ትግራይ ያበቀለቺውን ሰይጣን አምበርክከን አስረን ኮነ ፍስሐ ወ ሰላም አሰሮ ለሰይጣን ብለናል!
ዛሬም ከወላጆቻችን ሰንደቅ ዓላማ አብረን ቆመናል!
4/20/25 ሚያዚያ 12/2017
Ethiopian Semay
ከዘመነ አክሱም
ጀምሮ እስከ ዛሬ 2017 ዓ.ም ድረስ በየ አመቱ እየተከበረ ያለው የትንሳኤ በዓል ዕንኳን አደረሳቸሁ እያልን መልካም መኞታችንን
ሰናበስር፡ ዕጣንዋን እያሸተትን ቅብአ ሜይሮንዋን እየተቀባን በታቦተ ጽዮን ደረት ላይ ግራና ቀኝ ታቅፈን ያደግን እኛ 2 የአክሱም
ፍሬዎች የእየሱስ ትንሳዔ ስናከብር አብሮ በወያን መቃብር ላይ የኛም ዳግም ትንሳዔ አብስረናል።
የትግራይ ተወላጅ ሆኖ ወያነ ትግራይን መቃወም ማለት እናንተ ከምትገምቱት በላይ የሲኦል ህይወት ማሳለፍን ይቀላል። በሁለት ወገን ያም አያምነንም ፤ ያም አያምነንም፡ በሁለት ጅራፍ የመገረፍ ያህል ነው።
“ወያነ ትግራይ”
ራሱን ብቸኛ የትግራይ መሬት ባለቤት አድርጎ ራሱን እንደፈጣሪ በመቁጠር
ትግሬነታችንን በመንጠቅ ፤የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት ፤ በወላጆቻችን ቀብር እንኳ እንዳንገኝ ያገደን “የአጋንንት መንጋ” የሆነው
ይህ የፋሺስቶች ድርጅት፤ ሁለት ትውልድ በፈጀ “በረዢም የትግል ትንንቃችን” ጥለነው ፤ እነሆ ጅራቱን እንደ ውሻ ቆልፎ ፤ ተዋረዶ፤ ሐፍረት ተከናንቦ
“ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ አስገብተን፤ ጭቃ ውስጥ ጥለነው ሲጨማለቅ ማየታችን ለሁለታችን “ድርብ ትንሳዔ” ነውና ፤
እንደ ፈጣሪያችን እየሱስ መከራን ተቀብለን እነሆ “ትግራይ ያበቀለቺውን ሰይጣን አምበርክከን ፤ አስረነው ፤ ኮነ ፍስሐ ወሰላም በለናል!”።
እስመ ተዘከረነ
እግዚአብሔር በሕማምነ
እስመ ለዓለም ምሕረቱ
ወአድኅነነ
እምዕደ ፀርነ
እስመ ለዓለም ምሕረቱ
ዘይሁብ ሲሳየ
ለኩሉ ዘሥጋ
እስመ ለዓለም ምሕረቱ
ግነዩ ለአምላከ
ሰማይ።
እኛን በመዋረዳችን
አስቦልናል፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
ከጠላቶቻችን
እጅ አድኖናልና
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
ለሥጋ ሁሉ
ምግብን የሚሰጥ
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
የሰማይን
አምላክ አመስግኑ።(መዝሙረ ዳዊት)
መልካም ፋሲካ!
Ethiopian Semay

No comments:
Post a Comment