Monday, January 13, 2020

ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር ! ድጋፍ ለጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) ጥር 3/2012 ዓ.ም (ጃንወሪ 12/2020)


ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር !
ድጋፍ ለጋዜጠኛ ታምራት ነገራ

ጌታቸው ረዳ (Ethio  Semay)

ጥር 3/2012 ዓ.ም  (ጃንወሪ 12/2020)

“Eritrea Licks its wounds” (quoted BBC Focus on Africa) - during the Badime war between Eritrea bandits and Ethiopia gallants) ትርጉም ኤርትራ ቁስሏን ላሰች (ቢቢሲ ትኩረት በአፍሪካ- ዘገባ “ኢትዮ- ኤርትራ ዋር” ተብሎ በሚጠራው ስለ የባድሜ ጦርነት ሲዘግብ ኤርትራኖች 3/4ኛውን መሬታቸውን ጥለው ተሸንፈው “ፈርጥጠው ወደ አስመራ እና ወደ ሱዳን” እየሸሹ በነበሩበት ለታሪክ የተዘገበ ርዕስ ነው፤ “Eritrea Licks its wounds”
ከአዘጋጁ ማስታወሻ
ለኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አንባቢዎቼ መልካም ንባብ እያልኩ ላልተወሰ ጊዜ ከምኖርበት ካሊፎረኒያ ለህጸጽ ጉዳይ ወደ ሌላ ስለምጓዝ፤ እስክመለስ ድረስ “ጭር” አንዳይላችሁ ይህንን ረዢም ሰነድ ያቆዩያችኋል።  መልካም ሰሞን ያድርግልን።  

አሁን ወደ ታሪካዊ ክርክራችን ትንታኔ ልግባ።
ወያኔና ሻዕቢያ በውጭ ሃይላት ተደግፈው በሕገ ወጥ መንገድ መንግሥትነት ተቆጣጥረው አንድ አገር ለሁለት ከፍለው፤ 1998 ተጠያቂነት በሌለው ጦርነት ውስጥ 70 ሺሕ ሕዝብ ህይወት አጥፍተው አንዳቸውም ተጠያቂ አልሆኑም። የድሃ ልጅ ሞቶ ቆስሎ እነሱ አሁንም ሥልጣን ላይ አሉ።


ትግሬዎችን የተካው በኮለኔል አብይ አሕመድ የሚመራው ተረኛው ዘረኛው የኦሮሞዎች አፓርታይድ መንግሥት ከመጣ ወዲህ የጄዳ ስምምነት ተብሎ ሳውዲ ውስጥ የተፈረመው አንቀጽ 4 በጠቅላላ አወዛጋቢው የ1200 ኪ.ሜ የድምበር መስመር ባድሜን ጨምሮ ሕገወጡ “የአልጄሪሱ ስምምነት” መሰረት አድርጉ ለኤርትራ ሊሰጥ በምዕራባውያን አለቆቻቸው የሚመሩት የተባበሩት መንግሥታት ሊቀመንበሩ አንቶንዮ ጉተሬዝና ቻዳዊው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ‘ሙሳ ፋቂ ሞሃመት” አፈራራሚነት ፈርሟል። ይህ ሴራ  በሕግም በታሪክም ዉሃ ባይቋጥርም፤ ሊጎዳን የተሴረ ሴራ ነውና ይጎዳናል። አንዳንድ ጅል ኢትዮጵያውያን ጦርነቱን ለማቆም ሰላም ለማምጣት ስለሚረዳ  ባድሜ ለኤርትራ ያለ ቅድመ ኩነት/ሁኔታ መሰጠት አብይ የገባበትን ውል እንደግፋለን በማለት  የመለስ ዜናዊን ሴራ እውን እንዲሆን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲጪሁ እየሰማን ነው ።

 ኢትዮጵያን በመጉዳት የሚመጣ የሴረኞች ሰላም ከተጨባጩ ሃቅ የራቀ ስለሆነ፤ መነሻውና ማቆሚያው በቅጡ ካላወቅነው፤ ሰላም ፤ሰላም፤ሰላም ብቻ ስለተመኘን ሰላም ሊመጣ አይችልም። ሰላም ያመጣል ተብሎ መለስና ኢሳያስ በበረሃ ስምምነታቸው መሠረት ኤርትራን ካስገነጠሉ በኋላ እስከ 70ሺ የሰው ህይትን በርካታ ንብተረትና መፈናቀል ደርሻል። ምክንያቱም ግልጽ ነው። በሴራ የተፈጸመ  የድብብቆሽ ፌርማ ቀን ጠብቆ ይፈራርስና ጸቡ ያገረሻል።

ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፤ ኤርትራኖችም ሆኑ ወያኔዎችና ዛሬም ያለው አደገኛው የመለስ ዜናዊ ኮቴ የተከተለው “ኦነጉ” አብይ አሕመድ ኢትዮጵያንም ሆነ ሕጋዊ ውክልና ያላቸው መሪዎች ስላልሆኑ ከሥልጣን ተወግደው፤ ኤርትራን የሚረከብ ቡድንኢትዮጵያዊነትንአክብሮ አንድ አገር የሚያደርግ፤(ሕዝባችን አካላችን ናቸው ብንልም እነሱ ስለማይፈልጉን እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ኤርትራኖችም ሆኑ ኤርትራ ውስጥ ያሉ ኤርትራውያኖች አገራችን የምትሰጣቸው አቅርቦትና ጠቀሜታ ትተው የፈለጋቸው ይሁኑና) ወይንም ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የባሕር ወደባችንን በፈቃዱ ለኢትዮጵያ እንዲያስረክብ የሚፈቅድ ቡድን ወይንም የሚገደድ ቡድን ሲፈጠር ያኔ ወሳኙና የሰላም ምንጩና መፍተሄው ይህ ይሆናል።

አናደርግም የሚሉ ከሆነ እና የኢሳያስና የሻዕቢያ  መንገድ እንከተላለን የሚሉ ከሆነ፤ ጊዜ ይፈጃል እንጂ በመጪውየነቃ ትውልድከባንዳነት የጸዳ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወደ ሥልጣን እንዲወጣ ሲደረግ፤ ወይንም የኢትዮጵያ አምላክ በአስገራሚና አስደንጋጭ ተአምራቱባንዳውመለስ ዜናዊናአበ ነብሱየነበሩት አባ ጳውሎስን በተአምር እንዳስወገዳቸው ሁሉ፤  አብይ አሕመድም” በተመሳሳይ ጥሪ ወደ ሌላኛው ዓለም “ከተጠራ”  አንድ አገር ወዳድ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ወታደር ወይንም ሲቪል ወደ ስልጣን ሲቆጣጠር፤ ባንዳዎች የወሰኑት ውሳኔ ሽሮ ከላይ የጠቀስኩትን የሰላም አማራጭ መንገድ አንወስድም ብለው የሚያንገራግሩ ኤርትራ ቡድኖች ከተከሰቱ፤ የናፈቁትን ጦርነት ከፍቶ፤ ዓሰብን 30 አመት የተኮናተሩትን ዓረቦችን እንደለመዱት ማራወጥ እና ባሕሮችንን መለስን መቆጣጠር፤ የአሉላ አባ ነጋ፤ የአምደፅዮንን ታሪክ መድገም የመጨረሻው አማራጩ የመፍትሔ ሃሳብ ሲፈጸም ብቻ ነውሰላም እያልን የምንኳትተው ሕልም እውን የሚሆነው”። የኤርትራኖች አቅምም ያው ባድሜ ላይ ያያችዩት ነው። “Eritrea Licks its wounds” (quoted BBC Focus on Africa “ኤርትራ ቁስሏን ላሰች” (ቢ ቢ ሲ)

ካልሆነ ሰላም ስለተፈለገ፤ መነሻውና ምክንያቱ ሳንዳስስሰላምበገዛ ፈቃዱ በነዚህ ወረበሎች ጊዜ ሊመጣ አይችልም።ሁለቱም ወረበሎች የሚሰጡት መልስ ለጦርነቱ መነሻ እና ለሰላም ጠንቅ በመሆኑ፤ ያለ ሕግ የተነጠቅነውን የኤርትራ መሬታችንና በባርነት የያዙትን ሕዝባችንን በድርድር ያስረክቡን። ካልሆነ ጦርነቱ መቼም ቢሆን አይቀሬ ነው።  ደርግን በሴራ አስወግደው ኤርትራን ሲገነጥሉ “ጦርነት አይቀሬ ነው” ብየ ጽፌ ተናግሬ ነበር (ብዙ ወገኖቼ ይህንን ይመሰክራሉ) እንዳልኩትም በ1989 በኢሳያስ ፀብ ጫሪነት ዘግናኝ ጦርነት ተደረገ። አሁንም ይደገማል~~~~!!!  ባንዳዎችም ሆኑ የተቀራችሁ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ኢትዮጵያ አገራችን እንዴት እና ለምን እንደተበደለች ምክንያት አለኝ፤ ምክንያቴን አንብቡ።

          ኤርትራኖችና የ እንእኒምናባዊ ሕልም
                    
 በዚህ-ጽሑፍ ሻዕቢና ወያኔዎች (ዛሬም አብይ አሕመድ) 27 አመት-መልስ ያጡበትና ያሳፈራቸው አንድ አጭር እና ግልጽ ጥያቄ እንመለከታለን። ድሮ በልጅነታችንእንእኒ” (ሲነበብ ይጥበቅ) የሚባል ዘመን ነበር ሲሉ ወላጆቻችን ያጫውቱናል።  እኛም ያንኑ ትረካ ተቀብለንዝናብ ሲዘንብጓደኛሞች የሆንን ሁሉ ሁሌም በምንጫወትበት ሞቃታ ስፍራ ሰብሰብ ብለን ተጠጋግተን በብርዱ ላለመጠቃት ተኮማትረን ተቃቅፈን  ስለዘመኑ እውነተኛነት በዓይናችን ያየን ይመስል የራሳችንን ቅጥያ ጨማምረን አጣፍጠን ከፊት ለፊታችን የሚታዩ የድንጋይ ኮረቶች ሁሉ የዛው ዘመን የአምቧሻ ቅሪት መሆኑን በእርግጠኝነት እናወራ ነበር። ዘመኑምዘመን እንእኒይባል ነበር።

 በዛ ዘመን ምን ነበር? ብለን ስንጠይቅ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ነበር ማረስ መዝራት፤ መውጣት መውረድ አያስፈልግም ነበር።ብዘመን እንእኒ ሕምባሻ እንተሎ እምኒድንጋይ ሁሉ አምቧሻ የነበረበትየእንእኒ ዘመንአጣፍጠው ወላጆቻችን የነገሩንን እና እኛም ጨማምረን ስለ ዘመኑ መልካምነት እናወራ ነበር።ታዲያ እግዚሃር በሰው ልጆች ስነ ምግባር ተቆጣና አምቧሻው ወደ ድንጋይ ለወጠው ይባላል። ኤርትራኖችምድሪ ባሕሪነፃ ስትወጣ ወደዘመን እንእኒተመልሳ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ሆኖ አንደሚቀየር ለእናቷ ኢትዮጵያም ከሚትረፈረፈው አምቧሻዋ አንደምታጎርሳት ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው የኤርትራ ኢኮኖሚስቶች ያልቀባጠሩት ዲስኩር አልነበረም።

አንድ እውቅ የጦቦያ ጸሐፊ (ማን መሆኑን አላስታወስኩትም) ኤርትራ ነፃ ስትወጣ፤ድሮ በጥንት ጊዜ ራሴን ችዬኤርትራስባል የነበርኩኝ  አገርነኝ  ታዲያኢትዮጵያየምትባል ከኋላየ የተፈጠረች 60 አመት ዕድሜ ያላት አገር በጉልበት አጠቃልላኝ ነው እንጂ አገር ነበርኩኝ፤ አሁን  ግን ነፃ አውጡኝ፡ እያለች እረፍት ስለነሳችን ነፃነቷን ለመስጠት ተዘጋጅተናል እና ኤርትራ የምትባል አገር በፈጠርካት በዚች ዓለም-ምድር ተዘግባ ታውቃት ነበር? ብለው እግዚሐርን ሲጠይቁት ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ብሎ መዝገቡን ሲፈትሽ ማግኘት አልቻለም። አንዲህ የምትባል አገር አላውቅም! ምነው ጊዜን ባታባክኑብኝብሎ እግዚሓርም ራሱ ተገርሞ ነበር ይባላል። ትክክለኛ አባባሉ ባይሆንም በራሴው ማጠጋጋት (ፓራፍሬዚንግ) እንዲያ ብሎ ጽፎ ነበር።ኤርትራ ዛሬ 22 አመቷ ነው ነፃ ከወጣች። እገምጠዋለሁ ያለቺውየዘመን እንእኒ ቅዠትድንጋይ ብቻ ሆኖባት ፈዝዛ ቀረች።

ኤርትራ ሁሉም ሞክራዋለች። ግድያ፤ ዘር ማጥፋት፤ ሕዝብን ወደ ባርነት መለወጥ፤ ጥቁር ገባያ፤ ሌብነት፤ ስም ማጥፋት፤ ውሸት፤ጉራ፤ ወንጀል፤ ጦርነት፤ሽብር፤ስደትና ዕብደት፤ ሁሉንም ሞክራዋለች። ከዚህ ወዲያ የሚቀራት መደምደሚያዋ ወደ አመድነት መጓዝ ነው።ከዚያ ጣረ ሞት መዳን ከፈለገችየቀራት አማራጭኢትዮጵያዊነትዋንበቁርባንተቀብላ ከዘላለማዊው ቅዠት (ደሉዥን) እና ሞት መዳን ነው። ካልሆነ ግን እንደምታስታውሱት “የኢሳያስ ኤርትራ” ከባድመ ጦርነት በኋላ “እጅግ ከፍቷት ስለነበር የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት እንዲቃጠሉ የወሰነባቸው በሽታ የለከፋቸው የአውስትራሊያ በጎችን በምጽዋት ተመጽውታ መሳቂያና መሳለቂያ እንደሆነቺው ሁሉ  በውንብድና የፖለቲካ በሽታ የተለከፈች መንድር በመሆንዋ የመጨረሻ ዕድልዋመበላሸት፤ ስደት፤ ጦርነት፤ሞት፤ውርደትይሆናል።በውንብድና እና በውሸት በዘር ፖለቲካ ተለክፈው ለሚሰቃዩ ኤርትራኖች እና የወያኔ ትግሬዎች ፈውስ አለን። ኢትዮጵያነት!! የተሰኘ መድሃኒት።
ኢትዮጵያዊነት ለምን? የሚሉ የኢሳያስ አለቅላቂዎችና ጀብሃዎች መሪዎች እና የትግራይ ወያኔዎች የታሪክ አተላዎች ክቡር ፕሮፌሰር አስራት የተናገሩትን ልጥስላቸውና ልሸጋገር። ጥቅሱን ያገኘሁት ከፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ ነው።

... 1991 (...) ሐምሌ 1-5 (...). “ቻርተርበተሰኘው ስብሰባ ላይ ሰማዕቱ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ቃላቸው እንዲመዘገብላቸው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ


 ይህ ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም የመወሰን የመተው ወይም የመሰረዝ ስልጣን የለውም ፡፡ ሆኖም አንድ ሰው በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የወቅታዊ ሁኔታ ሁኔታ ይገነዘባል ይህም በወንድማማቾች መካከል የደም ጠብ መቋረጡን እንዲሁም የአሁኑን የሰላም እና የዴሞክራሲን ፍጥነት ይጨምራል ፡፡ ኢሕአዴግና ሕዝባዊ ግምባርም በወንድማማች እና እህትማማች (በኢትዮጵያ-ኤርትራዊ) ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በአፋጣኝ ለመስራት የኢትዮጵያን እና የይቅርታ መንፈስ እንዲመጣ ለማድረግ ልዩ የቅርብ ግንኙነታቸውን ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡..” በማለት ጠቃሚ ምክርና ተቃውሞ አቅርበው ነበር።

ሆኖም ጀሮ ስላልነበረ፤ ፕሮፌሰሩ የሰጉትን ነገር ተፈጸመ የባድመ ጦርነት ተከሰተ። አሁንም የሚያምነን የለም። አንዴ በክሕደት የተቀረጸ ሕሊና ጩቤው እስኪነካው ድረስ አይነቃም።

አትዮጵያዊነት!!!” የዘላቂ ሰላም መፍቻውና ቁልፉ እሱ ብቻ ስለሆነ በዛው ፈውስ ተዳኙ ነው ያሉት። ይኼ ፈወስ በትዕቢት ንቃችሁ ወርውራችሁት እንደወትሮው በመንገዳች ግን፤ ዘላቂ ሰላም ሳይሆን ዘላቂ ጦርነት ብቻ ነው የሚከተለው እውንኢትዮጵያዊነትእየተናቀ፤ ባንዳነት እየጎለበተ ከሄደ፤ ሰላም የሚባለው የነ ሻዕቢያ እና ወያኔ እንዲሁም አዲሶቹ  ኦሮሞ ባንዳዎች የሚዋሹትየሰላም መንገድ አጭበርባሪዎች የቀየሱት የባንዳዎች መንገድ ስለሆነ ሕዝባችን ለሁለተኛ ጥፋት እንዳትራመድ እነዚህን በጠራ ዓይን እና ሕሊና መርምሩት።

ታሪክ አለን! ታሪካችን ባንዳዎችም ሆኑየተባባሩት ግሳንግስ መንግስታት ማሕብር”  ሊጠመዝዙት አንፈቅድም። ቢሞጅሩም ምንም አያደርጉም የድምበር ተመራማሪው እንግሊዛዊው አስተያየት አድምጡ” ኢትዮጵያ ካልተስማማች ማንም ሃይል ሊያስገድዳት አይቻለውም ብሎ ነበር’። አገር ወዳድ ወይንም ባንዳ የሚያስብለን ታሪካችን እና መልህቃችበጊዜአዊ አስቸጋሪ ማዕበል ስንለቅ ወይንም አጥብቀን ስነይዝ ብቻ በዚያው ስያሜ እንጠራለን ሁለታችን የሚለየን ታሪክ በማጉደፍ እና ታረክ አጥብቆ በመያዝ ነው። የወላጆቻችን አደራ አናስበላም። አርበኞች ነበሩን፤ ታሪክና ታሪካቸው አለን;፡ታሪካችን እና ጭብጨጣችንም እነሆ አንብቡ። ኢትዮጵያ አለቀላት ብለው ከጠላቶች ጋር የሚደባለቁ ከሃዲዎችኢትዮጵያ እንዳላለቀች  ዛሬም ነገም አለን! አለን! አለን! እንላቸዋለን።፡ታሪካችን እነሆ። መልካም ንባብ….

ጣሊያኖች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ Ethiopia E Finita !!!! (ኢትዮጵያ አለቀላት) የሚል መፈክር የያዙ ትሬንታ ኳትሮዎች አዲስ አበባን ወርረዋት እንደነበር ጆን ስፔንሰር Unity and territorial integrity (የግዛት ውሁድነት) በሚለው መጽሐፉ ጠቅሰው እንደነበር አንድ የዛሬው የቅርብ ወዳጄ የሆኑ በጦቢያ መጽሄት ላይ ጠቅሰው ነበር። የተጠቀሰው መፈክር፤ ዛሬ ያለምን ጥርጥር ኤርትራ ካለ ኢትዮጵያ መኖር የማትችል በጉራ ብቻ የተነዳች፤ ኗሪዎቿ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ሰሓራ የሚሰደዱባት፤ደካማ አውራጃዎችን የያዘች፤ ያለቀላት የተበላሸች መንደር ነች። ሰርጓም ሞትዋም 25 አመት ውስጥ ተጠናቀቀ። ዕጣ ፈንታዋነፃነት” (የኤርትራ ባርነት) ብላ የገለጸቺውን ነፃነቷንከአመዳም ሕይወት ለመውጣት’ ስትል እንደገናእራስዋን መፈተሽአለባት።ለ25 አመት የተሰጣትየኦክሲጅን ስሊንደርአልቋል! ከዚያ ወዲያ መቀጠል full of difficulties/ ነው። ብልሽት! ነው የምለው ዛሬ አይደለም። ቆይቷል።


ኤርትራዊው አማረ ተኽለ ዴንቨር ዩኒቨርሲቲ ለዶክተሬት ዲግሪው መመረቂያ የጻፈው የምርምር ወረቀት The creation of the Ethio-Eritrean Federation; a case study in post-war international relations, 1945-1950. ላይ እንዲህ ይላል፤-

ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩት የአካባቢው ታሪክ የማያውቁ ወይም ሊቀለብሱት የሚፈልጉ የሙሶሎኒ ፋሺስታዊ ፖለቲካ የሚጋሩ ብቻ ናቸው።ይላል።

 አማረ በድሮ ጊዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ኢትዮጵያዊነቱን አምኖ ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረ፤ በኋላ ታስሮ ሲፈታ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስራ ለመመለስ ሲሞክርይህ ሰውዬ አባርሩልኝብሎ / ጐሹ ወልዴ አንዳይቀጠር የከለከለው ሰው እንደነበር ኤርትራኖች ፅፈውበታል። አማረ ተኽለ የዛሬ አያድርገው እና ያኔ ሕሊናው ሲከተል በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ የኤርትራ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩ ሰዎችን “/Neo Fascist ፋሺስትናቸው ብሎ ለዲዘርተሼን በጻፈው የመመረቂያው የጥናት ጽሑፍ የነገረን ረስቶት ጊዜ መስተዋቱ! ዛሬ እራሱ ወደ ኒዮ ፋሺስቶቹ በመቀላቀል፤የኤርትራ ርዕሰ ውሳኔ ኮሚሽነር/አስመራጭበመሆን የውስጥ እና የውጭ የወረበሎች ስብስብ ያዘጋጁትን የወያኔና የሻዕቢያ ሬፈረንደም ባዘጋጁት ሴራ ውስጥ በመሳተፍ እንድትገነጠል ከጣሩት ቀዳሚ ኤርትራዊያኖች አንደኛው / አማረ ተኽለ ነበር።
ባለ ሁለት ምላሱ አማረ ተኽለ ወንበዴዎቹ ያዘጋጁትን የግንጣላ ሴራ ስለ ሪፈረንደሙ እንዲህ ይላል፤

 “the referendum process as one of the fairest and freest of referendums ever.” የድምፀ ውሳኔው ሂደት የተካሄደው በቅንነትና በነፃነት ከተካሄደባቸው ሂደት አንዱ ነው።”
 ሲል ዘረኛው እና ኢፍትሃዊው ሬፈረንደም ከማድነቁ በላይ፡ የሻዕቢያ ተቀጣሪ ሆኖ ቱልቱላውን በመንዛት Eritrea is in the stage of democratic transition በሚል ንኡስ ርዕስ በዲሞክራሲያዊ ሽግግር ድልድይ እንድትራመድ እየመራት ያለው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ አፍሪካ በታሪኳ ያላየቺው ጠንካራ መሪ በማለት።

 There is, as is almost universally agreed by African social scientists, the need for a strong leadership to guide this process. Eritrea is blessed with such a strong leadership whose source of legitimacy is a Rousseauean General will of the population has shaped and shares the vision of the government. It is this leadership that you demonize as authoritarian either out of ignorance or political malice.

ሲል የምሁርሊጥ”-ነቱን አይ ኤውየወያኔ አፈ ቃላጤ ለነበረው ፖል ሄንዝ March 21 /1999 በባድሜ ጦርነት ጊዜ በጻፈው ጽሑፉ ነግሮናል። አሁን አለማፈር ጠንካራ መሪ ብሎ ሲያሞግሰው የነበረው ኢሳያስን በመቃወም፤የኤርትራ ነፃነትበኢሳያስ ዲክታቶሪያል ባሕሪ እየተረገጠ ነው፤ ሲል ተቃዋሚ ሆኗል። ዛሬ ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸችበረዶ ውስጥ ተቀብራ መውጫ ቀዳዳው ጠፍቶባት ያለች መንደርእንደሆነች እኔ ብቻ ሳልሆን፤ ደጋፊዎቿ የሆኑ የውጭ አገር ሰላዮች እና ጸረ ኢትየጵያ ሃይላትም ይህንን እየደገሙት ነው።
ለምሳሌ’- December 2013, Herman Cohen አንዲህ ብሏል።
“bringing “Eritrea in from the cold” was overdue.” ኤርትራ “ከሠጠመችበት በረዶማ ብርድ የማስወጣቱን ሂደት አሁን ነው” ይላሉ በሺወቹ ዶላር እየተከፈለው በጥብቅና ለኤርትራ የሚሰራው አማካሪያቸው ኮኸን ሄረመን እና መሰሪው ጸረ ኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ቅርብ ወዳጅና
የ ኦጋዴን ነፃ አውጪዎች አማካሪ አምባሳደር ዴቪድ ሺን-David Shinn’። ይህ መሰሪ ደግሞ “The idea that Assab belongs to Ethiopia is outdated” ሲል ይከራከራል።

 ልብ በሉ። አገራችን ምን ያህል የባንዳዎች ብዛት እና የውጭ ጣላት እየተረባረቡባት እንዳሉ ጥልቅ ግንዛቤ ይኑራችሁ።ለዚህ ነው ይህነን ሰፊ ትንታኔ አንድታነቡ በትዕግስት የምጠይቀው። የኦጋዴን እና ኤርትራ ተገንጣዮችን የሚያበረታታው የዴቪድ ሺንንአናርኪንግግር ወደ ጎን እንተው እና ኤርትራ ያለ ኢትዮጵያብርድልብስመኖር እንደማትችል ካወቁ በኋላ Ambassadors Princeton Lyman, Herman Cohen, David Shinn’ ኤርትራን ከቀዝቃዛው በረዶ እናወጣት ብለው አዲስ ዘመቻ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። የፈረንጆቹ ኰቴ ተከትለውም አዳዲሶዩ የግንቦት 7 ባንዳዎችምኢሳያስን ወደ ፍርድ አታቅርቡት” “ኢትዮጵያን ይወዳል” “አማራዎችን ጠልቶ ወይንም ገድሎ አያውቅም” “አይገድልም’ ‘አይሰርቅምዜጎች አያንገላታም፤ አይገርፍም፤በተጨማደደ ሸሚዝ፤ በበርባሳ ጫማ በጨረጨሰ መኪና የሚጓዝ፤ ካለ ውሃዊስኪ የማይቀምስ” ፤ ምርጥ ሕክምና ፤ምርጥ ትምህርት በነፃ የሚሰጥ፤ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን መሪ ነው” (ይህንን ያለው አንዳርጋቸው ጽጌ) ሲሆን እነ ብርሃኑ ነጋ፤ እነ ንአምን ዘለቀም ተመሳሳይ የባንዳ ጥብቅና ሲናገሩና ሲቆሙ ወደ ተባባሩት መንግሥታት “ፐቲሽን” (ለኢሳያስ ድጋፍ) ሲያመለክቱ አድመጠናል/አንብበናል። እነዚህ የኛዎቹ ባንዳዎችም በነ ሄርምን ኮኸን መንገድ እየተጓዙ ነው። ያውም ዓይን ባፈጠጠ ጥብቅና እና በሚያሳፍር  መልኩ። 

ፈረንጅም ሆነ ባንዳ ኢትዮጵያውያን ለኤርትራ መሰረታዊ ስቃይ መነሾግንጠላው መሆኑን ሊገባቸው አልቻለም”።  የኤርትራ ጥያቄ እና ትግሉ ከጅምሩ የተወላገደ መነሾ መሆኑን መረዳት አቅቷቸዋል። ዛሬም ሊሂቃኖቹ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ጉዞ፤- ለሃፍረታቸው መሸሺያ ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር ከመወሃድ ኤርትራትሙትብለው ኤርትራኖች ራሳቸው ፈርደውባታል። ሞታለችም። ይህንን ሁኔታ ያሳሰበው በጀርመን የብረይመን ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር (የፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መደሃኔ “ይኼውና ኤርትራ ሞታለች! ትግል ለሀገር ትንሳኤ!!” በማለት ጥር 2007 ዓ.ም (ጃኒዋሪ 2015) የፃፈው ባለ 58 ገጽ ዝርዝር ማሕደር ማንበብ ጠቃሚ ነው። ፕሮፌሰሩ በሌላ ጽሑፉ ‘ብዙ ኤርትራውያን በቅኝ ግዛት፤ በፈደረሽንና በኮንፈደረሽን መሃል ያለውን ልዩነት ፍጹም አያውቁም፡፡” ሲል የምሁራኖቹ ግብዝነት በመገርም ሰፊ ዝርዝርም እንደሰራበት አስታውሳለሁ።

ሞት የውርደት መሸሻ ዋሻ ነውና፤ ከውርደታቸው ለመሸሽ ሲሉ ሞቷን እያቀላጠፉላት ይገኛሉ።
 ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ መኖርም ሆነ በፌደረሽን መኖር እንደሚጎዳቸው የድሮ የባሕር ነጋሽ ተወላጆች በፌደረሸን ጉዳይ አጣሪ ኮሚቴ ሆነው የመጡ የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኞች አስመራ ተገኝተው በነበሩበት ወቅት በአቤቱታ መልክ ገልጸዉ እንደነበረ ታሪክ ዘግቦታል። ኤርትራ እስከ 1889 . (..) ድረስ፤ መረብ ምላሽ/ምድሪ ባሕሪ/ባሕረ ምድር/ባሕሪ ነጋሲ/ባሕረ ነጋሽ እየተባለች ስትጠቀስ የነበረቺው የጥንቷ ኢትዮጵያ አካል ‘ሓንቲ ኢትዮጵያ/አንድ ኢትዮጵያ’ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” ብለው በመነሳትማሕበር ፍቕሪ ሀገርድርጅትን የመሰረቱ ወላጆቻቸው መገንጠሉ ኤርትራን እንደሚጎዳ እና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ራሷን ችላ መኖር የማትችልበት ምክንያት ለሕብረቱ ጥያቄ  ምክንያቶቹ ካቀረቡዋቸው ነጥቦች ውስጥ በምጣኔ ሀብቱ እና በቤተሰባዊ ግንኙነት በሚመለከት ከክረስትያኖቹ እና ከእስላም ማሕበረሰብ ተወክለው አቤቱታ አቅራቢዎች በሁለት ነጥቦች የሚከተለውን አቤት ያሉበትን አቤቱታቸውን ታሪክ ዘጋቢዎች በጦቢያ መጽሄት ላይ ያኔ ኤርትራ ነፃ ወጣህ ባለችበት ወር ከዘገቡት ሰነድ ልጥቀስ።
 እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ ረዢሙን አቤቱታ ባጭሩ ላስቀምጥ ያንብቡት፡፡

                  ከሁሉ አስቀድሞ መርማሪው ኮሚሲዮን ባቀረበው ውስጥ እንደተገለጸው እኛ የኤርትራ ሕዝብ ለኑሮአችን በቂ የሆነ እህል በደጋው አገር ለማብቀል የማንችል መሆናችንን አረጋግጠናል። ይህም በመሆኑ ስንዴ ጤፍ እነዚህን የመሳሰሉትን ለኤርትራ ሕዝብ ምግብ የሚያገለግሉት ከኢትዮጵያ መግዛት አለብን።..”  ብለው ነበር። ዛሬ፤ እውን ሆኖ ጤፍ፤በርበሬ፤ ቡና የመሳሰሉ ምግብ ቅመሞች ወደ ኤርትራ የሚገባው በጥቁር ገበያ በትግራይ መንደሮች፤በጁቡቲ፤በየመን፤በሱዳን ዞሮ እየገባ ነው፤፡

 እንደዚሁም ደግሞ የእስላሞች ሊግ ቃል አቀባይ ባደረገው መግለጫ የሚከተለውን ተናገረ፦
              
 የኤርትራ መሬታችን ጤፍ የማያፈራ መሆኑን በኢትዮጵያ ሰሜን የሚገኘው የትግራይ ክፍል እንደዚሁ በመሬት በኩል ድሀ ሆኖ ለኤርትራ ምንም ዓይነት ጥቅም የማይሰጥ በመሆኑ በየአመቱ በብዙ ሺሕ ሕዝብ የሚቆጠሩት ሕዝባችን ከብቶቻቸውን እየያዙ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ጐንደር አውራጃዎች ተሻግረው ከብቶቻቸውን ያበላሉ። በዚህ ሁኔታ የትግራይ መሬት በምሥራቅ ኤርትራ ክፍል ላሉት በቆላ ውስጥ ለሚኖሩት ሕዝቦች ከብት የሚያግጡበት ሥፍራ ሲሆን፤ ጐንደር ደግሞ በምዕራብ አውራጃ ለሚኖሩት የሚበዙት እስላሞች ለሆኑት ሕዝቦች ከብት ማሰማርያ ሆኖ ይገኛል። ስለዚህም በምሥራቅና በምዕራብ ኤርትራ (በምፅዋ እና እሱንም በመሳሰለው አውራጃ) ላሉት ክርስትያኖች እስላሞች ለኑሮአቸውን ከኢትዮጵያ ውስጥ አድርገዋል። እነሱም ከኤርትራ ውስጥ ለመኖር ቢፈልጉ ኖሮ በረሃብ ባለቁ ነበር።ይል እና በመቀጠልም፤-……

ለሕዝቧ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዓይነት ምግብና እህል ከኢትዮጵያ በመግዛት ብቻ የምትደገፈው ኤርትራ ከጥቂት ጨው በስተቀር ወደ ውጭ የምትሸጣቸው ሌላ ዕቃ የላትም። ይህም በመሆኑ ያገር ውስጥና የውጭ አገር ንግዳችን የሚበዛው ክፍል በትራንዚት ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ የንግድ ዕቃና ለኤርትራ ሕይወት የሚያስፈልግ ምግብ ብቻ ሆኖ ይገኛል። ይህን የመሰለው ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገው ንግድ ቢቋረጥ የምፅዋ ወደብና መላውም ኤርትራ ንግዶች ሥራቸውን ያቆማሉ። ከእነዚህም ከኤኮኖሚ ማስረጃዎች በስተቀር ይበልጥ ጠቃሚነት ያለውና ከአእምሮአችንም ምንጊዜም የማይለየው ከሦስት ሺሕ ዘመን በፊት ጀምሮ ቅድመ አያቶቻችን አንድ የኢትጵያ ሕዝብ ክፍል ሆነው የነበሩበት መሰረተታዊ ጉዳይ ቀርቦ ይገኛል። የጋራ ጥንታዊነታችን የልምዶቻችን የቋንቋዎቻችን ፤የሃይማኖቶቻችንና የጥቅማጥቅሞቻችን መተሳሰር በጣም ጥልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ግልጽና ተገቢ በሆነ አኳሗን በሚያጠግቡ ለመግለጽ ምቹዎች ናቸው።

በማለት በምጣኔ ሃብቱ ረገድ የሚደረስባቸው መከራ ከላይ የተነበዩት ፍራቻ ትክክል ሆኖ ይኼው በዓይናችን እያየነው ነው (ድበቁ የኤርትራ ርሃብ በሚል የተዘገበ ቪዲዮ፤ ወይንም እኔ በአንድ ዘገባ ባቀረብኩት ውስጥ ኤርትራኖች መንገድ መውጣት እያፈሩ ቤት እያንኳኩ  ህጻናት ይዘው ቁራሽ እንጀራ እንዴት እንደሚለምኑ፤ ያቀረብኩትን አስታውሱ)

ቀጥሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ የመዋሃድ ጉዳይ ዋል እደር ማይባልበት መሆኑን እና ተሎ እንዲፋጠን ሁለት መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ኤርትራኖች በተመሳሳይ መልክ ጥያቄአቸውን አቅርበዋል። ያካተቱት ዝርዝር ሐተታ ረዢም በመሆኑ፤ የመጀመሪያዋን ብቻ ልጥቀስ፦ አንዲህ ይላል፤-

 እኛ በኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር ሁለት መቶ ሺህ የምንሆን ኤርትራውያን በኤርትራ ውስጥ የሚኖር ወንድሞችና ዘመዶች አሉን። የእነሱንም ችግር ብዙ ከመሆኑ በስተቀር በዚያ ክፍል በሚገኘው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ውስጥ አለመጠን ተጨቁነው ይኖራሉ። የሚበዙት የተማሩት ኤርትራውያን ከኤርትራ እየተሰደዱ ባሁኑ ጊዜ በእናት አገራቸው (ኢትዮጵያ) ውስጥ በነፃነትና በመልካም የኑሮ ደረጃ ተደስተው የሚኖሩ መሆናቸውን እዚህ ላይ ማንሳት አስፈላጊ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ካገራችን መለየታችን ብቻ ሳይሆን ከወሰን ባሻገር ያሉት ወንድሞቻችንና ዘመዶቻችን በችግርና በጭቆና ውስጥ እንዲኖሩ ማወቃችን ነው። ስለዚህ የኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ጉዳይ በተቻለ ፍጥነት አንድ ውሳኔ አንዲያገኝ ልመናችንን እናቀርባለን።
ሲሉ እነሱም በበኩላቸው ጥያቄአቸው ለኰሚሽኑ በደብዳቤ ገልጸዋል።

የወያኔ ትግራይ ባንዳው መለስ ዜናዊና ኢሳያስ አፈወርቅ ሴራ በኢትዮጵያ

የትግሬ ባንዳዎች ኢትዮጵያን የባሕር ወደብ አልባ ለማድረግ ለኤርትራኖች ወግነው የተጠቀሙባቸው የቅን ግዛት ካርታዎች እና ውሎች በዛሬው ዘመን ውድቅ መሆናቸውን ለማየት የተለያዩ ካርታዎችን እንመልከት እና ውይይታችንን እንደምድም። ድርጎቹ እነ ሻለቃ ዳዊት /ጊዮርጊስ እና ካሳ ከበደ እንዲሁም ንአመን ዘለቀ የመሳሰሉ የኤርትራ ነፃነት በሕግ የታወቀ ነው፤ ያለቀለት ነው፤ ኤርትራ፤ ዓሰብ፤ ወዘተወደ እሚለው ዝባዝንኬና ጥያቄ አንመለስም  (ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ) የሚሉን ጨለምተኞች ወይንም የወያኔ ትግሬ ባንዳዎችዓሰብ! ዓሰብ! የሚሉ የአማራዎች ጥያቄ ነውየሚሉን ባንዳዎች ሁሉ እነዚህ ካርታዎች እንዲያጤንዋቸው እንጠይቃቸዋለን።

ሦስት ካርታዎችን እንመልት

 የሚከተሉት 3 ታሪካዊ የተለያዩ የኢትዮጵያ መልክአ ምድሮችን እንመለከታለን። ይህ መልክአ ምደር/ማፕ የፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ የምርምር ውጤቶች ስለሆኑ አስቀድሜ ለሳቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በእነዚህ መልክዓ ምድሮች የምንመለከተው ቁም ነገር ጣሊያን ከአፄ  ምንሊክ ጋር ያደረገው የድምበር ውል በማፍረስ እራሱ ያዘጋጀው 1888 እስከ1928  ኢትዮጵያን ያዋሃደ የመጀመሪያው የኮሎኒ/የወረራ መልክዓ ምድር /ካርቶግራፊን እንመለከታለን። ከዚያ 5 አመት ግራ እና ቀኝ በጀግኖች እየተዋከ ቆይቶ 1933 . ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ተባረረ።

ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ጣሊያን በሠራው ካርቶግራፊ እና እራሱ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ አንድ ግዛት መሆናቸውን የሰራውን እና ውሉን አፍርሶ የሰራውን መልክዓ ምድር ተከትለው ሕዝቡን በማማከር እና ከላይ ባስነበብኳችሁ የኤርትራ ጥያቄና ፍላጎት እሳቸውም ጠቅልለው ሕጋዊ መልክዓ መሬታቸውን እስከ 1966 . ድረስ አስተዳደሩ።

 ከዚያ ደረግ 1966 እስከ 1991 . ድረስ የተረከበውን ሕጋዊ መልክዓ ምድር ሲያስተዳድር ቆይቶ በዚያ 17 አመት ውስጥ ውስጣዊ የድምበር አስተዳዳር ለውጥ አደረጎ ዓሰብን እና ሌሎችን በራስ ገዝጀሪ መንደሪ’ (ሪዲሰትሪክቲንግ) ሕግ በመከተል አስተዳደሩ ወደ ወሎ አዛውሮታል።

 የመረብን ወንዝ ጥሼ ወደ ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ ድምበር ከገባሁ በጣሊያን እና በምንልክ የተደረገው ዉል አይጸናም ብሎ የፈረመበትን ዉል ድምበር ጥሶ 1928 . ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ወርሮ የኮሎኒ አዲስ መልክዓ ምድር የሰራበትን ብቻ ሳይሆን፤ እኔ በሆነ ምክንያት ኤርትራን ለቅቄ ስወጣ፤ ኤርትራ ለሕጋዊ ባለቤቷ ለኢትዮጵያ አስረክባለሁ፡ ያለውን ዉል ሁሉ ማጤን ያስፈልጋል።

 ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ደርግ ጊዜ በወላጆቻቸው አስተዳዳር ሥር በአጥንታቸውና በደማቸው ተከብሮ የቆየው የባሕር ነጋሽ ምድር ዛሬራሳቸውንወያኔብለው የሚጠሩ ትግራይ ውስጥ የበቀሉ ባንዳዎቹ የኤርትራ ጉዳይ የኮሎኒ ጥያቄ ነው፡ በቅኝ ግዛት የያዘቻት ደግሞ ኢትዮጵያ ነች፡ ስለሆነም መለክዓ ምድሩን ለማካለል በኮሎኒ/በቅኝ ግዛት ደምብ እና ካርታ ተደራድረን ኤርትራን ጉዳይ እንፈታለን ያሉትንም ቢሆንየኮሎኒሕግም ቢሆን አልተከተሉም። አሁን አሁን ከአልጄሪስ ስምምነት ወዲህ ብዙ የወያኔ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው የነበሩ ስምምነቱ የወያኔ መሪዎች እንጂ የሕዝብ ውሳኔ እንዳልነበረ ሁለት ያታወቁ የትግራይ ተወላጆች እንዲህ ይገልጹታል፡-

 “Before anything else, the people living in the region called “Eritrea” are, Tigreans. The idea of “Tigreans” and “Eritreans” as separate peoples, was never ours. See editorial (December 1993) Ethiopian Commentator, Haile Mariam Abebe.).
ሻዕቢያዎች እየነገሩን ያሉት ኤርትራ ነፃ የወጣቺው በሕግ ሳይሆን በጉልበታችን ነው። ብለዋል። በትግሬ ምሁራን የሚገለጸው እውነታው ግን እንዲህ ነው፦

“When the EPLF was pinned down by Mengistu’s army in Nakfa, the Tigrean fighters arrived for its rescue twice. During the “Red Star Campaign” of 1982, for instance, Tigreans fought in Nakfa on the Eritrean side, for nine months. Furthermore, without the supreme sacrifice of the Tigreans, the demand for Eritrean independence would have been little more than a bargaining chip for a negotiated settlement.”  ( Alem Abbay (1993) “An Unappreciated Gift Horse in the Mouth”, The Ethiopian Times, March/April 1,No. 2) 
አለም ዓባይ ከላይ የነገረን፤ “….ሻዕቢያ በመንግስቱ (ኢትዮጵያ) ወታደር ናቕፋ ላይ ተገፍቶ ትንፋሽ አጥሮት ከተራሮቹ ግድግዳ ተጣብቆ ሞቱን ሲያጣጥር  የወያኔ ትግሬ ተዋጊዎች ወደ ናቕፎ ገስግሰው ቶሎ ደርሰውለት ከፍተኛ መስዋዕት ከፍለው ከደርግ ሃይለኛ ብትር ባያድኑት ኖሮ የሻዕቢያ መጨረሻ ዕድል ከኢትዮጵያ ጋር በደርድር ይቋጨው ነበር።እንዳለው ሁሉ እውነትም ሻዕቢያ ዓሰብን ለመስጠት ዝግጅነቱን ለደርግ መግለጹ ይታወሳል።

ወያኔዎች የኰሎኒ የግዛት ማፕ ብለው ወደ ዓለም መድረክ ለድርድር (ለሴረው) ሲቀርቡ ይዘውት የመጡት ማፕየኰሎያሊስትዋ ጣሊያን እንጂ” “የኰሎኒያሊስትዋ ኢትዮጵያአይደለም። ምክንያቱ ምንድ ነው? ቢባል፤ የመጨረሻዋ ኢትዮጵያ ኮሎኒያሊስት ነች ሲሉ የደሰኮሩበትን ሁለቱወንበዴዎችበግብር ለመተርጎም የኢትዮጵያን ኮሎኒያል ካርታ ይዘው ከሄዱ ከታች የሚታየው 3ኛው ካርታ ሕጋዊ ሊሆን ነው። ደግሞ ዓሰብን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባ መሆኑን በደምብ ስለሚያውቁ እና ስጋት ስላደረባቸው፤ በለመዱት ዓመጽ እና ቅጥፈት ከውጭ ኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተመካክረውኢትዮጵያየት ትደርሳለችኢትዮጵያን አምበርክከናታልስለዚህ የበሰበሰ ጣሊያን ማፕ ብቻ ይዘን አንቅረብ ብለው ኤርትራን አስገነጠሉ።

 በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጣሊያን ካርታዎችም ቢሆን መርጠው (ፒክ ኤንድ ቹዝ) ነው ለግንጠላ የሚያመቻቸውን የበሰበሰውን የድሮ ማፕ የተጠቀሙበት።እንደነገርኳችሁ በማፕ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ ጣሊያን የሰራው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ያዋሃደው 1928 እስከ 1933 . የመጨረሻውን ውሉን አፍርሶ የሰራውን አዲሱን የጣሊን ቅኝ ማፕ ሊጠቀሙበት በቻሉ ነበር። ሆኖም ገብሩ አስራት በመጽሐፉ አንደገለጸው በባንዳው ወየኔ አመራር ውስጥ ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራኖች ሆነው ኤርትራኖችን ለመጥቀም ከነሱ ጋር ወግነው አገራቸውን ኢትዮጵያ ፍትሕ በተጻረረ ሁኔታ ኤርትራን አስገንጥለው 90 ሚሊዮን ሕዝብ ያለ ባሕር ወደብ አስቀርተው በጠላት አንደትከበብ አድርገው የፈርንሳይ ጥገኛ የሆነቺውን ከጅቡቲ እና ስርዓት ከፈረሰባት (ፈይልድ ስቴት) ከሶማሊዋ የሐርጌሳ የወደብ ተከራይ ቴናንት/ጥገኛ አደርገዋታል።

ሦስቱ ካርታዎች ወያኔዎች ለኤርትራ ጥብቅና ቆመው የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሲዘጉ፤ የተጠቀሙባቸው ወጋ ቢስ የሆኑየፈረሱ የቅኝ ግዛት መከራከሪያ ውሎችብለው የሚሞጉቱባቸው በምኒልክ እና በጣሊያን ፋሺስት መካካል ተደረጉ የተባሉ ሦስቱ ዉሎች 1900/19002/1908(እኤአ) ውሎች ናቸው። እነዚህ ውሎች ዋጋ ቢስ ናቸው አንቀበላቸውም ብልን የምንሞግትባቸው ምክንያቶች በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያቶች ነው። በቀላሉ አንዲገባችሁ ባጭሩ ላስረዳ፤-

1)    May, 1889 (ኤዘአ)ውጫሌ ውል እየተባለ የሚጠቀሰው ምኒሊክ ለመሳሪያ እና ለገንዘብ ልውጥ ኤርትራን ለጣሊያን ሸጧት የሚባለው ውል የያዘ እና ኢትዮጵያ የጣሊያን ቅኝ ነች የሚለው በጣሊያን ቋንቋ የተጻፈው ከአማርኛው ትርጉም እና ውል የሚጻረር በመሆኑ ምኒልክ ውሉ እንዲስተካከል በትዕግስት እየጠየቁ አንዲስተካከል ቢጠይቁም ጣሊያን አልለውጠውም በማለቱ ምንሊክ 1893 ( ) በግልጽ አወጁ፡ ዋጋ አንዴሌለው ለጣሊያን እና ለዓለም አስታወቁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ካልገዛሁ ብሎ 1888 ድምበር ጥሶ ( አቆጣጠር) ዓድዋ ላይ ጦርነት ከፍቶ ውርደቱን ተከናንቦ እጁን ሰጠ። ከዚያ በፊት የነበሩት ውሎች በሙሉ ፈረሱ።ለጊዜው ለሁለቱ ተዋጊዎች ደምበር ሆነው የሚያገለግሉ ሦስት ወንዞችን መረብ፤በለሳ እና ሙና እንደ ድምብር አጥር ሆነው ተወሰኑ።


2)  ምኒሊክ ሰራዊታቸው ይዘው ወደ ኤርትራ መዝለቁ ፤ጣሊያን ተዋጊ ትኩስ ሃይል፤ስንቅና መሳሪያ በባሕር እየተላከለት አንደሆነ እና በተጨማሪም እዚህ ለመጥቀስ የማያመቹ ሰፊ የሆኑ የመሃል፤የደቡብ እና የምስራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ክፍሎች ዝርዝር ትንተናዎች የሚሹ ሰፋፊ ያልተጠቀሱ ምክንያቶችም ጭምር ጦርነቱን መግፋት አደጋ አንዳለው በመገመታቸው ሰራዊታቸው ከድሉ በሗላ በደስታ ወደ እየ መንደራችን አንመለሳለን ብሎ መፍረስ በመጀመሩ እና በከብትና በሰውሕይወት ረሃብ እና በሽታ ትግራይ ውስጥ ግብቶ ብዙ ሰው ስላለቀ (የስንቅ ችግር) እና በመሳሰሉ ሁኔታው አመች ስላልነበረ ኤርትራ በጣሊያን እጅ ልትቆይ ወሰኑ። ኤርትራ ሲቆይ ድምብር እንዳያልፍ ተፈራረመ።ኤርትራ ለቆ ሲወጣምኤርትራለባለቤቷ ለኢትዮጵያ አንደምታስረክብ 1896 እና 1900 (ኤአ) ውል ገባ። ኤርትራ ለማንም መንግሰት /ሃይል/ተዋዋይ አሳልፋ ለመስጠት ወይንም መሸጥ አንደማትችል ፈርማለች። (በሗላ ቃሉን አጥፎ ኤርትራ ለእንግሊዝ ሰጥቶ ወጣ፤ ወይንም አንግሊዝ በጉልቷ ነጠቀች)


የተጠቀሱት ስመምነቶች አስመልክተው አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩት ታላቁ የታሪክ ምሁር / ሃይሌ ላሬቦ እንዲህ ይላሉ።

 “It should be emphasized that the treaties of 1902 and 1908 under which Eritrea claims the disputed territories are essentially flawed. These territories belong indisputably to Ethiopia and until Italy, in its attempt to provoke another war with Ethiopia annexed them in 1929 by force, they were administered by Ethiopia. What makes even more difficult the settlement of conflict between the two countries according to the colonial treaties is the fact that the geographical map of Eritrea has constantly changed during and after those treaties as the following instances highlight:

Even under Italian rule, considerable part of Eritrea was under the sovereignty of Ethiopia. This includes the huge expanse of land under the control of Dabre Bizen and its dependencies (daughter monasteries) that were directly administered by the imperial Ethiopian government. If Eritrea insists that the border should be marked according to the above-mentioned colonial treaties, it is within Ethiopia's power to claim back these territories and those forcibly annexed by Zolli in 1928 and 1929. In both ways, Eritrea is bound to lose substantial mass of its land. Moreover, the control of Dabre Bizen and its dependencies will give Ethiopia a safe gateway to the important port of Massawa. Understandably, this will have serious consequences for Eritrea as an independent state.
ጣሊያን ኤርትራን እያስተዳደራት እያለም ቢሆን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘው ደብረቢዘን ገዳም ሳይቀር በኢትዮጵያ ኣስተዳደርና ንብረት ነበር (በውጫሌ ውስጥ ተጠቅሷል)


http://www.ethiopianreview.com/2001/Article_HaileMLareboAPRJUN_2001.html

3)   ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ አልደፍርም ያለበትን የድምበር ውል እንደገና ጥሶ በመረብ እና በኦጋዴን ገብቶ 1928 (ኢዘአ) ኢትዮጵያን ወረረ። 5 አመት ሲዋከብ ቆይቶ ተሸንፎ ወጣ። ከዚህ በፊት የነበሩ ውሎች ሁሉ ፈረሱ።

4)  ከዚያ በኋላ በእንግሊዝ ተንኮል ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መዋሃድ ሲኖርባት ከሃያላኑ አንዱ በመኖሩ ኤርትራን እና ትግራይን ገንጥሎ ለማስተዳዳር እንዲመቸው ፍላጎት ስላደረበት  ኤርትራ ውስጥ እቆያለሁ ብሎ ተንኮል ሰራ። በዚህ ጭቅጭቅ ተነሳ። ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በኋላ 4 ሐያላን መንግስታት ሲባሉ የነበሩት የመሰረቱት የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ መርማሪ አካል በደረሰበት ጥናት መሰረት፤ የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር ጉባኤ ኤርትራ በንጉሡ የዘውድ አስተዳደር ሥር ሆና ፤የራስ ገዝመብት ተሰጥቷት 10 አመት ከቆየች በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ትዋሃድ ብሎ ውሳኔ ሰጠ። 1900/1902/1908 የነበሩ ዉሎች እንደገናለሦስተኛ ጊዜበዚህ ባዲሱ ሕይወት እና አስተዳደራዊ ለውጥ ተሻረ።

5)  1944 . (ኢዘ ) ኤርትራ እላይ እንደተመለከታችሁት መሰረት በሕዝቡ ተወካዮች ኤርትራ ከኢትዮጵያ ሙሉ ውሕደት አደረገች። በዚህ ለአራተኛ ጊዜ የቆዩ ዉሎች በሙሉ ፈረሱ።

6)  ዓሰብ ከዋነኛው የኤርትራ ማሕበረሰብ 400 .ሜትር ርቀት ርቃ ትገኛለች። ለብዙ አመታት መላትም እስከ ደርግ ፍጻሜ ድረስ ከኤርትራ ይልቅ ምጣኔ ሐብታዊ (ንግድ) እና ማሕበራዊ ግንኙነት ከኤርትራ ይልቅ ከኢትዮጵያ ጋር ነበር። ዓሰብ ለደሴ 70/ ትርቃለች። የወደብ መጠቀሙ መብት እና ሂሳቡን በሕግ ምረኩዝ ስታሰሉትወያኔዎችባሕር ወደብ ለኛ መከልከላቸው ትግራይ ትግርኚ መደብ ሊጠብቁት የፈለጉት ሴራ አለ (ዓሰብ ወደብና አካባቢ አስቀድመው ወደ ትግሬ አጠቃልለውት እንደነበር በረሃ ውስጥ ያዘጋጁት ካርታ ይመሰክራል) ወይንም በሥልጣን ያሉ ትግሬዎች ወደ ኤርትራ የሚያደሉት፤ ሙሉ በሙሉ ወይንም የሁለት ደም ዲቃላዎች ሆነው ይበልጥ ለኤርትራ በማዳላታቸው ነው። ከሁለቱ አንዱ።

7)   ወያኔዎች አልጀሪስ ሄደው ባቋቋሙት ፈራጅ አካል 1902/1905/1908/ ጠሊያን የሰራው ካርታ እና ስምምነት አንፈረዳለን ሲሉ በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔይግባኝማለት እንደማይቻል የተፈራረሙበት ምክንያትም ከዚያ በኋላ የተሰሩ ካርታዎች እና ውሎች ካቀረቡይዘውት የሄዱት ውሉየበሰበሰ፤የማይሰራ መሆኑን አስቀድመው ስላወቁ፤ይግባኝየሚያግድ ስምምነት ሆን ብለው መፈራረማቸውለ፤ግልፅ ሴራ መሆኑን ያሳየናልነ። ለወደፊቱም በሕጉ መሰረትአንድ የመንግስት ተወካይ/አካል/ ሆን ብሎ የአገሩን ጥቅም የሚጎዳ ስምምነት ከፈረመ ስምምነቱ እንደገና እንደሚመረመር የተባበሩት /ሕግ ይጠቅሳል። እነ ሻለቃ ዳዊትና ካሳ ከበደ ግን ይህንን ሊደብቋችሁ ይፈልጋሉ።

     አሁን፤ ለማስረጃ ያቀረብኳቸው 3 የተለያዩ መልክዓ ምድሮችን እነሆ ተመልከቱ::

  ኢትዮጵያ የቅኝ ገዢ ነበረች “ከተባለ” በ1964 የካይሮ አፍሪካ ውል መሠረት በማድረግ ኤርትራ “የመጨረሻዋ” የቅኝ ገዢዋ የአሰመረችላትን የመልክኣ መሬት አስተዳደር ይዛ መገንጠል ነበረባት። ሆኖም የወያኔ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለመጉዳት በሕግ የተጣሰውን የኢጣሊያ ቅኝ ገዢ መስምርን  በመጠቀም በሴራ እንዴት እንደጐዱን ተመልከቱ። ለዚህም ነው  በሴራ የተፈጸመ ውል ነው ስለዚም አንቀበልም የምልበት ምክንያት።ይኼው ተመልከቱ። ካርታውን በትልቁ ለማየት በኪ-ቦርዳችሁ ላይ Ctr + የሚለውን ሁለቱን ቁልፎች አብሮ መጫን ነው። (Ethio Semay)
Ethio Semay


   እንደገና ልድገመው፡ በዚህ መረጃ መሰረት ኮሎኒዎች ነን ከተባልን የመጨረሻው የኮሎኒካርታ” የቀረጸው እና የመጨረሻው ኮሎኒያሊስት ማን ነው? የሚለው ጥያቄ እናቅርብ። ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ ባዕድ ነች በለውናል። በኮሎኒያሊሰት ካርታ/ማፕ እንዳኛለን ካሉ እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ለምን ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? 1964 የካይሮ ውሳኔም ተገንጣዩ የመጨረሻው ቅኝ ገዢ የሰጠው መሬት/ቅርጽ ይዞ ይሄዳል ይላል። መጨረሻ ቅኝ ብለው ወያኔዎች የሰየሙንም እኛ ከሆንን፤ ኢትዮጵያዊያን ቢሆኑ ኖሮ የኛን ካርታ ይዘው መከራከር ነበረባቸው። መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው።

ባንዳዎቹ በእውነተኛ ክርክር ጎሮራቸው ስለታነቁ ለዚህ ጥያቄ እስካሁን ድረስ መልስ ሲሰጡበት የሰማነው መልሳቸውኢትዮጵያ ያለ ወደብ 27 አመት ኖራለች ስለዚህ አያስፈልገንምወይንም በስብሐት ነጋ መልስ መሰረትዓሰብ ሳይሆን ጅቡቲ ነው ለኛ ለኢትዮጵያ የሚረባው” (ዓሰብን አትጠይቁ ወደ ትግራይ- ለትግራይ ትግርኛ መርሃ ግብሩ ስለሚጠቃለል ማለቱ ነው)። ወያኔዓሰብበትግራይ ክልል ያካተተ ካርታ ሰርቶ እንደነበረም ታውቃላችሁ):: ኤርትራኖችም ሆኑ የወያኔ ትግሬዎች  ለጥያቄአችን ቀጥተኛ መልስ ሊመለሱልን አልቻሉም። 27 አመት ያለወደብ ከጅቡቲ፤ከሶማሊ ወደብ እየተከራዬን ኑረናል፤ ስለዚህ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል፤ የሚለውመልስ ሲያጡ የሚመልሱት መልስ ነው።  ለነገሩ ኑሮ አይባልም እንጂ ኤርትራም  እኮ 27 አመት ወደቧ ባዶ ሆኖ ኖራለች። ጥያቄአችን አጭር፤ቀጥተኛና ግልጽ ነው!!!  27 አመት ዳክረው መልስ ያጡበት ጥያቄ አሁንም እንዲመልሱልን እንጠይቃቸዋለን።

ዛሬ የፈራነው እና የተነበይነው አውን ሆኖ  የየመን ሁቲ ተዋጊዎችን ለመጨፍለቅና የቀይ ባሕር ወሽመጥ ለመቆጣጠር የነበራቸው የዘመናት  ሕልም ዓሰብ እና ምጽዋ “አሜሪካኖች፤ኤኢሁዶች፣ኢራኒያኖች እና ዓረቦች (UAE…) ተከፋፍለው ይዘውታል።፡ይህንን ስንል፤ ውሸታሞች ሲሉን የነበሩት ዛሬውሸታሞቹእኛ ወይንስ እነሱ?  The UAE is scrumbling to controle posrt in Africa ወይንም Eritrea: Another Venue for the Iran-Israel Rivalry.


(ሳውዝ ፍሮንት በመባል የሚታወቀው ‹‹ፎረይን ፖሊሲ ዲያሪ›› በሚባል ፕሮግራሙ የቀረበው አጭር ግን ጥልቅ መረጃ የያዘ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ “Arab Coalition Expands into the Horn of Africa” በሚል ርዕስ ባሰራጨው ዘጋቢ ፊልም፣ ‹‹ይኼ ለኤርትራ ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን የገጠማትን የመነጠል ችግር የሚፈታ ነው፤›› ብሎታል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት የደረሰባትን ‹‹የሥርዓተ አልበኝነት›› ፍረጃም ነፃ ያወጣል ብሏል፡፡ ‹‹በእርግጥ ኤርትራ ማንም ቢሆን ገንዘብ የሚሰጣት ከሆነ ከመደገፍ ወደኋላ አትልም፤›› ይላል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የቀረበው ሐተታ፡፡ በአሰብ እየተገነባ ያለው ወታደራዊ ኃይል በአፍሪካ ቀንድ ከዚህ በፊት ያልነበረና የመጀመሪያው መሆኑንም ጠቅሷል፡፡ ‹‹ለአካባቢው (ለአፍሪካ ቀንድ) አደገኛ እንቅስቃሴ›› በማለት የአፍሪካ ቀንድ የዓለም አቀፉ የግጭት እንቅስቃሴ መናኸሪያ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን ያስቀምጣል፡፡

ይህ ሃቅ እውን ሆኖ ከተገኘ በኋላ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል ሲሉን የነበሩ የወያኔ አለቅላቂ አሽከሮች (አይጋ ድረገፆች፤ ትግራይ ኦን ላይን እና የወያኔ ሎሌዎች ሁሉ) ባለፈው 6 አመት በፊት ዓረቦች  ዓሰብን ተቆጣጥረውታል ሲባልመንግሥታችን፤ እባካችሁ ወሳኝ የሆነ አርምጃ በመውሰድ ኢሳያስን አስወግዳችሁ  ስጋት የሆኑብንን ዓረቦችን ኣባርሩልንብለው ሲጮሁ ሰምተናል። ዛሬ ደግሞ ወያኔ ከሥልጣኑያለ ጥይት ተባርሮ  ወደ መቀሌ ሲሸሽ ትግራይ ኦን ላይን የተባለ የትግራይ ትግርኚ አቀንቃኝ ድረገጽ ሰሞኑ ታምራት ነገራ ስለ ኤርትራ ጉዳይ ኢ-ሕጋዊነት አስመልክቶ በሰጠው አስተያጥ  ኤርትራነውያኑን ወግነው እንደ ለማዳቸው አንደ ውሻ ሲጮሁ አንብበናቸዋል።

እንግዲህ ወደ ቁም ነገሩ ልመልሳችሁ እና ወያኔዎች የኤርትራን ጉዳይ መፍትሄ ለማግኘት በኮሎኒያሊሰት ማፕ እንዳኛለን ካሉ ለምን እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? ጥያቄአችን አጭር እና ቀጥተኛ ነው። ለመረዳት አያስቸግርም።
ይህንን ለመመለስ 27 አመት ፈጀባቸው- አሁንም መልስ የላቸውም፤ ዛሬም ለጥያቄችን መለስ እየጠበቅን ነው። ወይ ኢትዮጵያ የኤርትራ ቅኝ ገዢ አልነበረችም በሉን ወይንምመነበረች” ካላችሁ ደግሞ ጥያቄአችንን መልሱ። ካልሆነ ክርክራችሁ አንጅት የሚያሳርርየፖለቲካ ጨዋታ ነው ፕሮፈሰር / ሃይሌ ላሬቦ አንዳሉት

“…the time gap that exists between these treaties and the Eritrean independence is so vast, and the change in status that Eritrea underwent during this same period is so intricate as to make any appeal to colonial treaties and OAU charter of no use beyond political gimmickry.”
(Colonial Treaties in the Context of the Current Ethio-Eritrean Border Dispute and Settlement 4th International Conference of Ethiopian Studies, November 6-10, 2000, at the Institute of Ethiopian Studies, Addis Abeba University. Ethiopian Review Ethiopian Review, April 2001)  

ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር ጉራዋን እና ዕብደቷን ካላቆመች መጪው ዘመን የኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ እየጠበቃት ነው። ምርጫው የራሷ ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ)


No comments: