ክፍል 2
በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር
የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ
ማኒፌስቶ 11
ትርጉም
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ) Ethio
Semay
March 14, 20213/
………. ካለፈው ክፍል 1 የቀጠለ ክፍል 2-
……..አንድ የነበረን ሕዝቦች ለሁለት ተከፍለን ከስትራተጂ መንገዳችንን
በማሰናከል የሕዝባችንን ቁጥር እንዲመናመን በማድረግ ትርጉም ወደሌላው ህይወት እንድንገባ ያደረገቺን የጠላቶቻችን አገር ነች (ኢትዮጵያ)
አሁን ኢትዮጵያ በምትባለዋ አገር ሆነን ጥያቄአችንን ልንመልስ እንችላለን
ብለን ላለፉት 27 አመታት የታየው ማሳያ ድሉ ያልመታ የተቃጠለ ተስፋ ነው። ማወቅ የነበረብን ኢትዮጵያዊያኖች በሕልምም ከኛ ጋር
የማይገናኙ ብቻ ሳይሆን እኛን ለመጉዳት ከሚያውጠነጥኑ በሕዝብ ቁጥር ብዛት ከሚበልጡን ጋር የተዳበልናት/የተቀላቀልናት/ አገር ናት።
27 አመት የቆየንበት ምስጢርም በስለላና በወታደራዊ መዋቅሮች ተጠቅመን የቆየንበት ምስጢር ካልሆነ በስተቀር ጠላቶቻችን እኛን ተቀብለው
የኛን ሃሳብ አምነውበት አብረን የኖርንበት ጊዜ አልነበረም። ለኛ
እንደምትመች አድርገን ስላልተጓዝን ያለፍንባቸው 27 አመታት ጉልበታችን አሟጥጠን ያሳየነው ጥረት ስህተተኛ መንገድ ነበር።
ኢትዮጵያ እኛ ፈለግናትም አልፈለግናትም ከአፈጣጠርዋ ትክክለኛ አፈጣጠር
ስላልነበረ ልትቀጥል ነው ወይስ አትቀጥልም ሌላ ጥያቄ ሆኖ ፤ትቀጥላለች ብንልም እንኳ ካለፉት 27 አመት የተለየ ኣከሄድ መሄድዋ
አይቀሬ ነው። እርግጥ አማራ እና ኦሮሞ በስም ዲሞክራሲ በሚደረገው የበላይነት መራኮት መጋጨታቸው አይቀርም። ሆኖም በዚህ አሰላለፍ
የሃይል ሚዛን አይተን ከኦሮሞ ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር እንደ ቁማር መጫወቻ ካርድ ይዘናቸው ‘መፍትሄ አድርገን ልንጠቀምባቸው’ እንችል
ይሆናል። ይቻላልም እንበልና እኛ 6 % ከመቶኛው 6 ደምጽ ይዘን የምናገኘው ውጤት እኩልነትን የሚሳይ ሳይሆን የነሱ ባርያና ተገዢ
ከመሆን አናመልጥም።
እነዚያ እንደ እኛዎቹ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ንኡሳን ብሔሮች የጋርዮሽ
ድምጽ ጣምራ በማድረግ ግምባር እንፍጠር ብለን እንወዳደር ብንልም እነዚህ አናሳ ብሔሮች ከኛ ከትግሬዎች ይልቅ ወደ ኦሮሞዎቹ መለጠፋቸው
አይቀሬ ነው። በነሱ ተማምነን የጋር ግምባር መፍጠር ዘላቂ መፍትሄ አይደለም። ይህንን ለማብራራት ትንሽ ዘርዘር ስናደርገው፤ እነዚህ
አናሳ ብሔሮች ቁጥራቸው ትንሽ ስለሆነ ውስጣዊ አንድነታቸው የላላ ስለሆነ ትንሽ ከተጓዙ በሗላ ስለሚፈርሱ የነሱ ድምጽ ለኛ ዘላቂነት
ያለው ትርጉም አይሰጥንም። ስለዚህ ምንም በድምጽ አናሸንፍም።
አናሳ የሚባሉት አስታማማኝ ጥመረት የማይሆኑበት ምክንያት ሌላው ለምሳሌ
ሶማሌን ብንወስድ ኢትዮጵያን ትተው የሚገነጠሉበት ዕድል የላቀ ስለሆነ ነው።በዛም ሆነ በዚህ ይህ ሁላ የገበጣ ጨዋታ ዕድላችንን
ከእጃችን አውጥተን ሌሎችን አምነን የምናደርገው ጨዋታ ስለሆነ ዋስትና ያለው የሕሊና እርጋታ አይሰጠንም። በዚህ ከቀጠልን የነጠረ
ብሔራዊ ዓላማ ይዘን ጥገኛ ሆነን እየንተሳፈፍን መኖር ብቻ ነው ማለት ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ባጭሩ እኛ እንደ ትግሬነታችን ኢትዮጵያ
ውስጥ ሆነን የምንገነባው መንግሥት አይኖርም። የመደራደሪያ ክርዶቻችን ስለተመናመኑ አሁን ያለው ዋስትና ይሆነናል ብለን የገነባነው
ሕገመንግሥታችንም ቢሆን በተቃራኒ ፍላጎታችን የሚጻረርበት ጊዜ ይመጣል። ስለሆነም 6 ሚሊዮን ድምጽ ይዘን ትርጉም ወደሌላው ጉልበት
ወርደን ታዛዦች እንጂ ወሳኞች ልንሆን አንችልም።
እነዚያ አሁን መንግሥትነት የተቆጣጠሩ ሃይሎች እንደ አማራው የከረረ ጥላቻ
በኛ ላይ የሌላቸው ቢሆንም፤ እየገነብዋት ያሉት ዓላማቸው “በኦሮሞዎቹ ምስል” የምትታነጽ ኢትዮጵያ ስለሆነ፤ ውሎ አድሮ እኛም የነሱ
ባርያዎች መሆናችን አይቀሬ ነው። የፋይናንስና ንግዶች በነሱ ቁጥጥር ስለሚውሉ ጸረ ትግሬ መሆናቸው አይቀርም። አብረው የሚዳበሉዋቸው
ጠላቶቻችንም ትግራይ ውስጥ የሚረባ ፕሮጀክት እንዳይታነጽ መስራታቸው የማይቀር ነው። አጣቃላይ ውጤቱ ትግራይ ወደ አመድነት መቀየርዋ
ነው። ይህንን እንግባበት ወይንስ ያ አይቀሬው ብሔራዊ “አገረ መንግሥት ትግራይ” ወደ ግንባታ ትግላችን እንግባ?
()- ብሔራዊ ዓላማችን የኛ አገር ምስረታ ባለቤትነት እውን ማድረግ ወይስ
ባርነትን አንምረጥ?
ቀደም ብሎ እንደተገለጸው እኛ ትግሬዎች
የገነባነው ባህልና ስልጡን ስነልቦና አለን። ይህ ማንነታችን የምንሞትለት ብቻ ሳይሆን ቁጡ ጠንካራ እልከኞች እንድንሆን አስችሎናል።ከአክሱም
ውድቀት ወዲህ በዓለም ውስጥ ተገቢውን በታችን ባናገኝም ከአክሱም ፍጻሜ ወዲህ እስካሁን ድረስ ያለው የተዘረጋው ዘመን የተጻረሩንን
በመመከት ጀግንነትን እንደ አንድ የሕብረተሰባችን መለያና መገለጫ ሆኖ እንደ ውርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፏል። የትግላችን
ምስጢር ከዚህ ባሕሪ የመነጨ ነው።
ይሁንና በዚህ ዓለም ተገቢውን ቦታ አላገኘንም። እንዲያም ሆኖ በ19 ክ/ዘመን
መጨረሻ አጼ ዮሐንስ እንደነገሰ ያቺ የሰለጠነቺዋ የአክሱም ዘመነ መንግሥት አገራቺን ለማነጽ/ለመፍጠር የሞከረበት ወቅት ነበር።
ወቅቱ የቅኝ ግዛት ተወዳዳሪዎች የበዙበት ወቅት ስለነበር ከነዚያ
የአፍሪካ ቀንድ ለመቀራመት ፍላጎት የነበራቸው ቅኝ ሃይሎች ጋር በመጋጨት
አገራችን ትግራይ በ7ኘው ክ/ዘመን ከመዳከምዋ በፊት የነበረውን የቀይ ባሕር ጆኦ-ፖለቲካዊ ሃያልነት ለማምጣት ሞክሮ ነበር። ሆኖም
በጣሊያኖች ሴራ እና ዛሬ ጠላታችን የሆነቺውን አሁን ያለቺውን አገር ኢትዮጵያ የገነባ ዛሬ ጠላታችን የሆነውን ሃይል (አማራ) ጥምረትና
ሴራ ግንባታችንን በመሰናከሉ ግቡን ሊመታ አልቻለም።
ዛሬ ሕዝባችን ለሁለት ተከፍሎ የማይድን ቁስል ይዘን እንድንኖር ተደርገናል።
መውደቃችንን እንዳይበቃ በ19 ክ/ዘመን ማገባደጃ የገጠሙንን ከአጼ ዮሐንስ ሕልፈት ወዲህ እያነሳን ያለንበት ምክንያት የመጥፎ ታሪክን
ሱስ የማንሳት ይዞን ሳይሆን፤ የገጠመን ተራ አጋጣሚ ሆኖ ሳይሆን አስፈላጊ ትውስታ ስለሆነ ነው። የአጼ ዮሐንስ መንግሥት በድል
ቢቀጥል ኖሮ ዛሬ አሁን እያየናቸው እየገጠሙን ያሉትን ችግሮች ይወገዱ ነበር። ይወገዱ ነበር በቻ ሳይሆን በዓለም ውስጥ ሊኖረን
የሚገባ የክብር መንበር ሌላ መልክ ይይዝ ነበር።
ባጭር አገላለጽ የአጼ ዮሐንስ ሕልፈት በ19ነኛው ክ/ዘመን ማገባደጂያ
የተፈጠረው ይህ የንጉሱ ሕልፈት “የዘመን መጠመዘዢያ ማኣዘን” (ተርኒንግ ፖይነት) ነው የምንልብት ምክንያት በሚከተሉት ምክንያቶች መሆናቸውን
መረዳት ያስፈልጋል፡
1) በዚህ
አጋጣሚ እኛ በሕዝብ ብዛት በቁጥር የበላይነትን ይዘን ጂኦፖለቲካዊ የበላይነት ይዘን ማነጽ ልንችል የነበረቺውንና ለዓለማችን ፍላጎት
የምትስማማ አገራችንን ከእጃችን ተነጥቀን ወደ ተንሳፈፈችና ጥገኛ ወደ ሆነቺው የአገር ትርጉም የሌላት አገር ለጠላቶቻችን የምትጥም
ለኛ የማትጥም አገር የገባንበት የዘመን መጠምዘዣ መሆኑ
2) …………………..ክፍል
3 ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment