Monday, March 22, 2021

ክፍል 3 በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ ማኒፌስቶ 11 ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay March 22, 20213

 

ክፍል 3

በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ

ማኒፌስቶ 11

ትርጉም

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

March 22, 20213


ካለፈው ክፍል ሁለት የቀጠለ፤

ባለፈው ክፍል ሁለት እንደህ በሚል ክፍል ነበር በይደር የተውነው………  “የአጼ ዮሐንስ ሕልፈት በ19ነኛው ክ/ዘመን ማገባደጂያ የተፈጠረው ይህ የንጉሱ ሕልፈት ለኛ ለትግሬዎች “የዘመን መጠመዘዢያ ማኣዘን” (ተርኒንግ ፖይነት) ነበር።በዚህ አጋጣሚ እኛ በሕዝብ ብዛት በቁጥር የበላይነትን ይዘን ጂኦፖለቲካዊ የበላይነት ይዘን ማነጽ ልንችል የነበረቺውንና ለዓለማችን ፍላጎት የምትስማማ አገራችንን ከእጃችን ተነጥቀን ወደ ተንሳፈፈችና ጥገኛ ወደ ሆነቺው የአገር ትርጉም የሌላት አገር ለጠላቶቻችን የምትጥም ለኛ የማትጥም አገር የገባንበት የዘመን መጠምዘዣ መሆኑ ማሳያ ነበር በሚል ነበር ትርጉማችንን ያቆምነው። በዚህ ክፍል ትርጉም ሦስት እንዲህ ይቀጥላል፤

‘ትግርኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ትግሬ እና ኤርትራ’ ቅኝ ገዢ በሚላቸው ጣለያን እና አማራው መንግሥት ትግራይ እና ኤርትራ በማለት ለሁለት ከፍለው ሃይላችንን ለማዳከም ያደረጉት ሴራ ጎድቶናል። ለሁለት መከፈላችንን ሳያንስ ወደ ኤርትራ የተካተተው ግማሹ ብሔራችን ከኛ ጋር የማይስማማና ከኛው ራዕይ ጋር የሚጋጭ ተጻራሪ ሃይሎች ሆነው እንዲፈጠሩ የፈቀደ ሁኔታ ነው። ሆኖም በሌላ በኩል ስንመለከተው ሁኔታው እኛ ትግሬዎች በቁጥር የማነሳችን እና ለሁለት በመከፈላችን ያህል ጠንካራ ሃይል እና ታሪካዊ ሃያል ሕዝብ ሆነን እንድንወጣ አድርጎናል። ዛሬ ኤርትራ ውስጥ ያለው ክፍል በባዕድ ሥር በመገዛቱ ምክንያት ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን የባዕድ ኣስተሳሰብ ባሕሪ ይዞ የሚጓዝ ስለሆነ በውስጡ አንድ ብሔራዊ ሃይል እንዲፈጠር ሁኔታው ስለፈቀደ፤ ተቆርጦ ወደ ኢትዮጵያ የተጠቃለለው ትግራይ ውስጥ ያለው ሃይልም በትግራዋይ ብሔረተኛ እና በኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ ለሁለት ተከፍሎ ያልነጠረና የተከፋፈለ ሃሳብ ይዞ እንዲጓዝ “የዘመን መጠመዘዢያ ማኣዘን” (ተርኒንግ ፖይነት) ብለን የጠራነው የዮሓንስ በሞት መለየት ለዚህ ክስተት ተጋልጧል።

በአፄ ዮሐንስ ህልፈት ምክንያት ተከትሎ የተከሰተው አስከፊው ሰበብ ተጋሩ/ትግሬዎች/ በአማራ አገዛዝ ሥር ወድቀን የራሳችንን የነጠረ ዓላማ ይዘን እንዳንጓዝ ጥገኛ ሆነን እንድንኖር በር ከፍቷል። የራስ መተማንነትን ተነጥቀን ከሥልጣኔ ጉዞ ታግደን ወደ ኋላ እንድንቀር አድርጎናል። ትግራይ ድሃ ነች ብለው የሕዝባችን የራስ መተማመን ለማደከም ሲሉ ከ100 አመት በላይ ጥቃት ሲከፍቱብን እኛም ተቀበልነው። በራሳችን የተፈጥሮ ፀጋና በታሪክ  የወረስነው ሥልጣኔ በጽናት መጠበቅ ሲኖርብንና ለተሻለ ሕልም ከማለም ይልቅ ወደዚያች ብዙሃን ደናቁርትና ያልሰለጠኑ ሕዝቦች ወደ ያዘች አገር ተቀላቅለን ልክ እንደ እነሱ ወደ እንሳሳ እርባታና ለም መሬት ወደ እሚያተኩር አድሃሪ የሆነ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ውስጥ ገባን። ባጠቃላይ ተገቢ ሥፍራችን የነበረው መገኘት የነበርንበትን የሥልጣኔ እርከን ወርደን ካልሰለጠኑት ሕዝቦች ጋር በመቀላቀላችን ወደ ተምበርካኪነት ሕልውና ተጋለጥን።

ያም ሆኖ ከአፄው ሕልፈት በኋላ ወደ አማራዎች አገር በሃይል እንድትዋጥ የተደረገቺው ትግራይ በወቅቱ ከነበሩት መሳፍንቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ብሔራዊ ልም የተሸከሙ ቢኖሩም እርስ በርስ ባለመናበባቸው ምክንያት በጠላትነት በመፈላለግ ግጭት ውስጥ እየገቡ ብሔራዊ ሕልማቸው ሊያሳኩ አልቻሉም። ለ100 አመታት ሲቀጥል የነበረው አሁን ዛሬ ነጥሮ የመጣብን  አደጋ በወቅቱ ሊረዱት ስላልቻሉ ወይንም “ኢትዮጵያ-አገራችን” ወደ እሚሉት የተሳሳተ ብሔራዊ አስተሳሰብ ሰለባ ስለነበሩ ፤ በጊዜው እርምት ስላልተደረገበት “ትግራይ” ከዚያው የእሽክርክሪት ፖለቲካ ሰብራ ልትወጣ ባለመቻልዋ እዛው ሰምጣ ቀረች።

በወቅቱ በነበሩት በመሳፍንቶቹ ሕሊና የታየው የተጋሩ ብሔራዊ ስሜት ነጸብራቅ የጀመረው ፍንጣቂ ቆይቶ ደግሞ በወቅቱ ምሁራን በነበሩት በእነ ገብረህይወት ባይከዳኝ የመሳሰሉ ምሁራን ተጋሩ የቀጠለ ስሜት ነበር። ሆኖም እነዚህ የወቅቱ የትግራይ ምሁራን ትግራይን አገራዊ በባለቤትነትን ለማጎናጸፍ የሚል የነጠረ አስተሳሰብ ታጥቀው ሳይሆን “ኢትዮጵያ የኛ ናት” (“ኢትዮጵያ ናትና እያ”) ወደ እሚለው መፍትሔ ወደ ያላመጣው ትግል ገቡ።

ከጊዜ በኋላ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የያዘ ነበር ማለት በሚቻል ዓይነት ትግል አንገቦ ተነሳ። በቀዳማይ ወያነ የተነሳው እምቢተኛነት እንደቀደሙት ሁሉ ግልጽ ከሆነ የብሔራዊ ትግል ዓላማ የራቀ ነበር።  ቀዳማይ ወያኔ እንቅስቃሴ የገጠመው ጥቃት ዛሬ እንደታየው በስመ ዲሞክራሲ እኛን ወደ ትርጉም የለሽ ሁኔታ እንዳስገባን የተሰራበት ሴራ ሳይሆን፤ ደመኛችን (ጠላታችን) የሆነች አገር ኢትዮጵያ “የኛ” (“ናትና”) ናት ብሎ ነው የታገለው። በዚህ በተኮላሸው ያልነጠረ አስተሳሰብ ምክንያት የተነሳ “እንግሊዝ” ሁለቱ ትግሬዎች (ኤርትራና ትግራይ) ወደ አንድ አምጥቶ አንድ አገር ለመፍጠር የታቀደው የእንግሊዞች ዓላማ “በቀዳማይ ወያኔ መሪዎች ተቀባይነት ሊያገኝ ባለመቻሉ” ምስረታው ባጭር ተቀጨ። እንግሊዝም ለራሱ ጥቅም ሲል ከኃይለስላሴ ጋር በማበር ቀዳማይ ወያኔን ደመሰሰው።

በዚህ አጋጣሚ ‘ወላጆቻችን በቀዳማይ ወያኔ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ብለው ይህን ይህን እንዲህ እንዲህ የመሳሰሉ አኩሪ ትግል አደረጉ’ ብሎ በወላጆቹ ትግሬዎች ገድል የሚኮራ ቢኖረም ያም ተገቢ ቢሆንም በትግራዋይ ብሔራዊ ዓይን አገራዊ ምስረታ ስንመለከተው ግን ይህ አመለካከት ያለፈው ጠማማ የሆነው የትግራይ አገር ምስራታ ብሔራዊ ስሜት አሰናካይና ጠላፊ ስለሆነ መታረም አለበት።

ከቀዳማይ ወያኔ ውድቀት በኋላም ቢሆን የኛ የተባለቺው አገር…………..     ክፍል 4 ይቀጥላል…..

አመሰግናለሁ።

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

 

 

 

No comments: