Sunday, July 6, 2025

አማራ እንጂ ኢትዮጵያዊ አልሆንም ኢትዮጰያዊነቴን መካድ መብቴ ነው፤ ባዩ የበላበት ድስት ሰባሪው አዝማሪው ፋሲል ደሞዝ ከጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/6/25

 

አማራ እንጂ ኢትዮጵያዊ አልሆንም ኢትዮጰያዊነቴን መካድ መብቴ ነው፤ ባዩ የበላበት ድስት ሰባሪው አዝማሪው ፋሲል ደሞዝ

ከጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/6/25

ካሁን በፊት በጽሑፎቼ ላይ “ትግሬ” ስል እና “ሕዝብ” እያልኩ ሁለት ቃላቶች ስጠቀም ከተሜውም ገጠሩም  በጠባብ ብሔረተኛነት እንደተበከለ የምጠበቅበት አገላለጽ እንደነበር ታስታውሳላችሁ። አምሐራው ላይ ግን ፋኖ የተባለ ሽምቅ ተዋጊ ከተመሠረተ ወዲሀ  አደገኛ የሆነ የፋሺስታዊያን ጎጠኛ ብሔረተኛነት አፍቅሮ የዞታል።  ስለሆነም “አምሐራ” እና “ሕዝብ” የሚባሉ “ሁለት ቃላቶች” ስገልፅ ከተሜውን እንጂ የዋሁ ከምንም ከምንም የሌለበትን የገጥሩ አምሐራ ሕዝብ የማይመለከት መሆኑን ልግለፅና ይህንን እንደ መግቢያ ላሰቀምጥ፡

ከላይ እንደገለፅኩት ፋኖ የተባለ ሽምቅ ተዋጊ ከተመሠረተ ወዲሀ አደገኛ የሆነ የፋሺስታዊያን ጎጠኛ ብሔረተኛነት በዙዎቹ በሃገር ውስጥ ከተሜው እና ውጭ ሃገር በሚኖር ሁሩም ማይሙም የአምሐራ ኢትዮጰያዊነትን መዳረሻው ስቶ ከአውራጃዊነት አልፎ ብጎጥና በመንደር ተደራጅቶ በየሚዲያውና በጦር ፍልሚያ እየተቧቀሰ ሕልውና ትግል ቀልብሶ አክራሪ ብሔረተኛ ሆኗል።

ይህ አደገኛ መንገድ “ሀ” በሎ የተጀመረው (ሰዎች አንቀብልህም ብትሉም) ጎጃም ውስጥ የበቀለው ፡ ሲናገር “የሁሩም ማይሙንም ሰሚ ጀሮ የሚሰልብ” ዘመነ ካሴ የተባለው አክራሪ ብሔረተኛ “መነሻችን አማራ ፤ መድረሻችን አማራ” የሚል “ስሜት ሰላቢ” እሾህ የሞላበት ጭቃ ያቦካው መነሻ እንደሆነ ገልጫለሁ። ከዚያ ጀምሮ የአምሐራ አክራሪ ብሔረተኛነት ቦታ ተሰጥቶት ተቀጣጥሎ ማቆም አልተቻለም።በዚህ ትችት የምንመለከተው አዝማሪው ፋሲል ደሞዝም የዚህ ብሔረተኛነት ወረርሺን ማሳያ ነው።

ሰሞኑን በየሚዲያው ሲዘዋወር ያደመጥኩት ሲያትል ላይ በተካኄደው በዚህ ዓመት የኢትዮጰያውያን የመዝናኛ በዓል ላይ እንዳልዘፍን ተከለከልኩ በሚል አገዱኝ ከሚላቸው ከገልሰቦች ጋር የገጠመው እሰጥ አገባ የተለያዩ ክሊፖች” (ቁርጭራጭ ንግግሮቹ) እዚህ በለጠፍኩት ስዕለ ድምፅ (አውዲዮ - ቪዲዮ) አንዱ ሲሆን፦ እዚሀ ላይ ሲናገር የሚደመጠው ድምፅ እንዲሀ ይላል፤

“አሁንም እደግመዋለሁ፤ ዛሬም አማራ ነኝ ፤ነገም አማራ ነኝ፤ ኢትዮጰያዊም አልሆንም! መብቴ ነው!

ይላል።

አሁን ያለኝ ጥያቄ እንዳልዘፍን ተከለከልኩ በሚልበት መድረክ “እንዲዘፍን ቢፈቀድለት ኖሮ በአማራነቱ ነበር እንዲጋብዙት የፈለገው ወይስ መድረኩ በተሰየመው “ኢትዮጳያዊነት” መድረክ? አምሐራነት እንጂ በኢትዮጰያዊ አልቀርብም ካለ አጋጆቹ (አግደውትም ከሆነ) ትክክል ናቸው። ይህ ብቻ ሳይሆን- መድረኩ ቢሰጠው “የአምሐራ ነጠላ ለብሶ ነበር ሊዘፍን የነበረው ወይስ “ሁሌም በየመድረኩና በሚያሳትማቸው ዘፈኖቹ የሚያውለበልባት ለማታለያ ተከናንቦ የሚለብሳት የዜግነት ማሳያ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ?”

አንድ የኪነት ሰው፤ ወታደር ማለት ነው። ክፍቅር ጀምሮ አገራዊ አንድነትን በማናቸውም መንገድ ማጠናከርና ማጎልበት ሲገባው ሆነ ተበሎ ከጣሊያን ወራሪዎች የተቀዳ በ1983 ዓ.ም  ጀመሮ ሕዝባችን በቋንቋ በጎጥ (በብሔር) የሚከፋፍልአፓርታይዳዊ ሕገ መንግሥት ከወጣ ጀምሮ ሕዝቡ ይህንን ከፋፋይ ተቀበሎ የራሱን መሞቻእየገዘገዘ” በሚታይበት ወቅት እንደ ፋሲል ደሞዘ ያሉ ከፈጣሪ የተሰጣቸው ድምፅ ተጠቅመው ያንን ከመታገል ይልቅ አከራሪ ቅስቀሳ ተቀባይ ሆነው ከነ ጭራሹ አማራ እንጂ ኢትዮጰያዊ አልሆንም ወደ እሚል ዝቅጠት ገብቷል

ኢትዮጰያ መሆን “ጠላት መጣ” ሲባል በጦርነት ጊዜ ብቻ ሁሉም ሰው አሃዳዊ/ውሁዳዊ/ ሀገርነቱን ለማሳየት በሰንደቅዓላማ መከናነብ ብቻ ሳይሆን ወይንም ኢትዮጰያዊ መሆን ሲሞቅ የሚጣል ሲበርድህ የምትከናነበው ልብስ ሳይሆን፡ ወይንም አንድ ውርጋጥ መሪና ቡድን ሥልጣን ላይ ውጥቶ ሰለበደለህ ኢትዮጰያዊነትህን መክዳት ሳይሆን” ስትወለድ ይተሸከመችህ፤ የዓየነ ምድር ገመናህ የተቀበለችህ፤ ቆሻሻህን የምትጥልባት፤ ስትሞት የምታቅፍህ መቀበርያህ ነች። ኢትዮጰያዊ መሆን ሲጨንቅህ ሳትከዳት፤ ስትቸገር የምታለቅስላት፤ ሲሰድቧት የሚያንገበግብህ “እናትህ” ማለት ነች።

ፋሲል ደሞዝ ማይምነቱን ያስመሰከረው ዛሬ ብቻ አይደለም። ታስታውሱ እንደሆን  አርንጓዴ፤ቢጫ እና ቀይ ሕብር ያለውን ባለ ሦስት ሕብሩ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ “የማንነቴ” መገለጫ በሚል የኢትዮጵያን ስንደቅ ለብሶ ባሳተመው ሙዚቃ ላይ አበሮ ከመልእክቱ ጋር የተቀላቀለው አስገራሚው መልእክት ነበር።

ደግሞ ፤ የፋሲል ደሞዝ የማንነቱ መገለጫ  የሆነው አማራነትንና ፋሲል ደሞዝ ሲለብሳት የነበረቺው የኢትዮጰያ ሰንደቅዓላማን የሚጸየፍ የነገድ ፖቲካ አቀንቃኙ <ጸረ አማራው> “በቀለ ገርባን ሃገራዊና የአምሐራ ወዳጅ አስመስሎ በዚሕ ስእለ ድምጽ ሙዚቃ ቅንብር ውስጥ አካትቶበት ኩፉኛ ተቆጥቼ  አንድ ትችት ማቀርቤ ታስታውሱ ይሆናል።

ሰንደቅዓላማን በሚመለከት የበቀለ ገርባ አስቀያሚ ማሕደሩ ልጥቀስላችሁ። ይህ አክራሪ  ግለሰብ ከወያኔ እስርቤት ከተፈታ በኋላ አስቃባጮቹን ለማነጋጋር በኛ ዘመን 2007 2015 በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር እዚህ አሜሪካ አገር መጥቶ በነበረበት ጊዜ ፎቶ ሊያነሱት ሲሉ ፣ ከጀርባም የኢትዮጵያ ባንዲራ  ስለነበር ( ባክ-ግራውንድ ) ሊገባ መሆኑን የተረደው በቀለ ገርባ  ፎቶ አንሺዎቹን  “አይ እኔ ከዚህ ባንዲራ አጠገብ ፎቶ አልነሳም” ሲል እምቢታውን እንደገለጸ በወቅቱ መነጋጋሪያ ሆኖ መሰንበቱን ይታወሳል። በወቀቱ ስትች እንዲሀ በየ ነበር፤

«አንተም ሆንክ እዚህ ያለው ተቃዋሚ ተብየው ማሕበረሰብ በቀለ ገርባን በፈለጉት ዓይነት “ሮማንትሳይዝ/ እያደረጉ እያቆነጃጁ ለታሳምኑን ብትጠሩም የበቀለ ገርባ ማንነት እንዲያ ያል አሰነዋሪ በጥላቻ የተበላሸ  ሰው በግድ ‘የአማራ ወዳጅና ኢትዮጰያዊልታደርጉት አይቻላችሁም።አዝማሪዎች ሆይ ሙዚቃን ሰታሳትሙ አማካሪዎቻችሁ በደምብ ምረጡ። ላንተም ሆነ አጋሮችህ የኪነት ሰዎች እና የአማራ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች በያላችሁበት አገርም ሆነ ከተማ የምጠይቀው አንድ ነገር አለ። በቀለ ገርባን ብርሃኑ ነጋን፤አንዳርጋቸው ጽጌን ከአማራ ማንነት፤ ከአማራ ሰልፍ ትዕይንት እና የሙዚቃ ስራዎቻችሁ ጋር እያገናኛችሁ ስታወድሱ በብዙ ንግግሮች፤ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች እና ጽሁፎችን አይተናል፤አንብበናል አድምጠናል። ስለ ኢትዮጵያ አንደነትን ስለ አማራ ማንነት ህይወታቸውን የሰጡትን ክቡር ሐኪም አስራት ወልደየስን እና የመሳሰሉ አገር ወዳድ አርበኞችን ስታካትቱ አላየንም። እነኚህ ሰማእት በሙዚቃዎቻችሁ ላይ እንዳይታወሱ ስለምን ሆነ? ለምንስ ፎቶግራፋቸው ሳይታይ የነዚህ ጸረ አማራ ግለሰቦች ስታቆነጃጁ መከራችሁን አያችሁ? ይህ ጥያቄ ለጎንደር (ከተማ) ፤ለባሕርዳር፤…ተሰላፊዎች እና እዚህ እውጭ አገር ላሉት ተቃዋሚዎች እና የኪነት ሰዎችን ይመለከታል (በጣት የሚቆጠሩትን አይጨምርም)።” ብ ነበር ፖለቲካው ላይ እያሽቃበጣችሁ ገንጣይና አስገንጣይ ደላላ ሁሉ እያወደሳችሁ ብዙ ብልሽት ፈጥራችሁብናልና ልብ ግዙ።

ያ እንዳይበቃ ደግሞ ከዚያ ከተቸሁት ሳይማር

ኧረ አሸሸ ነው አሸሸ

  አብይ መጣልን ከመሸ

እያለ እርሱ፤ ሻምበል በላይነሀና አንድ 9 የሚሆኑ አለቅላቂ ጨፋሪዎች ሰለ አብይ የሚያለቀል አሽቃባጭ ውዳሴ እያወደሰ አደንቁሮን ነበር።

ከዚያ ስሕተቱ ሳይማር ዛሬ ደግሞ አማራ እንጂ ኢትዮጰያዊ አልሆንም ይለናል።

እንዲህ ሲል

“አሁንም እደግመዋለሁ፤ ዛሬም አማራ ነኝ ፤ነገም አማራ ነኝ፤ ኢትዮጰያዊም አልሆንም! መብቴ ነው!” (ሞዛቂ ፋሲል ደሞዝ)

በመጨረሻም ለፋሲል ደሞዝ አማራነትና ኢትዮጵያዊነት ምንና ምን መሆናቸውን ማስተማሪያ ቢሆነው ይህንን የገጣሚ ሔኖክ የሺ ጥላ ልሳን ለጥቀስለትና ልሰናበት።

ሔኖክ እንዲህ ይላል

<< ስለ ኢትዮጵያዊነቴ ዛሬም ነገም ፣ እሰብካለሁ ። የማምንበትም ምንነቴ ነው፣ ማንነቴ ነው ፣ የማልፍቀው ፣ በክልል ባንዲራ የማልቀይረው ። ሳልፈልግ ተገድጄም ቢሆን ማነስ አልችልም ፣ አንደኛ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፣ በዛ ላይ ደሞ አማራ ነኝ ( ይሰማል ወይ ?)>> ይልሃል ሔኖክ የሺጥላ።

ሔኖክ <ሳልፍልግ ተገድጄም ብሆን ማነስ አልችልም። ማንነቴን በክልል ባንዴራ የማልቀይረው።” ሲል በቀላል እና ግልጽ አማርኛ ነግሮናል። አማራ እንጂ ኢትዮጵያዊ አልሆንም ኢትዮጰያዊነቴን መካድ መብቴ ነው፤ ባዩ የበላበት ድስት ሰባሪው አዝማሪው ፋሲል ደሞዝፋሲል ዛሬስ ትማር ይሆን?

መልካም ሳምንት

ከጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

No comments: