Sunday, November 30, 2025

ድሮ “የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” መሪዎች የነበሩት የእነ ዶ/ር አረጋዊ በርሐ እና ኢንጂነር ግደይ ዘርአጽዮን ዕድል ያላገኘው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ 11/30/25 ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

 

ድሮ “የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” መሪዎች የነበሩት የእነ ዶ/ር አረጋዊ በርሐ እና ኢንጂነር ግደይ ዘርአጽዮን ዕድል ያላገኘው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ

11/30/25

ታቸው ረዳ

Ethiopian Semay



አዲስ ክስተት ሰምተናል

ድሮየህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይመሪዎች የነበሩት የእነ / አረጋዊ በርሐ እና ኢንጂነር ግደይ ዘርአጽዮን ዕድል ያላገኘው በጎጃሙ የፋሺስቱ ክንፍ ላለመገደል ለወያኔ መሰዋት ያደሩ እና ከሥራው አባርሮ እስር ቤት አስገብቶ ደቦ ላሰቃየውበለውጡ ወቅትየተፈታው ጫካ ገብቶ ፋኖን ያደራጀ ፤ ብዙ የታገለ ፤ ከወያኔ ከቶ አላብርም ብኢትዮጵያዊከቡር ምስዋዕት መሆኑን እና ከጅምሩ ከጎጃም “የፋሺስቱ ክንፍ” ጋር ልዩነት እንደነበረው ጊዜ ሲያስረዳ ነበረው ጸረ ወያኔው ኢትዮጵያዊው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በተከሰተው ልዩነት ተገፍቶ ወደ አብይ ሕመድ ሥርዓት ሸሽቶ ገባ (የሚል ወበሚከተለውሰሞን እንመለከታለን።

ልፍሰፍሱ ማሃይሙ የሸዋው መከታው ማሞም ለወያኔ ካደሩት የፋሺስት ከንፎች ጋር በመወገኑ ክዶታል (ያንን ከመከታው ቃለ መጠይቅ ከወር በፊት አድመጠናል)

አሁን ያለው ጥያቄ እሰከንድርም ወደ ፋሺስቶቹ ክንፍ መሸብረኩን ወይንም አለመሸብረኩን መረጃ ካላችሁ ሃሳብ ስጡኝ።

ጌታቸው ረዳ -  Ethiopian Semay

Friday, November 28, 2025

የኢትዮጵያዊው እስከንድር ነጋ ቃለ መጠይቅ ኢትዮጵያ ጠሊታው የአምሐራ ብሔርተኛው ፋሺስት ቡድንን ኩፉኛ አስቆጥቶቷል ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/28/2025

 

የኢትዮጵያዊው እስከንድር ነጋ ቃለ መጠይቅ ኢትዮጵያ ጠሊታው የአምሐራ ብሔርተኛው ፋሺስት ቡድንን ኩፉኛ አስቆጥቶቷል

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/28/2025

በፎቶግራፉ ላይ የሚታዩት ሁለት የፍኖ መሪዎች የአምሐራ ተወላጆች የኢትዮጵያ ቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑ «ጸረ አምሐራ ጠላቶች ወያኔና ኦንግ ያረቀቁት በሥራ ላይ ያለው አፓርታይዳዊ ሕገ መንግሥት አንቀበልም ብለው ያኮሩን አረበኞቻችን «እስክንድር ነጋ እና ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ» ናቸው።

ሰላም ብያለሁ ፡ ወደ ርዕሳችን ልግባ

 ፋኖ ውስጥ የተሰገሰገው ይህ የተቆጣ ብሔረተኛ ፋሺስታዊው ቡድን ማንነቱን በተደጋጋሚ ሳይደባብቅ ነግሮናል። ይህ ቡድን የአምሐራን ጥቃት አስቆማለሁ በሚል ማታለያ ገብቶ ለአምሐራ ጥቃት ቀንደኛ ተጠያቂዎች የሆኑት ወያኔዎች እና እና የሻዕቢያ መሪዎች ከነ ተከታይ ሕዝባቸው ለማጥቃት ከሚመጣው ማንኛውንም አጥቂ ለመከላከል እነሱ ከመሞታቸው በፊት የአምሐራን ሕዝብ ለነሱ ሲል መስዋዕት እየከፈለ “ሞትና ውድመት” እየተጎነጨ ሕልውናው እንዲያከትም እናደረገዋለን ወደ እሚል ግልጽ የጸረ አማራ ሕዝብ ቡድን ተቀጣሪዎች እንደሆኑ ወጁት አዋጅ ወደ ሕዝብ ጀሮ ከተዳረሰ ሰንብቷል።

ከዚህስ ወዲያ ወዴት ነን? ብሎ የተቃወማቸው የራሳቸው ተራ ታጣቂ ሲያምጽና ሲጠይቃቸውም አልሰማሁም።

 ለጸረ አምሐራ ቡድኖች ባርያ መሆን ብቻ ሳይሆን የአምሐራን ማሕበረሰብ የዘር ጥቃት ማስፈጸሚያ የሆነውን የወያነ *አፓርታይዳዊ* ሕገመንግሥት በብዙ የፋሺስት ነገዶች ሰለተደገፈ እኛም ከፋሽስቶቹ ጋር በመወገን *አፓርታይዳዊ* የነገድ ሕገመንግሥት እንዲቀጥል እንታገላልን ብለዋል (ሁለተኛ ውርደት)።

  እስክንድር ከሁለት ሦስት ሳምንት በፊት ከውጭ አገር ሚዲያ በሰጠው የመታገያ አቅጣጫ ማስፈንጠሪያው የአምሐራ ሕልውና ሲሆን ማጣቀሻው ግን ኢትዮጰያዊነት ፤መሆኑን በመግለጹ ምክንያት ፤ ፋኖ ውስጥ የተሰገሰጉ «የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ሰለባቸው ከብሄር ፖለቲካ ውጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካ የማይታሰብ ነው የሚሉ ጨለምተኞችና በአፍቅሮ ወያኔ ጭንቅላታቸው የተሰለቡ ግለሰቦች እስክንድር በሰጠው ቃል መጠይቅ ውሃ የማይጨብጥ ትችት አቅርበዋል» (አበበ ካሳሁን)፤

ይህ ደግሞ  የወያኔ ፖለቲካ እንቀበላለን የሚለው ኢትዮያ ጠሊታው የአምሐራ ፋሺስቱ ቡድን፡ ኢትዮጵያዊው እስክንድር ነጋን አምሐራ ሳይሆን “ኢትዮፒያኒስት ነው” በማለት (እኛንም ጭምር ሲጠሩን እንደዚያ ነው የሚጠሩን) ሲንጨረጨሩ በየሚዲያው ሰምተናቸዋል።

“አንተ ብሔርተኛ ነህ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦለት  « “ብሔርተኛ አይደለሁም” ፡ “በአምሐራ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው የዘር ማጥፋት ህልቀት ለማስቆም ወደ ጫካ የገባሁ ኢትዮጵያዊ  ነኝ» ብሎ በመመለ; 

“የአምሐራ ፋሺስቶች” እስክንድር ነጋን «አምሐራ አለመሆኑን ይኸው ነግሮናል። እሱ ኢትዮጵያዊ እንጂ አምሐራዊ አይደለም  ስንል አልሰማም አላችሁ። አሁንስ ኢትዮጵያዊ ትግል ለማራመድ እንደወጣ አሁን ግልጽ ይሁንላችሁ!!» ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ‹የለመዱትን የብልግና ስድባቸውን ሲያዘንቡበት አድምጥኩ»።

ኢትዮጵያዊ  ነኝ በማለቱ የታወቁ የፋኖ መሪዎችና ሚዲያዎቻቸው እና ውጭ አገር የሚኖሩ የ“ቲክ-ቶክ” (የአየር ሞገድ ጠጅ ቤት) ሰካራሞችን አላስደሰተም።

 በፋኖ ስም ጭምብል ያጠለቁ የወያኔ እና ሻዕቢያ ተቀጣሪ የፋኖ ታጣቂ መሪዎች ብቻ ሳይሆን ያስቆጣ፤ ወያነ 27 አመት በየትምሕርት ተቋማትና ማሕበራት ሰለ “ብሔርተኛነት መሆን” እየቀጠቀጠ ባሕሪያቸው ለውጦ የቀረጻቸው ወደ ውጭ ሃገር የተሰደዱ ሃያ አራት ሰዓት ቀንና ማታ የአየር ሞገድ ጠጅ ብቶች ተጠዶ ዘረኝነትን ሲያሰራጭና ሲጋት የሚወል የአምሐራ ወጣትም (7 ትውልድ የደም ጥራት ጠያቂዎቹ እነ አቶ ተክሌ የሻው እና በኢሳያስ አፈወርቅ “ፍቅር ልቡ የነደደው” ማሃይሙ “ኢንጂነር” ይልቃል ጌትነት የመሳሰሉ ነጭ ጠጉር ያበቀሉት ጭምር ሳይቀሩ) እስክንድርን ‘ኢትዮፒያኒስት” እያሉ የሰው ልጅ ገዳይ ‘’ኩፍኝ በሽታ’’ የሆነው «ጠባብ ብሔርተኝነት» እያሰራጩ እያደመጥናቸው ነው።

ባልጠበቅነው ክስተት ዘረኝነት ወደ  “አምሐራ ወጣት” ሕሊና ተሸጋግሮ እርስበርስ “ኢትዮፒያኒስት ፤ ምስራቅ ጎጃሜ ፤ ምዕራብ ጎጃሜ ፤ ወሎየ ሽዌጎንደሬ ፤ ጎጃሜ ታች ጋይነቴ....ወዘተ  ወዘተ.. በሚል እየተጋደሉ እነሆ ኢትዮጵያዊነትን “በማውገዝ” እስክንድርን “ኢትዮፒያኒስት” የሚል ቅጽል መስጠት የሚያሳየን ጠ ድምፅ ነፍጥኛ ሲባሉ የነበሩበትን የሕልና ቁስል ዛሬ ያንን በግልባጭ “ኢትዮጵያዊውን” እስክንድር ነጋን እና እኛን “ኢትዮፒያኒስት” የሚል መጠሪያ (ኮድ) ሰጥተውናል። ዕድሜ መስተዋቱ!!!! የሚባለውም ለዚህ ነው።

እስክንድር ነጋ፤ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ትግል ሲያካሂድም ሆነ ጫካ ውሰጥ ገብቶም ብዕርና ፖለቲካዊ ትምሕርት ከማንገት ውጭ  «ጀርባው ላይ ብረት አንግቶ አይቸው አላውቅም»። የእስክንድር መሰረተ ድንጋይ (ባሕሪ) የሰውን ልጅ ላለመግደል የሚጠነቀቅ፤ እጅግ ትሁት፤በሙሉነት መተማመን (ኮንፊድንስ) የሚያሳይ፤ ተጻባኢዎቹን በጸያፍ ቃል አጸፋ ከመመለስ የሚጠነቀቅ; ብርቱ “ሞራሊስት” ነው። ይህ ደግሞ በተግባር አሳይቷል። 

በእስክንድር ዙርያ ብዙ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተደርጎበታል፤ ከተማ ውሰጥም  ፤ ጫካ ውስጥም የመግደል ሙከራ በሥርዓቶቹ እና በፋሺስት አክራሪ የፋኖ መሪዎች የግድያ ዛቻ ደርሶበት ታዝበናል። የእስክንድር ራዕይ የፋሺስት ፋኖ መሪዎቹም ሆኖ አከራሪ ደጋፊዎቻቸው  እስከንድርን ራዕይ አይቀበሉም፡ የገቡበት ፖለቲካዊ ረቂቀነትንም አላውቁበትም (ሰላላውቁበትና በራስ መተማመን ሰለጎደለባቸው የወያኔ እና ሻዕቢያ አቧራ ወልዋይ ሆነው አረፉት)

በዙዎቹ እየተነበረከኩ ለጠላት እየሰገዱ በየወቅቱ ልሳናቸው ሲለዋውጡ እስክንድር ከተማም ሆነ ጫካ ለሚቀርብለት ቃለ መጠቅይ ልሳኑን ለውጦ አያውቅም። ለምሳሌ ከሁለት አመት በፊት እስክንድር ለካናዳዊው ጋዜጠኛለጀፍ ፒርስ› የሰጠው ቃለ መጠይቅ ምን ነበር ያለው? አምሐራ ብለን የተነሳነው “ኢትዮጵያዊነታችንን ለመጣል ሳይሆን”

<< ኛ የብሄር ስም እና ማንነታችን ያገኘነው የዘር ማጥፋት ሰለባ ከሆኑሰዎች ነው። ሰለሆነም የእኛ ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ የዘር ማጥፋት መከላከል ነው>> Sep 8, 2023 ከጄፍ ፒርስ ቃለ መጠይቅ። ይላል እስክንድር። ግልጽ ነው?

አንዳንድ ይፋኖ ፋሺስት መሪዎች ግን (እንደ ዘመነ ካሴ የሚባል ልብ ወለደኛ) ያንን ራዕይ በመጣስ ፤«እኛ የመንታገለው ለሥልጣን ነው» ፤ “መነሻችንም መዳረሻችን አማራ ሆኖ 4 ኪሎ ለአምሐራ ሰጥተን የተቀረው ኢትዮጵያ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያኖቹ እንሰጣለን” ይላል።

ምክንያቱንም ሲሰጥ ጨካኝ ሰው መሆኑን እና ጀግንነቱነም በዕትብት የወረሰው መሆኑን ይገልጻል፡ እንዲህ ሲል፡

«እኔ ሚሊዮን ቢከመርብኝ  ዝሆን እና ጨካኝ ነኝ» ፣ «አሽናፊነትን ከእና ማህጸን ነው ያገኘሁት» ፣ «እኔ የነጋሾች የቀዳሾች የነጋሾችና አንጋሾች ዘር ነኝ» (ይህችኛዋ ከወያኔ ዘፋኞ የቀዳት ፋሺስታዊ ስንኝ ነች) ይላል የፋሺስት ባሕሪውን ለአምሐራ ሕልውና ሳይሆን ለሥልጣን እንደሚታገል እና 4 ኪሎም ለራሱ ወስዶ የተቀረቺው ኢትዮያዊያን (ለኛ እና ለእስክንድር ነጋ) በገመድ እየለካ ለማከፋፈል እንደሆነ ፣ ወደ ጫካ ገብቶም ሕዝቡ እንደጠበቀው ሳይሆን ፤ በሥሩ በዙ ሺሕ ታጣቂ ያስከተለ ወደ ድርጀቱ ሥር ያልገቡለት የጎጃም ታጣቂዎችንም እያሳደደ በመግደልና በግድ እንዲቀላቀሉት በማስገደድ የሚያሸብር ተራ ሽፋታ መሆኑን በተግባርና በአነጋገሩ ሲፈጽመው አይተናል።

“የዘር ማጥፋት መከላከል የሆነውን ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ” እስክንድር ሲነግረን፤ ዘመነ እና በሥሩ ያሉ አሽከሮቹ ግን «የነጋሽ እና የአንጋሽ ልጆች ስለሆኑ  አሽናፊነትን ከእናት ማህጸን ሳይወጡ ሰላገኙት ‘4 ኪሎን ይዘው’ የተቀረቺውን ቁራሽ መሬት ለኢትዮፒያኒስቶች አንሰጣለን የሚሉን ሕክምና ይሚፈልጉ ቅዠታሞች ናቸው» ።

እስክንድር ያለበት ድርጀትና የከበቡት የታጣቁ ደንቆሮ መሪዎች ብዛት ብዙም የተማሩና የነቁ ታጣቂዎች አለመኖር ምቾት እንዳልሰጠውና ለሱ የሚመጥኑ አለመሆኑን መገምት ይቻላል። ያለው አማራጭ ከውስጥ መከራውን እየተቀበለ፤ እዛው ሆኖ ዓላማው እያዳበረ በዙሪያው ያሉትን ደናቁርት “ችሎ” እያስተማረ ከጊዜ ዕድገት በኋላ እንዲቀበሉት ለማድረግ የወሰደው  ጊዜያዊ መጠለያ ይመስለኛል።

 መክንያቱም የተከበበውና ያለበት ሁኔታ እጅግ በደነቆሩ ታጣቂዎች ውስጥ ነው (እስከንደር ማለት ምድረበዳ ውስጥ የበቀለች ቅጠል ማለት ነው)።

እስክንድር በአምሐራ ድረጅት (ብሄሔረተኝነት ከሚያቀነቅን ድርጅት) ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያዊ ራዕይ (አጀንዳ) ለማረማድ እና ያንን አገር  ለማዳን ይቻላል ሲለን ፤ አይጋጭም ወይ? የሚሉ ሰዎች አሉ፡ ለምሳሌ በፖለቲካ አበላለት (አተናተኑን) የምወድለት ድሮ የ Hamer media አዘጋጅ አሁን የ ዘ-Ethiopia መዲያ አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ አምሃ ደገፋ ይህንን ጥያቄ ደጋግሞ ይጠይቃል። እስክንድር ነጋን በሚመለከት ፈጹም አይጋጭም። ለምን እንደማይጋጭ ምክንያት ላስቀምጥ ።

1ኛ እስክንድር በተለያዩ ወቅቶች በቃለ መጠይቁ ደጋግሞ እንደነገረን  በአምሐራ ሕዝብ ላይ የተነጣጠረን ጥቃት ለማስቆም ተጠራርተን ሕዝባችንን ለማዳን እና የአምሐራ ሕልውና ለማስቀጠል እንጂ እንደ ጠባብ ብሔርተኞቹ «የአምሐራ ሪፑብሊክ ለመመስረት የተደራጀን አይደለንም» ሲል ግልጽ ያድረገው ቢሆንም፡

ባለፈው ሰሞን «አበበ ካሳሁን» የተባሉ ጸሐፊ መከራከሪያየን በጥሩ አገላለጽ እንዲህ አቅርበውታል።

 የብሄር አደርጃጀት ሁለት አይነት የራሱ የሆነ አላማ አለው፤

Tribal movements embody two contrasting dynamics: -

 one seeks to oppress others, advancing the interests of its own group at the expense of outsiders, often by scapegoating and demonizing others to rally internal support.

In contrast, the other side consists of those who are targeted—demonized, persecuted, and even killed by the oppressors—who are left with no choice but to organize and defend themselves in pursuit of freedom.

አንደኛው ብሄረተኛው መልክ እና አካህይድ፡

 የራሱን ብሄር አደራጅቶና ሌሎችን በመወንጀልና የችግሩ ምክንያት አድርጎ በማቅረብ ህዝቡን አንቀሳቅሶ ስልጣን በመያዝ የራሱን ብሄር የበላይነት ማስጠበቅና መዝረፍ የሚፈልግ፤ የከሰሰውንም ብሄር ለማጥፋት በግልጽ ጀኖሳይ የሚያካሂድ የፋሽሽት እንቅስቃሴ ነው፤

ይህ አይነት እንቅስቃሴ ከጀርመን ናዚ ጋር የሚወዳደር፤ ልክ ናዚች አይሁድ ጠላት ነው፤ የጀርመን ህዝብ የበላይ መሆን አለበት፤ የሌሎችን ቦታ ወስዶ ለራሱ ማድረግ አለበት የሚለው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፤

በሃገራችንም የትግራይና የኦሮሞ ጠባብ ሄርተኞች ያደረጉት አማራን ሰይጣን አድርጎ ማቅረብ መክሰስ መግደልና ማረድ፤ ከዛም ስልጣን ይዞ ሃገርንና ህዝብን መዝረፍ ነው፤ ይህ ብሄርተኛ ጸረ ህዝብና ጸረ ሃገር ስለሆነ፤ ሁልጊዜ መቀጠል የሚችለው በህዝቦችን መካካል ጥላቻን በመፍጥርና ሁሌ እኛና እነሱ በሚል የፖለቲካ አካሄድ ነው፤

ከነሱ ውጭ የሆነውን ጠላት ብሎ ፈርጆ፤ የራሱን ህዝብ ጠላት መጣብህ በሚል ማስፈራሪያ ከጎን የሚያሰልፍ ከጥላቻ ውጭ ምንም ነብስ መዝራት የማይችል አደገኛ አካሄድ ነው፤ ህዝብና ሃገር የሚለው ምንም ትርጉም አይሰጠውም

ሁለተኞው የብሄር እንቅስቃሴ ደግሞ

 ተገዶ ማለትም በጠባብ ብሄርተኞች ተለይቶና በበሬ ወለደ ዉሸት ተከሶ በጅምላ የሚገደልውና የሚታረደው ህዝብ የራሱን ስለባ የሆነውን ህዝብ አሰባስቦ ህልውናውን ለማዳን የሚያደርገው ትግል ነው፤

ይህ ብሄር በራሱ አነሳሽነት ብሄራዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ ሌሎችን በመዝረፍ የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስብ ሳይሆን፤ ብሄርተኝነትን ተገዶ እንዲቀበል የተደረገ ነው፤

ይህ ሰለባ የሆነው ብሄር እንደሌሎች ማለት ፋሽሽት ብሄርተኞች ሌሎችን ጠላት የማድረግ ምንም ፍላጎት የለውም፤ ምክንያቱም አነሳሱም እራሱን ማዳንና ዋናው ጠላቱ ጠባብ ፋሽት ብሄርተኛ እንቅስቃሴ መሆኑን ሰለሚረዳ ምንም በብሄር ይደራጅ እንጅ ዋናው አለማው በሃገሪቱ የብሄር ፖለቲካን አጥፍቶ ህዝቦች እንደዜጋ በሃገራቸው ተስማምተውና ተከባብረው ፍትህ ያለበት ስር ሥርአት መመስረት ነው፤

ለዛም ነው የአማራ ብሄራዊ ትግ ከሌሎች ከትግራይና ከኦሮሞ ፋሽቶች ማለትም አማራን ጠላት ብለው ሃገሪን ከሚዘርፉና አማራን በጅምላ ከሚያርዱ ናዚች የተለየ ፍትሃዊ ትግል ነው የምንለው። ሲሉ ሁለቱ የብሔረተኞቹ ለዩነት አብራርተውታል።

ስለሆነም የኢትዮጵያዊው እስከንድር ነጋ ቃለ መጠይቅ ለኢትዮጵያ ጠሊታው የአምሐራ ብሔርተኛው ፋሺስት ቡድንን ኩፉኛ ቢያስቆጣውም፤ “ኢትዮጵያኒስቱ” ቡድን ለወያኔ እና ለሻዕቢያ እንሰዋለን ለሚለው ማፈሪያው «አቅል ጥበት እና ሆድ ቁርጠት» መሆኑን ይቀጥላል።

  መልካም ሳምንት

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

Monday, November 24, 2025

የዜግነትና ሌላ ሃገርነትን የሚመኝ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የሚያልም አጠራር በሜንጫ የምትመሰረት ኦሮሚያ እና የኦሮሙማ ልሳኖች ጌታቸው ረዳ Ethio Semay 11/24/25

 

የዜግነትና ሌላ ሃገርነትን የሚመኝ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የሚያልም አጠራር በሜንጫ የምትመሰረት ኦሮሚያ እና የኦሮሙማ ልሳኖች

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay

11/24/25

ከትናንት በስትያ ባቀረብኩት ስለ ታማኝ በየነ ትችት አስመልክቶ ሙን መግለጽ ያልፈለገ የጽሑፍ አጣጣሉ የተማረ የሚመስል የኦሮሞ ነገድ ተወላጅ በመሰንጀር መልዕክት ሰሞኑን «ስለ ታማኝ በየነ» የጻፍኩት ትችት አስመልክቶ “አሁን ያለው ሥርዓት ‹ኦሮሙማ ነው» ስትል ተመለክቸ አንተ እንደምትዘላብደው ትርጉም ሳይሆን  ትርጉሙ <<ኦሮሞነት>> ማለት እንጂ ምንም “ቶክሲክ/TOXIC” ቃል አይደለም በማለት ሊያስረዳኝ ሞከረ። እኔም «አሁን ያለው ሥርዓት ሳይሸሽግ በግሃድ የሚነግረን ልሳን አንተ እነድመትለው <<ኦሮሞነት>> ማለት <<ኦሮሞነት>> ማለት ነው በሚል የዋህና ቀጥተኛ ትርጉም የተወሰነ ሳይሆን የበግ ለምድ የለበሱ የትኩላዎች “የግንጠላና የስልቀጣ/ hegemony/ “ፕርጀክት” ያለው ልሳን ነው። ማስረጃውም ነገ በምለጥፈው ማስረጃ ተከታተለኝ» ብየው በዚህ ተለያየን።

እስኪሰለቸን ደጋግመን ስለዚህኦሮሙማየሚባለው ፕሮጀክት/ግብ/ ፈልሳፊው ማን እንደሆነ ግቡናቅኔው/ፊቹንማሳወቅ ስላለብን ኦሮሙማ ምን ማለት እንደሆነ ደጋግመን ያስረዳን ቢሆንም ፤ የኦሮሞ ምሁራን ሆን ብለው ቀጠተኛውን ትርጉም ብቻ በማስረዳት ሊሸፍፍኑን ቢሞክሩም ከነግቦቹና ነግግሮች ለማየት ይህንን ማስረጃ በድጋሚ ለማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ ሰላገኘሁት እነሆ «በክለሳ መንገድ» እንሂድበት

 ዘመናዊ ትምሕርት በቀሰሙ የኦሮሞ ምሁራን እምነት ኦሮሙማየሚል ቃል <<ኦሮሚያን በቅኝ ግዛት የያዘው የአቢሲኒያ (ኢትዮጵያ) ተስፋፊነት ማለትም የቢሲያኒ ሃበሻዎች ሥልጣኔ ባሕል ፤ቋንቋ፤ እና ሃይማኖት የሚጻረር ነጻ አሮሚያ ለመመስረት የምንጠቀምበት አታጋይ መርህ ነው>> በማለት << (ኦሮሙማ) ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን ምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ የሚታይ ነው።>> ሲሉ

 አንዳንዶቹ ደግሞ ኦሮሙማ <<ኦሮሞነት>> ማለት እንጂ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጻረር ባሕሪ ነገር የለውም ሲሉ ሰምተናቸዋል።

ከላይ ያለው የመጨረሻው አባባል   የዋሃን ሊያታልል ይችል እንደሆን እንጂ ከሥር መሠረቱ የቃሉ አመጣጥና የቃሉ ለውጥ ከጥንት የተጻፉ መጻሕፍት ስንመረምር እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን ትርጉም ያለው የዜግነትና ሌላ ሃገርነትን የሚመኝ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የሚያልም አጠራር ነው

        ስሙን የተፈጠረ 18ኛው /ዘመን ጀርመኖች የላኩት በጀርመናዊው የፕሮተስታንት ሚሺነሪ በምስራቅ አፍሪቃ የተመደበው የቅዥ ግዛት አስፋፊና ሰላይ የነበረው <<ዮሃን ክራፕፍ>> ነው።

ቃሉ ዛሬ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊነትን ለመተካት የብሔረተኝነት መገለጫ አድርገው የሚያቀነቅኑት ኦሮሙማ ዕሳቤም መሠረቱ የተጣለው ኦርማኒያ  (ጀርመኒያ) ከሚለው ተመሳሳይ የቅጂ ትርጉም በክራፕፍ እሳቤ ውስጥ ነው የዛሬው ኦሮሙማ ስያሜ የመነጨው።

ክራፕፍ የዘገበውን እንዲህ ይላሉ፡

<< …their language they call “Afan Orma” the mouth of the Ormas; so as the Ga*ll*as have no general name to indicate their nationality or its seat, I propose to include both the designation of Ormania” (Travels, Researches, and missionary Labors, During an Eighteen Years’ Residence in Eastern Africa p.61)

ይህንን ወደ አማርኛ ሲተረጉመው

<<.. ቋንቋቸውን አፋን ኦርማ ይሉታል የኦርማዎች አፍ ብለው ይጠሩታል እናም .. ዜግነታቸውን ወይም መኖሪያቸውን የሚያመለክት አጠቃላይ የሆነ የጋራ  ቦታና ስም ስለሌላቸው መኖሪያ ቦታቸውን ይገልጥ ዘንድ ኦርማኒያ የሚለውን መጠሪያ ሰጥቻቸዋለሁ። ብሏል (ዮሀን ክራፕፍ)

 ጥቅስ እንደላይኛው። (ሰረዝና ድምቀት የተጨመረ)

ዮሀን ክራፕፍ የኢትዮጵያን አንድነትና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ለመበተን የተላከ ለዛሬዎቹ ኦሮሞዎች ላቲን ፊደል ቀርፆ የሰጣቸው ጀርመናዊ ፕሮተስታንት ሚሺኔሪ ነው። መጽሐፉን ሰታነቡ በሚገርም ቁጣ  የሸዋ ኦርቶዶክስ አምሐራዎች ስለተከራከሩት የሸዋ አምሐራዎችን ቆሻሾች ይላቸዋል። ኦነጎች አምሐራን የመጥላት አባዜ ከየት እንዳገኙት ምልክቱን እዩት።

የክራፕፍ ውጤቶች የሆኑት የዛሬ ዘመን ኦሮሞ ምሁራንም ከላይ የተጠቀሰውን ሲያጠናክሩት በአንደበታቸው እንዲህ ሲሉ ያረጋግጣሉ፡

<< ኦሮሙማ ኦሮሞነት ነው ኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው የተለየ የሚያደርገው የኦሮሞን ማንነትና አጠቃላይ የሆነ ባህላዊ፤ ማህበራዊ፤ ሃይማኖታዊ፤ ልሳናዊ፤ ታሪካዊ ግዛታዊና ስነ ልቦናዊ ባህርያቶችን አንድ አድርጎ የያዘ መገለጫ ነው። ኦሮሙማ ኦሮሞዎች እንደ ሕዝብ የሚኖሩበትን ማረጋገጫ የሚሰጥ ማንነት ነው።>>

<<የኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን ምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ ይታይ ነበር>> (The Journal of Oromo Studies  VOLUME 9, NUMBERS 1 AND 2, JULY 2002 P.73) (The Journal of Oromo Studies  VOLUME 1 NUMBERS 1 AND 2, Winter 1994 p.97) (ምንጭ ዐምሐራ! ሕብራዊ ማንነቱና ተግዳሮቱ- ባንተአምላክ  አያሌው - ገጽ 365-366)

እንግዲህ ክራፕፍ የፈለሰፈላቸው የኦሮሙማ ትርጉም እና ለመጻፊያ የፈጠረላቸው የላቲን ፊደል እንዲሁም እንዲከተሉት ያስተማራቸው የጀርመን ፕሮተስታንት ባሕሪዎች የተቀኙት ኢትዮጵያን እንዲጠሉ የተቀረጸ አጀንዳ ስለነበር ኢትዮጵያዊነትን አብዝተው ይገፉታል፤ ኢትዮጵያዊ ፊደል የኦሮሞነት ጠላት አድርገው ይመለከቱታል። በሜንጫ የምትቋቋም የኦሮሚያ እስላማዊ ሀገር እንድትኖርም በግሃድ ይሰብካሉ። <<ከሩዋንዳ እስከ ኦሮሚያ>> የታየው የዘር ዕልቂት የሰለፊ እስልምና እና 18ኛው /ዘመን ወደ አፍሪካ የመጡ የጀርመን የፕሮተስታንትና የካቶሊክ ሚሺኔሪዎች የተቀነቀነ እንደሆነ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው ይገልጻል።

  አሁን ያለው ኦነጋዊው አብይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት የተቃኘው በዛው መስመር  በመሆኑ እራሱና  የሾማቸው የባለሥላጣናቶች ንግግር ኦሮሙማ ምን ማለት እንደሆነ ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው በመጽሐፋቸው   ለታሪክ ተዘግቦ እንዲቆይ  የዘገቡልንን እነሆ ለናንተም ይጠቅማልና እንመልከት፡

በመሪያቸው በአብይ አሕመድ ንግግር እንጀምርእነሆ፦

1- “ትናንት ያዋረደንን አዋርደነዋል፤ ትናንትና አትወጡም አትገቡም ብሎ አጥር ያጠረብን ዛሬ ወጥቶ መግባት ከእኛ ፍቃድ ውጭ አይችልም” (አብይ አሕመድ)

2- “ ሰው እየሞተ ችግኝ አይተከልም የሚለን ጠላት ነው፡ እንዳትሰሙት፡ ሰው እየሞተ የሞተበት ቦታ ችግኝ እንተክላለን ቢያንስ አስከሬኑ ጥላ እንዲኖሮው (አብይ አሕመድ)

3- “ታስሮ ጀግና ለመሆን የሚሯሯጥ ጋዜጠኛ አለ. ምርጫ ሳታሸንፍ ባለአደራ ምናምን የሚባል ጨዋታ ውስጥ የምትገባ ከሆነ ግልጽ ጦርነት ውስጥ እንገባለን። ይህ መታወቅ አለበት(አብይ አሕመድ)

4- አዲስ አበባ ውስጥ ያለው ማሕበረሰብ ኦሮሞ ጠል ነው (አብይ አሕመድ)

5- “ሰዎቹ (ዐምሐራዎች) የሚችሉት ሦስት ነገር ብቻ ነው፦ ጩኸት፤ልቅሶ ስም-ማጥፋት” ለአልቃሾች ብትችሉ መሀረብ (ሶፍት) ማቀበል እንጂ ምን አስጨነቃችሁ? ያልቅሱ ተውዋቸው። እኔ የሚያስጨንቀኝ ዝም ሲሉ፤ ሳይነፋረቁ ሲቀሩ ነው።ዝም አሉ ማለት  እኔ እነሱን እያስደሰትኩ እንደሆነ ይሰማኛል…! (ሽመልስ አብዲሳ)

6- ኦሮሞ ሕዝብ እዚህ ነበር የተሰበረው፡ እዚህ ነበር መዋረድ የጀመረው፡ እዚህ ነበር ቅስሙ የተሰበረው፤ ቱፋ ሙናን የዚያን ዘመን ታጋዮች የነፍጠኛ ሥርዓት እዚህ ነበር የሰባበራቸው። ዛሬ የሰበረንን ሰብረን፤ ከመሠረቱ ነቅለን፤ኦሮሞ በተዋረደበት ቦታ ተከብሮ ይገኛል። (ሽመልስ አብዲሳ)

7- አዲስ አበባ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሠፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት በዋቆ ጉቱ እና በታደሠ ብሩ ስም ትምህርት ቤቶች ከፍተን የሚማርልን ተማሪ አጣን። ስለዚህ ተማሪ ከቡራዩ እየጫንን እናመጣ ነበር፡፤ አምና የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ / ዐብይ በሰጡት ውሳኔ መሠረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች አስጀመርን።  5700 በላይ መምህራን አዲስ አበባ ውስጥ አስገብተናል። (ሽመልስ አብዲሳ)

8- ዓባይን ተሻግረን ባሕርዳር ድረስ ሄደን ግማሹን Convince ገሚሱን Confuse አደርገን ቁማር ቆምረን ቁማሩን በልተን ተሳክቶልን ተመልሰናል። እንዴት አደናብራችኋቸው ነው የምትሉት? ምን አገባችሁ? (ሽመልስ አብዲሳ)

9- አዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን ህዳሴ ግድቡን ኦሮሞ መቆጣጠር እንዲችል ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ ኦረሞዎችን በማስፈር ዲሞግራፊውን እየቀየረ ነው! ክልሉ ውስጥ ኦሮሞ 37% ደርሷል። (ሽመልስ አብዲሳ)

10- ብልጽግናን የሠራነው ለእኛ እንዲመች  አድርገን ነው። ብልጽግና የኦሮሞ ነው ብልጽግና ኦሮሞ ወይንም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው የሚመራው አምስት ቋንቋ የመረጥነው ለእነሱ አስበን አይደለም። ለኦሮሞዎች ብለን ነው። አማርኛ እየደከመ ነው፡ እየቀነሰ ነው። ኦሮምኛ ከአማርኛ በላይ እየተነገረ ነው(ሽመልስ አብዲሳ)

11- “ለአዲስ አበባ ብዙ መፍትሔ አለ። አንደኛው በሕገወጥ ሆነ በሕጋዊ መንገድ ሰው ማስገባት ነው። ሌላኛው አዲስ አበባን የማትጠቅም ከተማ ማድረግ ነው። አራት አምስት የፌደራል ከተማ እንመሰርታለን። ድንበር የመካለያ አዋጅ ወጥቷል። ለስሙ ነው እንጂ ይጸድቃል። (ሽመልስ አብዲሳ)

12- የኦሮሞ ትግል ማዕከል አዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ብቻ ናት (ሽመልስ አብዲሳ)

13 አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት አደስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆንዋን ተከትሎ ኦሮሚያ መዝሙር በት/ቤቶች መሰጠቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል (ሽመልስ አብዲሳ)

14- በቄሮ ትግል ፌስታሉን ይዞ ከእስር ወጥቶ ሲያበቃ ዛሬ ባለአደራ መንግሥት ብሎ ራሱን መሾም አልያም ባለተራ መንግሥት ብሎ ለውጥን ማጣጣል በምንም ስሌት ተቀባይነት የለውም። መንግሥታችንን ለመፈታተን ባለተራ ባለአደራ እያለ የሚያላዝነው ወደ ትክክለኛ መስመር ለመመለስ እንሰራለን። (አዲሱ አረጋ ቂጢሳ)

15- “እኔ እና / ታከለ ኡማ ጠዋትንም ማታም ሻይ አብረን ስንጠጣ፤ የኦሮሞ ጥቅም አዲስ አበባ ውስጥ ለማስጠበቅ፤ በተለይም ካሁን ቀደም ተገፍቶ ከአዲስ አበባ ሲወጣ የነበረውን አርሶ አደርና ኦሮሞነት ከከተማ ውጭ እንዳይሆን ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ እንደሆነነው (አዲሱ አረጋ ቂጢሳ)

16- ከሶማሌ የተፈናቀሉትን አምስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች  በአዲስ አበባ ዙርያ እና  በአዲስ አበባ ውስጥ አስፍረናል። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስድስት ሺሕ ሰዎችን አስገብተናል።  (ለማ መገርሳ)

17- አዲስ አበባ  የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት። አዲስ አበባ ኦሮሚያ  ዋና ከተማ መሆንዋን ተከትሎ ኦሮሚያ መዝሙር መስጠቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። (አበበች አደኔ)

እነዚህና የመሳሰሉ ሌሎች እዚህ ያልተጠቀሱ ንግግሮች << Ormania መርህ>> የተከተሉ ያልተሸፋፈኑ ጉልህ የሆኑ ኦሮሙማዊ የአጀንዳ አፈጻጸም ምልክታዊ ንግግሮች ናቸው

ከዚህ አንጻር 8 አመቱ የኦሮሙማ ፕሮጀክትና አንደበቶችን ስንመረምር በአምሐራ ሕዝብ ላይ የተካሄደው የዘር ማጽዳት ዘመቻ ስንመለከት እጅግ አክራሪ የተባሉት የአብይ አሕመድና ሌንጮ ኦነጎች ጴንጤያዊው መንጋ፤ የሰለፊ ኦሮሙማ እስላሞች” በሕልማቸው ይሆናል ብለው ያልጠበቁት ያለ አብይ አሕመድ እገዛ የመንግሥትን መንበር ተጠቅሞ ለኦሮሙማ ፕሮጀክት (ግብ) መሳካትና መፋጠን ከአብይ አሕመድና ድርጅቱ በላይ የሚተባበራቸው ወንጀለኛ ቡድን አያገኙም ነበር። እነሆ ተሳከቶላቸው 7 አመታቸው (ሚያዚያ 2018- 2025) ገዝተውን 8 አመታቸውን ለማስቆጠር ጥቂት ወራቶች ይቀራቸዋል።

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay