የልጅነት ትውስታዎች
እስከ ዛሬ ድረስ ያልተለያዩት የልጅነት ጓደኞች ኪዳነ እና ጌታቸው
ጌታቸው ረዳ
ኢትዮ ሰማይ
Ethio Semay
2/23/2021
ስንወለድ እትብታችን ተቆርጦ
የተቀበረው ከድንግል ጽዮን ማርያም አክሱም ከተማ አፈር ውስጥ ነው። ሁለታችን “ሀ” ብለን ትምሕርት መቁጠር እስከ ጀመርንባት ቀን
ጀምሮ እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ አብረን መጥፎዉንም ደጉንም ተካፍለን፤ በሚያስቅ እየሳቅን በሚያጨቃጭቅ እየተጨቃጨቅን አሁንም አለን።
ሊቃውንት እንደሚሉት እውነተኛ ጓደኞች ለማግኘት አስቸጋሪ ፣ ለመተው አስቸጋሪ እና ለመርሳት የማይቻሉ ናቸው፤ ይላሉ። እኔ እና
ኪዳነ እንዲህ ነበርን።
ሁለታችንም በትምህርታችን ጎበዝ
ተብለን ተለቅመን ከተመደብነው ክፍል አብረን ስንዘልቅ ከፍተኛ ውጤት ከሚያገኙት ጥቂት ትጉሃን ተማሪዎች ነበርን። ኪዳነ እኔን የሚበልጠኝ
በሂሳብ ነበር። እርሱ በሂሳብ ትምህርት የታወቀ ሲሆን እኔ ደግሞ በተቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ከፍተኛ ውጤቶች አገኝ ነበር። በሂሳብ
ጎበዝ ስለነበር ዛሬ በሚኖርበት አገር በከፍተኛ የመንግሥት ሥራ የኦዲቲንግ ሃላፊ ነው። በሂሳብ ደካማ ስለነበርኩ ኪዳኔ ያንን ማዕረግ
ቀዳሚ ሆኖ ያገኝ ነበር። በተቀሩት በማገኛቸው በ90ናዎቹ እና 100 መቶዎቹ የትምህርት ውጤቶቼ ለሂሳብ ማለፊያ/መሸፈኛ/ ውጤት
አደርጋቸው ስለበር፤ ኪዳነ ባጠቃላይ ውጤት ይበልጠኝ ነበር። ሆኖም አሉ ከሚባሉት ቀዳሚ ተማሪዎች ነበርን።
ኪዳነ በጣም እጅግ በጣም የምወደው
አብሮ አደጌ ነው። ኪዳነ የት/ቤቱ እና የቤቱ ስም “ሽሻይ” በሚል ስም ሲጣራ በተፈጥሮው ጸብ የማይወድ፤ እጅግ ቀልደኛ ሳቂታና
አዛኝ ነው። ከሰብኣዊ የሞራል መርሆ ከተዛነፍክ የሥጋ ዘመዱም ብትሆን ከመቃወም አይቆጠብም። በዚህ ባሕሪያችን ሁለታችን እንመሳሰላለን።
ጸበኛ ስላልነበረ ሞገደኞች ወይን ከቅርብ ጓደኞቻችን ውስጥ ሊተናኮሉት ከሞከሩ ዘልየ እመሃል ለመደባደብ የሚቃጣኝ እኔ ነበርኩ።
ጸጋዘኣብ ደሞዘ፤ ፍጽስሃጽዮን
ገሠሠ ኪዳነ እና እኔ አራታችን የማንለያይ፤የምንዋደድ አጅግ የቅርብ ጓደኞች ነበርን። የወቅቱ የክፍላችን ሴት ተማሪዎች ስለሚወዱኝ፤
ልጃገረዶች በመጥበስ እኔ አንደኛ ነበርኩ። ሲጃራ ማጨስ፤ መምህራችን ከገባበት ጠላ ቤት ወይንም ሻይ ቤት መግባትና መታየት ፤ልጃገርድ
መጥበስ አክሱም ውስጥ እጅግ አስፈሪ እና ጥብቅ ስለሆነ ለሴቶች ፍቅረኞቻችን ፍቅራችንን የምንገልጸው በድብቅ እና አጅግ መገናኘት
ካልተቻለም የፍቅር ግጥም እየገጠምን (አብረን በአንድ ክፍል እየዋልንም ቢሆን ‘እንደ ሰማይ ኮከብ የምትርቂኝና የምትናፊቂኝ’ እያልን
የምንጽፍላቸውን ግጥም “በመሸፈኛ” ደብተራችን ከውስጥ አስገብተን ሰው ሳያየን በምስጢር ደብተሩን ለፍቅረኞቻችን በመስጠት) ፍቅራችንን
እንገልጻለን። እኔ እና ኪዳነ የተፈጥሮ የሕይወት ጉዞና ግዴታ ሆኖ በተለያ
ሁኔታዎች መለያየት ኖርብን ተለያይትን ብዙ ኣመት ተነጣጥለንም ሳንነጣጠል አሁንም ማደጋችን የሚገርም ተፈጥሮ ነው።
ኪዳነ በሚመለከተው የፖለቲካ
መነጽር ‘የወያኔ መስመር በመቃወሙ’ አብረውን ያደጉ አንዳንድ ጓደኞቻችን “ወያኔ የተባለ ነገዳዊ የፖለቲካ ሃይማኖት “ፋሺዝም መሆኑን”
ሳይገባቸው የወያኔ አምላኪዎች ሆነው “እኛ የገነባት አገር እኛ ልናፈርሳት እንገደዳለን የሚለው የፋሺሰት ትግሬዎች ቅዠት” ጓደኛየን
ኪዳነን ለመወረፍ ሲቃጣቸው እጅግ ይገርሙኛልም ያስቆጡኛልም።
እኛ የገነባት እኛ ልናፈርሳት
እንገደዳለን የሚለው የፋሺሰት ወያነ ትግሬዎች ቅዠት ለሕዝባችን ስቃይ ምክንያት ናቸው። በታሪክ ያልሞከረውን ኢትዮጵያን የማፍረስ
ቅዠት የትግራይ ህዝብ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ፍቅር ወድቆ የራሱን ነገድ ማንነትና ታላቅነት እንዲያመልክ ተደርጎ ለብዙ
ሺህ ዘመናት አብሮ ከኖረው የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስነልቦናም ሆነ በእለታዊ ህይወቱና ማህበረሰባዊ ተራክቦው (social
interaction) እየተለየ መጥቶአል። ዛሬ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ኢትዮጵያውያኖች በጋራ ከሚጋሩዋቸው ብሄራዊ እሴቶች በተቃራኒ
የቆሙና ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ፤ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የተቃኙ ፋሽስታዊ እሴቶች ባለቤት በማድረግ ጨርሶ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ
ወጥቷል ማለት ይቻላል። የኪነጥበብ ስራዎች፤ ዘፈኖች፤ ትያትሮች፤ ፊልሞች ወዘተ የህዝብ መዝናኛዎች መሆናቸው ቀርቶ ጦረኝነትን፤
የትግራይን ሕዝብ የበላይነት፤ ምርጥነት፤ የንጹህ ዘር፤ የንጹህ ደም ባለቤትነት፤ ልዩና ወደር የሌለው የታሪክ ባለቤትነት፤ የሥልጣኔ
ባለቤትነት፤ ጀግንነት፤ አዋቂነት፤ ወዘተ አጉልተው የሚያሳዩ ከማንም ፍጡር የተለየ የበላይነት ስሜት የሚያነጸባርቁ የግንጠላ የፕሮፓጋንዳ
መሳሪያዎች በመጠቀም ከሰብኣዊ አስተሳሰብ አውጥተው ‘ራሺያል ሃይጂን” (ንጹህ ‘ዘረ መል’- “ክሊን ጂን”) የሚለው የናዚዎች አስተሳሰብ
እንዲከተልና በነገዱና በአካባቢው ፍቅር እንዲወሰን አድርገውታል። አሁን ያለው ትውልድ ከናዚያዊ “የዘር ንጽሕና” አመለካከት ራሱ
ነፃ ካላወጣ፤በዚህ ከቀጠለ ትግራይ እና አካባቢው የስቃይ የእሪታ የጦርነትና የእርዛት ቀጠና ሆና ትቀጥላለች።
የህ “ክፉ የፖለቲካ ሃይማኖት”
ብዙዎቹ አብሮ አደግ ጓደኞቻችን እርስበርሳችን እንድንራራቅ መንገድ ከፍቷል። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ባለቸው የናዚ አምልኮ ምክንያት ስንለያይ
እስካሁን ድረስ አብረን እንዳደግነው ዛሬም አብሮ ያልተለየኝ ጓደኛየ “ባለማስትሬት ዲግሪው” ምሩቅ የሆነው የሂሳብ ሊቁ ጓደኛየ
እና ወንድሜ ኪዳነ አፈወርቂ እጅግ እያደነቅኩ ለወደፊቱ ስለ ልጅነታችን ያሳለፍናቸው አክሱማዊ “ካራክተሮች” “ባህላዊና ትምሕርታዊ”
አዘል የሆነ “የልጅነት ትውስታችን” እንድ መጽሐፍ አብረን ለመጻፍ እያሰብን ነው።
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ Ethio
Semay አዘጋጅ
No comments:
Post a Comment