ያለ ዳርቻ “መሃል” ህይወት የለውም!
ጌታቸው ረዳ
መልስ ለቴድሮስ ጸጋዬ
3/6/22
ይህ ጽሑፍ ክፍል 2 ነው።
ይህ ጽሑፍ ወደ ክፍል 3ም የሚቀጥል ጽሑፍ ነው።
ይህ ጽሑፍ “አዎ ዓድዋን በዓል
ለማክበር እንመጥናለን”
ከሚለው ክፍል 1 ጽሑፌ የቀጠለ ነው።
ቴድሮስ ጸጋዬ (ርዕዮት) ስለ ዘንድሮው 126ኛው የዓድዋ በዓል አከባብር አስመልክቶ የተቸበትን አንስቼ ተችቼዋለሁ። ያንን ያላነበባችሁት በድረገጼ “ኢትዮፕያን ሰማይ” ተለጥፏል፡ ያንን መመልከት ነው።
ዛሬ የምንመለከተው በዛው ሃተታው በዓሉን አያይዞ ስለ ትግራይና ኢትዮጵያ አስመልክቶ የተቸበትን “አክሱም፤ዓድዋ፤ዮሃንስ፤ አሉላ…” ወዘተ የትግሬዎች ብቸኛ አስኳል ነው፤ የሚለው የብዙ ትግሬዎች የተሳሳተ አጉል “ብቸኛ አስኳልነት” እና የባለቤትነት ስሜት ስለተናገራቸው ንግግሮቹን እንመለከታለን።
እንዲህ ብሏል፡
<< ኢትዮጵያ ቀዳሚም ዳግማዊም ልደትዋ ትግራይ ሆኖበት ነው፡በቃ! መከራውን ያያል! ወደ ሗላ የኢትዮጵያን ታሪክ ሄዶ የኢትዮጵያ ቀዳሚ ልደት የት ነው? ሲባል “አክሱም” ያደርሰዋል። ወደ እዚህኛው ዘመን መጥቶ ኢትዮጵያን የተበየነበት እንደገና በመስዋእትነት የተባጀችበትሥፍራ የት ነው ቢባል “ዓድዋ” ይወስደዋል፡ “ምን ያድርገው! በጣም እኮ ነው የተቸገረው?” ኢትዮጵያን ሲያስብ ቀዳሚም ዳግማዊም መነሻዋ ኢትዮጵያ ሆነበት፤ አሉላ ሆነበት! ባሻይ አውዓሎም ሆኑበት! ዮሐንስ ሆነበት። ያ ችግር ሆነባቸው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ውስጥ “በኮር ስቴትነት” (በአገር ስኳልነት) ትግራይ ነች……….>>
የሰለቸ የትግሬዎች ብቸኛ አርበኛነት ጉራ አሉላ የ1887 (በፈረንጅ ዘመን) ነጭን ያሸነፈ ብቸኛ የትግሬ ጀኔራል እያሉ የሚቀባጥሩት መስመር የዘለለ ትምከሕት’ ስንመለከት አፍሪካኖቹ የእነ ሞሮኮው አብደል ከሪም (The lion of the rif) እስፐይኖችን የተዋጋ ጀግና እንዲሁም በቀስት ብቻ ከ300 በላይ ማርኮ የገደለላቸው ጀርሞኖችን የርበደበደው የታንዘኒያው ርበኛ “Chiefe Mkwawa” እና ሌሎች አፍሪካ አርበኞች እንዳልነበሩ በብቸኛነት እኛ “ትግሬዎች” የሚለው ትምክሕት በሚቀጥለው ሌላ ክፍል ስለምንመለከተው ያንን እዚህ ላቁምና
የተሳሳተው ትምክሕተኛው የትግራይ አክራሪ ሃይል ትርክት እስክመለስበት ጊዜ ለዛሬ “ትግሬዎች” እነማን ናቸው? ከሚለው እንደመደርደሪያ እንጀምር::
የጥንተ ታሪክ (ክላሲክ ሂስቶርያን) ተመራማሪው ሊቅ ጣሊያናዊው ኮንቲ ሮሲኒም ሆነ ኤድዋርድ ግሌሰር እንዲሁም አያሌ የታሪክ ሊቃውንት ስለ ትግሬዎች ነገድ አመጣጥና ስማቸው አስተያታቸው ሰጥተዋል። ከነዚህ መሃል ጣሊያነዊው “ኮንቲ ሮሲኒ” ባጠናው መሰረት እጅግ የማከብራቸው መምህሬና ወዳጄ የነበሩት ነብሳቸው በገነት ያኑርልን የፈረንሳይ፤ ፖርቺጋልኛ፤ ጣሊያኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ የነበራቸው ዶ/አለሜ እሸቴ የላኩልኝን ማሕደር እንዲህ ይላል።
According to Conti Rossini the Tigre may have been originally a Semitic Beja, living north of the Ge’ez. The Tigrai were the Tigre’ who would in the 7 century, marched south, over the highlanders conquer and occupy the Ge’ez Axum putting an end to the Ge’ez Axumite ruling dynasty.
The name Tigrai was indeed as we shall see later, the name given to all vassals, conquered people and regions within the context of Tigre’ society.
Also according to Conti Rossini, the present day Tigrai originally spoke Tigre, the language of the semitic Beja. A semitic language known as Tigrigna (ትግርኛ) different from Tigre (ትግረ) appeared centuries later following Tigre’s (ትግረ) invasion and settled south of Mereb and after assimilation with the Agaw Ge’ez.
The Tigre imposed their name on the region as well as on its ancient spoken language Ge’ez. Tigre- (ትግረ) Tigrigna (ትግርኛ) separation and development into different directions was a slow and gradual process since the two languages differed sufficiently, as Italian differed from French.”
ትርጉሙ ካላበላሸሁት ጠቅላላ ግንዛቤው እንደሚከተለው ነው።
<<እንደ ኮንቲ ሮሲኒ አባባል “ትግረ” የተባለው ነገድ፤ ጥንተ መኖርያው መጀመሪያ ከግእዝ በስተሰሜን የሚኖር ሴማዊ ቤጃ ሊሆን ይችላል። የዛሬው ትግሬዎች የቤጃ ትግረ ነገዶች ናቸው።ትግራይ ‘ትግረ’ የተባለው ነገድ በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሚኖርበት አካባቢ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ዘመቶ፣ ደጋውን ክፍል በመያዝ “አክሱምን” በመቆጣጠር የግዕዝ አክሱማውያን ገዢ ስርወ መንግስትን ፈንግሎ ያዘ።
ትግራይ የሚለው ስም በኋላ እንደምናየው በትግራይ ማህበረሰብ አውድ ውስጥ ተያያዥ “ቫሳሎች” (ቀጠናዎች) የነበሩ ኗሪ ህዝቦች መኖርያ የተሰጠው ስም ነበር።
እንዲሁም ‘ኮንቲ ሮሲኒ’ እንደሚለው፣ ከወረራው በሗላ የአሁኑ ትግራይ የሴማዊው ቤጃ ቋንቋ የሆነው “የትግረ” ቋንቋ ይናገር ነበር ። ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የትግረ ቤጃን ወረራ ተከትሎ “ትግርኛ” በመባል የሚታወቅ ሴማዊ ቋንቋ ታየ። ይህ የሆነው ከመረብ በስተደቡብ እና ከአገው ግእዝ ጋር ከተዋሃደ በኋላ ነው።
የቤጃ ትግሬዎች ስማቸውን በክልሉ ላይ እንዲሁም በጥንታዊው የንግግር ቋንቋው ግእዝ ላይ ጫና አሳደሩ። በሗላ የቤጃው ትግረ ተከትሎ የተወለደው “ትግርኛ” ጊዜ ወስዶ መለያየት የመጣው በሂደት ሲሆን የተለያዩበት አቅጣጫ እጅግ ቀርፋፋ (አዝጋሚ) ነበር።
ይህንን ለማገናዘብ ልክ ጣሊያንኛ ከፈረንሳይኛ ቋንቋ ሲለያዩ ሁለቱ ቋንቋዎች በበቂ ሁኔታ የራሳቸው ቅርጽ ሲወስዱ ቀስ በቀስ በአዝጋሚ ሂደት ነበር።>> (ኮንቲ ሮሲኒ- ደብዳቤ ለጌታቸው ረዳ ‘አለሜ እሸቴ’ (ምንጭ በሂደት ላይ ካለው መጽሃፌ የተወሰደ)
እንግዲህ የፈረንሳዩ እና የጣሊያንኛው መለያየት ከላይ እንዳየነው የቤጃዎቹ የትገረ ቋንቋና እና የዛሬዎቹ የትግርኛ ቋንቋም እንዲሁ ነበር። ሲሉ አስተያየታቸው ሰጥዋል።
በዚህ አጋጣሚ ልብ ማለት ያለብን አዝጋሚ ሂደቱ ወስዶ ሲወለድ “ከግዕዝ” “አገው” “ኩናማ” “ዓረብኛ” የመሳሰሉ እንዲሁም ምንጫቸውና ትርጉማቸው የማናውቃቸው ቃላቶችን በማስገባት “ትግርኛ” ቋንቋ ተወልዷል። በነገራችን ላይ ጥንት የነበረው ትግርኛ እና አሁን ያለው ትግርኛ በአጻጻፍም በልሳንም ልዩነት እንዳላቸው ከጥንት ሰነዶች ማየት ይቻላል። ለዚህም ነው የራያዎቹና እንደርታዎቹ ከአክሱሞቹ ዓድዋዎቹና ሽሬዎቹ የቃላትም የልሳንም አጠቃቀም የተለየ ያደረገው ዩኒፎርሚቲው አንዳዊነት ያለመጠበቁ ምክንያት አዲሱ ቋንቋ ሌለውን ሩቅ ያለው አካበባ አዲሱ ቋንቋ “ሲጫነው እና ነባሩም ቋንቋ በእምቢተኛነትና በተቀባይነት በመስተጋብርነት ሲገፋፋ” ልዩነት አሳይቷል።
ከላይ እንዳየነው አንድ ሕዝብ ጥንታዊ ቅርሶች በሚገኙበት አካባቢ እየኖረ ስለሆነ ጥንታዊ ነው ማለት አይቻልም። የኦሮሞዎችን ታሪክ መመለክት በቂ ነው። አሮሞዎች እንደ ተቦጫጨቀ ጨርቅ እየዘለሉ አማራውን ትንሽ ነክተው ዘልለው ትግራይ ድረስ ቡጫቂ አካባቢ ኦሮሞ ተናጋሪ ናሪ መኖሩን ስትመለከቱ ልክ የትግሬዎችም እንዲሁ “ትግራይ ውስጥ የሚገኙ” ትግራይ ተብለው የሚጠሩት ኦሮሞዎች በሂደት ትግራይነታቸው ቢረጋገጥም (ቢጠሩም) መሰረታቸው የአካባቢው ጥንታዊ የራያ (ማይጨው) ኗሪዎች ግን አይደሉም። ለዚህ ነው የትግራይ ኗሪ ትግርኛ ተናጋሪው በትግራይ “ክልል” ተንሰራፍቶ በመኖሩ ከማንም ጋር አልተዳቀለም ማለት አይቻልም የምለው ለዚህ ነው።
ትግሬዎች “የትግረ ቤጃዎች” ስርወ ነገድ አስቀጣዮች ናቸው የሚሉ ተመራማሪዎችም ስላሉ ዛሬ “አክሱም” በብቸኛ ባለቤትነት “የምስክር ወረቀቱን” አምይዘው እኔ ብቻ ነኝ የሚለው ስስትነትና ትምክሕት “ላንቃው እስኪደርቅ ድረስ በየሚዲያው ሊለፈልፍ” ቢችልም የሚያዋጣው ግን አይደለም።
እንግዲህ ይህንን ካየን ወደ ክፍል 3 “አስኳል” እኛ ነን “ምን ታረጉት” የሚለው የቴድሮስ ጸጋየ አጉል ትምክሕት “ያለ ዳርቻ መሃል ህይወት የለውም” የሚለው በክፍል 3 በሚቀጥለው አክሱም “የሶሪያዎች፤ የግብጾች የግሪኮች፤የመን ሳባዎች፤ የእስራኤል አይሁዶች፤ የዓረቦች… ወዘተ…ወዘተ አስተዋጽኦ ያለበት “አክሱማዊው አስኳል” የትግሬዎች ብቻ እንዳልሆነ እንመለከታለን።
ሁሉም በልኩ እያየን እየተጠነቀቅን “ተው! እየተስተዋለ እንጂ!” የምልበት ምክንያት ለዚህ ነው።
እስከዛው ሰላም እንሰንብት
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment