Friday, September 26, 2025

አባቶቻችን ተማርክዋል እኛም ተደግመናል የሚለው የፋኖ አማራዎች እና የወያኔ ትግሬዎች ዘረኛ መፈክር ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/26/25

 

አባቶቻችን ተማርክዋል እኛም ተደግመናል የሚለው የፋኖ አማራዎች እና የወያኔ ትግሬዎች ዘረኛ መፈክር

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

8/26/25


ይህንን ስታነቡ የምትንጨረጨሩ የፋኖ ደጋፊዎች እንዳላችሁ አልሳትኩም። ያ ለ27 አመት በትግሬዎች ፡ ሁለት አመት ደግሞ በናንተ ያስተዋልኩት ባሕሪ ነውና ይሚገርመኝ አይሆንምና ትችቱ ቢጎመዘዛችሁም የጠቅማችኋልና ዋጡት።

«አባቶቻችን ተማርክዋል እኛም ትደግመናል» የሚለው መፈክር የተደመጠው መጀምሪያ በትግሬዎች ነበር አሁን ደግሞ አማራዎች  ከትግሬዎቹ የቀዱት እጅግ አሳፋሪ የሆነ «ዘረኛ መፈክር» ወሎ ውስጥ ማስተጋብታቸው የሚያሳየን 36 አመት ሙሉ የተዘረጋው “ብከላ” የአማራው ወጣት ታጣቂም ጭምር እንዳልማረው ምልክት ሰጪ ነው።

ከናንተው በፊት አባቶቻችሁን ማርከናዋል እያሉ ተማራኪዎቹ ወላጆቻችን እንዲያዋርዱና እንዲያንኳስሱ የተገደዱት ምርኮወያነ ወደ አዲስ አበባ ድል ቀንቶት ሲገባ፤ እንደ «የባዕድ ወራሪ ጦር ሰራዊት ታይተው» ከነቤተሰቦቻቸው ጭምር ተበትነው ከሰውነት በታች ሆነው እንዲታዪ በድህነት  በልመናው-ዓለም ተሰማርተው የሰውን ዓይን አጎንብሰው እያዩ «የተወለዱበት ዘርና ምድር እንዲረግሙ የተደረጉት» በወያነ እና ሻዕቢያ አጠራር «ሠራዊት ደርጊ» ፤ «ሠራዊት አምሓራ» የደርግ ሠራዊት» ፤ «የአማራ ሠራዊት» በማለት ሲጠርዋቸው የነበሩትን “የኢትዮጵያ ሰራዊትን” ነው “ወላጆቻችሁ” እያሉ የሚጠርዋቸው

ይህ አባባል የማይረዳው ሰው ካለፉት የወያኔ ዘረኛ  ንግግሮች የማያውቅ ድንቁርና ያሸነፈው የአማራ ወጣት ካልሆነ በቀር ፤ እኛ ከትግራይ እና ኤርትራ የተፈጠርን ትግርኛ ተናጋሪዎች “የተማረኩትን ወታደሮች በዛው አባባል «በሉ እንጂ እያሉ ሲያስገድድዋቸው» ምን ለማለት እንደፈለጉ ስንኙን እናውቃለን።

ታስታውሳላችሁ “ይድርስ ለጎጠኛው መምህር” መጽሐፌ ላይ የጠቀስኩት የወያኔ የመጀሪያው የጫካ ዘፋናቸው?

 ትግርኛው እንዲህ የላል።

<<ጨቆንትና  አምሓሩ ምስ ታሪክ ፀሓፍቶም

    ንዓና ዓብሊሎም ታሪኽና ጎቢጦም

    ኣለዉ ይምክሑ ብደም ወለድና

    ንቃለስ ተጋሩ ክምለስ ቅያና>>

 

ትርጉም

<<ጨቋኞቻችን አማራዎች እና የታሪክ ጸሓፊዎቻቸዉ እኛን ጨቁነዉ ታሪካችነን አፍነዉ በአባቶቻችን ደምና ዝና የነሱ ያባቶቻቸው ደም እና ዝና በማስመሰል ዛሬም  እየተመኩበት ስለሆነ ታሪካችንና ዝናችንን ለማስመለስ እንታገላቸዉ>> ይላል።

»አባቶቻችን እና አባቶቻቸው» የሚሉ ስንኛዊ የወያኔ  አጠቃቀሞች  እስኪ በደምብ አጢኑዋቸው?

ካሁን በፊት ወያኔዎች ያንን ዘረኛ መፈክር በሙርኮኞች ላይ ሲያስገድዱ ፤

«ስር የሰደደ የበታችነት ስሜት የወለደው የትግሬ ፋሽስታዊ ልዕልና የቪዲዮ ማስረጃ» (ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 12/25/2021 የሚል ትችት መጻፌ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ በዚህ በለጠፍኩት በስዕለ ድምፁ (ቪዲዮ) የምታደምጡዋቸው የወያኔ ትግሬና የፋኖ አማራ ታጣቂ ካድሬዎች በኢትዮጵያዊያን የጦር ሙርከኞች ሕሊናላይ ከኢትዮጵያዊ ባሕልና ስነምግባር ያፈነገጠ ነውረኛና ዘረኛ መፈክር” ስለተደመጠው መፈክር እጅግ ገርሞኛል

«ወላጆቻችሁን ማርከናል እናንተ ልጆቻቸውንም ማርከናችኋል» የሚለው መፈክር “በኛ እና በነሱ” ቅኝት የተቃኘ ቀጣይ የኢትዮጵያ የዘርኞች ጦርነት መዳረሽያው የት ይሆን?

በዛው ቪዲዮ «ወላጆቻችን ተማርከዋል እኛም ተደግመናል» በሚለው ወያኔዎች ወሎን ሲቆጣጠሩ ወያኔዎች የለጠፉት ዘረኛ መፈክር ላይ ሙርኮኞቹ መፈከር እንዲሉ ተገደው ሲያስሰሙ ቪዲዮውን በጥንቃቄ ስትመለከቱት ሙርከኞቹ ከውስጥ የተሰማቸው ቅሬታና ንዴት፤ መፈክሩን የማስተጋባቱን ውስጣዊ ልግመተኛነት ማየት ትችላለችሁ (የፋኖ መርኮኛዎችም ላይ ያየሁት ተመሳሳይ ነበር)። ግራ እጃቸው እያነሱ በሉ የተባሉትን ዘረኛው መፈክር እንዲሉ ቢገደዱም ጠቂቶች ካልሆኑ እጅግ ብዙሃኑ የቅሬታ ሐዘን የተቀላቀለ እምቢተኛነታቸውን በዝምታ አሳይተዋል።

ወደ ፋኖዎቹ ከመግባቴ በፊት የወያነ ትግሬ ታጣቂዎች ለምን ይህንን መፈክር መረጡት የሚለው ታሪካዊውን አመጣጡ እንመልከት።

 ወያኔ ድሮም ሆነ በቅርቡ በወረራቸው የአማራክልሎችየተከተለው የፋሺሰቶች ፖለቲካ ደጋግሞ ያሳየን አስነዋሪነቱ በከዓለም አቀፍ ሕግ ውጭ በሆነ አያያዝ የሰው ልጆች ልዕልና እና ክብር በሚነካ የሙርከኞችን ሕሊና በሚጎዳ መልኩጠመንጃደግኖ በማስፈራራትየእራሳቸውን እና ወላጆቻቸውንሰብአዊ ክብር የሚነካመፈክርእንዲያስተጋቡ ያደረገበት ምክንያት፡

በዙዎቻችን የትግራይ ተወላጆች እንደምናውቀው በትግርኛው “ወለዶም” (ወላጆቻቸው) ብለው የሚጠርዋቸው በሻዕቢያ እና በወያነ ትግሬ የቃላት አጠቃቀም አማራው ላይ የሚቀስር ሲሆን “ወላጆቻቸው” ተብለው የተጠሩት ፤ «ደቂቀ ምኒልክ» ብለው የሚጠሩዋቸው “የአማራ ልሂቃንን” ከዚያም የቀዳማዊ ሃይለሰላሴ ዘመን ፤ የደርግ ዘመን የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ነው። እነዚህ ደግሞ ምንም እንኳ ኦሮሞዎች፣ ከአማራዎች፣ ከትግሬዎች፣ ከጉራጌዎች፣ ከሶማሊዎች፣ ከደቡቦች፣ ከጋምቤላዎች፣ ከቤኑሻንጉሎች ... ወዘተ የተወጣጡ ወታደሮች ቢሆኑም ፤ በጥቅል “የአማራ ወታደሮች” ይሏቸዋል።

ወያኔዎችና እና ሻዕቢያዎች ደርግን ማረክን ሲሉ አማራን ማረክን ማለታቸው ነበር፡ (ተጋዳላይ ትግራይ አርኪብካ በሎ ነቲ ዓሻ አምሓራይ-

«የትግራይ ታጋይ እያሯሯጥክ በለው ያንን ሞኝ አማራ»፡የሚለው  ክ4 አመት በፊት እንደ አዲስ ወደ ወሎ ሲገቡ ሲጨፍሩበት የነበረውን ቪዲዮ የለጠፍኩትን አስታውሱ)

በኢትዮጵያዊያን ነውር የሚባለውን ነውር ለጀሮአችን የሚቀፍ እንግዳ ነገር “ታጣቂ ብሔረተኞች” በሙርከኞቻቸው ላይ የለመዱትን አሸማቃቂ መፈክር ተገድደው እየደጋገሙ እንዲያስተጋቡ መስማትና እንደገና አሁን በአማራ ታጣቂዎች ሲደገም የሚነግረን ነገር አንድም የፋኖ ትግል ወያኔ ከውስጥ ገብቶ እየመራው ነው ፤ አልያም ዘረኝነት አማራውንም በክሎታል ማለት ነው።

 ይህ ድርጊት በዓለም አቀፍ የስነ ሕሊና ምሁራን ልዩ ትርጉም አለው።ድርጊቱን ስትመለከቱት ወያኔ ካለው የአማራ ጥላቻ ማስተጋባት አጋጣሚውን በመጠቀም ልዕልናውንና ዘረኛነቱን” በተማረኩት ምስኪኖች አንደበት እንዲስተጋለት በማድረግ ሙርከኞቹን እንዲጨነቁ ማድረግ የምርኮኞችን ሕሊና “ቶርቸር” ማድረግ ነው ፋኖ ይህንን ዘረኛ መፈክር “በየእርሻቸው እና ምጣድ ቤቶች» ደፋ ቀና የሚሉትን ኢትዮጵያዊያን የሰራዊቶቹ ድሃ ወላጆች ባልዋሉበት ጦርነት እየተጠቀሱ  “ወላጆች” እየተዘለፉ ነው። እነዚህ ወላጆች የሚባሉት የሰራዊቱ ወላጅ እናትና አባቶች ብሔረተኞቹ በሚያሰቀምጡት ካንደ ነገድ የተገኙ ወላጅ እናት የመጡ ሳይሆን ከመላዋ ምድሪቱ የተውጣጡ መስኪን ወታደሮች ናቸው።

ፋኖዎቹ የተለያዩ የማምለጫ ቃላቶች ሊጠቀሙ አይችሉም። መሪዎቻችን ተማርከዋል፤ እኛም ተደገመናል” እና  «ወላጆቻችን ተማርከዋል እኛም ተደግመናል» የሚል ቃል ለየቅል ትርጉም አላቸውና ማምለጫ ምክንያት የለም። ለመሆኑ ፋኖ ሥልጣን ብይዝ እነዚህ ወታደሮች የአብይ ወታደሮች ናቸውና ወያነ እንዳደረገው እነሱን በትኖ ወደ ልመና አሰማርቶ የራሱ የአማራ ሰራዊት ሊያሰማራበት ነው? በቃ ግልጽ እኮ ነው!

እኔ እንደገባኝ በፋኖ እና በወያኔ መካከል ያለው ባሕሪ የተማረኩት የባዕድ ሰራዊቶች አድርጎ በማየት በትምክሕት የተወጠረ ራሱን ክዚያ ባዕድ ተብለው ከተወለዱ ወላጆች የመጡ ሰራዊቶች ላይ ትምክሕታዊ የበላይነትን ማሳየት፡ ያ ካልሆነ ደግሞ ራስን በበላይነትና በየበታችነት ስሜት የሚጋጭ ሁለቱ በውስብስብነት ተጋምደው አንዱ አንዱን ለመሸፈን የሚደረገው የሕሊና አለመረጋጋት የሚታዩ የስነልቦና ክስተት ካልሆነ በስተቀር ፤ ‹ወላጆቻችሁ ማርከናቸዋል እናንተም ተደጋማችሁኋል› የሚል በፋኖ የተደመጠው ከወያኔ ተቀብለው የቀዱት ዘረኛ መፈክር መወገዝ ያለበት ነውረኛ ባሕሪ ነው። የተማረኩትን ወላጆቻቸው ክብር እዲያኮስሡ ማስጨነቅ የሚገርም ከሥተት ነው

ሕሊናቸው በተጨናነቀባቸው በማያውቁት ጫካ ገብተው በተማርኩ ምስኪኖች ልዕልናን ለማሳየት መሞከር የበታችነትን ስሜት ለማካካስ የሚያገለግልየመከላከያ ዘዴነው። የበላይነትን ለማጎናጸፍ በተማረኩ ወታደሮች ላይ ወላጆች እንዲኮሰሱ የሚጥሩ ሻዕቢያ፤ የኦነግ ፤ የወያኔና የፋኖ መሪዎች ስድ ባሕሪ” የተጥናወታቸውበሽተኞችናቸው።

በጫካ ስደነት የሰክሩ ታጣቂዎች  በምስኪን ምርኮኞች ላይ እራሳቸው በአሸናፊነት ረድፍ እያስቀመጡ በሄ ቁጥር ለበታችነታቸው ስሜትምክንያታችንነው ብለው ለሚወነጅሉት ማሕበረሰብ አጋጣሚውን አግኝተውበቁጥጥራቸው ሥር ሲገባከዛው ማሕበረሰብ በመጣሙርከኛላይ እራሳቸው የሚሰቃዩበትን የበታችነታቸውን ስሜትይጭኑበታል። እየሆነ ያለው ይህ ነው።

ይህንን ሲያደርጉ በበታችነት የሚሰቃዩበት የሕሊና ጭንቀታቸው እንደ መውጫ መስኮት ይጠቀሙበታል። በዚህ ቪዲዮ ላይ ወያኔዎችና ፋኖዎች በማረኩዋቸው ወታደሮች ላይ የፈጸሙት አስነዋሪ ስነምግባር እያየነው ያለው ዓይነተኛው መነሻ ከላይ የጠቀስኩት ይፋና እና ድብቅ ከሆነ ጥላቻ የተነሳ ነው።

ድርጊቱና መፈክሩ እጅግ መረን የለቀቀ ነው።እራሳቸውንና በጦርነቱ ውስጥ የሌሉትን የሙርከኞቹ ወላጆችበዓለም አቀፍም ሆነ ሃይማኖታዊ ሕግ injurious to dignity የሚባለው ክብረ ነክ የሞራል መበስበስብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው። ኢትዮጵያዊያን በማፈሪያነት ለታሪክ ማስረጃ ሊዘግቡት የሚገባ ቪዲዮ ነው።

የሚገርመው ደግሞ በታጣቂዎቹ ገረም ሚዲያ ተብየዎቹ የመበከል ባሕል ያልሰለቻቸው አንዳንዶቹ በተቃውሚነት ስም የሚጠሩ ግን የወያነ መሪዎች ብዕና አሳማሪ ሚዲያዎች ሲሆኑ ፤ አንዳንዶቹ ሚዲያዎች ደግሞ በተቃዋሚነት የቆሙ የምናውቃቸው እሥሥቶች ይህንን የዘረኞች መፈክር እድምቀው አወንታዊ መዝሙር እያሰመሰሉ ከበሮ ሲደልቁ በየሚያዲያቸው ሲያስተጋቡት መስማት አግራሞት ጨምሮብኛል።

ቪድዮው በተመለከትኩበት ዓይን እራሴን መልሼ የምጠይቅበት አጋጣሚ ነበር።እውነት ለአማራው መነሳት ስቀሰቅሰው የነበረው ትግል ፤ እውን ትግሉ ተጠልፎ በእነዚህ ውርጋጦችና ጎጠኞች ስር መውደቁ አሳዘነኝ። አንድ የቅርብ ወዳጄም ባለፉት ወራቶች ስንወያይ ዕድሜውን ሙሉ የታገለለትን የአማራ ጉዳይ በረዢሙ አመታት ጊዜውን የሰዋለትን ትግል በነዚህ ኩታራዎች እጅ ወድቆ መበላሸቱን አይቶ አመርሮ የገለጸልኝ አስታወስኩኝ።

አጋጣሚ ይህ ቪዲዮ ስመለከት ሰመማ ወደ እሚባል ገጠር የሚወስድማይ አድራሻ|” ከሚባል ሽሬ እንዳስላሴ እና ሰለኽለኻ መካክል አቋርጠን ከወያኔ ተጋዮች ጋር ስንጓዝ (እኔ ወደ ሱዳን ነበር እምጓዘው) ስሙን የማላስታውሰውነገር ግን መልከመልካም እና ለግላጋ ረዢም ቁመና ካለው የታጋዮቹ ዋና መሪ ጋር እያወራን ንጓዝ ዛች ቦታ ላይ ስንደርስ የሆነ የራዲዮ መልእክት ጥሪ ደረሰውና መነጋገር ጀመረ። በንግግሩ ውስጥ ከዚህ ቪዲዮ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ንግግር ከተጣራው የራዲዮ ሞገድ ላይ ወላጆቻቸውን ማርከን ልጆቻቸውንም እየማረክን ነው!” …“ተቀበልከኝ?የለዋል: በትግርኛ፤ እርሱም አዎ! አዎ!” እንደማለት ይመስለኛል በፈገግታ እርሱምበኮድመልስ ሰጠውናግንኙነቱንበዛው ተቋጨ።

ስናወራው የነበረው ጥሞታል መሰለኝ ልጁ ወደ እኔ መለስ ብሎአካባቢያችንውግያ ነገር ስላለ ፤ቃኚ እስኪያጣራልን ድረስ ትንሽ እዚህ እንቆያለን ብሎኝ ከኔ ራቅ ብሎ ሄዶ ጥቂት እንደቆየንጉዞአችን እንድንቀጥል ሆነ

ዛሬ ያየሁት ቪዲዮና ያደመጥኩት መፈክር ተመሳሳይነቱ ሳነጻጽረው ይህ የስነሉባና ትምክሕታዊ የበታችነት (የዘረኛነት) ስሜት ቀደም ብሎ በረሃ ላይ እያሉ የነበረ መሆኑን ራሴን የማስታውስበት አጋጣሚ ሆኖ ዛሬ አማራ ፋኖዎች ደግመውት ሳገኘው፤ እጅግ ፤ እጅግ ገርሞኛል።

የእግዚአብሔር የበኽር ልጅ ኢትዮጵያ ሆይ ባለሺበት ሰማይ ይህንን ጉድሽ “የሰማሽ ነው”?

ጌታቸው ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY