Tuesday, December 16, 2025

ክፍል 2 የፋኖዎች ወንጀል አልፏል እርሱት የሚለን ፍርደገመድሉ ዳኛ ሃብታሙ አያሌው ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/16/25

 

ክፍል 2

ፋኖዎች ወንጀል ፏል እሱት የሚለን ፍርደመድሉ ዳኛ ሃብታሙ አያሌው

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 12/16/25


በዚህ አስገራሚ ውሸት ልጀምር፡

«እስክንድር ነጋ አዲስ አበባ ገባ ፥ ከሥራዓቱ ጋር ሲደራደር ነበር.. »  የሚል የውሸት ዜና አድምጣችሁ ይሆናል። እንዲሀ የሚሉት ረዳት ፕሮፈስር ትንግሩ እና አሳየ ደርቤ የሚባሉ የዘመነ እና የምሬ ወዳጆ የፋኖ ‘የሚዲያ ስርጭት’ ደጋፊዎች ናቸው። ትንግርቱ ገብረፃዲቅ ማለት ድሮ ሃገር ውስጥ እያለ ካልተሳሳትኩ ጣቢያው “የአማራ ኮርፐረሺን ቴሌቭዥን” ይመስለኛል መደበኛ ሃያሲ የነበረ ነው። ረዳት ፕሮፌሰር ትንግርቱ ገብረፃዲቅ “ትግራይ” የሚለው ስምወንጀል ስምን የሚያመለክት ሰለሆነ በሕግ መሰረዝ እንዳለበት የጠየቆመ ሰው ነው። (among other things, he suggested the criminalization of even the name Tigray):: አንዳንድ ሰዎች ውሸትን ሲደፍሩ ልቅ ናቸው።

የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ውሸታሞች ለምን እንደሚዋሹ ሲናገሩ ፤ ያልተመረመረ የበታችነት ወይንም ድብቅ ውሰጣዊ የሕሊና ጭንቅ የፈጠረው ውጥረት ለማስወገድ ነው ይላሉ። ውሸት ልምድ ሆኖ ከዚያም የእምሮ ብስለት አሰናክሎ መርዝ ሆኖ mentally toxicant and can escalate over time በመምጣት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሊሄድ የሚችል አመንጪ አደጋ  አለው ይላሉ። 

ታዲያ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ያለ እጅግ ዓይን አውጣ ውሸት ለመዋሸት ምን አስገደዳቸው? ስንል ከላይ ያየነው ወይንም ሲያድጉ ይዘውት የመጡበት ባሕሪ ሊሆን ይችላል።

እንደ እኔ እንደ እኔ እስክንድር ከሚገባው በላይ በመይገባ ጥላሸት ቀብተውታል፥ የግድያ ምኞት እንዲገደል ዝተውበታል። ስለዚህ ይህ ሕዝብ የሚከላከልለትን ሰው የማያክብር በመሆኑ ይህ የተጨማለቀ ትግል ጥሎ ወደ ውድ ባለቤቱ እና ልጁ ገብቶ ትግሉን ጥሎላቸው ይምጣ እላለሁ።

 እዚህ ውጭ አገር ሆነው ጥላሸት የሚቀቡትን እሱን ለመተካት ሐሞትና ብቃት ካላቸው ይሄው ሰሞኑን የEritreaው የሻዕቢያ መንግሥት «ለአማራ ያልሆነ ቀሚስ በጣጠስ» በማለት፤   ለነ ትንግርቱ፤ ለነ ይልቃል፤ ለነ ተስፋየ ወ/ሥላሴ ፥ ለነ መአዛ መሐመድ እና ለነ አቻምየለህ ታምሩ ፥ ለነ አብርሃም አንሙት... ወዘተ...ወዘተ  አሜሪካ ውስጥ የጥገኘት ችግር ከገጠማቸው  የEritreaው የሻዕቢያ መንግሥት እንደሚቀበላቸው ፈቃደኛነቱን ስለገለጸ፣ እነሆ ጨቄን ማቄን  ቀሚሴን  ነጠላየን ሳትሉ ይህንን ዕድል ተጠቅማችሁ «እስክንድር ላይ» የምታወርዱትን መመጻድቂያ ምላሳችሁ በተግባር ለማሳየት ይህንን የመሸጋገሪያ ዕድል ተጠቅማችሁ በአሥመራ አድርጋቸሁ ወደ ጎጃም ሰተት በላችሁ ጠመንጃ ታጥቃችሁ እስክንድርን ማድረግ ነበረበት የምትሉትን ጉራችሁን በተግባር እንድታሳዩን እነሆ ይህ የማጣሪያ ፈተና አጋጣሚ መጥቶላችኋልና! ተሎ የሞቀን አልጋችሁን ጥላችሁ እንድትመጡ «አሥመሪኖ» ትጠራችለችና « የጉራ መልቀቂያችሁ የሆነውን « የ ዩ ቱብ ማይካችሁን/ድምጽ ማጉያችሁን/ ለስንኩላን እና ለሽማግሌዎች ትታችሁ ሂዱና፡በግባር አሳዩን።

ያለ ምሕረት የምትወርፉትን እስክንድር እዚህ ይምጣ እናንተ ደግሞ ወደ ትግል ሜዳ በመዝለቅ መሸጋገሪያ ዕድል ተከፍቶላችኋልና ተሎ ሂዱ።  ሃሎ! !አሥመራ! ሃሎ! ሃሎ! ሃሎ! አሥመራ ይል!?

አንባቢዎች ይህ ከ12 ሺሕ ኪ/ሜ ርቀት ሆነው እስክንድርን የሚወፉ የምላስ  አርበኞች ፤ የፈተና ማጣሪያቸውን መገኘቱን አገረማችሁም? በጣም የሚገርም የማጣሪያ ፈተና ድንገት  መከሰቱ የሚገርም ነው።

አሁን ወደ ዋናው ርዕሳችን ወደ ሃብታሙ አያሌው ላምራ

ሃብታሙ አያሌው የማደንቀው ብሩህ የፖለቲካ ተንታኝ እና ለሃገራችን ሊለካ የማይቻል እጅግ ከባድ መስዋዕስት የከፈለ ጀግና ኢትዮጵያዊ መሆኑን ደጋገግሜ የመሰከርኩለትና ያሞገስኩት የቁርጥ ቀን አርበኛ ነው። ያንን ብርቱ በሳል ተሟጋች አንደበቱ ማሳነስ ከቶ አይቻልም።

 እንዲያም ሆኖ  አንዳንድ ወቅት በ MYTHYCAL ቅዠት ውስጥ ይዋኛል። በስሑት ከሚዋኛችው አንዱ በDecember 1/2025 ሕዳር 22/2018 <<የአገዛዙን ቅጥረኞች አደገኛ ሴራ የሚያጋልጥ ማስረጃ፥ የነ ማስረሻ ሰጤ መንገድ እና መሬት ላይ ያለው እውነታ ! December 1/2025>> በሚል ባቀርበው ፕሮግራም ላይ

 እንዲህ ይላል፡፟

  « አርበኛ ዘመነንም፤ አርበኛ መክታውንም፤ አርበኛ ደረጀንም፤ ያላቦኩት ነገር ንገሩኝ፡የሚያመሰግኑት አካል እኮ የለም።  የአፋብሃ ካንድ አመት ወይንም በሰባት ስምንት ወር ወደ ኋላ እየጠቀሱ፤ ያ እንዲህ ብሎ  ነበር ፤ እንትና  እንዲህ ብሎ ነበር፡ እያሉ ያ አለፈ ! በቃ አከተመ! እነሱ እየተነጋገሩ ነው።  ዘመነ እና እንትና እንዲህ ተባብለው፤ ተካክደው...የሞኝ ዘፈን “ሁልጊዜ አበባዬ ሆይ፡ እነሱ አለፉት አልኩህ እኮ፡  ሙሾ አታውርድ! ያንተ ሙሾ የሚፈልገው የለም (የሚሰማው የለም) ጥግህን ያዝ እዛው! አከተመ! በቃ! የአማራ ትግል ጭቃ እቀባለሁ የምትል የምትራወጥ ተጋልጠሃል፤ ከዚህ በኋላ አትሞክር።» የላል ሃብታሙ አያሌው።

ሃብታሙ «ጥግህን ያዝ! ከዚህ በኋላ አትሞክር፤ ሙሾ አታውርድ፤ ሙሾህን የሚሰማህ የለም! አለፈ እኮ በቃ! እነሱ አለፉት አልኩህ እኮ» እያለን ያለው ፍርደ ገመድሉ ጋዜጠኛ ሃበታሙ፤ ምከንያቱስ መንድነው “ዝም በሉ ጥጋችሁን ያዙ› ወደ እሚል ድምዳሜ ሊገባ ፈለገ?

ከዚህ ዘልቀን መሰረታዊ መነሾዎቻችን መመርምር ያስፈልጋል። የሚጎመዝዙ ዋሾ መሪዎችና ነብሰ ገዳዮችና ወረበላ ታጣቂና መሪዎች በፋኖ ድርጅቶች ውስጥ በገፍ ተፈልፍለዋል። ውለን አድረን ሠለጠንን ባልንበት ዘመን ወደ አራዊት ባሕሪ ተለውጠን አምሐራን አምሐራን በመግደል የተጀመረው ወንጀል ተሻግሮ ሬሳ እንዳይቀበርም እየተደረገ መሆኑንም እየሰማን ነው። አሁን ደግሞ አምሐራን አምሐራን መገዳደል መጀመራቸውና “እንዳይኖሩ ሁሉንም እንጨርሳቸዋለን” እያሉ ያለ ምንም ሰቀቀን በሚዲያ ለሕዝብ ወጥተው “የጭፍጨፋ ወንጀል” እንደሚፈጽሙ በኩራት በመደንፋት ስብእናቸውን አሽቀንጥረው የጣሉ ወያኔ እና ኦነግን የሚመስሉ “የጫካ ነብሰገዳይ ወረበላዎች” አፍጠው መጥተዋል።

 አምሐራዎች ኢትዮጰያዊ የአምሐራ ባሕሪያቸውን ጥለው ወደ አረመኔያዊ ባሕሪ ገብተዋል።

ፋኖዎቹ ሊነጋገሩ ይችላሉ፤ሊሰዳደቡም ሲያሻቸውም ሊታረቁ ሊተቃቀፉ አብረው ማዕድ ሊጎራረሱ ይችላሉ። ሊነጋገሩ፤ ሊታረቁና ሊተቃቀፉ ያልቻሉት ግን  እኛ እየጮህንላቸው ሰላሉት እነሱ የገድለዋቸው፤ ያፈንዋቸው፤ የገርፉዋቸው ፤ በእምብርክክ ያስኬድዋቸው አረጋውያን እናቶች ቄሶች፤ ወጣቶች ፤ ፋኖዎች ሰለ ዘረፉዋቸው ፤ በምንም ፖሊታካ ውስጥ የሌሉት የተቃዋሚዎቻቸው ቤተሰብ “ከማሕበርሰቡ ቡና እንዳይጠራሩ፤ ቀባሪ እንዳያገኙ ፤ ሰርጋቸውና ሐዘናቸው ላይ ማንም ሰው እንዳይገኝ በማወጅ ፤ ገበያ እንዳይገበያዩ ሸቀጥ እንዳይሸጡና እንዳይገዙ እንዲታገዱና ፈጽሞ ክማሕበራዊ መስተጋብር እንዲነጠሉ በአዋጅ ደለ ያሳወጁላቸው፤ ሰለ ሽብር የለቀቁባቸው ንጹሃንን ፤ በጫካ በትረ ሥልጣን ያለ ምንም ወንጀል የተረሸኑና ደብዛቸው የጠፉ ሰዎች ፣ ልሳን ሰናስደምጥ ሃበታሙ በተቃራኒ «ይህ ለሳን እንዳይደመጥ ፋኖዎች አንድነት ለመፍጠር እየጣሩ ስለሆኑ ‹ዝም በሉ ጥጋችሁን ያዙ» እየተባን ያለነው በሃብታሙ አያሌው ነው።

እሰቲ እነዚህ ሁለት የፋኖ ጭካኔ  አዋጆችን እንመልከት

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል አዋጅ

1ኛ- በአሁኑ  ሰዓት ሠርግ ለማሠረግ ያሰባችሁ ፤ ተስካር ለማውጣት ያቀዳችሁ፤ ክርስትና ለመደገስ የተዘጋጃችሁ ይህ የሕሊና ተጋድሎ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እንድታራዝሙት ።

2ኛ- <<ለሥርዓቱ ያደሩ አማራ የሆኑ የሚሊሺያ የአድማ ብተና ቤተሰቦችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዕድር ፤ከሰንበቴ ማሕበርና ከሌለቹ ማሕበራዊና ግብረገባዊ (“መስተጋብራዊ” ማለት ይመስለኛል“ ግብረገባዊ ሲል) ሥርዓቶች ባስቸኳይ እንዲገለሉ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።>>  ይላል።

3ኛ- << የሚሊሽያና አድማ በታኝ እንዲሁም የመሳሰሉት እርምጃ ተወስዶባቸው ሞተው ሲገኙ ፍትሃት እና ልቅሶ እንዳይደረግላቸው” ጥሪ ያስተላልፋል።>> ሕዳር 6/2016 የአማራ ሕዝባዊ ሃይል ፋኖ።>>

 

የጎንደር “ፋኖ” በጋሻው ክፍለ ጦር ቃኘው ብርጌድ የተባለ “ጂሃዳዊ ፋኖ” ያስተላለፈውን አዋጅንም እመልከት፤

ይህ ወረበላ ቡድን እራሱን ወደ “የሃይማኖታዊ  ታጣቂ/ መሊታንትነት” በማሸጋገር “ታሊባናዊ መሰል ሽብር፡ በሕዝብ ላይ እያራመደ  አረቄና ሲጋራ ፀረ ሃይማኖታችን ሰለሆነ ጎንደር ውስጥ አረቄና ሲጋራ መጠቀምም ሆነ መሸጥ የተከለከለ ነው፡ በማለት፤

በዚህ ምክንያት

 አረቄና ሲጋራ የመሳሰሉ በመሸጥ የምትተዳደር በሚጥል በሽታ የምትሰቃይ ምስኪን ድሃ የዕለት እንጀራዋን የምታገኝበትን ሥራ ዘግታ  በረንዳ አዳሪ ሆና በልመና መተዳደር እንዳለባት፤ አግተው ሲያሰቃይዋት ከሰነበቱ በኋላይህች ምስኪን በማስፈራራት መተዳደርያዋን እንድትዘጋ ፤ ካለሆነ በደጋሚ እንደገና መጥተው እንደሚጠልፏት አስፈራርተው ቃል አስገብተዋት “በዋስ” ተለቃለች

(2) በወቅቱ በተዘረጋው ቪዲዮ የታጠቁ መሩቃን ታጋ በግድ ጾም እንዲጾሙና ክርስትያን ያልሆኑትም በፋኖ ውስጥ በሚገኙ ለዚህ ተግባር በተሰማሩ በፋኖ ባሕታዊ/መኖክሴ አማካይ እስላሞችም ፤ አይሁዶችም ይሁኑ ከርስትያኖች ካሉ “ሰለቆሸሹ” ጸበል ተረጭቶባቸው ንስሃ ገብተው ተጠምቀው ወደ የጎንደር “ፋኖ” በጋሻው ክፍለ ጦር ቃኘው ብር ወደ እሚከተለውና የክርስትና ሃይማኖት ዕምነትና መመሪያ እንዲገቡ መመርያ እየሰጠ ሲያስፈራራቸውና ሲያስገድዳቸው ታደምጣላችሁ።

ካሁን በፊት ጎጃም ውስጥ በዘመነ ካሴ የሚመራ አረጋውያን እናቶና ቀሳውስት እንዲሁም  መምሕራንና ተማሪዎችን በማፈን፤ በመረሸን ፤የትምህርት ተቋማት እንዲዘጉ ማድረጉ ቦኮ-ሐራማዊ እርምጃ እንደሆነ ወቃል። ያ እንዳይበቃ ካለ የዘመነ ካሴ ታጣቂ ጎጃም ውስጥ ሌላ ፋኖ እንዳይንቀሳቀስ እስክንደር ነጋን መሪ እንዲሆን  መርጠህ ከነሱ ጋር ወግነሃል በማለት ዘመነ ፤ አሰረስ እና ዘነበ  የተባሉ ደም የጠማቸው ነብሰገዳዮች የኮሎኔሉን ድርጅት አዋክበው የገደሉትን ገድለው ኮሎኔሉንም በመንግሥት ወታደሮች ተከቦ እንዲያዝ አድርገው ፤ የተቀሩት የኮሎኔሉ ታጣቂዎች  ወደ ዘመነ እሽክርና እንዲገቡ «መሪያችን” ዘመን ነው» በሉ እያሉ እያሰገደዱ እያስማሉ እንዳስግበዋቸው በወቅቱ ቪዲዮውን ለጥፌ አሳይቻቸኋለሁ።

ጎንደርና የጎጃም ፋኖ ታጣቂ ቡድን  “አደገኛ ወረበላና አክራሪ” ነው ስል የነበረውና አሁንም እየከሰስናቸው ያሉት ያለምክንያት አይደለ። ይህ ድት እንዳይነሳ «ጥግህን ያዝ፤ ዝም በል» ማለት ለምን? ዝምታው እሰከመቸ ነው? ገደቡስ መቸ እንደሚያቆም ተነግሮናል? መቸ ነው ሰለ ገመናቸው መነገር የሚፈቀደው?

አንድነት እንፈጥራለን እያሉ ያሉት እነማን ናው?

ከፍተኛ አመራር በሚባሉ እና መካከለኛ አመራርም እታችም ያሉ ሉጓማቸው የበጠሱ ታጣቂዎች ገና እግር ሳይቸክሉ አስኳይ የዕርማት መንገድ እንዴት እንደሚወሰድ ባላውቅም ፤ እርማት ካለተደረገበት መግደል ብቻ ሳይሆን «ዘመነ ካሴ የተናዘዘውን ባሕሪውን ስንመለከት «ጥይት አርከፍክፍበትና ጥይት ካለቀብኝም መላው ስወነቱን በእሳት አቃጥለዋለሁ» የሚል መሪ ነኝ ከሚል የሽምቅ ተዋጊ ዲስፐሊ የጎደለው አመራር እንዲህ ያ አነጋገር ሲገር ከሥሩ ያሉት ታጣቂዎች ምን ዓይነት የጭካኔ ባሕሪ እንደሚተገብሩ መገመት አያዳግትም።

  እንዲሀ ያለ ንግግር የሚሰነዝሩ «አንዳንድ» የፋኖ መሪዎች ማሕደራቸው ንን ያስነበናል? ማሕደራቸው የሚያሳየው ልከ እንደ የትግሬ ወያኔዎች  ፍትሕ የናቁ፤ አጉራ-ዘለሎች እንጂ የትሕ ሰዎች  አይደሉም።  በአንድነት ሥም «የፍትሕ ያለህ» እያሉ የሚጮሁትን የተበዳዮች ድምጽ እንዳይሰማ ማድረግ «ወያኔዎች ክጫካ የመሩትን የመት ጥሰት ያኔ ከጅምሩ ያለ አግባብ ሰለ ተዘረፉ ፤ ሰለ ተበደሉ፤ ሰለተረሸኑ ሰዎች «ደጋፊዎቻቸው» ቢጮሁላችው ኖሮ፤ ወንጀል ፈጻሚዎቹ መግደልን እና በሥልጣን ባልገው ሙጡኝ ብሎ ለ27 አመት አይቆዩም ነበር። አለመታደለል ሆኖ መላው የትግራይ ምሁር ወንጀል ሲፈጸም ልክ እንደ የጀርመን የናዚ ደጋፊዎች ግድየለሽ አንጭብጫቢዎች ነበሩና መሪዎቻቸው የፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂነት ሰላለበረበት ያንን መፈጸም ቀጥሉበት።

አሁን ፋኖም ውስጥ እያየሁት ያለው ያንን የትግሬዎች ምሁራን ያሳዩት ባሕሪ በአማራ ፋኖ መሪዎች እና ደጋፊዎችም እየተደገመ ነው።

በአብድነት ሥምም ይሁን አንድ መሪ ድል ስላአስገኘ የጦርነት ድል የገመና መሸፈኛ መሆን የለበትም

በቅርቡ ወሎ ድር በተደረገው ፋኖ እና የመንግሥት ሠራዊቶች «ወላጆቻችን ተማርከዋል እኛም ተደግመናል» የተባለለት በድል ስካር ሰክረው በተማራኪዎች ላይ ያስፈከሩዋቸው የወያኔዎች “መፈክር” ታታውሳላችሁ? ‘’አዲስ አበባ ልንገባ ነው’’ ብለው አየሩን ሲያውዱት ነበር። ያ ስነ ምግባር የጣሰ «ዘረኛ መፈከር» በደጋፊዎቻቸው ዓይን «ድል በመገኘቱ ምንም አልቆጠሩትም ነበር።

የፋኖ መሪዎች ትድል ሲያስገኙ ያንን ድል ገመና ላላቸው የፋኖ መሪዎች መሸፈኛ ሆኖ ደጋፊዎቻቸው በደሰታ ስካር እያስፈነደቀ ጩቤ ሲያስረጣቸው አይተናል። ድል የገመና መሸፈኛ መሆን የለበትም

Glory is like a circle on the water

Which never ceases to enlarge itself.

Till by broad spreading it disperse to naught. (p.386 Cultural Amnesia) ከሚል መጽሐፍ ያነበብኩት፡

ትርጉም፤ (በግርድፉ ስተረጉመው) እንዲህ ማለት ነው፦

«ክብርና ድል ልክ በኩሬ ውሃ ላይ ትንሽየዋን ክብ ሰርቶ እንደ እሚዘረጋ የውሃ ንዝረት ማለት ነው። ትንሽየዋ ክብ እየተለጠጠች መዘርጋትዋን ትቀጥልና ፤ መላው የውሃውን የቆዳ ስፋት ልትሸፍን ስትንጠራራ በጥልቁ ሃይቅ ተሰንጋ (ተውጣ) መጨረሻ ላይ ራሷን በማጥፋት ወደ ባዶነት ትለወጣለች።» እንደማለት ነው።

 ልጆች ሆናችሁ “ጸጥ” ያለውን በአንድ የውሃ ኩ/ሐይቅ/ትንሽየ የድንጋይ ኮረት ስትወረውሩ ምን ትዝ ይላችኋል? “ትንሽ የንዝረት ክብ ሰርታ ሰፊውን ኩሬ ደስ በሚል እሽክርክሪት ተዘርገታ መጨረሻ ኩሬው ስፋት አለውና ሁሉንም ላዳርስ ስትል ዳርቻውን ስታዳርስ ከእይታችሁ ትጠፋለች።  ይህ የሚነግረን “ድል አገኘሁ ብለህ በስልት ሳትይዘው መላውን ምድር በትዕቢት ታናውጥና መጨረሻ ተለጥጠህ የፎከርከበትን ድል ይከስማል ማለት ነው።  

ጫካ ውስጥ ያሉት ገመና ሰርተው ማን ይይዘናል የሚሉት ፋኖዎችም ሆኑ አዲስ አበባ ውስጥ ተቀምጦ  የመንግሥ ሥልጣን ተጠቅሞ ማን ይይዘናል የሚሉ «ዘመናይ ሽፈቶች» በሚሰጡን የመሸፈኛ አስካሪ ትዕይንት ገመናቸውን እንዲቀጥሉበት ድጋፍ መስጠትና ዝምታን ከመረጥን ባሕል ሆኖ ይቀጥላል። እየሆነ ያለውም ይህ ነው፡

ፋኖዎች አንድ እየሆኑ ሰለመጡ ያንን እንዳይናቀፍ ዝም በሉ፤ ማለት ቂልነት ነው።

ምክር

አፓርታይዱን ሥርዓት ከአማራ ምድር (ክልል) ለስወጣት የዓላማ ብ ካላጣላቸው ሁሉንም አንድ መሆን ቢጥበቃቸውም ፤ በባሕሪ አለመጣጣም ካልተስማሙ ደግሞ አንዱ አንዱን ሳይዘልፍና ሳይገድል ሕዝቡን አስተባብረው በየቅጣጫቸው ጠላትን አዋክበው ከአካባቢው ማስወጣት ይችላሉ። አሁን ባሉበት የጠላትነት መተያየት ለማስቆም የግድ አንድ መሆን አይጠበቅባቸውም። ምክንያቱም የባሕሪ አለመጣጣም፤ የዓላማ አለመግባባት የጥላቻና ቂም ቆጠራ አንዱ ባንዱ የግድያ ታሪክ አለባቸው። በስም አንድ መሆን ጫና አንድ ቢሆኑም ችግር ይከተላል።

 ለዚህ መፍሔው በያሉብት ረግተው አንዱ አንዱን ሳይተናኮል፤«ማአከላዊ ጠላትን የማዋከብ ስምምነት» መፈራረምና መስማማት ከጀመሩ ፤ ይህ የመሰማማት ሂደት ቀስ እያለ እየተለሳለሱ ገመናቸውን ተማመነው ለተጠያቂነት ዝግጅነታቸውን አሳውቀው፤ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቀው ፤ አንድ ወደ መሆን ያመጣቸዋል። እኔ የአንደኛው ፋኖ መሪ ብሆን በዚህ አጀንዳ ነበር እንስማማ ብየ የምጠይቀው። ይህንን ለስምነት እጩ ሂደት ነው። ይህ ሂደት «የነጋሲ እና የአንጋሽ ልጆች ነን፤ ገና ሳንወለድ ለኛ የተሰጠ በትረመንግሥታችንን እናስጠብቃለን የሚሉትን “የፋሺስት ከንፎች” ባሉብት እንዲቀጥሉና አካባቢያችውን እያስተዳደሩት እንዳሉት ቢቀጥሉ ማንነታቸው ነጥሮ እንዲታይ ይረዳል። ያ ካልሆነ የወንጀል ተዋናዮችና ቀና አሳቢ የሆኑ የፋኖ መሪ እና ተዋጊዎች ጋር በስመ አንድን ከተወሃሃዱ ዘይትና ውሃ ሆነው መጨረሻ ወንጀለኞቹ (የሥልጣን ሱሰኞቹ) ደጋጎቹን መሪዎች እየዋጡ ከጊዜ  በኋላ ከማጥፋት አይቆጠቡም።

 ያ ካለሆነም ፤ ደጋጎቹ በሥልጣን ሱሰኞቹ እየተዋከቡ ፤አለመጣጣም ይመጣና ፤ ላለመገደል ሲሉ «በቅርቡ እንዳየነው ሸሽተው እጃቸውን ለጠላ ይሰጣሉ፤ ወይንም ወደ ውጭ የሚያመልጡበት መንገድ ካገኙ ትግሉን ጥለው የሰደዳሉ»። 

አሁን ሃብታሙ አያሌው  በዚህ ሁለት አመት ውስጥ ፋኖዎች እርስ በርስ የተረሻሸኑትን እና የተወነጃጀሉትን ፥ ንጹሃን ሰዎች እያንበረከኩ ቀጥተው የረሸንዋቸውን የወንጀል ድረጊት ታንሱ ፡ «የሚመስል አባባል» ከግቢያ ላይ የጠቀስኩትን የሃብታሙ አያሌው አባባል፤ «የተሰራው ወንጀል አታሱ የሚል ቃ በቃል እንኳ ባይጠቀምም»  የዘመነ ካሴም ይሁን የተለያዩ የፋኖ ቡድኖች የፈጸሙዋቸው ወንጀሎች እና ሲካሰሱባቸው የነበሩትን (እውነታ ቢኖራቸው) «ስለ አንድነት ሲባል» እርሱት የሚለው ስለ አንድነት ሲባል የፍትሕ ምላስ እንዲለጎም የሰበከበን አባባሉ አልቀበለውም።

ሰለ ማስረሻ ሰጤ ያለውን እና ስም ባይጠቅስም ጋዜጠኛ ጌጥየ ያለው ሰለተባለ ጋዜጠኛ ምን እያለ እንደጠቀሰው ጭምር እንመለከት።

አሁንም ሚዲያው የሸፈነው ሰለ ማስረሻ ሰጤ ወደ ኦሮሙማው ሥርዓት መግባቱን እና ሰላይ ሰለ መኖሩን ነው የሚወራው። ከጀምሩ ብርሃኑ ነጋ እና ሻዕቢያ ግርፍ የነበረው ዘመነ ካሴ ፋኖ መስርቻለሁ ካለጀምሮ በታጣቂ መንደሮች የተከሰተው “ብጥብጥ ነው”።ምንም ታአምር እሱ ከሚመራው ፋኖ ካልተቀላቀለ ንም ታጣቂ ጎጃም አማራ ድር ውስጥ መንቀሳቀስ የለበበማለት፤ ማስርሻ ሰጤንም ኮሎኔል መካንንት የሚባለውንም እና በካታዎቹ እያሳደደ ከቀጠናው አስወጥቷቸዋል

ማስረሻም ጨንቆት ወደ   እንዲጠለል አስገድዶታል። ስለ ማስረሻ ጎጃምን መልቀቅ ሃብታሙ የሚለው ግን «ትዳር ይዞ ከአማቾቹ ጋር ሸዋ ተቀምጦ ነበር» እያለ የከስዋል

ሌላ መረጃ የሰማሁት ደግሞ ፤ «እስክንድር ነጋ ከአብይ ጋር ይደራደር ስለነበር ይቅርታ የጠይቀን» የሚለው ከራሱ በላይ የሚኮፈስ ተሰፋይ ወልደስላሴ የተባለ ከ‘አፋብሃ’ ኦፕራ-ዊንፍሪ ከማአዛ መሐምድ ጋር ሲናገር ያደመጥኩት፡

«ማስረሻ ትዳር ነበረው፤ ባለቤቱ ከተማ ውስጥ ለአንድ አመት ሙሉ በመንግሥት ዕውቅና 100 ሺ ብር በወር «እየላከላት» በወረዳው ውስጥ መንግሥት የጥበቃ አጃቢ አደርጎላት ትኖር ነበር» ሲል አድምጫለሁ።

እንግዲህ ማስረሻ «የጫካ መሐመድ አላሙዲ» ነበር ማለት ነው (100 ሺ ብር በወር ከጫካ ይልክላት ነበር ይላል) ሂዳችሁ አድምጡት። በየወሩ 100 ሺ ብር ሲልክላት የሰንድ ማሰጃ ግን አላቀረበልንም።

እነዚህ ባሕላዊ ጋዜጠኞች የት እና እንዴት እንደሚሰለጥኑ አልገባኝም።

ሃብታሙ አያለው ደግሞ የነገረን፤ « (ማስረሻ ሰጤ- ሽዋ ግብቶ ፤አግብቶ አንዲት ጎጆ ውስጥ ከአማቾቹ ጋር ተጠግቶ ጥጉን ይዞ ሲኖር የነብረው ሰውየ...»  ሲለን ፤  

የፋሺስት ታጣቂ ቡድኖች የዜና ምንጮች ክንፍ እያሉን ያሉት ግን ከሃብታሙ አባባል በመለየት የማስረሻ የትዳር ባለቤቱ ከማስረሻ ጋር ጫካ የምትኖር ሳይሆኑ ባንድ የከተማ ወረዳ ውስጥ ትኖር እንደነበረች ነው። ስለዚህ ማንኛቸውን እንመን?

 እንዲያም ሆኖ ታጋይ አልነበረም የሚሉን ፡ ሰውየው  የውጭ ጉዳይ እና የድርጀቱ አመራር አባል ሆኖ እስከ ከዳበት ሰሞን ጀምሮ በዛ ከፈተኛ ምደባ ተመድቦ ይታገል እንደነበር ይነግሩናል።

ይህ ተስፋየ የሚባለው የዘመነ ሚዲያ ቱልትላ እየነገረን ያለው «ማስረሻ 100 የታጠቁ ታጋዮች ነበሩት»  ይለናል (100 ታጣቂ ነበረው ግን ታጋይ ሳይሆን ትዳሩ ላይ ነበር የሚለው ምላሳቸው አይጣረስም?

አንዳንዶቹ ደግሞ ማስረሻ እጁን ሲሰጥ ጦር ሰላልነበረው “አንዲት ውሻ ብቻ አስከትሎ ፌስታል ይዞ እንደገባ በፎቶም በዜና መልክም ነግረውናል።  ማንኛቸውን እንመን?  

ሁሉንም እንዳለ መቀበል የለብንም። ማስረሻ “ሰላይ ነበር” የሚለው ፤ በልዩነት የሚለዩትን የጫካ ተዋጊዎች “ስም መለጠፍ” በወያም በሻዕቢያም ፤ በኦንግም የተለመደ የጫካ ፖለቲከኞች ባሕሪ መሆኑንም ታሳቢ ፣ማድረግ ተገቢ ነው ።  ሰላይ ኖሮም ሊሆን ይችላል፤ ላይሆንም ይችላል። ጋዝጠኞች ነን የሚሉን ለማመን የተረጋገጠ ሰነድ እጃቸው ላይ ይዘው አላሳዩንም። ክርከሩ መስፍን የተባለው ከመንግሥት ጋር ሲነጋገር ቅጂ በመደመጡ ምክንያት፤ እስክንድርም ፤ማስረሻም ሰላዮች ነበሩ ከሚለው መላምት በቀር ጭብጥ ያለው የተያዘ የድምጽ ቅጂ ሊያቀርቡ አልቻሉም

በተለይ የሚገርመኝ ነገር፤ ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር ሲደራደር ነበር እያሉ አመድ ሲያቦኑ እሰማለሁ፡ አንዳቸውም እሰካሁን ድረስ «ደርድር» ምን ማለት እንደሆነ እና «ሲደራደሩ ነበር» የሚሉት መከራከሪያ « እጅ ሰለመስጠት ነው? ወይስ ምንድ ነው ሲደራደሩ ነበር ማለት???» ስለምን ነበር «ሲደራደሩ ነበር ይሚባለው?»

መስፍን ከሚባለው ሰውየ በቀር፤ እስክንድር፤ ወይንም ማስረሻ.. እያሱ...ወዘተ... ከመንግሥት ጋር « በምን ጉዳይ ሲደራደሩ እንደነበር» ምንም የጽሑፍ፤ የድምጽ ቅጂ ማስረጃ የቀረበ፤ የተገኘ የለም።

ድረጅቱ ደካማ ነው/ አዎ! ሁሉም ፋኖ የሚባሉት የአምራር ችግር አለባቸው። “ጥይት ምተኮስና እንደ ወያንዎቹና ሻዕቢያዎቹ የተዋጣላቸው አዋጊዎችና በተንኮልም  ባመራር ጠበብም የተካኑ መሁራን  አመራር የላቸውም።

 ወደ ሃብታሙ ስንመለስ ማስረሻ ላለመረሸን በተነሳው ክፍፍል ተፈጠሮ ከነሱ ውስጥ ነጥሮ ለጥቃት የተጋለጠው እና ላለመገል ሲል ሸሽቶ ሲታገለው ወደ ነረው ለአፓርታይዱ ኦሮሙማ እጁን ሰጥቷል። እሱ ብቻ ሳይሆን የጫካ ኑሮ መርዋቸው መካከለኛ አመራር የነበሩትም አብረው ተከትለውት እጅ ሰጠተዋል።እነሱም እጅ ሲሰጡ ልክ እንደማስረሻ ምክንያታቸውን ያስቀምጣሉ።   

ሃብታሙ ሰለ መረሽን እና አለመረሽን አስመልክቶ ግን እንዲህ ይላል

«ማስረሻ እንትን ሲል አምልጦ ነው፤ ሊረሸን ሲል ሊሞት ሲል አመልጦ ነው፤ሊረሽኑት ሰለ ፈለጉ አመለጠ... ሆይ ሆይ  ... ሊረሽኑት ፈላጎት ቢኖራቸው ማን ይዘዋቸው ነው ረሻኞች ናቸው እያሉ.... (ስማቸውን የሚያጠፉ)። ይላል ሃብታሙ ፋኖዎቹን ረሻኞች አይደሉም እያለ ሲከራከርላቸው።

 

መጀመሪያ ሃላፊነቱን የሚወስደው ማስረሻ እራሱ ቢሆንም ፥ በሁለት ቅርቃር እንዲቀረቀር ከጎጃም እንዲባረር ከዚያም ሽዋ/ወሎ ውስጥ ገበቶ ልዩነት ተፈጠሮ አማራጫ ሳይሰጡት በመቀርቀሩ «ለመጥፎ ነገር እንድሚፈልጉት!! ወዳጁ ኮለኔል ፋንታሁን» እንደነገረው ሲያውቅ፤ አማራጭ ሲያጣ  ወደ ከተማ እንዲገባ በማድረጋቸውን ሃላፊንት ይወስዳሉ።

 ልዩነት የጀመረው ወያኔን ለማዳን የአማራ ሕዝብና ታጋይ መስዋዕት መከፈል አለበት በሚሉት እና በተቃወሙት መካከል ነው። ለዚህም «ባንዳው ተፈራ ማሞ» ለሠልጣኝ ተመራቂዎቹ የመንግሥት ታጣቂ ወያኔን እና ሻዕቢያን ለመውጋት ቢመጣ «ቅድሚያ መስዋዕት የምትሆኑት ለትግራይ እና ለኤርትራ ሕዝብ ነው ፥ ከዚያ ሞት ከተረፋችሁም ለአማራ ሕዝብ ነው» ባለበት ወቅት ፡ ማስረሻ በመቃወም ድምጹን ሲያሰማ፤ ሰምተናል።

የ ‘አፋሕድ’ መከታ ማሞ ደጎሞ ተፈራ ማሞን ደግፎ የማስረሻን ሃሳብ ተቃውሞ “ንግግሩ እኛን አይወክልም” ፤ (የተፈራ ማሞ አባባል እንደግፋለን) ብሎ መስመሩ ከማን ጋር እንደሚገጥም ነገረን። ይፋ የሆነ መካረር ማድመጥ የጀመርነው ከዚያ ወቅት ነው።

«  

 

 

 

ሃብታሙ ስለ ማስረሻ ሰላይነትና ብልጽግናነት ሲኮንን፤ የተቀሩት የዲሞክራሲ ገምቢዎችና ከወንጀል የፀዱ «ብፁአን» የሆኑ፥ በዚያም ውህደት ለመፍጠር እንድሚገኙ ነግሮናል። የሚገርመው ግን የጎጃሙ የዘመነ ፋኖ የትግል አጋር የሆነው የወሎው ምሬ ወዳጆ ለአማራ ሕዝብ ያሳወቀው  ደግሞ ‘’አፋሕድን’ የሚመራው አባ ዱላ ገመዳ እንደሆነ ነው። ያ ከሆነ አባ ዱላ ገመዳ ከሚመራው የሽዋው ‘’አፋሕድ’ ጋር ውህደት መፍጠሩን ሃብታሙ ለምን ደገፈው? የሚለው ልጠይቅ።

ምሬ ወዳጆ ስለ እስክንድር ነጋ፤ ሰለ  ሎኔ ፋንታሁን ሞሓባ እና ስለ የሸዋ ፋኖ ድርጅት እንዲህ ያለውን ላስታውሳችሁ፡

«ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሓባ ባንዳንድ ሃይሎች ስለተጠለፈ አባርረነዋል!

ሰለ አፍሕድም እንዲህ ይላል፦

<<የሸዋ ፋኖን እየመራ ያለው አባ ዱላ ገመዳ ነው>> ሲል የወነጅለዋል። ታዲያ  ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሓባ ባንዳንድ ሃይሎች ስለተጠለፈ ካባረረው ጋር! ‘አፋሕድ  እየመራ ያለው “አባ ዱላ ገመዳ” ከሆነ>>ከሃብታሙ ይህንን እያወቀ ማስረሻ ወደ “”መንግሥት” ገብቶ ከአባ ዱላ (ከአብይ አሕምደ) ጋር ስምምነት መፈጸሙን ካወገዘ፤ እንዴት የጎጃም እና የወሎ ፋኖ ድርጅቶች ጫካ ከሚገኘው የአባ ዱላ ገመዳ ድረጀት (አፋሕድ) ጋር  ውህደት (ስምምነት) ሲደረግ መደገፉ እንዳለበት ለምን በዝምታ ሊያልፈው መረጠ?

 

የምሃይሙ ምሬ ወዳጆ  አባባል ውሸት ከሆነ ከዋሾች ጋር ይሚደረግ አንድነት  ምን ያህል ርቀት ሊሄድ ነው? እሱ ብቻ አይደለም ፤ “እስክንድር ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አይደለም” ብሎ ካለው ተፈራ ማሞ እና ኢትዮጰያዊው እስክንድር እና የአማራ ዜግነቱን ያውጀ ተፍራ ማሞ ጋር ውሃ እና ዘይት ሆነው በውሕደቱ ላይ እንዴት ሊጣጣሙ ነው?

 

ሃያሲና ጋዜጠኛ ሃብታሙ አያሌው ማስረሻን ሰላይ ነበር ሎ ደምድሟል። ሰላይ እንደነበርም ነገሩ ይፋ ከመሆኑ 3 ሳመንት በፊት አውቅ ነበር የላል። ትዳር ላይ እንጂ ትግል ውስጥ እንዳነበረስ ከ3 ሳመንት በፊት ነው የተነገረው?

 

 ማስረሻን ሰላይ እንደነበር ብቻ ሳይሆን ፡ ከመረሸን የዳነው ከጫካ ሸሸቶ ያመለጠው ጋዜጠኛ ጌጥየ ሰለተባለው ወጣት ጋዜጠኛም ጭምር በሚገርም አወነጃጀል እሱንም “ፖለቲካ የማያውቅ ፈርጥጦ ኡጋንዳ የመሸገ” ሲል ወንጅሎታል።

 

ስለ ጌጥየ ያለውን እንመልከት

ጌጥየ «ከታወቁ አራት የአፋሕድ ጋጠወጥ አመራር አባሎች ገዳይ ጥይት በልመና ይሁን ወይንም በድርድር (?) ከመረሸን የዳነውን  ከሸዋ በአዋሳ አድርጎ ከዚያም ወደ ኡጋንዳ ተሰደደ የተባለው ከፋኖ ጋር አብሮ ሲታገል የነበረው ጋዜጠኛ ጌጥየን ( ሃበታሙ በቀጥታ ስሙን ጠቅሶ ባይናገርም) ሃያሲው ሃብታሙ ስለ ጌጥየ እንደሆነ አልጠራጠርም።

 በዚህ አጋጣሚ ፥ ጋዜጠኛ ጌጥየን እንደ «የመንግሥት ሰላይ» አድርጎ ያቀረበው መስሎኝ በዚያ እተቻለሁ በየ ትንሽ ማሳሰቢያ ጽፌ መኖሬ የታወሳል። (ለዚያ ስሕተት ሃብታሙንና አንባቢዎችን ይቅርታ እየጠየቅኩ)፤አሁን ግን የሃብታሙ አባባል ደግሜ ሳደምጠው በስሕተት ተረድቸው ሰለነበር ትክክለኛው የሃበታሙ አባባል በሚከተለው አባባሉን  እተቻለሁ፡

 እንዲህ ይላል፤

«ፖለቲካ ማወቅ ማለት በአዋሳና በማንምን አቋርጦ በሞያል አቋርጦ ሩጦ ወጥቶ ኡጋንዳ መመሸግ ነው? በጀግንነት የሚታገለውን ማነወር ከየት የመጣ ሞራል ነው?» ሲል ይናገራል።

በፋኖ ትግል ውስጥ ጫካ ውስጥ የነበረው በቅርቡ ከጫካ ወጥቶ በዚያ ጉዞ ተጉዞ ኡጋንዳ የተጠለለው ሰው ጋዜጠኛ ጌጥየ ያለው ነው። ይህ ጋዜጠኛ ድግሞ ሳይወድ ተግድዶ ለስደት ተዳርጎ  ከመረሸን ተርፎ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት ፋኖዎቹ ሰው ሲረሽኑም እንደሚያውቅ መናገሩና እና ስለ ታላቁ እስክንድር ነጋም ለስም በመሪነት ይቀመጥ እንጂ በዛ ነፃነት ውስጥ እንዳልሆነ መናገሩን ይታወሳል። ሃብታሙም እስክንድርን ለጥያቄ አቅርቦ ሰለ ጉዳዩ ጠይቆት “በነፃነት” እንድሚንቀሳቀስ መልስ ስጥቷል (የ እስክንድር እኔ ነፃ መሪ ነኝ የሚለውን አላምንም፤ በዙ ምልክቶች ሰላሉ)።

ያ ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኛ ጌጥየ ያለው የሃብታሙ የፋኖዎች ሰለ ወደ አንድነት እየመጡ ነው አባባል በቅርቡ እንዲህም ያቀርበዋል፡

የአማራ ፋኖ ትግል ዓላማው እንዲሳካ ከተፈለገ የአንድነት ጉዳይ በጣም የግድ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አንድነቱ በከፍተኛ ደረጃ እየዘገየ ነው ያለው። መዘግየት ብቻ ሳያሆን ቢመጣም ሙሉ በሙሉ የአማራ ፋኖ በጠቅላላ በአንድ ሳምባ ሊተነፍስ የሚችልበት የአማራዊ  የፋኖ አደረጃጀት  ይኖራል የሚል ግምት የለኝም።  ይህ አባባል በዙዎቹን ስምታቸው እንደሚጎዳ እገምታለሁ።  ነገር ግን ለመሳሌ በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ የታወቁ ሁለት ጠንካራ የሚባሉ ድርጀቶች 2 ናቸው (አፋሕድ እና አፋብሃ)። እነዚህ አንድ አደረጃጀት ሆነው እንትና መሪ እንትና  ምክትል ብለው በደስት ሊያንበሸብሹን ይችላሉ። ሆኖም ባንድ ማዕቀፍ ባንድ ቋጥ ውስጥ አንድ ይሆናሉ የሚል ግምት የለኝም። ከነሱ የሚያፈነግጥ ስላለ ፡ አሁንም እያየን ሰላለ ማለት ነው።

ለምሳሌ እንደ ዋና ማዕከል አድርገው የሚያዩት የወያ ጉዳይ ነው፡ በዚያ ልዩነት መንጠባጠብ ይኖራል......» ይላል ጋዜጠኛ ጌጥየ፡

 

 ታዲያ ጋዜጠኛው ሰለ ፋኖዎቹ ምንነት በማስረዳቱ እና አንዳንዶቻችንም እንዲሁ ውህደቱን አስመልክተን የፋኖዎቹ ገመና በመናገራችን ሃብታሙ አያሌው ግን  «በጀግንነት የሚታገለውን ማነወር ከየት የመጣ ሞራል ነው?» ጀኖቹ እዛ ዋጋ ሲከፍሉ «ወደ ኡጋንዳ ሮጦ ሸሽቶ መመሸግ ነው?» ሲል ጌጥየን ይወቅሰዋል። « ጋዜጠኛ ጌጥየ  ከጫካ ትግሉ የተሰናበተው “ትግሉን ሰልችቶት ሸሽቶ ወደ ኡጋንዳ  ሸሽቶ ፥ የማይረባ ፖለቲካ ለማራመድ እንደሆነ  አድርጎ ነው እየከሰሰው ያለው (ያውም ሃብታሙ  ከማንኛችን በፊት ሰለ ጋዜጠኛው ደህንነት ጉዳይ እየተከታተለ ሲያስረዳን እና ቀዳሚ መረጃ የነበረው ሰው ሃብታሙ ነበር) ታዲያ አሁን ጋዜጠኛው ከትግሉ ሸሸቶ ኡጋንዳ እንደተወሸቀ አድሮ ማሳነስ ምን አመጣው።

ጋብታሙ ለዚህ መነሻ ያደርገው «መከታው ማሞ ዘመነን እና መሰሎቹን አንድነት ለመፍጠር እነሱን በአካል ለማግኘት ከሽዋ ወደ ጎንደር በመጓዙ የበቃ ፖለቲካ ማለት ያ እንደሆነና «ኡጋንዳ ውስጥ መሽጎ» ያንን መቃወም «ኢሞራላዊ» እንደሆነ፥ የሞራል ጥያቄ ያቅርባል።

“ያ ሞራል የመጣው መከታው ወደ ጎንደር በመጓዙ የሞራል መለኪያ ምልክት ሳይሆን ፋኖዎቹ “ሰው እንደረሸኑ” ፋኖዎቹ አንድ ቢሆኑም በወያኔ ጋር መስራትና አለመስራት እና የመሳሰሉ ምክንያቶች ባንድ ቅርጫት ሊያስገባቸው የማያስችሉ ነግሮች እንዳሉ ነው ጋዜጠኛ ጌጥየ የሚያቀርበው ምክንያት ።

ይህንን በማለቱ «ፖለቲካ ማወቅ ማለት በአዋሳና «በማንምን አቋርጦ በሞያሌ አቋርጦ ፥ «ሩጦ» ወጥቶ ኡጋንዳ መመሸግ ነው? በጀግንነት የሚታገለውን ማነወር ከየት የመጣ ሞራል ነው? የሚለው የሃበታሙ ትችት «ዝም በሉ» ከማለት የተለየ አይደለም።  

ሃብታሙ ስለ ማስረሻ ከርሸና ማመለጥ ጉዳይ ውሸት እንደሆነ አስምለክቶም እንዲህ ይላል፤-

«እሚረሽኑ ቢሆኑ ማን እጃቸው የዟቸው ነው? ረሻኞች አድርጎ መሳል ሰለተፈለገ? ....» በማለት ፋኖዎቹ ሰውን አይረሽኑም ወደ እሚል ምከራከርያ ያስገባናል። “እሚረሽኑ ቢሆኑ» እና «ሊረሽኑት ፍላጎት ቢኖራቸው” ማለት ረሽነው አያውቁም፤ አይረሽኑም ማለት ነው። ያንን ቃል ግለጽ ሲያደርገም ረሻኞች አድርጎ መሳል ሰለተፈለገ ....»  እያለ ሃብታሙ ፋኖዎች ‘’መብት ጠባቂዎች’  እንደሆኑ  ሙግት ሲያቀርብ ፤  «አዎ ፋኖዎች ሲረሽኑ አውቃለሁ» የሚለው ጋዜጠኛ ጌጥየ ፣ምስክርነት ስንመለከት ፥ ፋኖዎች እሚረሽኑ ቢሆኑ እና ፋኖዎችን ረሻኞች አድርጎ መሳል ሰለተፈለገ የሚለው የሃብታሙ ለፋኖዎቹ  ያቀረበው መከላከያ ውድቅ ያድረገዋል።

ሃብታሙ በመቀጠል፡

«በነጋርችን ላይ የሚያስቅ ነገር አፋሕድ ውስጥ ከወያነ ጋር ልስራ ብሎ ያቀረበ አካል የለም» ወያነ ሰለ’ሚመጣ ከብአዴን ጋር እንስራ ያሉ ግን አሉ። ድርጀቱ ማስረጃ አለው ማቅረብም አለበት» «የነበረው የልዩነት አመለካከት ይህ ነበር፤ ሌላ ነገር ቢሞክሩ እንዳትሰሙ!» ይላል ሃብታሙ ማስረሻን ብቻ ለመክሰስ ሲሞክር።

 «አፋሕድ ውስጥ ከወያነ ጋር ልስራ ብሎ ያቀረበ አካል የለም እንበልና ፤ በካፒቴን ማስረሻ ሰጤ እና በጎጃም/ወሎ ፋኖ “የፖለቲካ ሃርለቶች”  መካከል የተነበረው መሳሳብ አስመለክቶ ማስረሻ እኒህ ማለቱ ይታወሳል፦

 «ዝርዝር ሁኔታዎች በማስረጃና በመረጃ ለሕዝባችን የምናሳውቅ መሆኑን  እየገለጽኩ ስለዚህ በግራም በቀኝም ያሉ የፋኖ አመራሮችና የፋኖ አባላት የማንም ዕርዳታ ሳንፈልግ “በራሳችን መቆም  እንችላለን”።

«በበሰበሰ ቁምባላ» የሚሸወድ  የአማራ ወጣት የሚታለል እንደሌለ መታቅ አለበት። ስለዚህ በራሳችን እንቁም.......

«እኛ ኢትዮጵያን እንወዳለን፤ እንደ ሀገር ኢትዮጵያ እንድትቀጥል እንፈልጋለን፤ ነገር ግን የወያነ ዓላማ አንግቦ ኢትዮጰያ እንድትበታተንና  ደካማ ሀገር እንድትሆን የሚፈልግ አውዳሚ ስብስብ በሕዝብ ትግል ወደ አንድ አካባቢ እንዲመሽግ እንደተደረገ የሚታወቅ ቢሆንም ....የዚህ  አጋርና የዚህ ፈረስ ሆኖ መምጣት “በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ ባርበኛነት ስም የሚንቀሳቀስ  ማንኛውም አካል፤ ሊያቆም እንደሚገባ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።» ሲል

መከታው ማሞስ ምን እንዳለ ለቀባሪው ለሃብታሙ ላርዳው? የ ‘’አ ፋ ብ ሃ’’ አመራር የሆነው የወያነና ሻዕቢያ ሰላይ ተፈራ ማሞ  «ለወያነ እና ለሻዕብያ መሰዋት» የአማራ ወጣት ለተጠቀሱት ቡድኖች መስዋዕት እንዲሆን ሲያውጅ፤ ማስረሻ ያንን በመቃወሙ ከላይ ያየነው ንግግር ሲያስተላለፍ

‘አ ፋ ሕ ድ’ ምክትል መሪ መከታው ማሞ ግን የ“አፍብሃ” አመራር የተፈራ ማሞ ባንዳዊ ንግግርን በመደገፍ ምን ነበር ያለው?

ልጥቀስ፤-

« «ምናልባት አርበኛ ካፕቴን ማስረሻ  በተለቀቀው (ንግግር) ሙሉ በሙሉ አላዳመጥኩትም ፤ሙሉ በሙሉ ባልሰማውም ዞሮ ዞሮ  በደረሰኝ መረጃ እንደ አመራር ፤ እንደ አፋሕድ ሥራ አስፈጻሚም የሚወክል እንደ ረጅትም ምንም ዕውቅና የለውም። እንደ ድርጅትም እንደ ግልም ምንም የምናውቀው የለም። «(መልዕክቱም) አፍሕድን የሚወክል አደለም» ብየ ነው የምገልጸው።በተሰጠው መልዕክት ላይ የአፍሕድ አቋም እንዳልሆነ ለመግለጽ እወዳለ»። የላል መከታው ማሞ።

አስቂኝ መሆን የነበረበትስ ይህ የመከታው ንግግር ነው። ወያነ ሰለ’ሚመጣ ከብአዴን ጋር እንስራ ያሉ ከነበሩ ፥ ወያነ እና ሻዕቢያን ለማዳን ከወያነ እና ከሻዕቢያ ጋር እንሰራለን ካሉ ወገኖች ጋር  ንግግራቸውን በመደገፈ ማስረሻን በመቃወም የተፈራን መልዕክት የአፍሕድ አቋም እንደሆነ ለመግለጽ እወዳለሁ የሚለን መከታው ማሞስ በምን ተለየ? ግልጽ እኮ ነው።

 በንግግራቸው አደለም እየፈረድን ያለነው? እንደዚያ ከሆነ ግልጽ እኮ ነው።

በነገራችን ላይ የማስረሻ ከእነ መከታው ንትርክ የጀመረው ከዚያች ቀን መሆኑን የመናውቅበት ምክንያት እሰከዛች ዕለት መከታው ማሞ ማስረሻን «አርበኛ›› እያለ ነበር በታጋይ ማዕረግ ሲጠራው የነበረው። ገባችሁ????!!!!!!! ከላይ የመከታውን ንግግር እዩት።

ሃብታሙ በመቀጠል እንዲህ ይላል፤

 አርበኛ ዘመነን ጭቃ ለመቀባት መነሳት ምድነው ዓላማው፤ የአማራ ሕዝብ ምንም አይቅረው ነው? ይህ ነው ዓላማው» «የምንለው አጥተን አይደለም ፤ የትናንቱን ብንዘረዝር ማን ምን እንዳጠፋና ምን እንዳደረገ እምናነሳው ነገር ይኖረናል። ያ አስፈላጊ አይደለም ፥ ወደ ላ የምናየው ወደ ፊት እንድንራመድ እሰከረዳን ድረስ ነው አለበለዚያማ ለምን ወደ ላ እናያለን።

ወደ ፊት እየሄድክ ወደ ኋላ ማየት ለምን የጥቅማል?  በእስፖኪዮ እንኳ የምናየው ወደ ፊት እንድንሄድ እንዲረዳን እና ወይንም ፓርክ ለማድርገ ስንፈልግ ብቻ ነው» ይላል ሃበታሙ   

 ካለመታከት ፋኖዎቹን አትንኩ የኋላ ታሪካቸው ምንም ይሁን ምንም እርሱት መኪና ስንነዳ የኋሊት መስተዋት የመንጥቀመው መኪናውን ፓርክ ለማድርገ ካልሆነ ምንም አይፈይድም” ይላል።

ያ አባባል ራሱ መጀመሪያ ያለውን እንደገና ያንን ያፍረሰዋል፡

«ወደ ሃላ የምናየው ወደ ፊት እንድንራመድ እሰከረዳን ደርስ ነው አለበለበለዚያማ ለምን ወደ ኋላ እናያለን»  ይላል ሃብታሙ። ታዲያ «ወደ ኋላ የምናየው ወደ ፊት እንድንራመድ ሊረዳን ከሆነ ወደ ኋላ ማየት ካቆምን ወደ ፊትም በደህንነት ያለ አደጋ መራመድ አንችልም። ምክንያቱም ሃብታሙ እራሱ መራመድ እንደሚረዳን ያምን እና እንደገና ወደ ኋላ አንመልከት ይላል። ወደ ኋላ መመልከትን ካቆምን ወደ ግራም ወደ ቀኝም ለመግባት ስንፈልግ ከኋላችን እና በግራና ቀኝ በኩል እየነዱ አቃጫ እየቀየሩ ድንገት መጥተው እኛ ለመቀየር ወደ ምንፈለገው መስመር ሊገቡ ሲፈልጉ ኋላ ያሉትን እና በጎን ያሉትን ፈጣን  መኪኖችን ካላየን በድንገት መስመር ለመቀየር ስንል ተጋጭተን አደጋ እንዳናግኝ ስለሚረዳን የግድ መፈተሽ አለብን። የኋላ መመልከቻ መስተዋቱን በመፈተሽ ትራፊክን መከታተል እና ሊከሰቱ ለሚችሉ አደጋዎች ለማስቀረት መዘጋጀት ስለሚያስችል ነው (አደለም እንዴ?)።

 በፖለቲካውም ረገድ አሁንም ይሁን ካሁን በፊት የመንግሥት መንበር ተቀምጠውም ይሁን ጫካ ውስጥ የሽምቅ ተዋጊ መሪዎች ሆነው በሕብረተሰቡ ላይ ጉዳት ያደረሱ ሰዎች የኋላ ጀረባቸውን ሳይፈተሹ ስለ ሰላም ሲባል  በተደጋጋሚ ወደ ሥለጣን እየመጡ ያንን ወንጀል እንዲቀጥሉበት እየተደረገ ያለው የሃገራችን ችግር ዋናው ምንጩ ፖለቲከኞች የኋላ ታሪካቸው ሳይመረመር ሰለሚቀጥሉ ነው ችግሩ እየቀጠለ ያለው።

የፖለቲካ እጩዎችን ዳራ ማጣራት የሕዝብን አመኔታ ወደነበረበት ለመመለስ፣ የግለሰቦችን ታማኝነት እና ለሕዝብ ሹመት ተስማሚነት ለማረጋገጥ እና ሊከሰቱ የሚችሉ በሙስና መባለግንን፣ ስልጣንን ያለአግባብ ፤ መጠቀምን፤ግድያን ወይም አምባገንነነትን እና የደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል የፖለቲካ እጩዎችን የጀረባ ታሪካቸውን ማጣራት አስፈላጊ ነው። ሥራ ለመቀጠር፤ ማጣራት እንደሚኖር ሁሉ ለሽምቅ ተዋጊነት መሪ ለምሆንም ይሁን ለፖለቲካ እና ሥልጣን ለሚቀርቡ ሰዎች ካሁን በፊት ገራፊዎች መኖራቸውንም ይሁን ፥ ምን ወንጀል መፈጸማንቸውና አለመፈጸማቸው በሕዝብ መነፅር ታይተው መቅረብ አለባቸው።

ታዲያ ሃብታሙ ሲያራምደው የነበረውን ይህንን ጠቃሚ መስመሩን ዘንገቶ በመንሸራተት  «ስለ የፋኖ አንድነት ሲባል ገመናቸውን አትናገሩ ዝም በሉ» ይላል (ለተጎጂዎች)። ጠመንጃን ተገን አድርገው ገመና ሰለ ፈፀሙ ሰዎች መናገር «ጥላሸት» በሚል ቃል መግለጹ አስገራሚ ነው። «ዘመን ካሴን ለምን ጥላሸት ለመቀባት ተፈለገ?» በማለት የዘመነ በጠመንጃ የመባለግ ባሕሪን ማጋለጥ ‹ጠላሸት ነው አትቀቡት» ይለናል።

የዘመነና ታጋሪዎቹ  በጠመንጃ ተመከተው የዜጎችን መብት ተጋፍተዋል ማለት ፥ ጥላሽት መቀባት ሳይሆን « በተግባር የሆነውን እና ያደረገውን አምባገነንነትን ነው»።   ታጣቂዎም ይሁኑ ሥልታን ላይ ያሉትና ያለፉትን የጀርባ ማሕደራቸው እንዳይጠና ዝም በሉ፤ ጥላሸት መቀባት ነው፥ ማለት ኢትዮጵያን በቀጣይ ብጥብጥና ግዳዮችና የተለያዩ በገመና ማሕድር የተመዘገቡ ወንጀለኞች እና ፖለቲከኞች «በአንድነትና በሰላም ስም» በሥልጣን እንዲቀጥሉ እየተደረገበት ያለው ዋነኛው ችግር ይህ የሃበታሙ «ወደ ኋሊት አንመልከት» አባባሉ ነው።

ወደ ኋላ እያየሽ በሃሳብ ከማለም ቀኑ እንዳይመሽብሽ ትላንት ዛሬ አይደለም የሚለው የዝነኛው ዘፋኝ እሳቱ ተሰማ ዘፈን እና ስለ ፖለቲካና ፖለቲከኞች  ወደ ኋላ ጀርባቸውን  ማየት ለየብቻ ነውና «ወደ ኋላ የምናየው ወደ ፊት እንድንራመድ ድጋሚ አደጋ እንዳይከሰት ነውና

በዚህ ልሰናብታችሁ፦

የአሸፊነት ዕጣ ፈንታው ግምባሩ ላይ ተነቅሶ ወደ እዚህ ምድር የተላከ አዲስ ትውልድ የጀረባ ታሪኩ መፈተሽ ጥላሸት መቀባት አይደለም።

 «እኔና አጋሮቼ  እንደምናሸንፍ የተጻፈው ፤ከእናቶቻችን ማሕጸን እያለን ነው። ወኔነትና ድል አደራጊነትም የተጋትነው በእትብት ነው። ይህ ትውልድ የአሸፊነት እጣ ፈንታው ግምባሩ ላይ ተነቅሶ ወደ እዚህ ምድር የተላከ ተውልድ ነው። አዲሱን ታሪክ የምንጽፈው እኛ ነን፤ የሃገሪቱ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በወጣቱ በኛው እጅ ነው... ጥቅምት 10/2017 (የጎጃም ፋኖ ዘመነ ካሴ)

እያሉ በናዚዝያዊያን እና በፋሺቶች ዕጣን ታጥነው  ቅዥት የተጠናወታቸው ሰዎች አሸናፊነታቸው "ግምባራቸው ላይ ተነቅሶ ወደ እዚህ ምድር" “የወረድን ነን”  የሚሉ የሃገሪቱ ዕጣ ፈንታ ወሳኞች እኛ ነን ሲሉን ፥ ያለፉትና አሁን ያሉት ግፈኞችና ፋሺስቶች  የምነገላገልበት ቀን በጉጉት እየናፈቅን ሳለ ፤ ጫካ የወጡት ደግሞ የሃገራች ቀጣይ ዕጣ በኛ በወጣት ፋሺስቶች እጅ ነው እያሉ ማንነታቸውን በግሃድ ሲነግሩን "ሲፈጠሩ ግምባራቸው ላይ ተሸናፊዎች ናችሁ ተብለው ግምባራቸው ላይ ንቀሳት ተነቅሰው ወደ እዚህ ምድር የወረዱ ምስኪን ተሽናፊ ሕዝቦች» ባጠቃላይ የሃገሪቱ መከራ ቀጣይነት አስግቶኛልያም በውርስ፤ በተወልጄነት፤ በደም ጥራትና ባሸናፊነት ትከሻቸው የሚያስብጡ የትመከሕታዊ ልሳኖች ወያኔንም ሂትለርም ሙሶሎኒንም የት እንዳደረሳቸው አይተናል በጥሞና መጠበቅ ነው።

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጰያዊው  አማራ ሕዝብ እግዚሃር ይታደገው!

ሰላም እንሰንብት

ጌታቸው ረዳ Video


No comments: