Please Read ሀቅ ያንቃል after this news
To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ signNews
Monday, January 09, 2012
Asmara
The Indian Ocean Newsletter on its headline “Behind Closed Doors” has published the following secret news.
President Issayas Afewerki is believed to be in regular contact with his sworn enemy the Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi. At least according to stories leaked from source close to the Eritrean Head of State from sometime. Although I is unclear what they have in mind. According to them, secret private conversation have been held between the two men for several months via secured telephone links and even via secured the skype internet communication system.
The Italian authorities are even believed to have offered to host a secret meeting between the two leaders on their territory. Wait and see.
Posted on www.ethiopiansemay.blogspot.com
Editor Getachrew Reda getachre@aol.com
የሚታየው የወያኔ ገበና ማህደር አዲሱ መጽሐፍ ለመግዛት $30.00 ዶላር ሲሆን ይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፍ ደግሞ $25.00 ወይንም ሓይካማ የሚለው የትግርኛ መጽሐፌ ደግሞ $15.00 ዶላር ብትልኩ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።Getachew Reda P. O.Box 2219 San Jose, CA 95109 getachre@aol.com Phone (408) 561- 4636
ሀቅ ያንቃል
ከ፡ ኦርዮን ሞዲ
ሀቅ ባያንቅ ኖሮ ደከም ያለ የሀቅ ጠረን ያለውንም ውሸት ለማስተናገድ በሞክርን ነበር ። ወይ ነዶ ! አልሆነምና ሀቅን መቀበል እንደ ኮሶ መድሐኒት የግድ የምንጠጣው ሆኖ አለ ።
· ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊ አይደሉም ያለው፤
· ኦሮሞዎች የሃበሾች ቅኝ ተገዢ ናቸው ያለው
· ለመጣው መንግስት ሁሉ መሳሪያ የሆነው፤
· ኣሮሚያ ነጻ መንግስት መቋቋም ብቻ ነው መፍትሄው ያለው፤
· ከሻዕቢያ ጋር ሆኖ የአሶሳን ፍጅት፤ ከወያኔ ጋር ሆኖ የበደኖን እልቂት ያመጣው፤
· ከወያኔ ጋር አብሮ ዘረኝነትን ያስፋፋውን፤
· ከሻዕቢያ ጋር አብሮ ንጹሓንን የገደለውና ዛሬም ለዚህ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል ምሳሪያ የሆነው፤
· የጭፍን ጥላቻ አባወራው
ኦነግ ተሳስቸያለሁና የተሳሳተ አቅዋሜን ቀይሬያለሁ ትቸዋለሁ ቢል ምንኛ በሀቅ ደስ ባለን ነበር። ግን አልሆነም ።ኦነግ አቅዋም ቀየረ ፤ መገንጠልን ተወ ስንባል የነበረው በአስመራ የመሸገው ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ አቅዋም ቀየረ በሚል ነበር። ለተባለው ለውጥ ምንም ተጨባጭ መረጃ አልነበረም። በስሞኑ ግርግር የተቆጣው የዳውድ (ፍሬው) ኦነግ በግልጽ የቀየርነው አቅዋም የለም፤ እንደ ኤርትራና ደቡብ ሱዳን ነጻ መውጣት ነው ግባችን ያለው። ዳውድ ኢብሳ በፖለቲካ አርቆ አስተዋይነት የሚታማ አይደለምና ፍላጎቴ ውድቅ መንግስት (ፌይልድ ስቴት) የሆነችውን ኤርትራን መሆን ወይም ገና ነጻ ወጣሁ ባለች ማዕግስት ህልውናዋ ብልጭ ድርግም እያለ ያለውን ደቡብ ሱዳን ነው ማለቱ የሚጠበቅ ነው። በፈረደበት አማራ ሕዝብ ላይም የዳውድ ኦነግ የከፈተው አጸያፊ ዘመቻም መጠቀስ ያለበት ነው። ይህን በዚህ እናሳርገው።
የዚህ ኪነት አቀነባባሪዎች ወይም ሳህሌ ደጋጎዎች አይደክሜዎች ናቸውና ወይም ክመጀመሪያው የተሰጣቸው ተልዕኮ ኦነግን መከፋፈል ክሆነ ዋናውና ብቸኛው ኦነግ ነኝ ባዩ ካሳየው ብስጭት መገመት ይቻላል። እነ አይታክቴ ላይ ታች ብለው የወያኔ ጀኔራሎች የነበሩ ግን ወደ ኤርትራ የከዱ ጀኔራሎችን አግኝቷል ። ጀኔራሎቹ ለዳውድ እጅ ነስተው ቢቀላቀሉትም (ኦነግ በውስጡ አጠራጣሪ ግለሰቦችና ወንጀለኞችን ሲሰበስብ የመጀመሪያው አይደለም) ሳይውል ሳያድር ተለይተውታል ። ሁለት የነበረው ኦነግ ዳውድ ቢክድም ሶስት ሆነ ማለት ነው ። ጀኔራል ከማል የተባለው ክዳውድ የተለየው በፖለቲካ አቅዋም ልዩነት ሳይሆን በአካባቢና ምናልባት ሀይማኖትም ሳይሆን አልቀረም (ክርስቲያን ወለጋና አሩሲ እስላም) የሚሉ ቢኖሩም ሌሎች ደግሞ የቀድሞ የወያኔ ጀኔራሎችን ከዳውዱ ኦነግ የነጠለው ዳውድ አማራ የሚለው ግን መሪው የጉራጌ ተወላጅ (ብርሃኑ ነጋ) ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ነው የሚሉ አሉ። [1] በዚህም በዚያም በነከማል የሚመራ የኦነግ አንጃ (አንጃ ስም ቅሚያ ዋና የማደናገሪያ ስልቱ ነውና ) ራሱን ኦነግ ብሎ ብቅ አለ ። ይህን አንጃ መማጠን ከተጀመረ ውሎ አድሯል ። ኦነግ ተቀየረ እያልን ነውና እርዱን እንጂ ተባሉ ። በኤርትራ ምይይጥ እንዲሉ ውይይቱ ተጧጧፈ ። አንጃው ከመገንጠል አቅዋሜ ወይ ንቅንቅ አለ ። ምለላው በረከተ ። ቢያንስ አንድ የባዕድ ሀገር በነገሩ ዘው አለ ። ዳውዶች እንደሚሉት ከሆነ መለስ ሲወገድ የአዲስ ኦህደድነት ቦታ ክፍት መሆኑም ተነገረ። አንጃው ቋመጠ-- ለስልጣን የማያቋምጥ አንጃ ለመሆኑ በየት ይገኛል ? ከወደ ሎንዶን አንድ የግንቦት 7 መሪ ወደ አስመራ ደጋግሞ አቀና ። ዻውድ ፊት ነሳው ሲባል የአንጃው መሪ (አዎ ቢገርምም እሱም እዚያው አስመራ ነው) ግን ጆሮውን ሰጠው ። ተንኮሉ ጨሰ ይላሉ የዳውድ ሰዎች በኦሮሚኛ። አንጃው አቅዋሜን ሳልቀይር የቀየርኩ መስዬ የምታይበት መንገድ ይፈለግልኝ አለ ። “ጽሉል” ተመሲልካ ወይም “እብድ” መስለህ ራታቸውን ጨርስባቸው እንደሚለው የትግሪኛ ተረት አንድነትን የደገፍን መስለን ግንጠላን እናመቻች ዘንድ አቀራረቡን ዚቁን ቃኙልን ሲሉ አንጃዎቹ ጠየቁ ። ቅንብሩ ጊዜ ፈጅቶ በአዲሱ አመት (የባዕዳን) በሚኒሶታ ከተማ ብቅ አለ። “ዕጹብ ድንቅ” ብለው እንዲለፍፉና እንዲጽፉ የተዘጋጁ ክፍሎች ሚኒሶታ የአንድነት ቤተልሄም ሆነች ብለው ዘመሩ። ክዚሁ ቦታ ስብስባ ኢትዮጵያውያኖች በአንጃው በተጠሩ የአሜሪካ ፖሊሶች መባረራችውን ግን አንዳችውንም ራሳችውን የአንድነት ደጋፊ ነን ባዮች ሳይጠቅሱ ቀሩ ።
1. በባዕዳን እርዳታ ግንቦቴዎቹ ሚዲያውን (መገናኛ ብዙሃኑን) በሀገር ቤትም ሊቆጣጠሩ መጣራቸው እየታየ ነው ። ዳዊት ክበደ ሰተት ብሎ ኣሜሪካ ገባ ። አራያ ተስፋማርያም በተሰደደብት ህንድ ሳይቀር ግድያ ተሞክረበት፤ተሰቃየ ። ዳዊት የሐበቫ ጋዜጣ አዘጋጅ ግንቦቴ ሆን--የኦነግ አንጃ ሀብሾችን ውድ ስብሰባው ጠራ ብሎ ዋሽቶ አምነውት የሄዱት በፖሊስ ሲባረሩ ታዘብን ። በዚህም በዚያም አለን በመድረክ የሚሉት የግንቦቴዎች ወይም የአሜሪካ ቅጥረኞች መሆናችው ምስጢር አይደለም ። የኢሳት ሃላፊ ተብሎ የተሾመው አበባ ገላው (ከአውሮጳ ተውስዶ በሲኣይኤው ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሰለጠነ) የዚሁ ቡድን አካል ነው ። ለኤሳት 40 ሺ ዶላር ክናሽናል ደሞክራቲክ ኢንስቲትዩት አገኝሁላችሁ ባዩ ይህ አበበ ነው።[2] የተባለው ኢንስቲትዩት ደግሞ ለወይዘሪት ብርቱካን የነጻ ትምህርት ክፍያ ያድረገላት የሲአይኤ ተቋም መሆኑ ይታውቃል ። የተወሳሰበ ይመስላል? አይደለም። ምንጩ አንድ ነው ። አንዱ ኣንዱን እየጠቀሰ “ የተሰበረ ዜና ” በሚል ኡኡ ይሉብናል ።
2. ይህ “ ጦር ” ነው በዕቅዱ መሰረት የኦነጉ አንጃ ፕሮግራሜን “አሻሻልኩ” (አሜንድ አደረግኩ) ሲል ተዓምር ብለው፤ ኦነግ መገንጠልን እምቢ አለ ብለው በሬ ወለደን ሊያሳምኑን በጋራ የተንጣጡት ። ኩኔታው ብኣፍ ሰተት፤ ብእግሪ ሸርተት መሆኑን ለመሸፋፈን ነው፡፤ የነከማል ጦማር ያው የኦነጉ ነጻ ኦሮሚያ አቅዋም መሆኑን ለመሸፈን ።
3. እውን ግንቦቴዎቹ ለኢትዮጵያ ከቆሙ ለምንስ ከኢትዮጵያ አንድነት ህይሎች ጋር መተባበርን ተቃወምክ ሲባል የግንቦቴው መሪ (ከአህያ የዋለች ጊደር…ተማረች እንደሚባለው ግለሰቡ ጸረ አማራነት እየተናነቀው ነውና!) ጭራሽ የአንድነት ሀይል የሚባል የለም ብሎ ከመካድ አልፎ አሉ የሚባሉትን ዘልፏል ። ለምን?
4. የሚኒሶታ ጦማር ይዘቱ እንዳይመረመር ለምንስ ግድግዳዎች በዙ?
5. ክማልም ዳውድም አስመራ ከሆኑ የሚኒሶታ ጦማርና የግንቦቴዎቹ እንቅስቃሴ ሁሉ በሻዕቢያ የተቀነባብረ ይሆን ወይ? ኢሳያስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የመቶ ዓመት የቤት ስራ ሰጠሁ ባለ በሰባት ዓመቱ ይህ ህዝብ ለኢሳያስ ራሱ በታታኝ የቤት ስራ ስለስጠው (ጠብና ጦርነት ከወያኔዎች ጋር) አምባገነኑ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከመራወጥ አርፎ አያውቅም ። ለመሆኑ የራሱን ሕዝብ/ ከሚያስለቅስና ኢትዮጵያን ከሚጠላ ሀይል ጋር መተቃቀፍ ክህደት ቢባል ያንሰዋል?
ይህን ካልን በኋላ ወደ ጦማሩ እናምራ ። እውን የኦነጉ አንጃ አቅዋም ቀየረ ? ከማል ከዳውድ ተለየ ያው በሻዕቢያ ስር በአስመራ ሁለቱም የኦነግ ዋና መሪ እኔ ነኝ ይላል በሚባለው የሻዕቢያ ጀኔራል ጣዓመ ቁጥጥር ስር ቢገኙም?
ሀቅ ያንቃል
የኤኤፍዲ ጊዜ የነበረው ሩጫና ጉራ ከረዩ ትዝ ይላችኋል? የዋሽንግተን ተላሎች ለዳውድ ኢብሳ ቆመው ሲያጨበጭቡና ቪቫ ሲሉ? ግልጽ የሆነው ሰነድ እያለ ያልተጻፈ እያነበቡ ራሳችውን አታለውና ተታለው ለኦነግ (ይቅርታ ሌላ ተገቢ ቃል አላገኝሁም) መጋዣ ሊሆኑ ሲሯሯጡ? ዛሬም ይህንኑ ለመድገም በግንቦቴዎቹ መሪነት ጩሀት በርክቷል ። ትላንት ኤ ኤፍ ዲን ደግፈው ሲጮሁ ከርመው (ተሳስተን ነበር ግን ሳይሉ) ዛሬ ደግሞ ከማል መገንጠልን ተወ ብለው በባዶ ሲባርቁ ይደመጣሉ ፡፤ ሀቁ ግን ውሀ ቢንጡት ውሀ ነው ። ለምክንያት ድመት ሞተች እንዲሉ ይህ ሁሉ ላይ ታች ፤ለመለስ ተኪዎች አጃቢ ተለጣፊ ለማዘጋጀት ሲሆን በ 1983 አሜሪካና እንግሊዝ የሸረቡብንን የግንጠላ ሰራ ለመድገም ነው። በምዕራባውያን የተገደለው ጋዳፊ በወቅቱ ይህ “ራስን ዕድል በራስ መውሰን በሚል ሽፋን በምዕራባውያን የሚገፋው አቅዋም አፍሪካን ለመበጣጠስ የተዘጋጀ ነው” ሲል አውግዞ ነበር ። ግንቦቴዎቹ ኢትዮጵያን አይወዱም--ከርሳቸውና ገንዘብን እንጂ! ለዚህ ደግሞ ምስክር መጥራትም የሚያስፈልግ አይደለም ።
የሴራው አጀማመርና አካሄድ የሚያሳየን ድፍድፉ ከወደ ላንግሌ ቨርጂኒያ (ሲ አይ ኤ) መምጣቱን ነው። በዋና አካሂያጅነት የተመረጠው ደግሞ ጥንትም ከእነ “ስም አይጠሬዎቹ” የሰራውና በተለይም ታሪካዊ ይሆን የነበረውን የሙት ከተማ አድማን ያኮላሸው የግንቦቴዎቹን ዋና መሪ ነው። በቅድሚያ የቅንጅት ክፍፍል ተካሄደ። የግንቦቴዎች ቡድንም ብቅ አለ ። ገንዝብም ጀሌዎችም ተለገሱት። የአስተማሪነት ሽፋንም አገኘ። (ጸረ ኢትዮጵያው አብዱል አባቦራ በተባበሩት መንግስታት መስሪያ ቤት ተቀጣሪነት ሽፋን አይደል ስለላውን የሚያካሂደው?) ። ግንቦቴው ቡድን በሀገር ቤት አባሎቼ ያላቸውን በየጊዜው ከማስበላትና ለወያኔ ጉራና ጥቃት ሰለባ ከማቅረብ ሌላ ምንም የሰራው ቁም ነገር የለም። ምስጢሩን እንኳን መያዝ የሚችል ቡድን አይደለም ። የዛሬ ዓመት የአባላቱ ዝርዝር ስምና ቴሌፎን ቁጥር በይፋ ባልታወቁ ሰዎች ተሰራጨ። ሰሞኑን ደግሞ የግንቦት 7 የአውሮጳ ቅርንጫፍ የተቀዳ ስብስባ የወያኔ አይጋ ፎረም አስራጭቶታል። (ኦነግና ግንቦት 7 በድርጅታዊ መዝረክረክ አንድ ናቸው) ። በዚሁ መንገድ ከቀጠልንም ኦነግ የተባለውም ቢሆን ለሻዕቢያ ተራ ሽብር መሳሪያ ክመሆንና ለወያኔው አመቺ ማስፈራሪያ ከመሆን ሌላ ከዚህ ሁሉ ዓመት የሻዕቢያና ባዕዳን እርዳታ በኋላ ነጻ ያወጣው ስንዝር መሬትም የለ? ቢኖርም እነዳውድ አስመራን ለቀው የሚሄዱ አለመሆናችውን የሚያውቁ ያውቃሉ።[3] ስለዚህም ሂደቱ ሲጀመር ከግንቦቴዎቹ ሌላ ድርጅት ለአፈር የሚል ዘመቻ ተከፈተ ። የ 500 ዶላር አርበኞች ክስተት መጣ ። ኤሳት የሚባለው የቴሌቪዥን ጣቢያም በአጭር ጊዜ በወያኔ ታፍኖ በሀገር ቤት መታየቱ ቢያበቃም ([4]) በኣሜሪካና ምዕራቦች ገንዘብና ቁጥጥር ስርጭት ጀመረ) ። በአጭር ጊዜ በከተማ ትጥቅ ትግልና አመጽ ወያኔን ልንጥል ነው ብለው ተስፋ ሰጡን ። የኣማራ ሕዝብ ከየት ወዴት ብሎ ጽፎ የወያኔን ዘረኛ ፖለቲካ የደገፈው የግንቦቴዎች ምክትል መሪ ወደ አስመራ መለስ ቀለስን ተያያዘ ። “ ሁሉን ሀይሎች የማስተባበር ” ዕቅድም ይፋ ሆነ ። ይህ ዕቅድም የሻዕቢያን ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ እነ ዳውድ፤ አርበኞች ግንባር፤ ዴምህት ወዘተ ሁሉ ከግንቦቴዎች ጋር ተመያየጡ ። የሻዕቢያ ዋና ተልዕኮ የአንድነት ሀይሎችን ለማግለል መሆኑ ግልጽ ሆኖ መጣ። ግንቦቴዎቹም የዳውድ ኦነግ ኣቅዋም ቀይሯል ብለው እመኑን ጥሪን አስተጋቡ ። አማኝ ጠፋ። ዳውድም የቀየርኩት የለም እያለ ደረቀ ። ኦነግ እንደገና ተከፋፈለ ተባለ ። እሰየው ያለው ክፍል ጥቂት አልነበረም ። የሕዝብ ጥላቻ ያናወዘው ኢብሳ ጉተማ አስታራቂ ልሁን አለ። ግንቦቴዎቹ ተገንጣዮቹ ሊታረቁ ነው ብለው ሲፈነድቁ የሕዝብን ትዝብት አተረፉ ። ወልደጋብር ይሄ ያዋጣል ወይ የሚል የጠፋ ይመስል አቧራው ጤሰ!
1. የነ ከማል ቡድን የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለም ስንል የነበረው ስህትት ነውና ትተነዋል፤ አርመነዋል አላለም፡
2. የነ ከማል ቡድን የኦሮሞ ሕዝብ የሐበሻ ቅኝ ተገዢ ነው ስንል የነበረው ስህተት ነውና ትተነዋል፤ቀይረነዋል አላለም፡
3. የነ ከማል ቡድን የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቀ መፍትሔው ተገንጥሎ ነጻ ኦሮሚያን መመስረት ብቻ ነው ስንል የነበረው ስህተት ነውና ትትነዋል፤ ቀይረነዋል አላለም ።
1. የወያኔ የጎሳ ወይም የብሄረስብ ፈደራል ኣውቃቀር ሀገርና ሕዝብን ክፋፋይና ጎጂ ነው። 20 ረጅም ዓመታት አይተነዋል ።
2. በሻዕቢያ የታጠቀና የተደገፈን ኦነግ ከቦታው ከደረሰ በኋላ ልነቅንቅ ማልቱ ቀላል አይሆንም።
3. የክማል ቡድን የመገንጠልን መንገድ በግልጽ ትችያልሁ እስካላለ ድረስ (ይህም አፋዊ ይሆን ተግባራዊንትን የሚጠይቅ ነው) ጅብ ቢያንክስ መዳን እስኪያግኝ ነውና ሁነታው ሲያመቸው ምን እርምጃ መውስድ እንደሚመርጥ መገመት ይቻላል ። ሻዕቢያ ራሱ ባለ ሶስት ኣማራጭ ሕዝበ ውሳኔ አካሂዳለሁ ካለ በኋላ አስመራ ሲደርስ ንጻነት ወይስ ባርነት የሚል አጉልና የይስሙላ አማራጩን አቅርቦ የፈለገውን እንደፈጸመ አይተናል ።
የክማል ጦማር ፈደራል ሬፑብሊክ ማቋቋም ካለም በኋላ የዚሁ ረፑብሊክ ዋና ተልዕኮ የብሄረስቦችን የራስ ዕድል በራስ የመወሰን መብት ማክበርና የህዝብን ውሳኔ ማክበር መቀብልንው ሲል አስፍሯል ። ያበጠ ይፈንዳ ነው ነግሩ ውይም ብዙሃኑ ቢያንቡም አይገባችውም ተብሎ ተደምድሟል ማለት ነው። አልሸሹም ዞር አሉ የተባለውም እዚህ ላይ ነው ። ዳውድና ከማል ጠባችው በፖለቲካ ኣቅዋም ዙሪያ በተከሰተ ልዩነት ላይ አይደለም የሚባለውም ለዚህ ነው ። የግንቦቴዎቹ የሚዲያና ፓልቶክ ጩሀት ሊሽፋፍነው የማይችለው ሀቅ ይህ ነው--ያንቃልም ። ላብራራ----
1. የክማል ቡድን ሆን የዳውድ ቡድን የራስን ዕድል በራስ መወሰን መርሆን የሚረዱት በኢትዮጵያ አንድነት ክልል ሳይሆን ሁለም በመግንጠል ውይም ግንጠላን በሚያመቻች ሻዕቢያዊ ስልት ነው ። ብቃላት ሽፍንፍን አቅዋሜን አልደብቅም ያለው ይዳውድ ቡድን ግልጽ በሆን መንገድ ቅኝ ግዛት ነንና ጥያቄው መገንጠል ሳይሆን የግድ ነጻነት ብቻ ነው ብሎናል ። ህቁን ተናግሮ የመሸበት ማደር ይሏል ይህ ነው ። የክማል ቡድን የልቡ አቅዋም ይህ ነው ግን በግንቦቶቹ ተቃኝቶ ማድናግርና ሐበሻ የሚለውን ወገን ማድናገሩን መርጧል ።
2. የክማል ቡድን ፈደራል የተባለው ሬፑብሊክ ሲቋቋምና ምናልባትም በነ ከማል መሪነት የራሱ ጦርና ፓርላማ ያለው የኦሮሚያ ፌዴራል ረፑብሊክ እውን ሲሆን ባለስልጣኖቹ ሬፌሬንደም (ሕዝበ ውሳኔ) እንዲጠራ ያደርጉና (በቀጥታ ወይም በፓርላማ አማካኝነት ግንጠላን/ እውን ያደርጋሉ ማለት ነው ።
3. ኦነጎች ስልጣን ሲባሉ ነጻ ኦሮሚያ ያሉትን እርግፍ አድርገው ትተው ለሹመት እንደሚሰለፉ በደርግም ሆነ በወያኔ ጊዜ ያየነው ሀቅ ነውና ነገም ይደገም ይሆናል ብሎ መጠበቁ ስህተት ላይሆን ይችላል ። ኢብሳ ጉተማ ለወያኔ፤ ከማል ለወያኔ አገልግለዋል--ሁሉንም መጥቀሱ አስፈላጊ አይደለም ። የታሪክ ጋቢያቸው ቆሽሿል በአጭሩ ። ይህ ክስተት ቀጠለ አልቀጠለ ግን ብዙ ሚዛን ወይም አንደምታ የለውም ክትግላችን አንጻር ። የከማል ቡድን የዳውድ ኦነግ እንደከሰሰው ለግንቦቴዎቹ ኦሕዴድ ቁጥር ሁለት ሆኖ ቢገኝ ለኢትዮጵያ መክራዋን አይቀንስላትም--ያባብሰዋል እንጂ! መለስ በሌላ ወያነ ተተክቶ ይህንን ሰቆቃ ግንቦቴዎችና እነከማል ቢያጅቡ ሌላ ዙር ትግል ይጠብቀናል ማለት ነው ።
ከ ኤ ኤፍ ዲ በባስ ትንኮል ተሽርቦብናል ። ባዕዳኑም ፤ ሻዕቢያም አሉብት ። ይህን ማየት ያቃተው ኣኢትዮጵያዊ ሀገሩን ጥፋት እየዳረገ ነው ። ይህ መታወቅ አለበት ። ኦነግ የከማል ሆነ የዳውድ-- የገላሳ በይፋ የኦሮሞን ኢትዮጵያዊነት አምኖ፤ መብትን በኢትዮጵያ አንድነት መስረት ፈላጊ ሆኖ በይፋና በማያውላዳ መንገድ መገንጠልን መተዉን ቢያሳውቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ--በመጀምሪያ ደረጃ በኢትዮጵያ ያለው ኦሮሞዎች ሁሉ በድስታ ያቅፉታል፡ ይድግፉታል። መንገዱ ይህ ነው። የግንቦቴዎቹ መንገድ አያዋጣም ። ኤ ኤፍ ዲ ክሽፏል፤ ክስሟል። የሚኒሶታዎቹ ጦማር ውድቅ ይሆናል ። የሕዝብን ፍላጎት አያሟላምና ።
[1] በዚህ ጽሁፌ ውስጥ ደጃዝማች፤ ኢንጂኔር፤ ዶክተር ፕሮፌሰር ወዘተ የተባሉትን ሹመቶች አልጠቅስም።
[2] ስለ ኤሳት ጉድ ኣቶ ከፍያለው ማሞና ለሎችም ያወጡትን ማጋለጫ ያነቧል።
[4] ዛሬም ኤሳት የሚንቀሳቀሰው በመዋጮና በነጻ ጋዜጠኞች ነው ብለው የሚያምኑ የዋሆች አሉ--አያሳዛንም?
Posted at www.ethiopiansemay.blogspot.com
Editor - getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment