Friday, April 18, 2025

የጎንደርና የጎጃም ፋኖ ክርስትያናዊ ቦኮሐራምና ክርስትያናዊ ታሊባን እየፈፀሙት ያለው ሃየማኖታዊ ሽብር! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/18/25

 

የጎንደርና የጎጃም ፋኖ ክርስትያናዊ ቦኮሐራምና ክርስትያናዊ ታሊባን እየፈፀሙት ያለው ሃየማኖታዊ ሽብር!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 4/18/25

ኦነግ አምሐራን እንዲህ አደረገ ግፍ ፈፀመ እያሉ ሲጮሁ እራሳቸው የፋኖ ታጣቂዎች ደግሞ የቦኮ ሐራምና የታሊባን ፖሊሲና ተግባር በአመሐራ ሕዝብ ላይ እየፈፀሙ ናቸው።

መጀመሪያ ለቪዲዮው ትንታኔ የአዲሰ ኮምፓስ አዘጋጅ ኤርምያስ ለገሰን እያመሰገንኩ አንድ ነገር ልበል። በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱት በአምሐራ ሕልውና ትግል ሥም የታጠቀ የጎንደር “ፋኖ” በጋሻው ክፍለ ጦር ቃኘው ብርጌድ የተባለ “ጂሃዳዊ ፋኖ” አስነዋሪ ተግባር ነወ።

ይህ ወረበላ ቡድን እራሱን ወደ “የሃይማኖታዊ  ታጣቂ/ መሊታንትነት” በማሸጋገር “ታሊባናዊ መሰል ሽብር፡ በሕዝብ ላይ እያራመደ  አረቄና ሲጋራ ፀረ ሃይማኖታችን ሰለሆነ ጎንደር ውስጥ አረቄና ሲጋራ መጠቀምም ሆነ መሸጥ የተከለከለ ነው፡ በማለት፤

በዚህ ምክንያት

 አረቄና ሲጋራ የመሳሰሉ በመሸጥ የምትተዳደር በሚጥል በሽታ የምትሰቃይ ምስኪን ድሃ የዕለት እንጀራዋን የምታገኝበትን ሥራ ዘግታ  በረንዳ አዳሪ ሆና በልመና መተዳደር እንዳለባት፤ አግተው ሲያሰቃይዋት ከሰነበቱ በኋላይህች ምስኪን በማስፈራራት መተዳደርያዋን እንድትዘጋ ፤ካለሆነ መጥተው እንደሚጠልፏት አስፈራርተው ቃል አስገብተው “በዋስ” ተለቅቃለች

(2) በቪዲዮው ላይ የምታዩዋቸው “ታጋቾችም” በግድ ጾም እንዲጾሙና ክርስትያን ያልሆኑትም በፋኖ ውስጥ በሚገኙ ለዚህ ተግባር በተሰማሩ መነኩሴ አማካይ  ጸበል ተረጭቶባቸው ንስሃ ገብተው ተጠምቀው ወደ የጎንደር “ፋኖ” በጋሻው ክፍለ ጦር ቃኘው ብር ወደ እሚከተለውና ወደ እሚያዘው የክርስትና ሃይማኖት ዕምነትና መመሪያ እንዲገቡ ታጋቾቹን መመርያ እየሰጠ ሲያስፈራራቸውና ሲያስገድዳቸው ታደምጣላችሁ።

ካሁን በፊት ጎጃም ውስጥ በዘመነ ካሴ የሚመራ አረጋውያን እናቶና ቀሳውስት እንዲሁም  መምሕራንና ተማሪዎችን በማፈን፤ በመረሸን ፤ የትምህርት ተቋማት እንዲዘጉ ማድረጉ ቦኮሐራማዊ እርምጃ እንደሆነ ተነጋግረንበታል።

የጎንደሩና ይጎጃሙ ፋኖ ታጣቂ ቡድን “አደገኛ ወረበላና አክራሪ” ነው ስል የነበረውም ያለምክንያት አይደለም።  እነሆ ማስረጃው!


No comments: