Tuesday, December 2, 2025

የጨለማው ርዝመት የተመቻቸው መንትያ ፋሺስቶቹ አንዱ በጫካ አንዱ በከተማ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 12/2/25

 

የጨለማው ርዝመት የተመቻቸው መንትያ ፋሺስቶቹ አንዱ በጫካ አንዱ በከተማ!

ታቸው ረዳ

 (Ethiopian Semay) 12/2/25

የሚታየው ፎቶ ታፋኙ (የሄሊኮፕተር አብራሪው የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ  ወንድም) “ፋኖ አብርሃም ሰጤ” ነው

ሰላም እንደምን አላችሁ?

(1)      

በመጀመሪያ ወንበር ላይ በተቀመጠው በከተማው ወፈፌው ጀመር፡ 

«የአንድን ወፈፌ ወንበር ለማስጠበቅ የሚከሰከሰውን የሀገር ሀብትና ገንዘብ አስባችሁት ታውቃላችሁ? “ደመወዜ ያንሰኛል” እያለ የሚቀልድብን አቢይ የሚያሠራቸውን በትሪሊዮኖች የሚገመቱ የቤተ መንግሥትና የሪዞርት/መናፈሻ ፕሮጀክቶችን ትተን ለወንበሩ ጥበቃና ለጦርነት የሚያወጣው ብቻውን ለኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን ያለብዙ ማጋነን ለአፍሪካ ሀኪሞችና መምህራን በቂ ደሞዝ ሊሆን የሚችል ነበር፡፡

 

የሀገሪቱ አጠቃላይ የፀጥታና የመከላከያ ሠራዊት ሁሉ ሪፓብሊካን ጋርድ በለው፣ ደኅንነት በለው፣ ፖሊስ በለው፣ ደምብ “አስከባሪ” በለው፣ … ሁሉም ቀን ከሌት የሚኳትነው የሰውዬውን ወንበር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሰሞኑን ለምሣሌ 50 ሺህ ፖሊስ አዲስ አበባ ላይ ተራግፎ እኛኑ መውጫ መግቢያ እያሳጣን ነው፡፡ መከላከያም እንደዚሁ አዲስ አበባን አጨናንቋታል - ሁሉም የአእምሮ ህመሞች የተከማቹበትን የአንድ ዕብድ ወንበር ለመጠበቅ ነው ይሄ ሁሉ ግርግር፡፡» (ይነጋል በላቸው)

ወደ ጫካው ፋሺስት ደግሞ እንመልከት፡

«ፋኖ ትግል እንደጀመረ ታጋዮቹ ከፍተኛ የውጊያ ሞራል ነበራቸው፡፡ በጥቂት ጊዜ ውስጥም የአቢይን ዘረኛ ኦሮሙማ ጥለው ኢትዮጵያን ከወደቀችበት አዘቅት ለማንሣት ከፍተኛ ጉጉትና ወኔውም ነበራቸው፡፡ የዛሬውን አያድርገውና ከሁሉም አቅጣጫ ወደ ትግሉ ሜዳ የጎረፉት ታጋዮች ፍላጎት ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነበር፡፡ አንዳንድ ችግሮች ቢኖሩም በዚያች በፈረደባት የትግርኛ ተረት “ለምጣዲ ሲባል ዐይጧ ትለፍ” ብለው ታጋዮች እየተቻቻሉ ብዙ ጊዜ አለፈ፡፡ እየቆዬ ግን ነገር መበላሻሸት ጀመረና በዚህ አስጠሊታ ሂደት ብዙ ጀግኖችንና ብዙ ሀብት ንብረት በሤራና በተንኮል አጣን፡፡ ራስ ወዳድነት የነፃነት ትግሉን አጠየመው።» (ይነጋል በላቸው)

አራት ኪሎ የተቆጣጠረው ከተማ ሰላለው ናዚው የኦሮሙማው ቡድን በዙ ሰላልንበት እሱን ወደ ጎን እናስቀምጥ እና የአምሐራ ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ጫካ የገቡት የተለያዩ ዱርየዎችና ዘራፊዎች የአምሐራን ሕልውና ሽፋን በማድረግ ወደ ሦስተኛ አመቱ የያዘው የፋኖ ፋሺስቱ ክንፍ እና ሚዲያዎቹን እንመልከት።

«በዓለም ጂኦግራፊያዊ ክልል ውስጥ ራሱን የቻለ፣ ነፃ እና ኩሩ ሕዝብ ሆኖ እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያውያዊ ዜጋ አንዳንድ ችግሮች ቢሮሩትም እንደዛሬው ለክፋት የሚጥል የዘር እና የባህል ወረራ ሳይደረግበት ሕልውናውንና ነፃነቱን ተጠብቆለት ቆይቶ ሳይታሰብ በድንገት በ1966 ነባሩን ሥርዓት ተወግዶ “በቀይ ሽብር ፤ነጭ ሽብር የኮሚዩኒዝም ሥርዓት” ሲተካ ወደ ጥቃት ገበያ ተጎትቶ ገባ።

ከዚያ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ነጻነቱ ተወስዶበታል። ለጥቃት ገበያ ያዘጋጁት ደግሞ ደጋግመን እንደገለጽነው «ወያኔ ኦነግና ሻዕቢያ» ሲሆኑ ያንን የፋሺስቶች ፖለቲካ አፈርሳለሁ ብሎ ፤ በብዙዎቻችን  ግምት ለኢትዮጵያ ሕልውና መከታ ይሆናል ብለን ስንጽፍለት የነበረው “የአማራ ፋኖ”  ኢትዮጵያዊ የትግል ፕሮግራም እና አመራሮችን ሳያዘጋጅ (ለመዘጋጀት የቀረቡትም እነሆ ሰሞኑን ፤ ግድያውና አፈናው የቆየ ቢሆንም) እንደምንሰማው ግልጽ የሆነ ማፈን፤ማሰርና ማሳደድ ጀመረ) በወያነ ጦርነት የማረከውን ጠመንጃ ሳያስበው “ጠመንጃህን ፍታ” ሲባል ድንገት ባንኖ ወደ ጫካ ሲገባ ለ27 አመት ሲጋተው የነበረው አውራጃዊና መንደርተኛዊነት በሽታ ተጋብቶበት  “የነገድ ፖለቲካ” ተረካቢ ሆነ። እነሆም፤ «የንገሥታት ልጆች ነን፤ በእናቶቻችን ማሕጸን እያለን ለመሪነት የታጨን ልዩ አፈጣጠር ያለን አማራዎች ነን ፤ወደ እሚል ፈጹም በቅዠት የሚፎልል ፋሺስታዊ የሆነ “ኢትዮጵያውነትን” የሚያኮሥስ መንደርተኛ በመሆን “ሞቴ ከወያነ እና ከሻዕቢያ በፊት ያድርገው” እያለ ለጸረ ኢትዮጵያ ኃይላት (ፕሮክሲ) ወኪል ነኝ የሚል አዋጅ አውጆ የአገራችን አደጋ ተጨማሪ አካል ሆኖ ተከስቷል።» (ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

(2)    በጫካ ወንበር ላይ መቀመጥ ያማረው መንትያው የጫካ ወፈፌው

ሰሞኑን የተከሰተው ወያኔ እና ሻዕቢያዎች ከመሞታችው በፊት የአማራ ሞት ይቅደም  የሚለው  ብሔርተኛው የፋኖ   ቡድን እና ጸረ  ወያነ በሆነው በኢትዮጵያዊው የፋኖ ቡድን መካከል ተፈጠረ ተብሎ የሰማነው ግልጽ ልዩነት አሁን ግሃድ ሆኗል።

እነኚህ በልዩነት የወጡት በቁጥር ጥቂት የሆኑ (ለጊዜው  ስጋት ምክንያት ራሳቸውን የደበቁና ገሃድ የሆኑ) ግምባር ቀደም የተባሉት ጸረ ወያኔ ኢትዮጵያዊያን ፋኖዎች መካከል ውስጥ ስሙ ገንኖን የወጣው የወታደራዊ ሄሊኮፕተር አበራሪው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ነው።ላሁኑ ከሞት አምልጦ የት እንዳለ ታማኘ የሆነ ተጨባጭ መረጃ እስካሁን አላገኘሁም።

የወያኔ/ሻዕቢያ ቅጥረኛ ሆኖ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤን ለመዋጥ ያነፈነፈው ደም የጠማው «የዘመነ እና የመከታው ማሞ» ቀጣይ  ሰለባ የሆነው የማሰረሻ ሰጤ ወንድም የሆነው «አብርሃም ሰጤ› የተባለ ታናሽ ወንድሙን አፍነውታል።

ዕጣ ፈነታው በቅጡ ያልታወቀው ከነዚህም ውስጥ ዕውቁ ኢትዮጵያዊው ኮሎኔል ፋንታሁን ሞሃቤም እየከበቡት ነው  ተበሎ በስፋት ሲወራ ነበር። ያንን በጊዜ ሂደት የምንሰማው ይሆናል።

የሚገርመው ግን የሄሊክፕተር አብራሪው የካፒን ማስረሻ ሰጤ  ወንድም “ፋኖ አብርሃም ሰጤ” በሚመለከት የEthio Selam (ኢትዮ-ሰላም) አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴድሮስ አስፋው በግሩም ትንተና እንዲህ ያቀርበዋል፡

«ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፤ ወንድም “አብርሃም ሰጤ” የሚባል ወንድም አለው። ማስረሻ ከአፋሕድ ጋር በነበረበት ወቅት ወንድሙ “አብርሃም ሰጤ” አብሮት ለበርካታ አመት ሲንቀሳቀስ የነበረ ነው፤ ታዲያ አሁን በተፈጠረው አለመጣጣም፤ እነ ማስረሻ ሲያመልጡ ይህንን ልጅ እንደ መያዣ ያዙት።

 ይህንን ልጅ በድንገት ያፈነውም አሁን በማስረሻ ምትክ የተሾመው በአፋሕድ ሥር የጎጃም ዕዝ ሐላፊ ተደረጎ የተሾመው “አሻግሬ ባየ” ይባላል። “አሻግሬ ባየ” ይህንን ልጅ አፍኖታል። ማፈን ብቻ ሳይሆን ለነ አስረስ ማረ ሊያስረከቡት ነው ይሚል ሰምቻለሁ።ይህ አፋሕድ ሲባል የነበረ ቡድን አሁን ላይ ከነ አስረሰ ማረ ጋር ታር። ሰለዚህም ለእነ አስረስ ሊያስረከቡት ነው። ምከንያቱም ማስረሻ ሰለ አፋሕድ ሰነድ እንዳለው ይታወቃል፡

 (እዚህ ላይ ቴድሮስ እንዲህ ያለበት አባባል ልክ ነው።

 ምከንያቱም ታስታውሱ እንደሆን የፖለቲካ መሃይሙ “መከታ ማሞ” ባለፈው ወር ወደ ጎንደር ተጉዞ ከወያኔ ሻዕቢያው ቅጥረኛ የ «ጎጎ ቡድን (የጎጃም ጎንደር ፋኖ ) እና ለሻዕቢያ የሚሰልለው  የወሎው  ባሕላዊው ጀነራል ተፈራ ማሞ የሚመራው  የፋኖው ቡድን) የጋራ ቅጥረኝነታቸው ለመስማማት ሄዶ በነበረበት ወቅት፤ «ማስረሻ» ሰለ እነዚህ አፍቃሬ ወያኔዎች ተጠይቆ ምስጢራቸው በማስረጃ እጁ ላይ እንዳለ እና በቅርብ ጊዜ እንደሚያጋልው መናገሩ ታስታውሳላችሁ።

 ጋዜጠኛ ቴድሮሰ አስፋው ማሰረሻ “እጁ ላይ መረጃዎች ሰላሉት” ነው እያለ ያለው ያንኑ ነው)።

 ወንድሙን እንደ መያዣ  የያዙት ለሁለት ጉዳይ ነው “ማስረሻ አለኝ ሰለሚለው ማስረጃ” እና “ማስረሻ ወደ መንግሥት እጅ ቢሰጥ መያዣ አድርገው የያዙት ወንድሙን ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ ቤተሰቦቻቸው በጣም ተጨንቀዋል። ይሙት ይኑር ጭንቅ ውስጥ ስለነበሩ ፤ ድንገት ወደ ቤተሰቦቹ ደውለው 300,000 ብር አሁኑኑ ከላካችሁ እንለቀዋለን በማለት የማስለቀቂያ ብር ጠየቁ።

የታፈነው የማስረሻ ወንድም ቤተሰቦቹ አሁን ላይ ለነ አስረስ ተላልፎ ተሰጥቶ ይሁን፤ ምን ሆኖ ይሁን የሚታወቅ የለም። በወንድሙ ምትክ ወንድሙን አፍነው የዘውታል፤ ይኑር አይኑር የታውቀ ነገረ የለም።» ሲል ቴድሮስ አስፋው በግሩም አቀራረብ የጫካ ፋኖ ፋሺስቱ አፋኝ ከንፍ ምንነት አስደምጦናል።

እንግዲህ በካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ምትክ ሰሞኑን  ወደ ዘመነ ካሴ ጫማ ሥር የወደቀው በአፋሕድ የጎጃም ዕዝ ሐላፊ ተደረጎ ማሃይሙ መከታው ማሞ የሾመው “አሻግሬ ባየ” ሥራውን የጀመረው አብሯቸው ሲታገል ከነበረው ይህ በፎቶው ላይ የምታዩት የማስረሻ ሰጤ ታናሽ ወንድም በማፈን እና በማሸበር ነው።

ክ የሚግረን የዛሬ ገፊዎች የነገ ተገፊዎች፤ የዛ አፋኞችና ገዳዮች የነገ ታፋኞች እና ተገዳዮች፤ ይሆናሉ። በማንኛቸውም የፋሺስት ድርጀቶች ያየነው ይህ ባሕሪ ነው። በወያኔ አይተናል በሻዕቢያ አይተናል። ዛሬ ደግሞ በፋኖ ፋሺስቶች የታየ እና ቀጣይ ባሕሪ ያ ነው። በ7  እና በ2 አመት የጨለማ ክብደት የተመቻቸው መንትያ ፋሺስቶቹ አንዱ በጫካ  አንዱ በከተማ  የየራሳቸው ዙፋን ገንብተው ጓዶቻቸው እና ተራ ዜጋ እያገቱ ማፈን ፤ ማሳደድ፤ ማሰር ማስጨነቅና እና መረሸን ከዚህ ወዲያ የሚቀጥል አሳዛኝ እና ዘግናኝ ትዕይንት ይሆናል።

ሰላም እንሰንብት

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay

 

 

No comments: