጥላቻ እንወጣለን፤ ሱዳኖች ሶማሊ ኤርትራ ጂቡቲ ወዘተ.. እንደዚሁ ከጦርነት ለመውጣት መወያት አሻግረን ማየት ይገባል።እኔ ኤርትራዊ ነኝ ኢትዮጵያ ነኝትግራይ ነኝ ፥ ሶማሊ ነኝ ፥ወዘተ..፣ የሚለው መስበር ካልቻልን ችግር ነው። ምንም እንኳ እኔ ኤርትራዊነቴን አጥብቄ ብይዘውም በአካባቢየ ያሉት ሕዝቦች “ከጎረቤታችን ኢትዮጵያ” በሰላም መኖር የምንችልበት መንገድ እንጂ በጦርነት መፍታት ጥሩ መፍትሄ አይሆንም። ይላል።

(ይህ አባባል ትንሽ ፈገግ አላስኘህም? እሱ ኤርትራ የሚላት ሃገሩ ሃገር ብሎ ሁለት የባሕር በር ይዞ እኛ ያለ ባሕር  በር ቆመን ከሱ ጋር ጉርበትና  እና ሰላም እናድርግ ሲል የሚገርም ነው፤ አደለም?)፤

 የሚከተለው ጥያቄ ጠያቂት ደግሞ የለየላት ማሃይም ነች፤
ጥያቄ- ወ/ሮ ጽገ፤- የኔ ጥያቄ ዶ/ር ተከስተ ስለ ፈደረሺን ስትናገር “የአንድንት ማሕብረ አባሎች ፍደረሺኑን አልተቀበሉትም ነበር  ብለሃል። ግን ለምሳሌ እነ አቦይ ወልደአብ ወልደማርያም የማሕበር አንድነት አባላት ነበሩ ነፃትን የሚጠይቁ ይህንን እንዴት ልታጣጥመው ነው?

ሌላው ጥያቄ ደግሞ- ከዶ/ር በረከት እና ዶ/ር ዓለምሰገድ ተስፋይ ጋር ልዩነት አለን ብለሃል፤ እኔ ይማውቀው ግን  ልዩነት የላችሁም፡ ለመሳሌ ዶ/ር በረከት የሚለው “እኔ በሕይወት እያለሁ ሕልሜ ኢትዮጵያን እና ኤርትራ አንድ እንዲሆኑ ለማየት ነው የምመኘው ሲል ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ይህንን መኞቱን ገልጿል፤ ስለዚህ ልዩነት የላችሁም። ስለ ዓለምሰገድ ተስፋይ ደግሞ ብዙ ጽሑፎቹ ስለ ትግል፤ እና ስላሳለፈው የትግል ታሪክ ነው የጻፈው፤ ስለዚህ ልዩነታችሁ ምንድ ነው? አንተ ኤርትራ ተወልደህ አድገህ አሁን ኢትዮጵያ ነኝ ስትል ምን ማለት ነው?

ተከስተ መልስ፡

በመጀምሪያ ጥያቄሽ ልጀምር፡ኢትዮጵያ ወይንም ሞት ሲሉ የነበሩ የአንድነት አባላት የተከትሉት መስመር ኤርትራ የሚባል አገር የለም ነው ሲሉ የነበሩት

ያች ማሃይም ሴት ንግግሩን ታቋርጥና እንዲህ ትላለች

እንድያ!አይሉም ነበር!

 ተከስተ በመቀጠል ፤ የኔ እህት የአንድነት አባላት ሲሉት የነበሩት «ኤርትራ የሚባል አገር የለም» ሲሉ ነበር ፡ አደለም እንዴ?

ሴትዮዋ መሃል ገብታ “የማይሉም ነበሩ” ትላለች፡

ተከስተም ንግግሩን በመቀጠል

ግለሰቦች እንደ እነ ራስ ተሰማ የመሳሰሉት ገለሰዎች የፈለጉት ሊሉ ይችላሉ፤ እኔ የምልሽ ግን እንደ ማሕበር ያቺ የአንድነት ማሕበር “እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን” ኤርትራ የሚባል አገር የለም፤ ነበር ሲሉ የነበሩት። የንትርኩ ምክንያትም ያ ነበር። የሃገር ፍቅር አባላት ሲጠልዋት የነበሩና አምርረው ሲታግሉዋት የነበሩዋት ዋና ነጥባቸው “ኤርትራ የምትባል አገር እንዳትፈጠር ነበር ዋና ትግላቸው

አሁንም  ደንቆሮዋ ሴትዮ ተከስተን ታቋርጥ እና እንዲህ ትላለች

“አዎ ኤርትራኖችም እንደዚሁ ኤርትራ አገር ነች ብለው ይቃወሙዋቸው ነበር!»
ተከስተ ይቀጥል እናመልስ ለመስጠት ሲሞክር

መጨረሻ ላይ  ጣልቃ እየገቡ ሊያስጨርሱት አልቻሉም፤ እስኪጨርስ መቆየት አልቻሉም እና መሃል እየገቡ ያቆሙታል፤ አንዱ እንዲህ ይላል፤

“ሁሉም በዛው መስመራቸው አልቀጠሉም እነ አስመሮም እነ ተድላ ባይሩ አንድነቱን እያጣሉ ወደ ጀብሃ ሄደዋል...ስለዚህ ‘ኮንሲስታንሲ’ አልነበረውም” እያሉ ያስቆሙታል።

ተከስተ ይቀጥል እና

« አልተቆራረጠም ኮንሲስታንሲው እንዳለ ነበር።ለምሳሌ ከተመሰረተበት ከ1941እሰከ 1950 ኤርትራ የምትባል አገር አያውቋትም! ሊያውቁዋትም አይፈልጉም እያልኩ ያለሁት ያ ነው። በኋላ ከ1952 ፈደረሽን ከመጣ ባኋላ ግን ራሱ ያቻለ አርዕስት ነው።

ጥያቄ አቶ አሮን ገብርሰላ

ላንተ ያለኝ አክብሮት ብዙ ነው፡ መጀመሪያ Italian Colonialism in Eritrea የሚል መጽሐፍህ የት አገኘዋለሁ?

በማከልም፤ እናንተ ኤርትራኖች ከተቀሩት አበሾች የላቀ አዋቂዎች ናችሁ ብለው ጣሊያኖች የበላይነትን ሰብከዋቸዋል ሲል “ሃሮልድ ማርኮስ” ጽፎታል። በዚህ አንተስ ምን ትላለህ?

ተከስተ መልስ -

በጣም አምሰግናሃለሁ። Italian Colonialism in Eritrea የምለው ‘ጉጉል’ ብታደርገው በነፃ ታነበዋለህ።

በማስከተል ስለ የበላይነት ጉዳይ ሃሮልድ ስለጠቀሰው ጉዳይ “አዎ ጣልያኖች ኤርትራኖችን እናንተ ከሌሎቹ አበሾች የላቃችሁ ፍጡራን ናችሁ “እስማርት” የሆናችሁ ዘሮች ናችሁ የሚል ትምሕርት በደምብ ሰርቶባታል። በጣም የሚያሳዝነው ግን ይህ የጣሊያን ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ተቀብለን ማንጸባረቃችን እጅግ ያስዝነኛል። እኛ 50 አመት ሙሉ የጣሊያን ወታደሮች ሆነን፤ የነሱ በር (ጌት) ጠባቂዎች ፤ ገረዶችና አትክልት ኮትኳቾች ሆነን ያየነው ነገር ረስተን  እንዴት ያንን የመሰለ የሚያሳፍር የጣሊያን የትምክሕት ትምሕርት ተቀብለን ሁላችንም እኔም ጭምር ከዚያ እኔ ነኝ የበላይ ባይነት ትምክሕት አለመወጣታችን እጅግ አስዛኝ ነው

ለመሳሌ የኤርትራ ታሪክ  የሚጀምረው በጣሊያን ነው ካልክ (ብዙ ኤርትራኖች እንደሚያምኑት) መጀምሪያ ማንነትን ማሳነስ ነው።ታሪክህን መካድ ነው። ከዚያ ታሪካችን ከጣሊያን የሚጀምር ነው የሚለው እምነት/አገርነት/ ከዚያ ጣሊያን ከተወልን ስነልቦና አልወጣንም። ከዚያ በፊት እነማን እንደነበርን መካድ ነው

ጥያቄ አሁንም እኔ አሮን ነኝ በድጋሚ የመጣሁት

ሰለ ፈርዲናን ማርቲን አንድ ነገር እንድትል ሰለጠየቅሁህ አልመለስክልኝም ረስተሃታል።

ተከስተ መልስ ፤ አዎ-  ፈርዲናን ማርቲን  ኤርትራን ሲገዛ የነበረ ነው፡ እጅግ የረቀቀ ፖለቲከኛ ግን ደግሞ እጅግ ዘረኛ ነበር። እውነታው ሲናገር “እኛ ለመግዛት እንጂ ለማስተማር አልመጣንም፡ ጣሊያንኛም ከሆን እራሳቸው በሂደት ይማሩታል” ብሏል። እሱ ከሄደ በኋላ ግን በ1907 እሱን የተካ ገዢ “ኖ ፥ ኖ እንደዚያ እማ አይሆንም ፣እኛ እኮ ሐላፊነት አለብን፤ በማለት ከእንግዚዝ ከፈረንሳይ ከአፍሪካ ውስጥ የሚያድረጉት በማይተናነስ 4 ት/ቤቶች ከፍቷል። አንድ ለካቶሊክ አንድ ለእስላም፥ አንድ ለኦርቶዶክስ ፥አንድ አስመራ ውስጥ ት/ቤቶች ከፍተው ትምህርት እንዲሰጥ አደረገ። ትምሕርቱ ግን እስከ 4ኛ ክፍል ብቻ ነው የተከፈተው

ጥያቄ፤-

ጨፋና ሃይለማርያም እባላለሁ(UK)፡

ጥያቄ የሚተዶሎጂ ጥያቄ ነው፡-አንተ እና ዓለምሰገድ ተስፋይ እና በረከት ሃብተሰላሰ የምትለያዩበት በምተዶሎጂ ነው ወይስ በምንድ ነው? ለምሳሌ ዓለምሰገድ በዚህ አመት የጻፈው መጽሐፍ ከጀብሃ አባላት ብዙ ወቅሳ ደርሶበታል። ........

ተከሰተ መልስ ፤- ለምሳሌ ራስ ተሰማ ያላሉትን አሉ ወይንም ያሉትን አላሉም ብየ መጻፍ የታሪክ አዘጋገብ አይደለም። እኔ እና ሁለቱም የጠቀስካቸው ሰዎች ልዩነታችን ብዙ ነው። ጋሽ በረከት ለምሳሌ በ1989 Eritrea and United Nation የሚል መጽሐፍ ሲጽፍ እዛ ላይ ሊያሰፍረው ሊጠቅሰው ሊመዘግበው ሊጽፈው የሚገቡት ብዙ ነገሮች እያወቀ ሆን ብሎ አልጻፋቸውም። ይህ በታሪክ አዘጋገብ ነውር ነው።  እኔ እንደተመራማሪ ይህንን አላደርግም፡ በፍጹም። አንድ ጉዳይ  ሰታጠና ወይ ሙሉውን መመዝገብ ነው ወይንም አለማጥናት ነውካጥናህ ደግሞ የነበሩትን ክስተቶች ሳትጨምር ሳትተው ማቅረብ ይገባል። ነገሮችን መመዘን ልላ ጉዳይ ነው ግን ሆን ብለህ ሳታቀርበው ማለፍ ነውር ነው። የዓለምሰገድ ተስፋይ ስንመጣ ደግሞ በእውነት የሱ እማ የባሰ ነው። ስለ ዓለምሰገድ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ።

ጥያቄ -በያን ነጋሽ እባላለሁ፦ በረከት ነው አንተ ነህ “ኢትዮጰያ እና ኤርትራ ከመሞት በፊት  የምመኘው አንድ አገር ሆነው ለማየት ነው ምኞቴ ያልከው? ያ ከሆነ አንተስ ምን አስተያየት አለህ በዚህ?

ተከስተ። እኔ አይደለሁም። ይላል፡ ተከሰተ። (ተከስተ በዙም አልራቀም በዚህ መልስ ላይ- እኔ ላክልለት። በረከት እንደዚያ ብሎ የተናገረው ቪ ኦ ኤ ላይ ቀርቦ በትግርኛ ነው። በረከት ያቺን ካለ በኋላ ኤርትራዊያን መጽሐፉን ሲያስመርቅ ይሁን ብቻ ላይብረሪ መሳይ መጻሕፍት ያለበት ቦታ እሱ ፊት ለፊት ቁጨ ብሎ ኤርትራዊያኖቹ ለምን እንዲህ አልክ ብለው ሲጠይቁት እንዲህ ማለቴ በሌላ ተተርጉሞብኝ ነው እንጂ እንዲያ አላልኩም በሎ ንግግሩን ሽመጥጥ አድረጎ ካደ (በረከት የሚገርም ሰው ነው፤ አውዲዮውም አለኝ )። ይህንን ንግግሩ የፊተኛውም የካደበትም  ሁለቱ አድምጨዋለሁ በትግርኛ)።

የሆኖ ሆኖ ወደ ተከስተ ልመልስህና ፤ ተከስተ ይቀጥልና እንዲህ ይላል አንተ ስላልከው የናሺናሊዝም/ናሺናሊቲ  ጉዳይ፤ አስቀድሞ እንደነገርኩህ እኔ ኤርትራ ውስጥ አውራጃ አከለጉዛይ ወረዳ/ገጠር “ማዕረባ” ተወልጀ ያደግኩ በእናቴ በኩል “ዓፋር” ባባቴ በኩል ደግሞ  ከእነ ራሰ ተሰማ ጋር ዝምድና ያለኝ ግን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ በየሃለሁ። እምነቴ ኤርትራና ኢትዮጵያ ድምበር የለውም፤ አሁን ያለው ድምበር “ሰው ሰራሽ፤ በመሪዎች አፈና  የተሰራ ሰው ሰራሽ ድምበር ሆኖ ትርጉም የለሽ ነው

ጠያቂው ጣልቃ ይገባና «ኢትዮጵያ እንጂ ኤርትራ የሚባል አገር የለም ማለትህ ነው?

ተከስተ አዎ አልኩህ እኮ እ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ኤርትራ የሚባል ነገር ድሮውኑ መኖር የማይገባው ነው። ሕዝቡም ስሜቱም አንተም አታውቀውም፡ ምክንያቱም የሕዝቡ ስሜት በኢሳያስ የታመቀ ነው። በ1918 አዲሰ አበባ ውስጥ ነበርኩ፤ በወቅቱ አብይ አሕመድ እና ኢሳያስ ተስማምተው በነበሩበት ወቅት ሕዝቡ 3 ወር ሙሉ እንደ ጎርፍ ጎርፎ ድምበሩን ጥሶ ሲመጣ ያየነው ትዕይንት አንተም ዓለምም ያየነው ክስተት ነው። ያ አንድ ነገር ያሳይሃል። በኋላ ግን ሁለቱም መሪዎች ተስማመተው እንዝጋው ብለው (መረጃው አለኝ እከታተለው ሰለነበር) ሲዘጉት ሕዝቡ ባለበት ተዘግቶ ዝም አለስለዚህ የታመቀ ስሜት አለ። ለዚህ ነው ድመበሩ ትርጉም የለሽ እንደሚሆን ለወደፊቱ የማምነው።ኢትዮጵያዊያንም በትግሬዎችም ወገን የሚሉት ኤርትራዊያን የኛ ሰዎች ናቸው፤ ወንድሞቻችን ናቸው  ከማለት አልፈው የሚጠይቁት ተከታታይ የማይቆም ቀጣይ ጥያቄ አላቸውያንን ግምት ላይ ማስገባት አለብህ።  

እዚህ ላይ ልጠቅስልህ የምፈልገው ኢሳያስና ዓብይ አህመድ ድምበሩን እንዝጋው ሲሉ ምክንያታቸው ሲገልጹ « ኤርትራ ሕዝቧ ታጣለች ወደ ኤርትርራ በገፍ ሊጎርፉ ነው፤ኢትዮጵያዊያኖች ኤርትራዊያኖችን «አያቅፉዋቸውም» ተብሎ ነው በስምምነት ቁጭ ብለው ተወያይተው የዘጉት። ይህ የተከታተልኩት እና Documented ነው። I have been following it closely. እኔ ሁኔታዉን ተከታትየዋለሁ። በነዚህ አንድ ሕዝቦች ድምበር መኖር አልነበረበትም፤ አንድ መፍትሄ መደረግ አለበት። መፍትሄው ምን ይሁን የሚለው ጥያቄ የሁላችን ጥያቄ እና የቤት ሥራ ነው። ሲል ተከስተ ምልስ ሰጠ።

ተከስተ መስመሩ ግልጽ ቢያድርግላቸውም፤ እንደምታውቀው የኤርትራ ምሑራን ሕሊናቸው የተበላሸ ስለሆነ «ሰላም ያስፈለገናል፣ ወዘተ....»ይሉና ያንን እዚህ ድረስ ያደረሳቸው የስደት የሞት ፤ የወርደት መንገድ እንዲያርሙት ሲነገራቸው ቆም በማለት ያዘነበሉ የምሰሉና (ሰላም ሰላም ይሉና)ያቺ አጉል ኩራት ሊተውዋት ይዳዳቸውና ተመልሰው ወደ እዛቺው አጉል የአገርነት ኩራትይመለሳሉ። የሚገርመው ደግሞ ከኢትዮጵያ ያላቸው ነገር ሳያጨርሱ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ችግር ለመፍታት ይመለከታሉ።ለዚህም አዘጋጁ እንዲህ ይላል።

 አዘጋጁ እንዲህ በመደምደም ፐሮግራሙን ይዘጋዋል

“አዎ እንተም ካንተ ጋር ነኝ። እንኳን ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ምስራቅ አፋሪካ የሚያገናኘን አንድ ነገር መደረግ አለበት። በኢኮኖሚ መተሳሰር ወዘተ---ይህንን እና የመሳሰሉ ናቸው ከችግር ሊያሰወጣን የሚችለው። የልና እንዲህ ሲል ወደ ጭቃ ይገባል፡

“ሆኖም” ናሺናሊዝም የሚባለው ባሁኑ ሰዓት ጠንካራ መንፈስ ውስጥ ሰላለ ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊ እያልኩ ከዚህም ከዚያም መርገጥ የማያስችል ሁኔታ ነው ያለው። አንደኛው አገር ውስጥ እንደትሆን ነው አሁን ያለው የናሺናሊዝም ሁኔታ የሚገፋፋህ። ካንዱ ወዳንዱ የሚያንቀሳቅሰን አይሆንም። 35 አመት  ነፃነት መጥቶ አገሪትዋም በኤርትራዊያን አስተዳደር እጅ ስለሆነች ወዲያ ወዲህ እንድትል አያስችልም።ሆኖም አንተ እንደ የታሪክ ተመራማሪ አንተ «ኢትዮጵያዊነትህ ነው ወይስ ኤርትራዊንትህ ነው የሚያይልብህ?

ተከስተ መልስ- “እየሳቀ” እኔ ይህንን ልመልስልህ አልችልም። ከአስመራም ይሁን ከተወለደኩበት አውራጃ አክለጉዛይ “ማዕረባ” ከወጣሁ 50 አመት ሆኖኛል፤ ተመልሸ አላውቅም። አንድ ነገር የማውቀው ግን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ኤርትራ ለምን ከኢትዮጵያ እንደተለየች ትግል ውስጥ  እንደገባች ተረድቶኝ አያውቅም

ያቺ ቅድም ከላይ የጠቀስኩዋት የምሁር ማሃይም ሴት በማከታተል እንዲህ ትጠይቀዋለች፡

 ለምን? እንዴ! መታገል ነበረባቸው እንጂ? ትላለች፡

ተከስተ በመመለስ ፡ “ምን ሆነው ነው ትግል ውስጥ የገቡት?

ሴትየዋ እንዲህ ትመልሳለች

« ኤርትራዊያን ስለሆኑ!!»

ተከስተ እንደገና ይመልስላታል፤

«መቸ ጊዜ ነው ኤርትራዊያኖች ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑበት ወቅትና ዘመን? አሁን ኤርትራ የምትየው አገር ጣሊያን ሲመጣ ሦስት ቦታዎች (አካባቢዎች በተከስተ አባባል “አገሮች” ቦታዎች ለማለት ነው በትግርኛ ተናጋሪ ተለምዶ አገር ሲባል “ዓዲ” አካባቢ/ቦታ/ትውልድ ቦታ እንደማለት ነው) ዓፋርከበሳ እና መታሕት (ቆላማ የሱዳን አካባቢ የሚዋሰን ኤርትራ እሰላማዊ ዘላን ሕዝብ የሚኖሩበት አካባቢ) እነዚህን አንድ አደርጎ ነው ኤርትራ ብሎ አሁን ያለው ትርምስ ሊያስከተልብን የቻለው የጣሊያን መዘዝ

በማለት ተከስተ ቃለ መጠይቁን ይደመደማል። አዘጋጁም ተከስተን ለሰጠው ቃለ ምልልስ አምስግነውት ተዘጋ።

ማጠቃለያ- እንዳደመጥኩዋቸው ምሁራን በሚል ስም ቢጠሩም ኤርትራኖቹ ጭራሽ በጣም ወደ ኋላ ተሽንክረው የቀሩ እጅግ አሳዛኝ ካልቶች ናቸው። ከዘመኑ እና ከሁኔታው ጋር ጭራሽ የማይለወጡ ስደት ፥ ሐፍረት እና ውርደትን እንደ ባሕል እና እንደ ኩራት  የሚቀበሉ ከፍሎች እንደ ኤርትራኖች ቀጥሎም የወያኔ ተከታይ ትግሬዎች ከቶ ማግኘት አይቻልም።

 ደህና ሁን!

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

 

 


No comments: