Monday, July 28, 2025

ከፋሺስቶች ላቅ ከናዚዎች ከፍ ያለው የወያኔ ትግሬ ጭካኔ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/28/25

 

ከፋሺስቶች ላቅ ከናዚዎች ከፍ ያለው የወያኔ ትግሬ ጭካኔ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/28/25

ደደቢት ከወያኔ መሰረታዊ ሜዳ ላይ፣ ዜሮ ስድስት (ባዶ ሹድሽተ) ተብሎ የሚጠራ እስር ቤት፤ ለትግራይ ሕዝብ የናዚ ስርዓት የሚፈጽሙበት ነበር::  ይህ ከአደጉ በሗላ (ምስገበሉ) የተመለሱበት ሜዳ ስለነበር፤ ለሞት ተፈርዶ ወደዚሁ ሜዳ የሚላክ እስረኛ፤ ስጋውን በፍጹም አሞራ አልበላውም::የእስር ቤቱ ጭካኔና ስርዓት አጽረጋ ከተባለው ስፍራ እንደጀመሩት ዓይነት ነበር:: የኢዲህ ደጋፊ ነህ፣ ልጅህ ወይም ወንድምሀ የኢዲህ ታጋይ ነው፣ ተብሎ ይያዝና፤ ወደዚሁ ዜሮ ስድስት "ባዶ ሹዱሽተ" እስር ቤት ይወሰዳል፤ እንደደረሰም ስለ ንብረቱ ብዛትና መጠን የትስ እንዳለ ይጠየቃል::

መጠይቁ እንደበቃ ለጥቂት ቀን ደህና ቀለብ እየተሰጠው በሁለት በሶስት ቀን ውስጥ ከሌላ ተመሳሳይ እስረኛ ጋር እየተረዳዳ፣ ቢያንስ ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ  እንዲቆፍር ይታዘዛል፤ የጉድጓዱ ስፋት ወይም ዓይነት የሰው መቃብር አይመስልም፤ እንደ ውሃ ጉድጓድ ጠበብ ብሎ እየተቆፈረ አፈሩ ዙሪያውን ይከመራል፤ እስረኛው የቁም መቃብሩn ጭሮ እንዳበቃ ይወጣና በገመድ እጅና እግሩ ታስሮ፣ ዓለም በቃኝ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ ይመልሱታል::

ወያኔዎች እስረኛቸው ከመሞቱ በፊት ሲሰቃይ ማየት በጣም ያረካቸዋል::ቶሎ እንዳይሞት ትንሽ ቂጣና ጥቂት ውሃ በሜንጦ መሳይ በገመድ (በመገለል) ያቀብሉታል:: ሽንትም ሆነ ዓይነ ምድር መፀዳጃው ከዚያችው ጉድጓድ ውስጥ ነው::አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በሗላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት የለም:: እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋት በጎኑ መተኛት አይችልም::ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም ብቻ ነው::

ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር ፣ ሌሊት በብርድና በጤዛ እየተሰቃየ፤ የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ በሚፈጠሩት ትሎች (ዱቃ) ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም:: ቆዳውን ሰርስረው፣ ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱቃዎች ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው ቅብር ያድርጉታል::

አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በሗላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት የለም::እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋትና፤ በጎኑ መተኛት አይችልም::ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም ብቻ ነው::ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር ሌሊት በብርድ በጤዛ እየተሰቃየ፤ የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ በሚፈጠሩት ትሎች (ዱቃ) ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም::ቆዳውን ሰርስረው፣ ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱ ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው ቅብር ያድርጉታል::

ታዲያ  ከዚሀ አሰቃቂ ሞትና አውላላ ሜዳ ላይ ሳይታሰር እህልና ውሃ አጥቶ ከወደቀው ህይወቱ ሳታልፍ ጆፌ አሞራ (ንስር) ዓይኑን ሲነጥቀው መከላከል ካቃተውና ከነህይወቱ አሞራ ሥጋውን ከሞረቸፈው ሻዕቢያ ግፍ ከፈጸመበት ምርኮኛ የደርግ ሠራዊት የትኛው የሻል ይሆን? ብለን ብንጠይቅ ለሚዘገንን የተለያየ አሰቃቂ ሞት፤ ከናዚ ላቅ ብለው የተገኙ፤ ሰው ለሰው ህመም መፈወሻ ከቅጠልና ክፍራፈሬ መድኃኒት ለማግኘት ምርምር በምካኄድበት ዘመን የሻዕቢያ እና የወያኔ ፈላሰፋዎች (የአጎትና የአክስት ልጆች) በታሪክ ለትውልድ የሚያሳፍርና የሚያስኮንን፤ በወገን ላይ መግለጽ የሚያስቸግርና የሚዘገንን ጭካኔ አገዳደላቸው አይበላለጡም ብሎ ማለፍ ይቻላል።

በጉድጓድ ውስጥ ከነህይወቱ በትል ተበለቶ እንዲሞት የሚፈርዱበት ዓላማቸውን ላላመነና የሚጠረጠሩት የትግራይ ተወላጅ ብቻ ነው። በዚህ የጭካኔ አገዳደል ተሰቃይተው እንዲሞቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች እነ “ሃበተ ገብረተንሳይ፤ ተኽላይ ገብረመስቀል ፤ ወይዘሮ ወርቂ ምንጭራ እና ልጃቸው አቶ አታክልቲ ሥዩም ( በከተማ ሸራሮ ራፖል ጸሓፊ የነበረ ልዑል ራሥ ሥዩም መንገሻ ልጅ)” አሉበት።

በነገራችን ላይ ምናልባት ታሪኩን ለማታውቁ ፤ራስ መንገሻ ሥዩም ከለውጡ በፊት ቀደም ብሎ፤ አቶ አታክልት ሥዩምን ፤ ወንድሜ አይደለህም፤ አባቴም ልጃቸው መሆንክን አልነገሩኝም ብለው ያለተቀበሉት በሽሬ አውራጃ ሰየምት አድያቦ ውስጥ የሚኖር ሰው ነበር።

እናቱ መደባይ ታብርና ሠመማ ያደጉ ከጠቁር ቤተሰቦች (ድሮ ባርያ) ተብለው ተንቀው ከሚጠሩ ወይዘሮ የተወለደና፤ እናቱም እስከለውጡ ድረስ በከበረቴ ሥርዓት ጥላ ያዥ አስከትለው በስናር በቅሎ በመንሸራሸር እሰከ እርጅናቸው ድረስ ተከብረው የኖሩ ወይዘሮ ነበሩ።

ምንም እንኳ ራስ መንገሻ አታክልትን በወንድምነት ባይቀበሉትም ቅሉ፤ የተወለደበት አውራጃና የአካባቢው ሕዝብ የመሳፍንት ዘር መሆኑን ስለሚያውቁ ፤ ወያነ ትግራይም ዘሩንና ሐረጉን ስለሚያውቅ አረጋገጦ ነበር ለሞት ያበቃቸው።.......

ግደይ ባሕሪሹም - አሞራ -ገጽ 207-209

 እያለ የወያኔዎች የጭካኔ ጥግ ይዘረዝራል።

አመሰግናለሁ።

  ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 

No comments: