የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጅ እና ምላስ ብቻ የሆነው ተግባረቢሱ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ!
ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው
ረዳ (Ethiopian Semay)
ትርጉም Sunday,
December 06, 2020
ወደድንም
ጠላንም “ኤርትራኖችና ትግሬዎች” ለሚያምኑበት በጽናት የመቆማቸው ባሕሪ ማድነቅ እንጂ ማናናቅ አይቻልም። በአንጻሩ ይህ ትርጉም ተርጉሜ ሳቀርብ፤ ደደቡ ውጭ አገር የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ (በተለይ
የንግድ ባለቤቶችም ሆኑ አማራዎች) በአሉላ ሰለሞን የተነገረው መርዛማ
ንግግር ምንም እርምጃም ሆነ ስሜት እንደማይሰማቸው አውቃለሁ። ለታሪክ እንዲቀረጽ ግን ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ።
“በትግራይ ሚዲያ ሃውስ” የተላለፈው ማሕበረሰብንና አገርን የማፍረስ እንዲሁም ጋብቻ በዘርና በፖቲካ ከ የመከፋፈል ቅስቀሳ ሲያስተላልፍ ልክ ሩዋንዳው ውስጥ ፖለቲካን ተንተርሶ “ሁቱ እና ቱትሲ” ለፍጅትና ለትዳር ፍቺ ይቀስቅስ የነበረው “radio Mille Collines” “አሉላ ሰለሞንና የትግራይ ሚዲያ ሃውስ” ባልተናነሰ ቅስቀሳ ሲያውጅ፤ ከላይ የጠቀስኳቸው ማሕበረስቦችና ንግድ ቤቶች በላያቸው ላይ የተላለፈው የጥላቻ ቅስቀሳ ምንም እንደማይሰማቸውና አውቃለሁ። የማንበብና የተተረጎመውንም ለሕዝብ እንዲዳረስ እንኳ የማድረግ ፍላጎት እንደሌላቸው ከፌስቡክ ገጾች ማየት ትችለላችሁ። ድክመታችሁ እስከዚህ ጥግ ይደርሳል።
ወያኔዎች የኛን የኢትዮጵያዊያን በተለይም የአማራውና በተለይ የነጋዴው ማሕበረስብ “ልፍስፍስነት” እና ደደብነት ለ30 አመት ስለሚያውቁት፤ የፈለጉት ቢናገሩ ምንም እንደማይሆኑ አውቀዋልና ፤ አሉላ የፈለገው የጥላቻና አገር የማፍረስ ቅስቀሳ በኩራት በድፍረት እና በሃይለቃል አስተላልፏል ። እኛ ወደ ቁልቁል ስንወርድ እነሱ ወደሽቅብ ሲሄዱበት የነበረበት የ30 አመቱ ጉዞ ምስጢሩ ፤ለሚያምኑበት ተሎ “ሪኣክት” በማድረግ አቋም ይወስዳሉ። ትግራዋይነት ብለው በኩራት የሚናገሩበት አቋምም ይህ ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በተለይ አማራዎችና የንግድ ባለሃብቶች “ከምላስ” በስተቀር ቢሰደቡም ፤ቢዋረዱም ደንታ እንደማይሰጣቸው ለ30 አመት አይቻለሁ፡ ዛሬም ያው ናቸው። አመማችሁ አይደል? እንዲሰማችሁ ነው እየጻፍኩ ያለሁት!! ከአሉላ ሰለሞን ምላስ ይልቅ የኔ ከተሰማችሁ ምንም ማድረግ አይቻልም። አሁን ወደ አሉላ ሰለሞን አማርኛውን አስተካክየ የተረጎመኩትን ንግግሩ ይኼው። ትከክለኛ ቅጂው ኢትዮጵያን ሰማይ አሁን ተለጥፏል። ለፌስቡክ አንባቢም እነሆ።
ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው
ረዳ (Ethiopian Semay)
ትርጉም Sunday,
December 06, 2020
ብዙ ሰዎች ከተረጎምኩት የማይረቡ
ነጥቦችን እየቀነጫጨቡ በየፌስቡክ ሲለጥፉ በማየቴ አንባቢዎች ሙሉውን ትርጉምና ይዘት ለማየት እዚህ ኢትዮጵያን ሰማይ ላይ ተለጥፏል
ይኼው።
የአሉላ ሰለሞን
የጥላቻ አዋጅ የተላለፈበት ቴ/ቪዥን Tigrai Media
House
ቀን 12-05
20
ቃለመጠይቅ
አቅራቢ አቶ ሃይለ - የTigrai Media House መድረክ አዘጋጅ)
የመድረኩ ተሳታፊ - አሉላ ሰለሞን፡ (የሚዲያ ሃውስ ዋና ሥራ አስክያጅ)
የውይይቱ አርዕሰት “ትግራይ - ዛጊድ ዝተረኸቡ ዓወታት ምዕቃብ 12/05/2020…(ትግራይ ውስጥ እስካሁን ድረስ የተገኙ ድሎች ስለ መጠበቅ 12/05/2020)
ፌስቡኩ ላይ ተያያዥ ሆኖ የተለጠፈው ሌላ ርዕስም “በትግራይ ህዝብ ላይ የቀጠለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ 12-05 20” የሚል ይነበባል። https://youtu.be/uFyMwSg_MM0
የቃለመጠይቁ ምንጭ ከታች የተለጠፈው
የፌስቡክ ድረገጽ፡
https://www.facebook.com/tmhtv/videos/400078718098046
ትግራይ - ዛጊድ ዝተረኸቡ ዓወታት ምዕቃብ 12/05/2020… (ትግራይ ውስጥ እስካሁን ድረስ ስለ ተገኙ ድሎች መጠበቅ 12/05/2020
ከቃለ መጠይቁ የተወሰዱ ፍሬ ነገሮች፡ ከትግርኛ ወደ አማርኛ እንደሚከተለው
ተርጉሜዋለሁ።
ማሳሰቢያ
አቶ አሉላ ሰለሞን እነዚህን በሚመለከት በጽሑፍ ካሁን በፊት ማቅረቡን
እራሱ ይናገራል። ጽሑፉ የት እንደለጠፈው አላየሁትም። ሆኖም በራሱ ፌስቡክ ወይንም በሚዲያ ተለጥፎ ከነበር ለወደፊቱ እፈልገዋለሁ።
እስከዛው ግን ተጨማሪ ብሎ ያቀረበው የቃለ መጠይቁ ይዘት እነሆ እንዲህ ይላል።
1-ሃይማኖትን በሚመለከት፡
ትግሬዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፤ ከኢትዮጵያ ካቶሎክ፤ ከኢትዮጵያ ፕሮተስታንት
ቤተጸሎቶች እንዳይጽልዩ !! እራሳቸው ከነዚህ ተቋማት እንዲያገልሉ በጽሑፍ ካሁን በፊት አቅርቤአለሁ፤ ዛሬም ይህንኑ ጥሪ አቀርባለሁ።
በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሰትያን መደረማመስ አለባት (ትግርኛው “ዱዋዕዋዕ ክትብል አለዋ”)። ትግራዋይ ሁሉ አቅምህና
ንብረትህ ትግሬዎች በሚመሰርትዋቸው ተቋማት እና በትግራይ ብቻ እንድታውለው ይሁን። therefore (ዘርፎር) የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን
ከምትባል እራስህን አርቅ። የትግራዋይ ቤተክርስትያን እንጂ ኢትዮጵያ የምትባል ጠላታችን ስለሆነች መጠሪያችን “የትግራይ ተዋህዶ፤
የትግራይ ካቶሊክ፤ የትግራይ የፕሮተስታንት ቤተክርስትያን ፤የትግራይ ኢቫንጀሊካል ቤተክርስትያን ተብለው እንዲሰየሙ ማድረግ አለበን”
(period! ፒሪየድ!)። እስላም ከሆንክም “የትግራይ ምስልምና” ብላችሁ
መስርቱ።
የትግራይ
ሕዝብ ሆይ! እነዚህ ፈጽመው አይፈልጉህም። በተጠቀሱት እምነቶች በትግሬነታቸው ችግር አይታይባቸውም። ችግሩ ያለው በዋናነት ኦርቶዶክስ ላይ ነው። ዋሻ ነው። ያ ዋሻ መፍረስ አለበት!!
ካሁን በፊት ቀደም ብለው ይህንን እንደሚመጣ ቀደም ብለው ያወቁ አስተዋይ ትግሬዎች የትግሬዎች ቤተክርስትያን መስረት ስለነበር አሁን
ከዚች ከዳተኛ ከሆነቺው የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እራሰክን አግልል። ቄሶች ድያቆናት ጳጳሳት የሆናችሁ ትግሬዎች ሁሉ ከዚያ ውጡ! ወጥታችሁ የትግራዋይ ቤተክርስትያን መስርታችሁ ትግሬዎችን ብቻ አገልግሉ።
2- “ቢዝነስ” በሚመለከት የሚከተለው ጥሪ አቀርባለሁ፤
የእንጀራ ቤቶች፤ ምግብ ቤቶች የሥጋ ቤቶች በጠቅላላ የኢትዮጵያዊያን ንግድ
ተቋማት በሚባሉት ሁሉም ቦታ ግብይት እንዳታደርጉ!! በገንዘብ እቅማቸውን
ማጠናከር ብቻ ሳይሆን መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ። ይፈጅዋችሗልም። እነዚህ ጨካኞች ናቸው!! ብምትመገቡዋቸው ምግቦች ውስጥ
መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ ተጠንቀቁ። በመርዝ ተመርዛችሁ ከመሞት ለመዳን ከፈለጋችሁ መፍትሄው ትግሬዎች፤ ኤርትራኖች እና
በአካባቢያችሁ ባሉት የኦሮሞ ንግድ ቤቶች/ቢዝነስ/ ካሉ ከነሱ ጋር ተገበያዩ። በተለይ ደግሞ ያቺ ልሙጥ ባንዴራ የሰቀሉ ወይንም በንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ
ካያችሁ እንዳትገበያዩ ሌላ ቀርቶ ቅመምም ጭምር እንዳትገዙ።
በኢትዮጵያ የሚጠራ ወይንም ኢትዮጵያ የሚባል ስም ያለባቸው ማሕበራት እንዳትገቡ።
መረዳጃ ማሕበር ይሁን ምንም ይሁን “ኢትዮጵያ” የሚል ካለበት
ከነዚህ ማሕበረሰቦች ጋር እንዳትቀላቀሉ። በሙሉ አግልሏቸው። ገንዘባችሀ በትግሬዎች ብቻ “Spend” አድርጉ። አንዳንዱ “አሉላ
ሰለሞን” “ራዲካል” ሆነ ምናምን ሊሉዋችሁ ይችላሉ። ኖ! እስኪያማቸው
ድረስ መነገር አለበት። ማወቅ አለባቸው። ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችን አይወዱህም እና ባጭሩ ከነሱ እራስክን ነጥል።
3- የእግዚአብሔር ሰላምታን በሚመለከት።
አማራዎች
“ወንድሞቼ ሰላም እንባባል እንጂ ወንድማማቾች እኮ ነን ምናምን ብለው
“ሰላም” ቢሏችሁ ሰላም እንዳትሏቸው። ከአማር ጋር ጭራሽ እንዳታነጋግሩዋቸው! አማራ የሚባል “ሱፐር ማርኬት፤
ሞል ፤ ሌላም ሌላ ቦታ ስታገኝዋቸው ሰላም አትበሏቸው። ወዳጅነት
ኖሯችሁ፤ አብራችሁ ስተበሉ ስትጠጡ የነበራችሁ ሁሉ “አቁሙ!” ጦርነቱ
ሳይደግፍ “ሳይለንት” (ዝም ካለም) ፤ አማራም ቢሆን ተባባሪ ነውና አቁም! የትግራይ ሕዝብ ሲበደል አሳዝኖኛል ስትል ስላልሰማሁህ ጠላት ነህ ብላችሁ
መልሱለት። ወዳጅነታችሁን አብሮ መብላት መጠጣትን አቁሙ። ስለትግራይ መበደል ምንም ያልተነፈሰ ሰው “ከዚህ ሰው ጋር በጋራ አብራችሁ
“እንጀራ በሳህን” የምትበሉ የምትጠጡ ከሆነ ያ የምትመገቡት ምግብ ጸር ሆኖ ይገላችሗል። የምትጠጡትም የወንድሞቻችሁ ደም ማለት
ነው። ስለዚህ በተለምዶ ተዋልደናል ትዳር መስርተናል ምናምን የሚባል ዝበዝንኬ ዛሬ አይሰራም።
ትዳር መስርታችሁ ከሆነ ወይንም ወልዳችሁ ከሆነ ወላጀቻቸው ናቸው በቦምብ
ሕዝብን እየጨረሱ ያሉት። ስለዚህ አንድ ሰው ከትግሬ ጋር ተጋብቶ ትዳር መስርቶ ወልዶ ከብዶ ከሆነ ወይንም ከትግሬ ጋር ፍቅር ይዞት
ከሆነ የመጀመሪያ “requirement ሪኳየርመንት” መሆን ያለባት
“በትግራዋይ ላይ የታወጀው ጦርነት ማውገዝ መቻል አለበት” ይህ ሰው ከትግሬ ሴት ጋር ለመጋባት ኳሊፋይ ለመሆን ሪኳየርመንቱ ይህ መሆን አለበት። አንድ
ሰው ከትግሬ ሴት ጋር ወይንም ከትግሬ ወንድ ጋር ለመዳር ከፈለገ ወይንም ከፈለገች “በችግራችን ወቅት ከትግራይ ሕዝብ ጋር እቆማለሁ
የሚል ወይንም የምትል መሆን አለባት። መመዘኛው ይህ መሆን አለበት። ካልሆነ ግን “ኢትዮጵያ” ምናምን የምትል ከሆነ “ዞር በይ! ብላችሁ አባርሯት”!!
4- ኢትዮጵያ
ምናምን እያለች እራስዋን በኢትዮጵያ የምትሸሽግ ከሆነ
ሀ-ወዲያ በሏት! ከቤታችሁ አባርሯት ወይንም አባርሩት፤
ለ-ግንኙነታችሁ በጣጥሱት!!
ሐ-ጓደኝነት ከሆነም (ወዳጅነታችሁን) በጣጥሱት፤
መ-ትዳር ከሆነ አፍርሱት፤ ማሕበራዊ ግንኙት ከሆነ በሙሉ በጣጥሳችሁ
ወደ ቆሻሻ መጣያ ጣሉት!
ሠ-ባጭሩ እንዲሰማቸው ማሳየት አለባችሁ!
Life ለኛ መራራ ሆና ለሌላኛው መጣፈጥ የለባትም። ባጭሩ ህይወት ማለት
“ትግራዋይ” ሳይጥማት ሌላው ተመችቶች እያጣጣመ እንደማይኖር ማሳየት አለባችሁ። ይህ ከየት ይጀምራል ብትሉኝ። መጀመሪያ ከቤተሰብ
መጀመር አለበት። ቤተሰቦቼ እየተጨፈጨፉ እየተሰደዱ እኔ ከነዚህ ለመሰደዳቸው ምክንያት ከሆኑት ጋር ቁጭ ብየ ከበላሁ ከጠጣሁ ማፈር
አለብኝ። ስለዚህ ለጠየቅከኝ ጥያቄ “ድል በድል ሆነናል” የምለው ምክንያት “ትግራዋይ ሁሉ በጠቅላላ ይንን ተግባራዊ እያደረገ
መሆኑን ስለማውቅነው፤ በዚህ በኩል ነው ስኬታማ ነን የምለው”። በማለት
5- በመጨረሻም ማንኛውም ትግራዋይ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳይጓዝና ቦይኮት ማድረግ እና በንግዱ በኩል የነበረው ገቢ ዓለም እንዲጠየፈው በማድረግ
እንክትክት እስኪል ድረስ ዘመቻ ማድረግ አለብን።
በማት የቃለመጠይቁ አዋጅ በዚህ ይደመድማል።
ትርጉም ጌታቸው ረዳ ((Ethiopian Semay) Sunday, December 06, 2020
No comments:
Post a Comment