ጌታቸዉ ረዳ (ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ)
www.Ethiopiansemay.blogspot.com
getachre@aol.com
ዛሬ የምተቸዉ ሁለት ርእሶች በጣምራ ነዉ። አንደኛዉ ትችቴ- በጋዜጠኝነት ስራ የተሰማሩ የጋዜጠኛነት ትርጉም ሳያዉቁ ጋዜጠኞች የሆኑ እና እየሰሩት ያለዉን ኩነኔ። ሌላዉ በወያኔ ተቃዋሚነት የቆሙ የራሳቸዉን የቤት ሥራ ሳይሰሩ በወያኔ የሚያመካኙ ምክንያት አብዢ ተቃዋሚዎችን በሚመለከት ነዉ።
ትችቴን ከመቀጠሌ በፊት በወያኔ ምክንያት የሚወዳትን አገሩን ጥሎ የአስራ 13ዓመት ታዳጊ ጽፃን ልጁን ይዞ በሕንድ አገር በስደት እየኖረ ዛሬም ወሮበላዉ የደደቢቱ ነብሰበላዉ ቡድን እየተከታተለ ረፍት እየነሳዉ ላለዉ የጋዜጠኝነት ሙያዉ በረግባር እያስመሰከረ ያለዉ የኢትኦጵ ጋዜጠኛ የነበረዉ ኢየሩሳሌም አርአያን (አርአያ ተስፋማርያም)ለመርዳት በገንዘብ እና በሞራል እንዲሁም ወደ ዓለም አቀፍ የፍትህ ተቋማት በማመልከት እየረዱት ያሉትን የቁርጥ ቀን ኢትዬጵያዊያን ዜጎች ባለፈዉ አምድ ስም ዝርዝራቸዉ አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል። እርዳታችሁን እስከቀጠላችሁ ድረስ ስም ዝርዝራችሁን ለታሪክ እየዘገብን ለማስቀመጥ ስማችሁ በተከታታይ እንዘግባለን።
ባለፈዉ ሰሞን ባገኘሁት መረጃ አቶ አለሙ ብያድጌ-የተባሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ወደ አርአያ የላኩትን ገንዘብ ደርሷል። ተቀብሎታል፡ በራሱ እና እናት በሌላት ታማሚ ህጽፃን ልጁ ኢየሩሳሌም አርአያ አመሰግንልኝ ስላለኝ፡ ምስጋናዉ በዚህ የህዋ መገናኛ መልዕክት ይድረሰዎት፡ እናመሰግናለን። ቀጥሎ ወደ ዓለም አቀፍ ተቋማት በመጻፍም ሆነ በዌብሳይታቸዉ መልክቱ ለሕዝብ እንዲደርስ የተባበሩትን ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ። ከነዚህ ዉስጥ ባለፈዉ ሳላመሰግን ያለፍኳቸዉ በጎ አድራጊ ተባባሪዎች አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ አቶ ተድላ አስፋዉ እና የደብተራዉ የህዋ መገናኛ ሰሌዳ ዝግጅት ክፍል አመሰግናለሁ። የኢትዬጵያ አምላክ “ከመጎደኛ ፤ከሆድ አደር -ህግ አልባ ወሮበላ ጥቃት” “ከመከራ”፤”ከሥራ እጦት”፤ “ስራ ከማያሰራ በሽታ” እና “ከኑሮ መፈናቀል” ይሰዉራችሁ ለማት እፈልጋለሁ።
የጋዜጠኛነት ትርጉም ሳያዉቁት ጋዜጠኞች የሆኑ ጋዜጠኞች እየሰሩት ያለዉ ኩነኔ
ኩነኔ ማለት “በስሙ መዋሸት፤አለ ኣግባብ መጠቀም፤አታድርግ ተብሎ በሃይማኖት የተደነገገ”በሕግም በሞራልም የተወገዘ ማለት” ነዉ። “ሜይ 3 የዓለም ጋዜጠኞች ቀን” ተብሎ በዓለም ሕዝቦች የተደነገገ በዓል እንደሆነ ኣብዛኛዎቻችሁ በዕለቱ የተላለፉት ዜናዎች የተከታተላችሁ የምታዉቁት ጉዳይ ነዉ።
እራሱን “የኢትዬጵያ ነፃ ፕሬስ/የጋዜጠኞች ማሕበር” እያለ የሚጠራ በክፍሌ ሙላት የሚመራ (ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ) ፤ አብርሃ በላይ፤ (ኢትዬ- ሚዲያ)፤ ክንፉ አሰፋ( አቲዬ-ፎረም)፤ ዳዊት ከበደ (የድምፅ አዘጋጅ) (የዛሬ አያድርገዉ እና ኤልያስ (ኢትዬፕያን ሬቪዉ) (ዛሬ ከነዚህ ሰዎች ጋር በኣባልነት ይኑር ኣይኑር የሚታወቅ የለም)፤ እና ስም ዝርዝራቸዉ ለኛ የማይታወቁ ሌሎች አባሎችን ያካተተ ነዉ።
ይህ ድርጅት በጋዜጠኛነት ማሕበር ምን እንደሰራ እና ምንስ እየሰራ እንዳለ በዘገባ መልክ እወክላለሁ ለሚለዉ ሕዝብ መግለጫ ያወጣበት ጊዜ አይታወሰኝም። ካለም በሙያዉ አንፃር ማዉጣት የነበረበትን መግለጫ እና የስራ ዘርዝር ዉጤት ዘገባ በጣም ጥቂት ነዉ ማለት ነዉ። እነኚህ በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰልፈን ወያኔ “አላናግር አላሰራ”አለን በማለት ከወያኔ ማነቆ ወጥተዉ ወደ ዉጭ አገር በመምጣት በዚህ የይስሙላ ማሕበር ከተሰባሰቡ በሗላ ያሳዩት የጋዜጠኝነት ሙያ ጥረት እጅግ ደካማ ብቻ ሳይሆን፤ የሕብረተሰቡን አንድነት ከበጠበጡት ጥቂት የፖለቲካ ጎረምሶች (ማለትም ቅንጅት ሲበጠበጥ ከኤልያስ ክፍሌ ከእነ አንዳርጋቸዉና ብርሃኑ ነጋ፤ ከብርቱካን መዲቅሳ ወገን ጋር በመወገን……) የቅንጅት ሊቀመንበር የነበሩት ኢንጂኔር ሃይሉ ሻዉልን በሚሊዬኖች ብር ዘርፈዋል እያሉ ስም ከምያጠፉት ጋር ቦድነዉ ለሕብረቱ መደፍረስ ከጎረምሶቹ በላይ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ጋዜጠኛ ማለት ማንም ይሁን ማንም፤ የትም ቦታ ይሁን-አንድ ዜጋ ከሕግ ዉጭ በደል ሲደርስበት፤ ያንን በደል ሕዝብ እንዲያዉቀዉ በማድረግ ሙያ ላይ የተሰማራ ማለት ነዉ። ቀዳሚ ተግባሩ የሕብረተሰቡን ሰባዊ መብት በስልጣን እና በገንዘብ የተደላደሉ ክፍሎች እንዳይበድሉት መከላከል ማስተማር መሟገት ማጋለጥ ማለት ነዉ። እነኚህ ሰዎች ግን ወደ ዉጭ አገር ከመጡ በሗላ የሰርዋቸዉ ስራዎች ሲመዘኑ ፤ ለድሃዉ እና መናገር “ላልቻለ ልሳን”-የቆሙ ሳይሆኑ ፡ ለስልጣን የቋመጡ ግለሰቦችን ወደ ሚዲያዉ አዉድማ በማዉጣት አጉልተዉ እያሳዩ እንደበሬ ወደ ሳቡት የሚሳበዉ ህብረተሰብ ዓይን ዉስጥ በመለኮትነት እንዲታዩ ምቹ ጉዝጓዝ በመሆን ቡድናዊ የጋዜጠኛነት ስራ እየሰሩ ነዉ። ከብረቱካን እስከ ብረሃኑ እስከ ግዛቸዉ እስከ ገብሩ እና ስየ እስከ መረራ ባልቻ አስከ በየነ አሁን ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍንን “ወያኔ”-እስከ ማለት የደረሱ ፖለቲከኞቻቸዉን በድጋፍ ቆመዉ የተጨማለቀ ማፈርያ ሚዲያቸዉን ባልነቃዉ ሕብረተሰብ እየረጩ ሲያወናብዱ ይታያሉ።
አብርሃ በላይ የተባለዉ “የኢትዮ ሚዲያ”-ባለቤት የመለስ ዜናዊ ወያኔ ድርጅት በመቃወም “የዉዥምብራሙ እና አድር ባዩ” የገብሩ አስራትን ሌላዉ የወያኔ ግልባጭ በመደገፍ ወላጆቻችን እና ቤተሰቦቻችንን የገደሉት እና በእሳት ሲጠብሷቸዉ የነበሩ እነ ገብሩ ፤እነ አዉዓሎም እነ አበበ ተክለሃይማኖት (የአብርሃ በላይ “አርበኞች”) በመልሶ ማቋቋም ፕሮፖጋንዳዉ ስራ ተጠምዶ የኢትዬጵያ ሕዝብ ጠላቶችን በግብዝ ህሊናዉ እየካበ ያለዉ“ስራ”እንዳይበቃዉ ዛሬ ደግሞ የኢትዬጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማሕበር የተባለዉ የይስሙላ ማሕበር የሚወክለዉ ሰዉ በማጣት “አዉስትራልያ” ዉስጥ ከሚገኝ አንድ የአበሻ የራዲዬን ዝግጅት አዘጋጅ “አብርሃ በላይን” በመጋበዝ ስለ “ፕሬስ” ምንነት እና ሃካፊነት “የሜይ ደይ 3” በዓልን አስመልክቶ እንዲያብራረለት የሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ላዳመጠዉ ሰዉ እና አብራሃ በላይ ከሚናገራቸዉ እና በግብር እንዲፈጽማቸዉ ተጠይቆ በተደጋጋሚ ደካማነቱ እና ወገንተኝነቱ ያሳየበት እና ከሙያዉ ጋር የሚጻረር የሰራቸዉ “ጣራ ብላሽ” ከሚናገርለት የሙያ ዘርፍ በሚመለከት ትዝብቱን ለናንተዉ ልተዉ።
አብረሃ በላይ “የሜይ 3 በዓል” ሲያብራራ ፕሬስ ያለበትን ሃላፊነት ሲያብራራ ፣ ጨቋኞች ዜናዎችም ሆኑ የዜጎችን እሮሮ እንዳይገለጡ እያፈኑት እንደሆኑ ገልጿል። ዜጎች ሲበደሉ ያለወገንተኛነት ማስተጋባት የፕሬስ ሃላፊነት መሆኑና በጨቋኞች ሰበብ ጋዜጠኞች እየደረሰባቸዉ ያለዉን በደል ለማስታወስ እንደሆነ (አጠቃላይ አባባል)የበዓሉ ትርጉም ገልጿል፤፡ በዚህ ትርጉምም አብርሃ ለጋዜጠኞች መብት ለተግባርነቱ የቆመ ሆኖ እንዳለ ተናግሯል።
አብርሃ በላይ ከጋዜጠኝነት ተግባር ፍጹም የማይገናኝ ስራ እየሰራ እንደሆነ ሁላችሁ የታዘባችሁት ጉዳይ ነዉ። አብርሃ የጋዜጠኛነት ትረጉም ሁሉንም በእኩልነት ማስተናገድ መድረክ መፍጠሩስ ይቅር መተርጎምስ ይቅር ራሱን በፖለቲካ ድርጅት ዉስጥ አባል በመሆን “ለዓረና ቡድን/ለብርቱካን ቡድን/(መድረክ)” እንደ ሚከራከር እና ሌሎችን የመለስ ተቃዋሚ ድርጅቶችን (የአብርሃ ድርጅትም ጨምረዉ የሚነቅፉ፤የሚቃወሙ)-የሚዘልፉ፤ስም የሚያጠፉ፤ የሚወነጅሉ ጽሁፎች በዌብ ሳይቱ ዉስጥ እንዲለጠፍ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ከታዘብነዉ ሰዎች የሚሰወር አይደልም። ይህ ሰዉ የፖለቲካ ድርጅት አባል እንጂ “ጋዜጠኛ” ሆኖ ሁሉንም እንደየ ዕድገቱ፤እርመጃዉ፤ እንደየ ብርታቱ እና ደካማነቱ ለድርጅቱ ሳያዳላ ያቋቋመዉ ሚዲያ በእኩል እያገለገለ አይደለም።
ይህ ግለሰብ ባንድ ድርጅት ብቻ ሳሆን በሲቪክ በጋዜጠኛነት እና በፖለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ በብዙ ዘርፍ ከጋዜጠኛነት ባሕሩ ዉጭ በመሰማራት ለሕብረታችን ጠንቅ ከሆኑት ጥቂቶቹ አንዱ መሆኑን በተደጋጋሚ የተተቸ ጉዳይ ነዉ። አስገራሚዉ ነገር ግን በጋዜጠኛነት ሙያ አበሳቸዉ ያዩ ጋዜጠኞች፤ (በየአረብ አገሮች በየእስር ቤቱ የተሰቃዩ ስቃይ ዉስጥ የሚገኙትን የትግራይ ተወላጆች እና ሌሎቹ ወንድሞቻችን/እህቶቻችን ለመርዳት ያስተላለፉኩለትን “የእንተባበር ጥሪ”-ጀሮ ዳባ ያለዉን ሳናነሳ፤ እንዲሁምአምናከ5’000-በላይ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዬጵያዊያን (እረጉዞች/እመጫቶች/አዛዉንቶች/ህፃናት አካለ ስንኩላን..) በዘረኞች ከደቡብ ምስራቅ እና አከባቢዉ እርሻ እና መኖርያቸዉን ለቅቀዉ እንዲወጡ ተደርጎ በየሜዳዉ በየትምህርት ቤቶች አዲስ አበባ ተጠልለዉ እንደሚገኙ የጀርምን ራዲዬ ጣቢያ ያስተላለፈዉን ዘገባ (በራሴዉ “በኢትዬፕያን ሰማይ” ብሎግ አሁንም ቪድዬዉ ተለጥፏል- እሱን ያድምጡ) አዳምጦ የራሱን የማጣራት ሂደት በማድረግ ለህዝብ ይፋ እንድያደርግ እና የዜናዉ ቅጅ በራሱ ድረገጽ እንዲለጥፈዉ ብጠይቀዉ - እሱን ትቶ ስለ ዶ/ር ያቆብ ሃይለማርያም ጥብቅና ቆሞ “ለምን ተነካብኝ” ኩፍኛ በመጮህ ለጠየቅኩት ጥያቄ መልስ ጀሮ ዳባ ከመስጠቱ ሌላ አንድ ኬኒያዊ ጋዜጠኛ ያዘጋጀዉን የኦነግ ሽምጥ ተዋጊዎችዉ ብርታት እና የዱር ቤቴ ፕሮፓጋንዳ ነበር የተጠመደዉ። በተለይም የዘር ማጥፋት የተለከፉት አንዳንድ ጠባብ ብሄረተኞች እና ጸረ አማራ ሕብተረሰብ የተጠመዱ “ነብሰ ገዳይ፤ ብላሾች”-እየሰሩት ያለዉን ወንጀል እንዲያጋልጥ እና እርዳታ እንዲደርስላቸዉ ለዓለም ህብረተሰብ እናስታዉቅ (/ጻፍላቸዉ/ተሟገትላቸዉ/ለሕዝብ አስታዉቅ/) ሲባል ከሚያመልካቸዉ ቡድኖች እና ግለሰቦች ዉጭ “ቅንጣት ታክል ከበሬታ እና አዘኔታ” የሌለዉ ወገንተኛ ጋዜጠኛነቱን ዛሬም እየቀጠለበት ነዉ።
አብርሃ በላይ በቀርቡ የኢትኦጵ ጋዜጠኛ የነበረዉ አርአያ ተስፋማርአም (ኢየሩሳሌም አርአያ)ን ችግር ለመቅረፍ በምን መንገድ ብንረዳዉ እን ብንተባበር የተሻለ ነዉዩ ብየ ላቀረብኩለት የአክብሮት እና የኢትዬጵያዊነት እንተባበር ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቤለት ቅንጣት የሃሳብ መለስ አልመለሰልኝም። በእኔ እና በሱ መካከል ያለዉ የፖለቲካ አመለካከት የማይገናኝ እንኳ ቢሆንም- ልዩነታችን አንዳለ አምቀን ለጊዜዉ 13 ዓመት በሽተኛ ታዳጊ ህፃን ያለ እናት ብቻዉን እየተንከባከበ በስደት አገር በሕንድ አገር መከራዉን እያየ ላለዉ ባልደረባዉ እንነጋገር ብየ ስለዉ እንዳመሉ “ጀሮ ዳባ”-ማለቱን እና የሰዉየዉ የሕሊና ብስለት እና ጋዜጠኛ ነበርኩ ብሎ ለሚለዉ ሙያ ያሳየዉ ከበሬታ ሳነፃፅረዉ “ኢትዬጵያ” የምንላት አገር መቸ “ከደንቆሮ ዋሻ”-ነፃ እንደምትወጣ በጣም ጭንቅ ይለኛል። በቅርቡ ታዝባችሁት ከሆነ ኢትዬ-ሚዲያ ድረ ገጹ ላይ የኦሮሞለ ብሄረተኛነት “ቀዳሚ” የፖለቲካዉ መርህ ባደረገዉ የስታንፈርዱ ምሩቅ ወጣት ጃዋር መሃመድ እና ብርሃኑ በተባለ ግለሰብ በቪኦኤ አማርኛ በተደረገዉ ክርክር ሌላዩን የክርክሩ ክፍል ሳያወጣ የመጨረሻዋን “የ ዓረና ትግራይ አባል የነበረዉ በወያኔ መሰሪ ተገደለ የተባለ አረጋዊ ገ/ብረዬሃንስ” ስም ጃዋር በመጥቀሱ “ የወያኔ መንግስት ትግራይ ዉስጥ በእነ ገብሩ የዓረና እንቅስቃሴ ምክንየት ተደናግጧል”-ብሎ በማለቱ እሷን “ለማድመቅ”-ብቻ የመጨረሻዋን ክርክር ብቻ መርጦ ለጥፏታል። እንግዲህ የአብርሃ በላይ ሕሊና “ሳይክ”በቅ-ርብ ያጠናችሁ ሰዎች ምን ማለት እያልኩ እንደሆነ ይገባችሗል። በሱ ቤት ሌሎቹ ሁለት ክፍሎች ላድማጭ ጠቃሚ አይደሉም። ልናደምጥለት የፈለገን ግን “ትግራይ፤ ዓረና…”የሚሉ ሃረጎች እስካሉ ድረስ እንሱን ብቻ እትኩሮታችን ለማድግ መማጸኑ ነዉ። (ከፈለጋችሁ ሌላ ልጨምር -የተቀሩት ለሌላ ቀን እናቆያቸዉ!!)
ልቀጥል!ኢየሩሳሌም አርአያን በሚመለከት መቸ እሱን ብቻ ነበር በትብብር እና በሃሳብ እንዲረዱ የጠየቁት!በእስክስታ ሙያ የታወቀ እስክስታ መቺ ነዉ የሚባልለት አዲስ ድመፅ ተብሎ ሚጠራዉ ሌላዉ ‘የዉዥምብራሞች ቡድን መሪዎች አድማቂ እና አድናቂ”-አቶ አበበ በለዉ የተባለዉ የራዲዮን አዘጋጅም ለአብራሃ በላይ ስልክ ለሱም አብሬ ልኬ በጣም አስገራሚ መልስ ነበር የመለሰልኝ።
ሦስት ጊዜ በኢመይል ልኬ ጀሮ ዳባ ሲለኝ ፤ አልደረሰዉ ይሆን?ብየ ጨነቀኝ እና ስለክ ደወልኩለት። ስለ ኢየሩሳሌም እና የ13-ዓመት ህፃንዋ በበሽታ እና በመጠለያ እጦት አልባሌ ቦታ ወድቀዉ እየተንከራተቱ እናዳሉ እና ለዚህ መነሻ ምክንያትም በዝርዝር አስቀምጬለት ሳበቃ ፤ “አሁን ምን እነድናደርግለት ነዉ የምትጠይቀን?’ሲለኝ መልሼ ያንኑን ዝርዝር ደግሜ ስለማንነቱ በይበልጥ ለማቀውም ከፈለገም ተጨማሪ ማህደሮች እንዲያነብብ ጠቁሜዉ ሳበቃ፤ ብያንስ “ቃለ መጠይቅ አድርግለት እና አድማጮችህ እንዲያዉቀት በዚህ አስፈላጊ ትብብር ቢያደርጉለት…” ብየ ለጠየቅኩት “ከሌሎቹ ዝባዝንኬዉ” መልሱ ማመን ያቃተኝ ግን “ስልክ ስደዉል እኮ “ከኪሴ እያወጣሁ” ነዉ” ሲለኝ “ክዉ”ብየ ነበር የቀረሁት። ያኔዉኑ አንደበቴ ሁሉ ተዘጋ፡ ካግራሞቴ የተነሳ የምለዉ ሁሉ ስለጨነቀኝ “ኢየሩሳሌምን ካሁን በፉት በጆሮየ ሰምቼዉ አላዉቀዉም”-ሲለኝ፤ ‘የቆዩ እና የቅርብ ጹሁፎቹን እንዲያነብብ’-ከጠ ቆምኩት በሗላ “አረ የማቃቸዉ የኢትኦጵ ጋዜጠኞች ጓደኞች አሉኝ ፡ እጠይቃለሁ” ላለኝ አመስግኜ ተሰናበትኩት። ላለመተባበር ምክንያት ሊሆነዉ የሚችል ጠይቆ ያገኘዉ መልስ ምንም እንደሌላ በርግጠኝነት መናገር ብችልም፡ ጋዜጠኛዉ ካጋጠመዉ የህይወት ፈተና ምንም ይሁን ማን ኢትዬጵያዊዉን ጋዜጠኛ ላለመርዳት ቅንጣት ምክንያት ሊኖር አይችልም።
ካግራሞቴ ካጋገምኩ በሗላ ንግግሩ ስለቆጨኝ በኢንተርኔት መልክት “ቃለ መጠይቅ እድርግለት እንጂ “የሁለት እና የ አምስት ብር የስልክ መደወያ ካርድ/ፈቃድ” ካጣህ ገዝቼ ልላክልህ አልኩት። ያንንም ጀሮ ዳባ አለዉ። እኔ የገረመኝ ያማርኛዉም የትግርኛዉም የ ኦሮምኛዉንም አጠቃላይ ስራስኪያጅ የሆነዉ የቪኦኤዉ አቶ ንጉሴ ስለ አቶ አበበ ሲናገር (አዲስ ድምፅ ራዲዮ ለመርዳት በተዘጋጀዉ ግብዣ) የካበዉን የጋዜጠኝነት የምስጋና ክምር፤- ቁልሉ “ደሳለኝ” የተባለዉ የወያኔ አህያ ተሸክሞ አይችለዉም (አዉዲዬዉ ደግማችሁ ብታዳምጡት አሁንም ሆነ ካሁን በፊት አበበ የፈጸማቸዉን በታኝ ቡድናዊ ተግባሮች ሳመዛዝን ም ሆነ አብርሃ ክንፉ አሰፋም ሆኑ ሌሎቹ በዚህ ጉዳይ ያሳዩት ትብብር (በተለይም የክንፉ አሰፋን (ኢትዬ ፎረም ዳት ኦርግ አዘጋጅ) ለሌላ ቀን እናኑሮዉ- ያንን መንካት ጊዜ ይፈጃል!) ሰዉየዉ ቀን በርቶለት እራሱ ይተችበት።
ታገሱኝ ጉዴ ገና አላለቀም፤ ልቀጥል ነዉ። ጥሪየን መቸ በነዚህ ብቻ ተወሰነ!በኢየሩሳሌም የተነሳ ማኣዛ ድምጽ (ፈረንጆች ሴክሲ ቮይስ የሚሉት “አሸብራኪ ድምጽ” ልበዉ?) ያላት ስታነጋግራት የጨዋ ሰላምታ እና ርህሩህ አንደበት የማይለያት የቮኦኤዋን “ወ/ሮ ትዝታ በላቸዉን”በስልክ አነጋግሬያት ነበር። አንዴ ብቻ ሳይሆን አንዴ በስልክ የመልክት መቀበያ ሳጥን ሁለቴ ደግሞ በአካል በስልክ ስለ አርአያ እና ስለ 13ዓመት ጽፃኒትዋ ልጁ ሁኔታ የምትረዳበት መንገድ ካለ አነጋገርኳት/ጠየቅኳት። ለ አንደኛዉ መልከቴ መለክቴን ላለመመለስዋ የሰጠቺኝ ምክንያትዋ “ዕረፍት/ቬኬሽን”-በመኖርዋ፡ ሁለተኛዉ የተቻለኝን ያህል እሞክራለሁ፡ ሦስተኛዉ ጊዜ እንደገና ስትዘገየኝ ለማስታወስ ስደዉል “አቶ ጌታቸዉ ደህና ነህ? አሁን ስትደዉል በስራ ስለተጠመድኩ፤ መልሼ ልደዉል?” እኔ ደግሞ “እሺ” ነበር ተባብለን ለመጨረሻ ጊዜ “ያለ ዉጤት” “ያለ መልሶ መደወል ” “ትብብር ባላሳየ” ጥያቄየ በደፈናዉ ጀሮ ዳባ መለሰቺዉ። ቮኦኤን በዚህ ጉዳይ በግልም ሆነ በስልክ መቀበያ መልከት ትተዉ የአንደኛቸዉም መልክት በራዲዮናቸዉ አልተላለፈም። ለምን?መልሱ ከኛዉ ከግብር ከፋዬች ለነዚህ ጋዜጠኞች በጋዜጠኝነት ሞያ እንዲያገለግሉን እና የራሳቸዉ ባልደረባም (ጋዜጠኛም)በጸረ ፕሬስ እርምጃ በሚያራምዱ አምባገነን ቡድኖች እና መንግስቶች ምክንያት ችግር ላይ ሲወድቁ ለዓለም እንዲነግሩ ደሞዝ ለሚቆረጥላቸዉ ለነዚህ “ጋዜጠኛ ተቀጣሪዎች”-እንዲመልሱልን እንተወዋለን። በዚህ አጋጣሚ ላማርኛዉ ክፍል ብቻ አይደለም፤ ለትግርኛዉ "አቶ በትረ ስልጣንም”በሌላ ጉዳይ (ማህበራዊ/ፖለቲካዊ) በሚመለከት እኔን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ደዉሎልኝ ስራዉ ከፈጸመ በሗላ፤ በእግረመንገዴ የኢየሩሳሌም አርአያ ጉዳይ እስኪበቃዉ አስረድቼዉ ሳበቃ ፤-እሱም ትብብር እንደ መሰሎቹ “የዉሃ ሽታ” ሆኖ ቀረ። በጉዳዩ አዝኛለሁ፤ነገር ግን እንዲህ እንዲህ ያለ ነገር ስለገጠመኝ በሁኔታዉ ለመተባበር ድርጅቱ ወይም አለቃየ አልተስማም እና አዝናለሁ። ነገር ግን በግሌ እረዳለሁ፤ በግሌ እተባበራለሁ፤ ከቻልኩ በገንዘብ ካልቻልኩ በሃሳብ እተባበራለሁ። ማለት የሚያግደን ባህል፤ሞራልና ሕግ የትኛዉ ነዉ? እንዴት ራሳችንን ከነበርንበት አስከፊ ኑሮ ተሎ ራሳነዉ?
እኔ የሚገርመኝ ከላይ ከአብርሃ በላይ ጀምሮ አስከ አበበ በለዉ፤ትዝታ በላቸዉ ክንፉ አሰፋ ዳዊት ከበደ……. በጋዜጠንነት ሙያ የተሰማሩ ከላይ የጠቀስኳቸዉ እና ያልጠቀስኳቸዉ ሰዎች ይወቁኝም አይወቁኝም ከኔ ጋርም የፖለቲካ አለመግባባት ይኑረንም በዚህ ሰብአዊ ጉዳይ ማሳየት የነበረባቸዉ “ስልጡን ኢትዬጵያዊነት” ሕሊና ምን ገጠመዉ? አዋቂነት፤ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነዉ? ለቡድን ፤በትዉዉቅ፤ ወይስ ለሰብአዊነት ስራ በሃላፊነት መወጣት?ሰዎች በትምህርትም፤ በስራም፤ መጽሃፍ በማንበብምና በማዳመጥ እና በመታዝብ የምንገበያቸዉ ዕወቀቶች ለዚህ ሰብአዊ ስራ ካላዋልናቸዉ ገበየናቸዉ ዕዉቀቶች መቸ እንድንገለገልባቸዉ ነዉ የምንቆጥባቸዉ? ዓለምን ያለምን መሪ እንድተቀር የምንመኘዉ ለምንድነዉ?አርአያንና ያስራ ሦስት ዓመት ዕድሜ ያላት ታማሚዋ ወጣት ኢየሩሳሌም ያለ መጠለያ በባዕድ አገር እንዲንከራተት ምክንየት የሆነዉ “ቅጥረኛ ጋዜጠኝነትን” ስራ እየሰራሁ “ሸራተን ሆቴል በዊስኪ እና በቡፌ” ስጋየን ከማለምለም ስጋየ በመከራ ተጠብሳ የህሊና ፍስሃ ይሻለኛል ብሎ ነዉ “ወደ ልመና” ዓለም ገብቶ እኛን በልመና እየተማጸነን ያለዉ።
ለመሆኑ እኛ እያንዳንዳችን ማን ነን? በዛዉ በልመና ዓለም ተምበርክከን “ጀ ቪ ኤ” ም ሆነ “ዩ ኤን ኤች ሲ አር”ን ተማጽነን እምባ አዉጥተን አልነበረም ወይ ከሱዳን ከጁቡቲ፤ከሶማሊያ፤ከየመን፤ከኡጋንዳ፤…..አሁን ወደያለንበት ሃብታም ዓለም ገብተን ቤት እና ንብረት የሆንነዉ? (እኔ እንኳ ድሃ ነኝ ለነገሩ እንጂ!)፡ ታዲያ ያንን ሃሩር፤ያንን ኑሮ ከመቼዉ ረሳነዉና ነዉ “አንድ ገጽ” በምንቆጣጠርባቸዉ ሚዲያዎች የነኚህን የተወጠረ የወንድሞቻችን ህይወት ማስተናገድ “እምቢ” ብለን ፈቃደኛነታችንን ላለመሳት በትዕቢት የተወጠርነዉ?አሁን ከዚህ ካለንበት ምድር “አያድርገዉና” “ዉጡ!!!!!!” የሚል ሁኔታ ቢፈጠር “ምን ይዉጠን ይሆን?! በነዚህ ጭለ፤ማ በሆኑ መንገዶች ዉስጥ መብራት ሆነን የተቸገሩትን የተቻለንን መርዳት ካልቻልን “ሆደ ቡቡነታችን”መለገስ ምንድ ነዉ ያስቸገረን? ኢትዬጵያዊ ርህሩህ ነዉ፤አዛኝ ነዉ እየተባለ ይነገርለታል። ሰዉ ሲሞት ሬሳ ላይ ዕንባችንን እያፈሰስን የኖህ ዝናብ ከዓይናችን ከረጢት ሲፈስ ይታያል፤ አንድ የታወቀ ሰዉ ሞቶ ለ ዓመቱ ዝግጅት ሲደረግ ስለ ሰዉየዉ ድንቅነት እተነገረ የዕምባችን ብረታቱ ማሃረማችንን ሲያስርሰዉ ይታያል። በመዘክሩ የተናገርናቸዉ ድምጾቻችን በየራዲዮኑ መድመቂያ ሆነዉ እናዳምጣቸዋለን። እዉነት በሙት ላይ እንደምናዝነዉ “ርህሩሆች” ነን? “ተገሐስ፡ እም እኩይ፡ ወግበር፡ ሠናየ፡ ወትነብር፡ ለዓለመ፡ ዓለም” (ከክፉ ሽሽ፤ መልካምንም አድርግ፤ ለዘላም ትኖራለህ” (መዝሙረ ዳዊት):: ልቤ ሲቃጠል እያነበቡኝ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ጠንንትህ እንዳትጎዳ እያሉ ለመከሩን ዉድ ወገኖቼ እያመሰገንኩ ፡ ለምን እየነደድኩ እንደሆነ እንደሆነ እና ከዉስጤም እየተጎዳሁ መሆኔን ይገባኛል፡ ለምክራችሁም በታም አመሰግናለሁ። ማለት የምችለዉ፦”ሲፈጥረኝ እንደዚሁ እንድነድ የተፈጠርኩበት ባሕሪ ነዉና ምን ላድርግ?”። አንዳንዶቻችን ታመንም፤ሞተንም፤ቆስለንም፤ተሰድደንም፤ታረዘንም፤ተሰድበንም ተዋርደንም፤ተቃቅረንም ”ኢትዬጵያ ሰላም”ትሁን ብቻ። ምኞቴ ያ ነዉ። ክፉ ዘመን ከወገን ከራስ ያቃቅራር። ክፉ ዘመን የለም፤ ክፉ ዘመን የምንፈጥረዉ ”ሳንተባበር ፤ሳንረዳዳ ስንቀር፤ሆድ እና ምቾት ሲያሸንፈን ብቻ ነዉ”። ክፉዉን ቀን አብረን እንዝለቀዉ፡ እዛዉ እንደርሳለን።
በተቃወሚ ድረገጾች “ስለ ፖለቲካ ነጻነት፤ስለ መናገር፤ስለ መተቸት፤ ስለ ጋዜጠኞች መታፈን መሰደድ፤መከራ ማየት መታመም መታረዝ ተጽፈዉ የምናነባቸዉ እዉን አትኩሮት እንዲደረግባቸዉ ከልብ የሚለጠፉ ጽሁፎች ናቸዉ? ወይስ “መለስ ዜናዊን” ብቻ ለማጋለጫ መሳርያ እንዲሆን ሆን ተብሎ የሚደረግ ፕሮፓጋንዳ? የፖለቲካ ጸሃፍት እና ተቺዎችስ የሚያቀርቧቸዉ ክርክሮች ባብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ነን ብለዉ በየድረገጾቻቸዉ የሚያስተናግዱ እነ ኢትዬ-ሚዲያ እነ ኢትዬፎረም፤አዲስ ድምጽ፤አዲስ ቮይስ፤አቡጊዳ አባይ ሚዲያ እና ( የኔን ጽሁፎች የሚያስናግዱትንም አንዳንዶቹን ይጨምራል) ለሁለም በእኩል ያገለግላሉ? መልሱ ‘አያስተናግዱም ነዉ”! (ስንመዝናቸዉ ባንዳንድ ስራዎቻቸዉ ከወያኔዉ ከልበ ቢሱ “ከ ዓይጋ ፎረም” “የዉሸት ከረጢት ድረገጽ” አይሻሉም። የነሱን የፖለቲካ መሪ የማያወድስ ትችት ከሆነ ተሽቀንጥሮ ይጣላል (በተለይም የሚቃወማቸዉ ከሆነ እና ጸሃፊዉ “ስታዉንች” የሚሉት የቡዳናቸዉ ተቺ ከሆነ!!!)። ዕደለኛ ከሆንክ ለምን ለሕዝብ እንዲነበብ የላክካቸዉን ትችቶች እንዳይነበብ ስትጠይቅ መልስ ታገኛለህ፡ እጅግ የሚጠሉህ ከሆነ 10ጊዜ ብትጠይቅም የምታገኘዉ መለስ “ጅሮ ዳባ” ነዉ። በቅርቡ እኔ የማከብራቸዉ በልጂግ አሊ የተባሉ ጸሃፊ ሰሞኑን ያቀረቡት የኔን ኡሮሮ የሚመሳሰል ኡሮሮአቸዉን በግሩም ብዕራቸዉ በሰፊዉ ያተቱትን ልጥቀስ
““….ወያኔ በሃገር ውስጥ ያሉትን ነፃ ሜዲያዎች እየዘጋ ፣ ጋዜጠኞቹን እያሰረ ፣ ደራሲዎችን እየገረፈ ፣ እየገደለ፣ እያሳደደ የሕዝብን የማወቅ መብት ገፎ የራሱን ደጋፊዎች ብቻ ነፃ አድርጎ በባዶ ፕሮፖጋንዳቸው ሕዝቡን ያሰለቹታል ። በዚህም ምከንያት ደግሞ በውጭ አገር ሕዝቡ ስለሀገሩ ሁኔታ እንዲያውቅ ፣ እንዲወያይ በሚፈልጉ ወገኖች የተለያዩ ድረ ገጾች ፣ ራዲዮኖች፣
ጋዜጣዎች ተከፍተው አገልግሎታቸዉን በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።
የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን በስደት ከተቋቋሙት ሜዲያዎችም መሀከል ጥቂቶቹ ራሳቸዉ በራሳቸዉ ላይ የሳንሱር ማዕቀብ የሚያደርጉ መሆኑ ነዉ ።ድረ ገጾቹ ባለቤቶቻቸው የማይደግፉትን አቋም የያዘ ጽሁፍ በፍፁም እንዳይወጣ ይከለክላሉ ። ባለፈው ወር "የተደበቀው ድርቅ "_በሚል የጻፍኩትን መጣጥፍ አንድ የድረ ገጽ ባለቤት ያለፈ ታሪክ ነውና አላወጣም ብሎ ፃፈልኝ ። ከድርቁ ጋር ተያይዞ የመጣው ችግር አልፏል --አላለፈም የሚለውን የመከራከሪያ ምክንያት በማቅረብ የድረ ገጹ ገዥ የራሱን ውሳኔ በመወሰን የሌሎችን የማንበብና የመተቸት መብት አግቶ አቁሞታል ። ምንም እንኳ ጽሁፉ በዚህኛው ድረ ገጽ ባለቤት ቢታገድም ሌሎች በዚህ ዓይነት ያልተመለከቱት ለንባብ አብቅተውታል ። በወቅቱ ስለ ድርቁ እንድጽፍ ያስገደደኝ ጉዳይ ቢኖር በቅርብ ጊዜ ሰለ ወያኔና ድርቁ በውስጥ አዋቂዎቹ ቢቢሲ ላይ የተጋለጠው ዜና ነው ። ወያኔ በእርዳታው ገንዘብ መሣሪያ ይገዛበት እንደነበር በሰማሁ ጊዜ ፣በዛ ወቅት እኔ የማውቀውን በደርግ በኩል ሲደረግ የነበረውን አጣቅሼ ነበር ለሕዝብ ለማሳወቅ የጣርኩት። የዚህ ድረ ገጽ ገዢ እሱ የሚፈልገውን ብቻ እንድጽፍለት ነው የጠየቀኝ ። ካልሆነ ግን እንደምንለያይ አሳስቦኛል። እንግዲህ ግለሰቡ ድረ ገጹን ለመጠቀም ከፈለግሁ እሱ የሚፈልገውን መጻፍ ሊኖርብኝ ነዉ ማለት ነዉ።እንግዲህ የድረ ገጾችን ባለቤቶች ለማስደሰትና ጽሁፋችን ለሕዝብ እንዲቀርብ ከፈለግን ሳንወድ ቅጥረኛ ጸሐፊ ልንሆን ነው ማለት ነው ። ይህ በጣም ያሳዝናል ።” (ከፍለን እንታገል ፤ ከቀለሉ አይቀር እንደገለባ (በልጅግ አሊ)
ኢየሩሳሌም ያደገችበት እንጀራ አምሯት በህንድ ደረቅ ቂጣ ስትሰቃይ (አም ተገኝቶ ቢሆን) እኛ ከተወለዱ ወር ላደረጉ ህፃናት ልጆቻችን ወይንም “ቤ ቢ ሻወር”-ለሚሉት ማለትም “ለምትወልደዉ እናት የደስታ የምኞት መግለጫ” (ገለብ የምንለዉ በትግርኛ) አስር ሺህ ዶላር የሚፈጅ የምግብ እና የሙዚቃ ድግስ በተንጣለለ አዳራሽ አስክስታ የምናቀልጠዉ፤ አበባ ተጎንጉኖ፤ማራኪ ምኡዝ ሽቶ ተቀብተን አምሮብን በመቶዎች ተሰባስበን የምንታየዉ ወይንም በየሙዚቃ ድግሱ በየምሽቱ በየምግብ ቤቱ የምንነሰንሰዉ ትርፍ ገንዘብ እዉነት ሕንድ አገር መጠሌአ እና በቂ ምግብ አጥታ በሰዉ አገር የምትንከራተት የጋዜጠኛዋ ልጅ ለወጣት እየሩሳሌም አርአያ ትንሽ ብር መለገስ ለምን አቃተን?
ዛሬ እዉነቱን ልናዘዝ፦ - የ ዕለት እንጀራም ሆነ የሰዉ ሃይል ትብብር የሚፈልግ የሰዉ ፊት የሚያስፈታ ጉዳይ ከሰዉ እጅ መጠበቅ ኩፉ መሆኑን የታዘብኩት ዛሬ እኔ በተግባር የማዉቃቸዉን ጓደኞቼ ስለ አርአያ እንዲተባበሩ ያላቸዉን እንዲጥሉ እየተሳቀቅኩ በሰቀቀን ስገልጽላቸዉ እና አንዴ ሳይሆን ደጋግሜ ሳሳስባቸዉ/ስጠይቃቸዉ የሚያሳዩኝ “ዳተኛነት/ልግምት”የሚሰማኝ ዉስጣዊ ስሜት ልገልጽላችሁ በጣም ይከብደኛል፤፡ ብቻ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ዓለም እረስተን ምቾት አዘናግቶን እንዳለ ለናንተ ለተማራችሁ ወገኖቼ ስገልጽላችሁ እየተሳቀቅኩ ነዉ። ያለንበት ዓለም አስተማማኝ እንዳይደለ እኔ ለናንተ አልነግራችሁም። ብቻ ባጠቃላይ ወደ እዛዉ ዓለም እንዳትገቡ ከስራ መፈናቀል፤አካልን ከሚያደክም ከበሽታ እግዜር ይጠብቃችሁ። የሰዉ ዓይን እንዳያሳያችሁ ለኔም ለናንተም እጸልያለሁ። ሕብረተሰባችን በጣም አሳዛኝ የመበታተን እና የቡድን ስብስብ አጥቅቶታል። አንዱ ላንዱ የሚያዝን ልብ አጥተናል።በተቻለ መጠን አሁንም የጋዜጠኛዉ አርአያ እና የልጁ ኢየሩሳሌም ሁኔታዉ እንዲሻሻልለት እየጣርን ስለሆነ-እስከዛዉ ድረስ ግን ዛሬም ትብብራቺሁ ስለሚፈልግ (ባለበት ኒዉ ደልሂ ቢያነስ አንዲት ጠባብ መኖርያ አነስተኛዉ 400ዶላር በወር ይጠይቃል-ልጅ ይዞ ያለ ስራ ለኢትዬጵያዊ ስደተኛ ክብደቱ ምን አህል መሆኑን አስሉት) እርዳታችሁን ያልለገሳችሁ አሁንም እርዱት እንላለን። የረዳችሁ እና አሁንም እርዳታችሁ በቀጣይነት አትንፈጉት፡ የረዳችሁም ርህሩህ ለሚባልለት ኢትዬጵያዊነት ምሳሌ ናችሁ እና ምስጋና ይድረሳችሁ። ቆጭቷቸዉ ለመርዳት ያሰቡ እና ከልባቸዉ እና ከትከሻቸዉ ላይ ካበጠዉ “ባለ ጊዜነት”ፈንቅለዉ ወጥተዉ የጋዜጠኛነት ሙያቸዉን ለጋዜጠኛዉ ባልደረባቸዉ ለማገልገል ፈቃደኛነት ለማሳየት ካሉ አሁንም ጊዜዉ አልመሸም እነሆ። የ13ዓመቷ የጋዜጠኛዉ ልጅ ኢየሩሳሌም አርአያ ህይወት እና ዕድል በያንዳንዳችን ተጭኖብናል እና የተቻለንን ለመርዳት እንተባበር። እያልኩ ወደ ሁለተኛዉ የምርጫዉ ጉዳይ አጭር ትችቴን ልግባና ልሰናበታችሁ።
ዉጭ አገር ያሉት ተቃዋሚዎች በግል የማከብራቸዉ የትግል አጋሮቼም ሆኑ ሌሎች በአካል የማላዉቃቸዉ አንዳንድ ተቃዋሚ ክፍሎች ኢትዮጵያ ዉስጥ በዚህ ወር ሊሚካሄደዉ ምርጫ “ልምን መሳተፍ አስፈለገ?”“ወያኔ እንደሚያሸንፍ እየታወቀ ለምን መሳተፍ አስፈለገ?”“ወዘተ ወዘተ….. በማለት የተቹትን ጽሁፍ እያነበብን ነዉ። ይሄኛዉ አዲስ አይደለም። ጋብ ያለዉ እና በጣም የሚያስደስት እርምጃ ያየሁት ግን በየሚዲያዉ በተለይም ዘረኞች የሚነዙት “ሃይሉ ሻዉልን ያለ መረጃ በመስደብ፤በመዝለፍ ወይንም በአሉባልታ በመወንጀል ፤ “ድረገጾቹ የሚለጡፏቸዉ የአሉባልታ ካርቱኖችንም ጨምሮ”-ድረገጾቻቸዉ ለዚህ ዓይነት ቡዱናዊ ፕሮፖጋንዳ ጠቀሜታ ለማዋል ሲታክቱ የነበሩት እንደ ኢትዬፎረም ዳት ኦርግ፤ ኢትዬሚዲያ .ዳት ካም እና አቡጊዳ የተባለዉ ጉደኛ ድረገጽም (የሕዝብ ወይስ የመድረክ ፖለቲካ ድርጅት ድረገጽ እንበለዉ?) ጭምር መረጃ የሌለዉ ስድብ እየቀነሱ እና ከዘረኞ ጸሃፊዎች ሰሞኑን ጋብ ያሉ ሆነዉ አግኝቼዋቸዋለሁ። ይሄ የተሻሻለ ይመስለኛል።
ባንዳንድ ተቃወሚ በኩል የሚሰነዘረዉ ያልተሻሻለዉ አመለካከት ግን “ወያኔ ማሸነፉ እየታወቀ ለምን ምርጫ ዉስጥ ይገባሉ?” የሚሉት ነዉ።ነገሩ አዲስ ትችት አይደለም። እኔ እንደ አዲስ እነኚህን ክፍሎች የምጠይቀዉ ደግሞ “-አስራ ስምነት ዓመቱን ወደ ጎን ትተን “ምርጫ” ከተባለ ወዲህ ምን ስራ ሰራችሁ?” ብየ ለመጠየቅ ነዉ። ቦይኮት አድርጉ ነዉ? ጭራሽኑ ምርጫ የሚባል ትርጉም አይሰጥም ነዉ? ምንድ ነዉ? ይሄ ምርጫ መሳተፍ ፋይዳ የለዉም የሚሉት ክፍሎች ባለፈዉም እንደዚያ ብለዉ ነበር። ነገር ግን ምርጫዉ የሰጠዉ ጠቀሜታ እነሱም የሚያጣጥሉት አይመስለኝም። (አሁን ዝርዝር ዉስጥ አልገባም)።
መዉቀስ ያለብን ምርጫ ዉስጥ ተገብቶ ከሚታየዉ ዉጤት አንጻር የተገኘዉ ዉጤት ከንቱ ከሚያደርግ እርምጃ እና ዉሳኔ ዉስጥ እንዳይገቡ ከወዲሁ መምከር እንጂ ገና ለገና “ወያኔ ያሸንፋል” ተብሎ የሚደረስበት ድምዳሜ በጣም ይገርማል። ወያኔ አሸናፊ የሚሆንበት ሁኔታ ካለ ከምርጫዉ በሗላ እንዳለፈዉ ተቃዋሚዎች የተራመዱበትን ጎዳና እንዳይሄዱ ነዉ። ዛሬም ተቃዋሚዎች በተናጠል መወዳደራቸዉ ለወያኔ አመቺ ቢሆንም፤ ለብቻም ቢሆን ወያኔን መጣል ይቻላል። የቺኑን የተገኘቺዉን አሸናፊ ዉጤት በቀላሉ እጅ ሰጥተዉ ወያኔ ወደ ሚኒሊክ አዳራሽ ግማሾቹም ወደ ፓርላማ ግማሾቹም ወደ ቤታቸዉ ተመልሰዉ ወያኔ የሚቀጥልበት ዕድል የሚሰጡበት ሁኔታ ከፈጠሩ ግን ወቀሳዉ መሰንዘሩ አግባብነት አለዉ። ነገር ግን ማንኛችንም ቢሆን ግምታዊ እንጂ በርግጠኝነት የሚሀኖዉን መተንበይ አንችልም እና! ይልቁንስ ‘ወያኔ እንደሚያሸንፍ እየታወቀ ፋይዳዉ ምንድ ነዉ?” ከማለት ከምርጫዉ በሗላ ለሚደረጉ ወያኔ ሊሰራቸዉ የሚዘጋጅባቸዉን ስርቆት እና አጭበርባሪ ዘዴዎቹን እያፈላለጉ እየፈተሹ በተጨባጭ ለዓለም ማጋለጥ ይበልጥ ትግሉን ዉጤታማ ያደርገዋል የሚል አቋም ስላለኝ በዚህ እንበርታ። ምርጫዉ አይረባም ካልን እነሱ ማድረግ የሚችሉትን ያ ነዉ ብለዉናል። እኛስ?
አመሰግናለሁ! www.Ethiopiansemay.blogspot.com Getachre@AOL.com 5/9/2010
Monday, May 10, 2010
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
8 comments:
ጤና ይስጥልኝ አቶ ጌታቸዉ። ለድረ-ገፅዎን ብዙ የብዙ ጊዜ ወዳጅ ነኝ። ለወገኖችዎ የሚደርጉትን አስተዋፃኦ እና በቅርቡም ለጋዜጠኛ እየሩሳሌም አራያ ያደረጉት ድጋፍ አድናቆቴ ከልብ ነዉ። ከዚሁም ጋር ተያይዞ ለደረሰበዎት፤ መጉላላት፣ ቅሬታ፣ ሃዘን፣ ... አንድዬ እንዲክስዎ የዘወትር ፀሎቴ ነው። በጠቃቀሱአቸዉ ግለሰቦች ላይ ጥርጣሬ እያደርብን የመጣን ሰዎች አለን፤ አይዝዎት ብቻዎን አይደሉም። ቀስ በቀስ ዱባዉ እየጠፋ፣ ሽሉም እየገፋ መምጣቱ አይቅሬ ነዉ።
ሌላዉ፣ በቅርቡ የሚካሄደዉን ምርጫ አስመልክቶ የሰነዘሩት አስተያየት (አቅዋም ማለቱ ሳይሻል አይቀርም። ምክንያቱም ከምርጫ ስነ-ስርአት ፍርርሙ ጀምሮ በተለያዩ መጥጥፎችዎ ሁሉ ሳየዉ የቆየሁት ነዉና) ግን ወገንተኝነትዎ ወደ የት አቅጥጫ እያቀና እንደሆነ ብዥታ ፈጥሮብኛል። እኔ እስክሚገባኝ ድረስ፣ አንድ የፖለቲካ ትግል የሚያካሂድ ግለሰብ ወይም ድርጅት፣ ያለፈዉን እና የወቅቱን ሁኔታ አገናዝቦ፣ መጪዉ ምን ሊሆን እንደ እሚችል በአግባቡ አጥንቶ የትግሉን አካሄድ ይነድፋል። በነደፈዉም የቅርብ እና የሩቅ ግብ መሰረት ይታገላላል፤ ያታግላል እንጂ እንደ ጉዋያ ነቃይ የፊት የፊቱን ብሎ ነገር የለም። ያዉም ወዶ-ገብ ተቃዋሚወቹ በምርጫዉ እንደሚሳተፉ እንጂ ከምርጫ በሁዋል ለሚመጣዉ ጣጣ ይህን ነዉ የምንከተለዉ ባላሉበት ሁኔታ፣ በደፈናዉ መደገፍ እናም አልፎም ሌሎችን ደግፉ ማለት፤ ተአስቅቦ ምርጫ ማድረጉ ይሻላል የሚሉትን ደግሞ ማብጠልጠል ክፉኛ እያስተዛዘበን ነው። አይ! አለመታደል። እንዲዉ ሲያስቡት፣ እስኪ ልጠይቅዎት፤ በዎያኔ ላይ ጫና ሊያደርግ/ጉ የሚችል/ሉ መንግስት/ታት፣ ሰብ-አዊ ድርጅት/ቶች የትኛዉ ወይም የትኞቹ ነዉ/ናቸዉ የዎያኔን ግፍ ያላወቀ/ቁ ብለዉ የሚገምቱት? ባለፈዉ ምርጫ ወያኔ ያደረሰዉን ፍጅት ያላወቀ አካል አለ/ነብረ ነዉ ሊሉን የሚፈልጉት? እረ እየተስተዋለ፣ አቶ ጌታቸዉ! መደገፍ የሚፈልጉትን ድርጅት መደገፍ እኮ መብትዎ መሰልኝ። ምርጫ ዉስጥ ገብተን የምናጋልጠዉ የወያኔ አዲስ ጉድ የለም። ጫና ሊያደርጉ ይችላሉ የሚሉአቸዉ አካላትም ወያኔን በማወቅ ረገድ ከእኔ እና ከእርስዎ ቢበልጥ እንጂ፣ ያነሰ እዉቀት የላቸዉም ብየ የማምን ሰዉ ነኝ። ሌላዉ ላይ እምነትን ከመጣል ደግሞ እርስዎም እንዳሉት "በቅድሚያ የራስን ድርሻ መወጣት"፤ በህዝባችን ኃያልነት መተማመን፤ ሞቱን ሞት፤ ትንሳኤዉን ትንሳኤ ማድረግ። በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ወያኔ እና ወያኔን የመሰለ ባይሆን እና፣ ትንሽም ቢሆን ብሄራዊ ስሜት ያለዉ መንግስት ቢሆን ኖር በምርጫ መሳተፍ የወግ ነበር። እንደ እኔ፣ ሌላዉን ሁሉ እስኪ ብንተዎዉ የሀገርን ሉአላዊነት ካስደፈረ እና በህዝባችን ላይ እየማገጠ ካለ አካል ጋር በምርጫ አልነካካም የምለዉ ለራሴ፣ ለህሌናየ ነዉ። ለእንዲህ አይነቱ አክል እዉቅና ላለማሰጠት ሳይሆን፤ እኔዉ ራሴ እዉቅና ላለመስጠት ነዉ። ከእንዲህ አይነቱ ርካሽ ጋር በመተቃቀፍ ላለመቆሸሽ፤ ላለመርክስ ነዉ በዋናነቱ በምርጫዉ መሳተፉን ተቃዉሞየ።
በመጨረሻም፣ ወንድማችን አቶ አለሙ ቢያድጌ ላደረጉት ወገናዊ አስተዋፅኦ እኔም ከልብ አመሰግናቸዋለሁ። ችግርን ያርቅላቸዉ፣ የሰይጣን ጀሮ ይደፈን እንጂ፣ ባጋጣሚ ሆኖ ችግር ቢደርስባቸዉ አብሮአቸዉ በእጥፍ ድርቡ የሚቆም ሰዉ አንድየ ይፍጠርላጨዉ። ሌሎችም እጃቸዉን ለዘረጉ ሁሉ ምስጋናየ ይድረሳቸዉ። የቁርጥ ቀን ልጅነቱንም ወገንን እና ሀገርን ለምታደግ እንደእሚያዉሉት/እያዋሉት እንደሆነ ተስፋ አለኝ። አበቃሁ። ቀናዉን ልቦና ይስጠን! አሚን በሉ ጎበዝ።
ከጌታቸዉ ረዳ (ከአዘጋጅ)
ይድረስ ለክቡር ወንድሜ አቶ ተኩዋለ፡
ለንፁህ ኢትዬጵአዊ እና ወንድማዊ ድጋፍ እና ላሳዩኝ ፍቅርዎትን ሁሌም በእዉነቱ ከልብ አመሰግናለሁ። እንድመልስለዎት ለጠየቁኝ ጥያቄ በአክብሮት መልሴ ይሄዉና።
በሚከተለዉ አስተያየትዎ ልጥቀስ እና ልመልስ።
አርስዎ ያሉትን በትእምርት ልጥቀስ
1-
“ሌላዉ፣ በቅርቡ የሚካሄደዉን ምርጫ አስመልክቶ የሰነዘሩት አስተያየት (አቅዋም ማለቱ ሳይሻል አይቀርም። ምክንያቱም ከምርጫ ስነ-ስርአት ፍርርሙ ጀምሮ በተለያዩ መጥጥፎችዎ ሁሉ ሳየዉ የቆየሁት ነዉና) ግን ወገንተኝነትዎ ወደ የት አቅጥጫ እያቀና እንደሆነ ብዥታ ፈጥሮብኛል።”
ምንም ብዥታ እንዲያድርብዎ አያስፈልግም። ወገንተኝነቴ ኢትዬጵያዊነት መሆኑን እንኳን ወዳጅ ጠላትም ካወቀዉ የዘመነ ርቀት አለዉ። ወገንተኝነቴ ለ እዉነት ነዉ። በሕዝብ ስም የሚያወናብዱ ኣምታቺዎችን በመረረ እታገላለሁ። በአቅዋማቸዉ እንደ ኩል ዉሃ የጠራ ኢትዬጵዊነትን የሚያስቀድሙትን ሁሉ ታላቅ አክብሮት እና ድጋፌ አልተለያቸዉም ትናንትም ዛሬም ለወደፊቱም ይቀጥላል። እንደሚያዉቁት እኔ ቡድን የለኝም። አንድ ሰዉ ነኝ። ኣንድ ሆኜም የሺዎቹ ኣጭበርባሪ ተግባር በኢትዬጵያዊነት ፈለግ እየተመራሁ አጋልጬያቸዋለሁ። የቆዩ ኣጭበርባሪዎቹችም ሆኑ ወያኔ በሁለት ጎራ ተቧድኖ ከተበጠበጠ በሗላ የተቀላቀሉን ኣችበርባዎችም ይሁን ከዝነኛዉ የግንቦቱ ምርጫ በሗላ ካዲስ አበባ እየፈረጠጡ አንደነታችንን የበተኑትን እና በሺዎቹ የተከተሏቸዉ በሬዎቻቸዉን ሁሉ በሚገባ መክቻለሁ። ሺ ኣጭበርባሪ እዉነትን ባስቀያሚ ቀለም ለመቀባት ብሎ ብሎ አልሆነለትም። ሌላ ቀርቶ ከምርጫዉ በሗላ እየፈረጠጡ በየምክንያታቸዉ ወደ ዉጭ የመጡ የወያኔ ጋዜጠኞች፤ዲፕሎማቶች፤ዳኞች ሁሉ ካጭበርባሪዎቹ ጎራ ጋር በመሰለፍ እኛኑን የወያኔ ጎራ አድርገዉ እነሱ የተገላቢጦሽ በኛ ጋር የወያኔነት ካባ ሊያለብሱን እንደሞከሩ የ ኢንተርኔት መዛግብቶች ህያዉ መረጃዎች ናቸዉ። ሌላ ቀርቶ “ብርየ ብርቅየ” የተባለዉ የወያኔ ሎሌ ሳይቀር ኢትዬጵያዊዉ ታየ ወልደሰማያትን” በክህደት ከስሶ የስድብ እና የንቀት ዉርጅብኝ ሲያወርደዉ የነበረዉ ጉድ የታዘቡ ኢመስለናል። የ ኢትዬ ሚድያዉ እና የ ኢትዬጵያን ረቪዉ እነ ክንፉ አሰፋን እና ኤልያስ ክፍሌን በሃይሉ ሻዉል ላይ ሲሰነዝሩት የነበረዉን አስነዋሪ ስድብ እና ውንጀላ ሳላወሳለዎት ማለቴ ነዉ።
እነዚህ ጉዶች “ብርቱካን ብርቱካን” ሲሉ ቆይተዉ ብርቲካን ስትተሰር “ህጉ አይፈቅድልንም እና ቢበዛ 300 ሰዎች ብቻ ነዉ ለሻማ መብራትም ሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳየት የምንችለዉ እያሉ የይስሙላ የዉጭ አገር ርሃብ አድማ ፤የፓልቶክ ጫጫታ እና ካዲስ አበባ በስልክ እየተጋበዙ በአዳማቂያቸዉ በቪኦ ኤ ቡድን ጋዜጠኝነት እየታጀቡ የሚሰጡት በ “ብርቱካን መሪያችን ናት” ቃለ መጠይቅ እና “ብርቱካን ትቅደም” መፈክር ተወስነዉ ቁም ነገር ሳይሰሩላት በሷ ጫንቃ ተንተልጥለዉ “መድረክ” ንን ግንቦት 7 ንን ፤ መድረክ እያሉ የሚንጋጉ የተኩላ እና የበግ መንጋ ድብልቆች ጉደኞችን ሁሉ በጥብቅ እቃወማቸዋለሁ። ይሄ ደግሞ ለ አደባባይ ግልጽ ሆኜ መከራከሬ እቅ ነዉና ከርስዎ አይሰወርም የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ ብዥታዎ ግልጽ ይሆንለዎ ዘንድ ይሄንኑ አስምሬ ልለፍ።
እነኚህ መንጋዎች ሃይሉን ፤ዲክታተር፤ስልጣን ፈላጊ፤ የወያኔ ቅጥረኛ እያሉ ታየ ወልደሰማያትንም በክህደት የሚከሱ ነዉረኞች ከመሆናቸዉ በላይ እነኚህ ቡድኖች ለቅንጅት መፍረስ ላንድነታችን መኮስመን፤ ለወያኔ ዕድሜ እና ፋታ መስጠት ከፍተኛ ሚና ተጫዉተዋል። ለወደፊቱ ግን በራሳቸዉ ድካም እና አመል መበተናቸዉ አይቀርም (ባንደኛዉ ክፍላቸዉ ፤ድብድባቸዉንና ደም መፋሰሳቸዉን የታዘበዉ መለስ ዜናዊ እንኳ ሳይቀር ፓርላማ ዉስጥ ቀልዶባቸዋል እና ለርስዎም የተሰወረ አይደለም ብየ አምናለሁ። ሃይሉ ሻዉልን ፤ታየን የሚዘልፉ ተደባዳቢዎች ናቸዉ አገር እንመራለን እያሉ የመለስ ዜናዊ መቀለጃ እና መሳቂያ እየሆኑ ያሉት)። አሁን እንዳሉት ከቀጠሉ፤ ወያኔ ያላግጥብናል፤አንድነት የሚባልም ህልም ሊሆንብን ነዉ።ድጋፍህ ለማን ነዉ ለሚሉኝም ጥያቄዎ- ድጋፌ ለመ ኢ አድ ለግሻለሁ። በዛዉ ድርጅት ዉስጥ እንደ ኩል ዉሃ የጠራ ኢትዬጵያዊንትን ያልተለያቸዉ ለዘመናት በዛዉ አቁዋማቸዉ የቆዩ ዛሬም እንዳሉበት የቀጠሉ በዘር ማንዘር የጎሳ ፖለቲካ ያልተተበተቡ ዉድ ኢትዬጵያዊያን እና ኢትዬጵያዊያት አሉበት እና ያለ ምንም ማመንታት በገንዘብ ባልረዳም ለ መ ኢአድ በህሊናየ ከፍተኛ አክብሮት አለኝ። እነ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ያማራን ሕዝብ እንደ አልባሌ ሲያዋርዱት፤ ኢትዬጵያዊነትን ሲያንቋሽሹ ፤ ዘረኛ መጻህፍት እየጻፉ ለጥቃት ሲያጋልጡት፤የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ወደ ሗላ ለማይሉ ወንጀለኞች እና ግብዞች በፕሮፓጋንዳዉ ረገድ “ያዉም በመጽሃፍ ታትሞ” እየተሰራጨ “ግፋ በለዉ’ እያሉ የ ጎሰኞችን ሕሊና እያሰከሩ ለብዙ ሺሕ ያማራ ሕብረተሰብ ጥቃት ምክንያት የሆኑትን እነ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የመሳሰሉትን ወንጀለኞች የለኮሱት እሳት ለማጥፋት ያለ እረፍት እየታገሉ ያሉትን ዛሬ በመ ኢ አ ድ ወስጥ ያሉት በጽናት የቆመዉ ዜጎች ወገንተኝነቴ ስገልጽለዎ በኩራት ነዉ። ታየ ወልደሰማያትን እና ሃይሉ ሻዉልን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከወያኔ እስከ ጋዜጠኞች ነን ባዬች እና የወያኔ እግር አጣቢ አሽከሮች የነበሩት በጉልተኛ እና በመሳፍንቶች በዘር ቆጠራ ህሊና ዛሬም የሚኮሩ እንደ እነ ተኮላ ሓጎስ የመሳሰሉት ስም አጥፊ ወራዳ ማፈርያዎች የተሞከረ ሴራ በሚገባ መክቻለሁ ለወደፊቱም እነዚህ ወራዳዎች ከማፈርያ ቀፎአቸዉ ወጥተዉ ብሄራዊ ወንጀለኞችን በሕዝቡ ጫና ላይ ተመልሰዉ ለመጫን የሚያደርጉት ሴራ ካላቆሙ በገሃድ መታገሌን አይቆምም። ወገንተኝነቴ አሁን ግልጽ ይሆንለዎታል ብየ አምናለሁ። በዚህ አቋሜ ብዥታ አይደርበዎት። አንድ!
From the editor part two
2- “እኔ እስክሚገባኝ ድረስ፣ አንድ የፖለቲካ ትግል የሚያካሂድ ግለሰብ ወይም ድርጅት፣ ያለፈዉን እና የወቅቱን ሁኔታ አገናዝቦ፣ መጪዉ ምን ሊሆን እንደ እሚችል በአግባቡ አጥንቶ የትግሉን አካሄድ ይነድፋል። በነደፈዉም የቅርብ እና የሩቅ ግብ መሰረት ይታገላላል፤ ያታግላል እንጂ እንደ ጉዋያ ነቃይ የፊት የፊቱን ብሎ ነገር የለም።”
ትክክል ነዎት። እኔም እኮ የምለዉ እና ካሁን በፊትም ያልኩት የወቅቱን ሁኔታ እና መጪዉ ምን እንደሚሆን ባግባቡ እናጥና ነዉ። የመድረክ እና የግንቦት 7 የሚባሉ የነመረራ እና የነገብሩ የእነ በየነ የነግዛቸዉ በግንቦትም የዘረኞቹ የነብርሃኑ እና አንዳርጋቸዉ ሬከርድ ያስመሰከረዉ ነገር ካለ የወደፊቱ ሁኔታ አስተምሮናል። እነ ብርሃኑ ነጋ “ ወያኔ እስር እስካስገባኝ ድረስ የሰዉን መብት የሚጋፋ የሚገርፍ መስሎ አይታየኝም ነበር” የሚል የዶክተርነት ማዕረግ የለበሰዉ የግንቦት 7 መሪ እና እነ ስየ እነ ገብሩን አትንኩ፤አትዉቀሱ፡ የሚሉንን ሁሉ ናቸዉ ያለፈዉንም ሆነ የመጪዉን ግንዛቤ ዉሉ የጠፋቸዉ። በጣም ከሚገርመኝ ነገር ፡ እነ ገብሩ እነ ስየ እነ አረጋሽ እና የዓረናዉ ዘረኛዉ ብርሃነ ሃይሉ ከኦሮሞ እና ከጉራጌ ከወላይታኛ ከአማርኛ ተናጋሪ ሊሂቅ ቡድን ጋር ግንባር በመፍጠሩ “ህብረ ብሔር” የሚባለዉ ቅልቅል ገንብተናል እና የተበታተነዉ ያገሪቷ አንድነትን ሰብስበናል የሚለዉ የፕሮፖጋንዳ ፍጆታቸዉ እጅግ አድርጎ አስቆ እንደገና ያሳዝነኛል። ለዚህም በታላቁ አድርባይ በ“ግዛቸዉ” እና በመሰል ጓዶቹ ዓይን ብሔራዊ ወንጀለኞቹ “አነ ስየ፤ አረጋሽ ገብሩ….” የትግራይን ሕብረተሰብ ወኪሎች ናቸዉና እነሱን አስከትለዉ መቀሌ ከተማ አዳራሽ ዉስጥ በሰበሰቡት ሕዝብ ፊት ቅንጅት በነበርንበት ወቅት “የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ነበርን” ትግሬን ወደ መጣበት ለማባበረር አቅደን ነበር፤ በንግግራችንም አረጋግጠናል፤ እያለ ሆን ብሎ “ለፖለቲካ ንግድ” በማያገባዉ ገብቶ አለቃዉ በነበረቺዉ ብርቱካን መዲቅሳ እንዳደረገቺዉ ቅሌት እሱም (ግዛቸዉም) ያንን ቅሌት በመድገም “በቅንጅት ስም” ለትግራይ ሕዝብ “ይቅርታ መጠየቁ” ሌላዉ አስጋራሚ የመድረክ አቅድ በ እግረመንገዴ አስታወሱኝ። መቸ ይሄ ብቻ! “ከወያነ ትገሬ ሌላ ወያኔን የሚጥል ሃይል ከቶ የለም” እያሉ እነኚህ ሰዎች ካልተጨመሩ ጉልበት የለንም ብለዉ የቀለጠዉ ሃሞታቸዉ በነዚህ ብሄራዊ ወንጀለኞች ሃሞት እየተገፉ “መለስ ዜናዊን” ማዉረድ በጽናት ያለ ሃፍረት ቆመዋል። አምላኪዎቻቸዉ የድሮ ወያኔዎች (ዲፕሎማቶች፤ጋዜጠኞች፤ ካድሬዎች እና የወያኔ ታጋዮች….) የነበሩ መሆናቸዉ ብናዉቅም ለምን ዓረና እና መድረክ የተባለዉ “ባዶ ከረጢት” ለምን ደገፉ ቢባል ፤ እነዚህ ተከታዬቻቸዉ የ ዓረናዉ አንቀጽ 39ን ፖሊሲያቸዉ ወይንም ሕዘእብን በቋንቋ ለይቶ ማስተዳደርን እና ማደራጀትን ሳይሆን “መለስ ዜናዊን “ በመቃወማቸዉ ብቻ ነዉ። ደጋፊዎቻቸዉ የሚሉት “ጠላታችን መለስ ይዉረድ እንጂ በሗላ እነ ስየ እነ ገብሩ በወንጀል መክሰስ ከፈለጋችሁ ክሰስዋቸዉ” የሚል ብስራት እየነገሩን ነዉ። የመክሰስ መብታችንም እንደሚጠበቅ እርግጠኞች ሆነዉ ማረጋገጫ ብለዉ የሚያቀርቡልንም “ መጀመርያ መለስን እናዉረድ እና መለስ ካወረድን በሗላ ያኔ እኔም ሆኑ ባልደረቦቼ ልትከሱን ትችላላችሁ” ብለዉ ግበሩ እና ስየ ስለነገሩን ስላለን “እመኑዋቸዉ” ይሉናል። አባባለቸዉ ሁሉ ሰለሚያስቀኝ - ትዝብቱ ለእርስዎ ልተዉ (ሳት ብየ በየፓልቶኩ በመጎብኘት እና በሚጽፉት የስብሰባ ዘገባቸዉ ሳነብብ የሚናገሩት ያ ነዉ)። እንግዲፍ የነዚህ ፖለተኪኞች ንድፍ (የዓረና የመድረክ ንድፍ) ይሄ ነዉ (መለስ ዜናዊን ጥለን በሗላ እንተሳሰብ ነዉ)። እርስዎ ያነሱትን የፖለቲካ ንድፍን በተመለከተ የሳሰበዎት ነገር ካለ እና እኔ ይኸንን በተመለከተ ማለት የምለዉ የቅርብ እና የሩቅ ንድፍ ነድፎ የወያኔ ግልባጭ መልሶ 18 ዓመት እንዳይነግስ ሕዝቡ “መ ኢ አ ድ” ን ቢደግፍ የተሻለ አስተማማኝ አገር ይፈጠራል የምለዉም ለዚህ ነዉ።
ወያኔን ያገለጉሉ ግልባጮች እና ከሌላ ብሄረሰብ የተዉጣጡ አለቅላቂዎቻቸዉንም ለጥንካረያችን እንከን ስለሆኑ ትግላችን ስልጣን ላይ ያለዉ አዉራዉ ወያኔዉ እና ግልባጩ ማለትም “ግልገሉን ወያነ” ጨምሮ በጣምራ እንድንታገል ግድ ሆኖብናል። ከወያኔ የወጡ ጋዜጠኞች፤ዲፕሎማቶች፤ ታጋየየች ዞሮ ዞሮዉ ያችን ስልጣን ለመሪዎቻቸዉ ለማጎናጸፍ ስለሚፈልጉ ከወያኔ እኩል እንቅፋት እንደሚሆኑ ካሁን በፊት ተተንብያለሁ! የተነበይኩት ያ ነበር ዛሬ እዉን ሆኖ እነ ስየ እነ ገብሩ አለቅላቂ ቡድን ባገር እና በዉስጥ አገር ፈጥረዉ እንዲያለቀልቅላቸዉ የወያኔ ጠበል አቅምሰዉት ስለ ስየ ተናጋሪነት እና ባሸናፊነት መዉጣት ፤ስለ አረጋሽ እንከን የለሽ አድዋዊት ተወዳዳሪነት ፕሮፖጋንዳ ለመጻፍ እንቅልፍ አጥተዉ ሲያቃዣቸዉ እያየናቸዉ ነዉ። ቪ ኦ ኤ የተባለዉ ጉዳም (ጉደኛ ) ራዲዬንም የሚለቀልቀዉ ያለቅላቂ ስራ በሰፊዉ ተያይዞት ከስየ ከገብሩ ከ አረጋሽ ከመራራ ከበየነ ከተመስገን ጋር ፍቅር ይዞት የ መ ኢ አድን መሪዎች እና ታላለቅ ሰዎችን ሳያስታዉስ ብሄራዊ ወንጀለኞችን እየጋበዘ ጥዋት ማታ ሳተላይት ዘረጋሁ በሚልብን መስመሩ ጠበላቸዉን እየረጨብን ነዉ። የጉድ ጉድ!!!!! ቪ ኦ ኤ የሚባል ጉደኛ ራዲዬን ሲነሳ የሚገርመኝ ነገር አቶ ንጉሴ መንገሻ የተባለዉ የዚያ ራዲዬን ሐላፊ በጠበሉ ርጭት ጫዋታ ላይ እሱም ተነክሮበት ይሆን እላለሁ እንጂ ራዲዬኑ በእንዲያ ያለ ቡድናዊ ጋጠወጥነት በተደጋጋሚ ባይሰለፍ ነበር እላለሁ። እንዲህ ያልኩበት ምክንያት ደግሞ “ጋዜጠኞች ነን የሚሉን ሙያቸዉን ትትዉ ራሳቸዉን በቡድን ጨዋታ አስገብተዉ” በመጨቃየቱ ጨዋታ ላይ ገብተዉ በማየቴ ነዉ። ወንድሞቼ! ጉደኛ ወቅት እኮ ነዉ የደረስንበቱ። ማንን እንዉቀስ? ወያኔ እድሜህ ይጠር! ግልባጩን ልኮ በጠበጠን።.......
በእዉነት፤ በሕልሜም በዉኔም ወያኔ በትግላችን ዉስጥ ገብቶ እንኳን ባርበበኝነት እና በተቃዋሚ የፖለቲካ ተጠሪነት ቀርቶ እንደዉ ወያኔ የሚባል መሪ ክፍለ ቅጣቱን እስኪያገኝ ድረስ ከሕዝብ የተገለለ ወንጀለኛ እንደሚሆን ነበር ያሰብኩት እንጂ ተቃዋሚዉን በግንባር ቀደም ይመራል ብየ አልሜም አስቤም አላዉቅም ነበር። የሆነዉ ግን ይሄዉ ነዉ። ስለዚህ የፊት የፊቱ ብሎ ነገር የለም የሚሉት አማርኛ እኔም ጋር ይሁን መ ኢ አ ድ ጋር እንደሌለ ለመግለፅ ነዉ በጥልቀት የሄድኩት። ትንሽ ስለ መ ኢ አ ድ ልበል። መ ኢ አ ድ ፣ ያለፈዉን እና የወቅቱን ሁኔታ አገናዝቦ፣ መጪዉ ምን ሊሆን እንደ እሚችል በአግባቡ አጥንቶ የትግሉን አካሄድ ነድፏል። ቁጭ ብለዉ ተራራ ላይ ወጥተዉ ነፃ እናወጣሃለን ያሉትን ነፃ እስኪያወጡት አልጠበቀም። የፊት ፊቱን መጀመርያ ልልቀም አላለም። ሩቅ ግብ አለዉ ፡፡ ጎሰኝነት ሳይሆን ኢትዬጵያዊነት! በዚያ ጉዞ ለዢም የተጓዘበትን ማህደር መመርመር አስፈላጊ ነዉ።
2- “ ያዉም ወዶ-ገብ ተቃዋሚወቹ በምርጫዉ እንደሚሳተፉ እንጂ ከምርጫ በሁዋል ለሚመጣዉ ጣጣ ይህን ነዉ የምንከተለዉ ባላሉበት ሁኔታ፣ በደፈናዉ መደገፍ እናም አልፎም ሌሎችን ደግፉ ማለት፤……….. ተአስቅቦ ምርጫ ማድረጉ ይሻላል የሚሉትን ደግሞ ማብጠልጠል ክፉኛ እያስተዛዘበን ነው። አይ! አለመታደል። እንዲዉ ሲያስቡት፣ እስኪ ልጠይቅዎት፤ በዎያኔ ላይ ጫና ሊያደርግ/ጉ የሚችል/ሉ መንግስት/ታት፣ ሰብ-አዊ ድርጅት/ቶች የትኛዉ ወይም የትኞቹ ነዉ/ናቸዉ የዎያኔን ግፍ ያላወቀ/ቁ ብለዉ የሚገምቱት? ”
ብለዉ የጠየቁኝ ነገር - እኔ ያልኩት “ ባንዳንድ ተቃወሚ በኩል የሚሰነዘረዉ ያልተሻሻለዉ አመለካከት ግን “ወያኔ ማሸነፉ እየታወቀ ለምን ምርጫ ዉስጥ ይገባሉ?” የሚሉት ነዉ።ነገሩ አዲስ ትችት አይደለም። እኔ እንደ አዲስ እነኚህን ክፍሎች የምጠይቀዉ ደግሞ “-አስራ ስምነት ዓመቱን ወደ ጎን ትተን “ምርጫ” ከተባለ ወዲህ ምን ስራ ሰራችሁ?” ብየ ለመጠየቅ ነዉ። ቦይኮት አድርጉ ነዉ? ጭራሽኑ ምርጫ የሚባል ትርጉም አይሰጥም ነዉ (ብርሃኑ ነጋ “የምርጫ ጨዋታ” “ቧልት” ብሎ ደምድሞታል)? ምንድ ነዉ? ይሄ ምርጫ መሳተፍ ፋይዳ የለዉም የሚሉት ክፍሎች ባለፈዉም እንደዚያ ብለዉ ነበር። ነገር ግን ምርጫዉ የሰጠዉ ጠቀሜታ እነሱም የሚያጣጥሉት አይመስለኝም። የዛሬዉም ካለፈዉ የሚያስገኘዉ ዉጤት የተሻለ ካልሆነ ጨዋታ ግን ሊሆን አይችልም (አሁን ዝርዝር ዉስጥ አልገባም)።
መዉቀስ ያለብን ምርጫ ዉስጥ ተገብቶ ከሚታየዉ ዉጤት አንጻር የተገኘዉ ዉጤት ከንቱ ከሚያደርግ እርምጃ እና ዉሳኔ ዉስጥ እንዳይገቡ ከወዲሁ መምከር እንጂ ገና ለገና “ወያኔ ያሸንፋል” ተብሎ የሚደረስበት ድምዳሜ በጣም ይገርማል ነዉ ያልኩት። ወያኔ አሸናፊ የሚሆንበት ሁኔታ ካለ ከምርጫዉ በሗላ እንዳለፈዉ ተቃዋሚዎች የተራመዱበትን ጎዳና እንዳይሄዱ ነዉ። እያልኩኝ ያለሁት። ዛሬም ተቃዋሚዎች በተናጠል መወዳደራቸዉ ለወያኔ አመቺ ቢሆንም፤ ለብቻም ቢሆን ወያኔን መጣል ይቻላል ነዉ እያልኩ ያለሁት።የቺኑን የተገኘቺዉን አሸናፊ ዉጤት በቀላሉ እጅ ሰጥተዉ ወያኔ ወደ ሚኒሊክ አዳራሽ ግማሾቹም ወደ ፓርላማ ግማሾቹም ወደ ቤታቸዉ ተመልሰዉ ወያኔ የሚቀጥልበት ዕድል የሚሰጡበት ሁኔታ ከፈጠሩ ግን ወቀሳዉ መሰንዘሩ አግባብነት አለዉ። ነዉ ያልኩት። ነገር ግን ማንኛችንም ቢሆን ግምታዊ እንጂ በርግጠኝነት የሚሀኖዉን መተንበይ አንችልም እና ይልቁንስ ‘ወያኔ እንደሚያሸንፍ እየታወቀ ፋይዳዉ ምንድ ነዉ?” ከማለት ከምርጫዉ በሗላ ለሚደረጉ ወያኔ ሊሰራቸዉ የሚዘጋጅባቸዉን ስርቆት እና አጭበርባሪ ዘዴዎቹን እያፈላለጉ እየፈተሹ በተጨባጭ ለዓለም ማጋለጥ ይበልጥ ትግሉን ዉጤታማ ያደርገዋል ያልኩበት ምክንያትም፡ የዉጭ አገር መንግሥታት የወያኔ ማንነት አያዉቁትም ማለቴ ሳይሆን “ድራማዉ ተዘግተዋል” ሲሉን “ትዕይንቱ ይሄዉና በሕያዊነት እንዲቀጥል አድረገናል” በማለት “ድራማዉ የተዘጋዉ በተራራ ጫፍ ላይ ወጥተዉ እንዲፈላሰፉ ቁጭ ብላችሁ ብሉ ያላችሗቸዉ የተራራ ከያኒዎቻችሁ ኣእምሮ ዉስጥ እንጂ በኛ በኩል ሰገነቱ ህያዉ ሆኖ በቀጣይነት ችቦዉ እንዳይጠፋ አድርገናል” እንዲሉ የሚያስችላቸዉ የትግል ድል ማስገባቸዉ ካረጋገጡ ከወያኔ ጋር ግብግብ መግጠማቸዉን ለወያኔ ጌቶች “መርዶ” መግለጫ ነዉ። ማለቴ ነኝ። እንደነ ብርሃኑ ነጋ ምርጫዉ ጨዋታ ነዉ ብሎ ለዉጭ አገር ጋዜጠኛ እና ላገር ዉስጥ ላለዉ ህዝብ ከመናገር አልፎ ፤ ምርጫዉ የወያኔ ጨዋታ ነዉ፤ አይረባም ካልን እነሱ ማድረግ የሚችሉትን ያ ነዉ ብለዉናል። እኛስ? ብየ ነበር የጠየቅኩት። እኛስ?
ከወደዚህ፣ ወደ እኛዉ፣ ዓለም ገና አስር አልሞልታም። በዘጠኙ እንደተቆናጠጥን ነን - ቶሎ መልስ አለመስጠቴ። ኖር ኖር ቢየ ነው የተቀብልኩት የዉድ ወንድሜን ምላሽ። ጤና ይስጥልኝ እያልኩ ነዉ ከወደ እዚህም የተከበሩ አቶ ጌታቸዉ ረዳ። በጣም በጣም ትህትና ለተቸረዉ ምላሽዎ ምስጋናየ ይድረስዎ።
ዉድ መንድም ጌታቸዉ፣ በብዙ ነጥቦች ተግባብተናል። እንደ አሁኑ በፅሁፍ ባናደርገዉም በተለይዩ መጣጥፎችዎ ስንግባባ መኖሩን ቀደም ብየ ያልኩትም ነዉ። ስለዝህም በዘረዘሩዋቸዉ ነጥቦች፣ በጠቃቀሱአቸዉ ሰዎች (ከድ/ር ታየን እና መሃንዲስ ኃሉን ሳይነካ) እና ድርጅቶች እኔም የተለየ ሀሳብ የለኝም። እርስዎ ባሉት ይቁዋጭ - ገልቱን ሲደጋግሙለት ወግ የደረሰዉ ይመስለዋልና።
በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ግን አፅዖት መስጠት እፈልጋለሁ - ባንዳንዶች ላይ የተለያየ ግንዛቤ ባይኖረንም።
1. በወድሜ በጌታቸዉ እንከን አልባ ኢትዮጵያዊነት ምንም ጥርጥር የለም። ዜግነቱን ሁላችንም ሳይሸራረፍ ይዘነዋል - እኩዮቹ፣ እነ መለስ እና የዘር ፖለቲካን የሚያራምዱቱ ሁሉ፣ ለእነሱም የተምበረከኩቱ ሳቀሩ። ፖለቲካዊ አካሄደዎን ለማለት ነዉ የነበረዉ እንጂ ኢትዮጵያዊነትዎን ለማጠቅ አልነበረም - በዜግነት ላይ ማን ቆራጭ አድርጎኝ። ከላይ የተወሰነለዎትን። ከመቀመጫየ ብድግ እያልኩ ይቅርታ፤ ካለው የእዚያ ዓይነት እንድምታ።
2. ለወገኖችዎ እና ለሀገርዎ እያደረጉ ያለዉ አስተዋፅዖ ሚዛን ዉስጥ የገባ ነዉ። ከዚህም ጋር ተያይዞ ብዙ ፈተናዎች እንዳሉበዎት ባይናገሩትም የወያኔን እኩይነት የሚያቅ ሁሉ የሚረዳዉ ነዉ። ወያኔ ንቆ የሚተዎዉ ጉዳይ የለዉም - እንኩዋን ጠላቴ ነዉ፣ ተቀናቃኘ ነዉ የሚለዉን ይቅርና ጠላት የመሰለዉን፣ ተቀናቃኝ የመሰለዉን እና በህልሙም እንኩዋ ሳይቀር ሲጠላዉ/ሲጣላዉ ያየዉን ሁሉ ለመብላት/ከመብላት ወደሁዋላ የማይል መፃጉ ፍጡር ነዉ። ለበቀል የተፈጠረ፤ በበቀል ያደገ፤ ለበቀል የነገሰ፡ እየተበቀለም የሚሞት። እናም አንድዬ መከታ ይሁንዎ ነዉ ማጣፊያየ።
3. "የፊት የፊቱን ..." ስል፣ ዉድ ወንድሜ ጌታቸዉ፣ መኢአድን አስመልክተዉ የከተቡልኝ እንዳለ ሁኖ (ለዚህም ምስጋና በድጋሜ) ፈቃድዎት ሆኖ እንደገና ብመለስበት፣ ትግላችን ያለፍንበትን የትግል ሂደቶች እና በውቅቱ ከምናደርገዉ ትግል ጋር ማገናዘብን ይጠይቃል። ይህ በራሱ ደግሞ ለመጭዉ ምን ሊያስከትል እንድሚችል ትንብርያን እና ለዚያም ከአሁኑ እርምጃችንን ልናስተካክል ይለናል። ትንቢት ይኖረናል። ትንቢት የሌለዉ ትግል ራእይውን ማየት ቀርቶ አያሸታትም። እባብ አዉቆ መርዙን እንደጣለ ይቆጠር። ለዚያዉም ወያኔን ያክል መሰሪ ባላጣ ጋር። ከተቃዋሚዉ ጋር ተቃዋሚ፣ ከደጋፊዉ ጋር ደጋፊ፣ ከብሄርተኛው ጋር ብሄርተኛ፣ ሀገራዊ ከሆኑት ጋር ሀገራዊ (እነስየን፣ ገብሩን፣ አረጋሽን፣ ነጋሶን፣ በየነን፣ መረራን፣ ተኮላን፣ ... ከዚህ አኩዋያ ያዩዋል)ምን አለፋዎት እስስትዋን አስንቆ ከሚለዋወጠው ጋር ነዉ እኮ ትግሉ። እናም ለዚህ እቡይ ፍጡር ስነ-ስራት ብሎ ነገር፤ ኢትዮጵያዊ ጭዋነት ብሎ ነገር ለእኔ እጅ ከመስጠት ያለፈ ትርጉም የለዉም። የመኢአድ ስሌት ለዚህ ነዉ የሚጎረብጠኝም። ወያኔ ሁሉ በእጁ፤ ሁሉ በደጁ። አምስት አመት ሙሉ የተዘጋጀበት። መኢአድ ከእጁም ከደጁም ምንም። ታዲያ ትግል በምን? ወያኔ ማንን ፈርቶ? መለስ ሰላማዊ ታጋዮች ነን ያልችሁ ሁሉ ለምርጫ ካልቀረባችሁ ወዮላችሁ እያለ በሚለፋደድ ፍጡር እኮ ነዉ ምርጫዉ እየተመራ ያለዉ መሰለኝ!። እናም ይህ ሰዉ እንዴት ብሎ ነዉ በካርድ ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ስልጣን መልቀቅ ቀርቶ የሚያጋራዉ!? እነማንን እንደሚፈልግ እያወቅን። መጭዉ ምን እንደሚሆን ቁልጭ ያለ ነዉ - መምሸት መንጋቱን መጠበቅ እሚኖርብን አይደለም። ወያኔ እስከ ግሳንግሱ ነግም ጉልት። በዚህ ሂደት ማንም ምንም አመጣም። አይ! ያለ ወዮለት!። ወይም አዎ! መጭዉም ያዉ ወያኔ ነዉ፤ ስለዚህ የምናገኛትን ካርድ ይዘን እንግባ ፓርላማ ሌላ ጉዳይ። ለዝህ ስሌት ማርከሻውን እየለፈፉ እና በቻሉትም መንገድ እየተገበሩ ያሉ በግለሰብም በድርጅትም (ከእነ ግ 7 ዉጭ) አሉ - ለጊዜዉ ትግላቸዉ ከዐይን አልገባም ይሆናል እንጂ በትግሉ ዉስጥ ዛሬም እንደ ወትሮአቸዉ እተማገዱ ያሉ የእትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መኖራቸዉን ዉድ ወንድሜ ያጡታል የሚል ግምት ከልቤ ተጥዶም አያዉቅ።
4. እና የመጨረሻዉ፣ ብዙም ያልጠብቅሁት። በግሌ ነዉ ይህን ሁሉ እንቅስቃሴ የማደርገው ያሉቱ። ድርጅት ስላልፈለጉ ነዉ? ወይስ ስላልተመቸዎት? ወይስ ድርጅቶች ሁሉ ስላልገጠሙዎት? ቢያንስ መኢአድ፣ በደንብ የሚያዉቁቱ? እረ ደግም አይመስለኝ ዉድ ወንድሜ፣ ጥፋት ካልሆነብኝ።
ወዮን፣ እንኩዋን በተናጠል ተባብረንም አሜከላዉ ቀላል አይደለም። እንደ እናንተ፣ እንደ እናንተ ያለዉ ካለ እስካአሁን በተናጠል እያካሄደ፤ ወያኔ እየሰመረለት ነዋ ትግሉ። ሌላ ምን ፈልጎ። በዉኑም በህልሙም እንዳንተባበር መስሎኝ ጥረቱ። አንድ በሬ ስቦ፤ አንድ ሰዉ አስቦ አልልም ከዝህ ላይ ወንድሜ መች ያጡታል ብዬ። በድጋሜ ይቅርታ፣ እያደረጉ ያለዉን አስተዋፅዖ አይሁንብኝ ማጣጣል - እንተባበር ትግላችን በረካ እንዲ ረብበት እንጂ ለማለት። አይ! ይብቃኝ፤ ስራ አስፍታሁ መስለኝ። ድንገት ወደ እሱም፣ ዓለም ገና እንደሆን ያለችዉ በዘጠኙ። ቀናዉን ልቦና ይስጠን። አሚን! እንበል።
ቸር ይግጠመን!
ከወደዚህ፣ ወደ እኛዉ፣ ዓለም ገና አስር አልሞልታም። በዘጠኙ እንደተቆናጠጥን ነን - ቶሎ መልስ አለመስጠቴ። ኖር ኖር ቢየ ነው የተቀብልኩት የዉድ ወንድሜን ምላሽ። ጤና ይስጥልኝ እያልኩ ነዉ ከወደ እዚህም የተከበሩ አቶ ጌታቸዉ ረዳ። በጣም በጣም ትህትና ለተቸረዉ ምላሽዎ ምስጋናየ ይድረስዎ።
ዉድ መንድም ጌታቸዉ፣ በብዙ ነጥቦች ተግባብተናል። እንደ አሁኑ በፅሁፍ ባናደርገዉም በተለይዩ መጣጥፎችዎ ስንግባባ መኖሩን ቀደም ብየ ያልኩትም ነዉ። ስለዝህም በዘረዘሩዋቸዉ ነጥቦች፣ በጠቃቀሱአቸዉ ሰዎች (ከድ/ር ታየን እና መሃንዲስ ኃሉን ሳይነካ) እና ድርጅቶች እኔም የተለየ ሀሳብ የለኝም። እርስዎ ባሉት ይቁዋጭ - ገልቱን ሲደጋግሙለት ወግ የደረሰዉ ይመስለዋልና።
በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ግን አፅዖት መስጠት እፈልጋለሁ - ባንዳንዶች ላይ የተለያየ ግንዛቤ ባይኖረንም።
1. በወድሜ በጌታቸዉ እንከን አልባ ኢትዮጵያዊነት ምንም ጥርጥር የለም። ዜግነቱን ሁላችንም ሳይሸራረፍ ይዘነዋል - እኩዮቹ፣ እነ መለስ እና የዘር ፖለቲካን የሚያራምዱቱ ሁሉ፣ ለእነሱም የተምበረከኩቱ ሳቀሩ። ፖለቲካዊ አካሄደዎን ለማለት ነዉ የነበረዉ እንጂ ኢትዮጵያዊነትዎን ለማጠቅ አልነበረም - በዜግነት ላይ ማን ቆራጭ አድርጎኝ። ከላይ የተወሰነለዎትን። ከመቀመጫየ ብድግ እያልኩ ይቅርታ፤ ካለው የእዚያ ዓይነት እንድምታ።
2. ለወገኖችዎ እና ለሀገርዎ እያደረጉ ያለዉ አስተዋፅዖ ሚዛን ዉስጥ የገባ ነዉ። ከዚህም ጋር ተያይዞ ብዙ ፈተናዎች እንዳሉበዎት ባይናገሩትም የወያኔን እኩይነት የሚያቅ ሁሉ የሚረዳዉ ነዉ። ወያኔ ንቆ የሚተዎዉ ጉዳይ የለዉም - እንኩዋን ጠላቴ ነዉ፣ ተቀናቃኘ ነዉ የሚለዉን ይቅርና ጠላት የመሰለዉን፣ ተቀናቃኝ የመሰለዉን እና በህልሙም እንኩዋ ሳይቀር ሲጠላዉ/ሲጣላዉ ያየዉን ሁሉ ለመብላት/ከመብላት ወደሁዋላ የማይል መፃጉ ፍጡር ነዉ። ለበቀል የተፈጠረ፤ በበቀል ያደገ፤ ለበቀል የነገሰ፡ እየተበቀለም የሚሞት። እናም አንድዬ መከታ ይሁንዎ ነዉ ማጣፊያየ።
3. "የፊት የፊቱን ..." ስል፣ ዉድ ወንድሜ ጌታቸዉ፣ መኢአድን አስመልክተዉ የከተቡልኝ እንዳለ ሁኖ (ለዚህም ምስጋና በድጋሜ) ፈቃድዎት ሆኖ እንደገና ብመለስበት፣ ትግላችን ያለፍንበትን የትግል ሂደቶች እና በውቅቱ ከምናደርገዉ ትግል ጋር ማገናዘብን ይጠይቃል። ይህ በራሱ ደግሞ ለመጭዉ ምን ሊያስከትል እንድሚችል ትንብርያን እና ለዚያም ከአሁኑ እርምጃችንን ልናስተካክል ይለናል። ትንቢት ይኖረናል። ትንቢት የሌለዉ ትግል ራእይውን ማየት ቀርቶ አያሸታትም። እባብ አዉቆ መርዙን እንደጣለ ይቆጠር። ለዚያዉም ወያኔን ያክል መሰሪ ባላጣ ጋር። ከተቃዋሚዉ ጋር ተቃዋሚ፣ ከደጋፊዉ ጋር ደጋፊ፣ ከብሄርተኛው ጋር ብሄርተኛ፣ ሀገራዊ ከሆኑት ጋር ሀገራዊ (እነስየን፣ ገብሩን፣ አረጋሽን፣ ነጋሶን፣ በየነን፣ መረራን፣ ተኮላን፣ ... ከዚህ አኩዋያ ያዩዋል)ምን አለፋዎት እስስትዋን አስንቆ ከሚለዋወጠው ጋር ነዉ እኮ ትግሉ። እናም ለዚህ እቡይ ፍጡር ስነ-ስራት ብሎ ነገር፤ ኢትዮጵያዊ ጭዋነት ብሎ ነገር ለእኔ እጅ ከመስጠት ያለፈ ትርጉም የለዉም። የመኢአድ ስሌት ለዚህ ነዉ የሚጎረብጠኝም። ወያኔ ሁሉ በእጁ፤ ሁሉ በደጁ። አምስት አመት ሙሉ የተዘጋጀበት። መኢአድ ከእጁም ከደጁም ምንም። ታዲያ ትግል በምን? ወያኔ ማንን ፈርቶ? መለስ ሰላማዊ ታጋዮች ነን ያልችሁ ሁሉ ለምርጫ ካልቀረባችሁ ወዮላችሁ እያለ በሚለፋደድ ፍጡር እኮ ነዉ ምርጫዉ እየተመራ ያለዉ መሰለኝ!። እናም ይህ ሰዉ እንዴት ብሎ ነዉ በካርድ ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ስልጣን መልቀቅ ቀርቶ የሚያጋራዉ!? እነማንን እንደሚፈልግ እያወቅን። መጭዉ ምን እንደሚሆን ቁልጭ ያለ ነዉ - መምሸት መንጋቱን መጠበቅ እሚኖርብን አይደለም። ወያኔ እስከ ግሳንግሱ ነግም ጉልት። በዚህ ሂደት ማንም ምንም አመጣም። አይ! ያለ ወዮለት!። ወይም አዎ! መጭዉም ያዉ ወያኔ ነዉ፤ ስለዚህ የምናገኛትን ካርድ ይዘን እንግባ ፓርላማ ሌላ ጉዳይ። ለዝህ ስሌት ማርከሻውን እየለፈፉ እና በቻሉትም መንገድ እየተገበሩ ያሉ በግለሰብም በድርጅትም (ከእነ ግ 7 ዉጭ) አሉ - ለጊዜዉ ትግላቸዉ ከዐይን አልገባም ይሆናል እንጂ በትግሉ ዉስጥ ዛሬም እንደ ወትሮአቸዉ እተማገዱ ያሉ የእትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መኖራቸዉን ዉድ ወንድሜ ያጡታል የሚል ግምት ከልቤ ተጥዶም አያዉቅ።
4. እና የመጨረሻዉ፣ ብዙም ያልጠብቅሁት። በግሌ ነዉ ይህን ሁሉ እንቅስቃሴ የማደርገው ያሉቱ። ድርጅት ስላልፈለጉ ነዉ? ወይስ ስላልተመቸዎት? ወይስ ድርጅቶች ሁሉ ስላልገጠሙዎት? ቢያንስ መኢአድ፣ በደንብ የሚያዉቁቱ? እረ ደግም አይመስለኝ ዉድ ወንድሜ፣ ጥፋት ካልሆነብኝ።
ወዮን፣ እንኩዋን በተናጠል ተባብረንም አሜከላዉ ቀላል አይደለም። እንደ እናንተ፣ እንደ እናንተ ያለዉ ካለ እስካአሁን በተናጠል እያካሄደ፤ ወያኔ እየሰመረለት ነዋ ትግሉ። ሌላ ምን ፈልጎ። በዉኑም በህልሙም እንዳንተባበር መስሎኝ ጥረቱ። አንድ በሬ ስቦ፤ አንድ ሰዉ አስቦ አልልም ከዝህ ላይ ወንድሜ መች ያጡታል ብዬ። በድጋሜ ይቅርታ፣ እያደረጉ ያለዉን አስተዋፅዖ አይሁንብኝ ማጣጣል - እንተባበር ትግላችን በረካ እንዲ ረብበት እንጂ ለማለት። አይ! ይብቃኝ፤ ስራ አስፍታሁ መስለኝ። ድንገት ወደ እሱም፣ ዓለም ገና እንደሆን ያለችዉ በዘጠኙ። ቀናዉን ልቦና ይስጠን። አሚን! እንበል።
ቸር ይግጠመን!
ይቅርታ - ድጋሜ ከሆነ ይታለፍ። ትንሽ አስቸግሮኝ አልሄድ ብሎ።
From the Editor /Getachew Reda
ለተከበሩ ዉድ ወዳጄ፤
ዉይይታችን በባገራችን ቋንቋ እና ደንብ ማድረጋችን የተሰማኝ ደስታ እየገለጽኩለዎት፤ ባጠቃላይ እርስዎ እንዳሉት ባብዛኛዎቹ ነጥቦች ከተስማማን ለመስማማታችን እና ባንድ የጉዞ መንገድ እየተራመድን ስለሚያመለክት የተቀረዉ ጥቃቅን ነጥብ በእግረመንገዳችን እየተወያየን ወደ አንድ ስምምነት እንደርስበታልን። ያ ደግሞ ሩቅ አይሆንም።
የድርጅት አባል የመሆን አለመሆን ጉዳይ አንስተዉ ስለጤቁኝ ነገር- መልሴም የድርጅት አባል ሆነዉ ወርሃዊ መዋጮ ከሚያደርጉ አንዳንድ አባሎች በላይ በሚዲያዉ በኩል ድርጅቱ መሪዎች ላይ ለሚደርሰዉ የስም ማጥፋት ዘመቻ ድርጅቱ ከመድረሱ በፊት ቀድሜ ማለትም በዋሽንግተን፤ስያትል፤ቺካጎ፤ስቶክሆልም፤ሎስ አንጀለስ፤ቦስተን፤ ካናዳ፤ ለንደን እና በሌሎች ከተሞች ሚርመጠመጡ ወስላቶች የሚሰነዘረዉ አሉባልታ ቀድሜ ስመክትለት ከድርጅት አባልነት በላይ መሆኑን ይወቁልኝ። ይህ ስራ የምሰራዉ ላንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ወስላቶች በሌሎች ቀና ኢትዬጵያዊአን/ት መሪዎች እና ዜጎችም የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲደርስባቸዉ “እዉነት” የተባለዉ ድርጅቴን ይዤ መክቻለሁ ትናንትም ዛሬም ለወደፊቱም። ለዚህ ነዉ አባል መሆን ያልፈለግኩት። የመከላከል የመዉቀስ ነፃነቴ የተጠበቀ ይሆናል ማለት ነዉ።
ኢትዬ-ሚዲያ ወይንም ጸረ ትግሬነት ፕሮፖጋንዳ እንዲሰራጭ የሚያደርግ “ኢካድ ፎረም” (ኢትዬፕያን ካረንት አፈይርስ) ወይንም ኢትዬ-ፎረም- ዳት ኦርግ የተባለዉ የክንፉ አሰፋ ሚዲያ የሲቪጀክ እና ፖለቲካ ድርጀት አባሎች ስለሆኑ ሚዲያዉን ለነሱ ድርጅት እና መሪዎች ብቻ እንዲያገለግል ስለከፈቱት ድርጅታቸዉ የስም ማጥፋት ዘመቻ በሌሎቹ ላይ ከዘመተ (ለነገሩ ቀዳሚ ስም ማጥፋት ዘመቻ የተሰለፉት እንሱ ናቸዉ እንጂ)፤ በተዘመተባቸዉ ክፍሎች ስም ዘልለዉ “ነዉር ነዉ” አትዋሹ” በዉሸት መሪዎች መዝለፍ አይገባም” የማለት ነፃነት የላቸዉም። ምክንያቱም “ድርጅታቸዉን ማጋለጥ ሊሆንባቹ ነዉና”። ሁሉም በዉሸት የተዘፈቁ ስለሆኑ አንዱ ካንዱ አይሻሉም።
ለምሳሌ አንድ “ልጅ ተክሌ”እያለ ራሱን የሚጠራ ካናዳ የሚኖር የዘረኛዉ ድረግጽ የ ኢካድ እና የ ኢትየየፎረም ፓል ቶክ አዘጋጅ ነኝ የሚለዉ ወጣት ባህሪ ቢገነዘቡ፤ ከዉሸት ወደ ዉሸት የሚዘፈቁትን ሁሉ እያደመቀ ራሱንም መጨረሻ ላይ ‘የሻዕቢያ” ባለስልጣናት ለ ኢትየየጵያ በጎ አሳቢነት መስበክ የጀመረበትን ሁኔታ እና በሻዕቢያ በዓል ላይ ተገኝቶ የማረከዉን የሻዕብያ ፍቅር/አንድነት/ሙዚቃ በቪዲዬ ቀድቼ እልጥፍላችሗላሁ በማለት በድረገጹ የሰበከዉን ሰበካ ስንመለክት፤ እንደዚሁም የግንቦት 7 የሕዝብ ግንኙነት መኮንን ነኝ የሚለዉ የ“ማዴቦ” ፕሮፖጋንዳን (ኢካድ ፎረም የለጠፈዉ የቪዲዬ ቃለ መጠይቅ) ስንመዝነዉ- ሰዉዬዉ “ግንቦት 7 እንኳን ከሸዕቢያ ከ ኢሳያስ አፈወርቅ ቀርቶ ከሰይጣንም ጋር ቢሆን መስራት አለበት፤ተገቢም ነዉ.።” የሚሉ ሰዎች “የመኢአድ መሪዎችን እነ ዶ/ር ታየ ወልደሰማያትን አነ ኢንጀኔር ሃይሉሻዉልን” ከሰይጣን በላይ ሰይጣን በመመደብ አብሮ መስራት እንደማይቻል እና ከነሱ ይልቅ ኢሳያስ አፈወርቅ እና የሻ ዕቢያ አምባሲ መኮንኖች ግን “ለ ኢትየየጵያ አሳቢዎች፤በጎ አሳቢዎች እና የዋሆች…” መሆናቸዉን እየሰበኩ የሚያሰራጩትን አስነዋሪ ስራ በጣም የሚያስገርም ነዉ።
ይህ ሆን ተብሎ በጥናት የተደረገ የተቀነባበረ የጠላት ዘመቻ ነዉ ብንል የሚያስወቅሰን አይደለም። ቅንብበሩን በደምብ ስንመለከት ሌላ ቀርቶ አዲስ መጽሃፍ ጻፍኩላችሁ የሚላቸዉ የጋዜጠኛዉ ማስታወሻ ደራሲ “ተስፋየ ገብራአብ” እንኳ ሳይቀር ሃይሉሻዉል “በሚሊዮነር ለመሆነ ከወያኔ ጋር ተመሳጥሮ ሕዝቡን ሽጠዉታል….ከፖለቲካዉ ቢወጡ ይሻል ነበር….” እያለ በዚሁ በኢካድ ፎረም/ኢትዩጵያን ካረንት አፈይርስ ፓልቶክ” ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻዉን በማጧጧፍ ተካሄደዉ ዉሸትፕሮፓጋንዳን ብንመለከት የሚያሳየን ምንን ያመለክታል? ተስፋየገብራአብ “ስለ ሚለዬን ብር እያወራዉ አለዉን የስም ማጥፋት ወራዳ ተግባር መረጃ አቅርብ ብለዉ እንኳ አዘጋጆቹ ሊወጥሩት አልፈቀዱም። ምክንያቱም ዋናዉ ፍላጎታቸዉ በዉሸትም በምንም “ኢትዬጵያዊነትን ለማጎልበት የሚጥሩ ብዙ መካራ እና ስም ማትፋት ዘመቻ የተካሄደባቸዉ እነ ታየን እነ ሃይሉ ሻዉልን ማዳከም ፤ከታክ እንዲፋቁ እና የሰሩትን በከንቱ እንዲቀር የተደረገ ሆን ተብሎ የጠጠና ቅንብር ነዉ።
ስለዚህ እነዚህ የድርጅት አባሎች ስለሆኑ ድርጅታቸዉን መዉቀስ/መሪአቸዉን መቃወም ማስተካከል አይችሉም። ስለዚህም ነዉ እኔ የማንንም ድርጅት አባል ለመሆን የማልፈልገዉ። በጎ ለሰራ ቀና ድርጅት እና መሪ ከ አባልነት በላይ ባለኝ ዘርፍ እና ችሎታ አገልግላለሁ፤ ትንነትም ዛሬም ለወደፊቱም፤፡ ብቻ ኢትዬጵያን ከ ሲ አይ ኤ እና ከዓረብ ቅጥረኞች ይከዉላት እንጂ ልብ ብሎ ለተከታተለ ሰዉ ከበባዉ ባትዬጵያዊነት መሆኑን ላንዳፍታ መጠራጠር የለብንም። አሁን ደግሞ “እሳት” የተባለ የሳተላይት ቲ/ቪ በሌላ ልብስ መጥቻለሁ እያለን ነዉ እና በርዷችሓል እና ላሞቃችሁ ነኝ እያለን አለዉ “እሳት” ደግሞ እንዴት እንደሚያሞቀን እንጠብቀዉ።መከረኛ ዲያስፖራ! ንግገሬን ከመጨረሴ በፊት -ዲያስፖራን ማንሳቴ ላይቀር ይልቁንስ አንድ ጥሩ ፈረንጅ “ዲአስፖራዉን እንደ እኔ ሆኖ የወጠረልኝን ጥያቄ “በዩ ቱብ” ኢመልከቱልኝ። ብርቱካን ብርቱካን የሚለዉን በምላስ የሚጓዘዉን ወስላታን ሁሉ የወጠረዉን ጥያወቄዉን ይሄዉ ። Birtukan Mideksa And My Challenge To The Ethiopian Diaspora (ይሄ ሰዉ እንዴት ወደድኩት መሰለዎ! ለጠየቀዉ ጥያቄ ተግባራዊ እንድታደርጉ/እንድትተባበሩኝ አዳራሹ ዉስጥ የምትገኙ እግዶች እጃችሁን አዉጡ ብሎ “ዓይን ዓይናቸዉን” እያየ ) ሲጠይቃቸዉ ካሜራዉ ሆን ብሎ እጃቸዉን የሚያወጡ እንደሌሉ ወይንም ጥቂት ሰዎች መሆናቸዉ ስላወቀ ነዉ መሰለኝ “ሳያሳየን ደበቃት”። ሰዉየዉ ብርቱካን ብርቱካን ከማለት ሌላ በተግባር አልተሰለፋችሁላትም ነዉ ያላቸዉ።ምላሰኛ ብቻ መሆናችንን አዉቆናል ወደድኩት። እኔም ያለኩት ያንኑ ነበር። “እኛስ?” ስለ ቀና እና ቸር አስተያየትዎ አመሰግናለሁ። አንዳንድ የፊደል ስህተት በኖር ጊዜ ለማብቃቃት በችኮላ የተጻፈ ነዉና ከወዲሁ ይቅርታ ።
ዉድ ወንድሜ ገታቸዉ፣ አሁንም ምስጋናየ ይድረስዎ። የድርጅት አባል መሆን ወይም ባለመሆን ጥያቄ ያነሳሁት፣ በግሌ ነዉ እምንቀሳቀሰዉ ስላሉኝ እና ትንሽ ከግምቴ ዉጭ በመሆኑ ነበር። እናም እግረመንገዴን ወያኔን እና ግሳንግሱን (ልጅ፣ ደጃዝማች፣ ወይም ፊታውራሪ ተክሌን እና የመሳሰሉትን ሁሉ እንደ ማለት) ለመመከት እና ብሎም በማያዳግም ሁኔታ ከሀገራችን ምድረ-ገፅ እንዳልነበሩ ለማድረግ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በድርጅት አብረዉ መቆምን ግድ የሚል መሆኑን ለመግለፅ እንጅ - ይቅርታ ያጡታል ብዬ አይደለም።
እንዳሉት ግን፣ የድርጅት አባል ተኩኖ ድርጅቱን፣ አባላቱን፣ ሚስጥሩን፣ ንብረቱን፣ ... ከጥቃት የማይከላከል አባልነቱ ድርጅት አለኝ፤ አንድ ቀን ድርጅቱ ቢልለት ከጥቅሙ ተካፋይ ለመሆን ብቻ ነዉ። ሌላ ምን ይባላል። ድርጅቱም ሃሳቦችን ከላይ ወደ ታች፣ ከታች ወደ ላይ እና እንዲሁም አግድሞሽ (እንደ ሁኔታዉ ፈቃጅነት)ሁሉ የማያንሸራሽር ከሆነ ድርጅቱ አባል ሳይሆን የሚፈልገዉ ባሮች የሚሆኑት ነዉ ማለት ነዉ። እናም ሃሳብን በነፃ ማሸራሸር ከእሚያቅብ ድርጅት ዉስጥ ማንኛችንም ብንሆን ስማችንን ላንከትብ ልቦናችን ሊመራን ይገባል ሌላዉ ደግሞ። (መስጠት እና መቀበል የራሱ ደንቦች ያሉት መሆኑ እንዳለ ሆኖ)። በእንዲህ አይነቱ ሁኔታ፣ ሀገራዊ እና ወገናዊ ግዴታን በግለ-ሰብነትም ቢሆን ሲወጡ መቆየት ሌላዉ እና ጥሩው መንገድ ነዉ - ወንድሜ እየፈፀሙ እንዳለዉ እንደ ማለት።
በተርፈ፣ ለፊደላት ግድፈት አይጨነቁ - ዋናዉ ቁም ነገሩን ላግኘው እንጂ።
ማለፊያ ዉይይት አደርግን መቸም። ይልመድብን። በድጋሜ ያክብሮት ምስጋናዬ እስከ ወዲያኛዉ።
ተኩዋለ ነኝ።
Post a Comment