ኤርትራ የሞተችበት ቀን አክብራለች!
5/24/22
ጌታቸው ረዳ
“Wherever there is an
ignorant mass, you will see a flag of an ignorant leader fluctuating with
glory!”
(Mehmet Murat ildan)
ምድሪ ባሕረ/ባሕረ ነጋሽ/ ተብላ ስትጠራ የነበረቺው የጣሊያን ስርትዋ የዛሬዋ “ኤርትራ” ነፃ በመውጣትዋ ሳይሆን “ሞታ ተገንዛ የሞተችበት” ቀን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዘጎችዋ ጥለዋት በመፈርጠጥ “የሸሹዋት”፤ሞታ የተገነዘቺበትን 30ኛዋ የሙት በዓልዋን አክብራለች።እንኳን ሰው የኤርትራ ውሾች ሳይቀሩ ተሰድደው በመጠለያ ጣቢያ ሲመዘገቡ በዜና ተመዝግቦ አድምጠናል።
ነፃነት ማለት ላሰቃየቻቸው ኤርትራ “የነፃነት ጣእም” ለኤርትራ ምን ማለት እንደሆነ ባይገባቸውም፤ ስደት ፤ባርነትና ሞት “እንደ ነፃነት” የሚያጣጥሙ ሕዝቦች በዓለም ውስጥ ኤርትራኖች በቻ ሆነው ስንመለከት እጅግ አስገራሚ ነው።
የሳሕል ተራራ “ጋንግሰተሮች” የሚንደላቀቁባት ምድር ኤርትራ በሚያሳዝን ሁኔታ “በዕልልታ የተቀበላቸውን ሕዝብ” ባርያቸው አድርገው የተቃዋሚ ኤርትራን ሬሳ ወደ አገር እንዳይገባ በማገድ፤ ሲያሻቸው፤ መግረፍ፤ ሲፈልጉ ዶክተሮችን “በኤይድ ቫይረስ” ወግቶ መበከልን ኤርትራኖች ራሳቸው የሚዘገቡዋቸው ዜናዎችን ስንመለከት፤ እውነትም የነፃነት ትርጉም “ኤርትራኖች ዘንድ ስትደርስ ትርጉም የላትም”።
በሕዝቡ ላይ “የመናገር ነፃንትን መንፈግ ፤የስደት፤የሞትና የፍርሃት” ቀንበር የጫኑበትን “የሳህል ጋንግስተሮች” የነፃነት ቀን ብለው “ኤርትራኖች” የገዢዎቻቸውን “የነጻነት ቀን” የነፃነታችን ቀን ነው ብለው እየጨፈሩ መመልከት እውነትም “ባሮች ጌቶቻቸው ሲታመሙ የሚታመሙ፤ ሲጨፍሩ አብረው የሚጨፍሩ፤ ሲስቁ አብረው የሚስቁ” አዳዲስ ባሮች በምድር ይከሰታሉ ተብሎ በትንቢት የተነገረው በኤርትራኖች ላይ አየነው።
የሚያሰዛነው
ግን ዳግም ላንመለስሽ ብለው “ድንጋይ” ወርውረውባት “የሰደቡዋትን” ፤ “ያወገዝዋትን” ኢትዮጵያ “እግርዋ ላይ ወድቀው ተሳልመው፤ጥገኝነት
ስጪን” ብለው ገብተው እንደገና አንመለስብሽም ባልዋት ምድር አዲስ አባባ ውስጥ “አህያ” እያሉ ኤርትራ ውስጥ ከጨፈጨፍዋቸው የአማራዎች
የጉራጌዎች፤የኦሮሞዎች፤ የጋምቤላዎች የጋሞዎች ፤የሶማሊ…አገር መዲና አዲስ አባባ ላይ ሲጨፍሩ ማየት ለኛ ኢትዮጵያዊያን “ሞትና
ውርደት” እንደሆነ ተሰምቶኛል።
ዳሩ ግን እነሱ ምን ያድርጉ? አብይና ወያኔ እስካሉ ድረስ “በአህዮች አገር” እንዲጨፍሩ ተፈቅዶላቸዋልና ነፃ በሚሊዋት ነፃ ኤርትራቸው ውስጥ ያልተፈቀደላቸው ነፃነት አዲስ አበባ ውስጥ አገኙዋት! “በሞኞች መንደር ቀምበር ይቆረጣል” ይባል የለ!
“Wherever there is an ignorant mass, you will see a flag of
an ignorant leader fluctuating with glory!” “መሃይም ሕዝብ ባለበት ቦታ ሁሉ የመሃይም መሪ ባንዲራ በክብር ሲውለበለብ ይታያል!”
( መህመት ሙራት ኢልዳን)
እውነት ነው። መሃይም ሕዝብ ባለበት አዲስ አበባ ውስጥ ፤ያውም የባሕር በራችን የዘጋንን የመሃይም መሪ ባንዲራ በክብር ሲውለበለብ ከማየት የሚያም ነገር የለም !”
ኤርትራ የሞተችበት ቀን አክብራለች! እንኳን የሞታችሁበት፤ ለስደት የዳረገቻችሁ ነፃነታችሁ ቀን አደረሳችሁ! ለእኛ ግን የተዋረድንበት፤ እናንተም ተሰድዳችሁ የምትጨፍሩባት ኢትዮጵያ በማግኘታችሁ “ከመሞት መሰንበት” ይሉታል ነፃነት ማለት ይህ ነው። ኢትዮጵያ ሆይ “የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የተባለው ለካ ለእንደዚህ አይነትም ነው።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment