በአስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ አገራቸው ጎን የቆሙ ታጋዮቻችን ጊዜ ሲጥላቸው ከጎናቸው እንቁም! ከፍ አድርገንም እንያቸው!
የመምህር ታየ ቦጋለ ፈታኝ ጊዜ አብረን እንድንቆም ጥሪ አደርጎልናል!
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
2/4/25
ታየ ቦጋለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ምሁር ነው። አሜሪካ ባጋጣሚ መጥቶ እዚህ ከቀረ ትንሽ ወቅት ሆኖታል። የኛ አስቸጋሪ ህይወት አገር ውስጥም እዚህም ቀምሶታል። ለሀገሩ ታስሯል፤ ተደብድቧል፤ ተሰድቧል፤ ህይወቱ ተመሳቅሏል።
ኢትዮጵያ እያለ ለዓፋሮችና ለቦረና ሕዝብ በመከራ ጊዜያቸው ዕርዳታ አሰባስቦ ደርሶላቸዋል። እነሆ ዛሬ መጥፎ ዕድል ሆኖ ከታመመ በሗላ ከሥራ ተሰናብቶ ፈታኝ ህይወት ውስጥ መገኘቱን በዚህ ባስተላለፈው የዕርዱኝ መልዕክቱ ማወቅ ችያለሁ።
የፖለቲካ ልዩነት ሊኖረን ይችል ይሆናል፡
ያ ልዩነት ግን ኢትዮጵያዊነታችንን እና ወንድማዊነታችንን ማስወገድ የለብንም። ፖለቲካና ዜግነት ለየብቻ ናቸው። ኢትዮጵያ በማለቱ
ብዙ መከራ አይቷል። እነሆ ዛሬ የሰው ፊት ማየቱ ቢያስቸግረውም “ኢትዮጵያዊያትና ኢትዮጵያዊያን” በመከራው ወቅት አቅፈን ደግፈን
<< የኢትዮጵያዊነት>> ትርጉም ገብቶን ጊዜው ያልፋል ፤ አይዞህ ማለት ተገቢ ስለሆነ እነሆ <<ነገ
በኔ>> የሚለው የኢትዮጵያዊያን ብሂል ሳንረሳ መልዕክቱን እንድታደምጡና የተቻለንን እንርዳው።
ታዬ
ቦጋለ በአሜሪካ ጎዳና
ተዳዳሪ ሆነ። ከኢትዮጵያም
ቢሆን ብር ልኩልኝ
ተቸግሬያለው
https://youtu.be/nKeWzQZkIx8?si=tQXa8pcr4QEIs1l1
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
No comments:
Post a Comment