አማራ
ሆይ! ይልቁናስ ለማይቀረው ፍልሚያ ተዘጋጅ!!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
Ethiopian Semay
3/29/23
“በበቀል ጥማት የሚነድ፣ የለም
እንደአቢይ አህመድ” በሚል ርዕስ ግጥም ቢጤ መጻፍ አማረኝና ወደለመድኩት የዝርው ጽሑፍ ዞርኩ፡፡ “ሥነ ግጥም መክሊትህ አይደለም!”
ብባልስ በኪናዊ አገላለጽ፡፡
ኢትዮጵያን
ምን ዓይነት በቀለኛና ተራ የተራ ተራ ውዳቂ ግለሰብ እየገዛት እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ ያቺን የመሰለች ድንቅ ሀገር በዚህ ከሲዖል
ባመለጠ ሰውዬ እጅ መግባቷና ለዚህን ዓይነት ውርደት መጋለጧ እጅግ የሚያሳዝን፣ ኅሊናንም የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ትንሣኤዋ
እስኪበሠር ድረስ እንደእሥራኤሉ የቀድሞ ፕሬዝደንት እንደኤሪየል ሻሮል በሰመመን ውስጥ ብቆይ ደስታው አይቻለኝም፡፡ ሻሮል ለአምስት
ዓመታት ገደማ ሳይናገር ሳይጋገር በሰመመን ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ነበር ከዚህች ምድር የተሰናበተው፡፡
አቢይ
አምባገነንነቱ እንዳለ ሆኖ በበቀለኝነቱ ከምድር ፍጡራን በእጅጉ የተለዬ ነው፡፡ ከኢንጂነር ስመኘው ጀምሮ እንኳን የገደላቸውን ብንቆጥር
ሥፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ያሰራቸውንና ከሥራና ከቤት ንብረታቸው ያፈናቀላቸውንም ቤታቸው ይቁጠራቸው፡፡ እርሱ ሳያውቅና ይሁንታውን
ሳይሰጥበት የሚከናወን ግፍና በደል ደግሞ የለም፡፡ ይህ ሰው መንግሥትን ያህል ሥልጣን ይዞ እንደተራ የመንደር ዱርዬ በቂም በቀል
በመመረዝ ሕዝብን እየፈጀ ነው፡፡ የመንግሥት መሪነትን ሚናና ግለሰብኣዊ የግል ፍላጎትን ድምበር አያውቅም ወይም ሊያውቅ አይፈልግም፡፡
በመሠረቱ መንግሥት እንደመንግሥት ከግለሰቦች ጋር እልህ ተጋብቶ የሕጻናት ፉክክር ውስጥ አይገባም፡፡ መንግሥት ተቋማዊ እንጂ በአንድ
አምባገነን ሰው ፍላጎት የሚዘወር ጠጅ ቤት አይደለም፡፡ እግዜር እንዴት ቢጣላን ይህን ሰው አምጥቶ አራት ኪሎ እንደጎለተብን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ የሰውነት ጠባይ በጭራሽ የለውም፡፡
ተመልከት! ኢትዮጵያን በዘርና በጎሣ ካልበታተንኩ ብሎ ዕድሜ ልኩን በዘር ፖለቲካ መሃንዲስነት የሚታወቀውን
ስብሃት ነጋን ማንም በማይቀናቀነው አምባገነናዊ ሥልጣኑ ከእስር ፈትቶ እያቀማጠለ ሲያኖር ቆዬና ሰሞኑን ደግሞ ለህክምና ወደ ውጪ
እንዲወጣ ፈቀደለት - እርግጥ ነው ይሄ በራሱ መልካም ነገር ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን አቢይ ሥልጣኑን በወያኔ እንዳይቀማ በቅርቡ
ሕይወቱን እስከመስጠት የደረሰውንና በጥይት ቆስሎ የተመለሰውን ጄኔራል ተፈራ ማሞን ህክምና እንዳያገኝ ከልክሎታል - ይሄኛው ወደርየለሽ
ግፍ ነው፡፡ ይህ ስም የለሽ ዕንቆቅልሽ ጤነኛ ነኝ የሚልን ዜጋ ሁሉ ያሳምማል፡፡ የአቢይ የበቀል ስሜት እየጋመ የሚሄድና ራሱንም
ለለየለት ዕብደት የሚዳርገው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ለነገሩ አቢይ ተፈራ ማሞን አይደለም ህክምና የከለከለው፡፡
አቢይ በዚህ ሰይጣናዊ ድርጊቱ ለአማራ ያለውን ጥላቻና ቂም በቀል ነው የገለጸው፤ በተፈራ በኩል አማራን ነው ሊገድል
የቋመጠው - አማራን ተስፋ ለማሰቆረጥ፡፡ ነገር ግን የአማራን ማሕጸን አላወቀውም፡፡ በጄኔኔራል ተፈራ ውስጥ ያለውን በ50 እና
60 ሚሊዮን የሚገመት አማራ ቢያንስ ቢያንስ በምናቡ ለመግደል አቢይ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ ይህን ሁሉም አማራ ሊረዳ ይገባዋል፡፡
እንጂ ተፈራ በግሉ አቢይን የበደለው ነገር
የለም፡፡ አቢይና ሽመልስ አማራን የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል፡፡ ከአራቱም ክፍላተ ሀገሮች አማራ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ
የተደረገው ለምን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ በጎጃምና በወሎ መስመር አማራ ወደ አዲስ አበባ ትውር እንዳይል ሲከለከል ስንትና ስንት
የሪፈራል ታካሚ ሕይወቱ አልፏል፤ የጄኔራሉ ጉዳይ አነጋጋሪ የሆነው ታዲያ አንደኛ ጄኔራሉ የአቢይ ባለውለታ ሆኖ ሳለና እንዲያውም
መንግሥት ራሱ አለ በተባለ ምርጥ ሆስፒታል ማሳከም ሲገባው በራሱ ወጪ ሊታከም ከሀገር ልውጣ ቢል የመከልከሉ ምሥጢር አልገባን
በማለቱ ሲሆን ሁለተኛ መንግሥትን ያህል ትልቅ አካል ያለምንም ምክንያትና የህግ አግባብ አንድን ለሀገሩ ሲል የቆሰለን ከፍተኛ መኮንን
ህክምና ከልክሎ የሞት ፍርድ የበየነበት በመሆኑ ነው፡፡ ይህ አቢይ ይህችን ሀገር ምን እስኪያደርጋት እንደምንጠብቅ ሳስበው
አንዳንዴ ይጨንቀኛል፡፡ ግና ደግሞ ቋቱ እስኪሞላና በፈረንጅኛው ፈሊጥ ለመግለጽ ያህል የግመሉን ወገብ የምትሰብረው የመጨረሻዋ ገለባ
በአቢይ የሥልጣን ኮርቻ ላይ እስክታርፍ በትግስት መጠበቅ ሊኖርብን ነው (The last straw that breaks the
camel’s back. ይለዋል ፈረንጁ)፡፡
አቢይ
ከአምባገነንም በላይ መሆኑንና ራሱን ከፈጣሪም አስበልጦ በኛ ላይ እንደሚዘባነን ለመረዳት ጥቂት ምሣሌዎችን እንመልከት፡፡ ይህ ሰው
በሚገዛት ሀገር ውስጥ መኖር በራሱ እንዴት እንደሚያሣፍረኝ አትጠይቁኝ፡፡
- ቀደም ሲል አሻንጉሊት የፓርላማ አባላቱ ወግ ደርሷቸው “ማን ባጸደቀው 49 ቢሊዮን ብር ነው አዲስ ቤተ መንግሥት እየሠራህ የምትገኘው?” ብለው ይጠይቁታል፡፡ እሱ ደግሞ በንዴት ይፎገላና “በመጀመሪያ የተሳሳተ መረጃ ነው የያዛችሁት፡፡ የጠቀሳችሁት በጀት 49 ቢሊዮን ሳይሆን 56 ቢሊዮን ነው፡፡ ስለሌላው እናንተን አያገባችሁም፡፡ለምኜ በማገኘው ገንዘብ የፈለግሁትን ብገነባ የናንተ ጉዳይ አይደለም፡፡” ብሎ በሀፍረት ኩምሽሽ አድርጓቸዋል፡፡ (የቅንፍ ወሬ ጥሩ ነው፡፡ የ1997ቱን የወያኔ ምርጫ ተከትሎ በርካታ ቀልዶች ነበሩ፡፡ አንዱን እነሆ! ፌዴራሎች “ተጭበርብረናል” በሚል መሪ ቃል ሠልፍ ወጡ፡፡ ጋዜጠኞችና የመንግሥት አካላትም ወደሠልፉ ይጠጉና “ምንድን ነው የተጭበረበራችሁት?” በማለት ችግራቸውን ይጠይቋቸዋል፡፡ በአጋዚያን ጦር የተሞላው የፌዴራሎቹ ቃል አቀባይም “ተጭበርብረናል፤ተጭበርብረናል! በመንግሥት ሚዲያ ‹ከፌዴራልና ከመከላከያ በተተኮሰ ጥይት 35 ሰዎች ሞተዋል‹ የተባለው ትክክል አይደለም፡፡ የገደልነው 165 እንጂ 35 አይደለም፡፡ ተጭበርብረናልና ይስተካከልልን፡፡” ይህ አቢያዊ ቀልድ ፈገግ ከካላሰኛችሁ አዝናለሁ፡፡)
- የጉራጌ ሕዝብ ሰሞኑን የክልል መንግሥትነት ሲጠይቅ አቢይ ምን አለ? “ክልል እንድትሆኑ ብፈልግ አምስት ደቂቃ አይፈጅብኝም፡፡ ግን ስለማይጠቅማችሁ አልፈቅድም፡፡”
አዲዮስ ፓርላማ! አዲዮስ የሚኒስትሮች ካቢኔ! በአንድ ሰው በጎ ፈቃድ ውሎ የሚያድር የምሥኪን 120 ሚሊዮን ሕዝብ ሕይወት በምናባችሁ ይታያችሁ፡፡ በቅርቡ በቀን ስንቴ መተንፈስ፣ ስንቴ ዐይኖቻችንን ማርገብገብ እንደሚኖርብን በዐዋጅ ሳይደነግግ ይቀራል? የአቢይ መንግሥት እኮ ምን ዓይነት ቀለም የተነከረ ልብስ መልበስ እንዳለብን የሚወስን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማትን ከመጥላቱ የተነሣ በልብሳችንም ሆነ በሰውነታችን እነዚህን ቀለማት ብናሳይ አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣን ምስኪን ዞምቤዎች ሆነናል፡፡ ዞምቤ ማለት በሰው አምሳል የተፈጠረ እንደኛው ተናጋሪ እንስሳ ማለት ነው፡፡
- የትግራይ ሽግግር መንግሥት ጉባኤ ሰሞኑን ደብረ ጽዮንን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት አድርጎ መረጠ ተባለ፡፡ የአራት ኪሎው አፄ ቦካሣ ያን ምርጫ አልቀበለው ይልና ሌላ ምረጡ ይላቸዋል፡፡ ጌታቸው ረዳን መረጡ ተባለና ውጤቱ ወደ አፄው ይላካል፡፡ እንደናርሲሰስ በራስ ፍቅር የወደቀው አጅሬ አያ እንደልቡ ግን ምርጫ ምናምን ሳይጠቀስ ጠ/ሚኒስትሩ ራሱ ለጌታቸው ረዳ ሹመት እንደሰጠው በሚዲያ አስለፈፈ፡፡ አዲዮስ ትግራይ! አዲዮስ ሕወሓት! አዲዮስ ምርጫ! (እዚህ ላይ ታዲያ “እዩኝ እዩኝ” ማለት “ደብቁኝ ደብቁኝ”ን እንደሚያስከትል ከወያኔ ይማሯል! ከምላሴ ፀጉር ይነቀል - ኦነጎች ግን ይህችን የወያኔን ዕድል እንኳን አያገኟትም፡፡) ሁሏም ተጠቅላላ በአንድ ዕብድ ሰው እጅ ገባችና ዕንቆቅልሹ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተወሳሰበ ሄደ፡፡ መጨረሻችን ያማረ ቢሆንም የጨለማው አስፈሪነት ግን አሳሳቢ ነው፤ የመስዋዕትነቱ ከግምት ያለፈ መጠን ያስጨንቃል፡፡
- በቀጥታ ከአቢይ ጋር ባይገናኝም - ለምንስ አይገናኝም ኧረ ይገናኛል - በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ምድር እየተስፋፋና እየተንሰራፋ የመጣው በሃይማኖት ስም የማጭበርበር ሰይጣናዊ አካሄድ በአሁኑ ወቅት ጫፍ ደርሷል፡፡ ይህ ድርጊት በሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የሚታይ ነው፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ ይመስላል፡፡ ነቢይት ብርቱካን ለአቢይ የተነበየችለትን የሃሳዊ መሲሕ የቁጩ ትንቢት ጨምሮ እነኢዩ ጩፋና እሥራኤል ዳንሣ በፕሮቴስታንት ስም በየቸርቹ የሚያሳዩት የተጠና ድራማና የሚረጩት መርዝ ቀላል አይደለም፡፡ እነትዝታውና በጋሻውም እንዳሻቸው የሚግጡትን ምዕመን መርጠው ጎራቸውን በመለየታቸው የሃይማኖቱ ጦርነት ጦፏል፡፡ የአቢይ ታናሽ ወንድምና ታላቅ እህት የሚመስሉኝ የፍቅርሲዝሙ ነቢይ ደምሳሽና የጸረ-ኦርቶዶክሷ ወ/ሮ ስንዱ (ራሷን እህተ ማርያም ብላ የምትጠራው ወፈፌ) ደግሞ መሣቅ ሲያምረኝ የምዝናናባቸው ናቸው፡፡ የየራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን መሥርተው ጠበል የሚያጠምቁና አዳሜ ሔዋኔን ኪሱን የሚያጥቡ ባለትዳር መነኮሣትና “ብፁኣን” አባቶች ቁጥር ደግሞ ከምንገምተው በላይ ነው፡፡ ዘንድሮ ብቻ ጉድ ነው፡፡….
አቢይ በበቀል ጥማቱ ማንም አይወዳደረውም ብያችኋለሁ፡፡
ይህ ሰው አንድን መንግሥት የሚመራ ሳይሆን ራሱ ጠፍጥፎ የሠራቸውን አሻንጉሊቶች እንዳፈተተው የሚጫወትባቸው ነው የሚመስለው፡፡ ሀገሪቱንም
ሕዝቧንም እንደራሱ የእጅ ሥራዎች ቆጥሮን ድመት ዐይጥን ከያዘቻት በኋላ ከመብላቷ በፊት እንደምትጫወትባት እየተጫወተብን ይገኛል፡፡
ይህንን ደግሞ ሌላው ዓለም በተለይም ምዕራቡ በሚገባ ያውቃል፡፡ አቢይ የሚወስዳቸውን ሀገር በታኝና ሕዝብ አስለቃሽ እርምጃዎች ሁሉ
የላኩት የውጭ ኃይሎች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማጥፋት በመሆኑ ግን አይቆጡትም ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጉለታል፡፡
የነዚህ ኃይሎች ዋና ዓላማ በአቢይና በጀሌዎቹ አማካይነት የፈረደባቸውን አማራንና ኦርቶዶክስን ማጥፋት ነው፡፡ ስለሆነም
ጄኔራል ተፈራ ለህክምና ከሀገር እንዳይወጣ መከልከሉን የተረዱት አሜሪካኖች ስብሃት ነጋ ዘንጦ በባሌ ሳይሆን በቦሌ ሲወጣ ትንፍሸ
አይሉም፡፡ “ኢትዮጵያንና አማራን ለማጥፋት
ሲዖል ድረስ እንሄዳለን” ያለው ጌታቸው ረዳ የትግራይ ፕሬዝደንት ሲሆንና አዲስ አበባ ላይ ሲምነሸነሽ የአንድ የሀገር ባለውለታ
ጄኔራል ጤንነት ለአሜሪካ ቀርቶ ለሀገሪቱ መሪ ተብዬ ደንታው ሊሆን አልቻለም፡፡ አሜሪካ በኬንያውያኑ ግዛቶች በነሞምባሣና
ማርሳቤት መኖር አለመኖር ራሱ የኔን ያህል እንኳን የምታውቀው ነገር ሳይኖር በወልቃይትና በራያ ያን ያህል ስትጨነቅ ማየት አጃኢብ
ያሰኛል፡፡ ወያኔ የሌላ አካባቢ ግዛት በጉልበት ወስዳ ወደራሷ ስታካትት ትንፍሽ ያላለች አማሪካ ዛሬ ደርሳ በሰው ሀገር የውስጥ
ጉዳይ እንዲህ የእርጎ ዝምብ ስትሆን ማየት የሰውን ልጅ የፍላጎት ባርነትን ያሳያል፡፡ ይህ ሁሉ ዕንቆቅልሽ በቅርብ ማለፉና ታሪክ
መሆኑ ባይቀርም ለጊዜው ግን ያሳብዳል፡፡
ካህንን በአደባባይ በጥፊ መምታቱና ቤተ ክህነትን ማዋረዱ አቢይ አህመድ ለምዕራባውያን ያሳየው የኦርቶዶክስ ጠልነቱ ዋና ምልክት ነበር፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ጥፊው ስላልበቃው እዚሁ አዲስ አበባ እምብርት ላይ ኃይሌ ጋርመንት በሚባለው አካባቢ በጠራራ ፀሐይ አንድን ካህን እንደ ሰማዕቱ እስጢፋኖስ በመንጋ ሆነው በመጀመሪያ በዱላ አናታቸውን በመቀጥቀጥና ቀጥሎም ሬሣቸውን በድንጋይ በመውገር የሥልጣን ማቆያ ቀብዱን በዐይን ጥቅሻና በአውራ ጣት የሞራል ድጋፍ ከምዕራባውያኑ ተቀብሏል፡፡ ይሄ አሰለጥ አቢይና መንጋው በዚህን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይህንና ከዚህም የከፉ ወንጀሎችን ሲፈጽሙ የሚታዘበው የምዕራቡ ዓለም ዝምታውን አፅንቷል፡፡ ይሄኔ የኬንያው ፕሬዝደንት የቤት ውሻ በአጥንት ታንቃ ብትሞት ኖሮ ቢቢሲንና ሲኤንኤንን የመሰሉ ምዕራባውያን የሚዲያ አውታሮች ቀዳሚ ዜናቸው ባደረጉት ነበር፡፡ እነኚህ ለይምሰል ያህል በብር ኖቶቻቸው ላይ “በእግዚአብሔር እናምናለን” (In God we trust.) የሚሉ ጉዶች አፍሪካዊ ወኪሎቻቸው የሚያካሂዱትን የሕዝብ ጭፍጨፋ እንዳላዩ የሚያልፉ መሆናቸውን እንደማናውቅላቸው ሁሉ ስለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ግን ላንቃቸው እስኪበጠስ 24 ሰዓት ይጮሃሉ፡፡ በእግዚአብሐር የሚያምን ሰው በሰው ልጅ እኩልነት ያምናል፤ በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው በዘርና በቀለም፣ በፆታና በሃይማኖት ልዩነት ሕዝቦች እርስ በርስ እንዲተላለቁ አያደርግም፡፡ በአጭሩ ዓለማችን የአስመሳዮችና የገንዘብ አምላኪዎች መድረክ ሆናለች፡፡ ይህ ደግሞ ቃሉ ነው፡፡ ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ደግሞ የግድ ነው፡፡ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም” ብሏላ! ደግሞስ ገና ምን አይተን! እሳት ከሰማይ የሚያዘንቡ ሓሣውያን በስሙ ይመጣሉ፡፡
የአማራውንና የእውነተኛ ኢትዮጵያዊውን አሸናፊነት ምንም ዓይነት ምድራዊ
ኃይል አያስቀረውም፡፡ አማራውያን አሸናፊ የሚያደርጋቸው ግፍና በደል የሚወልደው የጀግንነት መንፈስ ብቻ ሳይሆን ኦሮሙማዎች የሚከተሉት
ለከት የሌለው ጥጋብና ዕብሪት ከጽርሓ አርያም የመንበረ ፀባዖት ችሎት የሚታዘዘው መብረቃዊ ቅጣት ነው፡፡ ቄስ አባይ መለሰ
ሥጋ ወደሙ አቀብለውና ተቀብለው ወደቤታቸው ሲሄዱ በድንጋይ ተወግረው ሰማዕት የሆኑት ለዐረመኔ ጨፍጫፊ ኦሮሙማዎች ሳይሆን
ሻሸመኔና ጉራፈርዳ፣ መተከልና ወለጋ በኦነግ ተጨፍጭፈው እንደእንስሳ በግሬደር ለተቀበሩት ምስኪኖች የደም ካሣ ለመሆን ነው፡፡ ለሚረዳ
ሰው ካህኑ በጥፊ የተመቱት፣ ለመቁጠር የሚያታክት አማራና ሌላው ንጹሕ ኢትዮጵያዊ በኦነግ/ኦህዲድ ሸኔ የታጨደው ለኢትዮጵያ
ትንሣኤ እንደግብኣት ሊሆን እንጂ ለከሰረ የዘር ፖለቲካ መደላድል ሆኖ ወያኔና ኦነግ በኢትዮጵያ መቃብር እንዲጨፍሩ አይደለም፡፡
ስለዚህ ኢትዮጵያ የመነሳቷ ነገር አያሳስብህ፡፡
ለጦርነቱ ግን እንዘጋጅ፡፡ ኦሮሙማና ሕወሓት ሥልታዊ ትብብር በማድረግ አማራን ለመውጋት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ኦሮሙማ በደቡብ፣ ወያኔ በሰሜን በኩል አማራን ወጥረው ለመያዝ ተስማምተዋል፡፡ ኦነጋውያን በአቢይ በኩል ሁሉም ዓይነት የበጀትና የዘመናዊ ትጥቅ ድጋፍ ለወያኔ እየሰጡ ነው - ትብብራቸው እንዳልኩህ ለሥልት እንጂ ወያኔና ኦነግ እሳትና ጭድ ናቸው - የሚያገናኛቸው ነገርም የለም፡፡ ወያኔዎች አጉል እልህና የአልሞትኩም ብዬ አልዋሽም ዓይነት ወኔ ተጠናውቷቸው እንጂ ከኦነግ ይልቅ አማራው በብዙ ጅማቶች እንደሚተሳሰራቸው አጥተውት አይደለም፡፡ ግና እንደሚባለውም እልህ ጩቤ ያስውጣልና ወደባዳ አላምጠው ወደዘመድ መዋጥ አቃታቸው፤ ትዕቢት ደግሞ ውድቀትን ትቀድማለች፡፡ ከመነሻቸው ኦርቶዶክስንና አማራን ማጥፋት ዒላማ አድርገው መነሳታቸው ምን ጊዜም የሀፍረታቸው ምነጭ ነው፡፡ በዚያም ምክንያት በካፈርኩ አይመልሰኝ ትግራይን ይዘው ሊጠፉ ጀግነዋል፡፡ አጀማመርህ አጨራረስህን ይጠቁማል፤ ለማንኛውም ይቀጥሉበት፡፡ ማን እንደሚያተርፍ እናያለን፡፡ ኢትዮጵያ ግን ትነሣለች!!
የኦሮሞ ሸኔ በገፍ እየሠለጠነና በገፍ እየታጠቀ፣ የወያኔ ሠራዊት ከሞት አንሰራርቶ በገፍ እየሠለጠነና እየታጠቀ ሳለ አማራው ግን በብአዴን ታፍኖ ሥልጠናውና ትጥቁ ቀርቶበት የለት ከለት ሕይወቱን ለመምራት እንኳን እንዳይችል በገዛ ቀየው እየተሳደደ ነው፡፡ አማራው በሌሎች ክልሎችና አካባቢዎች ይቅርና በራሱ ክልልም እንዳይኖር ጠላቶቹ እየተናበቡ ከፍተኛ የኅልውና ሥጋት ደቅነውበታል፡፡ አማራው ንብረት ማፍራት እንዳይችል፣ እንዳይበለጽግ፣ አካባቢው እንዳይለማ፣ መንገድ እንዳይኖረው፣ ፋብሪካና ኢንዱስትሪ፣ መብራትና ውኃ፣ መልካ አስተዳደርና ዘመናዊ ትምህርት ቤት እንዳይኖረው፣ ቢታመም እንዳይታከም፣ ከሥፍራ ሥፍራ እንዳይንቀሳቀስ በትልቅ እስር ቤት ተጠርንፎ የመከራ ኑሮ እንዲኖር ተደርጓል፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና በደል የሚፈጸምበት ደግሞ ገና ትናንት ነፍስ ባወቀው በገልቱው ኦሮሙማ ነው፡፡ አፋርና ሶማሌም፣ ሲዳማና ጉራጌም፣ ወላይታና ከምባታም፣ ጋሞና ጠምባሮም፣ ጀምጀምና ደራሳም፣ አኙዋክና በርታም …. ሁሉም ተራውን እየጠበቀ እንጂ የአማራው ዕጣ ፋንታ እንደሚደርሰው ገሃድ የወጣ እውነት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ኦሮሙማዊ የጥፋት ጉዞ ግን የፍጻሜው መጀመሪያ ነው፡፡ ጥሩ አባባል አለ፡- በአቀበት ቁልቁል ሰውን የሚያባርር ሰው ለራሱም መጠንቀቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም ተባራሪው መሮት ዘወር ቢል አባራሪው አቀበት ይሆንበታልና፡፡
ለብርጋዴየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ እንጸልይለት፡፡ እንደአቢይ የማይሆነው እግዚአብሔር እንዳይጨክንበትና የነገይቱን ወርቃማ ኢትዮጵያ ሳያይ እንዳያልፍ ሁላችንም በጸሎታችን እናስበው - ሌላማ ምን ሲቀርበት፤ “ተኖረና ተሞተ” አሉ፤ የአሁኑ የኢትዮጵያ ኑሮ ምኑም አያስቆጭም፡፡ የሆነ ሆኖ ወደ ደጉ ዘመን እንሸጋገር ዘንድ በዚያም ላይ ሁሉም እንደየሥራው ምንዳውን ያገኝ ዘንድ ለሱም ለኛም እንጸልይ፡፡ ጸሎት ከአቶሚክ ቦምብም በላይ ነውና፡፡
ሁሌም እንደምለው የሃይማኖት አባቶች በየበዓታችሁ ዝጉና ለበጎቻችሁ ጸልዩ፡፡ እረኞች ካለበጎቻቸው
ምንም ማለት አይደሉምና መጽሐፉም “ተዓቀብ ዘንተ በዐቢይ ትጋህ” ይላልና አንዳንዶቻችሁን ከምናማበት አልባሌ ተግባራት
ተቆጥባችሁ በጸሎትና ምህላ ሀገራችሁን ከአረማውያን የጥፋት ውርጂብኝ ታደጉ፡፡ ሌላውን ለሥውሩ የመለኮት ተዓምር እንተወው፡፡ ቀኑ
ደርሷል፡፡ ሆኖም ቢሆን ወዮ ለኦነጋውያን!! ወዮ ለዚህ ሥጋ ለባሽ የአጋንንት ውላጅ!! ወዮ ለምድሪቱ፤ በሚታየኝ ነገር ሣር ነከስኩ፡፡
Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment