በወያኔ ታጋይ ምስል የጎጃም ፋኖን ማሸብረቅ ለምን ተፈለገ?
ከጌታቸው
ረዳ
2/23/22
ሌባው የፌስቡክ ዘራፊ Gizachew Menber Hi ይባላል ከድረገጼ የዘረፈው ምስል ታሪክ ላውጋችሁ!
በስዕሉ የምታዩት ፎቶግራፍ የወያኔ ታጋይ <<አማረ ታረቀ>> ይባላል።
ስለ አማረ ታረቀ ታሪክ በፌስቡኬና በድረገጼ ላይ ያቀረብኩበት ምክንያት
<<ኡር-ፋሺዝም የወያኔ ታጋዮች እውነተኛ መገለጫ>> በሚል ርዕስ12/23/2022 የ ኡር ፋሺዝም (Ur Fascism) ባሕሪ ምንነት ለመግልጽ የተጠቀምኩበት ምስል ነበር። ምስሉን ያገኘሁ በወያኔዎች
ከሚታተሙ ከጋዜጣና ከመጽሔቶቻቸው ለብዙ አመታት ካጠራቀምኩዋቸው ከቆየው የፎቶ ማጠራቀሚያ ሰነዶቼ ላይ ነው።
ታዲያ አለመታደል ሆኖ ሞራለ ቢስ የሆነ አዲሱ ትውልድ ሌባና አጭበርባሪ በብዛት የተፈለፈለበት ወራዳ ትውልድ በመሆኑ
የዘመኑ ጥበብ ይዞት የመጣው “ፌስቡክ” ለዘራፊም ለሌባም ለአጭበርባሪም ሁሉ በነጻ የተፈቀደ መድረክ ስለሆነ ፤ <<ኦርቶዶክስ
ተከታይ መስሎ>> <<የማርያምን
ስዕል>> በፌስቡክ ፕሮፋይሉ (መለያ) ለጥፎ አትስረቅ የሚለውን ትዕዛዝ ተላልፎ በሃይማኖት የሚነግድ
አስመሳይ የፌስቡክ ሌባና
ዘራፊ <<Gizachew
Menber Hi>> የተባለ
<<የዘመነ ካሴ የጎጃም ፋኖ ደጋፊ>> እኔ ከሦስት አመት በፊት የለጠፍኩትን የወያኔው ታጋይ የሟቹ <<የአማረ
ታረቀ>> ፎቶግራፍና ታሪክ ዛሬ February
21/2025 <<Gizachew
Menber Hi>> የተባለው
ይህ ሌባ በፌስቡኩ ላይ <<ሜጫ ያልከፈለችው ዋጋ የለም >> በሚል ርዕስ
<<አንዱአለም ምህረት>> በውግያ ተሰዋ የጎጃም ፋኖ ጀግና በማለት በሚያሳፍር የበታች ስሜትነትና ሌብነት ከራሴው ፌስቡኬ ያገኘውን የወያኔው <<አማረ ታረቀን> ታሪክ <<አንዱአለም ምህረት>> ለተባለው የጎጃም ፋኖ ተዋጊ በመስጠት የሚከተለው አስገራሚ ጀግናን የማጣት ስሜት ያመጣው ስርቆትና የሞራል ዕርቃን (ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?) እነሆ እንዲህ ይላል።
Gizachew Menber Hi
https://www.facebook.com/gizachew.menberhi
February 21/2025
<<ሜጫ ያልከፈለችው ዋጋ የለም
የሰው ፍጡር ሆነህ ለማመን የሚከብድ ጀግንነት ፋኖ አንዱአለም ምህረት የመራዊ ተወላጅ ሲሆን በውጊያ ላይ እያለ ከጠላት በተተኮሰ ከባድ መሳርያ አንድ እግሩን ካጣ በኋላ የተቆረጠው እግሩን በማንሳት
#ድል ለአማራ
#ድል ለፋኖ
እያለ ሲፎክር ስታይ አማራ በአለማችን ላይ ያለ አስገራሚ ህዝብ መሆኑን ትገነዘባለህ ታሪካችን በአግባቡ ይሰነዳል !!
ይህን ትግል ነው እንግዲህ ለግል ጥቅም የሚሮጡት ለመጥለፍ የሚሯሯጡት። ጋዜጠኛ ኤልያስ ደባሱ ያስታውሰኝ እንጅ ከአመት በፊት ይህን መረጃ አጋርቸው ነበር >
በማለት ለዓላማ የተሰዋ
አማራ ፈልጎ አጥቶ የወያኔዎችን ታጋይ አሟሟትና ምስልና ታሪክ “በመጥለፍ” (የራሱን ቃል ልዋስና
) ከላይ ያነባችሁትን “የዘመነ ካሴ የጎጃም አምሐራ ፋኖ”
ደጋፊዎች ዝርፍያ ይህንን ይመስላል።
እኔን እንዳስደነገጠኝና እንዳስገረመኝ እናንተም ይህንን አስገራሚ የበታችነት ስሜትና ጀግና ፍለጋ ወደ ትግሬ ታጋዮች መለጠፍ በወያኔ ታጋይ ምስል የጎጃም ፋኖን ማሸብረቅ ለምን ተፈለገ? ብላችሁ እንደምትገረሙ እገምታለሁ።
ወያኔ ትግሬዎች አማራውን ለምን ይንቁታል ብትሉ “በምደረ አምሐራ ጀግና የታጣ ይመስል” እንዲህ ያሉ ደደቦችን የዝቅተችነት ስሜት ያጠቃቸው የትግሬዎችን ጀግንነት የሚመኙ <<የራሳቸውን ፈልገው ያጡ>> አንዳንድ ተምበርካኪ አምሐራዎችን ስለሚታዘቡ ነው።
የሚገርመው ደግሞ በፌስቡኩ ላይ
የተሰጡት “አስተያየቶች” ብዙ ደንቆሮ እንዳለ ማሳያ ምልክት ያየሁበት ነው። አንዳንዱ በበዳሜ ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የተሰዋ ምስል
ነው ሲል አንዱ ደግሞ “ጅግናው አማራ ለታሪክ ሰነድ አስቀምጬዋለሁ” እያለ የሚጃጃል ከንቱ ትውልድም አለ። ያም ሆኖ
ትዝብታችሁን በትክክል ለማስጨበጥ እውነተኛው የለጠፍኩት የወያኔው አማራ ታረቀ ምስልና ታሪክ በድጋሚ እነሆ የሚከተለው ነው
ኡር-ፋሺዝም የወያኔ ታጋዮች እውነተኛ መገለጫ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
12/23/2022
https://www.facebook.com/photo/?fbid=860159945291867&set=pob.100038936079701
የ ኡር ፋሺዝም (Ur Fascism) ባሕሪ ምንነት የነገረን ተመራማሪው 7 የውጭ አገር ቋንቋዎች አጣርቶ መጻፍና ማንበብ ችሎታ ያለው ጣሊያናዊው “ኡምቤርቶ ኤኮ” ነው። በትርጉም ካልተሳሳትኩ “ኡር ፋሺዝም” ዘላለማዊ ሺዝም ማለት ይመስለኛል አንግሊዞች cult of tradition የሚሉት።
ኡር-ፋሺዝም ምንም ብንሰለጥንም አገዛዞች የተለያዩ ልዩነቶች ቢኖራቸውም የኡር ፋሺዝም ባሕሪ ዛሬም በተለያዩ ተዋጊ ቢድኖችና መንግሥታት ተኮልኩሎም ሆኖ በይፋ የሚታይ “ዛሬም” የሚገኝ “ልዩ” የሆነ ፋሺስታዊ ባሕሪ ነው። ዳሰስ ብታደርጉት ታገኙታላችሁ ይላል ተመራማሪው “ኡሜርቶ ኤኮ” ኡምቤርቶ ኤኮ በመጽሐፉ መግቢያ እንዲህ ይላል። በ1942 በአሥር ዓመት ዕደሜየ “ለሙሶሎኒ ክብር እና ለኢጣሊያ ዘላለማዊ እጣ ፈንታ እንሙት?” በሚለው የጥያቄ ርዕስ ላይ በኢጣሊያ ወጣት ፋሺስቶች መካካል በተደረገው የንግግር ውድድር “ብልህ ልጅ” ነበርኩና ባደረግኩት ንግግር አዎንታዊ አድናቆት በማግኘቴ የብልህ ተናጋሪ ወጣት ሽልማት ተቀዳጀሁ። ይላል።
ኡምቤርቶ ኤኮ << ህይወት>> ለኡር-ፋሺዝም <<የህይወት ትግል የለም>> ይልቁንም << ህይወት ለትግል ነው የምትኖረው>>ይላል።
ስለዚህ-ይልና
<< ህይወት ዘላቂ ጦርነት ስለሆነ በጸጋ ይቀበለዋል። ይህ ግን
የአርማጌዶን ስብስቦችን ያመጣል። ጠላቶች መሸነፍ ስላለባቸው የመጨረሻው ጦርነት ሊኖር ይገባል ስለሚል፤ በዛው ቦግ እልም እያለ ያልተቋረጠ የጸብና የጦርነት ጫሪነት የእንቅስቃሴው ሂደት ዓለምን በመቆጣጠር ወርቃማ ሰላምን ማምጣት ይቻላል የሚል ባህሪ አለው>> ይላል። ነገር ግን እንዲህ ያለው ሁሉንም ተቆጣጥሮ ሰላም የሚያመጣ ተስፈኝነት የተሳካለት ፋሽስት መሪ የለም>>
በማለት የኡር ፋሺዝም ባሕሪ ርቀት ይገልጽና መጽሐፉን ሳነበው፤ ከጠቀሳቸው የኡር ፋሺዝም 14 ባሕሪያቶች ውስጥ ቀልቤን የሳበው ከርዕሴ መግቢያ የለጠፍኩት በመጀመሪያው የ17 አመት የወያኔ የጫካ ጦርነት ዘመን “አማረ ታረቀ” የተባለ የወያኔ ታጋይ በውግያው ውስጥ ቀኝ እግሩ በከባድ የጥይት አሎሎ ተመትቶ ተቆርጦ በመውደቁ የተቆረጠውን እግሩ አንስቶ ወደ ሰማይ በመቀሰር የሞት ብስራቱን በጸጋ በመቀበል ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።
እንዲህ ያለ ሞት ኡምቤርቶ ኤኮ አንዲህ ሲል ይገልጸዋል።
<< … በእንደዚህ ዓይነት አመለካከት ሁሉም ሰው ጀግና ለመሆን ይማራል፡ በእያንዳንዱ አፈ ታሪክ ውስጥ ጀግና ልዩ ፍጡር ነው። ነገር ግን በኡር-ፋሺስት ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ጀግንነት “ብርቅ” አይደለም የተለመደ ነው። ይህ የጀግንነት አምልኮ
“ከሞት አምልኮ” ጋር በጥብቅ “የተያያዘ”
ነው። የፈላንግስቶች መሪ መፈክር “ቪቫ ላ ሙርቴ” ("ሞት ለዘላለም ይኑር!") ይላሉ። ይህ የሞት አምልኮ ባሕሪ በአጋጣሚ አይደለም፡ ፋሺስት “ባልሆኑ” ማህበረሰቦች ውስጥ ምእመናን “ሞት ደስ የማይል”
አንደሆነ ይነገራቸዋል። አማኞች ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ደስታ ላይ ለመድረስ “አሳማሚው መንገድ” እንደሆነ ይነገራቸዋል። በአንፃሩ የኡር-ፋሽስት ጀግና “የጀግንነት ሞትን” ይመኛል፣ ለጀግንነቱ “ሞት” “ምርጥ ሽልማት ተብሎ ይታወጃል። የኡር-ፋሽስት ጀግና “ለመሞት ትዕግስት የለውም””። ትዕግስት በማጣቱም
“ሌሎች ሰዎችን” ወደ “ሞት” ይልካል።
>>
በማለት የ ኡር ፋሺሰቶች
“ ቪቫ ላ ሙርቴ”
- "ሞት ለዘላለም ይኑር!" እያሉ የሞት ቅድስና በመስበክ በጦርነት ወቅት እኔ ልሙት እኔ ልሙት እየተሽቀዳደሙ ወደ ጦርነት እሳት በመግባት ይሰዋሉ። ይህ የኡር ፋሺዝም ከ14 ቱ ባሕርያቶች አንዱ ሞትን በቅድስና እንዴት እንደሚያመልኩት ስንመለከት የወያኔ እና የሻዕቢያ ተዋጊዎች ባሕር የ ኡር ፋሺዝም ባሕሪ እንደተላበሱ ከሚዘግብዋቸው የታሪክ ማሕደሮቻቸው ለማወቅ ችለናል።
የኡር ፋሺስት ተከታዮች ሞትን ስለማይፈሩ የሰው ልጆች የሞት ምንጭ በመሆን በራሳቸው ሞትን በቅድስና ስለሚቀበሉ በጦርነት ወቅት አስቸጋሪ (ጠንካራ ተዋጊዎች) ሆነው ይታያሉ። ጠንካራ ተዋጊነታቸው ምንጩ “ለመሞት ትዕግስት የላቸውም”። ሌሎች ሰዎችን በመረሸንም ሆነ ወደ ሞት ለመላክ ግድ የሌላቸው ገራፊዎችና ጨካኞች ናቸው። በሁለመናዊ መልካቸው ከኡር ፋሺዝም ገንዳ የተቀዱት የኦነጉ የአብይ አሕመድ “ኦሮሙማ” እና የመለስ ዜናዊ
“ህወሓት” ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ሱታፌ መታገድ አለባቸው እያልን የምንወተውተው ለዚህ ነው።
ሰላም-ሰንብቱ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment