Wednesday, March 17, 2021

የትግራይ ሕዝብ በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ? ስለ ማኒፌስቶ ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ጥያቄ ማብራሪያ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay March 17, 20213

 

 

የትግራይ ሕዝብ በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ?

ስለ ማኒፌስቶ ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ጥያቄ ማብራሪያ

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

March 17, 20213



ካለፈው የ ማኒፌስቶ 11 ትግራይ አገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ጥያቄ የሚለው የትግራይ ተገንጣዮች ‘የትግርኛ ማኒፌስቶ’ ትርጉም ሰሞኑን የምቀጥልበት ሲሆን ለዛሬ ስለ ማኒፌስቶው አንዳንድ ማብራሪያዎችን ባጭሩ አቀርባለሁ።

ወደ ማብራሪያው ከመግባቴ በፊት ይህ ከታች ያለው ማሳሰቢያ ለማስተላለፈው እወዳለሁ።

እባክዎትን አንድ ወንድም (ስምዎን ሰለረሳሁት ይቅርታ) አንዲት እህት ስለ አማራ ያደረግኩትን የአመታት ትግል ለማመስገን እንድታመሰግነኝ ፈልጋ ፈቃደኛነቴን ጠይቀውኝ ስልክዋን ሰጥተውኝ ነበር። ሆኖም ድንገት የእርስዎ “የፌስ ቡክ/መሰንጀር” ሰምም ይሁን የዛች እህት ስልክና ስም ስለዘነጋሁት እባክዎትን እንደገና በመሰንጀር ይጻፉልኝ። በብዙ መንገድ ስለምጠመድ ብዙ ጊዜ ብዙ ወዳጆችን የመርሳት ነገር ይታየኛልና ለብዙዎቻችሁ መልስ ባለመስጠቴ ይቅርታ። አመሰግናለሁ።

ሁለተኛው ማሳሰቢያ፤-

ጊዜየን መስዋዕት በማድረግ ትግሬዎች በቋንቋቸው ምን እያሉ እንዳሉ ትግርኛ ለማታውቁ ሰዎች በመተርጎም የምለጥፋቸው ጠቃሚ ሰነዶችን በብዛት ተሰራጭቶ ለሕዝብ እንዲዳረስ ላደረጋችሁ ታታሪ ዜጎች ምስጋና ይድረሳችሁ። 5000 የፌስቡክ ወዳጅ አለኝ፤ የሚገረመኝ ግን ከነዚህ 5000 ውስጥ ቢበዛ ከ30 እና 40 ሰዎች “ሼር” አያደርጉም። የትግሉ ስንፍና ለምን እንደተጠቃን ማሳያ መሆኑን ጥሩ ማስረጃ ነው። ጠላት ምን እንደሚል ካላወቅን በሃሳብ ተጠቂዎች ነን።፡ሼር ለምታደርጉ ዜጎች ጥረታችንን በመካፈላችሁ እጅግ አመሰግናለሁ።

ከብዙ ወራት በፊት ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ ላይ “አገር ያቀፈቻቸው ብዙሃን ሕዝቦችዋ ደናቁርት እስከሆኑ ድረስ የሰቆቃው ህይወት ማቆሚያ ሳይኖሮው አንዱ ‘ሲያባራ’ ሌላው ‘ይቀጥላል!’ (ጌታቸው ረዳ)” በሚል ርዕስ በጻፍኩት ጽሑፍ “ወጣቱ ቱርካዊው ““መሕመት ሙራት ኢልዳን” “የተባለው ፈላስፋ እንዲህ ሲል የገለጸውን ጠቅሼ ነበር፡

” በአንድ ወቅት ሚሊዮኖች ለአዶልፍ ሂትለር አድናቆት አሳይተዋል፤ እንዲሁም ደግፈዋል ፡፡ አላዋቂ የሆኑት ብዙሃኑ ብዙውን ጊዜ ቀላል እውነቶችን ማየት አይችሉም ፣ እና በግልጽም ግልጽ የሆኑትን ጫፎች የማየት ችሎታ የላቸውም! የታወቁት የብዙዎች ሞኝነት በታሪክ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጊዜያት ተረጋግጧል! እያንዳንዱን ጊዜ የተሳሳተውን መሪ ሲከተሉ በመጨረሻ ላይ እራሳቸውን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በሆነው የመዋኛ ገንዳ ተዘፍቀው ያገኙታል!” በማለት ገልጾ መኖሩን ጠቅሼ ነበር። እነሆ ለ27 አመት አላዋቂነቱን ያረጋገጠልን ብዙሃኑ ‘ማሕበረሰብ ትግራይ’ የተሳሳቱትን የትግራይ ሊሂቃን ሲከተል ቆይቶ፤ ዛሬ በመጨረሻ ሰዓት እራሳቸውን ባልገመቱት ቦታ አግኘተውት ለስቃይ እነሆ ተዳርገዋል።

 ለዚህ የጭለማ ህይወትና ስደት የዳረጋቸው የትግሬ ምሁራን በዘረጉት ትምክህት የማሕበረሰብን አነድነትና የተረጋጋ ህይወት የሚያደፈርስ ‘ፋሺስታዊ ማኒፌስቶ’ በመቀበላቸው ሰበብ እንደሆነ ብዙዎች ባትቀበሉትም እውነታው “የነገድ ፖለቲካ አስተማሪዎቻቸውን በማምለካቸው” ነው። እነሆ ዛሬ መራራው አማራጭ ከፊታቸው ተደቅኗል።

አማራጩም አንደኛው ለ45 አመት የተዘረጋው የፋሺዝም አምልኮ ከነ አካቴው መቃወምና ሊሂቃኖቹ በትግራይ ማሕበረሰብና በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸሙት የረዢም ጊዜ ወንጀል ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡና የተረጋጋ ኑሮ መመስረት፤ ካልሆነ ደግሞ ሞትን፤ርሃብን፤ስደትን እና እሪታን እያስተናገዱ የፈረሰ ማሕበረሰብ ሆኖ የሽምቅ ተዋጊ ሽብርተኛ ሃይሎች አገልጋይ ሆኖ አማራጭ ያልሆነ አማራጭን ይዞ መቀጠል።

ባለፈው ክፍል 2 ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም ሦስት ነጥቦችን ሳትገነዘቡዋቸው እንዳታልፏቸው የምፈልጋቸው ነጠይቦችን ላስታውሳችሁ፤

ማኒፌሰቶው የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን ጥሎ ሌላ አገር መመስረት እንዳለበት ምክንያት የሰጣቸው ነጥቦች

ቀዳሚው-

 ኢትዮጵያ አማራ የተባለ ማሕበረሰብ የገነባት ስለሆነች ለአማራው እንጂ ለትግሬዎች ስለማትመች ያትታል፡-

ሁለተኛው ፦-

ትግራይ በብዛት 6 ሚሊዮን ሕዝብ ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዛት ካላቸው ማሕበረሰቦች/ነገዶች/ ጋር በዲሞክራሲያዊ ድምጽ ለሥልጣን ቢወዳደር ደምጹ አነስተኛ ስለሚሆን “የአዛዥና ናዛዥነት” ሥልጣን ዳግም እንደማያገኝ ፤

ሦስተኛው ፦

ምክንያት ደግሞ አናሳ ከሚባሉት ነገዶች ግምባር ፈጥሮ ለዲሞክራሲ ቢወዳደርም አናሳ የሚባሉት ማሕበረሰቦች የማይታመኑ ስለሆኑ ውሎ አድሮ ከሥልጣን ተጋሪነት ስለሚወገዱ የራሳቸው አገር መመስረት እንዳለባቸው ያትታል። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለባችሁ፤ ትግሬዎች ተገንጥለው አገር ሲመሰርቱ ቀደም ብሎ ማኒፌስቶው እንደገለጸው “ትግራይ ውስጥ በሕዝብ ብዛት ትግርኛ ተናጋሪው ትግሬ” ስለሆነ አናሳ የተባሉት ትግራይ ውስጥ ያሉት ነገዶችን አሸንፈን የበላይነት በማረጋገጥ (የራሱን ቃል ልጠቀም -------“መሬታችን ላይ እንደፈለግነው” ማስተዳዳደር ስለምንችል፤ መገንጠል አማራጫችን ነው” በማለት ነው ‘ሁሌም’ ትግሬዎች “የበላይነት” በመፈለግ በፋሽታዊ ባሕሪውና መነሻው “ገዢ” የመሆን ፍላጎቱን በግልጽ መቀጠል እንዳለበት የገለጸው።                                                                               

ለዚህ ነው ትግሬዎች ካልገዙዋት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብለው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጫካ የወጡት።ወጣም ወረደ ትግሬዎች 27 አመት እንደፈለጋቸው ሲገዙ ሲመዘብሩና ሲገድሉ የነበረውን የግዛት ዘመን ሲያበቃ ሥልጣን ለዘላአለም ከትግሬ ካልቆየ አገሪቷን በትነን ሌሎቹን አናሳ የትግራይ ነገዶችን እንደፈለግን የምናደርጋቸው ተገዢዎችን ፈጥረን የበላይነት ዘላቂ ፍላጎታችንን ማረጋገጥ እንችላለን በማለት ከትግራይ እስከ ኤርትራ ለመዘርጋት ያቀዱትን የበላይነት ፍላጎት ብግልጽ ባለፉት ክፍል 1 እና 2 አይታችሗል።

ዛሬ እኔ የተወለድኩበት የትግሬ ነገድ የመገንጠል ፍላጎታቸው በተግባር እያሳዩን ስለሆነ ከ 34 አመት በፊት በጉልበት ወደ ትግራይ ያጠቃለሉትን የወልቃይት፤ሰቲት ሁመራ ፤ ጸገዴ ወዘተ…… ትልቅ መሬትና ሕዝብ የአማራ ነገድም ሆነ በነዚህ መሬቶች የሚኖሩ ሌሎች ነገዶች በምንም መልኩ እንደገና ትግሬዎች ሊወስዱት መፍቀድ እንደሌለበት በአጽንኦት የማሳስበው። ዛሬ የብዙዎቹ የትግሬዎች ጥያቄና ፍላጎት ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያና የመን አፍርሶ ትግራይን እንደ አገር ለመመስረት ከሆነ (እንኳን እና አገር እያፈረሱ አማራውን በዘር ጽዳት ወንጀል የፈጁትን ወንጀል እንዳለ ሆኖ፤ ትግሬዎች በሰላም አንድነትን ቢመርጡም በሕግና በታሪክ ዓይን እነዚህ ቦታዎች የትግሬዎች አይደሉም- ይህ እውነት ነው።) ፤ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው መሬቶች በፍጹም ወደ ተገንጣይ አገር አሳልፎ መስጠት የለበትም የምለውም ከሕጋዊ እና ታሪካዊ ብቻ ሳይሆን ማኒፌሰቶአቸው እንደሚያሳያው ትግራይን አገር ለማድረግ ከሆነ “ለአንድ ቀንም ቢሆን” እነዚህ ቦታዎች የትግራይን የምጣኔ ሃብትና የውጭ አገር መንገድ በር መክፈቻ አድርገው አማራውን ለመተናኮል ስለሚጠቀሙባቸው በነዚህ ቦታዎች የመስጠትና የመደራደር ነገር ዝግ መሆን አለበት። ማኒፌሰቶአቸውም ሆነ አሁን ጫካ ውስጥ ገብተውም ሆነ ተከታዮቻቸው ለኢትዮጵያ የሚመኙት ምኞት “ንቀትና ጥላቻ” አደጋው ለማንም ሰው ግልጽ ነው። 

ለትግራይ ምሁራንም ሆነ ተራው ማሕበረሰብ ማወቅ ያለበትና ላስተላልፈው የምፈልገው መልዕክት ወያኔ ኢትዮጵያችንን ለ27 አመት ሞት፤ ስደት፤ ውርደት፤ አመጽ፤ እንግልት፤ እስራት፤ ድብደባ፤ ጦርነት፤ ግድያ፤ ዘረፋ፤ ክሕደት፤ ግብረሰዶማዊ ዝሙት አገራችንን በተዘጋጀላት ሞገደኛ ማዕበል ውስጥ አስገብተው አሰቃይተዋታል። ትዕቢት ባሳበዳቸው ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ስሜት በራቃቸው ‘የቀወሱ የትግራይ ምሁራንና መሪ ድርጅታቸው ወያኔ) የሕዝባችን ሕይወት ዛሬም ሰግጠው ይዘውታል። እነዚህ ፋሺሰቶች 27 አመት ሙሉ ባዘጋጇቸው የጭለማ እስርቤቶች እርግብ ወጣት ሴቶችን መድፈር ሳያንሳቸው ተባዕትም ጭምር ደፍረዋል። አውላላ ሜዳ ላይ በቆሙ የኢትዮጵያ ሸበላ ወጣቶች ከሰማዩም ከፎቁም ጥይት በማዝነብ ቀጥፈዋቸዋል። ትግራይ ዛሬ በነዚህ ከሃዲዎች የኢያሪኮ ጩኸት የሚያበስር ‘ማንፌስቶ’ ይዘው ጫካ ገብተዋል። ታዲያ የትግራይ ሕዝብ በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ?

ማኒፌስቶ ክፍል 3 ከነገ ወዲያ ይለጠፋል ተከታተሉ……

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

No comments: