Saturday, January 25, 2025

የባሕል ለውጥ በእስልምና እና ጠባብ ብሔረተኛነት በትግርኛ ተናጋሪ እስላሞች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay1/26/2025

 

የባሕል ለውጥ በእስልምና እና ጠባብ ብሔረተኛነት በትግርኛ ተናጋሪ እስላሞች

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay1/26/2025

ስለ ፎቶግራፎቹ ማብራሪያ

የመጀመሪያው ፎቶግራፍ በተለይም ሽቅብ ስልክ ይዛ የምትታየው እህት ዓይንዋ ብቻ የሚታይ “ታሊባናዊና ሱዑዳዊ የዓለባበስ ባሕል የተከተለ አለባበስ ሲሆን፤

2ኛው ፎቶ ፤- ከፊት ለፊት የሚታዩት ሁለት እህቶቻችን የለበሱት አለባበስ ነባራዊውና ባለግርማው ሞገስ የተላበሰው የኛው የሆነው ጥንታዊው አገርኛ የትግራይ እስላም እናቶቻችን በኩራት የሚለብሱት የማንነታችን ማሳያ አለባበስ ሲሆን፤ለነዚህ እህቶች ያለኝን ክብር ቆቤን በማንሳት እጅ እነሳለሁ!

3ኛው ፎቶግራፍ-ፓክሰታናዊ ሴቶች የሚለብሱት ክንብንብ የባህል አለባበስ የተከተለ ሲሆን፤

4ኛው ፎቶግራፍ- የእስልምና ሃይማኖት ለፖለቲካ መጠቀሚያ ያደረገ እስላመዊ የኩፍያን ክብር የሚጻረር የወያኔ አርማ ያጠለቀ ወጣት ሲሆን፡

5ኛው ፎቶግራፍ- ጥንታዊውና የኛው የሆነው ሀገርኛው ኩራትና ማንነት የተላበሰ እኛ የምናውቀውና የምናከብረው የትግሬ እስላሞች አለባበስ ሲሆን፤ እኚህ ወንድማችን ባህላቸውን አክብረው በመታየታቸው ቆቤን በማውለቅ ዝቅ ብየ አክብሮቴን እገልጻለሁ።

6ኛው ፎቶግራፍ- ከውስጥ ጥቁር ከላይ ቀይ ክዳን የለበሰች፤ እንደ 1ኛዋ ፎቶግራፍ ዓይንዋ ብቻ የሚታይ መላው ሰውነትዋ የተከደነ  በጭቆና ስር ተገድደው በግድ የሚለብሱት አፍጋኒስታናዊያን እና አክራሪ የውሃቢ እስላም ፖሊሶች የሚቆጣጠሩባቸው ቦታዎች የሚለብሱት የባሕል አለባበስ ሲሆን ፡

ይህ ሁሉ የባህል ለውጥ ስንመለከት፤ ዓረባዊው የባሕል ብረዛው ትግራይ ውስጥም ምን ያህል ጠልቆ እንደገባ ለማየት የሚያስችለን ትዕይንት ነው።

አገራችን የነበራት ነባሩ የዋሁና ግርማ መጎስና ኢትዮጵያዊ ሞገስ ተላብሶ ከክርስትያን ወገኖቹ ጋር ተባብሮ የፈጣሪው ስርዓት ሲያከብር የነበረ ኢትዮጵያዊ እስላም እና እስልምና ተሽሮ ፤ አጅግ አክራሪ በሆነ በቋንቋ በአለባበስ ፤በባሕሪ አዲስ መልክ ይዞ ዓረባዊ ወደ ሆነው አሁናዊው እስልምና እንደተሸጋገረ በብዙ ረድፎች ማየት እንችላለን

 ትግራይም የዚህ አደገኛ ዓረባዊ የባሕል ብከላ ውስጥ በመግባት ከነባሩ ትግራዊ/ኢትዮጵያዊ እስላማዊ ባህል ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ የገባ መሆኑን ከመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ ያገኘሁትን በፎቶ ላይ የምታዩት ባህላቸውና አለባበሳቸው የተከተሉ እስላም እህቶቻችን እና በዓረባዊ ባሕል የተበከሉ ወጣት እስላም እህቶቻቻን በሁለቱ በኩል ያለው በፎቶው ላይ ልዩነቱን ማየት ትችላላችሁ።

  ይህ የባሕሪ ለውጥ የታየው ከ1983 ዓ.ም ወያኔ መንግሥትነቱን ከያዘ ጀምሮ ይኼው እስከዛሬ ድረስ እስልምና እና ክርስትና ሽፋን ሆኖ የፖለቲካና የባሕል ብከላ መሳሪያ ተደርጎ እንደቀጠለ ነው።ትግራይ ውስጥ እየታየ ያለው የእስላሞች ጥያቄ እና ተከትሎ የሚንጸባረቀው “ታፈንኩኝ” በሚሉት እስላሞች እና “አፍንሃለሁ” በሚለው አክራሪ ክርስትናው በኩል ያለው መሳሳብ ሁለቱ ፖለቲካ ሲሰሩ አይተናል።

እስላሞቹም ፖለቲካ ሲሰሩ ያየሁበት አንድ የእስላሞች (ቁርኣን) ትምህርት ቤት ተቋም ለጥፎት ያየሁት (በውስጠ ንግግራዊው ጽሑፍ) ለእስላም ፍትሕ ሰጪው እስላም የነበረው ፍትሃዊው ንጉስ “ንጉ አልነጋሺ” የሚባል እንደሆነ አንድ መፈክር ተይዞ አይቼአለሁ። ይህ “ፖለቲካ የተላበሰ ሃይማኖት” የሚነገረን ክርስትያናዊያን የአክሱም ንጉሶች እስልምናን በጥገኝነት አላስጠጉም፤ ፍትሕና ጥገኝነት ሰጪው ክርስትያኖቹ ሳይሆኑ እስላማዊው ንጉስ አልነጋሺየሚባል ነበር” የማለት የውስጥ ሴራ ተልዕኮ የሚያስተላልፍ ተልዕኮ ነው።

ይህ ዓይነት ተልዕኮ የሚበክሉት አክራሪ ዓረቦችና <<ኦነጋዊው አሕመዲን ጀበልና መሰሎቹ>> የሚጎተጉቱት አስተሳሰባዊ ተልዕኮ እንደሆነ ግልጽ ነው።

  ሰሞኑን በመቀሌ እስላሞች የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የታዘብኩት ኢትዮጵያዊው ነባሩ የትግራይ እስልምና ወዴት አቅጣጫ እየተጓዘ እንደሆነ ያየሁበት ጥሩ አጋጣሚ ነው። “ሕጃብ” የተባለው ሴት ዓረቦች የሚያደርጉት ዓረባዊ ልባስ” በትምሕርት ተቋማት እንዳናደርግ ተከለከልን የሚል ጥያቄ የሚጠይቁ መስሎኝ ስከታተል ነበር። ጥያቄያቸው ልክ ነው ፤ ልክ አይደለም የሚለው ክርክሩ የሚቆም አይደለም። አክራሪው ውሃቢ እና አክራሪ ክርስትያን ኦርቶዶከስ እንዲሁም ትግራይ ውስጥ የግንጠላ ፖለቲካ የሚያራምዱ ድርጅቶች ሁሉ የነሱን ድምጽ ለማግኘት ውስጥ በመግባት ህልውናቸው እስካሉ ድረስ መፈትፈታቸው አይቀሬ ነው።

ሁለቱም (ሦስቱ) ወገኖች ለየራሳቸው ፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ሁለቱም ሃይማኖቶችና ፖለቲከኞቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት መጠቀማቸው አይቀሬ ነው። ለምሳሌ በፎቶግራፍ ረድፍ 1ኛ፤ 3ኛ ፤ 4ኛ እና 6ኛ ረድፍ ፎቶግራፎች በመንግሥታዊ ትምህርት ቤቶች ያጠለቁት ፖለቲካዊ ቆብ እና የለበሱትን ልብስ ለብሰው በወታደርነት ፤በአስተማሪነት ተቀጥረው ለማስተማር ተከለከልን ቢሉ ወይንም በሕክምና ሥራ እንዳንሰራ ተከለከልን ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደረርጉ ፤ በሁለቱ በኩል የጦፈ ክርክር እንደሚደረግ የታወቀ ነው።

 ፖለቲካና ሃይማኖት

ኦሮሚያ በሚባለው አፓርታይዳዊ ክልል ውስጥ ለበርካታ አመታት እስልምናን የግንጠላና የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ መምጣቱ ለብዙ አመት የታየ ክስተት ሲሆን ፤ ትግራይ ግን የእስላሞቹ ቁጥር በማነሱ ምክንያት እንደ ኦሮሞው አካባቢ እስልምናውን ልክ እንደ ለኦነግ ፖለቲካ መጠቀሚያ እንደሆነው ነጥሮ ሊወጣ ባይችልም፤ ብዙሃን ቢሆኑ ኖሮ ያ ክስተት ይከሰት እንደነበር አያጠያይቅ። ሆኖም የባሕል ብከላው ገደብ እስካልተደረገበት ጊዜ የኢትዮጵያ አክራሪ ውሃቢ ወጣት (ፖለቲካዊ እስላሞች) “ግፋ በለው” ማለታቸውና ውጥረቱን ለማራገብ እንደ እነ “አሕመዲን ጀበል” ትግራይ ድረስ ነጋሽ እና አክሱም ድረስ በአካል እየሁዱ ካሁን በፊት እንዳደረጉት መሳሳቡ የሚያስቀጥሉት ይሆናል።

ሰሞኑን ይህችን ክፍተት አግኝተው የውሃቢያ  ሚዲያዎች ምን እንደሚሉ የተከታተላችሁ ካላችሁ፤ የትግሬ እስላሞች የወያኔ መጠቀሚያ እንደሆናችሁት ሁሉ የነዚህ ውሃቢያ መጠቀሚያ ላለመሆንም መጠንቀቅ ያስፈልጋችሗል።

 መቀሌ ውስጥ እስላሞቹ ያሳዩት ሰላማዊ ተቃዉሞና የመብት ጥያቄ በሰላማዊው ሰልፉ ያየሁት የተንጸባረቁት “አይከኖች” (ምልክቶች)  “ነጋሪ የፖለቲካ ጥቅሶችና ምልክቶች”  የሃይማኖት ጥያቄያቸው ያኮሰሰ <<የትግራይ ሃገርነት ካርታ የሚያጎላ>> <<የትግራይ ግንጠላን ያከበረ>> ፤ <<የኢትዮጵያን ጠልነት ያንጸባረቀ>> ፤ <<ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማችንን እንደመብት ረጋጭ አድርገው፤ የወያኔ ፋሺሰቶች ባንዴራ ግን መብታቸውን የምታስከብርላቸው>> አድረገው በኩራት የፋሺሰቶችን ምልክቶች እያውለበለቡ ፖለቲካውና ሃይማኖትን ቀላቅለው መቅረብ ድንቁርናው ልክ ያጣ እጅግ አስደማሚም አሳፋሪም ነው።

 የትግራይ እስላሞች ኢትዮጵያን ለማፍረስ አምሐራን ለመጨፍጨፍ ጫካ ገብተው እንደነበሩ በመንገር “ከነ ሕጃባችን 17 አመት እንደታገልን ሁሉ ዛሬም ከነ ሕጃባችን እንማራለን>>፡ እያለ ፋሺሰትትን የተቀበለ ፤ በብሔረተኛነት የሚፎልል ፖለቲካም የጨመረ ሰልፍ ነበር። እኔ እስካወቅኩት ጊዜ እስላም ሴቶች ሕጃብ ለብሰው አልታገሉም። ሕጃብ ለብሰው ሲታገሉና በየ ሸንተረሩ ሲሯሯጡ የሚያሳይ ፎቶግራፍና መስረጃ ካለ ያቅርቡና እንመናቸው፡

ያንን የትግል ታሪካቸው ለመንገርም ይመስላል ወጣት ሴት እስላሞቹ የለበሱት አለባባስ ጭራሽ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ታሊባናዊ አፍጋ ሴት እስላሞች እና ሳዑዳዊ ዓራባዊነት አለባበስ የተከተለ ፤ ዓይናቸው ብቻ ለማየት የሚያስችል ትንሽ ቀዳዳ ትተውመላ ሰውነታቸው የሸፈነ አስገራሚ የባሕል ክሕደትና ብረዛ የተከተለ እንጂ ኢትዮጵያዊ (“ትግራዊ” እስላማዊ የአለባበስ ) ባሕል ያልተከተለ ከወላጆቻቸው አለባባስ የወጣ ፤ እጅግ አስገራሚና አሳዛኝ የሆነ <<ዓረባዊ የቅኝ ተገዢነት የሚያሳይ ተምበርካኪ ትውልድ እንደተፈጠረ>> ያየሁበት ሰልፍ ነበር።ስትታገሉ ይህን መሳይ አለባበስ ነበር ለብሳችሁ ስትታገሉ የነበረችሁት ወይስ ቁምጣ ሱሪ ነበር ለብሳችሁ “ኤርትራን ለማስገንጠል” ስትትጋሉ የነበረው?

ይህ አለባበስ እውን የትግሬ እስላም አለባበስ ነው?

ይህ አሁን እያየነው ያለው የባሕል ወረርሺኝ በትግራይ ትግርኛ ተናጋሪዎች እንጂ በኩናማ፤በሳሆና ዓፋር  እስላማዊ ማሕበረሰብ አይታይም ፤ አይታወቅም። ለምን በትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ይህ የባሕል ወረርሺን ሊታይ ቻለ የሚለው ጥያቄ ራሱ የቻለ አርዕስት ስለሚያስፍልግ ለዛሬ ልተውና ወደ ዋናው ትኩረት ላምራ።

እስላሙም ይሁን ክርስትያኑ በደለኝ የሚለውን አስተዳደራዊ መሪዎቹን እንጂ መታገል ያለበት አገርና ባሕል ክዶ አገር አለኝ የሚላትን ኢትዮጵያ አገሩን በመክዳት ዓረባዊትግራዊኦሮሚያዊአምሐራዊ፤ ወዘተ… ነኝና አገር ትበጣጠስ ብሎ የጠባብ ብሔረተኞች መጠቀሚያ መሆን ጣጣ ይዞ እንደሚመጣ አሁን ካሉበት የኑሮ ሁኔታ እንዴት አልገባ አላቸው?

‘ባንተአምላክ አያሌው’ የተባሉ “አምሐራ” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ወደ ዓረብ አገር፤ ወደ አሜሪካ ወደ አውሮጳ ሃገሮች ሄደው እዛው ቆይተው ሲመለሱ ስለሚያሳዩት ባሕሪ እንዲህ ይገልጹታል፡

‘ብዙ ኢትዮጵያዊያን ውጭ ሀገር ሄደው ሲመለሱ ስብዕናቸው እሳቤያቸው ማንነታቸው ሁሉ ይለወጣል። አካላቸው እንጂ ሌላ ሁለንተናቸው ኢትዮጵያዊ አይመስሉም። ሲበዛ  ሴኩዩላርና አውሮጳዊ ለመምሰል ይሞክራሉ። ኢትዮጵያዊ እሴትን ማንጸባረቅንም እንደ ሗላቀርነት ይቆጠራል።…….’’ እያሉ ይቀጥላሉ;

ከላይ ያየነው ሁሉንም ኢትዮጵያዊን የሚነካ ትክክለኛ አባባል ነው። ወደ እስላም ወንድሞቻችን ስንመጣም፡ ለምሳሌ መቀሌ ውስጥ በሰላማዊው ሰልፍ ያየናቸው ሴት ወጣት እስላሞች ፎቶው ላይ እንደምታዩት አለባበሳቸው ትግራዊ (ኢትዮጵያዊ) የትግራይ እስላም እናቶቻችን አለባባስ ባሕል የተከተለ ሳይሆን 95% ዓረባዊ፤ ፓኪሳታናዊ፤ የመናዊ፤ ኢራናዊ ታሊባናዊ የአፍጋን ሴቶች አለባበስ ነበር ለብሰው ወደ ሰልፍ በገፍ የወጡት።

እንዲህ ያለ ዓይናቸው ብቻ የሚያሳይ የተንዠረገገ ልብስ ዓረባዊ የአለባበስ ባሕል በባሕል ሚኒሰትር (አውነተኛ የባህል ሚኒሰትር ትግራይ ውስጥ ካለ ፡-አትሳቁ- እንኳን እዛ አዲስ አባባም ኦሮሙማው አብይ አሕመድ የኦነግ መሪ በመሾም ኦነጋዊ የባሕል ሚኒሰትር ነው ያለው)፤ ይህ የባሕል በረዛ መቆም እንዳለበት በሕግ ቢታገድ ለምን ያንጫጫል?

ይህ የቦኮ ሐራም ፤ የታሊባን የፓኪስታን ፤ የሳውዲ አለባባስ : ኢትዮጵያ ውስጥ በመንሰራፋቱ በመላው ኢትዮጵያ ተከልሶ እንደገና ቢታሰብት ለኔ ምርጫየ ነው። ልብስና ባሕል ባልታጣ ለምን አፈር እየጠረገ የሚሄድ (አሁንማ የክርስትያን የባሕል ዙርያ ልበሶችም ይህንን መሬት እየተጎተተ አፈር እየጠረገ የሚለበስ ዙርያ ሴቶቻችን እየለበሱት ነው!)፡ ይህ አለባበስ ለምን ተመረጠ?

ልብሱ በብዙ ዓረብ  ምሁራን እንደሚሉት የዓረብ ክርስትያኖችም ይለብሱታል፡ ስለዚህ ሃይማኖት ልብስ ሳይሆን “ዓረባዊ የባህል ልብስ አለባባስና ምናልናትም ሙቀት ላይ የሚለበስ ስለሆነ” እንጂ ሃይማኖታዊ የግድ አይደለም ይላሉ።

 ጌታቸው ረዳ ለምን እንዲህ ይላል ብላችሁ አቧራ ልታነሱ መብታችሁ ነው; እኔ ግን አድርባይነትን (እወደድ ባይነበትን) የምጠላ፤ እንደምታውቁኝ “አካፋን አካፋ” የምል ስለሆንኩኝ፤ “ትችቴን ቢመራችሁም ዋጡት”።

ዓፋሮች ዓለም ባወቀው ሞቃታ ቦታ እየኖሩ አንደ ትግሬዎቹ መላውን ሰውነት የሚሸፍን የተንዠረገገ ፤ ለዓይን ማሳያ ብቻ ያለው አፈር እየጠረገ የሚለበስ ዓረባዊ ልብስ አይለብሱም። እነሱ የሚያደርጉት ልክ ከላይ በፎቶግራፍ 2 እንደምታዩት ፎቶ እስላም እናቶቻቻን ሲከተሉት የነበረው ጸጉራቸው ላይ እስላም መሆናቸውን መላያ “ሻሽ” ጣል በማድረግ ብቻ ነው የሚታዩት እንጂ መሬት ለመሬት የሚጎተትና ዓይንን ብቻ የገለጠ አስገራሚ አለባበስ አይለብሱም።  

ዓፋር እስላም ወንድሞቻችንም ኢትዮጵያዊነታቸውን አጥብቀው በመያዝ አግልድም/ሽርጥ/ እንጂ ፂማቸውን አዠርግገው የራሳቸው ያልሆነ የባዕድ ዓረባዊ ጀለቢያ አለባበስ አይለብሱም። ዓፋሮ ኩናማዎችና ሳሆዎች ጸጉራቸውና አንገታቸው ለዓየር ክፍት ነው።ታዲያ የኛ የትግሬ እስላም ሴቶች እህቶቻችን የእናቶቻቸውን አለባበስ ጥለው ታሊባናዊ ወይንም ቦኮሐራማዊ ፖሊስ ያስገደዳቸው ሕግ ሳይኖር ዓረባዊና ወያኔያዊ መሆን ለምን መረጡ?

መቀሌ ውስጥ በዚህ ጥቂት ቀናት በሰላማዊ ሰልፋቸው እንደነገሩን የትግሬ እስላሞች ኢትዮጵያዊን ሳይሆኑ “ትግሬዎች” እንደሆኑና የትግሬ መለያቸው ሰንደቅዓላማም እንደላቸው ነግረውናል። መንገር ብቻ ሳይሆን ትግራይን እና ኤርትራን ለመገንጠልም እንደታገሉ የትግራይ ሃገርነት ካርታቸውም “በታፔላ/ሰሌዳ” ለጥፈው መታገላቸውንም በኩራት ነግረውናል

የወያኔ የ17 አመት ትግል ምን ነበር? 

አምሐራን በዝባዥና ፤ቅኝ ገዢ ፤ አምሐራን ‘አህያ’ እያሉ ነው ፤ ትግራይን ነፃ ለማውጣት የታገሉትና ማኒፌሰቶአቸው የሚነግረን። አደለም እንዴ? እነዚህ እስላም እህቶቻችን እንደ ኦነግ (አስሊ የተባለች አምሐራን ስትጨፈጭፍ የነበረች ዛሬ አሜሪካ ሚኔሶታ የምትኖር ኦነጋዊት) ሴትና ወንድ እስላማዊ ታጣቂዎች አምሐራን ሲያርዱ <<አላህ ወ አክበር>>  እያሉ ሲያርዱ እንደነበሩ ሁሉ የትግሬ ታጋዮችም ተመሳሳይ ቡራኬ እያወረዱ እንደሚያርዱ ማስረጃ ባይኖርም፤ አምሐራ ሲጨቁናቸውና ሲበዘብዛቸው እንደነበር አምነው ነበር ከወያኔ ጋር 17 አመት የታገሉት። በድርጅታዊ ማኒፌስቶና አመራር ተደራጅተው ወያኔዎች አምሐራው ላይ ጭፍጨፋ ሲፈጽሙበት እንደነበርም የወልቃይ መሬት ማስረጃ ነው። ከዚያም አልፎ ድርጅታችሁ 27 አመት ኢትዮጵያን ያለ ባሕር ያስቀረና ያዋረደ የትግላችሁ ውጤት ነበር። ታዲያ እንዴት የወያኔ ታጋይ መሆን “ኩራት” ሆኖ ባንዴራውና ካርታው አክብራችሁ “ኩራት” ብላችሁ ያዛችሁት?

ለነገሩ ዛሬ አምሐራ ትግራይ ውስጥ የለም፤ አፈነን የምትሉት አምሐራ የትም ሥልጣን ውስጥ የለም፤ እያፈነን ነው የምትሉት የወያኔ አስተዳደርና ስርዓተ ትምሕርትም አክብራችሁ ባንዴራውና ካርታው ይዛችሁ በኩራት መሰለፋችሁ ትንሽ ዛሬም አታፍሩበትም?

ለመሆኑ እናንተ የትግሬ እስለም ወጣቶች (ሴትም ወንድም፤ ጋዜጠኞችም) “እስላማዊ ኦነጎች” ኦሮሚያ በሚባለው የደም መሬት አምሐራን አጋድመው “አላህ ወ አክበር” እያሉ ሲያርዱት እናንተ ብዙዎቻችሁ ለምን ዝም አላችሁ? የክርስትያን ወገናችሁ ሲታረድ 36 አመት ሙሉ ለምን ድምጽ አልሆናችሁለትም?

ደራሲ ባንተአምላክ እንዳለው

‘ኦነጋዉያን ትናንትም ዛሬም እስልምና የክርስትያን ጎረቤቶቻቸው የሚቃወሙበትና የሚጠቁበት መሳሪያ መሆኑ አሁንም በተግባር እየታየ ይገኛል።ይላል። ኦረሚያ ክልል አምሐሮች (እስላሞች አምሐራዎችና ክርስትያን አምሐሮች) ሲታረዱ፤ አብየተ መቅደሶች በእሳት ሲጋዩ <<አላህ ወአክበር>> እየተባለ … የቤተአምሐራ (ወሎ) ወንድሞቹ የሆኑት ሙሰሊሞች እያረደ እንዴት ሳያፍር “አላህ ወ አክበር” ይላል? በአምሐራ አንገት መታረድና ደም መፍሰስ የሚከበር አላህ እንዴት አይነት አላህ ነው?>> ይላል ደራሲ ባንተአምላክ።

እውነት ነው <<በአምሐራ ደም መፍሰስ የሚከበር አላህ እንዴት አይነት አላህ ነው?>> ብሎ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን <<እናንተ ሕጃብ አድርጋችሁ 17 አመት ታገልንለት ያለችሁት ወያኔያችሁና ባንዴራችሁ ማንን ነበር ሲታገል የነበረው? አምሐራን እና ኢትዮጵያን አደለም!? ወያኔያችሁ የጋራ ግምባር ፈጥሮ አንድነት የፈጠረው <<አላህ ወ አክበር>> እያለ የአምሐራን ደም ከሚያፈሰውና ደም ከሚጠጣው “ኦነግ” ጋር እንደነበር ታውቃላችሁ?

 ይህ እየሆነ ለምን የወያኔ ካርታና ባንዴራ ወድዳችሁ የኢትዮጵያን መልክአምድርና ሰንደቅዓላማዋ ከሰላማዊ ሰልፋችሁ አስወገዳችሁት? “ የቱርክ ቅጥረኛው ግራኝ አሕመድን “የነፃነት አርበኛችን”  የሚሉት <<ኦነጎቹ እነ አህመዲን ጀበል>> ግንኙነት እንደምታደርጉ አንዳንድ ወዳጆቻችን ይነግሩናል።

 እነዚህ ውሃቢዎች የክርስትና እምነትን በተለይ  አምሐራውን ለማጥፋት ከነ ማን ጋር እንደተጎዳኙ ይታወቃል፤ የውሃቢ ራዲዮን እና ዩ ቱበሮች ክፍተቱን እየተጠቀሙ ምን እንደሚሉ እያደመጥናቸው ነው። ስለዚህ የትግራይ እስላም ወንድምና እህቶቻችን (የዛሬ ወጣት እስላሞችን ነው እየተናገርኩ ያለሁት) ሃይማኖትን ከወያኔያዊ ፖለቲካ አስወጡትና ራሱን የቻለ ጥያቄ አንጸባርቁ እንጂ ፖለቲካዊ ነክ የሆነ “ወልቃይትን ያጠቃለለ የወያኔን ካርታና የወያኔ ባንዴራ” ይዛችሁ ኢትዮጵያን መልክዓምድርና ሰንደቅዓላማ የሚጻረር ፖለቲካ ከመስራት እንድትቆጠቡ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ልምከራችሁ።

ትግራይ ኢትዮጵያዊት እንጂ ሌላ አይደለችም። ወያኔነትንና እስላምነትን  ደባልቃችሁ “ሮማንቲሳይዝ” ማድረግ ሁለት ተጻራሪ ነገሮችን ማገናኘት ለፖለቲካ (ዌፖናይዝድ) መሳሪያነት እንጂ ለሃይማኖት መብት አይረባም።ባሕላችሁን፤ አለባበሳችሁን እንደ ወላጆቻችሁ እንደ ጥንቶቹ የትግራይ እስላሞች እንጂ ዓረባዊ ባሕል አለባበስና አነጋጋር በመከተል ያልሆናችሁትን ለመሆን አትጓጉ። ካሁኑ ይታሰብበት!

ከ36 አመት በላይ በቀጣይነት የኢትዮጵያዊነት ባሕል ተዳክሟል፤ግን እንደገና ያብባል

የውጭ ሰዎች እንዳሉት “We Shall overcome!”

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

No comments: