Tuesday, March 29, 2022

ለትውስታችሁ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ለማን ቆሞ ነበር? ጌታቸው ረዳ (Getachew Reda--Ethiopian Semay)

 

ለትውስታችሁ፤

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ለማን ቆሞ ነበር?

ጌታቸው ረዳ

 (Getachew Reda-- Editor Ethiopian Semay)

የህ ሰነድ ለማሳየት የፈለግኩት ምክንያት በዚህ 4 አመት ውስጥ ወደ ትግሉ የተቀላቀላችሁ አዳዲስ ታጋዮች ከናንተ በፊት ሲደረግ የነበረው እልክ አስጨራሽ የተለያዩ ትግሎች በተለይ አማራ ብሶቱ እንዳይናገር ሲታፈን የነበረ ውስብስብ “ሴራ” በግምባር ታግለናል።

በወቅቱ ታገዮች የተባልነው እጅግ በጣት የምንቆጠር ነበርን። ሁለት ትግል ታግለናል። “ኣንደኛው” በፖለቲካው መድረክ ገብተው አማራውን ለማፈን ያካሄዱት የምሁራን ሴራን ስንታገል “ሁለተኛው ትግላቨችን እና ከባድ የነበረው ደግሞ” አሁን በሺዎቻችሁ በተጋይነት ተሰልፋችሁ ለአማራና ለኢትዮጵያ  የምትጮሁ አገር ውስም ሆነ ውጭ አገር ያላችሁ ወገኖቻችን በመተኛታችሁ እናነተን ከተኛችሁበት ለመቀስቀስ ሌላው ፈታኝ ትግል ነበር። እውነት ለመናገር ደምጻችን እንዳይሰማ ስታፍኑነም ሆነ ስትሰድቡን የነበራችሁ እና ለሴረኞቹ በገንዘብም በሞራልም በመሳተፍም ከጎናቸው ጋር ቆማችሁ እኛን ስታስገግሩ የነበራችሁ እና የባሳችሁብን እናንተ ነበራችሁ። እነሆ ትግላችን ፍሬ አስገኝቶ አገር ውስጥም ውጭ አገርም ወደ ትግላችን በመቀላቀላችሁ በጠመንጃም በብዕርም የምታተገሉ ታጋዮች እኛ ጥቂቶቹ እናንተን ሚሊዮኖችን አፍርተን በማየታችን ተደስተናል። ቢሆንም ቀይ መስመር የሚያሳይ ምልክት እያየሁ ስለሆነ “አክራሪ” ላለመሆን ጥንቃቄ ቢደረግ እግረ መንገዴን እመክራለሁ።

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ለማን ቆሞ ነበር?

ሴራው ከኦነግ ከኢሳትና ከግንቦት 7 እንዲሁም ከሻዕቢያ ጋር የተያያዘ ጸረ አማራ የተጎነጎነ ጉድ ነበር። ድርጅቱ ሕዝባዊ ስብሰባ በጠራ ቁጥር ኤርትራኖች ዕደል ተሰጥቶኣቸው አማረውን እና ኢትዮጵያን በቅኝ ገዢነት ሲዘልፉበት የነበረ መድረክ ነበር። ቢያምም ታሪክ ነውና እንድተውቁት ለትውስታችሁ እነሆ።

(1)   የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተበሎ የሚጠራው የፖለቲካ አቃቂረኞችየኢትዮጵያ እና የኦሮሞ አገራዊ ምስረታ ንቅናቄስንለው የነበረ ድርጅት ነው። ግንቦት 7 እና ኦነግ የሚያሾሩት አማራ ሕዝብ ደምፅ ለማፈን ሲሰራ የነበረው ይህ ድርጅት ምርኩዝ የነበሩት የኢሳት ሰይጣናዊ ሰዎች እና ምሁራን ተብየ አስቂኝ ምሁራኖች የተጓዙበት ጉዞ አሳያችሗለሁ። እኛም ከነዚህ ሰዎች ጋር በወቅቱ የገጠመን ግብግን እጅግ አድካሚ ነበር። የሚገርመው ደግሞ ይህ ድርጅት ግምባር ቀደም የስብስቦቹ ዋና ተጠሪ የነበረው አማራው “ዶ/ር ጌታቸው በጋሻ’ እና የመሳሰሉ አማራዎች ነበሩ። አሁን ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው ወደ ልቦናው የተመለሰ ይመስለኛል። ላለፈው ክረምት አይሰራም፤ ለወደፊቱ እናስብ በሚል ምረቴን  ወደ ጎን አድርጌዋለሁ። ሰነዳቸውን ለምስክርነት ታዩታላችሁ።

ይህ ሰነድ ኢሳት የተባለ ብዙ ጸረ አማራ የሆኑ ግለሰቦች የተሰባሰቡበት ሚዲያ ድርጅት በ እነ ሲሳይ አገና እና ንአምን ዘለቀ “አሞካሺነትና” እና በኢሳት ቲቪ ዋና “አቃፊነት” (ስፖንሰር) ሲካሄድ የነበረ የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ በሽፋን ተንቀሳቅሶ ለጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ለሆነው  በሰው ልጆች ደም እጁ የተጨማለቀው አሸባሪ የሆነው ለኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር “ኦነግ” ፖለቲካ በማመቻቸት ሲሰራ የነበረው ከላይ የተጠቀሰው የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የተባለው “ቡድን” በአማራ እና ኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት ሴራ ሲሰራ ነበር? ሴራው ከታች እንመለከተዋለን።

አሁን ላለንበት ለውጥ የተባለው የከሸፈው ለውጥ በከንቱ አልመጣም። ብዙ መስዋእት ከፍለናል። ሴራውን ስናጋልጥ ብዙ ዘለፋ ሲደርስብን እንደነበር ይታወሳል። የተጋፈጥነው አውነት ሆኖ መረጃው እነሆ በጽሑፍም፤ በቪዲየው/አውድዮም ሲዋሽ የነበው  ቅጥፈታቸው በወቅቱ አወጣነው። በወቅቱ ላልነበራችሁ ወይንም ከጊዜ ብዛት ታሪኩን ከትውስታችሁ ለጠፋ እንደገና እንድታስታውሱት “ኢትዮጵያን ሰማይ” የመዘገበው የወቅቲ ሰነድ ተመልከቱት እነሆ እንዲህ ነበር።

(1)

የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድ

ሰሞኑን በአራት የተቃቃሚ ድርጅቶች ማለትም፡-

በግንቦት 7 (G7) በኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) በሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( SNDM ) እና በአፋር ህዝብ ፓርቲ (APP) መካከል በዋሽንግተን ዲሲ ኦክቶበር 30 2016 ..የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የሚባል ስብስብ ተፈራርመው መመስረታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የስምምነት ሰነድ ከተካተቱት ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች እና ለህዝብ ያለተገለጡት ጉዳዮች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን የያዘ ነው።

* የአማራ ህዝብ ተወካይ ባለመኖሩ በስብስቡ አለተካተተም የተባለው ውሸት ነው።

* የንቅናቄው ሰነድ እንዳለ የግንቦት 7 ፕሮግራም የተቀበለ ነው።

* የንቅናቄው ሰነድ በወያኔ መንግስት የወጣውን እና አሁን ወያኔ እየተገበረው ያለውን ህገ መንግስት ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ነው።

* ንቅራቄው በወያኔ መንግስት የተዘረጋውን የአስተዳደር መዋቅር እንዳለ የተቀበለ ነው።

* የንቅናቄው ሰንደ ወያኔ እንደሚለው የኢትዮጵያን ህዝብሕዝቦችእያለ የሚጠራ ነው።

* ይህ በነዚህ በአራቶ ድርጅቶች የጸደቀው ሰነድ ካሁን በኋላ ሰነዱን ማንም ማሻሻም አይችልም የሚል ማሰሪያ አንቀጽ አለው።

* አዲስ ወደ ንቅናቄው የሚገቡ ድርጅቶች በአራቱ ድርጅቶች የጸደቀውን ይህንን ሰንድን እንዳለ ተቀብለው መግባት እንጅ ሰነዱ እንዲሻሻልና እንዲስተካከል የመጠየቅም ሆን የማሻሻል ጥያቄ መብታቸው የተከለከለ ነው።

* ግንቦት 7 ( G7 ) የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ODF ) ማንኛውም የአማራ ድርጅት ተወካይ ወይም በአዛጋጆች ተጋብዞ የነበረው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በዚህ የንቅናቄ ስብስብ ውስጥ ሊገባ አይገባውም የሚል እገዳ ጥለዋል።

* በንቅናቄ የተገኙት የአፋር እና የሲዳማ ድርጅቶች የአማራ ህዝብ ተወካይ የለለበት የድርጅቶች ስብስብ የትም አይደርስምና የአማራ ህዝብ ተወካይ በንቅናቄው ስብስብ እንዲካተት ከፍተኛ ድምጽ ያሰሙ ቢሆንም  ግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) ግን የአማራ ተወካይ በንቅናቄው ውስጥ መገኘት የለበትም በማለት እገዳ ጥለዋል።

በዚህ አጋጣሚ የአፋርና የሲዳማ ህዝብ ድርጅቶች ሃላፊዎች ምንም እንኳ በጉልበተኞቹ በግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) መሪዎች ተጽእኖ ምክንያት የአማራ ህዝብ ተወካይ በስብስቡ እንዳይገኝ ቢደረግም እናንተ ግን እውነተኛ የነጻነት ታጋዮች በመሆናችሁ የአማራ ህዝብ ተወካይ የለለበት ስብስብ ዋጋ የለውም ብላችሁ ያነሳችሁት ጥያቄ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የአማራ ህዝብ ያላችሁ ቅን ልብና ወገናዊትነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ለእናንተ ያለው አክብሮት ከፍ ያለ መሆኑን እየገለጽን በዚህ አጋጣሚ ላሳያችሁት አጋርነት እናመሰግናችኋለን።

አቶ ተክሌ የሻው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅትና ሊቀመንበር እና የአማራ ህዝብ ጠባቃየኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድን በሚመለከት የሰጡትን አስተያየት ከዚህ በታች ያድምጡ።

ስለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄን - Ethiopian National Movement የአቶ ተክሌ የሻው አስተያየት

https://youtu.be/j4gLQDvHUM8

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ (Getachew Reda Ethiopian Semay)

 

 

No comments: