Monday, January 30, 2023

በፋሺዝም ፍቅር የወደቀው የሰዎች ቅሪተ አካላት ሊቅ ዘረአሰናይ ዓለምሰገድ ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 2/30/23

 

በፋሺዝም ፍቅር የወደቀው የሰዎች ቅሪተ አካላት ሊቅ ዘረአሰናይ ዓለምሰገድ

ጌታቸው ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY

2/30/23

ትናንት ማታ ይህንን ጽሑፍ በማዘጋጅበት ወቅት ፕሮፌሰር ዘረአሰናይ አለምሰገድ አዲስ በተዋቀረው የትግራይ ካቢኔት ከተመረጡት የውጭ አገር “ዲያስፖራ ትግሬዎች” አንዱ ነው። ሌላኛዋ ድግሞ በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ስራ የነበራት እዚህም እዛም ወያኔን ወክላ ስትንቀዠቀዥ የምናያት ዶ/ር አክሱማዊት የተባለቺዋ ሌላኛዋ ወያኔ መሆንዋን የትግራይ ወያኔ ዜና ማዕከሎች አስተጋብተዋል።

በዚህ የተነሳ ሳይንቲስቱ ዘርአሰናይ አለምሰገድ “ከጦርነት መከላከል ወደ ሙከራ ሰላም” በሚል  ርዕስ ትግሬዎች በተሰበሰቡበት አዳራሽ የተናገረውን ለታሪክ ጸሐፍትና እንዲሁም ለጋዜጠኞችና አወያዮች ይጠቅም ዘንድ ለማሕደራችሁ ይዘገብ ዘንድ እነሆ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ አባባሎቹ ፋሺሰታዊ/ ናዚአዊ መሆናቸውን እያመሳከርኩ እተነትናለሁ።

ካሁን በፊት ሰለ ዘርአሰናይ አንድ ጽሑፍ አቅረቤአለሁ። ዘርአሰናይ አለምሰገድ ትውልዱ የእኔ እትብት በተቀበረባት እኔ ከተፈጠርኩ በሗላ የተወለደ ወጣት አክሱማዊ ነው።

በምርመራዬ በተመለከትኩት መሰረት ወያኔ ከመመስረቱ በፊት ዕድሜው የ4 አመት ህጻን ነበር። በሙያው ዓለም በአንደኛ ደረጃ እውቅና ያወቀው  paleoanthropologist ነው ። ፖሊዮንተሮፖሎጂስት ማለት ከመሬት ጥናት ጋር የተያያዘ የጥንት ሰዎችቅሪተ አካላትን” ያጠና ሊቅ ማለት ነው። ግኝቱ እንደምታውቁት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 3 ሚሊዮን ዕድሜ በላይ ያላት የመጀመሪያዋ የሰው ልጅ የሆነች ህጻን “ሰላም” የተባለች ሙሉ አካላዊ አጥንቶችዋን ያገኘ ነው። ስለዚህ ተማሩ ከሚባሉት ክፍሎች በላይኛው እርከን የሚገኝ ምሁር ነው።

ታዲያ ይህ ምሁር በሚያሳዝን መልኩ የወያኔ ፋሺሰት ርዕዮትን የሚከተል ወጣት ሆኖ ሳገኘው በጣም አዘንኩ።  ወያኔዎችን “መሪዎቻችን” በሚል ያቆለጳጵሳቸዋል። ለምን በፋሺሰቶች ርዕዮት ፍቅር ሊወድቅ ቻለ የሚለው መልሰ ለማግኘት፤ የጀርመን አለም አቀፍ የሃይማኖት፤ የሳይንስና የፍልስፍና ሊቃውንት ለምን በናዚ ፍቅር ሊወድቁ ቻሉ የሚለው ጥናት አብሮ ስለሚመለስ ያንን በተመለከተ የሕሊና እና የልቦና ሊቃውንት የጻፍዋቸውን በርካታ መጻሕፍቶችና የጥናት ወረቀቶችን ኣግኝቶ ማንበብ ይረዳል።

ይህ ምሁር መሪዎቼና መንግሥታችን ሚላቸው መሪዎቹ የሚናገሩትን በመድገም ጦርነት ጀማሪዎቹ “ወራሪዎች” በሚላቸው እንደተጀመረና የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀልም በትግራይ እንጂ  በአፋሮችና አማራዎች እንደተፈጸመ አያምንም ወይንም ተናግሮ አያውቅም።

ከሦስተኛው “ራይክ” ውድቀት በኋላ ጀርመኖች ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሌሎች አገሮችን በሰፊው ተጠያቂ አድርገዋል። የናዚ ጋዜጠኛ ሂልዴጋርዴ ሮዝሊየስ የተባለ በ1946 ‘ጦርነት በመጀመራችን ጥፋተኛ እንዳልሆንን እያንዳንዱ ጀርመናዊ ያውቃል’ ሲል ተናግሯል። ፕሮፌሰር ዘርአሰናይም ከዚህ አልተለየም።

ስለ  ዶ/ር ዘርአሰናይ ዓለምሰገድ ካሁን በፊት ጥቂት አስተያት ሰርቼ ነበር። ድንገት ድረገጽ ስመለከት ወጣቱ በወያኔ “ፈሲቲቫል” ተገኝቶ ብዙ ምሁራን እና ደናቁርት ትግሬዎች የተገኙበት አዳራሽ ላይ ተገኝቶ የተናገረውን ንግግር የዜና ማዕከሎች እንደ አዲስ ለጥፈው ፕሮፓጋንዳውን ሲለጠፉለት አይቼው፤ እኔም ሳደምጠው ካንድ የተማረ ሰው የማይጠበቅ ያውም የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ተመራማሪ ከሆነ ምሁር ፋሺሰቶችን ሲያወድስና ትግራይ ውስጥ ያሉት ታሪካዊ ቅርሶችና ድንቅ የአክሱማዊያን ዘመን ውጤቶች ከትግሬዎች ሌላ ባለቤት እንደሌላቸው ሲናገር እርግጠኛ ሆኖ ነበር በሃይለኛ ቃል እየተናገረ አድማጮቹን በግርምታና አድናቆት ሲያንጨበጭባቸው የነበረው።

እስኪ የዚህ ምሁር ክርክር እውነታ ካለው አንድ ባንድ እንምልከት።

<<  በሺዎች አመታት ያስቆጠረ  የአክሱም፤ የይሓ፤ የገረዓልታ ፤ የማይ ጋዕዋ፤ የመዛብር እና የተምቤን ጥንታዊ የዓለት ምሽጎች በዚህ ወረራ  አፍርሰውታል ወይንም የራሳቸው ሊያደርጉዋቸው ላይ እና ታች እያሉ ነው።

ረዢም ፍልስፍና፤ኪነጥበብ፤ የንጉሥ ካሌብ፤ የቅዱስ ያሬድ ፤ አባ እስጢፋኖስና ዘርአያዕቆብ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ሳይረዱት የራሳቸው ሊያደርጉዋቸው በመድከም ላይ ናቸው። ያልተረዳቸው ነገር ግን ይህ ሁሉ የትግራይ ባህልና ክብር በብዙ ደምና መስዋዕት የተገነባማ የተጠበቀ አንደሆነ አላወቁም። >>

ሲል የተጠቀሱት ጥበቦችና ዕድገቶች የትግሬዎች እንጂ ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ነገድ የአክሱም ዘመን ሥልጣኔ ክብርና ጥበቃም ሆነ ለግንባታውም ለህለውናው ቀጣይነት መስዋዕት ወይንም አስተዋጽኦ ያደረገ ማንም የለም። ይላል ዓይኑን በጨው አጥቦ። (አማራውም አገውም… ሌላውም አይመለከትም፤) ሲል ደምድሟል።

በተመሳሰይ መልኩ ባለፈው ሳምንት መቀሌ ውስጥ እነ ጻድቃን ወ/ልደተንሳኤና ፋሺሰቱ ምግበይ የተባለው የወያኔ አዋጊ በተሰበሰቡበት አዳራሽ “ጌታቸው አረጋዊ” የተባለ የወያኔ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲል የነ ዘርአሰናይ አባባል ደግሞታል፤-

<< ከአክሱም ውድቀት በላ የትግሬዎች ፈጠራ የሆነው የቤተክሕነት ትምህርት ከደብረዳሞ፤ አክሱም ወዘተ.. ጠቅልሎ ወደ ጎንደር ነው የሄደው፤”ዋልስ ባጅ” የተባለ የታሪክ ጸሐፊ “ዋልድባ” በሚል መጽሐፉ ውስጥ ትናንት ስመለከት እያሱ ቀደማይ የተባለ የጎንደር ንጉሥ በየሳምንቱ ሊቃውንት የተባሉ ከትግራይ ከማንኛውም ቦታ እየሰበሰበ ጠጅ እየጋበዘ ሊቃውንቱ ሁሉ ወደ ጎንደር እንዲከማቹ አድርጎ ትግራይ በተገላቢጦሽ ወደ እዛው እየሄዱ መማር ጀመሩ። ስለዚህም እውቀታችን ሌሎች የራሳቸው አደረጉት ይላል።

 አንግዲህ ያሬድ አንኳ ወደ ጎንደር የሄደው በ6ኛው ክ/ዘመን አካባቢ ነው ይህ ጋዜጠኛ የሚያወራው ደግሞ አክሱም ውድቀት በላ ይላል ጋዜጠኛ ጌታቸው አረጋዊ።

ዶ/ር ዘርአሰናይም ይሁን እርሱን የመሰሉ ስለ ቅዱስ ያሬድ ስራዎች ትርጉማቸው እናውቃለን አማራው አያውቅም የራሱም አይደለም ለሚሉት ሁሉ ይህንን ጥያቄ ላቅርብለት።

ቅዱስ ያሬድ ስራ የትግሬ እንጂ የአማራ አይደለም ስትል ማስረጃህ ምንድ ነው? የሚል ልጠይቅና ወደ ማብራራቴ ልግባ። ወዳጄ ሰዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን የጻፋቸው ጽሁፎችን እየተመለከትኩ አንዳንድ ጉዳዮች እንዲያብራራልኝ ሁሌም እጠይቀዋለሁ። አምሳሉ የኪነት ምሁር ነውና ሁሌም እጠይቀዋለሁ። አምሳሉ እንዲህ ይላል።

<<፡አክሱም የትግሬ የሚመስላቸው ሰዎች ቅዱስ ያሬድ አክሱማዊ ነው ሲባል ትግሬ ይመስላቸዋል፡፡ በእርግጥ ቅዱስ ያሬድ በተነሣበት ዘመን ትግሮቹ ወደ ሀገራችን ከገቡ ብዙ የቆዩ ባይሆኑም እዚህ ሀገራችን ውስጥ ነበሩ፡፡ ይሁንና ከዓመታት በፊትም እንደገለጽኩት ቅዱስ ያሬድ አማራ እንጅ ትግሬ አይደለም፡፡ ይሄውም ይታወቅ ዘንድ የዜማ ምልክቶቹን ሥያሜዎች  ቅናት ድፋት፣ ደረት ጭረት ይዘት አንብር ሒደት እርክርክ ድርስ ቁርጥ ብሎ በመሠየም ማርኛ አድርጓቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ አማራ ለመሆኑ ይሄ ግልጽ መረጃ የማይበቃው ካለ ራሱን ቅዱስ ያሬድን ጎንደር ተሠውሮ ካለበት ቅዱስ ቦታ ደብረ ሐዊ ከተባለው ዋሻ (የማያምኑ ወገኖች ያረፈበት ቦታ ይሉታል) ሔዶ በሱባኤ ሊጠይቀውና ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ >>

እንግዲህ ዶክተር ዘረሰናይ አለምሰገድ ይህንን እንዴት ይመልሰው ይሆን? በጎሰኛነት ስሜትና በተሳሳተ የፋሺሰት ትምህርትና የተሰበከው ለወጣቱ ዘርአሰናይ ብቻ ሳይሆን በውሸት ያደጉ የፋሺሰት ካድሬዎችና ባልሆነ ትምክህት ስትወጣጠሩ ትዕግስት ይኑራችሁ እያልኩ የምመክረው ይህንን ፈታና እንደሚደቀን ስለማውቅ ነው። እውነታው ይኼው ሰጥቻችለሁና መልስ ካላችሁ ሜደውም ፈረሱም እነሆ!  አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል! ስለሆነ በዚያኛው ወገንም “ሹል” ብዕር አለና እየተስተዋለ ይሁን! የምለው ለዚህ ነው።

ዘርአያዕቆብም ለምን ከአክሱም ወደ ሸዋም ሆነ ወደ  ኢምፈራንዝ (ጎንደር) ሄዶ “ዘርአያዕቆብ ኢምፈራንዛዊ”  ተብሎ ትዳር መስርቶ እንደኖረ  የሚነግረን ነገር እነዚህ አካባቢዎች የጥንታዊዋ አክሱም ሕዝቦች መኖራቸው ማሳያ ነው።  ለዚህ ነው ሁሌም ለትግራይ ወገኖቼ የምመክረው “እየተስተዋለ እንጂ” የምለው።

አክሱም የትግሬዎች ነው የሚለው የዘርአሰናይ የታሪክ ስግብግብ የኔነት ብቻ ባሕሪ መልስ እንዲሆነኝ የማቀርበው ጥቅስ ተመራማሪው የምጣኔ ሃብትና የታሪክ ምሁር የሆነው አቻምየለህ ታምሩን ነው።

አቻምየለህ ከታች የጻፈው መልስ በእንግሊዝኛ ሲሆን አቻም የጻፈውም ተገንጥለው “ሃገረ ትግራይ” የሚባል አገር ለመመስረት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ለተገነጠሉ ፋሺስትነትን የተከተሉ ለወያኔ የፖለቲካ ቄሶችን የሰጠው መልስ ነበር።  ልክ አንደ ዘርአሰናይ እነዚህ ቄሶችም “ግዕዝም ሆነ ሃይማኖትና ስልጣኔ”  ብቸኛ  የአክሱም ስልጣኔ የትግሬዎች ብቻ ነው የሚል የግንጠላ አዋጅ ሲያስነግሩ የሰጣቸው መልስ ነበር። ይህንን ወደ አማርኛ ተርጉሜ ላቅርበው። እነሆ አቻም እንዲህ ይላል፦

<<  የአክሱም ታሪክ እና ስልጣኔ በቡድን ቢከፋፈል የማይሆነው ለትግሬ እና ለትግራይ ብቻ ነው። የአክሱም ማዕከል የሆነው የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ ከትግሬ ወይም ከትግራይ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። የኢትዮጵያ መንግስት ማዕከሉን አክሱም ከተማ ሲያደርገው ትግራይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም ሆነ ትግራይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ “ትግሬ” (ትግራዎት) የሚባል ሕዝብ አልነበረም።,,,፣>> ይልና በመቀጠል

እንደ እነፕሮፌሰር ዘርአሰናይ የማሳሰሉትን አርኪዮሎጂሰቶችንም አንዲህ ሲል ይማጸናቸዋል።

<< በነገራችን ላይ አክሱም የትግሬ ሥልጣኔ እንደነበረች የሚያሳይ አንድ የታሪክ ማስረጃ (የድንጋይ ጽሑፍና የአርኪዮሎጂ ማስረጃ) አለኝ የሚል የትግሬ ብሔርተኛ ፕሮፌሰርና ዶክተር አርኪዮሎጂሰት ካለ እኛ ስህተተኞች ሆነን እነሱን የምናምን  መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን። ይህ የሚያቀርብ ተመራማሪ ካለ ምስጋናችን ወደር የለውም። >> ሲል የእነ ዘርአሰናይ ዓለምሰገድ “ፉፋነት” በባዶ አስቀርቷቸዋል።

እነሆ በተጠየቀው መሰረት ዘርአሰናይ እስካሁን ድረስ አንድም የድንጋይ ምርምር አክሱምም ሆነች የአክሱም ስልጣኔና ግዛት የትግሬዎች ብቻ መሆንዋን ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም።

እንቀጥል፡-

ዶ/ር ዘርአሰናይ በሚገርም አገላላጽ ስለ ትግራይና የትግራይ መሪዎች በፋሺስታዊ  አንደበት እንዲህ ይላል፡

<< እኛ ከትግራይ ውጭ የምናመልከው ሕዝብ የምንምበረከክለት የምንሰግድለትና የምንሳሳለት ሕዝብ ማንም የለም!! >> ይላል። በተመሳሳይ  “Tembrant als Erzieher” የተባለ የናዚዎች ጋዜጣ

“German for the Germans. A Jew can no more became a German than a plum can turn into an apple. There is no one outside of Nordic race that we bow down to.”

ይህ አባባሉ፤ ናዚዎች ከኖርዲክ ዘር ሌላ የምንሰግድለትና የምናመልከው ሌላ ዘር ወይንም ሕዝብ የለም የሚሉት ኣይነት አባባል አንድ ነው።

 ከዚህ ሌላ ዘርአሰናይ ሽልማቱን ለመቀበል ቫቲካን ጣሊያን አገር ሄዶ የአለም ሊቃውንት በተሰበሰቡበት አዳራሽ “ስለ ትግራይ ጦርነት ነበር ብዙውን ንግግሩ ያጠፋው። እዛ ላይ አንደ ምሁር ትግሬዎች በአፋሮችና በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረሱት ጉዳት አንዲትም ቃል አልተነፈሰም። በሚገርም ሁኔታ ደግሞ በመግቢያው እኔ “ኢትዮጵያዊ ትግሬ” ነኝ እያለ ሲናገር ትግሬዎች ስብሰባ ላይ ሲህድ ግን “እኔ ከትግራይ ሕዝብ ውጭ የማመልክውም ሆነ ደጅ የምጠናበት ወይንም የምሰግድለት ሕዝብ (ዘር) የለም ይላል።

በመቀጠል ፕሮፌሰር ዘረሰናይ እንዲህ ይላል፡

<< ወራሪዎቻችን ብዙዎች ናቸው። መንግሥታችን (የወያኔ የትግራይ ማለቱ ነው) ስለ ሰላም ሲማጸኑ ከፍራቻ ኣይደለም …..ዛሬ የገጠመን ጦርነት የዘር ማጥፋት ውጊያ ነው። መጀመሪያ በመሪዎቻችን ሕሊና ውስጥ ያለውን አስተሳሰብ ለማጥፋት ሞክረዋል፤ ሳይሳካለቸው ሲቀር  መሬታችን ንብረታችን ለመዝረፍ ሞክረዋል ፤ በከፊል ተሳክቶላቸዋል። ያለተሳካላቸው እና ምስሩን ያለወቁትና ሊያገኙት የማይቻላቸው ንነታችንን ነው። ትግራዎትነታችን በሻንጣ ውስጥ ወይንም በአለት  ምሽግ ውስጥ የተደበቀ በቀላሉ የሚገኘው  ማንነት አይደለም።ማንታችን ‘በልባችን፤ በአንጎላችን የተጠበቀ ነው። ይህ ነው ያልተረዳቸው>> ይላል፡

በተመሳሳይ  ሂትለር “መይን ካምፕፍ” (የኔ ትግል) በሚለው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፤

<<  የኖርዲክ ማንነት ማንም ዘር ሊያገኘው የማይቻለው በሕሊናቸው ውስጥ የታቀበ ማንነት ነው። ሰዎች የአፈጣጠር (ፋካልቲ) ልዩነታቸውን ሳይረዱ Pug-Dog (ድንክዬ ውሻ) የ“Grayhound” (ቀጭን፤ ሸበላ፤ ፈጣን ሯጭ እና አዳኝ የሆነ ውሻ ) ሥራ ተክቶ እንዲሠራ እንደማሰልጠን መሞከር  ዓይነት ነው። ፑድል (ትንሽየ ውሻ) በማንኛውም የሥልጠና ዓይነት ብታሰለጥናት በአንዱ ወይም በሌላ መልኩ የታቀበን ነገር ቆፍራም ሆነ አሽትታ ልታገኘው የማይቻላት ምክንያት የአፈጣጠር ጥራቶች ልዩነት እንዳለ ሰዎች ሊረዱ አልቻሉም >> ይላል ሂትለር።

ዶ/ር ዘርአሰናይም እኛ “እና እነሱ” በሚለው አመለካካቱ ከሂትለር አልተለየም።

ይህ ሁሉ ጽንፈኝነት የማየው ብዙውን ጊዜ በትግራይ በምሁራን ላይ ነው። ታዲያ የትግራይ የምሁራን ባህሪ እንዴት እንደምተረጉመው ስጥር ይጨንቀኛል። የትግራይ ቀደማይ እና ዳግማይ ወያነ በእነ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ  አለምሰገድ አድናቆት ተችሮአቸው ሲመለኩ በመጀመሪያውም ሆነ በሁለተኛው ወያኔ አማራ፤ አማራ፤አማራ የሚለው መነሻ እንደነበርና፤ “የአማራን ብሔር እስከዘላለሙ ሰላም እንድያጣ” በመመሪያ ተነድፎ የገዛ ደም አጥንታቸው የሆነውን ማሕበረሰብ እስከዛሬ ድረስ በመጥላትና ደም በማፍሰስ መነሻ ያደረገ የትግራይ ናዚዎች እንቅስቃሴ ወደ ስልጣን መጥቶ “መንግስታችን እና መሪዎቻችን” የሚል ምሁራን በሚባሉት በእነ ዘርአሰናይ አላምሰገድ አንደበት የሙገሳ ማዕረግ ሲቸራቸው የነዚህ ምሁራን “ድውይነት” ባህሪ ለመግልጽ ብሞክርም ምን ብየ አንደምገልጽአቸው እቸገራለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Thursday, January 26, 2023

የጠቅላይ ሓሳዩን ጓደኞች እንተዋወቅ!! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 2/27/23


የጠቅላይ ሓሳዩን ጓደኞች እንተዋወቅ!!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

2/27/23

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ዲያቢሎስ በሙሉ ኃይሉ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ የሚከታተል ሁሉ ይረዳዋል፡፡ ይህን የሚክድ ጤናማ ሰው ይኖራል ብዬም አልገምትም፡፡ ዋናው ጤነኞች ስንት ይሆናሉ የሚለው ጥያቄ ነው፡፡

ወደ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ማለቴ ሚኒስትራቸው ጓደኞች ከማምራታችን በፊት እንደተለመደው ስለሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ስለምትገኝበት የመከራ አዘቅት ጥቂት እንበል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ዲያቢሎስ ዲያቢሎስ እያዋዛ ሀገራችንን የለዬላት የደም ባሕር እያደረጋት ነው፡፡ እንደምገምተው በአሁኑ ወቅት የመለስ ዜናዊን የተኮነነች ነፍስ ጨምሮ ታላላቅ የሣጥናኤል የሲዖል ባለሟሎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የመጨረሻውን አርማጌዴዖን በማከናወን ላይ ናቸው፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ብናይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ፍም እቶን ላይ ተጥዳለች፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ እንዲሁም ከሞላ ጎደል በሁሉም ጠቅላይ ግዛቶቿ ሶዶም ወገሞራዊ ነበልባል እየተንቀለቀለ ነው፡፡ በውጤቱም በሁሉም የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በግልጽም ሆነ በእጅ አዙር የተቀመጡት አክራሪ ኦሮሞዎች ከዋናው ቤተ መንግሥት እስከ ክልል መስተዳድር እየተናበቡና እዚያና እዚህ በደስታ እየቦረቁ አማራን በመጨረስ ላይ ይገኛሉ፡፡

 የኦነግ ቅን ታዛዥ የሆኑት ብአዴኖችም ሆዳቸው አይጉደል እንጂ እንመራዋለን የሚሉትን አማራ በአቢይና ሽመልስ ቅልብ ጦር ለማስፈጀት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ሰሞኑን ሰሜን ሸዋ ውስጥ የአማራን ልዩ ኃይል በተኛበት በኦነግ ማስጨፍጨፋቸው አንዱ ማስረጃ ነው፡፡ አማራም በተዘረጋለት ወጥመድ ዘው ብሎ በመግባት ወያኔ የጠነሰሰለትንና ኦነግ/ኦህዲድ የተረከበውን በአማራ ላይ የታወጀ ጄኖሳይድ (የዘር ፍጂት) ማስተናገዱን ቀጥሎበታል፡፡ እርግጥ ነው መጨረሻው ድሉ ለአማራና አማራዊ ኢትዮጵያውያን መሆኑ ባይጠረጠርም ለጊዜው ግን የተዘረጋው ኦነጋዊ ሞራ የሚያስነብበን ሌላ ነው፤ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር ተጠምዶ፣ ወደ አማራነት ነገዳዊ ስሜትም አልወርድም ብሎ በብዛትም በዕውቀትም ከማንም ሳያንስ እንዲሁ እያለቀ የሚገኘው አማራ በመሆኑ የዚህን ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮ የሚጋራ ሌላው ጎሣና ነገድ ሁሉ በመጨረሻ ከዚህ የተገፋ ሕዝብ ጋር በመተባበር ጠላቶቹን ድባቅ እንደሚመታ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ አዚሙ ሲለቀው፣ መከራው እስከአንጀቱ ሲዘልቀው የሚፈጠረውን ማየት በርግጥም ያጓጓል፡፡

ፖለቲካውን የተቆጣጠሩት ኦነጎች ሃይማኖቱንም ለብቻ ለመቆጣጠር ባቀዱት መሠረት ይሄውና ያላንዳች ሀፍረት ድፍን ማይማንን በድፍረታቸው፣ በዘር ሐረጋቸው፣ በቋንቋቸውና በሥልጣንና ገንዘብ ወዳድነታቸው መሥፈርት በመመልመል ጳጳስና ፓትርያርክ  በሚል ሹመት አንበሽብሸው ኦርቶዶክስን እየበታተኗት ነው፡፡ ከደነቆሩ አይቀር ታዲያ እንደዚህ ነው፡፡ ጥጋብ ኅሊናን ያሳውራል፡፡ ትናንትን ያስረሳል፡፡ ነገን ያርቅና የሽዎችን ዕድሜ በመስጠት በዕብሪትና ትምክህት ያደነዝዛል፡፡ እንደጥጋብ መጥፎ የለም፡፡

ኦነግ/ኦህዲድ ጥጋቡን መቆጣጠር አልቻለም፡፡ የጠገበ ደግሞ ከተራበም በከፋ እንደሚታዘንለት ብሂሉ አስቀድሞ አጽድቆታል፡፡ የጠገበ የሚናገረውን ብቻ ሳይሆን የሚያደርገውንም አያውቅም፡፡ ዕውቀት ላይ ያልተመረኮዘ ጥጋብ ደግሞ ገደል ይከታል፡፡ ለጊዜው ግን በሚያጥበረብር ጊዜያዊ ድል ያጃጅላል፡፡ አርፎ የተኛውን አማራ ከወዲያ ከወዲህ የሚጎነታትሉትና ዘሩን ለማጥፋት የሚራወጡት ተረኛ ኦሮሞዎች መጨረሻቸውን ያብጅላቸው እንጂ አካሄዳቸው እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ከወያኔ አለመማራቸው ደግሞ የድንቁርናቸውንና የጅልነታቸውን ለከት-የለሽነት በጉልኅ ያመለክታል፡፡ የወያኔን ጥጋብ መጨረሻ ያዬ ከወያኔም ብሶ እንዲህ ሲቀብጥ መታዘብ ከማሳዘን አልፎ የሰውን ልጅ ተፈጥሮ እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡ ውሻና ድመት እንኳ ከውሻና ከድመት ይማራሉ፡፡ የነዚህ ድንቁርና ግን ይለያል፡፡

እንደእውነቱ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ አትጠፋምም፡፡ ከዶፉ ዝናብ የሚተርፈውን አንድዬ ይወቀው እንጂ ከጎርፉና ከውርጅብኙ በኋላ ኢትዮጵያ ከነሙሉ ግርማ ሞገሷ ትነሳለች፡፡ በምን መልክ እንደሆነ አላውቅም እንጂ ዓለምንም ትመራለች፡፡ አዲስ ነገር አልተናገርኩም፡፡ በተደጋጋሚ ሲነገር የተሰማውንና ብዙዎች እንደቀልድ የሚወስዱትን ነባር የአበው ቃል ለማስታወስ ያህል ነው፡፡

ኢትዮጵያ የምትነሳ መሆኗ እንዳለ ሆኖ መጥፋት ካለባትና የዓለምም ፍጻሜ በርግጥም ደርሶ ከሆነ ከዚህ ጊዜ የበለጠ የትንቢቶች መገጣጠም ታይቶ እንደማያውቅ መመስከር ይቻላል፡፡ ሌሎች ሀገራት ጣጣቸውን ጨርሰው የምጽዓትን ቀን የመጨረሻ ፊሽካ  እየተጠባበቁ እንዳሉ ሀገራቱ ከሚመሩት ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ሕይወት መገንዘብ እንችላለን፡፡

በብዙ ሀገራት ጳጳሳትና መነኮሳት ሳይቀሩ የግብረ ሶዶም ኃጢኣቶች ሰለባ ከሆኑና እንዲያውም አብያተ ክርስቲያን ወደ ጭፈራ ቤትና ወደ ሙዚየምነት ከተቀየሩ ቆየት አሉ፡፡ በብዙ ሀገራት የእግዚአብሔርን ስም መጥራት እንደፋራ የሚያስቆጥርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ቁሣዊነትና ኢ-አማኒነት ፋሽን ከሆኑ ሰነበቱ፡፡ ኢሉሚናቲ በመባል የሚታወቁትና በግልጽም በተዛዋሪም የዓለማችንን ፖለቲካና ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው በመንግሥታት ጀርባ በተለጠፈ ሥውር አንቀልባ ውስጥ ሆነው ምድርን የሚዘውሯት ኃይላትም ሰዎችን ከፈጣሪያቸወ ጋር አለያይተው ዓለማችንን በሞራልም በምግባርም ባዶ እያደረጓት ነው፡፡ የኢትዮጵያን ያህል የማያስጨንቋቸው ሌሎች ሀገራት እንዳሉ ቢገመትም በወጥመዳቸው ሳትገባ የቀረችውና በታሪኳና በሃይማኖቷ ጠንክራ ዲያቢሎስን ሌት ከቀን እንቅልፍ ትነሳ የነበረችው ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ እርሷንም ወደጨለማው ግዛታቸው ለማካተት በተለይ ልጃቸውን አቢይ አህመድን ወደ ሥልጣን ካመጡ ወዲህ በተወሰነ ደረጃ እየተሳካለቸው ስለመሆኑ ብዙ ምልክቶች ይታያሉ - ለጊዜው ቢሆንም አልተሳካላቸውም ማለት አንችልም፡፡ በዚህ ዘመን ከነሱ አመራር ውጪ የሚንቀሳቀስ ኃይል የሚገጥመው መከራና ፍዳ ቀላል አይደለም፡፡ ራሽያን ማየት በቂ ነው፡፡ የቬንዚወላው መሪ ሁጎ ሻቬዝ የተገደለበትንም ምክንያት መመርመር ተገቢ ነው፡፡(የጆን ፐርኪንስን መጽሐፍ አንብብ ከፈለግህ! Confessions of an Economic Hitman)) በሀገራችንም ጥቂቶች ብዙኃንን እንዴት አንቀጥቅጠው እንደሚገዙ ማየት ይቻላል፡፡

በ40 እና በ50 ሚሊዮን የሚገመተው አማራ ድብልቅልቁ እንዲወጣ ተደርጎ በራሱ ሰዎች ሳይቀር ወደ መቀመቅ እየወረደ የመታየቱ ምሥጢር የሚገናኘው ከዚህ ዓለም አቀፍ ሰይጣናዊ የጥፋት ኃይል ነው፡፡ እንጂ ኦነግም ሆነ ሕወሓት ወይም አጋሰሱ ብአዴን ከሰሜን ሸዋ ጦረኞች የሚያልፍ ኃይል አስፈልጓቸው አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለውና የወደፊቱ አስፈሪ ጨለማም የተጋረጠብን ንግርቱ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ የተከበብነው በሐጎስና በቶሎሣ ወይንም በከርሳም ሎሌዎቻቸው አገኘሁና ደመቀ ብቻ ሣይሆን በሉሲፈርና የርሱ ታዛዥ በሆኑት በነኤሎን መስክ፣ በነአንቶን ሌቪና አድሪ ኖርተን የጨለማው ግዛት አባላትም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ የገጠመን ጦርነት ከሕዝብ ብዛት አኳያ የስንፍናና የፍርሀት አድርገን ልንወስደው እንችል ይሆናል እንጂ ረቀቅ ያለና መናፍስትም የሚሣተፉበት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ መፍትሔው ግን ቀላል ነው፡፡ ተመጣጣኝ ጥረት ማድረግ ብቻ፡፡ ከነሱ የበለጠ ትኩረት መስጠት፡፡ አለመፍራት፡፡ የፈጣሪን ጦርና ጋሻ መታጠቅ፡፡ ጎልያድን በሚመስሉ ግን በቀላል ንፋስ በሚበተኑ የአጋንንት መንጋዎች ላይ ዳዊታዊ ወንጭፍን መጠቀም፡፡ የጠላትን ኃይል አክብዶ አለማየት፡፡ በቃ፡፡

ልድገመው!

ኢትዮጵያ ይህን ጊዜ ታልፈዋለች፡፡ ስታልፍና ለማለፍ ስትጥር ግን ብዙ ዋጋ ትከፍላለች፡፡

ተመልከት!

 ፖለቲካው በማን እንደተያዘ እናውቃለን፡፡ ለማስታወስ ያህል አንዳቸውም ሀገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት የሌላቸው ሆዳሞች፣ በሀሰት ዲግሪዎች የተንበሸበሹ ማይማን፤ ከ6ኛና ከ7ኛ ክፍል ያላለፉ ደናቁርት፣ ከሆዳቸው በቀር ዘመድ የሌላቸው ዓሣሞች፣ ፍትህን በገንዘብና በዘረኝነት እንዳሻቸው የሚያዛቡ ዳኞች፣ በሙስና ህግንና መመርያን የሚጥሱ መለዮ ለባሾች፣ ሀገርን በመሸጥ ጭምር ሀብት የሚያካብቱ ሚኒስትሮችና ኮሚሽነሮች ወዘተ. የሚመሯት ሀገር የትም አትደርስም ብቻ ሳይሆን በየቀኑ ወደመቀመቅ እንደምትነጉድ ለመገንዘብ ከዐይናችን በላይ ዋቢ አያስፈልገንም›፡፡ በፖለቲካው ተስፋ ስንቆርጥ ወደሃይማኖቱ መዞራችን ደግሞ አግባብ ነው፡፡

ሃይማኖቱን ስናይ ሁሉም በሚባል ደረጃ በኃጢኣትና በወንጀል ድርጊት የጨቀዬ ነው፡፡ የትኛው የሃይማኖት መሪ ስንት ሀብት አካበተ፣ ከስንቷ ዲቃላ ወለደ የሚለው የቁጥር መበላለጥ ካልሆነ በቀር ሁሉም በኃጢኣት ሥር የሚርመጠመጥ ከንቱና የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ማንም በማንም ላይ ወቀሳ ለመሰንዘር የሞራል ብቃት የለውም፡፡ ለምሣሌ ይህ ሁሉ ግፍና በደል በተለይ በወለጋና በትግራይ እንዲሁም በሸዋና በሻሸመኔ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ልክ እንደአቡነ ጴጥሮስ ግፈኞችን አውግዞ የሰማዕትነትን መለኮታዊ ፀጋ ለመቀበል አንድም ጳጳስ አልደፈረም፡፡ በልማዳዊው አገላለጽና እንደውነቱም ከሆነ አንድ ሰው መነኮሰ ማለት ሞተ ማለት እንደመሆኑ የሞተ ሰው ምንም የሚፈራው ነገር ሊኖር ባልተገባ ነበር፡፡ …. ስለሆነም የጠፋነው ሁላችንም ነን፡፡ የጠፋነው ከአናት ጀምሮ ነው፡፡ የጠፋነው የቃየልን ወንድምነት ሁላችንም በመጋራታችን ነው፡፡ እናም ንስሃ መግባት ያለብን ሁላችንም ነን፡፡ ክፉ ነገር የታዘዘብን ሁላችንም ከእግዚአብሔር መንገድ በመውጣታችን ነው፡፡ ከፈጣሪ ትእዛዝ የወጣ ደግሞ መልካም ነገር አይጠብቀውም፡፡ አመልካች ጣታችንን እንመርምራት፡፡

ይህን ስል ግን ለቅጣት የተላኩብን የእነ አቶ አካለወልድ (የፕትርክና ስሙ ማን እንደሆነ ረሳሁት) መፈንቅለ ሲኖዶስ ትክክል ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ይህ አስቂኝ ድራማዊ ክስተት መጋረጃው ሲዘጋ ይበልጥ በሣቅ የምንፈነዳበት አስገራሚ ትራጂ-ኮሜዲ ነው፡፡ አናት ከተበላሸ ግርጌም ይበላሻል - በፖለቲካውም በሃይማኖቱም፡፡

በሀሰትና በማስመሰል በዓለም የአንደኝነትን ሥፍራ የሚይዘው ጠ/ሚኒስትር ተብዬው ግለሰብ ከትምህርት ደረጃው ጀምሮ ብዙ ይወራበታል፡፡ በ94 ዲግሪ ወስዶ በ96 12ኛን እንደጨረሰ ይነገራል፡፡ ነገሩ ሁሉ “አንበሣ ምን ይበላል?” ቢሉ “ተበድሮ”፤ “ምን ይከፍላል?” ቢሉ “ማን ጠይቆ” እንዲሉ ሆነና ጉዟችን ሁሉ የጭቡና በማኅበራዊ ዕብደት የታጀበ ሊሆን በቃ፡፡

ጨካኝነቱንና ፀረ-አማራነቱን በተግባር እያየነው ስለሆነ መስካሪ አንፈልግም፡፡ ዋሾነቱንና አስመሳይነቱንም በግልጽ የምናይለት፣ እርሱ ግን አብዝቶ የሚኮራበት አጋንንታዊ ባሕርይው ነው፡፡ “ኳስ አበደች” ማለት አሁን ነው ታዲያ፡፡

በመሆኑም በዚህ በብዙ የተምታቱ ስብዕናዎች የሚሰቃይ ሰውዬ ሥር የምትማቅቅ ሀገር እንደነ “ነቢይ” ደምሳሽና እንደነ “እህተ ማርያም” የመሳሰሉ አጭቤዎች ይህን ገልቱ ዜጋ ኪሱን ሲሞልጩትና አእምሮውን ባዶ ሲያደርጉት ብናይ በማንም ልንፈርድ አንችልም፡፡ የዓሣ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ አቢይ አህመድ ዋሾና አጭበርባሪ ሆኖ ሳለ ቸርቹ ውስጥ የሰበሰበውን ጅላንፎ “በባንክ ደብተርህ 10 ሽህ ብር ኢየሱስ ጨምሮልሃል፤ ላቤን የተረግሁበትን ሶፍት ብትበላ ትፈወሳለህ፤ ማታ ነይና ልጸልየልሽ ታረግዣለሽ….” እያለ በሦስትና በአራት ዓመት ሕጻን አእምሮ ምዕመናኑን ቢያጃጅል የሚፈረደው በማንም ሳይሆን በሚጃጃለው ገልቱ ዜጋ ነው፡፡

በየቦታው የሚደረገውን ስንሰማ ኢትዮጵዊ ሆኖ መፈጠርን እንጠላለን፡፡ እጅግ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ነን፡፡ በሃይማኖት ስም የሚፈጸመው ማጭበርበር ገደቡን አልፎ በተለይ አሁን አሁን መንግሥት የለንም እንጂ የመንግሥት ያለህ ያስብላል፡፡ በበኩሌ የዘመኑን ማለቅ የምረዳው ከዚህ አኳያ ነው፡፡ በሃይማኖት ረገድ ህጸጽ መኖሩን ስጠቁም ደግሞ በሁሉም ሃይማኖቶች ማሉቴ ነው፡፡ ከአንድ ዝቅተኛ ገቢ ካለው ደብር ከፍተኛ ገቢ ወዳለው ደብር ለመዛወር አንድ ቄሰ ገበዝ ለሀገረ ስብከቱ ባለሥልጣን የሚከፍለውን ጉቦ ብትሰሙ ታብዳላችሁ፡፡ ስለዚህ ቅርጽና ይዘቱ ይለያይ እንጂ በሁሉም ሃይማኖት የተንሠራፋውንና እግዚአብሔርንም ፊቱን እንዲያዞርብን የሚያስገድደውን ንቅዘትና ነውር ቆጥረን አንዘልቀውም፡፡

እህተ ማርያምና “ፍቅርሲዝም” የሚባልን አዲስ እምነት ዘባራቂው ወጣት ደምሳሽ ግን ለጠቅላዩ በጣም የሚቀርቡት የነፍስ ጓደኞቹ መሆናቸውን ሳልጠቅስ ይህችን ጽሑፍ መጨረስ የለብኝም፡፡ ለመዝናናት ያህል እነዚህን ሁለት አጭበርባሪ የሰይጣን ልጆች ስመለከት በዓይነ ኅሊናየ የሚታየኝ አባታቸው አቢይ አህመድ ነው፡፡ ራሱን ቁጭ አድርጎ ነው የወለዳቸው - በመንፈስ፡፡ የነሱ ቀላል ነው - የሚያጃጅሉት ጥቂት ነውና፡፡ የአቢይ ግን ሀገርን የመምራት ያህል ትልቅ ኃላፊነትና ልጓም በመያዙ እንጦርጦስ እየከተተን ነው፡፡

ሌሎችም አሉ፡፡ እነ እስራኤል ዳንሳ፣ እነ አዩ ጩፋ፣ በሁለት ካራ በሊታው ዳንኤል ክብረት፣ ወዘተ. የዚህ አብሾዋም ጠ/ሚኒስትር የቅርብ ጓደኞችና የዓላማው ተጋሪዎች ናቸው፡፡ መጪውን ጊዜ በጣም ፍሩ ታዲያ፡፡ ዕብድና ወፈፌ ሀገር ሲመራ ዕዳው ብዙ ነው ወንድሞቼና እህቶቼ፡፡

አብዝተን  እንጸልይ፡፡ መከራው በቶሎ እንዲያልፍ፤፣ የቅጣቱ መጠን ለዘብ እንዲል፣ የተደበቀው ወርቃማው መንግሥት በቶሎ እንዲገለጥና የጉግማንጉጉ መንግሥት ወደመጣበት የጥልቁ ጨለማው ግዛት እንዲመለስ ሁላችንም በየምናምንበት የሃይማኖት ራስ ተንበርክከን እንለምን፡፡ ወቅቱ የአሥረሽ ምቺው ሳይሆን የአርምሞና የሱባኤ ነው፡፡ በተቻለን መጠን ከቡረቃና ከጮቤ ረገጣ  እንታቀብ፡፡  

 

 

Wednesday, January 25, 2023

የኢሳያስ ወታደራዊ ሃብሪስ ፣ ናርሲሲዝም እና ደደብነት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/25/2023

 

የኢሳያስ ወታደራዊ  ሃብሪስ ፣ ናርሲሲዝም እና ደደብነት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

1/25/2023

በርዕሱ ላይ የተጠቀሱት የእንገሊዝኛ ቃላቶች ትርጉማቸው ኋላ በምጠቅሰው ሃተታ ታገኝዋቸዋለችሁ። እያደረ የሚገርም ትዕይንት እየመጣ የምናርፍበት ጊዜ አጣን።፡በኦሮሙማው መሪ አብይ አሕመድ ጋባዥነት ወደ ትግራይ ገብተው የነበሩት የኢሳያስ ወታደሮች በተፈጠረው ድንገተኛ የቶከስ አቁም ስምምነትና በወያኔ ታጣቂዎች ላይ “ወሳኝ የሚባሉ የጦር መሳሪያዎች”  የማስፈታት ሂደት ተከትሎ ዱርየዎቹ የኤርትራ ወታደሮች ሰሞኑን ከትግራይ ሲወጡ በዘረፉዋቸው መኪኖች ላይ  GAME OVER THAT IS WHO WE ARE!!”………. (ጌም ኦቨር እኛ እነደዚህ ነን) የሚል ጽሑፍ ለጥፈው በሚያልፏቸው  የትግራይ ከተሞች ጎዳና ላይ ይህንን በገሉህ ለጥፈው በትግራይ ሕዝብ ላይ ያሳዩት ንቀት “ትምክሕታዊ እኔነታቸው” ካየሁ በኋላ፤ ወያኔም ሆነ ትግራይ ውስጥ ለወደፊቱ የሚበቅል ታጣቂ የሽምቅ ወታደር ከተፈጠረ የኢሳያስ ወታደርን ብቻ ሳይሆን የኢሳያስን ስርዓት ሰላም የሚያሳጣ ተዋጊ ሃይል ቢፈጠር ተቃውሞ የለኝም። ያውም ድጋፍ እሰጣለሁ።

 

ይህ ብቻ ሳይሆን ባድሜና የቀይ ባሕር ወደባችንነ ያለ ሕግ የነጠቀው መሬትም የሚያስመልስ ተዋጊ መመስረት የግድ ነው።  

ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔና  የኢሳያስ አፈወርቂ የጭን ገረድ (አብይ አሕመድ በኢሳያስ ግራ ጣት ላይ ቀለበት ሲያስገባለት ፎቶግራፍን አትርሱ) የሆነው “አብይ አሕመድ” ቢሆንም፤ ለወደፊቱ ኢሳያስን የሚቀጣ የሽምቅ ወታደሮች ከትግራይ ቢመሰረት የትግራይ ሕዝብ ድጋፉን መስጠት አለበት። ሌላ ታጣቂ ሃይል እንዲከሰት እስክጠይቅ ድረስ ያደረሰኝ እንዲህ ያለ የሻዕቢያ ብልግና ምን ያህል እንዳበሳጨኝ ማየት ትችላላችሁ።

ወያኔ የሚባል የፋሺሰት አመራር በአማራ ላይ ያለው ጥላቻ ከማርገብና አብይ አሕመድ ላይ እንዲያተኩር ከአማራ ሕዝብ ጋር ዘላቂ ሰላም ፈጥሮ የጋራ ተዋጊ ፈጥሮ ያገሪቷን ጦር ሳይነካ አብይ አሕመድን ለመገርሰስ ከመጣር ይልቅ “ያገሪቱን ወታደር በተኙበት አፍኖ በመጨፍጨፍ” ጸቡ እንዲባባስ አድርጎ በራሱ ላይ ሞት በመደገስ  ለኢሳያስ አፈወርቂና ለአብይ አሕመድ ምቹ ጊዜ እንዲያገኙ አደረገ።

ከዚያም ኢሳያስ ዘው ብሎ ከገባ ወዲህ በትግራይ ሕዝብ ሕይወት ምን በደል እንዳደሰራ በዝርዝር የማውቀው ባይኖረኝም፤ እላይ የጠቀስኩትን በመኪናው ላይ የለጠፈው አስነዋሪ ብልግና እና አንድ ደደብ ኤርትራዊ  እስላም (የፋሺሰት ዘረኛ ቃላቶችን ሁሌም የሚጠቀም ጋዜጠኛ ይሁን ፌዘኛ) አክሱም ሃውልት ላይ ቆሞ ፎቶ ተነስቶ “እኛ እንዲህ ነን የሚለው ከንቱ ጉራ ሳየው “ኤርትራኖች በትግራይ ውስጥ የዘር ማጥፋትም ሆነ ሌብነትና የሴቶች አመጽ” ማድረጉን አልጠራጠርም። ለዚህ ደግሞ መጪው ጊዜ ኤርትራኖች ከባድ ዕዳ እንደሚያስከፍላቸው መገመት ይቻላል።

የኢሳያስ ወታደራዊ ሃብሪስ” (እብሪት) ፣ናርሲሲዝም” (እዩኝ እዩኝ ባሕሪ)  እና ደደብነትን የሚያስተነፍስ ሃይል ከትግራይ የሽምቅ ተዋጊ እንዲመሰረትና የምስራቅ አፍሪቃ ጎብለል የመሆን ፍላጎት የነበረው ሕልመኛው  ወሮበላው ኢሳያስ ልክ በ1998 እራሱ በጫረው እሳት ማኘክ ከሚችለው በላይ ሃፍርት የተከናናውን ያህል ለወደፊቱም እንዲከናነብ ማንኛውም ታጣቂ አለሁ ካለ ድጋፌን እሰጠዋለሁ

ኢሳያስ ይህን ጽሑፍ በወታደሮቹ በኩል መልዕክት እንዲለጥፉ በማድረጉ ኤርትራ በራስዋ ላይ ፋታ የማይሰጥ የወደፊት ቅዠት እንደፈጠረች ማወቅ አለባት። ኢሳያስና አብይ አሕመድ በሰሩት የጦር ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ እንዲከሰሱ የሚያደርግ ማንኛውም የህግ ቡድን ድጋፌን እሰጣለሁ። ያ እስኪሆን ግን ትግራይ ውስጥ ኢሳያሰን የሚቀጣ አፈንጋጭ የሽምቅ ተዋጊ ቡድን እንዲመሰረት ጥሪ አቀርባለሁ። ኢሳያስ በቅርቡ በፈጣሪ ወይንም በራሱ ዕብሪት ይወገዳል። ዕዳ ከፋዩ ግን ሕዝቡ ሆኖ ማየት ያሳዝናል።

አመሰግናለሁ፡

 

 

Monday, January 23, 2023

ከመርሳት ማዳን ያለብን ታላላቅ ትውስታዎቻችንና ማንነታችን ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/23/23


ከመርሳት ማዳን ያለብን ታላላቅ ትውስታዎቻችንና ማንነታችን

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 1/23/23

Please do not forget to watch the video attached at the end after you read.

ባለፈው ጊዜ ስለ ልደቱ አያሌው ተከታታይ ጽሑፍ ማቅረቤ ታስታውሳላችሁ። ትችቴ በልደቱ ይሁን እንጂ እንደ ልደቱ የመሰሉ በሺዎቹ ከሃዲ (ባንዳ) ፖለቲከኞችና (ደካማ) ምሁራኖችን ነው የተቸሁት።

በፖቲካው አለም ብዙም ልምድ የሌላችሁ አንባቢዎች ትችቴ እንደ ቀላል ትችት መስሎ ሊታያችሁ ይችላል።  ለ30 አመት የዘለቅነው እልህ አስጨራሽ ትግል  ባንዳዎችን በመታገል ነበር።። ባንዳ የነበሩ ዛሬ በሚሊዮኖች ግምባር ቀደም ታጋዮች ሆነው ተቀላቅለውናል። ብዙዎቹ  አመርቂ አስተዋጽኦም እያደረጉ ነው። ወደ  እኛው ጎራ ለመቀላቀል በቀላሉ ዘው ብለው አልነበረም የተቀላቀሉን። ዕንቅልፍ አጥተን በምንጽፋቸው በምንከራከራቸውና በምናነቃቸው የብዕር ትግላችን ነው። ወያኔ በጠምንጃ እንዳልተወገደ ታውቃላችሁ። እኛ በምንጽፋቸው የብዕር ትግሎች ወጣቱን ስላስነሳነው ነው።

የኔ የፌስ ቡክ ወዳጆች የሆናችሁ አዳዲስ ወጣቶች በፌስቡክ ላይ ስንቶቻችሁ እንደተከታተሉኝ መረጃ ባይኖረኝም (ጽሑፉን አንብበው ምልክት ሳይሰጡ የሚያልፉ አንባቢዎች ስላሉ) በድረገጼ ላይ ግን የቆዩ ደምበኞች ስላሉኝ ስለሚከታተሉኝ በርካታ ሰዎች እንዳነበቡት አውቄኣለሁ።  አዲሱ ትውልድ ለ30 አመት ባሳዛኝ ደረጃ የማንበብ ችሎታና ፍላጎቱ “በሴራ” እንዲዳከም በመደረጉ ብዙዉን ጊዜ ሰፋፊ ሰነዶችን ከማንበብ ይልቅ ፎቶግራፎችን አጅግ “ጥልቀት” የሌላቸው አጫጭር ጽሑፎችን እና የመሳሰሉ ጊዜያዊ እርካታ በሚሰጡ የማሰብ ችሎታን በማይፈታተኑ ላይ ትኩረት በማድረግ ሕሊናው ሳያውቀው እየላሸቀ አሁን ላሉ ገዢዎቻችን ብቻ ሳይሆን ለሚመጡ ገዢዎችም ተመቺ “ተንቀሳቃሽ ዕቃ” ሆኖ እያየነው ነው።

እባካችሁ “ሼር” አድርገት ወይንም “እባካችሁ አንብቡኝ እማ!?” በማለት የሚማጸኑዋችሁ  ጸሐፍያን ገጥሞዋችሁ ያውቃሉ? ከነሱ አንዱ እኔው ነኝ። የሚያስለምናቸው በጣም ግልጽ ነው። ትውልዱ ግብዝ በመሆኑ እባካችሁ እያሉ የሚለምኑበት ምክንያት ከላይ በገለጽኩት ምክንያት የተሰለበ በመሆኑ ነው። ስለዚህ ካነበቡኝ ውስጥ አገራዊ ቁጭት በማሳደር ጥቂት የሚቆጫቸው ሰዎች ካገኘሁ በእነዚህ ጥቂቶች ሕሊና ውስጥ ካደረ ሌላውን እያስተላላፉ በጠላቶችና በባንዳዎች የተዳከሙትና የተፋቁትን የወላጆቻችን ቅርስም ሆኑ የተነጥቅናቸው የወደብ ባሕሮቻችንና በመጠቃት ላይ ያለው ሰንደቃላማችን ከመርሳት ማዳን ያለብንን ትላልቅ ማንንታችንን ሊያሳድሱት ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። ብዙ ሰዎች አላወቁትም እንጂ የትግሉ ዋናው መርሕ ይኼው ነው።

እኔ የምተቻቸው ፖለቲከኞች ስለ መጻኢዋ አገር እጅግ አደገኛ ተምበርካኪዎች የሆኑትን ነው ። ከልምድ ምን እንደሚከሰት አውቃለሁ። ለምሳሌ ይህ አደገኛ የኦሮሙማ የአብይ አሕመድ ሥርዓት ከመምጣቱ በፊት ከአመታት በፊት “በተቃዋሚ ስም” ሲታገሉ የነበሩት እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ብርሃኑ ነጋም ሆኑ መሰሎቻቸው ላይ የጻፍኩትና በቃለ መጠየይቅም የተናገርኩት ነገር አንድ ሃቅ ነበር ።

ላስታውሳችሁ፤-

 “ወያኔ ሲወገድ በሚከሰተው መጪው አዲስ ሥርዓት ትግላችን የሚሆነው ከነዚህ የአሁኑ ተቃዋሚዎች ጋር ነው” ብየ ነበር። ያለኩትም ሆነ። ኢሳት የነበሩ ብዙዎቹ ጋዜጠኞች ፤ ታማኝ በየነ፤ አቡበከር አሕመድ፤ አሕመዲን ጀበል፤እነ ንአምን ዘለቀ፤ የሕግ መምህርና ጠበቃ አለማዩየሁ ገብረማርያም (አልማርያም) ፤ ጠበቃ ደረጀ ደምሴ ቡልቲ፤ ብርሃኑ ነጋ፤ቅጣው ያየህይራድ (ኔዘርላንድ)፤ የሺዋስ አሰፋ ፤ ብርትኳን መዲቅሳ ወዘተ..ወዘተ…በደፈናው  ወያኔን እንቃወማለን ሲሉ የነበሩት ብዙዎቹ ዛሬ የማን ደጋፊዎች እንደሆኑ የምታዩት እውነታ ነው።

 በኢሳትና ርሃኑ ነጋ በኩል ወደ ኢትዮጵያዊነታቸው ተመልሰዋል እያሉ ሲሰበክላቸውና ሲያደነቁሩን የነበሩት መላው የኦሮሞ ነጻ አውጪዎችና እነ ታማኝ በየነ ሲጮሁላቸው የነበሩት እነ አሕመዲን ጀበልና አቡበከር አሕመድ ..ወዘተ..ወዘተ… ዛሬ የማን አገልጋዮች ሆነው ፤ ብዕራችን ዛሬም በነሱ ላይ እያነጣጠረ እረፍት እንዳሳጡን ህያው ምስክሮች ናችሁ። ያኔ ትግላችን የሚሆነው ከነዚህ ሰዎች ጋር  ነው ብየ እንዲያ ስናገር ያመነኝ ይኑር አይኑር አላውቅም። ያምናሉ ብየም አልገመትኩም ነበር። ያኔ ሕዝቡ ተሰልቦ ስለነበር።

ነገን በዛሬ ይመሰረታል የሚባለው ልክ ነው። የዛሬ ባንዳዎች የነገ ክፉ ውጤት አመንጪዎች ናቸው።  ዛሬ ፖለቲከኞቹ ሲንበረከኩ ነገ አገርም አብራ ተምበርካኪ ትሆናለች። በተምበርካኪዎች ምክንያት የተነጠቅነውን ሁለቱ የባሕር ወደቦቻችን ምን ዕዳ እያስከፈለን እንዳለ ዓለም ያውቀዋል።

ባለፈው ወቅት የጠቀስኳቸው ምጽዋ ላይ የተሰውት ጀኔራል ተሾመ እንዳሉት “መስኮት የሌለው ቤትና ባሕር የሌለው አገር አንድ ነው” እንዳሉት ኢትዮጵያም  ዓለም ተዘግቶባት የሶማሊያ፤ የጅቡቲ የዓረቦች የኤርትራኖች የአሜሪካኖች ወዘተ…. ግብር ከፋይ ሆና “የቀይ ባሕር ባርያ” ሆና  መቀጠልዋ ስትመለከቱ ስንቶቻችሁ እንደሚቆጫችሁ አላውቅም። በዚህ ባሕር ዕጦትና በውስጥ ጦርነቶች ብዛት ምክንያት ከጊዜ ብዛት ጭራሽኑም አገሪቱ ለባህር ወደብ የምትከፍለው ዕዳ ሳትከፍል ብትቀር እንደማትፈርስ ወይንም ምዕራባዊያንም ሆነ አረቦች ወይንም ግብጾች እንደማይወርሩን እርግጣኛ ሆኖ ዋስትና የሚሰጥ የለም። እንደምታዩት አገሪቱ እየኖረች ያለቺው በልመና በሚገኘው ስንዴ ነው።

ትናንት ወደቦቻችንን አስረክበናል፤ ዛሬ ደግሞ የቆዩ ቅርሶችን እየፈረሱ ሃውልቶች እየተደረመሱ ናቸው። ይቀጥልና ኦረሙማ የተባለ አረመኔ ቡድን “ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን” ለማፍረስ መፈንቅለ ፓትርያሪክ አድርጓል። ለዚህም ተዋናዮቹ ኦረመኔዎቹ  ብቻ ሳይሆን “የባንዳዎች እጅ” ድጋፍ ስላለበት ነው።

ስለሆነም ነው ለተምበርካኪ ፖለቲከኞችና ባንዳዎች ጀሮ አትስጡዋቸው እያልኩ ለ30 አመት የዘለቅኩበት ምክንያት ለዚህ ነው።

ሰሞኑን እኔን የመሰለ አንድ የሶቭየት ጻሐፊ ከታተመ ከ100 ዓመታት በኋላ የሆነው Pressenza የተባለው መጽሔትለህልም ፍላጎት” የሚል ርዕስ አውሮጳ ውስጥ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ  ብቅ ብሎ ሕትምት ሲጀምር: በነ ጎርባቾቭ የመሳሰሉ ሶቭየት ሕብርት ያፈራረሱ ባንዳዎች አንገታቸው ደፍተው የነበሩ “አገራዊያን” ምጽሔቱን ሲያነቡት “የትንሳኤ ጨረር” በሚል መልዕክት አጨናንቀውታል። እነ ጎረባቾቭና እነ የልሰን ወደ ሥልጣን ሲመጡ የቆየው “ዓለም አቀፍ ድሆችና ሰራተኞች ተባባሩ” የሚለው ታግዶ የነበረው የጥንቱ የሶቭየት ሕብረት ብሔራዊ መዝሙር ፑቲን ወደ ሥልጣን ሲመጣ ታዋቂ ኳየር (ኦርኬስትራ) ሊቃውንት ሰብስቦ እንደገና እንዲዘጋጅ አድርጎ ብሔራዊ መዝሙር ሆኗል።

የሶቭየት ሕብረት ከተመሠረተ 100 ዓመታት በኋላ  Pressenza መጽሔት በጃንዋሪ 10 2023 ብቅ ብሎ ለሕትመት ሲበቃ የቀረበው ሰፊ ሐተታ ቢሆንም ከመርሳት ማዳን ያለብን ትልቅ ትውስታ ለሙዚየሞች ብቻ አይደለም: ነገር ግን ለሚመጣው አዲስ ቅኝትና ትውልድ እንደ ቁሳቁስ ገና ያልተሰራ ትልቅ ተግባር መስራት ላይ ማትኮር አለብን ይላል።

ፀሐፊው በመቀጠልም እንዲህ ይላል፤

 << ከጥቂት ወራት በፊት ከዚህ አለም በሞት ከተለዩት ታላቅ ሰው ልጅ የቼ የበኩር ልጅካሚሎ ጉቬራ” ጋር በሃቫና እየተነጋገርን የሶቭየት ህብረትን በአለም ታሪክ ውስጥ ያለውን ሚና ለመተንተን ስንሞክር እንዲህ አለኝ፡-

(…) እያወራን ያለነው በሁሉም ጥርጣሬዎች ላይ ራሱን የቻለ እና አስደናቂ አብዮት ስላዳበረ ታላቅ ህዝብ ነው። የናዚ-ፋሺስት ጭፍሮችን በህዝቧ መስዋዕትነት አሸንፎ የሰው ልጅን በዋጋ የማይተመን ውለታ ሰራ ሕዝብ ነው። ሶቪየቶች የተለያዩ አይነት እና ስፍር ቁጥር በሌላቸው መስኮች ድንቅ ስራዎችን ሰርተዋል። ኢምፔሪያሊስቶች የውስጥ ተምበርካኪዎችን ይዘው ያን ታላቅ አገር ማፍረሳቸው እንዳይበቃ ሶቭየትን የመሰለ ታላቅ አገር መሰረቱና የናዚ ጦርን ያሸነፉ ታላላቅ መሪዎች ሃውልት እንዲፈርስና ስማቸው ከታሪክ እንዲፋቅ ያደረጉ ባንዳዎች ስመለከት እጅግ ይከነክነኛል።….” አለኝ ይልና

የውስጥ ተምበርካኪዎች በቆዩ ቅርሶች እና ታላላቅ መሪዎች ላይ የማጠልሸት ስራ ሲሰሩኢምፔሪያሊሰቶች” አላመኑም ነበር።  እኔም እንደዚህ አይነት ነገር ይደረግ ይሆናል ብየ ካላመኑት  አንዱ ነኝ። ያም ሆኖ ቢደርግም እንዲህ ያለውን ግዙፍ ሥራ ለማጥፋት የሚያስችል ኃይል እንደሌለ ሁልጊዜ እርግጠኛ ነበርኩ።  ከስሜታዊነት ወይም ከርዕዮተ ዓለም ዝምድና ያልተያያዘ አገራዊ ዙፋን ማደፉን የሚቆጨው እንደ በንድ እርሻ ላይ ጥሩ ቡቃያ በድንገት እንደሚበቅል ሁሉ እንዲያ የሆነ አዲስ ትውልድ እንደሚከሰትም አልጠራጠርም”  ብሎኝ ነበር ይላል ጻሐፊው

ካለ በላ ጸሀፊው፤

ያገራችን ታላቅነት ለማደስ ተነስተናል፤ እኛን ለመጨፍለቅ የሚገዳደሩም አይጠፉም፡ እተያየን ነው። ዓለም ያለ ተገዳዳሪ አልተፈጠረችም ወይንም አትኖርምና አገራችንም የጥንት ታላቅነትዋን ለማስነሳት አንድ ጉዞዋን ጀምራች። ከኢምፔሪያሊስቶች ተደናግጠዋል፤ ፑቲንም የወላጆቹን አርማ አንስቷል! ሲል ደምድሟል።

የተለያየ ስም ቢሰጠውም ጦርነት አወዳሚ ቢሆንም ላገር ክብር ሲባል እንደ አዲስ ቡቃያ አጋጣሚ ብቅ ብሎ ወደ ስልጣን የበቀለው ፑቲን ሩሲያኖች የቀድሞ ሉኣለዊነታቸውን እንዲያስታውሱ አድርጎ ምዕራባዊያኑን እያስጨነቀ ነው።

ይህ ልዩ እውነታ እኛ ኢትዮጵያዊያንም እንደ ፍጡራን ሰዎች ታሪካዊ ትውስታችን ይዘን እንድንቆይ ትልቅ ፍላጎት እንደሚሰማን ይነግረናል   ጥንታዊ የኢትዮጵያዊነት ፕሮጀክት ከብርሃን እና ጥላ ጋር ወደፊት የሚለው ቃል ተስፋ ሰንቀን  መሄድ አለብን። በነዚህ የ30  አመት የውስጥ ቅኝ ግዛት አሳዛኝ ገጠመኞች ማንታችን ቅርሶቻችን፤ ወደቦቻችን ፤ ሃይማኖታችን እና ታላላቅ አርበኞቻችን ለውርደት ተጋልጠው ማየት፤ መራራ ቢሆኑም  በማይምበረከኩ ልጆችዋ በማያቋርጥ ተከታታይ ንቃት “የተከናነብነው ውርደታችን” ዘላለማዊ ሆኖ እንደማይቆይ በጊዜ ሂደት ሊቀለበስ እንደሚችል ተምረናል።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

Haile Selassie Accepts Eritrea (1952)

https://youtu.be/w9LCjfPrDW0