በእንቅስቃሴ ነፃነት ላይ እገዳ ያደረጉ ሁለት ወረበላ ሥርዓቶችና ሰለባዎች
ጌታቸው ረዳ
2/12/25
Ethiopian Senmay
በግራ በኩል የሚታየው ምስል አፓርታይዱ “የአብይ አሕመድ የኦሮሙማ ሥርዓት” ሰለባ የሆነው የኢደፓ ፓርቲ መስራችና
መሪ ልደቱ አያሌው ለከባድ የቀዶ ጥገና ሕክምና ወደ አሜሪካ መጥቶ ታክሞ ወደ ሃገሩ ለመመለስ ቲኬት ቆርጦ ለመሳፈር ሲል
ሰሞኑን (ፌብሩዋሪ 2025 በፈረንጅ አቆጣጠር) በሕገወጥ መንግሥታዊ የሥልጣን እርከኖች ተቆጣጥሮ አፓርታይዳዊ ጸረ ኦርቶዶክስና
ጸረ አምሐራ የሆነ <<የኦሮሙማ ፕሮጀክት>> ለማካሄድ
ሥልጣን የተቆጣጠረው በአብይ አሕመድ የሚመራው <<የዱርየዎች ቡድን>> ወደ ግል
ንብረታቸው የቀላቀሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥብቅ ትዕዛዝ በማሳለፍ ወደ ተወለደባትና ወደ እሚኖርባት
ምድር ወደ ሃገሩ ኢትዮጵያ <<እንዳይገባ>>
የተከለከለው ልደቱ አያሌው ሲሆን ፡
በቀኝ በኩል የሚታየው ምስል ደግሞ “ትግራዋይነትን ዙፋን ላይ ለማንገሥ የታገለለትን ሥርዓት” ወሩ በማላስታውሰው
በ2006 (ኢትዮ አቆጣጠር) ባንድ ወቅት ወደ ሃገሩ እንዳይገባ ሰለባ የነበረው አክሱማዊው ብስራት አማረ ነው።
ብስራትን እዚህ ላመጣው የፈለግኩት ብዙ ሰዎች እንደ ዛሬ ያለው የአብይ አሕመድ ሥርዓት
ዜጋ እንዳይገባ የከለከለ ሥርዓት ታይቶ ተስምቶ አይታወቅም እያሉ ብዙ ዘጋቢዎች ሲናገሩ ስለሰማሁ ፤ ያለፈው የትግሬዎች ሥርዓት
ምን ያህል ይከታተሉት እንደነበር ባለውቅም ከላይ በጠቀስኩት ዓ.ም ብስራት አማረ አዲስ አበባ ቦሌ እንደደረሰ “የወያኔ ደህንነቶች”
ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ከልክለውት እንደነበርና ለዚህም በወያኔ የውስጥ ለውስጥ ሽኩቻ ሲደረግ እንደነበረና ብስራትም የአንደኛው
ወገን (ምናልባትም የስብሓት ነጋ) ደጋፊ ስለነበር ፡ <<ጌታቸው አሰፋ>> የተባለው የወቅቱ የደህንነት ሐላፊ ወደ ሃገር እንዳይገባና እንዲመልሱት ስላዘዘ
ከቦሌ አየር ማረፊያ
ወደ አሜሪካ እንደገና ወዲያውኑ እንዲመለስ
ተደርጓል።
ለዚህም እራሱ (ቅዳሜ ማርች 15/2014 በፈረንጆች አቆጣጠር) የተዋጣላቸው ጸረ አማራ
ዘረኛ ትግሬዎች የሚሳተፉበት “ገዛ ተጋሩ” በመባል የሚታወቀው <<የፓል
ቶክ>> ክፍል ገብቶ የተናገረው ላስታውሳችሁ።
የክፍሉ ዋና ባለቤት የነበረቺው የራያ እና አዘቦ “የጨርጨር፤መዀኒ” ተወላጅ
ነኝ የምትል የጎጃም ሕዝብን
<<ዝቅተኛ፤ ኢድየት
እና ሪታርድ ነው! ከዚህ ወዲያ “ሪታርድ” እያላችሁ ጥሯቸው>> በማለት የጎጃም ሕዝብን የዘለፈች የፓልቶክ
ስሟ <<ሕድያት
ትግራይ>> (እውነተኛ ስምዋ “አባዲት”) የተባለች “ለ ኤን ጂ ኦዎች” የምትሰራ ብስራትን (Saturday,
March 15/2014 በፈረንጅ አቆጣጠር) በእንግዳነት ጋብዛ ወደ አገር እንዳይገባ የተከለከለበት ምክንያት ስትጠይቀው፡
“አዲስ አበባ
አየር ማረፊያ ሲደርስ ወደ አገር አንዳይገባ መከልከሉና” እንዳይገባ ያገዱትም በራሱ ቃል <<ዲቃላዎች>>
የሚላቸው ሥልጣን ላይ ያሉ ከሁለት ዘር የተወለዱ ቡድኖች (ምናልባትም ከአገው ወላጅ አባት የተወለደው ጌታቸው አሰፋ ይሆናል
የሚል ግምት አለኝ) ምክንያት እንደሆነ መግልጹ በወቅቱ ብገልጽም የማስታወስ ችሎታችን ችግር ያለን መሰለኝ፤ ከልደቱ ሌላ
በታሪክ ወደ አገር አንዳይገባ በትግሬዎች (በነሱ ቃል ኢሕአዴግ) ሥርዓት የተከለከለ ሰው የለም ሲሉ ሚዲያዎች ስለሰማሁ ነው
ብስራትን እዚህ ያመጣሁት።
አሁን ወደ ልደቱ።
አብይ አሕመድ የወያኔ ሰላይና “ኩሊ” በነበረበት ወቅት ተቃዊሞች የመገደልና
የመንቀሳቀስ እግድ ይደረግባቸው እንደነበረ ያ ልምድ እንደቀሰመ የሚታወቅ ነው። አለመታደል ሆኖ ከ6 አመት በፊት ኢትዮጵያዊያን ሊሰሙት የሚፈልጉትን ንግግር
በመናገር ሕዝብን ያታለለና ንግግሮቹ ሁሉ ጊዜ ሳይፈጅ ቀልብሶ <<በኩሊነት>> ተቀጥሮ ሲሰራበት ከነበረበት <<አፓርታይዳዊው
የትግራዋይነት ፕሮጀክት>> በባሰ መልኩ ወደ <<አፓርታይዳዊ ኦሮሙማ ፕሮጀክት>> ለውጦ ኢትዮጵያን
ወደ <<ገሃነበ እሳት>> ጨመራትና እነሆ ዜጎች በሃይማኖታቸው፤ በቋንቋቸው በነገዳቸው
እየለየ በማጥቃትና ከመጨፍጨፍ አልፎ ፤ በፖለቲካ የሚለዩትን ተቃዋሚዎች
እየነጠለ በሚያስደነግጥ መልኩ ዜጎች ከሃገራቸው እንዳይወጡና እንዳይገቡ እያደረገ መሆኑን በልደቱ አያሌው ላይ የፈጸመው ሕገወጥ
የዱርየ መንግሥትነቱን አሳይቶናል።
ይህ አዲስ ነገር
መስሎ ቢታይም ካሁን በፊት ወያኔን የምንቃወም የትግራይ ተወላጆችም እኮ “ትግሬነታችን” ብቻ ሳይሆን 27 አመት ትግሬዎች ሥልጣን
ላይ ሲቆዩ ወደ እንደ ዜግነታችን ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ ወደ ተወልደንበት ትግራይ ክ/ሃገር ገብተን ያለምንም ስጋት መግባትና መውጣት
እንደማንችል እኮ እኔ ምሳሌ ነኝ። ስለዚህ ዜግንትና ነገድነታችን የተጣሰው ከወያኔ አገዛዝ ዘመን ጀምሮ ነው። ሕዝቡ አሁን ማድረግ
ያለበት በዚህ አየር መንገድ መጓዙን ያቁም።
ልደቱ ላይ የተፈጸመው አስናወሪ የዜግነት ጥቃት የሚመለከተው ተጠያቂው አብይ አሕመድ ነው። ዱርየው አብይ አሕመድ ፈረንጆች <<ኢቭል>> የሚሉት “እጅግ ቂመኛ” ነው። እቅንቅስቃሴን መገደብ ብቻ ሳይሆን ብዙ ሰዎች ኩሊዎቹን እያስላከ 6 አመት ሙሉ አስገድሏል። አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ።
ወደ ሃገራችሁ ኑ ብሏቸው በገርነታቸው ሃገር ሰላም ነው ብለው ተታልለው ወደ ሃገርቤት ከገቡት መካከል <<ኦነግን እና ወያኔን>> በመቃወም የታወቀው ድሮ ከሶቮየት ሕብረት ከሩሲያ የአምሐርኛ ቋንቋ ራዲዮ ፕሮግራም ጀማሪና አቅራቢ የነበረው የቅርብ ወዳጄ አንጋፋ <<ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ>> ወደ ሃገርቤት እሄዳለሁ ሲለኝ <<ሰውየውና ሁኔታው እስክናውቀው ድረስ ወደ ሃገር አትሂድ ትንሽ ቆይ>> ብየ በስልክ ተነጋግረን <<ግድየለም እስኪ ልሞክረው>> ብሎኝ አዲስ አባባ ከገባ ጥቂት ቃናት (እነማን እንደሆኑ ያልታወቁ) ለምሳ እንውጣ ብለው ወደ ቤት ሲመለስ “ደም ተፍቶ” በመርዝ የገደሉት አዲስ አበቤው የሎስቬጋስ ኔቫዳ ኗሪ የነበረው <<ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ>> በመርዝ ገድለውታል።
በዚህ ቂመኛ ዱርየ ሰው ቂመኛነቱ እንኳን ተቃዋሚው ; ትንሽ ከራሱ መስመር ወጣ ካለ የራሱ
ሰዎችን ሳይቀር ቂሙን የሚወጣበት መንገድ የሚፈልግ እርኩስ ፍጡር ነው። የራሱ ቀኝ እጆች የነበሩት <<ለማ መገርሳ፤ ጃዋር
መሐመድ፤በቀለ ገርባ፡ ….ወዘተ>> ላይ ሳይቀር ቁሙን የተወጣባቸው የተዋጣለት ዱርየ ሰው ነው።
ዛሬ ልደቱ ላይ የፈጸመው የዜግነት ጥሰት በራሱ ላይ መዘዝ ስቧል። ልደቱ በትግል ታሪኩ <<በሰላማዊ ሰልፍ ሕዝብ ጎዳናዎች ላይ አስሰልፎ እየመራ የወጣበት ሰላማዊ ሰልፍ>> መኖሩን ባላስታወስም “ልደቱ ወደ ሃገር ቤት ገብቶ እሰራዋለሁ ካለው የሰላማዊ ሰልፍ ይልቅ” “አብይ አሕመድ የልደቱ አያሌውን ዜግነት በመንጠቁ ምክንያት አብይ አሕመድ በራሱ ላይ የመዘዘው መዘዝ ይበልጥ የአብይ ዕርቃን በታሪክ ፊት ወጥቶ እንዲታይ ሆኗል”።
ይህ ልብልና ልደምድም፤
ይህ “የበሻሻ ዱርየ” የተቃዋሚዎችን ሬሳ ወደ ኤርትራ ምድር ተልኮ እንዳይቀበሩ የሚያግድ
የአስመራው ሻዕቢያ ኢሳያስ አፈወርቂን ባሕሪ በመላበስ ላይ ነው። ዜጎች ወደ ሃገር መግባት መከልከል ብቻ ሳይወስን ነገ የተቃዋሚዎችን
ሬሳ እንዳይገባ እንደሚያደርግ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሬሳም ጭምር መከልከሉ አይቀርም ፡ ያደረገዋል።
ይህ ጮርቃ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዜግነታቸውን በመንጠቅ ብቻ አልተወሰንም ኦርቶዶክሶችን <<ኦነጋዊያን ፖሊሶቹን በየጎዳናው በማሰማራት>> <<ማተባቸውና ሰንደቅዓላማቸው እንዲነጠቁ አድርጓል>>፡ <<አማርኛ ቋንቋም>> በኦሮምኛ ለመተካትና አማርኛን ለማጥፋት እየሰራ እንደሆነ በወኪሉ <<በሽመልስ አብዲሳ>> በኩል ተነግሮናል። አምሐራዎች ወደ ርዕሰ ከተማዋ ለሕክምናም ይሁን ለዘመድ ጥየቃ ወደ <<አዲስ አባባ>> እንዳይገቡም አግዷል። ለመግባት ከሞኮሩም <<አጋጅና አራጅ አዘጋጅቶ>> እንዲታረዱና እንዲታገዱ እያደረገ ነው። ዛሬ ልደቱን ወደ ሃገሩ እንዳይገባ መከልከሉን አሳዛኝና የሚያበሳጭ ቢሆንም <<አብይ አሕመድ የሥልጣኑን መጣያ ገመድ አንገቱ ላይ በገዛ ራሱ እየጠመጠመና መቀበሪያውም እየቆፈረ እንደሆነ ይታየኛል። ባጭር ጊዜም በፈጣሪ ፌርማ እንደ ጌታው መለስ ዜናዊ ከምድር በታች የሚቀበር ይመስለኛል>>። መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም ከመነጠቁ በፊት <<ሐዋርያ ጋዜጣ>> ላይ የባሕር በራችንን ያሳጣን መለስ ዜናዊ <<በፈጣሪ ትዕዛዝ ወደ ጥልቁ ወደ ኢትዮጵያ ሰማየ ሰማያት ይጠራል>> ብየ ነበር፤ የሆነውም ያ ነበር።
ሰላሙን ለናንተ
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment