አላልቅ ያለው አሳዛኙ የአምሐራ ሕዝብ መከራ!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)1/12/25
ፋታ በማይሰጥ በግል ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ከብዕሬ ርቄ ስለነበር ተከታታዮቼን ይቅርታ እያልኩ ፤ ቢዘገይም ያላባራው የሃገራችን መከራ ባያስደስትም በህይወት ለመቆየታችን እንኳን ለልደቱ አደረሳችሁ እንዴት ሰነበታችሁ!
36 አመት ሙሉ በአፓርታይድ ዘረኛ <<የአገር
በቀል>> ገዢዎች ከጣሊያኖች ከፋፍለህ ግዛ <<በከፋ መልኩ>> ኢትዮጵያዊያን ተጨፍጭፈናል፤ ተዋርደናል፤
ባሕራችን ተነጥቀናል፤ እርስ በርስ እንዳንዋደድ ድምበር ተበጅቶብን እየተላለቅን ተገዝተናል።
አሁን ደግሞ በከፋ መልኩ “የኦሮሙማው ቡድን” የሃገሪቱን
መስርያ ቤቶች ልክ እንደ ወያኔው ከቀበሌው እስከ ጽዳት ሰራተኛው ከአውሮፕላን ጣቢያው እና የፓስፖርት እደሳ - “ደህንነትና የኢሚግረሺን’’
ጽ/ቤት ሠራተኞችና የሃገሪቱ ዋና ከተማ ከንቲባ ፤ ብዙዎቹ ከሃገሪቱ ወታደራዊ የበላይ አዛዦች እስከ ጠ/ሚኒሰትር ሃላፊዎችና እስከ
አድራጊ ፈጠሪው “ናርሲስቱ”
አብይ አሕመድ ድረስ ያለው የሥልጣን አምባገነንነት ፍትሕን በማፈን ከጀነሳይድ የዘር ማጥፋት ጀምሮ ብዙ ወንጀሎችን በመስራት የሕዝቡን ባህል አኮላሽቶ ማንነቱን አሳስቶ የሕዝባችን ህይወት
ከድጡ ወደ ማጡ አስገብቷል።
ይህንን ከባድ ቀምበር ከሕዝቡ ጯንቃ ለማውረድ ቢሞከርም
አንዳንድ ልበ ሙሉ ደፋሮች መስዋዕት የከፈሉ ሰዎች ቢኖሩበትም ለ36 አመት የረባ ተቃዋሚ አላገኘንም። የፋኖ ትግል ከመጀመሩ በፊት
በ27 አመቱ ትግል ውስጥ ብዙ መጥፎ ክስተቶች ታይተውበታል። የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የነበሩት በብዙዎቹ ፓርቲዎች በከፍተኛ የፓርቲ
አመራሮች መካከል በተፈጠረ የስልጣን ግጭት ምክንያት ተከፋፍለው እርስበርስ ሳይስማሙ ቀርተው ባሳዛኝ ሁኔታ 27 አመት ሙሉ ኳስዋ
በትግሬዎቹ ሥርዓት ቁጥጥር ዘመነች። በዚህ ምክንያት የሥልጣኑ ሽሚያና
አለመስማማታቸውም “የተቃዋሚዎች መለያ”
ሆኖ ዘለቀና ያ መለያቸው ዛሬ ወደ ፋኖ ታጋዮችና ደጋፊዎቻቸው ተላልፎ
ቀጠለ።በሚያሳዝን ክስተት የሕዝቡን ዕምባ ሊታበስ ቀርቶ ባንዳንድ የፋኖ አደረጃጀቶችና መሪዎች የአጉራዘለላዊ ባሕሪ ምክንያት ልክ
ወያኔዎች ጫካ ወስጥ በነበሩበት ወቅት ሲያደርጉት እንደነበረው “አረጋዊያንን በእምብርክክ ማስኬድ፤ ሰውን መጥለፍና መረሸን” የዘወትር ክስተት
ሆኖ ለሚዲያ ቀረበ።
የሚያሳዝነው ነገር ተስፋ የተጣለበት ትግል የሚመሩት “ዲያስፖራ” ውስጥ የሚኖሩ ሕሊናቸው የተቃወሰ አደገኛ ቡና አጣጪ ሐሜተኞች ጫካ ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ የፋኖ መሪዎች ግፋ በለው ባይነት ሌሎችን የፋኖ መሪዎች ስብዕና እንዲያጠለሹ “የግፋ በለው ፈቃድ” ማበረታታቸውን ስናይ የአምሐራ ሕዝብ ሰቆቃ ገና እንደሚቀጥል የሚነግረን ምልክት ነው።
በሚገርም ሁኔታ እነዚህ አንዳንድ የፋኖ መሪዎች ነን የሚሉ
(በግልጽ ለመጥቀስ የዘመነ ካሴ ፋኖ ቡድን) እራሳቸውን እንደ እውነተኛ ነፃ አውጪ ፤ አምባገነንነትና ኢፍትሐዊነትን
እንቃወማለን ይሉና በዲሞክራሲ አሰራርና
በሕግ እንደሚገዙ ዲሞክራቶች አድርገው ይቆጥሩና ነገር ግን ከሁሉም በላይ የተመሰከረውና ያየነው ግን እነዚህ ተቃዋሚዎች
ዝቅተኛዋን ዲሞክራሲ
እንኳ በራሳቸው መተግበር አልቻሉም።
ጋዜጠኛን ያፍናሉ ፤ ከኔ በቀር ሌላ በአካባቢየ የታጠቀ ቡድን ላይ አልፈልግም፤ በማለት ይዝታሉ፤ ያፍናሉም ይረሽናሉም።
እነዚህ አመራሮች ለአምባገነናዊ አገዛዝ ቅርብ ናቸው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አምባገነኖች ሆነዋል። በዚህ ምክንያት የፋኖዎቹ ትግል
ሥርዓቱን መገርሰስ ቀርቶ የአማራን ሕዝብ
እንደ አሸን ማሰለፍ አልቻሉም። ስለዚህም ትግሉ በፍጥነት የታለመውን ግብ ሊመታ አልቻለም ። ስብዕናቸው እንግዳ
እና ለዲሞክራሲ ያልተዘጋጀ ፤ ትዕግስት አልባ የሆነ ፤ በፖለቲካዊ አካላቸው በዲሲፕሊን ያልተገራ
ሁሉም በኔው “ደም ሥር ይለፍ” የሚለው ጠባብነትና ልምድ አልባ ወጣትነታቸው ሲፈተሽ የከፋ እንደሆነ መገመት ችያለሁ።
ትግሉ የሚመሩት ብዙዎቹ ወጣቶች እንደመሆናቸው ብዙዎቹ በዘመነ ወያኔ የተወለዱና ያደጉ ወጣቶች ስለሆኑ ፋኖን ሲያደራጁ አብሮ ያደጉበትን ዘረኛ አስተሳሰብ ከውስጣቸው ሲታገላቸውና ሲያንጸባርቁት ይታያል። ይህ እያንበብናቸውና እያደመጥነው ያለው አውራጃዊነት አልፎም ጎጠኛነታቸው ስንመለከት የተነሱበት ዓላማ አበላሽቶታል። በዲያስፖራውም ተስፋፍቶ እንደ ወረርሺኝ ሰደድ ተቀጣጥሎ የትግሉ ፈር አቅጣጫ ስቶ ለአፓርታይዱ ኦሮሙማው ቡድን ፋሲካ ሆኖለት ሲስቅባቸው ይደመጣል።
እንደ ዘመናዊነትና ዕውቀት አይተውት ‘ኢትዮጵያና አምሐራ” ሁለት ተቃራኒዎች አድርገው በመሳል “ኢትዮጵያኒሰቶች” የአምሐራ ጠላቶች ናቸው” እያሉ በግሃድ የሚሰብኩ አምሐራዎች በብዝዛት እየተራቡ ናቸው። ለዚህ አደገኛ ጸረ ኢትዮጵያ ቅስቀሳ የሚያካሂደው ደግሞ በሽተኛው በ Intermittent explosive disorder የሚሰቃየው “የመረጃ ቲቪ” ዘመድኩን በቀለ የተባለው ሲሆን ፡ ያንን መርዝ ተቀብለው የሚያስረተጋቡ ብዙ አምሓራዎች አሉ።
እነዚህ አምሐራዎች ነን የሚሉ ዋጋ ላለመስጠት ሆኖም በስም መጥቀስ ይቻላል። በዲያስፖራ ፓልቶክ እውቅና ያላው አንድ ሰው ፤ የጎጃሙን ዘመነ ካሴ ምክትል የሆነው አስረስ ማረን << የባርያ ልጅ ነው>> ይለዋል። አንደኛው ደግሞ አብቶብስ ውስጥ ተሳፍሬ ትግሬ አለ ከተባ ትግሬ የሚል ስም ስሰማ አብሮ ላለመቀመጥ ካብቶቡሱ ዘልየ በፍጥነት እወጣለሁ፤ አማራ የተባለ ሁለ ትግሬ በተሳፈረበት አብቶቡስ አትሳፈሩ አስወግዷቸው የሚለው ልጅ የአብይ አገልጋይ የነበረ ፤ በጸረ ትግሬነቱ የምናውቀው <<ሃይለየሱስ>> የሚባል የኮምፓስ ዩ ቱብ ባለቤት የኤርሚያስ ለገሰ የቅርብ ወዳጅና “ሃያሲ” ነው።
በዛ አላበቃም። ሰፊዋን ሃገር ሠርተው አቁመው ያስረከቡን የዘውድ ሥርዓትና ነገሥታቶቻችንን ኩፉኛ ይዘልፋቸዋል። እሱ ብቻ አይደለም፤ ብዙ አምሐራ ወጣቶች በነገሥታትና በበርያ ጫዋ ፖለቲካ ገብተው <<አምሐራ እና ኢትዮጲያኒስቶች>> የመይገናኙ ጠላቶች እያሉ የሻዕቢያ የወያኔና የኦነግ ጸረ ኢትዮጵያነት ፖለቲካ የሚሰብኩ በየፓልቶኩ እያደመጥናቸው ነው (አምሐራዎች መሆናቸውም አረጋግጫለሁ)። የአምሐራ ሕዝብ እና ኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ ወይንም <<ኢትዮፒያኒሰት>> ሁለቱ የማይገናኙ ጠላቶች ናቸው የሚለው አደገኛ መርዝ ፤ ካሁኑ ካልቆመ አምሐራ ወጣቶች ልክ እንደ ኤርትራ ወጣቶች ልክ እንደ ትግሬ እና ኦሮሞ ወጣቶች ኢትዮጵያን ወደ መጥላትና መካድ መንገድ ያመራሉ። የአምሐራ ትግልም ያኮላሸዋል። የመከራው ዶፍ ሕዝቡ አይችለውም። ስለዚህም መቆም እንዳለበት እመክራሉ።
እስከዘው ለፋኖ መሪዎችና ለትግሉ መጠናከር ዋናው መፍትሄው፤
ካሁን በፊት የተነገረው የስድብ እና የሥም
ማጥለሸት ቅብብሎሽ ጨክኖ በመርሳት ስለ ሕዝቡ ስትሉ
ካሁኑኑ መነጋገር ካልጀመራችሁ አብይ አሕመድና ኦሮሙማው ጋንግ ልክ እንደ ወያኔ 27 አመት ሊገዛን ነውና ቂምን ጥላችሁ ስለ ሕዝቡ እና ስለ መሰዋዕቱ ‘የአሳምነው
ጽጌ’ ደም ብላችሁ በስልክ ተጠራርታችሁ አንድ ሆናችሁ ወደ ዋናው መንገድ ግቡ።
መልካም ሳምንት
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment