Friday, January 10, 2020

ክፍል 4 ድጋፍ ለታምራት ነገራ የኤርትራ ሕዝብ ባርነትን ተለማምዶ የሚኖር ሕዝብ ነው! በጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 1/10/2020 በፈረንጅ


ክፍል 4 ድጋፍ ለታምራት ነገራ
የኤርትራ ሕዝብ ባርነትን ተለማምዶ የሚኖር ሕዝብ ነው!
 በጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
1/10/2020 በፈረንጅ

ባለፈው ጽሑፌ በአዲስ ነገር ጋዜኛ በታምራት ነገራ ላይ ሲዝቱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን የ “You Tube” ተደባዳቢ የመንደር ጎረምሶች ለኤርትራኖቹ ወግነው በሌለ ዕውቀታቸው ሲዘላብዱ በዘረጉት አሳፋሪ “You Tube” ላይ ዘለፋቸውን አድምጠናል። በዚህ ጉዳይ የሳምነቱን ትችቴን ለማጠንጠን ሉዓላዊት ክብር ያላት ጥንታዊት ሀገረ ኢትዮጵያ ክብርና ሞገስ መቆርቆር ቀርቶ፡ እርስ በርሳቸው ለመደባደብ ወደ ግል መኖርያ ቤቶቻቸው እየሄዱ በር በማንኳኳት ለድብድብ ሲፈላለጉ የሚያሳይ እራሳቸው የቀድዋቸው “ቪዲዮዎች” ለኢትዮጵያ ሕዝብ እዩልን እያሉ ያምንም ማፈር በድብድብ ባሕሪ የሚኩራሩ፤ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት ደንታ የሌላቸው “የ ዩ ቱብ” የጎረምሶች በዕውቀት እንዲታነጹ ቢረዳቸው በሚል እሳቤ ይህንን ማጠቃለያ ቀርቤአለሁ፡ እነሆ።

ጽሑፌ የምጀምረው ለበርካታ አመታት “የባሕረ ነጋሽ”  በረሃ ለነፃነት ትግል ወጥቶ ሲታገል የነበረ “የባሕረ ነጋሽ” ተወላጅ ረዘነ ሃብተ ከተደረሰው መጽሐፍ ውስጥ የሚነበቡ ጥቅሶችና ከርዕዮት ሚዲያ ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተናገራቸው አንደበቱ በመጥቀስ ጽሑፌን እጀምራለሁ። ደም የተከፈለበት ባርነት-የኤርትራ ውድቀትና ህልሞችበሚለው መጽሐፍ ደራሲ “ረዘነ ሃብተ”  እንዲህ ይላል፡

1 “ኤርትራ እንደ አገር ትቀጥላለች ብየ አላምንም” (ከቃለ መጠይቅ)፤

2-  አብይ አሕመድ ከመጣ በኋላ ይህንን መጽሐፍ በአማርኛ ለማሳተም  ለ6 ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጫለሁ፤ “ራስ ሆቴልና “ሂልተንሆቴል” የማታየው የኤርትራ የደህንነት ሰላዮችና የምናውቃቸው ነብሰ ገዳዮች በርካታዎቹ እዛ ሲርመሰመሱ አይተናል። እነዚህ ለኢትዮጵያ እንደ አገርም ሆነ ለተቃዋሚ ኤርትራኖች በጣም አደጋ ናቸው”፤

3- ኢሳያስ “ኤርትራና ኢትዮጵያ” አንድ አገር አይደሉም፤አይተዋወቁም፤ ኢትዮጵያ 50 አመት ዕድሜ ያላት አገር ናት እያለ  ትልቅ አገር ሲያንኳስስ የነበረ ሰው እንዴት እንደ አንድ ንጉሥ “አዲስ አበባ” ውስጥ አቀባበል ይደረግለታል?”

4- “አገር የመምራት አቅም አለኝ የሚል አብይ አህመድ የኢሳያስ ባሕሪ ማወቅ ነበረበት” ፤ ከኢሳያስ ጋር መገናኘት እራሱ አደጋ እንዳለው ማወቅ ነበረበት”፤

5-“ኦሳያስ ስለ ኢትዮጵያ ያለው አመለካካት ቆሻሻ ነው” ከመላው ምስራቅ አፍሪቃ መሪዎች ጋር ቅራኔ የፈጠረ ሰው ነው”፤

6- በጣም የሚገርመኝ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ነገር ነው። ለራሳቸው ጠባብ ጥቅም ሲሉ ፤ “ሁለት አገሮች ነን፤ እንግዲህ ተለያይተናል ስለዚህ ሁለት አገር ሆነን በመከባበር መኖር ይቻላል.. እያሉ እያጋነኑ ስትሰማ በጣም ትገረማለህ፤ ችግሩ “ቦዝ ወይ ነው” በነዚህ ፖለቲከኞችም የሚንሳፈፍ ችግር አለ”።

7- ኤርትራዊ ማንነት የሚባል የለም
“የኤርትራ ሕዝብ ባርነትን ተለማምዶ የሚኖር ሕዝብ ነው!” 

በማለት “ደም የተከፈለበት ባርነት-የኤርትራ ውድቀትና ህልሞች መጽሐፍ ደራሲ ረዘነ ሃብተ “የባሕረ ነጋሽ” ተወላጁ ጸሀፊ ምስክርነት እውነታው አስፍሮታል። ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ የ6ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍ ያላመበቡ ‘የ ዩ ቱብ’ ንኮች ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ስለ ኤርትራ እውነታ በመናገሩ ስለ ኤርትራኖች ተወክለው እንገድልሃለን፤ እንድበድብሃለን የሚሉ፤ በሰለጠነ አገር ጥገኝነት ጠይቀው ተፈቅዶላቸው  ሲሰደዱ እናከብራለን ያሉትን ሕግ  በ “ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ”  ማማልከቻ አስገብተው  ‘የመኖርና የመስራት’’ ዕድል በሰላምና ባግባቡ እያከበሩ ከመኖር ይልቅ ዓለም “ወደ ሗላ” ጥሎት የመጣውን “የመደባደብ ባሕሪ” ትተው ኣእምሮአቸው በማንበብ እንዲያዳብሩ ይህንን እውነታ ያዘለ መጽሐፍ ፈልገው እንዲያነብቡ እጋብዛለሁ። የቪዲዮ ቃለ መጠይቁም እነሆ ይከታተሉ። 
ድል ለኢትዮጵያ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)  
“ኢትዮጵያዊነት ለኤርትራውያን ክብር እንጂ ባርነት አልነበረም… ኤርትራዊ ማንነት የሚባልም የለም…” ኤርትራዊው ጸሀፊ ይናገራል፡፡ 08/04/2019



No comments: