አምባ ሰሎዳ ወሳኝ አልነበረም ወሳኞቹ የኢትዮጵያ አርበኞች እንጂ
መልስ ለቴድሮስ ጸጋዬ (ርዕዮት)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
6/21/2022
በፍል 2 ትችቴ “ትግሬዎች እነማን ናቸው ስማቸውስ ከየት የመነጨ ነው? የሚለው አስነብቤአችሗለሁ፤ ዛሬ ከዚያ የቀጠለ ክፍል 3 ነው።
ክፍል 1 እና 2 ያላነበባችሁ ስለምትኖሩ የቴድሮስን ንግግር እንደገና ላስታውሳችሁ። “መንጋ ቡድን’ ለሚለው ክፍል ቴድሮስ እንዲህ ይላል፡
<< ኢትዮጵያ ቀዳሚም ዳግማዊም ልደትዋ ትግራይ ሆኖበት ነው፡በቃ! መከራውን ያያል! ወደ ሗላ የኢትዮጵያን ታሪክ ሄዶ የኢትዮጵያ ቀዳሚ ልደት የት ነው? ሲባል “አክሱም” ያደርሰዋል። ወደ እዚህኛው ዘመን መጥቶ ኢትዮጵያን የተበየነበት እንደገና በመስዋእትነት የተባጀችበትሥፍራ የት ነው ቢባል “ዓድዋ” ይወስደዋል፡ “ምን ያድርገው! በጣም እኮ ነው የተቸገረው?” ኢትዮጵያን ሲያስብ ቀዳሚም ዳግማዊም መነሻዋ ኢትዮጵያ ሆነበት፤ አሉላ ሆነበት! ባሻይ አውዓሎም ሆኑበት! ዮሐንስ ሆነበት። ያ ችግር ሆነባቸው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ውስጥ “በኮር ስቴትነት” (በአገር ስኳልነት) ትግራይ ነች……….>
ቀደም ብየ እንደገለጽኩት መንጋ ብሎ ቴድሮስ ለሚጠራው ቡድን ተቃውሞ የለኝም። አንዳንዱ ከመንጋም በላይ መንጋ እና መላው ትግሬ ወደ ፡”ማጎርያ በረት” እንድንገባ አዋጅ እንዲታወጅ አብይ አሕመድን ያሳሰቡ ተሳታፊዎች የሆኑ ስለሆኑ ቅሬታ የለኝም። ሆኖም ብዙዎቹ አገላለጾቹ እርምት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት ትችቴ በዚህ መንገድ አንዲታይ።
ዓድዋን በሚመለከት ወያኔ የሚባል ቡድን ከተፈጠረ ጀምሮ ትግሬዎች ችግር አለባቸው። በዘፈንም በፕሮፓጋንዳም ለ47 አመት ተከታታይ ውሸት የተሰራበት ስለሆነ ፤ “በጣሊያን ወራሪው ላይ በ1988 ዓ.ም በንጉሠ ነገሥት ምንሊክ የተመራው በዓድዋ ላይ የተቀዳጀነው የጦርነት ድል” የትግዎች እንጂ የአማራና የማንም ዚትዮጵያዊ ዜጋ ሱታፌ አይደለም ባይ ናቸው።
ወያኔ ከመፈጠሩ በፊት የነበሩ የትግራይ ደራሲያንና ምሁራን ዓድዋን በምኒሊክ የተመራ የመላ ኢትዮጵያዊያን የገድል ድል ፍሬ ነው ብለው ሲያምኑና አጼ ምኒልክ ትግራይን ከጣልያን የታደጉ ብለው ጽፈዋል።
ጥቂት ሽማግሌዎችና ዛሬ የመጣው ወያኔ የፈጠረው አብዛኛው የትግራይ ትውልድ ግን ተቃራኒ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ ምኒልክ ወደ ዓድዋ የዘመተው ከጣሊያን ጋር ምስጢራዊ ስምምነት አድርጎ ትግሬን ለማጥፋተተ ነው የሚሉ ትውለደች አሉ።
ይህንን ከሚያቀነቅኑት መሃል ለምሳሌ የትግራይ ግንጠላ ግምባር ቀደም አቀንቃኝና የአማራ ጥላቻው ከመምህር ገብረኪዳን ደስታ የባሰበት (ሳጤነው የሕሊና ቀውስ ያለበትም ይመስላል) የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው “ወጣት መሓሪ ዮሃንሰ” (እኔ “መሓሪ ዱቼ” ብየ የሰየምኩት) ይህንን ሌት “አስቂኝ ስብከት” ለትግሬዎች ሲሰብክ አድምጠናል።
በጦርቱ ወቅት አሉላ በዓድዋው ጦርነት አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም ትግሬዎች እንደሚሉት አይደለም። የቱርክ ልብስ የለበሰው የአሉላ ፎቶ ነው የሚባልለት የቱርኮች ያልሆነ ግን ዐረባዊ ልብስ የለበሰ እኔ የማልቀበለው፤ በሗላ ግን “ሃጋይ ኤርሊክ”የተባለው እስራላዊው ምሁር ”የአሉላ እውነተኛ ፎቶ” ያስተዋወቀን ብቸኛ ተመራራማሪ ሃጋይ ኤርሊክ ስለ የራስ አሉላ የህይወት ታሪክ ጸሐፊ የዘገበውን ስንመለከት ዓድዋን በሚመለከት የብዙ ትግሬዎች እምነት ጋር የተቃራኒው ነው።
ሃጋይ እየነገረን ያለው በጦርነቱ ወቅት የነበረው የራስ አሉላ በዓድዋ ጦርነት ሱታፌ ብዙም ግልጽ እንዳልሆነ ይናገራል።
በአሉላ ሥር የነበሩት ጦሮችም ጥቂቶች ናቸው፡ ሲል በራስ አሉላ የህይወት ታሪክ ዝርዝር መጽሐፍ ጽፎታል፡
እንዲህ ይላል፡
“Alula’s role in the battle itself is not known. He had only a small force, and probably played a limited part in the actual fighting.” (Ras Alula and the Scramble for Africa -A Political Biography; Ethiopia & Eritrea 1875-1897 Haggay Erlich P.193)
(ትርጉም)
"አሉላ በጦርነቱ ውስጥ የነበረው ሚና ብዙም ግልጽ አይደለም። የያዘው ጦር ትንሽ ኃይል ብቻ ነው፣ ምናልባትም በጦርነቱ ውስጥ የተወሰነ ሚና ተጫውቷል። (ራስ አሉላ እና ዘ ስክራምብል ፎር አፍሪካ -A Political Biography; Ethiopia & Eritrea 1875-1897 Haggay Erlich P.193) ይላል።
እስኪ ይህንን ለበርካታ አመታት ስጠይቅ የነበረውን ጥያቄ ዛሬም ደግሜ ልጠይቅ፡
ትግሬዎች ብቻቸውን ተዋግተው ጣሊያንን ማሸነፍ የሚችሉ ከነበረ፤ ለምንድ ነው የአጼ ምንሊክን ዕርዳታ ሊጠይቁ የቻሉት? ራስ መንገሻ ጣሊያንን መዋጋት አቅም ስላልነበራቸው እስከ ማይጨው ድረስ ጣሊያን በመድረሱ “አልቻልነውም እና” ክቡር ንጉሠ ነገሥትነትዎ ከእርስዎ የማኣከላዊውን መንግሥት ዕርዳታ ይድረስልን ስላሉ ምንሊክ መላው ኢትዮጵያ አዋጅ አስነግረው ወደ ትግራይ ሄደው ለዕርዳታ መጥተው ጣሊያንን አሸነፉት። ታሪኩ ይህ ነው፤ “በቃ!!”።
እንደ እነ መሐሪ ዮሓንስ አባባል ንጉሡ ወደ ዓድዋ የመጡበት ምክንያት ትግራይን
ለመፍጀት ነው እንደሚለው “ፈጠራ” ቢሆን ኖሮ ንጉዒዩ “ትግሬዎች ጣሊያን ይፍጃቸው” ብለው አዲስ አበባ መቀመጥ ይችሉ ነበር ፤አደለም
እንዴ?
ዓድዋ መጥቶ ተሸሰገ የሚሉት የትግሬዎች ምሁራን ፈጠራም ቢሆን ፤” የገበያ ኑ” ሃያሲ በጥሩ መንገድ እንዳስቀመጠው “ምኒልክ” እንደ ማንኛውም የአገር መሪ ዓድዋ ድረሰ መሄድም አይጠበቅባቸውም፤ ባሉበት ሆነው የጦር መኳንንቶችን ማዘዝና መከታተል ይችሉ ነበር ፤ ሆኖም እራሳቸው ሄደው ተሳትፈዋል። ንጉሥ እንጂ የወያኔ የሽምቅ ተዋጊ አዛዥ አይደሉም።
በመጽሐፌ እንደገለጽኩት እንዳውም እናቶቻችን እና ሴት አያቶቻችን የጣሊያን ዲቃላ ወልደው የምንወለደው ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው “ቪቶርዮ፤ ”ማርያ” ፤ “አንጀሊና” “ኦስካር” እና ጆቫኒ” ከመባል ምኒልክ አድኖናል። ታሪኩ ይህ ነው፤ በቃ!!
በታሪክ ትግሬ ብቻውን ጦርነት ገጥሞ ባዕዳንን ያሸነፈበት ታሪክ የለም። ዶጋሊ ኳዓቲት፤ሰሓቲት እንዲሁም በቅርቡ ወያኔ በረሃ ለ17 አመት ሲቆይም ሆነ እስከ ባድመ ጦርነቶች የሌሎች ክፍሎችና ኢትዮጵያዊያን ዕርዳታ ሳይጠይቁና ሳይጨመርበት ትግሬዎች ያሸነፉበት ጦርነት የለም።
ሁሌም ቢሆን በታሪክና በተፈጥሮ ሕግጋትና ጂኦግራፊያዊ ቁርኝት ምክንያት የትግሬዎች ዕጣ ፈንታ ከተቀሩት ወገኖቹ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ብቻውን መጋፈጥ ያስቸግረዋል።
እውነታው ይህ ሆኖ እያለ የዓድዋ ጀግኖች አንዱ ራስ አሉላ ቢሆኑም የመረጃ ስምሪት በማጠናከርና ጦራቸውን በመምራት (ከምኒልክና ከጣይቱ ጋር ሆነው- ሌሎች መረጃዎች እንደሚገልጹት) አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም አይሁዳዊው ጸሐፊ የወቅቱ የዓይን ምስክር ፈረንሳዊው ዘጋቢ ዋቢ በማድረግ እንዳጠቃለለው የትግራይ ሠራዊት ማለትም በራስ አሉላ በወቅቱ ራስ አሉላ የነበራቸው የሰራዊትና የሞራል መዳከም እንዲሁም ጎስቋላ ኑሮ እንደ ቀደሙ በከፍታ ወንብር ሊወጡ አልተቻላቸውም።
ምክንያቱም አምበሳ ሁሌም አምበሳ ሆኖ ሊቀጥል የተፈጥሮ ሕግ አይፈቅድም።ስለሆነም ከየአቅጣጫው ለጦርነቱ የከተቱ የመኳንንቱ ሰራዊቶች ጋር ሲነጻጸር የትግሬዎች ማለትም የራስ አሉላ አባ ነጋ ተዋጊዎች በቁጥር አነስተኛ ስለነበር የተካፈለው የጦርነት መጠንና ርዝማኔ እንደዚሁም ለዓይን የሚታይ ውጤት በማስገኘቱ ረገድ የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ከላይ ተገልጿል።
እንግዲህ የአሉላ ጦር በወቅቱ ያሳየው ጀብዱ ይህ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው ማለቱ የራስ አሉላ ወይንም የትግራይ ጦር ዘማቾች ጀግንነት ሱታፌ ይቀንሰዋል ማለት ባይሆንም የወያኔ አክራሪ ብሄረተኞች እንደሚሉት ሳይሆን ጦርነቱ በትግራይ ሕዝብ ጀግንነት ብቻ የተደመደመ/የተካሄደ እንዳልነበረ ነው። ጦርነቱ የጋራና ድሉም ሽንፈቱም ጀግንነቱም የጋራ፣ የመላው ያገሪቱ ህዝቦች ትግልና ውጤት ነው የምለው ለዚህ ነው።
ለዚህ ሁሉ የአሉላ ጦርና የሞራል ጥንካሬ መላላት ጦርነቱ ከመጀመሩ ከ4 አመት በፊት አሉላ ከራስ መንገሻ ጋር ስለተጣሉ ተከታይ አጥተው በትውልድ ራስ አሉላ በራስ መንገሻ እንዳይያዙ እየሸሱ በትውልድ ገጠራቸው “መነወ” (ተምቤን) ውስጥ ተደብቀው ይነሩ በነበሩበት ከዓድዋ እንደ መያዣ አስረው ወደ ተምቤን የዘዋቸው አብረው ከራስ ጋር ከተጓዙት አምስት ጣሊያን ምርኮኞች ውስጥ ጣሊያናዊው “ዲ ማርቲኖ” በሃጋይ ኤርሊክ መጽሐፍ ላይ እንደሚከተለው ይላል፤
De Marttino reported;
Alula fortified himself in Mannawe with a few
hundred followers and refused to free De Marttino and five other Italian
hostages he had taken from Aduwa. On 27 December 1892, with 2,000 troops
commanded by Ras Hagos, Mengesha
approached Mannawe, took up a position on the surrounding hills and started ruining
the fields and orchards.
Around midnight, accompanied by only fifty
followers. Including Dejazmach Abbay and Dejazmach Tedla Fanja, “the lame”,
Alula left his camp “like a thief running for his life”.
He led his small group of followers to an amba in Abergele. (24) on the way, he was deserted by Dejazmach Abbay, who brought the Italian hostages to Ras Mengesha’s headquarters near Manawe(24) De Marttino reported.
De Marttino continued reporting
“We were received by more than 2000 soldiers…. They all shouted “Alula kufu,, kufu (bad, bad).
Alula is morally finished even in Tigre. Alula and his chiefs have deserted him, even Dejach Teklehaymanot and Dejach Abay. He is left only with Tedla ‘the lame, Fitawrari Desta and forty followers on Amba an Aberhgele(Amba serago), from where he sends asking for mercy.” ( Haggay Erlich P.180-181)
“አሉላ 5 የጠለፋቸው ጣሊያኖችና እንዲሁም ጥቂት መቶ ተከታዮቹን ይዞ በመነወ ገጠር መሽጎ ይኖር ነበር። ከዓዱዋ የወሰዳቸውን 5 ጣሊያኖችን ለማስፈታት በታህሳስ 27 ቀን 1892 (ፈረንጅ) በራስ መንገሻ ትዕዛዝ በራስ ሐጎስ የሚመራ 2,000 ጦር ወደ “መነው” በመዝመት በዙሪያው ባሉ ኮረብታዎች ላይ ቦታ በመያዝ እርሻውን እና የአትክልት ቦታዎችን ማበላሸት ጀመረ።
ራስ አሉላም እኩለ ሌሊት አካባቢ በሃምሳ ተከታዮች ብቻ ታጅቦ ደጃዝማች አባይ እና ደጃዝማች ተድላ ፋንጃን “አንካሳው” ጨምሮ “እንደ ሌባ ነፍሱን ለማዳን ሮጦ በመሸሽ” ካምፑን ለቅቆ ሄደ።
ሸሽቶ ከጥቂት ተከታዮቹ ጋር በአበርገሌ ወደሚገኝ አምባ መሸገ። ሆኖም ደጃዝማች አባይ ከድተው በአሉላ እስር ተይዘው የነበሩት 5 ጣሊያኖችን ይዘው በመክዳት ጣሊያኖቹን መነወ አጠገብ በሚገኝ የራስ መንገሻ ዋና ማዘዣ መምርያ አስረከቡዋቸው።
ሲል ‘ዲ ማርቲኖ” ስለ አሉላ ሁኔታ ዘግቧል።
ዴ ማርቲኖ በመቀጠልም እንዲህ ይላል፤
“ነጻ ከወጣን በሗላ ከ2000 በላይ ወታደሮች ተቀብሎናል…. ሁሉም “አሉላ ኩፉ፣ ኩፉ (መጥፎ፣ መጥፎ)” ብለው ጮኹ።
“አሉላ ሌላ ቀርቶ በሚወደደው በትግሬዎች የነበረው ቅቡልነት ያበቃለት ወቅት ነበር። አሉላና የጦር መኳንንቶቹ ደጃች ተክለ ሃይማኖትና ደጃች አባይ ሳይቀሩ ከድተውታል። የቀረው ተድላ ‘አንካሳው’፣ እና ፊታውራሪ ደስታ እንዲሁም አርባ (40) ተከታዮቹ በአበርገለ አምባ (እምባ ሴራጎ) ላይ ሆኖ ለራስ መንገሻ ምህረት እንዲሰጠው መልእክት ላከ። ( ሃጋይ ኤርሊች P.180-181)
ይህንን የተዳከመ ሞራልና ጎስቋላ ኑሮ የሚያሳየን አሉላ የተዳከሙ እንደነበር “ትሬንዱ” ሲያሳይን የዓድዋ ጦርንት ሊከሰት አቅራቢያም ትግራይ ውስጥ ሞራላቸው እየደከመ ስለሄደና ብቸኛ ኢትዮጵያ አዳኝ “ምኒልክ ብቻ ነው” በማለት አዲስ አባባ እየኖሩ ስለነበር ዓድዋ ላይ ከየአቅጣጫው ለጦርነቱ የከተቱ የመኳንቱ ሰራዊቶች ጋር ሲነጻጸር የትግሬዎች ማለትም የራስ አሉላ አባ ነጋ ተዋጊዎች በቁጥር አነስተኛ ስለነበር የተካፈለው የጦርነት መጠንና ርዝማኔ እንደዚሁም ላይን የሚታይ ውጤት በማስገኘቱ ረገድ የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ከላይ አይተናል።
እንግዲህ የአሉላ ጦር በወቅቱ ያሳየው ጀብዱ ይህ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው ማለቱ የራስ አሉላ ወይንም የትግራይ ጦር ዘማቾች ጀግንነት ሱታፌ ይቀንሰዋል ማለት ባይሆንም የወያኔ አክራሪ ብሄረተኞች እንደሚሉት ሳይሆን ጦርነቱ በትግራይ ሕዝብ ጀግንነት ብቻ የተደመደመ/የተካሄደ እንዳልነበረ ነው። ጦርነቱ የጋራና ድሉም ሽንፈቱም ጀግንነቱም የጋራ፣ የመላው ያገሪቱ ህዝቦች ትግልና ውጤት ነው።
ስለሆነም ቴድሮስ ጸጋዬ
“ወደ እዚህኛው ዘመን መጥቶ ኢትዮጵያን የተበየነበት እንደገና በመስዋእትነት የተባጀችበትሥፍራ የት ነው ቢባል “ዓድዋ” ይወስደዋል፡ “ምን ያድርገው! በጣም እኮ ነው የተቸገረው?” ኢትዮጵያን ሲያስብ ቀዳሚም ዳግማዊም መነሻዋ አክሱም/ትግራይ/ ሆነበት፤ አሉላ ሆነበት! ባሻይ አውዓሎም ሆኑበት! ዮሐንስ ሆነበት። ያ ችግር ሆነባቸው።..” የሚለው ትችቱ
ወሳኙ ተራራ/ቦታ/ ሚነ ቢኖሮውም የሕዝብ ሱታፌ ቀዳሚ ነው። ድሉ የዓድዋ ተራራ በመሆኑ ሳይሆን የተሳታፊዎቹ ቆራጥ መስዋእትነትን ስለጠየቀ በድል ተወጥተዋል። ተሳታፊዎቹ ደግሞ የቁጥር መብዛትና ማነስ ቢኖረውም እንደ ዜጎች ከመላው አገራችን የተወጣጡበት የሱታፌ ውጤት እንጂ የተራረ ውጤት/የቦታ ውጤት ወሳንኝ አይደለም። ተራሮችን ይዘው የተሸነፉ ብዙ የታሪክ ገድሎችና አገሮች አሉ።
በክፍል 4 “ኢትዮጵያ ውስጥ “በኮር ስቴትነት” (በአገር ስኳልነት) ትግራይ ነች” ስለሚለው እምነቱ “ዳር ከሌለ መሃል የለም” በሚል የመጨረሻ ድምዳሜ በሚቀጥለው አቀርብና እንደመድማለን…
ይቀጥላል
“ሰላም” ለተጠማው ሕዝባችን ይሁን!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment