የትሕነግ ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን መቀሌ
ውስጥ ያለው
ሃውልታቸውም ጭምር መፍረስ አለበት!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian
Semay)
የካቲት 11/2017
ዓ.ም
ፎቶግራፎቹ የመጀመርያው
ከግራ ወደ ቀኝ ባሕረይን የሚገኘው ዓረባዊ ሓውልት ሲሆን ከሃውልቱ ወደ ቀኝ በኩል የሚታየው እሳት፤ የባሕረይን ሕዝብ አብዮት
አስነስቶ ከሃውልቱ አደባባይ ላይ እሳት ለኩሶ በመሞቅ ሳምንት ተኝተው ሰላማዊ አብዮት ሲያስነሱ ገዢዎቹ በሕዝቡ ላይ መትረየስ
በመተኮስ ጭፍጨፋ ያካሄዱበት ወቅት ነበር። ቀጥሎ ያለው ሃውልት አልጀሪያ የሚገኘው ዓረባዊ ሐውልት ሲሆን ሦስተኛው ከነዚህ
የዓረብ ሓውልቶች ወያኔዎች የቀዱት መቀሌ ከተማ የቆመው ለእነ መለስ ዜናዊና የፋሺት ድርጅት (ህወሓት) ታጋዮች ለነበሩት መታሰቢያ ሓውልት ነው።
ወያኔዎች ኤርትራን
ለማስገንጠል፤ ኢትዮጵያን ባሕር-አልባ ለማድረግና ኢትዮጵያን በቋንቋ ሸንሽኖ <<ራስ ገዝ አፓርታይድ ክልሎችን>>
እና አምሐራንና አምሐርኛን እንዲሁም ዓድዋ ላይ ጣሊያን ሲሸነፍ የተውለበለበቺው ሰንደቅዓላማችንን ለማጥፋት የተመሠረቱበት 50ኛው
አመታቸው ዛሬ የካቲት 11 እያከበሩ ነው።
ርዕሱ ላይ
እንዳያችሁት ብዙዎቹ ትግሬዎች ይህንን ሲያነቡ እሳት ላይ እንደሚጠበስ ስጋ መንጨርጨራቸው አይቀርም።
ፋሺሰቶች ሲነኩ
የሚያሳዩት ባሕሪ ስለሆነ አይገርምም እና ትግራይ የኢትዮጵያ ክ/ሃገርነትዋ በሕግ ወይንም በጉልበት እስካልተሻረ ድረስ ወደ ኢትዮጵያዊ
ሥርዓት መግባትና ሃገር የማፍረስና ጥላቻን በሃውልት ቀርጾ ለትውልድ የሚያስተላልፉ ሕዝብ ለሕዝብ ቀጣይ ጦርነት የሚጭሩ በየገጠሩና
ከተሞች የተተከሉ ትግራይ ወስጥ የቆሙት ሃውልቶቻቸው መፍረስ አለባቸው።
ታጋዮቻችን የሚሉዋቸው ያልሆኑትን <ነበሩ> እያሉ
በውሸት እንደሚክቡዋቸው ለዲሞክራሲና
ለእኩልት የተሰው ሳይሆኑ የወያኔና የሻዕቢያ ተዋጊዎች ከትግራይ እና ኤርትራ ተራሮች ጀምረው “በጋራ” ኢትዮጵያዊያንን እየገደሉ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢትዮጵያ ሠራዊትን “ወራሪ” “አምሐራይ” እያሉ ከጣሊያን በባሰ መልኩ
ኢትዮጵያዊውን ሠራዊት 1ሚሊዮን የሚገመት “ሠራዊት
እና ቤተሰቦቻቸው” ያለምንም መጠለያና ምግብ ወደ ጎዳና በትኖ ባለማዕርግ መኮንኖች “ኮከባቸው መለዮአቸውን መሬት ላይ አንጥፈው”
ሳንቲም እንዲለምኑ ያደረጉ የፋሺስት አለቆቻቸው ድርጊት ፈጻሚ ታጋዮች የነበሩ ናቸው።
ያልተሰውት የተቀሩት በህይወት ያሉት መሰል ታጋዮችም
ፋሺቱ መሪያቸው መለስ ዜናዊ ሲሞት ደም ዕምባ ያለቀሱ ፡ በፋሺሰት የደህንነት አለቆቻቸው እየታዘዙ አምሐራ የተባለው ምሁር እና
ኢትዮጵያዊነቱ በጽናት የያዘ የትግራይ ተወላጅ “ጸረ ወያኔ ነው እያሉ” ለቁጥር የሚያዳግት ግድያና ድብደባ በመፈጸም ተሳዳጁን
እንደ ጅግራ እመሃል ከተማ እያደኑ እንደ እነ አሰፋ ማሩ
የመሳሰሉትም ኢትዮጵያዊያን በጠራራ ጸሐይ አደባባይ ላይ ነጻ እርምጃ ሲወስዱ የነበሩ የግድያና የእስር ድርጊት ፈጻሚዎች እንጂ
ተሰው የሚሉዋቸውም ሆኑ በህይወት ያሉት ተጋዮች ካንድ ኩሬ “ከትግራይ የፋሺሰት ርዕዮት” የተቀዱ የፋሺስቶች ታዛዥ ተዋጊዎች እንጂ
<<ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ>> የታገሉ ታጋዮች አልነበሩም።
እነዚህን ታጣቂዎች አሰማርቶ ኢትዮጵያ የተሰራቺበት
ድር እና ማግዋን ጥንታዊ ክሮችዋን እንዲበጣጠስና እርስ በርስ እንዲፋጅ ኢትዮጵያ አሁን ላለቺበት መከራ የዳረጉ ይህንን የፈጸሙ
የወያኔ ትግሬ መሪዎችና ተዋጊዎች ቢያንስ ራሳቸውን ለፍርድ አቅርበው ይቅርታ ባይጠይቁም ራሳቸው እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው
የሚቆጥሩ ከሆነ የተጓዙት መንገድና ድርጊት አውግዘው መቀሌ ላይ የቆመው ሃውልትና በየከተማውና ገጠር ጋራ ሸንተረሩ ያቆሙዋቸው
የጥላቻ ቀስቃሽ ሃውልቶች እንዲፈርሱ አቋም መያዝ አለባቸው።
የኤርትራ የሽምቅ
ተዋጊ ሃይላት ስሜት በመኮረጅ ቀ.ሃ.ስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አክራሪ የትግራዋይነት ስሜት በማጎልበት
7ቱ የትግሬ ወጣት ተማሪዎች የመሠረቱት የ1967 ዓ.ም የትሓህት ሽምቅ ተዋጊ ድርጅት መሰረታዊ መነሻው ምንድ ነው?
መነሻቸው ልክ
እንደ ኤርትራኖቹ ለግንጣላ በድምጽ ብልጫ የትግራይ ሕዝብ አስፈቅዶ
ከኢትዮጵያ ለመገንጠል- (ሬፈረንደምና ፈቃድ እንደምታውቁት “ሽፋን” እንጂ ወያኔ አድርግ ያሉት የሚያደርግ ሕዝብ እንደነበርና አሁንም
እንደሆነ የምታውቁት ነው። ሆኖም ሥልጣኑንና ሃብቱን ተቆጣጠሩና ያንን ዕቅድ አዘገዩት) ለዚህም መነሻቸው <<አምሐራንና
ኢትዮጵያን ከነ ሰንደቅዓላማዋ እንደ ጠላት ቆጥረው>> ወደ ደደቢት በረሃ የወጡ ፤ ትምህርታቸው በቅጡ ያላጠናቀቁ
ተማሪዎች ናቸው።
መስራቾቹ እነማን ነበሩ? <<ልባቸው በኤርትራነት ፍቅር የተማረከ ፤ ሙሉ በሙሉ ከኤርትራ ወላጆች የተወለዱ ፤ ሦስቱ ወይንም አራቱ ከትግራይ ወላጆች የተገኙ፤ ወይንም አስመራ ያደጉ ኤርትራዊ ገንጣይ ባሕሪ የተላበሱ፤ ወይንም ግማሽ በግማሽ ትግሬና ኤርትራ ፤ እንዲሁም የድርጅቱ ዋና ምሐንዲስ የነበረው ከጊዜ በኋላ ወደ “ትግሬነት” የተለወጠው <<ከአምሐራው ጎጃሜው የደ/ዝማች አስረስ ተሰማ ልጅ ከሆኑት አቶ ዜናዊ አስረስ እና ከኤርትራዊትዋ ወ/ሮ አለማሽ ገብረልዑል የተወለደ ሟቹ መለስ ዜናዊ የመሳሰሉ ጸረ አምሐራ የሆኑ ፋሺስቶች የመሰረቱትና የገነቡት ድርጅት ነው።
ሃውልቱ ለነ
መለስ ዜናዊ ቆየት ብሎም ሞት እየጎተታቸው ለሚገኙት በትግራይ ወጣቶች ነብስ ሲጫወቱ የነበሩት ለወንጀለኞቹ ለነ ስብሐት ነጋ እና
ዛሬም “ሸዋ” የሚል ቃል ከምላሳቸው የማይለየው የወያኔ ታጣቂ “አዋጊዎች”
እና የፋሺዝም ትግራዋይነት ፖለቲካውን የሚዘውሩት ለእነ ደብረጽዮን፤ ጌታቸው ረዳ ፤ ሞንጆሪኖ ፤ ቴድሮስ ሐጎስ… የመሳሰሉ ጸረ
አምሐራና ኢትዮጵያ ግለሰቦች ሲሞቱ በማስታወሻነት ፎቶግራፋቸው የሚለጠፍበት የፋሺቶች ሐውልት ነው። ለነዚህ ነው የተተከለው።
ሃውልቱ የቆመላቸው
ታጋዮቹም መሪዎችም <<ገመናቸው>> ስንፈትሽና ትግላቸው ስንመረምር <<በወንጀል የተጨማለቁ፤ በጭፍጨፋ
፤ሃገር በመክዳት ፤ ኤርትራን በማስገንጠል እቦታው ድረስ ሄደው የተገደሉና የገደሉ ፤ ለኢትዮጵያዊነት ሳይሆን የወያኔ ድርጅት
ባንዴራ እያውለበለቡ ኢትዮጵያዊነታቸው ከድተው ለትግራዋይነት የበላይነት ዓላማ “የተሰው” የነ ስብሓት እና የነመለስ ዜናዊ ሎሌዎች ነበሩ።
በአመለካከት
የተቃወማቸው ሁሉ በየገጠሩና በየከተማው እየገቡ እንደ ጅግራ እያደኑ ዜጎችን ሲያሸብሩ የነበሩ <<ማፊዮዚ>>
‘የነብሰገዳይ ድርጅት’ ተዋጊዎችና ተላላኪዎች የነበሩ ናቸው (የራሴው ዘመዶቼም ጭምር)።
ኢትዮጵያ ወታደሮችን
ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነታቸውን አጥብቀው ያደመቁ ሃገር ወዳድ ኤርትራዊያን ከከሓዲዎቹና አምሐራን በጠላትነትን ከፈረጁ በስሜት ከሚጋልቡ
ደናቁርት የኤርትራ ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር አብረው መረጃ በመስጠትና በማሳፈን አሳልፈው ሲሰጡ የነበሩ ፤ እንዲሁም ዓድዋ ከጣሊያኖች
ጋር ጦርነት ሲደረግ በድል የተወጣችውን ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ያውለበለቡዋት ሰንደቅዓላማችንን ጨርቅ ነው ብሎ ኮከባዊ የሰይጣን አምልኮ ያለበትን ምልክት በማድረግ
ሃገሪቱ ውስጥ 44 ባንዴራዎች እንዲወለበሉና “እንድትዋጥ” በማድረግ የሃገራችን ኩራት የሆነቺውን የወላጆቻችን ዓርማ ከኢትዮጵያዊያን
ገላ የገፈፉ ባንዳዎች እንጂ ኢትዮጵያዊ ታጋዮች አልነበሩም።
አስተዋይ ጀርመኖች
ሃገራቸው ከናዚ አመለካከት እንድትጸዳ ለናዚ ታጋዮችና መሪዎች የተተከሉ ሃውልቶች እንዲገረሰሱ ወይንም ወደ ሚዚዮም እንዲታሸጉና
ናዚያዊነትን ከሕዝቡ ሕሊና ለማፅዳት ሞክረዋል።
ቤተ መፃህፍት፣
መጽሃፍቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉንም የናዚ ፕሮፓጋንዳ ቁሳቁሶችን እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል።
በተመሳሳይ ትግራይ ውስጥ በየትምህርት ቤቶችና መዋዕለ ህጻናት፤ በየሕክምና ተቋማትና ቤተ እምነቶች የወያኔ ናዚ ፓርቲ የሚያወድሱ መጽሐፈቶች፤ ግጥሞች፤ ዘፈኖች፤ መጽሔቶች፤ ጋዜጦች፤ ፖስተሮች፣ ሐውልቶች፣ በማን አለኝነት ጥንታዊ ስሞችን በመሰረዝ በታጋዮቻቸው ስም የተሰየሙት ሃውልቶች የመንገድ ስሞች ምልክቶች እና አርማዎች በሙሉ ተሰብስበው ወደ ማጎርያ ሙዚየም መታጎር ወይንም መፍረስ ወይንም መቃጠል አለባቸው።
በሚያሳዝን ሁኔታ ጥንታዊ ጥናት ለማካሄድ ወደ ትግራይ የሚሄዱ የውጭና የሃገር
የታሪክ ተመራማሪዎችና ጸሐፍቶች በሚያደናግር መልኩ “በአዳዲስ ስሞች” ብዙ ሸለቆች፤ መንደሮች፤ ገጠሮች ፤ ተራሮች፤ ሜዳዎችና ወንዞች”
በታጋዮቻቸው ስም በመሰየማቸው ተመራማሪዎቹ ችግር እንደሚገጥማቸው እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ለወደፊቱ ተመራማሪዎችን ከማደናገሩ በፊት
ያንን ችግር ከማስከተሉ በፊት የተሰየሙት ተጠንተው እንደገና ወደ ጥንታዊ ስሞቻቸው መለወጥ አለባቸው። ትግራይ የወያኔ ድርጅት ተከታዮች ንብረት ብቻ አይደለችም፡
የወያኔ ተቃዋሚዎች የሆንን የኛም የትውልድ
ቦታችንም ነችና ድምጻችን መሰማት አለበት!
ከተሰውት ታጋዮቻቸው
ደምቆ በግዙፍ ፎቶግራፍ በሃውልቱ አዳራሽ የተለጠፈለት የዚህ ድርጅት መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ያለ ባሕር በር እንድትቀር
ማመልከቻ ጽፎ ለእናት መንደሩ ለኤርትራ ወግኖ የተጫወተው ወንጀለኛው መለስ ዜናዊና መሰሎቹ እንዴት ሲሆን ነው ለነዚህ ከሃዲዎች
ሃውልት ቆሞላቸው “ሰማዕታት” ተብለው መዘከር የሚኖርባቸው?
የትግራይ ሕዝብ
ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ከሆነ <<ሃገር ያስደፈሩ ባንዳ ነብሰገዳዮችና ዘራፊዎችን ማውገዝ አለበት>> ካልሆነ አይደለሁም
ካለም ወያነ ማለት እኛ ነን እኛ ማለት ወያኔ ማለት ነው፤ ስለዚህ የወንጀሉ ተባባሪ ነን የሚለው እውን ሊሆን ነው።የሆነውም ያ ነው።
ሃውልቱ ቆሞላቸዋል
የተባለላቸው ታጋዮች ምንም የታሪክና የፖለቲካ ምጥቀት ያልነበራቸው ታጋዮቻቸውም በውሸት <<ለዲሞክራሲና
እኩልነት ሲሉ የተሰው ናቸው>> እየተባለ ለነ መለስ ዜናዊና ለታጋይ አሽከሮቹ ሲዋሽላቸው ስሰማ የትግሬዎቹ እውነታን
የማዛባት ባሕሪ መቸ እንደሚቆም ሁሌም ይገረምኛል።
ታጋዮች ሲባልላቸው
የነበሩት እኮ ብዙዎቹ እናውቃቸዋለን። ዲሞክራሲና እኩልነት ምን ማለት እንደሆነ የማያውቁ በህጻንነታቸው ወደ ትግሉ የገቡ
“ሰው ሲገድሉና ሲገርፉ” የነበሩ የፋሺሰቱ የነ ስብሓትና የመለስ ዜናዊ ታዛዥ ተዋጋዎች ሲፈጽሟቸውና ሲዘፍኑዋቸው ከነበሩት
መልዕክቶች አኳያ የዲሞክራሲና የዕኩልነት የሚያስተላልፍ መልዕክት አልነበረም።
ይህ አጽንኦት
የሚሰጠው ለዲሞክራሲና ለዕኩልነት ነበር የተዋጉት የሚባልላቸው ተዋጊዎች ምን ሲያደርጉ እንደነበር እኮ እናውቃለን። ታሪካቸው አንብበናል፤
በአካል አይተናቸዋል፤ አወያይተናቸዋል፤ ስሜታቸው አንብበናል፤ አምሐራ ማለት ምን ማለት አንደሆነ ሲተረጉሙት፤ካንደበታቸው የሚወጣ
አስጸያፊ ቃል አድምጠናል፤ ፍጹም ፤ እየተባለላቸው የነበረው ያልነበሩ ፤ “ግደል ሲባሉ የሚገድሉ፤ ደብድብ ፤ እሰር ፤ አሰቃይ”
ሲባሉ የሚፈጽሙ፤ አባት እህት ወንድም ግደሉ ሲባሉ ቤተሰቦቻው ሲገድሉ የነበሩ Cambodia’s Khmer Rouge; የካምቦዲያ
ኸመሩዥ ኮሚኒሰትና ፋሺስት ተዋጊ ዓይነት ገራፊዎችና በየገጠሩና በየከተማው በሕዝቡ ሕይወት ላይ ሽብር የሚለቁ የፋሺሰት ድርጅት
የሽብርና የጥፋት ታጋዮች የነበሩ ናቸው።
እዚህ
ሥልጣን ከያዙ አዲስ አበባ እንኳ ኢትዮጵያዊነታቸው አጥብቀው ለያዙ ዶ/ር ሃይሉ አርአያ ስለ ትግሬ መርማሪዎችና ፖሊሶች ምን
እንዳሉ ታስታውሳላችሁ።
<<…ከቤቴ እየደበደቡና እየተሳደቡ የወሰዱኝ የትግራይ ልጆች ነበሩ። ማዕከላዊ እንደደረስኩ ቀበቶዬን ያስፈታኝ የትግራይ ሰው ነው። ከእርሱ ተቀብሎ አንድ የፍሪጅ ያህል የሚቀዘቅዝ ክፍል አስገብቶ የቆለፈብኝ የትግራይ ሰው ነው። ሲመሽ ሽንት ቤት ወስዶ ያሸናኝ ሰው የትግራይ ሰው ነው።እየተሳደበ ቃሌን የተቀበለኝ የትግራይ ሰው ነው።በእርግጥ እኔ የትግራይ ሰው ሆኜ ከአንድ አካባቢ በወጡ ሰዎች ጥቃት እየደረሰብኝ እንደሆነ ከተሰማኝ ሌላው ሰው ምን ሊሰማው እንደሚችል አስቤ ለትግራይ ህዝብ ከልቤ አዘንኩለት። ይሄ ሁሉ የሚደረገው ለትግራይ ህዝብ ሲባል ነው መባሉ ደግሞ የበለጠ ሰላሜን ነሳው።>>
ይህን ምስክርነት የሰጡት የትግራይ ተወላጁ የቅንጅት ፓርቲ
አመራር የነበሩት ዶክተር ሃይሉ አርአያ ናቸው ። ተሰው ተብለው
ሃውልት የቆመላቸው ታጋዮች በሕይወት ዛሬ ቢኖሩ ኖሮ ከነዚህ አረመኔ ፖሊሶችና መርማሪዎች የሚለዩ አይሆኑም ነበር።
መቀሌ ውስጥ
የቆመው ጸረ ኢትዮጵያ የጥላቻ ሃውልት ለታጋዮቹ መዘክር በሚል ሽፋን የተገነባ ይሁን እንጂ ዋና ተልዕኮው <<በትግሬና
ኢትዮጵያ አስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ በታጠቁ ታጋዮች፤ በትግራይ ምሁራን
እና ጋዜጠኞች “ሸዋ”
የሚለው ቃል ዛሬም በየንግግራቸው ሲደነቅሩት የሚታይ የማይበርድ ቀጣይ የአምሐራ ሕዝብ ጥላቻና ጸረ <<ብሔረ ኢትዮጵያ>>
የሆነ “ግጭትና ጦርነት በዘላቂ ለማስቀጠል የቆመ” የወያኔ መሪዎች ያቆሙት የጥላቻ ሃውልት ነው።
ሃውልት አቁመናል፤ በየሰልፉ ለታጋዮች የደቂቃ ጸሎት እናድርግ እያሉ ሕዝብን
ለማታለል የሚጠቀሙበት ማታለያ ዘዴ ካልሆነ በቀር በሕይወት ያሉ በትግሉ ቆስለው እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ ጥይት ከገላቸው ውስጥ ተሰክቶ
የቀረ “ስራ የሌላቸው” የራሴ ወንደሞችና ዘመዶች ፤ በየ ስብስባው ለፕሮፓጋንዳ ማሳመርያ የሚያደርጉት <ዝኽሪ ንስውኣትና> (ለታጋዮቻችን
የሕሊና ፀሎት) እያሉ በውሸት የሚጸልዩት ማታለያ “ፀሎት” የሚያደርሱትም ሆኑ እነ ስብሓትና እነ ደብረጽዮን”
ሳይሆኑ የሚረድዋቸው እኔ ካለኝ ጥቂት ገንዘብ እየላኩኝ ነው ኑሮአቸው የሚገፉት። የነዚህ ፀሎት አድራሾች እውነታ ግን <<ዛሬም
ሂድና ሙት ቁሰል ትግራይ ትዕወት>> እያሉ ወጣቱን ማስጨረስ ነው። በመሪነት የተቀመጡትም የመሪዎቹ ልጆችና ዘመዶች
ግን በየፈረንጅ እና ቻይና ሃገር እያላኩ በምቾት አስተምረዋል፤ሃብት ገንብተዋል። <<ለማያውቅሽ ታጠኚ>> የሚባለውም
ለዚህ ነው።
ለዚህ ነው
ድሕረ ናዚ “ጀርመን እንዳደረገቺው” ኢትዮጵያም <<ኢትዮጵያዊ መሪ ስታገኝ>> ሃውልቱ ከስሩ ተደርምሶና ደቅቆ
ወደ ቆሻሻ መጣያ መጣል እንዳለበት ለብዙ አመት የምወተውተው።
አንድ ዘመዶቹ
በግፍ የገደሉበት እስከዛሬ ድረስ ምንም ፍትሕ ያላገኘና ወያኔዎችን መከስስ የማይቻልባት ትግራይ ውስጥ የሚኖር ስሙን ለመግለጽ የማልፈልገው
ሰው ፤ ባንድ አጋጣሚ ለጉብኝት እዚህ አሜሪካ መጥቶ ያነጋገርኩት አንድ የትግራይ ልጅ ስለ ሃውልቱ አንስቶ ሲያጫውተኝ፤ እንዲህ
ይላል፡
<<መቀሌ ጎዳናዎች ስዘዋወር የማያቸው የወያኔ አርማዎችና በተለይ ሃውልቱን ስመለከት በቦምብ የማጋየት ስሜት
ይጫነኛል።የቤተሰበቼ ደም ከንቱ ቀርቶ ገዳዮቹ ሃውልተ ቆሞላቸው ሳይ ብሶቴ ያስቸግረኛል፤ በተለይ ደግሞ እዚህ ውጭ አገር ሆነው የሃወልቱ ምስል
በየ ዩቱባቸው ለጥፈው ስመለከት የቤተሰቦቼ ገዳይ ድርጅት ተባባሪዎች ሆነው ሳያቸው በሰለጠነ ሃገር የመኖር ትርጉሙ “ኮንሴፕቱ” ሊገባ አልችል ብሎኝ ሁሌም አስባለሁ>>
ሲል ምሬቱን አጫውቶኛል።
በሚያስገርም
ሁኔታ ይህ ድርጅት ላለፉት 50 አመት ያመጣልን ምን በጎ ነገር አለ? ብሎ የጠየቀ የትግራይ ሕዝብና ምሁር አላየሁም። ሞት፤አካለ
ስንኩልነት ፤ ብጥብጥ፤ እርዛት፤ ውርደት፤ የባሕር ማጣት፤ ዘረኛነት፤ ሃገር አልባነትና ስደተኛነት “የወያነ ትግራይ” የትግል
ውጤት እንደሆነ ፍጹም ሊታያቸው አልቻለም።
በቅርቡ ከስንት
ውርደትና አካለ ስንኩልነት በኋላ ፤ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ ድርጅት ጋር ላለመቀጠል ዛሬ በቅርቡ አንዳንድ ትንሽየ ነጸብራቅ
እንኳ ቢታይም 99.9% ሕዝቡ የድርጅቱ “ባርያ” ሆኖ ለመቀጠል የወሰነ
ነው። ካደመጥኳቸው የወያኔ የበላይ አመራሮች ከነበሩት ሁሉ በተለየ ገምቢ አዲስ አስተሳሰብ ይዞ የመጣ አብሮ አደጌ <<ሳሞራ የኑስ>> (ጀነራል) ነው። አክራሪ ብሔረተኛነት ጭንቅላትዋ
ያሰከረው “ብራኸ ሾው” (ከፍታ) በማለት የምታዘጋጅ መድህን ገ/ስላሴ የተባለች የሚዲያው ባለቤት ሳሞራን ለመመለስ ስትጥር አልሆን
ብሏት ስትጨስ ያየናት ስትጠይቀው ሳሞራም፤-
“ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ጦርነት የሚያስኬድ ነገር ሁሉ “ፉከራም
ጭምር” ቀዳዳውን ሁሉ መድፈን አለብን ፤ ጦርነት ምን እንደሆነ አውቃለሁ፤ ጦርነት መርቻለሁ፤ አሁን ግን ስለ ሰላም መታገል እና
መስበክ አለብን፤ ካጎረባች ክልሎች ጋር ሰላም እንዴት እንደምናመጣ ማትኮር አለብን፤ ከጦርነት በመለስ ፤ ስለ ሰላም ብዙ መክፈልና
መታገል አለብን፡ወደራሳችን ከማየት ይልቅ ወደ ሁለተኛ ውጫዊ አካል በመመልከት አዙሪት ውስጥ መሽከርክር የለብንም፤ ከዚያ
እንውጣ!…>>
ሲል በሚገርምና በሚመሰገን ሃሳብ ከተቀሩት ደናቁርት የትግራይ ምሁራንና መሪዎች
ገንኖና ደምቆ የወጣ አክሱማዊው ሳሞራ የኑስ ነው።>> ለዚህ ቆቤን በአድናቆት አንስቼለታለሁ።
ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ተቃወመ እያሉ ሕዝቡ ለሁለት ስለከፈሉት የወያኔ መሪዎች ደጋፊና ተቃዋሚ ሆኖ በመታየቱ ብቻ <<ወያኔን የተቃወመ እየመሰላቸው ብዙ የሚያስጮሁት ሚዲያዎች ስሰማ የትግራይ ማሕበረሰብ ዛሬም የወያኔ ባንዴራ እያውለበሰበ በየ አደባባዩ ሲወጣ መልዕክቱ ምን እንደሆነ እንኳ ሚዲያዎች ሊረዱት አልቻሉም።
ማሕበረሰቡ
በብዛት ወጣት ነው። ይህ ወጣት ደግሞ የወያኔ ጡት (ፖለቲካ) እየጠባ ማደጉና ወያኔ ማለት የማይረሳ የናቱ ጡት መሆኑን ምን እንደሚል ላስደምጣችሁና
ልቀጥል፡
መቀሌ ውስጥ በትምክሕት ሲጨፈር የነበረውን የተለመደው የመቀሌ የእንደርታዎቹ የዘፈን ጭፈራ ንግግር በቪዲዮ የተቀረጸው በደስታ የቀለጠው ትምክሕታዊ የደስታ ጭፈራ እንዲህ ይላል፦
“ናዓና ዝመስል የለን” (እኛን የሚመስል
ተወዳዳሪ የለም) ፤ “ትግራዋይ
ዝመስል ባዓል ስረ የለን” (ትግሬን የሚያክል
ባለ ሱሪ ወንድ
የለም) ፤ “ሃ! ሁ! ምስ ወየነ እየ ዝዓበኹ)
፤ (ሃ! ሁ! ከወያኔ
ጉያ ነው ያደጉት!) “ሃ! ሁ~ ወያነ እንዳበልኩ
እየ ዝዐበኹ” (፤ ሃ! ሁ! ወያኔ
እያልኩ ነው ያደግኩት) …መቐለ ፤መቐለ!!! (መቀሌ! መቀሌ!)
“ናይና! ናይና ናይና!!” (የኛ ነች የኛ!!) “ኣየኹም ናይና!!”
(የኛዎቹ ኣይዝዋችሁ!!)
ይህ ወጣት
ነው ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ሚዲያዎች በተሳሰተ ድምዳሜ ደርሰው <<የትግራይ ሕዝብ ጦርነት ይብቃን አለ፤ ወያኔ ተቃወመ>>
እያሉ የሚዘግቡት፤ ጦርነት ይብቃን ስላለ ብቻ “የወያኔ ርዕዮት” ተቃወመ ወይንም የወያኔ መለያና አርማ ጣለ አወገዘ ማለት አይደለም። የናዚ ወጣቶች ጦርነት ይብቃ ብለው የስዋስቲካ ምልክትና
የሂትለር ዓርማ ካልጣሉ “ዞር አሉ አልሸሹም ነው”።ናዚ ወይንም ፋሺዝም የሚኖርበት ፍልስፍና ትዕቢትና እኛ ማን
አህሎኝነትና ጦርነት በመቆስቆስ ነው። ስለሆነም ትግሬዎች ፍኖተ ካርታቸው ካላስወገዱት፤ ጦርነት ስለተቃወሙ ብቻ ፤ እስኪደላደሉ
እንጂ ያ ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ አይሆንም። ፈረንጆች እንደሚሉት ፖለቲካቸው ካላስተካከሉት <<ጋርቤጅ ኢን ጋርቤጅ አውት>> (ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ)
ዓይነት ነው።
ስለሆነም ነው
ይህ የወያኔ ጡት እየጠባ ያደገ የወያኔ ሎሌ እራሱን ለማዳን ስንጥርና ስንታገልለት እጅግ ከባድ የሆነብን።
አሳዛኝና ከባድ
ያደረገው ደግሞ ምሁራኖቻቸው ከተከታዩ ወጣት የባሱ አሁን ወዳለው የድህነትና የሞት ሳጥን ለምን ከተትነው ለምን እንዴትስ ሊሆን
ቻለ? የሚለው መነሻ ለመፈተሽ ወደራሳቸው ከማየት ይልቅ ወደ ሁለተኛ ውጫዊ አካል በመመልከት አዙሪት ውስጥ ሲሽከረከሩ እናያለን።
አንዳንዱ የትግራይ ምሁር ደግሞ በጥላቻ የዛገ ልቦናው ከማጽዳት ይልቅ እንዳበዱ “እንደ ራቢድ” ውሻ የግንጠላ ፖለቲካ ላማስቀጠል በየሚዲያውና ሕዝባዊ ስበሰባ
ሲቅነዘነዙ እናደምጣቸዋለን።
ከባዱ ነገር
እነዚህ ምሁራን ከወያኔ ባርነት ላለመውጣት የሙጥኝ ብሎ ራሱን እገድላለሁ ከሚል “ከሰልፍ ሱሳይደር” በሽተኛ ሰው እንዴት ማስጣል እንደሚቻል የከበደ
ያህል ነው እየተጋፈጥነው ያለው የትግል ዓይነት።
50 አመት ሙሉ ያለሰቀቀን ሳትረበሽ ያሻህን ተናግረህ ነፃነትህን ጠብቀህ ትግራይ ውስጥ መኖር አይቻልም። የወያኔ
ባርያ ካልሆንክ ትግራይ ውስጥ ለመኖርና የትግራይ ተወላጅነትህ ሳትነጠቅ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባበት ብቸኛው መንገድ የ“ትሕነግ”
(TPLF) ፓርቲ አባል ሆኖ መቀላቀል ወይንም አጨብጫቢ ሆኖ ዝምታን መርጦ እንደ ልብህ ትግራይ መግባትና መውጣት እንድትችል፤ ከግድያና
ከመገለል ወይም ተሰውሮ ከመጥፋትና ንብረትህ ከማስወረስ ያለህ ብቸኛ መንገድ ያንን መምረጥ ነበር።
አሁንም ከነበራቸው
አስተሳሰብ ኢንች ፈቀቅ አላሉም። አልተለወጡም (የተቃወማቸው ሁሉ ዛሬም ይገድሉታል (የዘፋኙና በሙያው ኮምፕዩተር ኢንጂነር የሆነው የእምብዛ ታደሰን ገላ ቆራርጠው እንዴት
እንደገደሉት የሚታወስ ነው፡ የፈንቅሉ የማነ ንጉሴ አገዳደልና ሌሎቹም እንዲሁ የሚያመላክተን ዛሬም “TPLF” “ትሕነግን” መቃወም
ለሞት እንደሚያበቃ ነው) ።
እኔ እንደ ትግሬነቴ፤ትግራይ ውስጥ በአካል ተገኝቼ ቀርቶ
ነፃነት ባለባቸው ውጭ አገር እየኖርኩም እንኳ፤ በደናቁርት ውሾቻቸው አማካኝነት ድርጅታቸውን በመቃወሜ “ዛቻ፤ መገለል፤ስድብ እና
የትግሬ ተወላጅነቴን ማንነቴ መነጠቅ ወዘተ..ወዘተ” የመሳሰሉ የመብት
ጥሰቶች ደርሰውብኛል።
ባጭሩ ትግራይን በሚመለከት የመሰለኝን ድምፅ የመስጠት መብቴ
የተነጠቅኩኝ ሰው ነኝ። ሆኖም ስለታገልኳቸውና ግላዊ ነፃነት ስለተሰማኝም
ደስ ብሎኝ እኮራለሁ።
ከብዙ አመታት በፊት << የትግራይ
One-size-fits-all አጭበርባሪ ፖለቲካ>> የሚል
አንድ ጽሑፍ አሰራጭቼ በድረገጾች ተልጥፎ መኖሩን አስታውሳለሁ። <<የትግሬዎች One-size-fits-all
ፖለቲካ>> ሁሉም አስተያየት የሚያስተናግድ ድርጅት ነው ይበል እንጂ እንደ እስላማዊ ሃይማኖት አንዴ ከገቡ
በቁርአናቸው መውጣት እንደማይፈቀድ ሁሉ ከወጣም ደግሞ “ኢንፊደል/ኩፋር/ ተብሎ እንደሚገደል ሁሉ፤ በወያኔ አጠራር ከድርጅት ያፈነገጠ
ወይንም የጠየቀ “ጠላም” (ከሐዲ) ወይንም ሽዋዊያን ተጋሩ (የሸዋ ትግሬ) ተብሎ ተይዞ ይሰየፋል ፤ይደበደባል
ወይንም ደብዛው ይጠፋል።
ድርጅቱ እጅግ አክራሪ በመሆኑ ለክቶ ከሰፋው የትግሬነት ፓለቲካ ጥቡቆ ውጭ ስለ “የኢትዮጵያ ደህንነትና
ሰንደቅዓላማ” ጥብቅና ቆሞ የሚጠይቅ ታጋይም ሆነ እንደ እኔው ያለ ተራው ሕዝብ ይህንን የመሰለ ክርክር ይዞ መጋፈጥ ጠላት ተብሎ
ለሞትና ለመገለል እንደሚዳርግ እኔ ህያው ምስክር ነኝ። ፍትሕ በሌለው የሞትና የመሰወር እርምጃ የሚወስዱት ደግሞ እነሆ
ጀግኖች ተብለው መቀሌ ውስጥ ሃውልት የቆመላቸው ለፋሽት ርዕዮት የቆሙ አሁን ያሉት እና የተሰው የፋሺሰቶች የዙፋን በር ጠባቂዎች
የነበሩ ናቸው።
ይህ ትግራይ መቀሌ ውስጥ የተተከለው የነ መለስ ዜናዊ ሐውልት መታሰቢያነቱ <<ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን የሚያስታውስ>> ሳይሆን በጣሊያን እና በትግሬዎች መካከል የተካሄደ ጦርነተና የቆመ መታሰቢያ ሆኖ የተመሰለ ተምሳሌት ነው።
ሃውልት ይቁም ከተባለም <በወያኔዎች ግፍ የተገደሉና ደብዛቸው የጠፋ>> የሚል ሃውልት መቀሌ ውስጥ ይቁም። ሃውልቱ ማጠቃለል ያለበት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መብት የተዋደቁ የባሕር ወደቦችን ለማስከበር ኤርትራ ሳሕል ተራሮች ላይ መስዋዕት ለከፈሉ በወያኔ ታጋዮች የተገደሉ ጀግኖች እና በመለስ ዜናዊና በትሕነግ አመራር አባሎችና የድርጅቱ “ሓለዋ ወያነ” (በድርጅት ደህንነት ጥበቃ) አባላት በየገጠሩና በየከተማው በግፍ ለተገደሉ ደብዛቸው ለጠፋ ወጣት የትግራይ ታጋዮችም ሆኑ ድርጅቱን የተቃወሙ አረጋውያን እና ወጣት ምሁራን የትግራይ ተወላጆች፤
እንዲሁም በወያኔዎች ግፍ የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ “ሳንፈልጋቸው 27 አመታቸው!” ብሎ የተፋቸው ሥልጣን ላይ በቆየባቸው 27 አመት
ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ በወያኔ የደህንነት አባላት የተሰወሩ፤ አሰቃቂ ድብደባ ፤ ግድያና ጭፍጨፋ ለተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን
ጭምር ከወያኔ ሃውልት ጎን ለጎን ሌላ ሃውልት ይቁም።
ስለዚህም ነው ሃውልታቸው “ፀረ መብት፤ ፀረ አምሐራና ፀረ ኢትዮጵያ ትግላቸው” መልሶ መላልሶ የሚያስታውሰን፤
ለሃገር አንድነት ያልቆሙ ፤ <<ተጋዳላይ
ትግራይ አርኪብካ በሎ ነቲ ዓሻ አምሓራይ>> የሚለው መዝሙራቸው፤ ጭካኔያቸው ፤ ጭፈራቸውና መራራ ጥላቻቸው
ወደ ትውስታችን አምጥቶ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ዳግም የውስጥ ምሬትና ቁጭት ስለሚቀሰቅስ እርስ በርስ ዳግም ጸብ ላለመቀስቀስ መፍረስ
አለበት።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment