ታማኝን
ከሰውነት ወጭ መዝለፍ እና በዘር ማጥፋት መወንጀል ከነውርነት ባሻገር accusation in a mirror ነው!
ጌታቸው ረዳ
(ETHIOPIAN SEMAY) 5/11/2026
ሰሞኑን ታማኝ በየነ በአንዳንድ የሕሊና ቀውስ የሚሰቃዩ (ዩ ቱብ ላይ አዘውትረው የሚታዩ የዐዕምሮ ቀውስ ማስታገሻ መድሃኒት የሚወስዱ) እና አንዳንዱም በተቃዋሚ ወገን ሆነው ልቅ በሆነ ውንጀላ ታማኝን በትግራይ ጀነሳይድ የሚከሱ፤ወንጃዮች አድምጠናል።
ወንጃዮቹ ፍርድ ቤት ሄደው ከስሰው ሲያስቀጡት ግን አላየናቸውም። አንዳንዱ ወንጃዮች የወያኔ ሰዎች ሲሆኑ ፤ አንዳንዱ ደግሞ ምክንያቱ ባልታውቀ ምክንያት የወያነ ተቃዋሚ ሆነው ነገር ገን አጉል ተመጻዳቂዎች የትግራይ ሕዝብ ባለፉት ዘመናት “የፋሺስቶች ተባባሪ እና ደጋፊ ነው” ሲባሉ “አዎ ሲሉ የነበሩ” አሁን ግን አጉል እወደድ ባዮች ታማኝን በትግራይ ጀንሳይድ (ዘር ማጥፋት) ሲከሱት ሰምቻቸው እጅጉን ገርሞኛል።
አካፋን አካፋ ላለማለት ሲሽኮረመሙ አይቻቸው ይህ የኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ የመሞዳሞድ ባሕሪ መቸ እንደሚቆም ባይገባኝም ፤ ታማኝን ከሰውነት ውጭ መዝለፍ እና ጀነሳይደር ብሎ መዝለፍ “ነውር” ሲሆን የባንቱስታው ኦሮሙማ መሪው አብይ አሕመድን ለማወደስ የሄደበት ርቀት ግን እንደ እኔ ስብዕናውን ሳልነካ በርካታ ትቸቶች የጻፈ ተቺ አታገኙም።ታዲያ ታማኝን እስከ ጀነሳይድ ርቀት መወንጀል ለምን አስፈለገ? የናዚ ጀርመኖች እና የጀርመን ሕዝብ በንጽጽርም በፖለቲካም ወያነ እና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው በየ ለብዙ አመታት በማስረጃ ትከራክሬአለሁ። ያንን የሚያፈርስ ተአምራዊ ነገር አላየሁም። ታማኝ ግን በዚህ ከእኔው ትንታኔ ጋር አይስማም ፤ መስመሩ ከወንጃዮቹ ጋር የሚስማማ “የትግራይ ሕዝብ እና ወያኔ አንድ አይደሉም” ይሚል ነው። እንዲያ ቢልም በጸረ ትግሬነትና ጀነሳይደረነት ይወነጅሉታል። ጥያቄየ “ለምን ወነጀሉት?” የሚል ነው።
ከዚያ በፊት “አማራ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” ሲል ሲጨማለቅ የሰማነው ማሃይሙ አዝማሪ ፋሲል ደሞዝ ከታማኝ በየነ ሚስት ጋር ያስነሳው አረሱት የሚለው ዘፈን አላስዘፈን አለቺኝ በሚል “እሰጥ አገባ” ገብቶ በነበረበት ወቅት የአማራ ብሔረተኞቹ ፋሲል ደሞዝን ደግፈው እስዋን ሲከሱ “አማራ ጠሊታ ኦሮሞ ነች” እያሉ ጭራሽ ከኢትዮጵያዊነትዋ አውርደው እነሱ ወደ እሚከተሉት ወደ ጎሰኛነት መደብ ሲያወርድዋት ስመቸ የአማራ አክራሪ ብሔረተኞቹ ባሕሪ ምን ርቀት እንደሄደ አስገርሞኝ ነበር። ዛሬ ደግሞ ጭራሽኑ ታማኝን ጨርሶ ኢትዮጰያን ነፃ ለማውጣት ያድረገውን እጅግ ረዢም ምጥቀት ያድረገው አስገራሚ ጀግንነትና ልበ ሙሉንት ያስገኘው የትግል ፍሬ እና ስብአዊነት (ሌላ ቀርቶ ውነጃዮቹ ለምከሱት ለትግራይ ሕዝብ ሳይቀር ያበረከተው ሰብአዊ ዕርዳታ) እንዳልነበረ ማድቀቅ መነሻቸው የሰዎች ዓላማ እና ባሕሪ ምክንያታቸው የተለያዩ ነገሮች ያዘሉ ሲሆኑ ፤ ሦስት ዓይነት ወንጃዮቹን ታዝብአለሁ። 1ኛዎቹ ወያኔዎች ሲሆኑ 2ኛ የሕሊና ቀውስ የተጥናወጣቸው ዕብዶች ሲሆኑ 3ኛዎቹ ደግሞ ተቃዋሚዎች ናቸው።
በታማኝ ላይ ውንጀላ የሚያቀርቡ ከሳሾች ማለትም “ቀውሶቹን እና የወያኔ ጀሌዎች እና የወያኔ ፋሺስት ኤሊቶች” ውንጀላ የፖለቲካ ስነ ጠበብቶች "accusation in a mirror" የሚሉት ወንጀለኞች ራሳቸው እየሆኑ ሌሎችን በዘር ማጥፋት ወንጀል በመክሰስ ነጻ ነኝ በሚል የወንጀለኞች የተለመደ የስነ-ልቦና እና የፕሮፓጋንዳ ስልታዊ መሸፈኛ የሚጠቀሙ ክፍሎ ናቸው። የነዚህ ክፈሎች ውንጀላ ወደ ጎን እንተውና ፣ እኔን ያስገረሙኝ ግን ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉ ታማኝን በትግሬ ዘር ማጥፋት ሲወነጅሉት መስማት ካስገረሙኝ ወንጃዮች ውስጥ ይህ ቡድን ነው።
ከ16 አምት በፊት “ቆሽቴያቸዉ እያረረ ለሕዝብ ሲሉ በፈገግታ ጥራሰቸዉን የሚያብለጨልጩ ፖለቲከኞች እንፈልግ ፡ለፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ድጋፍ 2/9/2010” በሚል አንድ ትችት ጽፌ እንደነበር አስታውሳለሁ። ያን ለፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ ድጋፍ ነበር። ፕሮፈሰሩ የጻፉበት መነሻ «ቀኑ ሳይመሽ ብርሃኑ ሳይሸሽ» በሚል ርዕስ ነብሳቸው ይማርልን ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ተቃዋሚዎች በሕዝብ ድምጽ ተደግፈዉ የሚቃወሙትን የወያኔ ትግሬዎች መንግሥት ለማሸነፍ ከፈለጉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርጅት በተለይም ደግሞ “በመድረክ” እና “በመኢአድ” ፓለቲከኞች መሃል እርቅ በማዉረድ የጋራ ስምምነት በመቅረጽ የገቡበት የሰላማዊ ትግል ዉጤታማና በሳላ ፖለቲካ እንዲሆን ከፈለጉ ሕብረት ቢፈጥሩ ጥሩ መልካም ጅማሮ እና ሕዝቡም ለትግሉ የጋራ አትኩሮት እንዲኖረዉ ይረዳል፤ በሚል ለጋራ ትብብር ትግል የጠሩትን የአርቆ አሳቢ ጥሪ፤ አንዳንዶቹ ከድንቁርና ወይንም ለፕሮፌሰሩ አልያም ለየደድርጅቶቹ ካላቸዉ ጥላቻ የተነሳ ፣አፍራሽ የሆኑ መልሶች በተለይም በፕሮፌሰሩ ላይ የግል ጥላቻን እና ስብዕናቸውን የሚነካ ስድብ የሚያንጸባርቁ ከኢትዮጵያዊነት ስነምግባር ዉጪ ነውረኛ ቃላት የሰነዘሩ ግለሰቦች ካነበብኩ በኋላ ነበር ያንን ርዕስ የጻፍኩበት መነሻ።እኔ እና ፕሮፌሰሩ በዕድሜም ይሁን በትምሕርት አስተማሪ እና ተማሪ ነን። ሆኖም የጠበቀ ወዳጅነት የነበረን እጅግ የማከብራቸው ምሁር ቢሆኑም አንዳንድ ወቅት የማልስማማባቸው ጽሑፎ (ሓሳቦች) ሲሰነዝሩ እቃዋማቸው ነበር። እንዲያም ቢሆን ስብዕናቸውን የሚጻረር ተቺ ሲመጣ ግን እቃወም ነበር። ምክንያቱም ባንድ ጎራ ያለን ታጋዮች እንጂ በአፓርታይዱ ገዢ መደብ አልነበሩም እና።
ኢሕአፓዎችም እንዲሁ ለታሪክ መምህራችን እጅግ ሲበዛ ጠንካራ ወዳጄ የነበሩት ነብሳቸው ይማርልን ዶ/ር ዓለሜ እሸቴን በማይገባ የስም ማጥፍት እና ስድብ ሲዘልፉዋቸው ከጎናቸው ሆኜ ኢሓፓዎችን እና ኦነጎችን ስጋፈጥ ነበር። እሳቸውም ኢሕአፓዎች “የ ሲ አይ ኤ” ቅጥረኞች ናቸው ፤ ሲሉ ኢሕአፓዎችን ደግፌ “ማስረጃዎትን ያምጡ” እያልኩ ስተቻቸው ነበር።
እኔ ላይም ከትግሬዎችም ከኦነጎችም ከዋሃቢ እስላሞችም ያላባራ ሰብአዊ ማንነቴን የሚጋፉ የስድብ ጋጋታ እና ዛቻ ደርሰውብኛል። ልክ እንደ ታማኝ በየነ እኔም ተስፋ በመቁረጥ ደህና ሁኑ ይቅናችሁ በቃኝ እል እና የሕዝቡን ያላባራ ልቅሶ አላስችል ሲልኝ ተመለሼ 24 ሰዓት ሳይሞላኝ በማግስቱ እዛው ወደ መጋፈጫው መድረከ እመለሳለሁ።ብዙ ምሁራን ሰባዊ ግሰትና ስድብ ሲደርስባቸው የተገለሉ ያላወቅናቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
ለምሳሌ ልድቱ አያሌውን አዲስ አበባ የሂልተን ሆቴል (?) ጥሪውን ሲጠራ ገና ቅንጅት የሚባል ከመታወቁ በፊት በጠዋት ከጅምሩ (በወያኔ ዘመን) ጀምሮ እሰከ ዛሬ ድረስ እንደ እኔ በተከታታይ የተቸው ሰው ያለ አይመስለኝም። ሲተቹት ስብዕናውን የሚጋፈጥ ስድብ ሲሰደቡት ግን ያንን አውግዣለሁ። በቅርቡም አፓርታይዳዊው መሪ አብይ አሕመድ ልደቱ አያሌውን ወደ አገሩ እንዳይገባ ሲከለክለው መጀመሪያ ይተቃወምኩት እና ለልደቱ ድጋፍ የጻፍኩ እኔ ነኝ። ለልደቱ ብቻ ሳይሆን ወያኔውን ብስራት አማረን ወደ አገሩ እንዳይገባ የደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ በሥልጣኑ ተመክቶ ብስራት አማረን ከቦሌ አየር ማረፊያ ሲመልሰው ያንን ተቃውሜአለሁ።
ከጥቂት ወራት በፊት ታማኝ በየነን በአንድ የወያኔ የመለስ ዜናዊ ፖለቲካ አገልጋይ የነበረ እኛን እየተቃወመ ልጋጉን ሲረጭብን የነበረ አንድ የዲሲ ነዋሪ ሰው “ታማኝን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ ክስ መስርቶበት” ታማኝ ሲናገር እንደሰማሁት ከሦስት አመት በላይ የፈጀ የፍርድ ሂደት ሲካሄድ ኖሮ መጨረሻ ላይ ዳኛው ታማኝን በነፃ ማሰናበቱን ሰምቸ ደሰ በሎኝ በጓደኛው በጠበቃ አበበ ገላው በኩል «እንኳን ደስ አለህ በልልኝ ብየ» መልዕክት እንዲያስተላልፍልኝ አበበን ጠይቀው መልስ አልሰጥኝም። አበበን ነገረከው ወይ? ስለው “ይቅርታ ረስቸው ነው እነግረዋለሁ” ብሎኝ ነገሮት ይሁን አይሁን ፤ ከነገረውም ታማኝም ስተቸው እንደነበር ስለሚያውቅ ቅር ተሰኝቶብኝ ይሁን “አላወቅም” አመሰገናለሁ አላለኝም።
ይህ ሁሉ ያድረገኩበት ምክንያት እኔ እና ታማኝ የፖለቲካ አለመጣጣም እንጂ “የወያኔ ፓፒዎች” ታማኝን ሲያጠቁት አይቶ “እሰየው” በሎ እንድላዩ ማለፍ ነውር እና ከኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ውጭ ሰለሆነ ነው። ሰለዚህም ሁላችንም አንዳንድ የፖለቲካ መቃቃር ሊኖሩን ይችላሉ፤ ሆኖም “ጠላት” ያንን ክፍተት አይቶ “እንደ ጅብ ሥጋውን ሲገነጥለው እያዩ ማየት ጨካኝነት ነውና ነገ በኔ ማለትና ልብን ጠጠር አድርጎ “ሩቅ አለመጓዝ” መልመድ አለብን። ስለዚህ «ቆሽቴያቸዉ እያረረ ለሕዝብ ሲሉ በፈገገግታ ጥራሰቸዉን የሚያብለጨልጩ ፖለቲከኞች እንፈልግ» ያልኩብት ምክንያት ስብአዊነታችንን በሚጋፉ ቆሽቴያችንን በሚያሳርሩ ሰዎች መጋፈጥ ከባድ ቢሆንም በጠላት ወገን ሳይሆን በገዛ ተቃዋሚ ወገን ምክንያት ሕዝባችንን ነፃ ሳናደርግ ከትግሉ ላለምራቅ እንሞክር።
በፋኖ ደጋፊዎች ያየሁት እጅግ ያስገረመኝ አንድ ነገር ልንገራችሁ። ኮለኔል ፋንታሁን መሃቤ የተባለ ፋኖ ውስጥ ትልቅ ቦታ የነበረው በውስጣዊ ሽኩቻ ምክንያት ወደ አብይ አሕመድ አገዛዝ ሲገባ ጀግና እና መመኪያ ሲሉት የነበረው ሰውየ ባንድ ጊዝ ዕጥፍ ብለው ኮለኔሉን የሴት ቀሚስ አልብስው ፌስ ቡክ ላይ ፎቶ ሲልቁበት ማየት እጅግ የሚገርም አጸያፊ የፋሺስት ካልቶች ባሕሪ ያየሁበት አጋጣሚ ነው። ሁሉም ፋሺስቶች አንድ ባሕሪ አላቸው፡ ይህም ባንድ ካምፕ ውስጥ የነበረው አባላቸው ጀግና እና አንበሳ ሲሉህ ይቆዩና ባንድ ነገር ሳይስማማ ቡዱኑን ከለቀቀ “ለምን ተወን በሚል” ከ“redemptive” “ከቤዛዊነት” ውደሳ ወደ አይጥነትና ሴትነት ይገልጹሃል። በፋንታሁን ሙሃቤ ላይ የሴትነት ልብስ አልብሰው ፌስ ቡክ ላይ የሚያሰራጩትና የሚለጥፉት ደግሞ በሚገርም ነገር ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ ሴቶች መሆናቸውን ሳይ እጅግ ገርሞኛል።
ከድርጀቱ የወጣ የሴት ልብስ ማልበስ በቀዳማየ ወያነ የተፈጸመ ድርጊት ነበር፡ ኪዚያም በዳግማይ ወያኔ የወያኔው ከፈተኛ አመራር አባል የነበረው ጻድቃን ገብረተንሳኤ አሁን ትግራይ ውስጥ ካለው የወያነ አክራሪው ቡድን ተነጠሎ ከአብይ አሕመድ ጋር ወደ አዲሰ አበባ ስለተጠጋ ጣሊያኖች “ትግሬ አይደለም፣ ወደ ትግራይ እንዲገባ አንፈቅድም አሉኝ» ብሎ እራሱ ተገረሞ ሲናገር ሰምቸዋለሁ (ያው እሱም ከነሱ ጋር ሆኖ ሲለን የነበረው አባባል ነው እሱ ጋር ቀን ቆጥሮ ወደ ራሱ የዞረበት) ። ጣሊያኖችም አድርገውታል። በ1930ዎቹ የጣሊያን ፋሽስት መፈክሮች Believe, Obey, Fight" (Credere, Obbedire, Combattere) “እመን፣ ታዘዝ፤ ተዋጋ” የሚሉ 3 መፈክሮች ሲጠቀሙ ነበር፡ ከዚህ መስመር የወጣ በኮለኔሉም ይሁን በጻቃን ላይ የደርሰ ዕጣ ፈንታ ይደርሰዋል።
ሰዎች በትግል ላይ በቃኝ የሚሉበት የፖለቲካ ተንታኞች «Political burnout» የሚሉት በትግሉ ላይ በተለያዩ ምከንያቶች የመስልቸት ድካም ስሜት ሲሰማህ በቃኝ ትላለህ።ብዙውን ጊዜ ግለሰቦች ከአቅም በላይ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ጥረታቸው ከንቱ እንደሆነ ሲሰማቸው ወይም የማያቋርጥ በራስ ላይ ሲዘመትብህ መጨናነቅን ያስከትል እና በቃኝ ትላለህ። የመንገድ ተጓዥ የመንጠባጠብና የመድክም ተዕይንት ነው።
በትግላችን ላይ ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች አይቻለሁ። ለምሳሌ ቆሽቴን የሚያሳርሩኝ እየለዩ የሚሸልሙ ሸላሚዎች አሉ። በርካታ ሽልማት ሸላሚ ስብስበ ደረጀቶች አሉ። ትግል ስትገባ ለመሸለም አይደልም።ሆኖም ሸላሚ ድርጅቶች ወይንም ቡድኖች በሚያድርግዋቸው አግላይ-እውቅና (ሪኮግኒሽን) የሚያስከትሉት መጥፎ ተጸዕኖ አለ። አብዛኛዎቻችሁ ልብ ያላልችሁት ነገር ልነግራችሁ ነው።
በዚህ ሁሉ 50 ምናምን አመታት ፋሺስቶችን የሚታገሉ ከወያኔ ስብስቦች ጋር ብቅ ጥልቅ ሳይሉ “ሳይነካኩ” በጣት የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች አሉ። ከነሱ ውስጥ አንዱ የቅርብ ወዳጄ የሆነው “ዛሬ በጤና መታወክ ምክንያት” ከትግሉና ከማሕበረስብ ግንኙነት የተገልለው “ገብረመድህን አርአያ” ፡ ታማኝ በየነን የሚሸልሙ እና የመሳሰሉ አሜሪካ ሃገር የሚገኙ የሽልማት ድርጅቶች (ስብስቦች) ገበረመድህንንም ይሁን በትግሉ ውስጥ የታወቁ ብዙ መገለልና ስቃይ የደረሰባቸው ጥቂት የትግራይ አምበሶች በነዚህ ስብሰቦች ሕሊና እና ልብ አይታወቁም። ለምን? ለሚለው ጥያቄ ሳቀርብ መልስ ይለኝም ፤ ምክንያታቸው የሚያውቁት እነሱ ናቸውና።
ይህ ችግር በሽልማት አስጣጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ከሃገር ጀምሮ እሰከ ውጭ አገር ያሉት የዜና ማስረጫ ጣቢያዎች (ሚዲያዎች) በመክፈቻ ፕሮግራማቸው ላይ ትኩረት ለመሳብ በሰዕለ ደምጽ (ቪድዮ እና ፎቶ) የሚያሳይዋቸው መጀመሪያ የፕሮግራማቸው መክፈጫ ገጽ ላይ የሚታዩት አጭር፣ ፈጣን፣ ብልጭ ፤ ብልጭ የሚሉ የታዋቂ ሰዎች እና ተቃዋሚም ይሁን የገዢውም ሰዎች ፎቶዎች በየሚዲያው ሲታዩ ፡ በሚገርም ነገር ከወያኔ ፖለቲካ እና ተያያዥ ቡድኖች ጋር ብቅ ጥልቅ ያላሉ “ያልተነካኩ” “ያልረከሱ” ወያነ እና አሁን ያለው ገዢ በመቃወም ከፈተኛ ትግል ያደረጉ ከትግራይ የተገኙ ተቃዋሚዎች አንድም ሰው በማንኛቸውም ሚዲያዎች በመከፈቻ ፕሮግራማቸው ላይ ምስላቸው አይታዩም። ለምን? መልሱን የሚያውቁት እነሱ ናቸው። ያም ሆኖ ትግላችን ለሕዝባችን እንጂ ለዝና ስላልሆነ በዙዎቹ ከመጣው ጋራ አርጋች አሰርጋጅ ሆነው ወደ ሃገር ብቅ ጥልቅ ሲሉ ጥርሳችንን ነክሰን ፤ ከትግሉ ሳንወጣ ተስፋ ሳንቆርጥ አሁንም በተራራው አናት ላይ ቆመን እየጮህን እንገኛለን።
ለማጠቃለል፤
አማራዎቹ ወደ ትግራይ ሳይገቡ ፋሺስቶቹ ወደ ወሎ ገቡና ምድሪቱን ሁሉ
ሁቱዎች በቱትሲዎች እንዳደረጉት ፈጸሙ።
“አማራን እየለዩ የሚገድሉ ፤ አማራ ለጃገረዶችን እና መነኮሳትን የሚደፍሩ፤ ንብረት የሚዘርፉ፤ ፍየል ላም እና በሬ መድሃኒት እና የሆስፒታል እቃዎችን ፤ የትምሕርት መገልገያዎችን የሚዘርፉ ፤ የማውደም የስራ ምድብ እና ተልዕኮ ተስጥቶአቸው እንደ ሁቲ ሚሊሺያዎችና መደበኛ ሁቲ ; የወያኔ ፋሺቶችም ታጣቂ ሠራዊታቸው እና ሕዝቡን እያስተባበሩ ወደ አማራ ምድር ገብተው የሞትና የመደፈር ጭሆት እየተስተጋባ ፤ ምድሪትዋን በደም እንድትጨቀይ ሲያድረጉ ታማኝም ይሁን ሁላችን ምን ማድረግ ነበረብን? (አበይ እና ካቢንዎቹ ፤ የወያነ አመራር እና ከ50 አመት በላይ የዘለቀ የወያነ አንጋች ፤ጀሌና አንጭብጫቢ የሆነው የትግራይ ሕዝብ እና የትግራይ ምሑራን ከ50 አመት በላይ ለመከራውና ለአገር መፍረስ ተጠያቂ ቢሆኑም) ያ ሁሉ የደም ጎርፍ እና ወረራ ሲፈጸም ወያኔ ወደ ወሎ ሲገሰግስ ዝም መባል ነበረበት? ምንስ መደረግ ነበረበት?
ታማኝን በትግራይ ጀነሳይድ የሚከሱ ተቃዋሚ ነን ባዮች ለክሳቸው ነጥብ እስኪ አንድ ባንድ ያሳዩን እና እንመልከተው። ያልሰማሁት ታማኝ በየነ በትግራይ ላይ «የዘር ጭፍጨፋ” ወንጀል ተግባር ወይንም የዋለበት ንግግር ካለ ፤ ያንን የሚያስረዳኝ ሰው ካለ እዚህ መድረክ ጻፉልኝ እና በደስታ ለመስማት ዝግጁ ነኝ።ካለሆነ ግን አጉል የሚመጻደቁ ሰዎች በታማኝ ላይ ጭራሽ ስበዕናን የሚነካ ውርጅብኝም ሆነ(አንዳንዱም በሕግ የሚያሰጠይቅ ቃላትና ውንጀላ) መሰንዘር በፈጹም አስፈላጊ አይደለም።
ታማኝን መውቀስ ካሰፈለገ ፖለቲካውን እንጂ ጭራሽ ለኢትዮጵያ የሰራውን በጎ ተግባሮችን አስተዋጻኦዎች እንዳልነበሩ አድርጎ ገደል መከትተ ይህ ትውልድ ወድየት እየተጠጋ ነው? ያሰኛል።
ታማኝ በየነ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በተሰጠው የተፈጥሮ ጸጋ መስሕብ ምክንያት መንግሥትን ፤ሥርዓትን ድርጅትን የመገልበጥ፤ የማስለወጥ፤ የማስጠላት እና የማዳከም ሲፈልግም የማጠናከርና የማደራጀት፤ የማስጨፈር፤ የማስለቀስና የማ’ሳቅ አቅም አለው። ይህ ስጦታ በተፈጥሮ እንጂ በትምሕርት አይገኝም። ዘፋኝ ነው፤ ተነጋሪ ነው፤አስተዋዋቂ ነው፤ሙዚቀኛ ነው፤ እምባ አቅራሪ፤አዛኝና ርሕሩሕ ነው፤ተንኮለኛም ነው፤ ስሜት የሚጋልበው ከፍተኛ ሃገራዊ ፍቅር የሚታይበት ዜጋ ነው። ሃገራዊ ፍቅሩ መጠን ስለሌለው፤ በዚህ ሁሉ በጎ ባሕሪው ጥቂት ለሆኑ በራዥ ከላሽ እና አደገኛ ቡድኖችና ግለሰቦች በትግል ስም ሲደግፋቸውና እያቆለጳጰሰ ሲያሞጋግሳቸው ብሎም “የተሸለመውን የአምበሳ” ሽልማት ሲሸልምና ሲያሞካሻቸው የታየበት ጊዜም ጥቂት አይደለም። ለዚህም በራዦችና ጸረ አማራ ሃይላት እውነተኛ አገራዊያን ተመስለው እንዲታዩ ረድቷቸዋል። በዚህ ምክንያት ማን ከማን መለየት በሚደረግ የመነፅር ፍለጋ ጉዳት አድርሷል። ግን ፖለቲካው በቃኝ ካለ፤ ቢሆን ቢመጣ ጥሩ ነው ካለሆነ በቃኝ ካለ መብቱን አክብሩ እና የሱን ትግል ተክታችሁ አሳዩን።
ታማኝን በብዙ ርዕሶች ለብዙ አመታት ወቅሸዋለሁ። ከበዙ ይተቸሁበት ጥችቶች ለናሙና ላሳያችሁ፡
በመለስ ሞት ልባቸሁ ጥቁር ለለበሰ የተቃዋሚ መሪዎች ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን Sunday, September 9, 2012
በ2011 የተዋወቅናቸው ሦስቱ ታዋቂ ባንዳዎች ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
ታማኝ በየነ እባክህን አንበሳውን አምጣ በለው እና የመሪህን ፒኮክ አርማ ሸልመው! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Jul 24, 2014
ትችቴ ለታማኝ በየነ ጌታቸው ረዳ የኢትዮያ ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay SUNDAY, JULY 24, 2016
ወይ ጉድ ! "ኢትዮጵያውያኖች፣ ያገኘነዉን ታላቅ ሰጦታ አንዳናጣ አይናችንን ከፍተን መጠበቅ አለብን!? የበሉን" ተችት ለዓለማየሁ ገ/ማርያም እና ታማኝ በየነ
መላ ዘመኔን ላገለግለዎት ቃል እገባለሁ፡ ታማኝ በየነ ጌታቸው ረዳ Ethio Semay ክፍል 1 4/15/2021
አንዳርጋቸውን ማቆለጳጰስ በማወቅ ወይስ የፖለኢካ ጅልነት ታማኝ በየነ እና የአሻራ ሚዲያ ጥያቄና መልስ፤ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ
ለሚልዮን አማራ ነብስ ሳይለቀስ ለአምባቸው ጽጌ እምባ ተራጩበት፡ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 2014
የታማኝ በየነ ድግምግሞሽ እና ኢትዮጵያ ጠሊታው በረከት መንግሥትአብ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/19/25
የአዲስ አበባው የታማኝ በየነ ንግግር ሲፈተሽ
Nov 20, 2021 Getachew Reda Ethiopian Semay
እነዚህ ሁሉ ታማኝ የተቸሁባቸው የፖለቲካ ጉዳዮች ቢሆኑም ስብዕናውን የሚጋፋም ይሁን በዘር ጭፍጨፋ የሚከሱ ሰዎች ሳደምጥ ታማኝን ከመከላከል ወደ ኋላ አልልም። የአማራ ሕዝብም ይሁን ፥ ታማኝም ይሁን ፥እንደ እኔ የመሰሉ የትግራይ ተወላጅ ታጋዮች ወያኔዎች ወደ ወሎ ገብተው (በአብይ አሕመድ መስሪ ተባባሪነት) የምታዩት እታች የተለጠፈው ቪዲዮ የዘር ማጥፋት ወንጀልና ወረራ ሲፈጽሙ ታማኝ ምን ማድረግ ነበረበት? እኛስ ምን ማደርግ ነበረብን? የትግራይ “ሁቲ መሳይ” ታጣቂዎች የአማራን ንብረት መንኮሳት እና ልጃገረዶች ሲያበላሹና ሲዘርፉ ታማኝ ዝም ብሎ ማየት ነበረበት ነው የምትሉት?
በጥቅምት 24 13 2013 በርካታ ካምፖች የትግራይ እናቶች ሠራዊቱ ሲታፈን ፈንድሻ እየተበተኑ፤ቄጠሜማ እየነሰነሱ
ከበሮ እየመቱ የሠራዊቱን አስከሬን እምቧለሌ እየዞሩ ጨፍረውበታል፡ “ገድላችሁ ደማቸውን አሳዩን” ያሉ የእናት አንጀት የሌላቸው
እናቶች ደግሞ ወጠቱን አነሳስተው ሠራዊቱን አስጨፍጭፈዋል። ይህንን ያደረገ የትግራይ ሕዝብ ወደ ወሎ ሂዱ ብሎ ስንቅ እየሰጠ
ዕልል እያለ የተለጠፈው ቪዲዮ እንዲፈጽም አስደረገ። ይህ ሁሉ ሲፈጸም ታማኝም ይሁን አገር ወዳዶች ምን ማድረግ ነበረባቸው?
ዝም ብለው ጥቃቱ እንዲቀጥል መተባበር ነበረባቸው? ታማኝን ከሰውነት ወጭ መዝለፍ እና በዘር ማጥፋት መወንጀል ከነውርነት
ባሻገር accusation in a mirror ነው!
ወያኔዎች ደሴ ከተማ ገብተው የፈጸሙት ወንጀል የሚያሳይ ቪዲዮ
https://www.facebook.com/getachewsemay
ሂዳችሁ እዩት::
አምሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY

No comments:
Post a Comment