Saturday, January 25, 2020

የአማራ ወጣቶች ከዕንቅልፋችሁ የምትነሱት መቸ ነው? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
                                          
እንዴት ሰነበታችሁ? ለተወሰነ ሳምንት ለሥራ ጉዳይ ከምኖርበት ክ/ሃገር በርሬ ወደ ሌላ አገር ሰንብቼ በሠላም መጥቻለሁ። በተለየሁዋቸው ሳምነታት እምየ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ አሳዛኝ ክንዋኔዎች መከሰታቸውን ይህ  ለምን  ሆነ አልልም ምክንቱም  መንግሥት ሥልጣን በጫካ ሰዎችና በነብሰ ገዳዮች እስከተያዘ ድረስ አሳዛኝ የሕዝብ ዕምባና ጉስቁና ሊቆም አይችልም።

 “ወጣቱ ትውልድ” ሥልጣን የተቆጣጠሩትን ‘ዘመናይ ሽፍቶች’ በጉልበትም ሆነ በማዕቀብ ካልተጋፈጡት እና ዕረፍት  ካልነሱት አማራውንና የጋሞ ተወላጆችን በማጥፋት ላይ የተጠመደ “አብይ” የተባለው የቀን ጅብ ሕዝብን ከማጥፋት ሥራው ቀይታቀብም።    

በግዕዙ ልሳን ልጀምርና ወደ ትንታኔው እንግባ። “ጽልው እዝነክሙ ሃበ ቃለ አፍየ (ጀሮአችሁን ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ)። አዎ ከስሜት ውጡና ጀሮአችሁን ወደ እምጠይቃችሁ ጥያቄ አዘንብሉ።

አማራ ወጣቶች ከዕንቅልፋችሁ የምትነሱት መቸ ነው?
 ነቅተናል አትበሉኝ። ከነበራችሁ ዕንቅልፍ ባነናችሁ እንጂ አልነቃችሁም። አንድ ከትግሬ የሚወለድ የቅርብ ወዳጄ ስለ አማራዎች ሁሌም የሚለው ነገር አለው። አማራ በጣም አከብራለሁ፡ ዘረኛ ነህ አትበለኝና እውነቱን ልንገርህ፡ አውነታው ‘አማራ’ ጉረኛ ነው ሲሉ ስሰማ  እከላከልላቸው ነበር፡ አሁን፤አሁን ስታዘባቸው ግን 27 አመት ሙሉ ግፍ ሲፈጸምባቸው ፤ዛሬም ነቅተዋል በተባለበት ወቅት አብን የተበላ የወጣት ምሁራን ድርጅት መስርተውም ቢሆን የሕዝባቸው ግፍ ከቀኝ ወደ ቀን እየከፋ መሄዱ ስመለከት “ይህ በየ ዩቱብ” ላይ የሚለቀቀው ጠምንጃና ዝናር ታጥቀው በመቶዎቹ ታትመው  የሚለቀቁ “የሽለላ የሙዚቃ ሸክላዎች”   
ለመታየት፤ለጉራ ወይስ ለምን? የሚል ጥያቄ ይጭርበኛል”፤ ብሎ አውርቶኛል።

ይህ ትዝብት  አንዳንዶቻችሁ እንደ ዘለፋ  ትወስዱት  ይሆናል። አማራ እየደረሰበት ካለው ግፍና የዘር ማጥፋት ጋር ሲነጻጸር ይህ የሙዚቃ ሽለላና ቅስቀሳ ዛሬውኑ ካልሰራ ለመቸ ይሆን የሚል እኔም እጠይቃችሗለሁ። አማራ  እራሱ  ካልሆነ  ማንም ሊያድነው  እንደማይችል  አወቁ።  ጊዜው  በጣም  እየከነፈ  ነው።

  በሳምንትታ ተለይቼ ወደ ስፍራየ  ስመለስ የሰማሁዋቸው ዜናዎች እጅግ አስከፊ ናቸው። የአማራ ወጣት ሴት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመንግሥት ዝምታ (አንድ ወላጅ እንዳሉት “በመንግሥት ጠላፋ/ትብብር” ህላዌአቸው የት እንዳሉ አይታወቅም። ለጥምቀት  በዓል የወጡ የተዋህዶ ክርትና አማኞች በሐረር/ሐረሪ/ ፖሊስ ጥይት እየተደበደቡና ወደ ታቦቱ ጭምር ጥይት እየተተኮሰ የሃይማኖት ጥቃት መፈጸሙ ስሰማ፡ “ፖለቲካ እንመራለን” የሚሉት “የፋሺስቱ የኮሎኔል አብይ አሕመድ” ወደ ገብ አጫፋሪዎች ስለሆኑ ከነሱ ምንም  አልጠብቅም፡ እኔ የጠበቅኩት “አብን” የተባለው ድርጅት የት አለ? ይህንን ጥያቄ ስጠይቅ አብሬም የሽለላ ሙዚቃ የሚለቁት ጠምንጃና ዝናር የታጠቁት ሸላዮች ይህ ሁሉ ጉድና ጥቃት ሲፈጸም “እምቢታቸውን  ለምን አላሳዩም”?

ብአዴን የተባለው የወያኔ ሎሌ የነበረው ዛሬ የምዕራባውያኖቹና የዓረቦች ቅጥረኛ ለሆነው “ለኦነጉ የኮለኔል አብይ አሕመድ” እግር አጣቢ ሆነው ስላየናቸው የገዛ ወላጆቹ  “ሸታታ እግር፤ ልሓጭ እና  ትምክሕተኛ”  ብሎ የሚዘልፍ  ብአዴን የተባለ ማፈሪያ ስብስብ ለአማራ መሕበረሰብ እና  በተለይም ለተጠለፉት ልጃገረዶች ይከላከላሉ ተብሎ ተስፋ የሚጣልባቸው የጠላት ሎሌዎች ስለሆኑ ትኩረት አልሰጣቸውም። ትኩረቴ “አብን”  የተባለው  ድርጅት መሪያቸውን አሳስረው፤ በርካታ  አንስት  የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “በኦሮኦሞ ሽብርተኞች” ተጠልፈው፤ ብዙ አማራዎች  እየተገደሉ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ድምፃቸው የት ተሰወረ ?

እውነት ለመናገር አብን  ከተባለ ድርጅት ይልቅ የሌሊት ወፍ ይሻላል። የሌሊት ወፎች የዋሻ ጥግ ጥግ ላይ ይዘው የሌሊት ወፍ እንደሚጮህ ሁሉ መጮህ አልቻሉም። ከሌሊት ወፎቹ አንዳቸውም ከተጠለሉበት የጣራ ሰገነት ላይ ወደ መሬት ከወደቀ  ነፍሳቸው ይናደዳል። እጅግ ይጮሃሉ። አማራው ከመጮህና ከመናደድ አልፎ ተግባራዊ እምቢተኝነቱን መቸ ነው የሚያሳየው? ይህ ጥያቄ ወያኔ አዲስ አበባ ከተቆጣጠረበት ወቅት ጀምሮ አማራ ምሁራንን ስጠይቃቸው የነበረ ጥያቄ ነው። አብን ሆነ አማራ ወጣቶች ከስሜት ወጥታችሁ ሕዝባችሁን ከመጠለፍና  ከመገደል ለመከላከል ከነፍጥ እስከ ማዕቀብና “መሬት አርዕድ” የሆነ “ሰላማዊ ሰልፍ” አሁኑኑ “ነገ ጥዋት” መጀመር አለባችሁ።

 ሽለላው ፉከራው የፌስ ቡክ ንትርኩና ጉራውን አቁሙና ጠላቶቻችሁን መክቱ። ለመሆኑ የውርደት ትርጉም ታውቃላችሁ? ወላጆቻችሁ ውርደት የሚባል በላያቸው ላይ እንዲያንዣብብ አይፈቅዱም። ጣሊያንን አፈር ድሜ ያስጋጡ  እምቢተኞች ነበሩ፤ እናንተ ግን የየትኛው ችግኝ ዲቃላዎች እንደሆናችሁ ሊገባኝ አልቻለም።

አብይ አሕመድ የሚመራው ድርጅትም  ሆነ በዙርያው የተኮለኮሉ ጎስታፖ ፋሺሰቶች ለ27 አመት በወንጀል የተጨማለቁ በአሕዛብ ላይ የዘመቱ፤ምጥ በያዛት አርጉዝ የሚሳለቁ “ክራባት እና ሱፍ” ያጠለቁ የሰው  ልጅ ቀርጽ ያላቸው “የበረሃ ጭራቆች” ናቸው። ከወያኔና ከኦነግ/ኦፒዲኦ/ኦፌኮ “ፍትሕ” የምትጠብቁ ከሆነ ሕክምና ያስፈልጋችሗል። ለዚህ ነው “የአማራ ወጣቶች ከዕንቅልፋችሁ የምትነሱት መቸ ነው? ስል የምጠይቃችሁ።
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

No comments: