ሽልማት ሲሸለም አማርኛ ላለመናገር የተጸየፈ የኮካ ኮላው ትውልድ
እና
ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ጉልበት በማጠፍ ንቀት ያሳዩ የወያኔ ጋሪ ጎታች ፈረሶች
ጌታቸው ረዳ
(Ethio Semay)
በአሜሪካ አገር ሕገመንግሥት
36 አንቀጽ 301” (36 U.S. Code § 301) ብሔራዊ መዝሙርን እና ሰንደቃላማን በሚመለከት የከዋክብት ባንዲራ’ (Star-Spangled Banner) በመባል የሚታወቀው ስያሜ (Designation)
ቃላቶችንና እና መሳጭ የዜማ ጥንቅር የያዘ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር እና ብሔራዊ ሰንደቃላማ
ሲወጣም ሲወርድም ዜጎች (በርጌሶችና ወታደሮች) ማሳየት ያለባቸው ስነምግባሮችና ግዴታዎች ተደንግጓል።
ኢትዮጵያ እንደ አሜሪካ አገር
አንድ ወጥ የሆነ ቋሚ መዝሙርና ሰንደቃላማ ባይኖራትም መሪዎች ሲለዋወጡ የራሳቸው መዝሙር እየቀረጹ ሕዝቡን ሲያስዘምሩት ሰንደቃላማዋንም
እንደግል ንብረታቸው ያሻቸውን ምልክት የሚያኖሩባት ኢትዮጵያም አሳዛኝ ድርጊት ቢፈጸምባትም ለክብርዋ “መለያ” ተብሎ የተቀረጸ መዝሙርና
ሰንደቅ አላማ አላት።
በዚህ ሳምንት ውስጥ ይህንን በሚመለከት በመናበብ የተቀናጀ አገራዊ ጠል የሆኑ
ከትግራይ ክ/ሃገር የተወለዱ ወጣት የኪነት ሰዎች እና ከአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ አያሌ የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛነትን
ክብር ሳይሰጡ “በትግራይ ሕዝብ ሽፋን” ለወያኔ ፍቅር ወድቀው ኢትዮጵያ ያነጠፈችላቸው የክብር ምንጣፍ ሲጸየፉት አይተናል። በተለይ
የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎቹ በሕዝብና በሽማግሌ ወላጆች ፊት ለፊት ተቀምጠው ጉልበታቸውን በማጠፍ ያሳዩት ብልግና እየኖሩባት ያለቺው
አገር የምትከተለው ስነ ምግባር ውጭ ነው።
ወያኔ ባለፉት አርባ አምሰት
ዓመታት የፈጠረውን አዲስ የትግራይ ማህበረሰብ አመለካከታቸውም ሆነ ስነ ምግባራቸው ጨርሶ
ከኢትዮጵያዊነት ውጭ መሆናችወ ያየንበት ሌላኛው አጋጣሚ ነው ። ይህ በአዲስ የፋሽስት አስተሳሰብ የተቀረጸው
አዲስዩ የትግራይ ማህበረሰብ በርካታ አባሎቹ እንደ ሰው የሚገልጻቸውን በጥልቅ የማሰብና የማመዛዘን ክህሎት እንዳጡ ያሳየናል። ብዙዎቹ በትግራይ የኪነት ሰዎች የሚዘፈኑና
የሚተወኑ ትወናዎች በተለይ ደግሞ ዘፈኖቻቸው ስናደምጣቸው በአክራሪ ብሄረተኛነት የተለከፉ ያንድ ጎሳ አባሎች ህሊናቸውን ስተው አዙሮ
ማየትና ራሳቸውን መመልከት እንደተሳናቸው በተለያ ጊዜ ገልጸናል።
ይህ የህሊና መታወር በብዙ ሚሊዮን
የሚቆጠሩትን የትግራይ ማህበረሰብ አባሎች ባንድ መሪ ድርጅት፤ ባንድ ባለ “ራእይ መሪ” እየተመሩ በጭፍን ወደ ገደል እንዲገቡ ያደርጋል።
የጣሊያን ፋሽስቶች “ጣሊያናዊ መሆን ማለት ፋሽስት መሆን ነው፤ ፋሽስት መሆን ደግሞ ሙሉ ሰው መሆን ነው” የሚል መፈክር ነበራቸው።ይህ
ዛሬ ወያኔዎች “ወያኔ ማለት ትግራይ ማለት ነው፤ ትግራይ ማለት ደግሞ የክብር፤ የሞገስ፤ የጀግንነት፤ የአዋቂነት ወዘተ ምልክት
ነው” እያሉ ከሚኩራሩበት መፈክራቸው ጋር ይመሰላል። (ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ አምስተርዳም ኗሪ)
ሰሞኑን የታዘብናቸው የሕሊና መታወር ምልክቶቻቸውን እንመልከት
1) ኤሊያስ ታደሰ (ተዋናይ)
2) ሰላም ተስፋይ (ተዋናይት)
3) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ሰሞኑን የተመረቁ የግራይ ተወላጆች፤ (በቁጥር 9)
ኤሊያስ ታደሰ፡
ኤልያስ የተባለ ወጣት ዘፋኝ ይሁን ተዋናይ በቅጡ ባላወቀውም ከዜናው ተዋናይ እንደሆነ
ተረድቻለሁ። እንደ ዜናው መሰረት “ጉማ” በመባል የሚታወቀው አጭር
ፊልም በተዋናይነት በአበራታች መርሃ ግብር ሽልማት ሲበረከትለት ለአመስጋኞቹ እና ትግርኛ ማድመጥ ለማይችል ከመቶ ሚሊዮን በላይ
የያዘ የኢትዮጵያ የራዲዮና የቴ/ቪዥን ተመልካች ሕዝብ ንቀቱን ለመግለጽ በትግርኛ የተናገረውን ንግግር ላስነብባችሁ። (ከስር የአማርኛ
ትርጉሙን ይመልከቱ)
ትግርኛ፦
" ኣደይ ደም እናነብዐት፣
ሓወይ ተቐቲሉ ናብ ገደል እናተወርወረ፣ ሓፍተይ እናተደፈረት በዚ ሽልማት እዙይ ክሕጎስ ኣይክእልን። ዓደይ ናብቲ እነበረቶ ክብራ
ክትምለስ ከላ ክሕጎስ እየ:: (ኤልያስ ታደሰ)
አማርኛ፦
"እናቴ ደም ዕምባ እያለቀሰች ፣ ወንድሜ ተረሽኖ
ከገደል አፋፍ ላይ እየተገፈተረ ፣ ክብርዋን የጠበቀች እህቴ በቆሻሾች እየተደፈረች በዚ ሽልማት ልደሰት አልችልም። የእናቴ እንባ ሲታበስ
ሃገሬ ወደ ነበረ ክብሯ ስትመለስ ደስተኛ እሆናለሁ እደርስበታለው። ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን።" (ኤልያስ ታደሰ - ጉማ በተሰኘ አጭር ሲኔማ ተሸላሚ)
ይህ ወጣት የተጋበዘበት መድረክ
ለመቶ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያ ሕዝብ በመገናኛ ዘዴ በሚተላለፍ መድረክ ነው። እየተኮላተፈም ቢሆን አማርኛ እንጂ ትግርኛ የሚችል አድማጭ ከ104 ሚሊዮን ሕዝብ ምናልባት
4 ሚሊዮን ትግርኛ ተናጋሪ የትግራይ ሕዝብ ብቻ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። ታድያ የመልእክቱ እውነታ ከላይ እንደተተረጎመው ከሆነ
ልጁ በሽፋን ሰበብ ተጠቅሞ እንደ አስተማሪዎቹ ለአማርኛና ለአማራ ያለው ጥላቻ ለመግለጽ ‘ሆን ብሎ’ ከቤቱ ተመክሮ አመካክሮ ተዘጋጅቶበት
የመጣ ክፋት ነው።
“አገሬ ክብሯ ሲመለስ” ብሎ ሲል “ስለ የትኛዋ አገሩ ነው ክብርዋ ሲመለስ እያለ ያለው?” ኢትዮጵያን ማለቱ ከሆነ 27+3 በጠቅላላ 30 አመት በወያኔና በኦሮሙማው ኦነግ/ብልጽግና
የነበረው ክብሯ ተነጥቆ የውርደት ውርደት ማቅ ከለበሰች ከወጣቱ ዕድሜ በላይ አስቆጥራለች። 27 አመትስ አንገቱ ላይ ወያኔ እና ሻዕቢያ “ኩሹኽ” ብለው የሚጠሩት አፋሮች ወገባቸው በታች የመያገለድሙት ወያኔ ግን ለብርድና የሽምቅ
ተዋጊነት ማሳያ የሚጠቀምበት ስስ የአንገት “ጨርቅ” ጠምጥሞ በዩቱብ ላይ መታየቱ ስለቀረበት ነበር ያንን እንደ ክብር የቆጠረው?
የሚገርመው ነገር፤ ይህ አሰመሳይ ተዋናይ በተበረከተለት ሽልማት ‘ልደሰት
አልችልም’ ካለ የተቀበለው ሽልማት ለምን አልቀበልም ብሎ ልክ እንደ አመሳያው ‘ሰለማዊት ተስፋይ’ እቤቱ ቁጭ አይለም ነበር? ያቺ
ዋንጫም አጓጓቺው፤ ያቺ ለአማርኛ ያለው ጥላቻውም ለመግለጽ ደግሞ ዕድል እንዳታመልጠው ምቹ መድረክ አገኛና መጥቶ ተጠቀመባት። አዲስ አባባ መኖር
እንዴት አራዳነት ያስተምራል አንባቢ ሆይ!? ያውም እኮ ወዳጄ ይነጋል በላቸው ባንድ ወቅት እንደጻፈው (እኔም በመጽሐፌ እንደጠቀስኩለት) “ክርስቶስ፤- ‘ሁለት
ባላችሁበት ሦስተኛ እኔ አለሁ’ እንዳለው አዲስ አበባ አሥር ሰው ካየህ ያለ ማጋነን ሦስትና አራቱ ትግሬዎች ናቸው፡፡” ያለውን
ሳስታውስ ‘ኤሊያስ ታደሰም’ ዋንጫውን ወደ ኪሱ አስገባና በዚያው ለውጥ ትግርኛን በድምጽ ማጉያው አንቆረቆረላቸው። ከዚህ የበለጠ
አራዳነት የት ይገኛል!?
ሰላም ተስፋይ
ጥንት የጎንደር ክ/ሃገር የነበረው
የሑመራ/ወልቃይቴ ትውልድ አላት የሚሏት ሓረር የተወለደች በተዋናይነት አውቅና አላት የምትባል “በወቅቱ
አጠራር” “የጁንታው አወዳሽ” የሆነች ሌላዋ ጉደኛ ሴት ነች። የዚች ልጅ ውሸት ልዩ ታርጋ ተለጥፎላታል። የውሸት
መረጃ ካሰራጨቺው አንዱ ከብዙ አማታት በፊት በባድመ ጦርነት ጊዜ የፈረሰ ያውም ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ የተባለ አንድ የፈራረሰ ቤተክርሰትያን
ህንጻ የኢትዮጵያ ወታደሮች አፈረሱት ብላ አምሰት መቶ ሺሕ ተከታይ ያላት የሚባልላት ‘ኢንስታግራምዋ፤ ላይ በመልቀቅ የሃሰት ዜና
በማሰራጨትዋ ብዙ ሰው ሲጮህባት ፎቶውን አንስታዋለች። ፎቶግራፉ ብታነሳውም፤ ይቅርታ ግን አልጠየቀቺም። ለምን አትበሉኝ?” በትዕቢት የተወጠረ የወያነ
ጀሌ የይቅርታ ትርጉም አያውቅም። ያልተማረቺው ከየት ታምጣው?
ዛሬ ደግሞ እንዲህ ትላለች፤
"ሕዝቤ በጠላት አሰቃቂ ጭፍጨፋ፤ አስገድዶ መድፈር ፤ ዘረፋና ውድመት እየደረሰበት ፤ እኔ ልደሰት አልችልም።" በማለት ከተዘጋጀላት ትልቅ የእውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ላይ እንደማትሳተፍ እቤትዋ የተቀመጠች ተዋናይ ነች።
3) ከአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን የተመረቁ የግራይ ተወላጆች፤
ወያኔ የገጠመው የገዛ እራሳቸው መዝሙሩን መስማት ከካስጠላቸው (የገዛ እራሳቸው መዝሙሩ ስለጠሉት ግን አይደለም) ያም ቢሆን በምትኩ ለሕዝብ ክብር ሲሉ “የሕሊና ፀሎት” እንዲያደርጉና ሕዝቡ አብሮ እንዲጸልይ ጥያቄ በማድረግ ቅሬታቸውን ማስሰማት ሲችሉ ጭራሽኑ በበልግና እገራቸውን ወደ
ጉልበታቸው አጥፈው የንቀታቸውና የብልግናቸው መጠን ለማሳየት ሩቅ ተሻግረዋል። አንድ ምሁር በአገሬው በሽማግሌዎችና በወላጆች ፊት
አስጸያፊና ነውር ከተገቢና ከደምብ ለይቶ ካላወቀ ምን ትምህርት ተምረው እንደተመረቁ አላውቅም። የትግራይ ሕዝብ ግፍ ተፈጽሞበታል
ካሉ ለትግራይ ሕዝብ የሕሊና ጸሎት እንዲደረግ ለምን መጠየቅ አልቻሉም? ስላልተማሩ ወይንስ የፖለቲካ ተልእኮ ስላላቸው? ለመሆኑ ላቡን አንጠፍጥፎ ግብር ከፍሎ ያስተማራቸው ሕዝብ ፊት ተቀምጠው ጉልበት አጥኦ ንቀት ማሳይት ምን እሚሉት ፖለቲካ ነው?
የኮካ ኮላው ትውልዶች፤
እነኚህ ወጣቶች ወያኔ ከተፈጠረ
ወዲህ በቅርብ ጊዜ የተወለዱ በወያኔ ሥርዓተ ትምህርት ተኮትኩተው ያደጉ፤ “ወጋሕ ትበል ለይቲ” (ሌሊቱ እስኪነጋ) በመባል የሚታወቀው
የወያኔ “ቶክሲክ” (መርዛማ) ዘፈኖችን እየተዘፈነላቸው በየዳንስ ቤቱና በዓላት ዳንኪራ ሲመቱ ሌሊት ሙሉ እልልታ ሲያቀልጡ እራሳቸውን
አመርቅነው ሌላውን የሚያሳብዱ ዳንኪራ አስመቺና ዳንኪራ መቺ ሆነው “ኢትዮጵያን እንዲጠሉ” ተደርገው የተቀረጹ በጣፋጭ መጠጥና ምግብ
አቀናጥቶ ወያኔ በልኩ መጥኖ የቀረጻቸው አዲስ አባባ ከተማ
ያደጉ የኮካ ኮላ ዘመን ቅምጥል ትውልዶች ናቸው።
አየደረሰበት ስላለው ስለ ኢትዮጵያዊው ግፍስ ከመናገር ሆድ ይፍጀው እንበልና
፤ የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ ንብረቱ ያልተነጠቀ፤ ያልተደፈረ፤ያልተጨፈጨፈ፤ያልታሰረና ያልተደበደበ አስመስለው እኔ እና መሰሎቼ
ወደ ትውልድ አገራችን እንዳንገባ አግደውን ፤ ክብራችን ሲነጠቅ አይተው እንዳላዩ “ሲጨፍሩ” የነበሩ ዛሬ ከ27 አመት በሗላ ወያኔ
“በራሱ ጅራፍ ሲገረፍ” በማየታቸው ልባቸው ተሰብሮ ማዘናቸው እንጂ ስለ የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ ወያኔን እንዴት ነፃ ሊያደርጉት ይቻላቸዋል?
በስልኮቻቸው ፣ በኮምፒዩተሮቻቸው
፣ በአይፓዶቻቸው በትግራዋይነት ሰንሰለት የታሰሩ ያልተረጋጉ እነዚህ የኮካ ኮላ ትውልዶች የኢትዮጵያን ሰንደቅአላማና ብሔራዊ መዝሙር
(ብሔራዊ መዝሙሩም ወያኔ የገጠመው ቢሆንም) ‘አናውለበልብም፤አንቆምም፤አንነሳም’ የሚሉ የወያኔ ጫጩቶች መሆናቸው እንዴት ልንስታቸው ይቻለናል? ኢትዮጵያ ምድር ያውም አዲስ አበባ ውስጥ እየኖሩ “ኢትዮጵያ
አይደለንም” የሚሉ የባይቶና ፓርቲ “ዕብዶችም” እኮ መረን የጣሰው ድፍረታቸውን እኮ በቴ/ቪዥን
አስድምጠውናል።
ስለ ሰንቱ ደፋር የፋሺሰት ጫጩቶች ብለን እናውጋው! ዕድሜ ለአብይ አሕመድ፤ አንኳን “ትግራዋይ” እንጂ “ኢትዮጵያ እኔን አትመጥነኝም አትወክለኝም” ማለት
፤ የሰው ልጅ
ማረድም የሰው ልጅ ገድሎም የሰው ሥጋ መብላትንም ጭምር “የዲሞክራሲ አንዱ መገለጫ ነው” ብሎን የለ!? አበይ አሕመድ የነገርን
እኮ---እነዚህም እስራል አገር አንዳሉት ዓረብ ነን የሚሉ አንዳንድ የእስራሎቹ አክራሪ የክነሴት የፓርላማ
አባለት “ጥግ” እንዲቀመጡ አዲስ አበባ ፓርላማም
ወንበር ተፈቅዶላቸው የሰው ስጋ መብላት “መብት ነው” ለማትም መብታቸው ነውና እፈቅድላቸዋለሁ፤ሃሳብ አይታገደም ብሎናል እኮ “አስራለቃ አብይ አሕመድ”?
እነዚህ ወጣቶች ባለፉት ዕድሜአቸው
ውስጥ (27) አመት በሚያወድሱት በወያነ ስርዓት እና 3 አመት ‘በኦሮሙማው የአብይ አሕመድ ኦነጋዊ ሥርዓት’ በአማራ ማሕበረሰብ
ላይ የዘር ጭፍጨፋ ሲፈጸም እንደ ምሁር ወጣትነታቸውም ሆነ እንደ የኪነት አባልነታቸው አያውቁም ነበር ብሎ የሚከራከር ፍጡር አይኖርም።
ታዲያ እንደዛሬው ለትግራይ እንደተቆረቆሩት ሁሉ ለምን ያኔ አማራና ሌሎች ነገዶች ስቃይ ሲፈጸምባቸው አልከነከናቸውም ነበር? የሚል
ነው ሕዝቡ እየጠየቃቸው ያለው። እነሱም ሆኑ ሌሎቻችን የማንክደው ምክንያታቸው “በሕዝብ ጀርባ” “ለወያኔ” ማልቀስ ስለፈለጉ ነው።
አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከሰንደቃላማችን ጋር ጸብ ነበረው፤ ዛሬም “የመለስ ጫጩቶች” ፀባቸው ከሰንደቃላማችን ጋር
ነው።45 አመት የተረጨው “መርዝ” ለማጽዳት ሌላ 45 አመት የህሊና አጠባ ሊፈጅ ነው። ፈረንጆች እንደሚሉት It’s a cycle that goes on and on የበሽታው አገርሺነት እየቀጠለ የሚሄድ ዑደት ነው። የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ተነስቶ ይጥላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው እያልን ለማስረዳት
ስንደክም የነበረውም ይህ ክስተት እንደሚከሰት ስለምናውቅ ነው።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment