ሰውን ከነ ነብሱ መቅበርና በእሳት
ማቃጠል የወያኔ ትግሬዎች ባሕል!
በግደይ ባሕሪሹም
(የአሞራ መጽሃፍ ደራሲ)
((1985 ዓ.ም አማርኛ መጽሐፍ)
አቅራቢ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
3/13/22
ይህ ሰነድ በወዳጄ
ግደይ ባሕሪሹም አሞራው የተባለ አማርኛ መጽሐፍ የተገኘ ሲሆን እዚህ የተሰነደው ጽሑፍ በ1985 ዓ.ም ወዳጄ አቶ ግደይ ባሕሪሹም
አስፈቀጄ የምፍልገውን ክፍል ብቻ በኢንተርኔትና በመጽሐፌ ላይ እንዳስቀምጥ እና በድረገጼም የሚከተለው ክፍል እንዳትመው አስፈቅጄ
ነበር የጻፍኩት። ሆኖም አንዳንድ የፌስቡክ ባለቤቶች ጽሑፉን ከጥቂት አመታት በፊት ቆራርጠው የመጽሐፉንም ሽፋንና ፎተግራፍ ከድረገጼ
ላይ ሲቀዱት አበላሽተው እንደለጠፉት አይቻለሁ። እንዲያም ሆኖ ለደራሲውም ምስጋና ሳይሰጡ የተቆራረጠ ሰነድ ሲለጥፉት አይቻለሁና
እርማት ይደረግለት።
ወዳጄ ግደይ ስለ
ግል ህይቱ ታሪክ የጻፈው ሌላ መጽሐፍ እንዳርምለት ጠይቆኝ እኔ እና የድርሰት ችሎታ ያለው አንድ ወዳጄ አርመን ልኬለት ነበር፤
ፍላጎቱ አገር ውስጥ እንዲታተም ነበርና “ይታተም አይታተም አላወቅኩም( ወያኔ ሥልጣን ላይ እያለ ማለት ነው)።
ዛሬ የማቀርብላችሁ
ይህ ታሪክ በአማርኛ እና አማርኛ ለማያውቁ በትግርኛ ከአማርኛ ቀጥሎ ለጥፌዋለሁ። ትርጉም የራሴ።
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ
የሆነኝ ደግሞ ሰሞኑን እነማን እንደሆኑ በስም ያልታወቁ የትግራይ ተወላጆች በ (መንግሥት ታጣቂ ኦሮሞዎች ወይንም በኦነጎች ወይንም
በጉሙዝ ወታደሮች/የሽምቅ ታጣቂዎች…(?)) እየተባለ በቅጡ ያልታወቀ የሽብር ቡድን እነዚህ የትግራይ ተወላጆች ከነ ነብሳቸው ሲቃጠሉ
በቪዲዮ ሲሰራጭ ያዩ የወያኔ ሊሂቃን (ከጌታቸው ረዳ ጀምሮ እስከ ምሁራን ተብየ አሽከሮቹ ድረስ) ያቃጣላቸው “አማራ/ፋኖ” ነው
እያሉ ሲወነጅሉ ሰምተናል።
ሰዎቹ ሲቃጠሉም የትግራይ
ወያኔ ሴት ደጋፊዎች ሰብስበው፤ ወያኔዎች ለሰው ልጅና ለትግራይ ተወላጆችም ጭምር የሚራሩ ብጹአን እስኪመስሉ ድረስ ሴቶችን ሰብስበው
“ሲያስለቅሱ” ለፕሮፓጋንዳቸው መጠቀሚያ ሲያደርጓቸው በቪዲዮ ተለጥፎ አይቻለሁ።
አድራጊወ አማራ ነው
ብለው መወንጀሉስ እሺ ማስረጃ እስካላቸው ድረስ መወንጀል ይችላሉ፤ የገረመኝ ግን ትግረዎችን በእሳት ሲያቃጥል የነበረ ሰው ከነ
ነብሱ ጉድጓድ ውስጥ አስገብቶ “እስኪተላ” ድረስ ይገድል እንዳልነበረ ምንም የማያውቁ ምስኪን ጀሌ ሴቶችን ሰብስበው ሲመጻደቁ መስማት
የሚገርሙ የወያኔ ምሁራን በቪዲዮ ተሰራጭቶ አይቻለሁ።
እስኪ በአለም አቀፍ
የሽብር መዝገብ ለ47 አመት ስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው የወያኔ ሽብርተኛው ቡድን እወክለዋለሁ በሚላቸው የትግራይ ተወላጆች ላይ በረሃ
ውስጥ እያለ ምን ሲፈጽምባቸው ነበር? በማስረጃ እንመለከታለን።
ከእዚህ በታች የምታነብቡት አሰቃቂ የወያኔዎች የጭካኔ ማሕደር የተገኘው “አሞራ” ከሚለው መጽሐፍ በደራሲ ግደይ ባሕሪሹም (1985 ዓ.ም) የተገኘ ሲሆን ይህን አማርኛ ወደ ታች ቀጥሎ የምታነብቡት ክፍል ወደ “ትግርኛ” ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትየጵየን ሰማይ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 1999 ዓ.ም የተተረጎመ::
በግደይ ባሕሪሹም
(ከ አሞራ መጽሐፉ የተገኘ- ገጽ 197)
“…ሴቶች ለማገዳ እንጨት ለቀማ ከሠፈራቸዉ ወጣ ብለዉ ወደጫካ ሲሄዱ፤ በክረምት ወራት በጎርፍ የተጠራቀመዉን በደረቀው ወንዝ አፋፍ ላይ ዳሰሳ ጭራሮዉንና ጉቶዉን መምዘዝ ሲጀምሩ ፤ ጎርፍ ካጠራቀመዉ ቅርፊትና ግንድ ጋር የተቀላቀለ፤ የሰዉ አጽምና ያልፈረሰ የራስ ቅል፤ደጋግመዉ ያገኛሉ።
በተለይ በትግራይ ክፈለ ሃገር፤በሽሬ አውራጃ፤ በሰየምት አድያቦ ወረዳዎች ውስጥ፤የሰዉ አጽም ያልተበተነበት በረሃ’ና ቋጥኝ የለም። ከሰላሳ ሁለት ጊዜ የወያኔ እና በኢዲህ ጦርነት እልቂት ፤ አካባቢው በወያኔ ቁጥጥር ከዋለ ወዲህ፤ የኢዲህ ደጋፊ ነበርክ፤ነበርሽ ተብለዉ በወያኔ ቁጥጥር ሥር ከዋሉ በ ኋ ላ ፤በተሓህት አፈሙዝ እየተረሸኑ፤ በየፈፋዉና በየጋምስቱ የተደፉት፤ አፈር ተነፍጓቸዉ ፤ ፀረ ትግራይ “ኮራኹር አምሐሩ” ( የአማራ ቡችላ) እየተባሉ ለአሞራ ቀለብ የሆኑትን፤ የወለደና የተወለደ፤ተሸማቅቆ ያየ ቤት ጎረቤት ይቁጠረዉ።
በእርስ በርስ
ጦርነት ካለቀዉ ይለቅ፤ በጥርጠራና በጥቆማ ተይዘዉ፤ ለዘርና ለታሪክ እንዳይተርፍ፤ በስዉር (በሻዕቢያ ባንዳዎች) ያለቀው የትግራይ ሕዝብ እጥፍ ድርብ ነው።
ከክፍለሃገሪትዋ ከመቀሌ ከተማ ጀምሮ፤ በስምንቱ አዉራጃዎችና በአምሳ ሁለት ወረዳዎች ያለዉ ሕዝብ፤ፈጠን ብሎ ለእነሱ “በርከክ” ካላለና “ትግሬና አማራ” ወይም “ኢትዮጵያና ትግራይ” በሚለዉ መሰረታዊ መፈክራቸው ላይ፤ ጥያቄ ያቀረበ ሰው ሁሉ “ኢዲህ” ነው፤ እየተባለ ወላጅ በልጁ እጅ እንዲመታ እና እንዲረሸን ያደረጉት ለሻዕቢያ ያደሩ የሻዕቢያ ባንዳዎች፤ በግማሽ ከኤርትራ ክፍለ ሃገር በመወለዳቸዉ፤ለነገዉ ትውልድ ጥቁር ታሪከና የማይደርቅ ደም አተረፉ እንጂ፤ በተተኪዉ የትግራይ ትውልድማ ለልጆቻቸዉ ቂም አትርፈዉ፤አመላቸውን ይዘዉ በተራቸዉ ማለፋቸዉ አይቀርም።
ደግ ይሁን ክፉ ሰው መቸም እንደ ድንጋይ ለዘላለም አይኖርም። ከናዚ ጀምሮ የነበረ አረመኔ ሁሉ አላለፍም ብሎ ዛላለም የኖረ ሰዉ የለም። ይህች የአረመኔዎችና የካሃዲዎች የትምክህተኞችና የቂመኞች ዘመን በተራዋ ሳትወድ በግዷ ታልፋለች። ትዉልድና ታሪክ ግን ይቀየራሉ።
“ቁጥቋጦና ታሪክ ከመቃብር በላይ ነዉ” ይባል የለ!። ደርግ በቀይ ሽብር የከተማዉን ወጣት ሊጠርግ ፤ የሻዕቢያ ቅጥረኛ የሆነዉ ወየኔም፤ ትግራይ ዉስጥ በገጠሩ፤ ኢትዮጵያዊነቱን ያልካደና እምነታቸዉን ያላመነ ገበሬዉንና ወዛደሩን “ኮራኹር አምሐሩ፤ ሽዋዉያን ተጋሩ” (ያማራ ቡችሎች - የሸዋ ትግሬዎች) እያለች የ “ኢዲህ” ታጋይ ቤተሰብ ዘመድና አዝማድ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ፤በሬና ላሙን፤በግ አና ፍየሉን፤ አህያዉን በቅሎዉን፤ ደሮዉንና ጎተራ እህሉን፤ ማርና ቅቤዉን፤እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ፤ ለሐማሴኖች መደሰቻ ተብሎ፤ላሻዕቢያ ያልሰገደ’ምስኪን የትግራይ አራሽ ገበሬ፤ “ዘር ማንዘሩ” ከምድር እነዲጠፋ እየረሸነች፤ ለሌሎች መቀጣጫ ተብሎም በወጉ በቤተዘመድና በጎረቤት እንዳይቀበር፤ለንቃተ ህሊና ትምህርት ወደ በረሃ ተልኳል እየተባለ፤ ሳይመለስ የቀረዉ የቤትና ጎረቤት ሰዉ ታዝቢ ይቁጠረዉ።
ሻዕቢያ የተባለዉ የኤርትራዉ ድርጅት፤ በግማሽ ትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ዘመዶቹን፤ ወያኔ ትግራይ ድርጅት “ቁንጮ” ላይ አስቀምጦ፤በንጹህ የትግራይ ዘርና ትዉልድ ላይ ግፍ የፈጸመበት “በሃያኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጊዜ” እንደነበር፤ ለተተኪዉ የትግራይ ትዉልድ ታሪክ መጥቀስና ማዉረስ የተቆርቋሪ ወገን ግዴታ ነዉ።
ሻዕቢያ በወያኔ ትግራይ ስም ተሰይመው ፤ አመራሩን በወኪሎቻቸዉ ተቆጣጥረው፤ገበሬውንና አገር ወዳዱን የትግራይን ሕዝብ፤ ወጣቱንና ሕጻናቱን አሰባስበው (ትግራይ ዓደይ በል!!) “ላገሬ ለትግራይ በል!! እያሉ፤ የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት የጦርነት ምሽግና ተገን እንዲሆንላቸው አታልለውና አሞኝተው፤ ባልተወለደ አንጀታቸው በገዛ ጓሮው ኢትዮጵያዊነቱንና አነድነቱን በሚያስከብር የጠራናፊት ሠራዊት (ኢዲህ) እግር እነዳይተክል ትግራይ ወጣት እርስ በርሱ ወንድም በወንድሙ ላይ ሰይፍ እንዲማዘዝ አደረጉ።
ትግርኛ በመናገራቸውና ወላጆቻቸው ትግራይ ውስጥ ተወልደዉ የትግራይን መሬት ፍሬና እህል በልተው በማደጋቸው፤ ትግሬዎች ነን በማለት፤ትግራይን ህዝብ ”ለነጻነትህ ብርሃን ነው” እያሉ፤ በዘር ወገናቸዉ ለሆነው ለሻዕቢያ በተንኮል ተወክለዉ፤የትግራይን ሕዝብ የወገኑ የመሃል አገር ያማራና የኦሮሞ ወዳጅነት ለዘላለም እንዳይኖረው ፤በኤርትራዊያን ተጨቁኖ፤ በአማራውም ተጠልቶና ተራርቆ እንዲኖር፤ በተንኮል ወደ ገሃነም ጨለማ መሩት።
በነሱ አጠራር- “ዓጋሜ የአማራ ሰላይ”; በአማራውም በኩል “ባንዳ አስገንጣይ ተገንጣይ ታሪክ ሻጭ’ እየተባለ እንዲወቀስ፤ ዘላለም እንዲከሰስና በታሪክ እንዲኮነን አደረጉት። በሻዕቢያ መሠረተ ዓላማ የተጠመቁ ሃማሴኖች፤ የትግራይ ሕዝብ በመሀል አገር ህዝብ እንዲሞገስና እነዲመሰገን አይፈልጉም። ይልቁንም በትግሬውና በአማራው መካከል የከረረ ጠብ ተፈጥሮ የትግራይ ሕዝብ ከመሀል አገር የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየተጋጨና እየተነጫነጨ እንዲኖር፤እነሱ ግን” ግፋ በል -ጠቡን አታብርደዉ>> እያሉ የዳር ድንበር ጠያቂ ሳይኖራቸዉ በሰላም ሊኖሩ ሕልማቸው ነው።
ቀን የጣለው የትግራይ ሕዝብ ቂሙን ይረሳል ማለት መሽቶ አይነጋም እንደማለት መሆኑን አላወቁትም። “አንድ ቀን ዳግማዊ አሉላ ይወለዳል” ፤ ቀይ ባሕር ራሱ የኢትዮጵያ ድንበር መሆኑን የሚያረጋግጥ “ከተንቤን አንድ ሰዉ ይወጣል” ታሪክ ይደገማል!-/-/ ግደይ ባሕሪሹም።
ለአቶ ግደይ ባሕሪሹም በአንባቢዎች ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። ጌታቸዉ ረዳ
ለትግርኛ አንባቢዎች
ሰብ ብህይወቱ ቀቢርካ ምቕታልን ብሓዊ ምልብላብን ባህሊ ወየንቲ ትግራይ!
ኣሞራ ገጽ 207- 209
ካብ ግደይ ባሕሪሹም - ትርጉም ትግርኛ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ደጋፋይ < ኢ.ዲ.ዩ “ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት” ኢኻ ፡ ወድኻ ወይ
ሓዉካ እውን “ኢዲዩ” ኢዩ’ ተባሂሉ ይታሓዝ’ሞ፡ ናብ ‘ባዶ ሽድሽተ’ ይውሰድ። ኣብኡ ምስበጽሐ ዘለዎ ንብረትን ብዝሕን ኣበይ
ከምዘሎን ይጥየቕ። ንዝቐረበሉ ጥያቐ መልሲ ሂቡ ምስወደአ፡ ንቑሩብ መዓልቲ ‘እዚ ዘይባሃል ጡዑም ብልዒ”
እንዳተቐለበ ኣብ ካልኣይ ሳልሳይ መዓልቲ ምስ ከምኡ ዝበለ እሱር እንዳታሓጋገዘ እንተዋሓደ ክልተ ሜትሮ ዑምቀት ዘለዎ ጉድጓድ
ንክኹዕት ይእዘዝ።
ብስፍሓቱ ኮነ ብዓይነቱ መቓብር ሰብ እዩ ዝመስል። ከም ጉድጓድ ጽብብ ኢሉ
እንዳተኹዓተ ፤ እቲ ዝተፍሓረ ሓመድ ኣብቲ ኣፍ ጉድጋድ ከባቢ ወሰን ወሰኑ ዙርያ ምላሽ ይኹመር፡ አቲ ኡሱር ብደዉ ዝቕበረሉ
ናይ ደዋደዉ መቓብሩ ፍሒሩ እንተብቅዕ፡ ካበቲ ጉድጓድ ይወጽእ።
ብድሕሪኡ ብገመድ ኢዱን እግሩን ተኣሲሩ ናብታ ዝፋሓራ ጉድጓድ “ኣለም በቃኝ”
ይመልሱዎ።
ወየንቲ ኡሱር ቅደሚ ሞቱ እንዳተሳቐየ ምርኣይ ብጣዕሚ እዩ ዘርውዮም፡- ባህ
ይብሎም - ይፍስሁ። ቀልጢፉ ንከይመውት‘ዉን ቀስ ብቐስ እንዳማናጎዩ “ቁርማም ቅጫን - “ጽንቃቕ ማይን” መመሊሶም
ብመገለል ዝመስል መትሓዚ ብገመድ ሰዲዶም ናብታ ዝኣተወላ ጉድጓድ የቐብሉዎ። ”ሽንቲ ማይ ኮነ - ቀልቀል ዝናፈሰላ -ኣብታ
ዉሽጢ ጉድጓድ እዩ።” ሓንሳብ ናብታ ዝዃዓታ ጉድጓድ ምስተደርበየ ፡ምስኣተወ ፤ ብዝደኾነ ይኹን ታኣምር ተመሊስካ ምውጻእ
የላን።
እቲ ኡሱር ኣብታ ጸባብ ጉድጓድ ውሽጢ እግሩ ምዝርጋሕ ወይ ብጎኒ
ምድቃስ ኣይኽእልን። ክገብሮ ዝኽእል “ተኾርሚኻ ኮፍ” ምባል ጥራሕ እያ።
“ኩርምይ” ኢሉ፤ ቀትሪ “ብጻሓይ ሃሩርን” ለይቲ “ብቀዝሒ
ኣሳሒይታ” ፤ ብዱውሉ እንዳተሳቐየ ፤- ዝተወለደላ መዓልቲን ሃገርን ዝተወለደሉ ዘርኢን እንዳረገመ ምስኣስተንተነ፤-
ኣብ’ቲ ዘሰክሕ ከይዲ ሞት ቅድሚ ሙማቱ ግና እቶም “ካብ ኣብቲ ጉድጓድ መሬትን” “ኣብቲ ኣካላቱን ዝፍጠሩ ሓሳኹ’
መርዛማት ስለዘይኮኑ ዓይጓድኡን። ቀለጢፎም ኣይቀትሉዎን።
ቆርበቱ ሰርሲሮም፤ ሥጋኡ በሊዖም ዓዕጽምቱ ጎጥጚጦም ምፍርካሽ
እንትጅምሩዎ፡ አቲ ኡሱር ኣብ መወዳእታ ብኣፉን ብኣፍንጭኡን ከምኡዉን ብዓይኑን “ሓሰኻ ድዱቛታት ፎሎቕሎቕ” ይብሉ’ሞ መሰክሕ
ብዝኾነ መርገም ህይወቱ ምስሓለፈት፤- ካበዚ መርገም’ቲ ትርኢት ጭጉርጉር ዘይብሎም ወየንቲ አብቲ ኣፍ ጉድጋድ ዝተኾመረ ሓመድ
“ድፍን ድፍን” ኣቢሎም ኢዱን እግሩን ታአሲሩ ብኹርምዩ አብኣ ይቕበርዎ።
እሞ’ሲ ካብ ኮም’ዚ ዝመሰለ መስገልገላይ ሞት፤ አብ ማዕከል ሜዳ
አብ ማዕኸል ጸምጸም በረኻ ፤እንተይታአሰረ ማይን እኽልን ብምስኣን፤ ህይወቱ እንዳሃለወት “ዓቕሚ ስኢኑ” ዓይኑ እንዳራኣየ
“ኣሞራ” ዓይኑ እንትምንጥሎ፤ ዓርሱ ምክልኻል ምስ’ስኣነ፤ ህይወቱ እነዳተጋዓረት ፡ ስጋኡ ብኣሞራ እነዳተተኹቶኸ ተባዛጊሉ
ተማናጢሉ ህይወቱ ዝሓለፈ ፤ ምስ ሻዕቢያ ግፍዒ ካብዝፈጸመሉ ሙሩኽ ሰራዊት ደርጊን ፡ - አየናይ ኮን ይሓይሽ? ኢልና
እንተጠየቕና ንዘስካሕክሕ ዝተፋላለየ ስቅያት ሞት ምምርማር ካብ “ናዚ ጀርመናዊያን “ውጥጥ” ኢሎም፤ብጭካነ “ልዕል” ኢሎም”
ዝተረኽቡ “ወየንቲን ሻዕቢያን” ፤- ምስ እቶም ሰብ ንሰብ ካብ ሕማሙ ንክፍወስ ምርምር ዘካይዱ “ጥበብ አብዝተስፋሕፋሓሉ
ዘበን” እንትንዕዘብ ፤- ናይ ሻዕቢያን ወያነን ናይ ጭካነ-ተፋላሰፍቲን ተማራመርቲን፤ “ደቂ ኣኮን ደቂ ሓትኖን” ግን ኣብ
ታሪኽ ንወለዶ “ዘሕፍር ዘኹንን” ግብሮም አብ ልዕሊ ወገን ዝፈጸሙዎ እንትናጻጸር፤ “አሸጋርን መስካሕክሒ ጨካን ኣቃታትላኦም”
ክልቲኦም ወያነን ሻዓብያን ኣይባላለጹን ፤ኣይሳኾኑን፤-ኢልካ ጥራሕ አዩ ምሕላፍ ዝካኣል።
ብሂይወቶም እንዳሃለዉ ኣብ ዉሸጢ ጉድጓድ አትዮም እንዳተሳቐዩ ንክሞቱ
ዝፍረዶም ተጋሩ ፤ ብመትከሎም ዘይኣምንን ኣብ ጥርጣረ ዝኣቱን እዩ። ብከመዚ ዝበል ኣቃታትላ ተፈሪዱዎም ዝሞቱ እኒ “ሃበተ
ገብረተንሳይ፤ ተኽላይ ገብረመስቀል ፤ ወይዘሮ ወርቂ ምንጭራን ፤ አቶ
አታክልቲ ሥዩም (አብ ከተማ ሸራሮ ራፖል ጸሓፊ ዝነበረ ወዲ ልዑል ራዕሲ ሥዩም)” ዝመሳሰሉ ተጋሩ ይርከቡዎም።
ኣብ እግረ-መንገድና ምናልባሽ “አታኽልቲ ሥዩም” መን ሙኻኑ ዘይትፈለጡ
እንተዳሃሊኹም፤ ልዑል ራእሲ መንገሻ ሓወይ አይኮንካን፤ ኣቦይ’ዉን ኣይተዛረቡንን፤ ኢሎም ሕዉነቶም ዝካሓዱዎ ፡ ኣብ ኣዉራጃ
ሽረ ኣብ “ሰየምት” ኣብ ዉሽጢ “ኣድያቦ” ዝነብር ዝነበረ እዩ።
ትዉልዲ ዕብየት ወላዲቱ አብ መደባይ ታብርን ኣብ ሠመማን እየን።
ኣዲኡ ካብቶም ብናይ ቀደም ኣጻዋዋዓ “ጸለምቲ” (ባሮት) ታበሂሎም ተናዒቖም ዝጽረፉ ዝነበሩ ስደራቤታት ወረጃ ወይዘሮ እየን።
ንሰን እዉን ብክብሪ በቲ ዝነበረ “ባህላዊ መስፈናዊ ሥርዓት” መሰረት “ታሓዛይ ጽላል” ገይረን ፤ አሕሽኪረን ፤ ብስናር በቕሊ
ዝኸዳ፤ ክሳብ ጊዜ እርጋነን ብክብረት ተኸቢረን ዝነብራ ነበራ ዓባይ ወላዲት እየን።>>
ግደይ ባሕሪሹም (አሞራዉ ካብ ዝብል መጽሓፎም)
ትርጉም ትግርኛ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment