“ጃዋርና እስክንድር እየተናበቡ ሀገር ለማተራመስ ይሠራሉ” - ወ/ሮ ዐቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
Posted - Ethiopian
Semay
የወ/ሮ አዳነች ይህን ዓይነቱ መንግሥታዊ ንግግር የዶ/ር አቢይን ከባልደራስ ጋር የሚያደርገውን ጦርነት
ያወጀበትን የቁጣ ንግግር የተንተራሰ ለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያሻም - እየተናበቡ ሀገርን በማፍረስ ላይ የሚገኙትስ እነሱ ራሳቸው
ናቸው፡፡ ይህ ንግግር በተውኔቱ ዓለም ቢገለጽ ደምበኛ ሼክስፒራዊ ትራጂ ኮሜዲ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሽል መንጣሪዎች እየመሯት
ሀገራችን ወደገደል እንጂ ወደ ብልጽግናና ዕድገት አታመራም፡፡ ምኞት ግን አይከለከልም - ሊያውም ከማስመሰል የራቀ ቀናና ትክክለኛ
ምኞት ካለ፡፡
ጥቅምት 2012ዓ.ም ከ100 በላይ ንጹሓን አማሮችንና ለዘብተኛ የኦሮሞ ክርስቲያኖችን እንዲሁምና
ምናልባትም ከሌሎች ነገዶችም የተወሰኑ ዕድለቢሶችን ያስጨፈጨፈው በወቅቱ
“ሁለተኛው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር” ጃዋር መሀመድ በመንግሥት ዕቅፍ ውስጥ ሆኖ ያሻውን ሲያዝዝና ሲናዝ ለተመለከተ ቅን ታዛቢ በቅርቡ
የአክራሪ ኦሮሞዎች አማራ ላይ ባደረሱት ዕልቂትና የንብረት ውድመት ሳቢያ “ራሳችሁን ጠብቁ፤ ተደራጅታችሁ አካባቢያችሁን ከጥቃት
ታደጉ...” ብሎ አዲስ አበባን ከውድመት ለመከላከል የሞከረን አንድ ዜጋ በመናጆነት ማሰር በርግጥም የክፍለ ዘመኑ ቧልታይና ድንቃይ
የልጆች ትያትር የሚመስል አስቂኝ ግን መራር ቀልድ ነው፡፡ እንደዚህ
ያለ ዐይን ያወጣ መድሎና ወገንተኝነት በመንግሥት ደረጃ ከታዬ በግልማ እንዴት የባሰ አይሆን! ሀፍረትን መሸጥ እንደዚህ ነው፡፡
እንደ አንዳንዶች ግንዛቤ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ባያስጠነቅቅ ኖሮ ከተማችን ይሄኔ
ከገጠር በአይሱዙ ተጭነው በመጡ የጥፋት ኃይሎች እንደ አሌፖና ደማስቆስ የዶግ አመድ ሆና ነበር፡፡ ይህን የንጹሓን ዜጎች ዕልቂትና
የንብረት ውድመት መከላከልም እንደወንጀል ተቆጥሮ ወጣቱን “ራስህን ተከላከል፤ አካባቢህንም ጠብቅ” ብለው ያነቁ ከእስክርቢቶም በስተቀር
አንድም የጦር መሣሪያ የሌላቸው ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸውና በዘር ሐረጋቸው ምክንያት ብቻ ለእስርና እንግልት ተዳርገዋል፡፡
ይህን መንግሥት የሚመራው ደግሞ እንደዓሣ በባህር እንደሰው በምድር ነዋሪ የሆነው ዶክተር አቢይ ነው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ፡፡
በበኩሌ ከአቢይ መንግሥት ምንም አልጠብቅም፡፡ ተስፋችንን ሁሉ እያሟጠጠው ነው፡፡ ሰውዬው እጅግ አደገኛ
የጭቃ እሾህ መሆኑን በተደጋጋሚ በተግባር በማሳየቱ ከእንግዲህ አቢይ ኢትዮጵያን ወደ ወርቃማ ጊዜዋ ያሻግራታል ብሎ ራስን ማታለል
ሲበዛ የዋህነት ነው፡፡ ልጁ በነገሮች መሳከር ሳቢያ ድንገት እጁ የገባችዋን ዕድሜ ልኩን ሲቃዥባት የኖረውን የሰባተኛ ንጉሥነት
ሥልጣን ላለማጣት ሲል የማይቀጥፈውና መስሎ ለመገኘት የማይጥረው ነገር የለም፡፡ ይሉኝታን ባወጣ ሸጦ ስለበላ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው
በአንድ ጊዜ ጅብም አህያም፤ እሳትም ውኃም ለመሆን ከመሞከር አይመለስም፡፡ ይህን ቦታ ከመያዙ በፊት እርግጥ ነው ጥሩ ሰው ሊሆን
ይችል ይሆናል፡፡ ወንበሩን ከያዘ በኋላ የሚታይበት ጠባይ ግን እጅግ የተለዬና አስመሳይነት የበዛበት ለመሆኑ የሀገራችን ተጨባጭ
ሁኔታ በግልጽ የሚናገረው እውነት ነው፡፡ ለዚህም ነው የተበደለ ሲያይ አብሮ እያነባና ዕንባም ከጉንጭ እየጠረገ፣ የኦርቶዶክስ መስቀልንም
ከሙስሊሙ ክታብና ሙስባሃ አጣምሮ እየሳመ፣ የጴንጤን መዝሙር ከማጀት እስካደባባይ እየዘመረና እያዘመረ፣ ምናልባትም ታልሙድንና ቶራን
ከጽዮናውያን ምኩራቦች እያስተረጎመና እያስነበበ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ተከላም የዋሃንን እያነሆለለ፣ ... በየሥነ ግጥም ምሽቶችና
የድርሰት ምርቃቶችም በመገኘት የአርት ሰዎችን እየቀፈለ ... በሌላ በኩል ደግሞ የሥልጣን ተቀናቃኞችን በሥውር እየገደለና እያስገደለ፣
በዘር ልክፍት የደዌ ግርሻ አክራሪ ወጣት ኦሮሞዎችን በየሥልጣን ቦታው እየመደበና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸቱ ጥሩ ጥሩ ዜጎችን ግን
ከጥቅምም ከሥራም እያገለለ፣ አዲስ አበባንና ሀብቷን ከየገጠሩ ተጠራርቶ ለመጣ የቄሮና አባገዳ ግሪሣና መንጋ እያከፋፈለ... አማራን
ግን ከነስሙም አታንሱብኝ እያለ፣ የአማራን ክልል ሀብትና ሥልጣን ለታማኝ አሽከሮቹ እንደራሴዎች እያቃረጠ ... አይሆኑ ሆኖ የምናየው፡፡
ልጁ አስገራሚ ተፈጥሮ ያለው ሰው ነው፡፡ ሰይጣን ለተንኮሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ መጥቀሱን የማያምኑ የዋሃን ዜጎች በአቢይ የማስመሰል
“ጥበብ”ና በሚያሣየው የሃይማኖተኛነት ውስጠ-ወይራዊ ስብዕና በመማለል በኔ እንደሚፈርዱብኝ አውቃለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ከጥቂት ጓደኞቼም
ጋር ስከራከር ባለመስማማት ራሴን ከክርክሩ አገልላለሁ፡፡ የወደደ ሲጠላ እንዲህ ነው፡፡
በመጀመሪያው አካባቢ እርግጥ ነው እኔም መስሎኝ ተታልዬ እንደነበር አልደብቅም፡፡ እየቆዬ የተረዳሁት
ግን አቢይ ማለት የጨለማው ገዢ ሊቀ ሣጥናኤል ዓላማውን እንዲያስፈጽሙለት ከልጅነታቸው ጀምሮ አርሞና ኮትኩቶ ለቁም ነገር ካበቃቸው
ምድራዊ ሰብኣውያን ፍጡራን መካከል አንዱ መሆኑን ነው፡፡ እኔ ይህን እውነት በሚገባ አምኜበታለሁ፡፡ ምናልባት ይህን የኔን እውነት
ከሰይጣን ከራሱና ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ ሰው አያውቀው ይሆናል - ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የአቢይ ልዝብ ሰይጣናዊ
አንደበት ሌላውን ሁሉ ተውትና ፕሮፌስር አለማየሁ ገ/ማርያምን ሳይቀር አንበርክኳል፤ ምትክ የለሹን ለሀገር እንስፍስፍ ታማኝ በየነን
በፍቅሩ ጫማው ሥር ጥሏል፤ ፕሮፌሰር እንደሻው ነጋን የመሰለ አክሮባቲስት አሽከሩ አድርጓል፤ በርካታ የተቃውሞው ጎራ ሚዲያዎችን
አፍ አሲዞ በራሳቸው ጊዜ እንዲዘጉ አድርጓል፡፡ ብዙዎችን አሁን ድረስ በፍቅሩ እያማለለ እንዲያለቅሱለት በማድረግ ላይ ነው፡፡ ሰይጣን
እስከዚህ ድረስ ሰውን ያጃጅላል፡፡ ለእግዚአብሔር ብቻ አይደለም - ለሰይጣንም የሚሳነው የለም! ዋናው እምነት ነው፡፡ ካመንክበት
እንኳንስ ሰይጣንና አቢይ ድንጋይም ብዙ ተዓምር ይሠራልሃል፡፡ እውነት ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ እውነቶች በገሃድ እስኪከሰቱ
ጊዜ ይወስዳል፡፡
ኢትዮጵያ የተደገሰላት የመከራ ድግስ ቀላል እንዳይመስለን - የቆማጢት ልጅ “እማዬ እጄን አሳከከኝ”
ብትላት “ልጄ እኔም በአንድ ቀን አልተቆመጥኩም!” ያለችው ሦርያንና ሩዋንዳን ለኛ ለጀለንፎዎቹ ለማስታወስ ፈልጋ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ከሆነ በኋላ እዬዬ ዋጋ የለውም - ለዚያም ከበቃን እንዲያውም፡፡ አንድ መራር እውነት ላስታውስህ፡- የፌዴራል ተብዬውን ዋና ዋና
የፈላጭ ቆራጭ የሥልጣን ቦታዎች የተቆጣጠረው ኦህዲድ/ኦነግ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት አማራና ኢትዮጵያ ላይ የዘረኝነት የጥላቻ
ፕሮፓጋንዳ ሲነዛበት በነበረው ወጣት ኃይል ነው፡፡ ታከለም በለው ሽመልስ፣ አቢይም በለው ደቻሣና ቀልቤሣ .... ሁሉም የዚያን
ወያኔ ወለድ የአኖሌ ትርክት እየተቀለበ የበቀል ጥማቱን ለማራገፍ ጊዜ ይጠብቅ የነበረና በአማራው ላይ ታሪክ ለመሥራት ያቆበቆበ
ትውልድ ነው፡፡ ልዩነቱ አንዱ ወለጋ ጫካ ውስጥ ሲሆን ሌላውና ጓዳችን ውስጥ በራሳችን ስንቅና ትጥቅ እየተዋጋን ያለው ኃይል አዲስ
አበባ ላይ የፌዴራል ተብዬውን መዋቅር ይዞ እንደልቡ የሚፏልል መሆኑ ነው፡፡ ይህ የምለው ነገር ውሸት በሆነና እኔ ቀጣፊ በተባልኩ፡፡
ኢትዮጵያ ሲባል እንደኮረንቲ የሚነዝረው፣ አማራ ሲባል እንደ ዛር አዶ ከብሬ የሚያስጓራው ትውልድ ሥልጣን ይዞ ኢትዮጵያም ሆነች
አማራ ሰላም ያገኛሉ ብሎ ማሰብ ደግሞ በትንሹና በተለመደው አገላለጽ ከእባብ ዕንቁላል የዕርግብ ጫጩት ይፈለፈላል ብሎ እንደመጠበቅ ነው - ትልቅ ጅልነት፡፡
እነሱሴም ሆኑ እነ “ስንኖር ኢትዮጵያ፣ ስንሞትም ኢትዮጵያ” ነገረ ሥራቸውን እያየናቸው ነው - እነሱም
ብልጥ ሆነው ሞተው እንዴት ሕዝብን እያታለሉ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት አይከብድም፡፡ የ30 እና የ40 ዓመት ውርጋጥ የሦስት ሽህ
ዘመን የጋራ የአብሮነት ታሪክ ያለውን ያንቀላፋ ግን ያልሞተ ሕዝብ ለማሞኘት የተጓዙትን ርቀትና ያስመዘገቡትን ስኬት ስንመለከት
በርግጥም ዕድል ሲሰምርና ዕድል ሲያንጋድድ ልዩ ምስል ሊፈጠር እንደሚችል
ከሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መረዳት አያቅተንም፡፡ ሆኖም ሁሉም ነገር አላፊ መሆኑ ያጽናናናል፡፡ እንደመጽሐፉ - ለመትከል ጊዜ አለው፤
የተተከለውን ለመንቀልም ጊዜ አለው፡፡ ለመነሣት ጊዜ አለው፤ ለመውደቅም ጊዜ አለው፡፡ ሮም በአንድ ቀን እንዳልፈረሰች ሁሉ በአንድ
ቀንም አልተገነባችምና የሞኞች ግዝፈት ብልኆች ከዳተኝነታቸው እስኪላቀቁ ድረስ ነው፡፡ የሚያዋጣው በፋሲካ ሰሞን ከተቀጠረችዋ የቤት ሠራተኛ ትምህርት መቅሰምና ራስን
ከታሪክ ሂደቶች ጋር ለማስተካከል መሞከር ነው - ብዙም ሳይረፍድ፡፡ ታሪክ ጨካኝ ነው - ምሕረትን አያውቅም፡፡ ከአጼ ኃይለ ሥላሤ፣ ከደርግና
ከወያኔ ያልተማረ ንክር ያለ ደንቆሮ ነው፡፡ መለስና መንግሥቱ ኃ/ማርያም በተሰሚነታቸውና ጠርዝ ባልነበረው ዐረመኔያዊ አምባገነንነታቸው
ያልቻሉትን የታሪክ ዱላ ጮርቃው አቢይ ይችለዋል ብሎ ማሰብ አነሰ ሲባል ሞኝነት አሊያም ካድማስ ወዲያ ማዶ አገር እንደሌለ የሚያስቆጥር
አላዋቂነት ነው፡፡
እነዚህ በሥልጣን አራራ ያበዱና በፍቅረ ንዋይ የሰከሩ ዘረኞች የዘመናችን ጴጥሮሶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ
ከመፋፈራረሷ በፊት ከሦስት ጊዜ በላይ ይክዷታል፡፡እጅግ አስፈሪ ኃይል ማዕከላዊ መንግሥቱን ተቆጣጥሯል፡፡ ሀገራችን በሰሜንም በደቡብም
በምሥራቅም በምዕራብም እንደሌጦ ተወጥራ ትገኛለች፡፡ እነጃዋርና እነአቢይ የሥልት እንጂ የዓላማ ልዩነትና የጠብ መንስኤ የላቸውም
- ጥላቸው የሥጋ ጥል ነው፡፡ ዓላማቸው አንድና አንድ ነው - እሱም በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ሌሎችን በገዳ ሥርዓት የሚያንበረክክ ታላቋን
ኦሮሚያ መመሥረት ነው፡፡ ልዩነት ካልነው ሌላው ልዩነት አንዳቸው ዓላማቸው በፍጥነት እንዲሳካ ሲፈልግ ሌላኛው በእርጋታና በዘዴ
እንዲሆን መፈለጉ ነው፤ ሌላው ልዩነት የሥልጣንና ሀብት ክፍፍል ነው፡፡ እንጂ እዚያም ውስጥ ያሉት እዚህኛው ውስጥ አሉ፡፡ እዚህኛው
ውስጥ ያሉት እዚያኛውም ውስጥ አሉ፡፡ አባተ ኪሾ እውነቱን ነበር፤ “ኤርትራውያንን ጭነህ ላክ” ቢሉት “እናንተው ለዩዋቸው እንጂ
እኔ በምን አባቴን አውቃቸዋለሁ” ብሎ ትግሬዎቹንም ከአዋሣ ጠፍንጎ ለወያኔ ላከላቸው ይባል ነበር ያኔ፡፡ አሁንም እንደዚያ ነው፡፡
ነገር ይደጋገማል - ኦነግ ሸኔን ከኦነግ ኦህዲድ መለየት የሚችል ማሽን ተፈጥሮ ከሆነ የቸርች ኦፍ ሴተን መሥራች የቀሲስ አንቷን
ሌቪ ሙት-መንፈስ ይንገረን፡፡
ልድገመው - በወያኔ ተንኮልና ሤራ የኦሮሞና የትግሬ ወጣት ሲኮመኩም ያደገው አማራን አምርሮ እንዲጠላ
የሚያስችል የዘረኝነት መርዝ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ፈርዶባት ከአማራ ጋር አያይዘው እንድትጠላ ስላደረጓት ወጣቶቹ ለዚህች ጥንታዊት
ሀገር ያላቸው ጥላቻም የዚያኑ ያህል ነው፡፡ መፍትሔው ለሰማይ ለምድር የከበደ ይመስላል፡፡ በኪነ ጥበቡ ውለን እናድራለን እንጂ
እንደነዚህ ሰዎች ሁኔታ ቢሆን ኖሮ አዲስ አበባ በደም ባህር ላይ የምትንሣፈፍ ፍርስራሽ ከተማ በሆነች ነበር፤ አንድም ፎቅ ቆሞ ባልተገኘ፡፡ ይህን መከላከል ወንጀል የሆነው እንግዲህ በፌዴራል
መንግሥቱ ውስጥ በተሰገሰገው አፍቃሬ ኦነግ ሸኔ ቲም ለማ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እጅግ ይገርማል፡፡
ኦሮሚያ በሚባለው አካባቢ ሲሰለጥን የነበረው ያ ሁሉ ለመቁጠር የሚያስቸግር ሠራዊት ለምን ዓላማ እንደሠለጠነ
ሰሞኑን ትልቅ ፍንጭ እየሰጠን ነው - ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥሉ የነበሩት እነዚሁ ሥልጡኖች እንደነበሩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
አማራ ራሱን እንዳይከላከል በበጀትና በተላላኪ ምስለኔዎች እያሽመደመዱ ኦሮሚያ ተብየውን ክልላዊ መንግሥት ግን ልክ እንደ አንዱ
አውሮፓዊ ኃያል አገር ለማድረግ ምን ያህል የተናበበ ሥራ ይሠሩ እንደነበር የምናውቀው ነው - ይህንን እውነት የሚክድ በርግጥም
አድርባይና ሆዳም ነው ወይም ከዕውቀት የፀዳ እልም ያለ ደንቆሮ፡፡ ሁሉም ፈዞና ደንግዞ እያየ ያለው ይህ ድራማ መጨረሻ ምን ሊሆን
እንደሚችል ሰሞኑን በቂ ምልክቶችን ስላየን ሌላው ቆሞ ከማየት ተቆጥቦ ራሱን መከላከል ወደሚያስችለው ዝግጅት መግባት እንዳለበት
በዚህ አጋጣሚ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ራስን ከጥቃት መከላከል በአሁኒቷ የኦህዲድ ኢትዮጵያ ወንጀል ቢሆንም ሜዳ ላይ ተገትሮ አንገትን
ለግብጽ ገጀራ መስጠት ግን ለማንም አይመከርም፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይነት በወንበዴ መንግሥት ሲጨፈለቅ ራስን ከዕልቂት ለማዳን ሥልት
ነድፎ መንቀሳቀስ ቢያንስ ዘር ለማትረፍ ይረዳልና ሁሉም በዚህ ረገድ ማድረግ ያለበትን ብዙ ሳይረፍድ ያድርግ፡፡ ከሩዋንዳ እንማር፡፡
አሁኑኑ!!
እርግጥ ነው ከፍ ሲል እንደተገለጸው የኦሮሞው ማዕከላዊ መንግሥት ራስን መከላከልን አይፈቅድም፡፡
ሰሞኑን አየነው፡፡ “ዝም ብላችሁ ታረዱ እንጂ መሸሽም ሆነ ንብረት እንዳይቃጠል መከላከል አትችሉም” የማለት ያህል አስገራሚ ትዕዛዝ
ሲሰጡ ታዝበናል፡፡ ቄሮዎች አማሮችን ሲያርዱና ንብረታቸውን ሲዘርፉና ሲያቃጥሉ የሚሸሸውን ሰው የሚያግዱና ከዘረፋ ለማስጣል የሚሞከረውን
ሀብት ንብረት እንዳይወጣ ሲከለክሉ የነበሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት እንደነበሩ በስፋት ተነግሯል፡፡ የመንግሥትን ቅርጽ ከያዘ
የዘር ፍጅት ለማምለጥ ደግሞ ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡ የኔ ነው ብለህ የምትጠጋው ኃይል ከሸሸኸው ኃይል በባሰ ወይም በተካከከለ
ሁኔታ ሕይወትህን ሲቀጥፍ ወይም ሲያመናጭቅህ መፈጠርን ያስጠላል፤ የፈጣሪንም ኅልውና እስከመጠራጠር ሳይቀር ይፈታተናል፡፡ ሰሞኑን
የሆነው ይሄው ነው፡፡ የነገው ደግሞ ከዚህ የከፋ መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ አማራነትና ኢትዮጵያዊነት ወንጀል ሆነዋልና ለመጨረሻው የአልሞትባይ
ተጋዳይ ፍልሚያ እንዘጋጅ፡፡ ቁርጡን ካወቅነው የትግሉ ውጤት የሚያዘነብልበትን አቅጣጫ ለመተንበይ ቀላል ነው፡፡
ራስን ከጥቃት መከላከል ወንጀል የሆነባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ ከአሁን በኋላ ይህን መንግሥት
ማመን አስቸጋሪ ብቻ ሣይሆን በፍጹም የሚቻል አይደለም፡፡ ቄሮ ሲመጣብህ መሸሽና አንገትን ከቆንጨራ ለማዳን መሞከርም በህግ የሚያስቀጣ
አንቀጽ የሌለው ወንጀል ሊሆን ነው፡፡ አክራሪ ኦሮሞ ሲመጣብህ ቆሞ መጠበቅና የሚደርስብህን በጸጋ መቀበል ህግን እንደማክበር ከተቆጠረ
ከእንግዲህ አገር አለኝ ማለት አንችልም፡፡ መንግሥት እነጃዋርን አሰራቸው ማለትም አይቻልም፡፡ የሚደረግላቸው ክብካቤ ልዩ እንደሆነ
እየሰማንና እያየን ነው - ከርቸሌ ገብቶ ያልታሰሩ የቅንጅት አባላትን ሲሾም ሲሽር እንደነበረው እንደኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል ጃዋር
እስር ቤት ውስጥም ሆኖ የመንግሥትነት ጠባዩ የለቀቀው አይመስልም - እንደምናየው ከእስረኛ ዓለም አቀፍ አያያዝ በተለዬ ሁኔታ በቪ8
እና በተለዬ አክብሮትና አጀብ ነው ወደ ፍርድ ቤት እንኳን የሚመላለሰው፤ ተፅዕኖው ቀላል አይደለም፤ በዚህ አኳኋን በቅርብ እንደሚፈታም
መገመት አይከብድም፡፡ ለምሣሌ በበቀደም አንድ የጊዜ ቀጠሮ ለነእስክንድር ተጨማሪ ምርመራ 13 ቀን ሲፈቀድ ለነበቀለ ገርባ ግን
11 ቀን ነው፡፡ ምን አለፋችሁ - ይህን በዘረኝነት የጠነባ የአቢይ መንግሥት በሰላም ካልተገላገልን የኢትዮጵያ ትንሣኤ መቼም እውን
አይሆንም፡፡
ይልቁንስ ትንቢትን ማክሸፍ የሚቻል ከሆነ በየሃይማኖታችን አጥብቀን እንጸልይ፡፡ መጪው ጊዜ ካለፈው
እጅጉን ከባድ ነው፡፡ ትልቅ ሰውም የለም፤ ሃይማኖትም የለም፤ ሃይማኖተኛም የለም፡፡ በሁሉም ከስረናል፡፡ አንድ ነገር ቢነሳ ማንም
አያድነን፡፡ ዓለም ደግሞ የባለጌዎች መናኸሪያ ከሆነች ቆየች፡፡ እንጂ የንጹሓንን ደም ለማፍሰስ አውስትራሊያና አሜሪካ መሽገው ጃዝ
የሚሉ ተኩላዎችን ለማስቆም የሚከብድ ሆኖ አልነበረም፡፡ ዘመኑ የመጨረሻው መሆኑን እንድናምን የሚያስገድደንም ይሄው የጭካኔ ትስስር
ነው፡፡
ማኅበረሰቡ በሞራል ላሽቋል፤ በሃይማኖት ወድቋል፤ ባህልና ወጉን ተነጥቋል፤ ማኅበራዊ ወግ-ሥራታዊ
ተራክቦው ከሞላ ጎደል ተበጣጥሷል፡፡ በቀደምለት ዮንሐስ አካባቢ ገዳም ሰፈር በሚባለው ልዩ ቦታ የታዘብኩት ክስተት ኢትዮጵያ እንደሀገርም
እንደህዝብም ትልቅ ችግር ላይ መውደቋን አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው - እኔ በራሴ ተሸከርካሪ ቀስ ብዬ እያለፍኩ ነው፡፡ አንድ የቆመ ዲኤክስ መኪና ተነስቶ ሊሄድ ማርሽ እያስገባ
ነው፡፡ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ሁለት የጉሊት ሴቶች ተንደርድረው ሲመጡ አያለሁ፡፡ ሣር ቢጤ ይዘዋል፡፡ አንደኛዋ ማንም ሳይነካት ከመኪናው
የኋላ ኮፈን ጋር በዘዴ ተጋጨችና ተምበልብላ ወደቀች፡፡ መኪናው አልገጨም፤ የጀመረውንም እንቅስቃሴ ወዲያውኑ አቆመ፡፡ ትያትር የማይ
መሰለኝ፡፡ ይህንን የአጭበርባሪዎች ዘዴ በፊትም አውቀዋለሁ፡፡ እንደዚህ ሲገጥመኝ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ያቺ በራሷ ጊዜ ጎማው ሥር
የወደቀችው ሴትም ጓደኛዋም ያገር ያለህ እያሉ ጩኸታቸውን ማቅለጥ ጀመሩ፡፡ ሹፌሩ ደነገጠ፡፡ ሕዝብ መሰባሰብ ጀመረ፡፡ እኔ ንዴት
ብልጭ አለብኝና ከራሴ መኪና ወርጄ በጩኸት ወደ ጀማው ተቀላቀልኩና ሕዝብና መንግሥት ህግና ሥርዓትም ያለ መስሎኝ “እነዚህን ሴቶች
ከመነሻው አይቻቸዋለሁ፡፡ ትያትር እየሠሩ ነው፡፡ ልጁ አልገጫቸውም፡፡ ...” እያልኩ ምስክርነቴን ባደባባይ መስጠት ጀመርኩ፡፡
ፖሊሶችም ነበሩ፡፡ የአካባቢው ሰው ግን እኔን ሳይሆን ሴትዮዋን ደግፎ ይንጫጫ ጀመር፡፡ ትያትሩ መንደር አቀፍ መሆኑ ገባኝ፤ እርግጥ
ነው ሰፈሩ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች መኖሪያ ይመስላል - ያን ያህል የሞራል ዝቅጠት ይኖራል ብሎ መገመት ግን
ይከብዳል፤ እየሆነ ያለው ግን ሌላና አስደንጋጭም ነው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም በኔ ይዝቱ ገባ፡፡ ሁኔታው ሳያምረኝ ሲቀር እያበድኩ
እየተከንኩ አካባቢውን ለቅቄ ሄድኩ፡፡ ራቅ ብዬ ስከታተል የተወሰኑ ሰዎች ተገጨች የተባለችውን አጭበርባሪ በመኪናው ጭነው ሄዱ፡፡
ቀጥሎ የሚሆነውን መገመት ቀላል ነው፡- መንገድ ላይ ይደራደሩና “ማገገሚያና መታከሚያ ጥቂት ገንዘብ ስጣትና እዚሁ ተስማሙ” ይባልና
ገንዘብ ተቀብለው ባለመኪናውን ይሸኙታል፤ “ገጪው”ም ከህጋዊና ህክምናዊ ውጣ ውረድ በመገላገሉ ያላመነበትን ነገር አድርጎ ከውጣ
ውረድ ይድናል፡፡ እስከዚህ በስብሰናል፡፡
በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየእምነት ቤቱ፣ በየምናምኑ ... ሁሉ እንደዚህ ያለ ንቅዘት በስፋትና በጥልቀት
ይታያል፡፡ ይህን መበስበስ ለማስወገድና ወደ ትክክለኛው ስብዕና ለመምጣት ራሱ ብዙ ጊዜንና ብዙ ትግስትን፣ ብዙ የተማረ የሰው ኃይልንና
በጀትን፣ ብዙ ቆራጥነትንና የሀገርና የወገን ፍቅርን፣ ... በጣም ብዙ ብዙ ነገርን ይጠይቃል፡፡ አቢይም የዚህ የበሰበሰ ማኅበረሰብ
ውጤት ነውና በውሸታምነቱ የተቆራኘው የአጋንንት መንፈስ ከየትም እንዳላመጣው በዚህ አጋጣሚ መመስከር ይቻላል፡፡ በወለድነው እንጦራለን፤
የዘራነውንም እናጭዳለን ... በዚህ መሀል ግን አዲዮስ ሀገር፤ አዲዮስ የመንግሥት ህዝባዊ አገልጋይነት፤ አዲዮስ የሞራልና የሥርዓት
ዕሤቶች.... አዲዮስ ህግና መንግሥት ... የአሥር ዓመት ሕጻን ልጁን የደፈረና የደበደበ ዋና ሳጅን የዘጠኝ ዓመት እሥራት ብቻ
የሚፈረድባት ሀገር ዱሮውንስ ምን ሀገር ሆነች .... ውይ ኢትዮጵያ! ቺድ! በቃኝ እባክህን፡፡ ሳይጠጡ የምታሰክር፣ ሳይኖሩባት
የምታስረጅ ሀገር!!
ma74085@gmail.com
No comments:
Post a Comment