Saturday, August 15, 2026

የአሉላ ሰለሞን "የውሻ ፊሽካ" (dog whistle) በአማራ ሕዝብ ላይ ያስተጋባው ዛቻ እና የሞት ቲኬት አስተናጋጅነት ክፈል 1 ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/13/22


የአሉላ ሰለሞን "የውሻ ፊሽካ" (dog whistle) በአማራ ሕዝብ ላይ ያስተጋባው ዛቻ እና የሞት ቲኬት አስተናጋጅነት

ክፈል 1

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/13/22

አሉላ ሰለሞን በአምሐራ ሕዝብ ላይ ከነፈሩን የነክሰበት የዛቻ ንግግሩ

ትግሉን እና ተውናዮቹን  ለማስተካከል የተቻልንን ያህል ብናስተምርም ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ መሻሻል ባለማሳየቱ ትርፉ ድካም እየሆነ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ፋኖ የተባለውም የባሰ መንደርተኛ ሆኖ የሕዝቡን መከራ እራዘመ በማየቴ “ከማስተማርና ከመተቸት” ለመቆጠብ ስፈልግ አንዳንድ ነገሮች ፍጥጥ ያሉ ውሸቶችና ድርቅና የሞላበት ክሕደት የሚጫወቱ የጥላቻ ተዋናያን በኩራት ሲመጡ ማየት አላስችል ይለኝ እና እንደገና ወደ ክርከሩ እመለሳለሁ። ለዚህም ሰሞኑን የሆነውን መንሻየ ነው፡

መጀመሪያ አሜሪካ ውስጥ ያሉም ይሁኑ በሌሎች ሃገሮች የሚኖሩ መላው ኢትዮጵያዊያን የሕግ ባለሞያዎች የወያኔዎቹ ባለውለታ “አሉላ ሰለሞንም” ይሁን በሕዝብ ላይ ብዙ ግፍ የፈጸሙ የወያኔ ባለሥልጣናት በምቾት ዓለም በኩራትና በድሎት ሲኖሩ የኛዎቹ የሕግ ምሑራን እነዚህን ግፈኞች በሕግ ፊት ባለማቆማቸው የሕግ መሁራኖቻችን “የቁም ሞታቸው እንደሞቱ” እቆጥረዋለሁ።

ለዚህም አሉላ ሰለሞን የተባለው ግማሽ ቅማንት፤ ግማሽ ትግሬ ነኝ የሚል (በራሱ ፌስቡክ እንደገለጸው) ካሁን በፊት የሩዋንዳዎቹ የሁቱ አሰርቱ ቃላቶች የሚመሳሰሉትን “በአማራ” እና በመላው “የኢትዮጵያ ሕዝብ” ላይ ያወጀው የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጆች ሰሞኑን ባንድ ሚዲያ ቀርቦ “እነዚያ ያስተላለፍኩዋቸው ቅስቀሳዎች በመቀስቀሴ እኮራለሁ” በማለት በኩራት እራሱን ሲኮፍት ሰምቸው፤ ለኩራቱና ለፉለላው የቁም ሙት የሞቱትን የሕግ ምሁራኖቻችን ደካማነት በማይቱ ቢሆንም ፤ እኛ የዚህን የጥላቻ ሰካራም አጉል መኩራራቱን ለማጋለጥ ለታሪክ መዝገብ ምንነቱን እያስመዘገብን እናልፋለን። ወደ ትንተና መመለሴም መነሻየ ይህ ነው። በክፍል ሁለት የኮራባቸው አዋጆቹ በሕግ ፊት ምን እንደሚመስሉ እመለስበታለሁ ፤ ለዛሬ ክፍል 1 ይህንን እንመልከት።

ቪዲዮው ላይ የምታደምጡት የአሉላ ሰለሞን “የ100 አመት” የአማራ ሕዝብ (ነፍጠኛ) የጨፍጫፊነት እና  የጨቋኝነት ታሪክ የፈጠራ ውሸትና ቅስቀሳ ቢሆንም ፤ በሕግ ትንታኔ የፈጠራው ትርክት The "Lie as a Catalyst"፡- አነቃቂ ኃይል (catalyst) ሆኖ ትርክቶቹ ራሳቸው በሂደቱ ውስጥ ሳይለወጡ ወይም ሳይሟጠጡ፣ በቡድኖች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን፣ መድልዎን (ለይቶ) ማን እንደሆነ በመለየት ትርከቱ አነቃቂ ሞተር ሆኖ ጥቃቶችን ያፋጥናሉ ወይንም ያስነሳሉ።

 እንደ አሉላ ሰለሞን የመሳሰሉ የጥላቻ እና የውሸት ትርክት ሰባኪዎች በአማራ ሕዝብ ላይ ጥቃት እንዲደርስ "እንደ ማነሳሻ የሚያገለግል The "Lie as a Catalyst"፡- ውሸት " የሚጠቀሙበት ቃል የአማራ ሕዝብ “በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ” 100 አመት ከፍተኛ ጭፍጨፋ/ግፍ/ጭቆና እንደፈጸመ እና ግፍ የተፈጸምባቸው ነገዶችም በአማራን ሕዝብ ላይ ለመበቀል ለጥቃት ጉጉት ከንፈራቸው እየነከሱ እንዳሉ ይናገራል።

 በቪዲዮው ላይ የምናደምጠው የሰልሞን አሉላም ሆነ የባልደረባው (ማሃይመዋ ሴት) የፈጠራ ትረካዎች  እየነገሩን ያሉት “በታሪክ የ100 አመት ጭፍጨፋ በሌሎች ነገዶች እና በእኛ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጸማችሁብን” ቅሰቀሳ የሚነግረን ነገር “ የአትሮሶሲቲ ፕሮፓጋንዳ”  ወይም "የሐሰት ባንዲራ ማውለብለብ” false flag narratives" ትረካዎች እየተባሉ የሚጠሩትን ነው እያሰራጨ ያለው። የሕግ መጻሕፍት (እንዳነበብኩት) የሚነግሩን አመላካቺነታቸው “The "Lie as a Catalyst"፡- has frequently been used as a psychological trigger to justify preemptive violence or retaliation in real-world conflicts.” ይህ ማለይ የእነ አሉላ ሰለሞን ፤ የእነ ኦነጎች (አብያ አሕመድ ንግግር ጨመሮ) የእነ ወያኔዎች ንግግር እና ማኒፌስቶ በእውነተኛ ግጭቶች ውስጥ እንዲህ ያሉ የውሸት ትረካዎች እና አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር ወይም አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደ ስነ-ልቦናዊ ማነሳሻነት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውሏል፡ ይላሉ። የ አሉላ የፈጠራ የ100 አመት ትርክት የሚያሳየን በሕግ ትንተና ይህንን ያመላክታል።

ነፍጠኛ (Coded Language) አሉላ ሰለሞን እና እሱ የሚያመልከው የወያኔ ማኒስቶፌስቶ የአማራን ሕዝብ በCoded Language በምስጢራዊ ቋንቋ ነፍጠኛ ሲሉ ይጠሩታል።ይህ "የውሻ ፊሽካ" (dog whistle) ይባላል።

ይህንንም ጥቃት ለመሰንዘር ወይም አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜ እየጠበቅንላችሁ እንጂ የመቶ አመት ጥቃት በአጸፋዊ እርምጃ ለመመለስ ዝግጁ ነን። እያለ ነው “በራሱ አንደበት”። አሉላ እና መሰሎቹ በአማራ ሕዝብ ላይ ከንፍሩን እየነከሰ እንዳለ ሳይሸሽግ ለዓለም ሲያውጅ  በሕግ ትንታኔ ሕዝብንና ከትግሬዎች ጋር በተጋቡ አምሐራ ባለተዳሮችን ከንፈሩን በመምጠጥ/በመንከስ ለጥቃትና አጸፋዊ እርምጃ እያነሳሳ እንዳለ ሳይሰጋ ያውም እንደ ኩራት እንድሚቆጥረው ይናገራል።

ነፈጠኞች ቀናችሁን ጠብቁ እያለ ከንፈሩን ለጥቃት ዘግጅት መጠበቁ የአምሐራ ሕዝብን (ነፈጠኖች) እንደሚጠላ እና ወቅት እየጠበቀላቸው እንድሆነ ሲገለጽ የጥላቻ ንግግር የዛቻና መስፈርቶች እና ትርጉም እየነገረን ነው፡- አሉላ ሰለሞን አመች ወቅት እየጠበቀና መላውን

የአማራ ሕዝብ ለማጥቃት ከንፈሩን እየነከሰ መሆኑን እና ወታችሁን ጠብቁ እያለ ያለው አብዛኛዎቹ የዛቻ ንግግሮቹ የህግ ማዕቀፎች ውስጥ የተጠቃለሉ እና የጥላቻ ንግግር ነው። ሩዋንዳ ዕልቂት ያፋጠነው ከነፍሩን ሲመጥ የነበረ ሕዝብ ወቅት ጠብቆ “የዛቻ ንግግሩን ወደ ግብር ለወጠው”።

አሉላ ሰለሞን በተለያዩ ወቅቶች ፣በሃገር፤ በሰንደቅ ዓላማ ፤ በነገድ በሃይማኖት፣ ልጆች ወልደው በሰላም ሲኖሩ በነበሩት ባለትዳሮች (በጋብቻ ላይ) የሚያጠቁ ንግግሮች ሰብአዊ ክብርን የሚነኩ (ኮዲንግ) ንግግሮችን ሲናገር ሰምተናል።

በአምሐራ ሕዝብ ላይ በሐሰት የተረከው የ100 አመት ጨፍጫፊነት/ግፍ ፈጻሚነት እና ነፍጠኛ የሚሉ ሁለቱ  የአሉላ ንግግሮቹ በሕግ ትንተና የጥቃት አፋጣኝ ቤንዚኖች  (Catalyst) ናቸው። የአቀጣጣይ ቤንዚኖቹ ውጤት እንዴት እንደሚሰራ እንመልከት

የሀሰት ትረካዎች ሚና፡ ጉዳት ወይም ጭቆና እንደደረሰ የሚገልጹ ሀሰተኛ ክሶችን መፍጠር ወይም እንደ መሳሪያ መጠቀም፤ በተከሰሰው ቡድን ላይ ጥልቅ ጥላቻን፣ ከራስ ቡድን ውጭ ላሉት ላይ ጠላትነትን እና ስር የሰደደ አድልዎትን ለማራመድ እንደ ሰበብ ሊያገለግል ይችላል። ይላል ያንበብኩት የሕግ አተናተን። ከዚህ የተሻለ ካለም የሕግ መሁራን መልስ እጠብቃለሁ። በሌላ አገላለጽ The "Lie as a Catalyst": Faking narratives of severe repression (often referred to historically as "atrocity propaganda" or false flag narratives) has frequently been used as a psychological trigger to justify preemptive violence or retaliation in real-world conflicts. (እንደ ማነሳሻ የሚያገለግል ውሸት"፡- ከፍተኛ ጭቆና እንደተፈጸመ የሚያሳዩ የፈጠራ ትረካዎችን (በታሪክ "የጭካኔ ድርጊት ፕሮፓጋንዳ" ወይም "የሐሰት ባንዲራ" ትረካዎች እየተባሉ የሚጠሩትን) ማሰራጨት፣ በእውነተኛ ግጭቶች ውስጥ አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር ወይም አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደ ስነ-ልቦናዊ ማነሳሻነት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውሏል።) የላሉ የጥላቻ ትርጉም ተንታኞች።

ስውር ቋንቋን በመጠቀም (ኮዲንግ/ ነፍጠኛ/የሚል ቅጽል ስም መስጠትን) የተወሰነ ቡድንን የሚያነጣጥር «የውሻ ፉጮት» "ዶግ ዊስል" (dog whistle) ምን ይመስላል? ጠቀሚታው "ተዘዋዋሪ የጥላቻ ንግግር" (implicit hate speech) ለማስተላለፍ የሚረዳ ስልት ነው።

Hidden Meaning: A targeted group hears the secret, biased code- ተናጋሪው የሚጠቀምባቸው ቃላቶች (ነፍጠኛ) ለሰፊው ሕዝብ ምንም ጉዳት የሌላቸው የሚመስሉ ተራ ቃላት ቢመስሉም ቃላቶቹ ለታለመው ግብ የተለየ እና ስውር የሆነ ነጣይ አዘል መልእክት ለማስተላለፍ የመጠቀም ስልት ነው።

ሆኖም የቃላቱ አጠቃቀም ስልት Hidden Meaning: ሕቡእ (ሽፋን) ያለው ድምጸት ሰላለው ተራ ሰሚው ቀለል አድርጎ ሊተረጉመው ቢችልም (አልፎም የሕዝቡን ሕጋዊ መጥሪያ ስም ተረስቶ ከጥላቻ አራጋቢዎች የሰማውን ኮድ “ነፍጥኛ” የሚለው ስም ዘላቂ /ቅቡል/ ስም እንደሆነ አድርጎ ሊጠቀመው ይችላል)፤ በድብቅ ቃል የተጠራው የአምሐራ ሕዝብ/ነፈጠኛ) የሚለው ቃል ግን (The targeted group hears the secret, biased code) ግን ትርጉሙ ምን ለማለት እንደተፈለገ የተሰነዘረበት የጥላቻ ቃል እና መስጢር ለምን ግብ ሊውል  እንደተፈለገ ይገባዋል።

ባጨሩ

Ordinary Words:

Speakers/hate groups use everyday terms that do not sound bad on their own.

ተራ ቃላት፡

(የጥላቻ ቀስቃሽ ተናጋሪዎች የሚጠቀኑባቸው ቃላቶች በራሳቸው መጥፎ ስሜት የማይፈጥሩ የሚመስሉ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚዘወተሩ ቃላትን ይጠቀማሉ።) ለምሳሌ ነፍጠኛ የሚለው ቃል በዕለት ተዕለት  የሚዘወተር ቃል ቢሆንም ክ1981 (1993 በፈረንጅ ዘመን) ግን ምን ትርጉም እንዳለው እያደመጥን ነው።

Deniability: The speaker can claim they meant something else if people get upset.  ሰዎች ከተበሳጩ፣ የተጠቀመበት ቃል ሁለት ትርጉም ሊኖሮው ሰለሚችል ተናጋሪው እንዲህ ማለት አርበኛነትን የሚገልጽ ቃል ነው ወይንም እንዲህ ለማለት የፈለግኩት ሌላ ነገር ለማለት እንደነበር ነው ብለው ክሕደት ውስጥ ይገባሉ።ለዚህ ነው ሁለት ትርጉም ያለው ቃል መረጠው ዘረኞች ጥላቻችወን ለማስተላለፍ የሚጠቀሙበት። አሉላ ሰለሞን ግን ካጠቃቀሙ ሊያመልጥ አይችልም (ከንፈር እየመጠጠና እና እየነከሰ የምሐራን ሕዝብ ለመበቀል ወቅት እየጠበቀ እንደሆን ነው ከአራት አመት በፊት የነገረን)።

ይህ የሰሞኑ የ አሉላ ሰለሞን አላልኩም ክሕደት ወይንም እኮራበታለሁ አባባል፤ በእርሱ ብቻ አለተጀመረም፡ ለምሳሌ የሑቱ 10ቱ ቃላት ተብሎ የሚታወቀው የጥላቻ ቅሰቀሳ አዋጅ ያረቀቀው የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜ በተመሳሳይ በወደጆቹ ሚዲያ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ሲደረግበት ሙልጭ አድርጎ በመካድ የተጻፉት አዋጆች እያጣመመ “ሰዎች በመሰላቸው” ሊያቀርቡት ችለው ይሆናል አንድም ማስረጃ በጽሑፌ ውስጥ ቱትሲዎቹ እንደሚሉት አላሳፈርኩም” እያለ እንደ አሉላ ሰለሞን ሲክድ ሰምተነዋል። አሉላ እና የሁቱ ሩዋንዳው ሐስን በስምና በአገር የሌላ አገር ተወላጆች መሆናቸውን ካልሆነ በስተቀር “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” እና “የሩዋንዳው ሐሰን ንገዜ” የባህሪ ተመሳሳይነት ይገርማል።

ፍርድ ቤቱ ውስጥም ሲጠየቅ እንደ አሉላ እያጭበረበረ ሲመልስና ጣልቃ እየገባ ሄግ ፍርድቤቱ ሲረብሽ “የመሃል ዳኛዋ” (ፈረንጅ ነች) << አርፈህ ተቀመጥ ካልሆነ አስወጣሃለሁ!!>> ስትለው ነበር። ውጭ አገር የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን የሕግ ምሁራን እና በየ ኤምባሲው የሚርመጠመጠው የኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብና የሕግ ባለሞያዎች እንዲህ ያለች ዳኛ ዘንድ አሉላ ሰለሞን እንዲቀርብ ማድረግ ሳይችሉ “መቅረታቸው” ሁሌም ይገርመኛል።  

ለዚህም ነው ሰሞኑን፤ በተናገርኩት እኮራለሁ! ከሳሾቼ የት አሉ? ይምጡና ይክሰሱኛ! ማንም ፍርድ ቤት ቢያቀርበኝ ደስታውን አልችለውም\ ሲል በጥላቻ ንግግሩ ሲኩራራ መስማት ያስታወሰኝ ነገር ወያኔው ብስራት አማረ ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ  የአማራ ጥላቻውን የገለጸበትን መጽሐፍ ለማስመረቅ ሄዶ በነበረበት ወቅት ፤ «ወደ አሜሪካ ከተመለሰ ጫካ ውስጥ 17 አመት አማራ ላይ የፈጸመው ግፍ እና መሰል ወንጀሎች አስመለከተን ወደ ሕግ እናቀርበዋለን”» ብለው በዙ ሕዝብ ደስ ብሎት እነ ጠበቃ አበበ ገላው እና በርካቶች  ሲያጋግሉት ቆይተው፤ ብስራት አማረ ወደ ‘ኦሃዮ’ አሜሪካ ሲመለስ ‘ገዛ ተጋሩ” ተብሎ ሲጠራ በነበረው የጥላቻ ሚዲያ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ሰለ ጉዳዩ ሲያብራራ ፤ “እነዚህ ፍካሪዎች” የት አሉ?  እነሆ አሁን ተመልሻለሁ ለምን ታዲያ አይከሱኝም? እያለ ሲዘባበት የሰማሁትን ነው አሁን አሉላ ሰለሞን “ተዲ አዋሳ” በተባለ ሚዲያ ቀርቦ “የት አሉ ታዲያ ለመን አይከሱኝም” ሲል በተናገርኩት እኮራለሁ እያለ ሲኩራራ መስማት የኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብና የሕግ ባለሞያዎች በቁም መሞታቸውን ማሳያ ነው። ክፍል የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ 10ቱ ቃላት ከእነ ትርጉማቸው በክፍል 2 በዝርዝር አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 

No comments: